ዎል ዲዮራንት

quotes:
  • የሴት ደረጃ
  • ‹‹እስላም በዐረቦች አገር የሴትን ደረጃ ከፍ አድርጓል። ሴት ሕጻናትን ከነሕይወታቸው የመቅበርን ልማድ አስወግዷል። በፍርድ ሂደቶችና በንብረት ባለቤትነት መብት ወንድና ሴትን እኩል አድርጓል። ለሴቷ ሐላል በሆነ ሥራ ላይ የመሰማራት፣የመውረስና ሠርታ ያገኘችውን ሀብት በባለቤትነት እንዳሻት የማድረግ መብት ሰጥቷል። በዘመነ ጃህሊያ የዐረቦች ልማድ የነበረውን ሴቶችን ከሌላው ንብረት ጋር ከአባት ወደ ልጅ ማስተላፍን ያስቀረ ሲሆን፣የሴትን የውርስ ድርሻ የወንዱ ድርሻ ግማሽ አድርጎ ያለ ፍቃዳቸው እንዳይዳሩም ከልክሏል።››


  • ቅድሚያ ለሃይማኖት
  • ‹‹የሙስሊሞች ስነምግባራዊ መርሆዎች፣ሕጋቸው፣መንግስታቸው፣ሁሉም በሃይማኖት መሰረት ላይ የቆሙ ነበሩ። እስላም ከሃይማኖቶች ሁሉ እጅግ ቀላሉና ግልጹ ሃይማኖት ነው። መሰረቱም ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው።››


  • የቁርኣን ደረጃና ትሩፋቱ
  • ‹‹ቁርኣን ምናባቸውን ሲቀሰቅስ፣ስነምግባራቸውን ሲቀርጽ፣በመቶ ሚሊዮኖች የመቆጠሩ ሰዎችን አእምሮና እሳቤ ሲሞርድ ለአስራ አራት ምእተ ዓመታት በሙስሊሞች ትውስታ ውስጥ ተጠብቆ ኖሯል። ቁርኣን ከሁሉም ይበልጥ ገርና ቀለል ያለ፣ከሁሉም ይበልጥ ከውስብስብነት፣ከድፍንፍን ምስጢራት፣ከካህናዊ ጣዖታዊ ስርዓታት የጸዳ ዐቂዳን በሰው ልቦና ውስጥ በሰው ልቦና ውስጥ ይተክላል። የሙስሊሞችን የስነምግባርና የስልጣኔ ደረጃን ከፍ በማድረግ ረገድም ትልቁን ሚና ተጫውቷል። የማሕበራዊ አነዋነዋርና የማሕበረሰባዊ አንድነት ስርዓት መሰረቶችን የተከለላቸውም እርሱ ነው። የጤና አጠባበቅ ሕጎችን እንዲከብሩ አበረታቷል። አእምሮአቸውንም ከብዙ አፈተረቶችና ግምታዊ ቅዠቶች፣ከግፍና ከጭካኔ ነጻ አውጥቷል። የጫንቃ ተገዥዎችን ሁኔታዎችም አሻሽሏል። ግፉአን ተዋራጆች በነበሩት ልብ ውስጥም የክብርና የልዕልና መንፈስ ዘርቷል።››


  • የተሟላ ክቡር ሰብእና ያላቸው ሰዎች
  • ‹‹ሙስሊሞች - በጥቆማ እንደሚባለሁ ሁሉ - ከክርስቲያኖች ይበልጥ የተሟላ ክቡር ሰብእና ነበራቸው። ከነርሱ ይበልጥ ቃል ኪዳን ጠባቂዎች፣ከነርሱም ይበልጥ ለተሸናፊዎች ርህሩሆች ነበሩ፤ክርስቲያኖች በ1099 ዓመተ ልደት ኢየሩሳሌምን ሲይዙ የፈጸሙትን ዓይነት አረመኔያዊ ተግባር ሙስሊሞች በታሪካቸው ውስጥ ፈጽመውት አያውቁም ማለት ይቻላል።››
Tags: