የደስተኝነትና የእርካታ ሃይማኖት

 የደስተኝነትና የእርካታ ሃይማኖት

‹‹እንዲህ ስል ራሴን እጠይቅ ነበር፦ ሙስሊሞች ድሆችና ኋላ ቀሮች ሆነው ሳለ ሕይወታቸውን ሞልቶ የሚያጥለቀልቅ ደስተኝነት የሚሰማቸው ለምንድን ነው?! ስዊድናውያን የተንደላቀቀ የብልጽግና ሕይወት እየመሩ በጭንቀትና በውጥረት የሚሰቃዩት ለምንድነው?! አገሬ ስዊዘርላንድ ጭምር የበለጸገችና የተንደላቀቀ የኑሮ ደረጃ ላይ የምትገኝ እየሆነች እዚህም ስዊድን ውስጥ የተሰማኝ ስሜት ነው የሚሰማኝ!! ከዚህ ሁሉ በመነሳትም የምሥራቅ ሃይማኖቶችን ማጥናት እንደሚያስፈልገኝ ተረዳሁና በሕንዱ ሃይማኖት ጥናቴን ጀመርኩ። ብዙ አላሳመነኝም። የእስላምን ሃይማኖት ማጥናት ጀመርኩ። ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ቅራኔ የሌለው ብቻ ሳይሆን የሃይማኖቶች መደምደሚያ ሆኖ ለሁሉም ቦታ የሚሰጥ መሆኑ ሳበኝ። ይህ ከንባቤ ስፋት ጋር መስፋት ጀምሮ ሙለ በሙሉ አእምሮዬ ውስጥ እስከ መስረጽ የደረሰው እውነታ ነው።››


Tags: