ሴት በሰው ሰራሽ ሕጎች ውስጥ

ሴት በሰው ሰራሽ ሕጎች ውስጥ

‹‹ሮማ ውስጥ ትልቅ ጉባኤ ተደርጎ በሴቶች ጉዳይ ላይ ተነጋገረ። ሴት ነፍስ የሌላት ፍጡር ናት፣በዚህ ጉድለት ምክንያትም መንግሥተ ሰማያትን አትወርስም፣እርኩስ ስለሆነች ሥጋ መብላትም ሆነ መሳቅና መናገርም የለባትም፤ሙሉ ጌዜዋንም በጸሎት፣በአምልኮና በአገልግሎት ማሳለፍ ይኖርባታል ብሎ ወሰነ። ከዚህ ሁሉ ሊከለክሏት በማሰብም በአፉዋ ላይ የብረት ቁልፍ ዘለበት አደረጉ። የከፍተኛውና የዝቅተኛውም ቤተሰብ ሴት መንገድ ላይ ትጓዝ የነበረውና ወጥታ የምትገባው አፉዋ እንደተቆለፈ ሆኖ ነበር። ይህም ሴት ልጅ የወንዶች ልብ ለማበላሸት ሰይጣን የሚገለገልባት የማሳሳቻ መሣሪያ ተደርጋ ከመወሰዷ አንጻር ይፈጸምባት ከነበረው አካላዊ ቅጣቶች በተጨማሪ ነው።››


Tags: