አጠቃላይ ጥቅሶች

quotes:
  • በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ እርስዎ የት ነዎት?!
  • ይህ በጣም ግዙፍ ከሆኑ የጋላክሲዎች ስብስብ ያንዱ ፎቶግራፍ ነው። ከነዚህ አንዱ ወይም በአንዲት ትንሽ ነጥብ ብቻ የሚወከለው የኛ ፀሐያዊ ሥርዓት (Solar System) ያለበት የፍኖተ ሐሊብ (Milky Way) ጋላክሲ ነው። በኛ ጋላከሲ ውስጥ ከ100000000000 የሚበልጡ ፀሐዮች የሚገኙ ሲሆን፣የኛዋ ፀሐይ ከመሬት 1300000 ጊዜ ትበልጣለች። የርስዎ ቤት 500 ካሬ ሜትር ነው ብንል መሬት ደግሞ 1020144000000 ጊዜ ከቤትዎ ትበልጣለች። የርስዎ ቤት ከርስዎ በምን ያህል እጥፍ ይበልጥ ይሆን?!


  • ግፍና በደል
  • ‹‹በአውሮፓ የፈላስፎች ጉባኤ ይጠራና ሴት እንደ ወንዱ ሁሉ ነፍስ አላት ወይስ የላትም? ያላት ነፍስ የሰው ልጅ ነፍስ ነው ወይስ የእንስሳት ነፍስ ነው? የሚሉ ነጥቦች ለክርክር ይቀርቡ ነበር። ክርክሩም ‹ሴት ነፍስ ወይም መንፈስ አላት ግን ከወንዱ ነፍስ በብዙ ደረጃዎች ያነሰ ነው› በሚል የጋራ አቋም ይቋጭም ነበር።››


  • ነቢዩ ዒሳ  ወንጌል ውስጥ ፈጣሪ አምላክ አንድ መሆኑን ያረጋግጣሉ
  • ‹‹ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደመለሰላቸው አስተውሎ፦ ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፣ስማ፤ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፣አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።›› ማርቆስ 12፣28-35


  • ወንጌል ስቅለትን ያስተባብላል ዕርገትን ያረጋግጣል
  • • ‹‹ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።›› ዮሐ 8፣59 • ‹‹እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ከእጃቸውም ወጣ።›› ዮሐ 10፣39 • ‹‹ይህ የሆነ፦ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።›› ዮሐ 19፣36 • ‹‹ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ . . ›› የሐዋ ሥራ 1፣11


  • የጥጃው ቀራጺ ሳምራዊው ነው
  • ‹‹የአላህ ነቢይ ሃሩን የጥጃው ቀራጺና የጣዖት አምልኮ አስተማሪ ፈጽሞ ሊሆኑ አይችሉም፤ሁሉም ነቢያት ለአላህ (ሱ.ወ.) አንድነት ለተውሒድ ጥሪ የሚያደርጉ ናቸውና። ከዚህ ውጭ ያለው ዘገባ የተዛነፈና የተበረዘ ነው። ከመሰል የተዛነፉ ዘገባዎች መካከል የሚከተለውን እናገኛለን፦ ‹‹አሮንም፦ በሚስቶቻችሁ በወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት። ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅጫ ቀረጸው፣ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፣እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።›› ዘጸአት 32፣2-4


  • ፍልስጥኤም ውስጥ በአልኸሊል (ሄብሮን) ከተማ በኢብራሂም መስጊድ የሚገኘው የነብዩ ኢብራሂም  መቃብር።
  • ፍልስጥኤም ውስጥ በአልኸሊል (ሄብሮን) ከተማ በኢብራሂም መስጊድ የሚገኘው የነብዩ ኢብራሂም  መቃብር።


  • ትእቢትና ታሪክን ማጣመም
  • ‹‹በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት ክርስቲያን ጸሐፍት በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሱትን የሰው ዝርዮች ምደባን አምነው መቀበል ጀመሩ። አዳዲስ መደቦችንም ጨመሩበት። ሰፍኖ የቆየው እምነትም ካህናትና ቀሳውስት ከሴም ዝርያ፣ፈረሰኞችና ተዋጊዎች ከያፌት ዝርያ፣ድሆች ከካም ዝርያ የወጡ መሆናቸው ነበር። ይህ ምደባ ስር ሰዶ በ1964 ከምዕራብ ቨርጄኒያ የአሜሪካ ሴናተር የሆኑት ሮበርት በይርድ ይህን የኖሕ ልጆች ትረካ የዩ.ኤስ. አሜሪካን የዘር መድልዖ ጭቆና ለማቆየት እንደምክንያት እንዲገለገሉበት አድርጓቸዋል።››


  • የነቢያትን ክብር ማዋረድ
  • የነቢያትን ክብር ማዋረድ - ‹‹ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፣ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም አባቱን ዕራቁትነት አየ፣ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፣ኋሊትም ሄደው አባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፣የአባታቸውንም እራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፣ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን፤ለወንድሞቹም ባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባርክ፣ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።››


  • የቡድሂዝም መጣረስ
  • ‹‹ቡድሂስቶች ወይም ከፊሎቻቸው የአምላክን መኖር ሲያስተባብሉ፣ቡድሃን የአምላክ ልጅ ነው ይላሉ። መንፈስ መኖሩንም ሲያስተባብሉ የሙታን ነፍስ በሌላ ፍጡር አካል ትመለሳለች ብለው ያምናሉ። ››


  • ግፈኛው የመደብ ክፍፍል
  • ‹‹የሕንዱ መደባዊ ክፍፍል እንዲከተለው የተደለደለ ነው፦ የነጮች መደብ፣ይህ የሃይማኖት መሪዎችንና አዋቂዎችን የያዘ ነው። የቀያዮች መደብ፣ይህ ደግሞ መሳፍንቱንና ፈረሰኞችን ያቀፈ ነው።የብጫዎች መደብ፣ይህ ገበሬዎችንንና ነጋዴዎችን ያቀፈ ነው። የጠቋቁሮች መደብ፣ ይህ ደግሞ የሞያና የእደጥበብ ሠራተኞችን ያጠቃለለ ነው። አምስተናው መደብ ወይም የእርኩሳን መደብ በመባል የሚታወቀው ደግሞ በተቀሩት የተናቁ ሥራዎች ላይ የተሰማሩትን ሁሉ ያካትታል። የላይኞቹ መደቦች በታችኞቹ መደቦች ላይ የጌትነት ሥልጣን ሲኖራቸው፣የታችኞቹ መደቦች ደግሞ ለላይኞቹ መደቦች አገልጋይ የመሆን ግዴታ አለባቸው።››


  • አላህ ግን አንድ ነው . .
  • ‹‹በምድራዊ ሃይማኖቶች ውስጥ ያሉትን አማልክት ብዛት መቁጠር ለተመራማሪዎች አድካሚ ሆኗል። የጥንት ግብጻውያን አማልክት ቁጥር ከ800 በላይ ነው። የሂንዱዎች አማልክት ብዛት ከ10000 በላይ ነው። በግሪኮች በቡድሂስቶችና በተቀሩት የምድራዊ ሃይማኖቶች ተከታዮች ዘንድም ይህንኑ ዓይነት ጣዖታዊነት እናስተውላለን።››


  • ፈረንሳይቷ ሴት
  • ‹‹በ586 ዓመተ ልደት በፈረንሳይ አንድ ክፍለ አገር ውስጥ ሴት ሰው ተደርጋ ትቆጠራለች ወይስ ሰው አይደለችም? በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ጉባኤ ተደርጓል። በጉባኤው መጨረሻ ተሰብሳቢዎች የደረሱበት ውሳኔ፣ሴት ሰው ነች፣የተፈጠረችው ግን ወንድን ለማገልገል ነው የሚል ነበር። የፈረንሳይ ሴቶችን በንብረታቸው ላይ የማዘዝ መብት የሚገድቡ ሕጎች ተሸረው ለመጀመሪያ ጊዜ ፈረንሳይቱ ሴት መብቷ የተከበረላትና በስሟ ተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ እንድትከፍት የተፈቀደላት የካቲት 1938 ዓመተ ልደት በወጣ ሕግ ነበር።››


  • ሴት እነርሱ ዘንድ . .
  • ‹‹በጥንታዊ የሕንድ ሕግጋት ውስጥ ፦ ተላላፊ በሽታ፣ሞት፣ገሀነም፣መርዝ፣እባቦችና እሳት ከሴት የተሻሉ ናቸው። በሕይወት የመኖር መብቷ ባለ ንብረት ጌታዋ ከሆነው ባሏ መሞት ጋር ያከትማል፤አስከሬኑ መቃጠሉን ካየች ራሷን ወደ እሳቱ ትወረውራለች፤ባታደርግ ዘላለማዊ እርግማን ይወርድባታል።››


  • ሴት በሰው ሰራሽ ሕጎች ውስጥ
  • ‹‹ሮማ ውስጥ ትልቅ ጉባኤ ተደርጎ በሴቶች ጉዳይ ላይ ተነጋገረ። ሴት ነፍስ የሌላት ፍጡር ናት፣በዚህ ጉድለት ምክንያትም መንግሥተ ሰማያትን አትወርስም፣እርኩስ ስለሆነች ሥጋ መብላትም ሆነ መሳቅና መናገርም የለባትም፤ሙሉ ጌዜዋንም በጸሎት፣በአምልኮና በአገልግሎት ማሳለፍ ይኖርባታል ብሎ ወሰነ። ከዚህ ሁሉ ሊከለክሏት በማሰብም በአፉዋ ላይ የብረት ቁልፍ ዘለበት አደረጉ። የከፍተኛውና የዝቅተኛውም ቤተሰብ ሴት መንገድ ላይ ትጓዝ የነበረውና ወጥታ የምትገባው አፉዋ እንደተቆለፈ ሆኖ ነበር። ይህም ሴት ልጅ የወንዶች ልብ ለማበላሸት ሰይጣን የሚገለገልባት የማሳሳቻ መሣሪያ ተደርጋ ከመወሰዷ አንጻር ይፈጸምባት ከነበረው አካላዊ ቅጣቶች በተጨማሪ ነው።››


  • እኩል መብት
  • ‹‹የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 26 ቀን 1964 ዓመተ ልደት ካስተላለፈው ውሳኔ በፊት የሴትና የወንድ ተማሪዎችን መብት (በክበባትና በተማሪዎች ማህበራት ውስጥ) እኩል አድርጎ አያውቅም።››


  • ከውቅያኖስ አንዲት ጠብታ
  • እስከ ዛሬ ድረስ የታወቀው ትልቁ ኮከብ VYCanis Majoris የተባለ ሲሆን ከኛ የሚርቀው በአምስት ሺ የብርሃን ዓመት ነው። መጠነቁሱ ከኛ ፀሐይ 9261000000 ጊዜ ይበልጣል። ይህም ዘጠኝ ቢሊዮን 261 ሚሊዮን ጌዜ ከፀሐይ ይገዝፋል ማለት ሲሆን ፀሐይ ደግሞ መሬትን 1300000 ጊዜ ትበልጣለች!!


  • ነቢዮች ከሰው ልጆች ምርጦችና ፈርጦች ናቸው
  • ‹‹የአላህን ነቢያትና መልክተኞቹን በተመለከተ ከተላለፉት የተዛቡና ተአማኒነት ከጎደላቸው ዘገባዎች መካከል መስከራቸውን፣ወይም ዝሙት ላይ መውደቃቸውን፣ወይም ሰዎች እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠታቸውን . . የሚያወሩ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ በአላህ ለተመረጡ ምርጦችና የሰው ልጆች ፈርጦች ከሆኑ የአላህ ነቢያት ቀርቶ በመልካም ስነምግባር ለታነጸ ተራ ሰው እንኳ የማይገባ መሰረት የለሽ ተረት ነው። ከመሰል ተረቶች መካከል ነቢዩ ዳውድን  አስመልክቶ (ሳሙኤል ካልዕ 11፣2-26)፤ስለ ኢያሱ ወልደ ነወዌ  የቀረበው (ኢያሱ 6፣24)፤ነቢዩ ሙሳን  አስመልክቶ የሰፈረው (ዘኁልቁ 31፣14-18) እና ሌሎቹም መሰል ጥቅሶች ለአላህ ክቡራን ነቢያት ፈጽሞ የማይገቡ ናቸው።››