ሞሪስ ቡካይ

quotes:
  • ቁርኣንና ዘመናዊ ሳይንስ ትከሻ ለትከሻ
  • ‹‹በቅዱስ ቁርኣን ላይ ጥናት አድርጌያለሁ፤ያጠናሁትም ያለ ምንም ቅድመ ውሳኔ፣የቁርኣን አንቀጾች ከዘመናዊው ሳይንስ ግኝቶች ጋር ምን ያህል እንደሚጣጣሙ ለመመርመር ስል አዎንታዊ በሆነ ነጻ አእምሮ ነው። በጥናቴም በዛሬው ዘመን ካለው ሳይንሳዊ አመለካከት አንጻር ትችት ሊቀርብበት የሚችል አንድም አባባል ያላካተተ መሆኑን ደርሼበታለሁ።››


  • ቁርኣንና ሳይንሳዊ ታምራቱ
  • ‹‹ቅዱስ ቁርኣን ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ግልጽ አንቀጾችን አካትቷል። ፕሮፌሰር ዩሱፍ መርዋ ‹የተፈጥሮ ሳይንሶች በቅዱስ ቁርኣን› በተሰኘ መጽሐፍ ውስጥ አንቀጾቹን ያቀረቡ ሲሆን ቁጥራቸውም በትክክል 774 ነው። ዝርዝራቸውም የሚከተለው ነው፡- ማቴማቲክስ 61፣ፊዚክስ 264፣አቶሚክስ 5፣ኬሚስትሪ 29፣ሬላቲቪቲ 62፣ስነፈለክ 100፣ከባቢያዊ አየር 20፣ውሃ ነክ 14፣የጠፈር ሳይንስ 11፣ዙኦሎጂ12፣የአዝዕርት ሳይንስ 21፣ስነሕይወት 36፣ጠቅላላ ጆዖግራፊ 73፣አንትሮፖሎጂ 10፣የከርሰ ምድር ሳይንስ 20፣የዩኒቨርስና ኹነቶች ሳይንስ 36።››




Tags: