የጥጃው ቀራጺ ሳምራዊው ነው

የጥጃው ቀራጺ ሳምራዊው ነው

‹‹የአላህ ነቢይ ሃሩን የጥጃው ቀራጺና የጣዖት አምልኮ አስተማሪ ፈጽሞ ሊሆኑ አይችሉም፤ሁሉም ነቢያት ለአላህ (ሱ.ወ.) አንድነት ለተውሒድ ጥሪ የሚያደርጉ ናቸውና። ከዚህ ውጭ ያለው ዘገባ የተዛነፈና የተበረዘ ነው። ከመሰል የተዛነፉ ዘገባዎች መካከል የሚከተለውን እናገኛለን፦ ‹‹አሮንም፦ በሚስቶቻችሁ በወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት። ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅጫ ቀረጸው፣ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፣እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።›› ዘጸአት 32፣2-4


Tags: