የዕውቀት ስልጣኔ

የዕውቀት ስልጣኔ

‹‹የዐረብ ስልጣኔን፣ሳይንሳዊ መጽሐፎቻቸውን፣ሳይንሳዊ ግኝቶቻቸውንና ስነ ጥበባቸውን በጥልቀት በአጠናን ቁጥር፣አዳዲስ እውነታዎችና ሰፋፊ አድማሳት ይገለጡልናል። ዐረቦች በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት ለቀደምቶቹ ዕውቀቶች መታወቅ ባለውለታዎች መሆናቸውን፣የምዕራባውያን ዩኒቨርሲቲዎችም ከነርሱ ድርሰቶችና ሥራዎች ውጭ ለአምስት ምእተ ዓመታት ሌላ ምንም ምንጭ ኖሯቸው እንደማያውቅ፣አውሮፓን በቁሳዊ አእምሯዊና ስነምግባራዊ ጎኖች ያሰለጠኗት እነሱ መሆናቸውን፣በአጭር ጊዜ ውስጥ እነሱ ያመረቱትን ያህል የዕውቀትና የስልጣኔ ምርት ያመረተ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አንድም ሕዝብ አለመኖሩንና በጥበባዊና ቴክኒካዊ ፈጠራ አንድም ሕዝብ ያልበለጣቸው መሆኑንም እንገነዘባለን።››


Tags: