ጎስታፍ ሎቦን

quotes:
  • በዐረባዊውና ዐረባዊ ባልሆነው መካከል ልዩነት የለም
  • ‹‹ሙስሊሞች የሚዛመዱባቸው አገሮችና ሕዝቦች የፈለገውን ያህል የተለያዩ ቢሆኑም እርስበርስ የሚተያዩት እንደ ባእዳን አይደለም። በአገረ እስላም በሁሉም መብቶች እኩል በመገልገል ረገድ በቻይናዊው ሙስሊምና በዐረባዊው ሙስሊም መካከል አንዳች ልዩነት የለም።እሰላማዊ መብቶችም ከአውሮፓዊ መብቶች በዚህ መሠረታዊ ነጥብ ይለያሉ።››


  • ገሩ እስላም
  • ‹‹የታላቁ እስላም ገርነት ከፍጹማዊው ተውሒድ የመጣ ነው፤በዚህ ገርነት ውስጥም የእስላም የጥንካሬ ምስጢር ይገኛል። እስላምን መረዳት በጣም ቀላል ሲሆን ሃይማኖቱ በሌሎች ሃይማኖቶች ውስጥ ከምናያቸውና ሚዘናዊ አእምሮ ከማይቀበላቸው እርስበርስ ከሚጣረሱ ነገሮችና ከውስብስብ ድብቅ ምስጢራትም የጠራ ነው። አንድ ብቸኛ አምላክ መኖሩን ከሚናገረውና ሰዎች ሁሉ አላህ ፊት እኩል ናቸው ከሚለው የእስላም መሰረታዊ መርህ ይበልጥ ግልጽ የሆነ ነገር የለም።››


  • የዕውቀት ስልጣኔ
  • ‹‹የዐረብ ስልጣኔን፣ሳይንሳዊ መጽሐፎቻቸውን፣ሳይንሳዊ ግኝቶቻቸውንና ስነ ጥበባቸውን በጥልቀት በአጠናን ቁጥር፣አዳዲስ እውነታዎችና ሰፋፊ አድማሳት ይገለጡልናል። ዐረቦች በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት ለቀደምቶቹ ዕውቀቶች መታወቅ ባለውለታዎች መሆናቸውን፣የምዕራባውያን ዩኒቨርሲቲዎችም ከነርሱ ድርሰቶችና ሥራዎች ውጭ ለአምስት ምእተ ዓመታት ሌላ ምንም ምንጭ ኖሯቸው እንደማያውቅ፣አውሮፓን በቁሳዊ አእምሯዊና ስነምግባራዊ ጎኖች ያሰለጠኗት እነሱ መሆናቸውን፣በአጭር ጊዜ ውስጥ እነሱ ያመረቱትን ያህል የዕውቀትና የስልጣኔ ምርት ያመረተ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አንድም ሕዝብ አለመኖሩንና በጥበባዊና ቴክኒካዊ ፈጠራ አንድም ሕዝብ ያልበለጣቸው መሆኑንም እንገነዘባለን።››


  • መካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት
  • ‹‹ሙሳ ብን ኑሰይር አውሮፓን ማቋረጥ ተሳክቶለት ቢሆን ኖሮ አውሮፓን ሙስሊም ባደረጋት ነበር፤ለሰለጠኑ ሕዝቦችም ሃይማኖታዊ አንድነትን ማስገኘት በቻለ ነበር። በዐረቦች ምክንያት እስፔን ሳይደርስባት ካመለጠችው የመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት ሁኔታ አውሮፓንም መታደግ በቻለ ነበር።››


  • ነፍስን መግራት
  • ‹‹ሳይንሳዊ ግኝቶችን እውን ለማድረግ እስላም ከሃይማኖቶች ሁሉ ይበልጥ የተመቻቸ ሃይማኖት ነው። ነፍስን ለመግራትና ስነምግባርን በማነጽ ፍትሕና ደግነትን ለማስፈን በማስቻልም ከሁሉም ታላቁ ሃይማኖት ነው።››


  • የስነምግባር መሰረቶች
  • ‹‹የስነምግባር መሰረቶች ቁርኣን ውስጥ ከፍ ያሉ ናቸው፤በርሱ ያመኑ ሕዝቦች ለዒሳ ሃይማኖት ያደሩ ሕዝቦች እንደተለወጡ ሁሉ በዘመን ለውጥ ተለውጠዋል። ከዚህ ጨምቆ ማውጣት የሚቻለው ዋነኛው ውጤት ለሕግጋቱ ባደሩ ሕዝቦች ላይ ቁርኣን ያሳደረው ታላቁ ቁርኣን ያሳደረው ተጽእኖ ነው። እስላም በሰዎች ልቦና ላይ ያለውን ሥልጣን ዓይነት ያላቸው ሃይማኖቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ለእስላም ያጋጣመውን ቋሚ ተጽእኖ የማሳደር ብቃት ያጋጠመው ሌላ ሃይማኖት ላይኖር ይችላል። ቁርኣን በምስራቁ ዓለም የሕይወት ዋልታ ነው፤ዱካው በጥቃቅኑ ዝርዝር የአነዋነዋር ጉዳዮች ውስጥ የሚስተዋል ነው።››




Tags: