ከቄሱ ጋር

ከቄሱ ጋር

ከቄሱ ጋር (1)

ምሽት

ላይ ቤተሰቡ ወደ ሆቴሉ ተመለሰ . . ጃንሎካ ለጆር
ጅ ስልክ ደውሎ ከቄስ ሎዊጂ ጋር ያለው ቀጠሮ ነገ ጧት አራት ሰዓት ላይ በቤተክርስቲያን መሆኑንና እርሱም እዚያ እንደሚጠብቃቸው ነገረው።

- ጃኖልካ ነው የደወለው፤ከቄሱ ጋር ያለን ቀጠሮ ነገ መሆኑን ነው የነገረኝ . . እናም ሕጻናቱን የት ነው የምንተዋቸው?

- ወይ ከኛ ጋር እንወስዳቸዋ፤ለን፣ወይ ደግሞ ከቤተክርስቲያኑ አቅራቢያ ባለው መናፈሻ እናቆያቸዋለን፣ውብ መናፈሻ ነው ያለው።

- መልካም፣ያ ይበልጥ የሚመች መሰለኝ።

ጧት ሁለት ተኩል ላይ ጆርጅና ካትሪና ከሕጻናቱ ጋር ከቤተክርስቲያኑ አቅራቢያ ወደሚገኘውና የተለየ የልጆች መጫወቻ ጥግ ወዳለው መናፈሻ አመሩ። ለሕጻናቱ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግላቸው ከጥጉ ኃላፊ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ማይክልና ሳሊን እዚያ እንዲቆዩ አደረጉ . . በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከቄሱ ጋር ለመገናኘት ወደ ቤተክርስቲያኑ አቀኑ . . ጃኖልካ ተቀበላቸውና ተያይዘው ሞቅ ያለ አቀባበል ወዳደረጉላቸው ቄስ ሉዊጂ አመሩ።

- ካትሪና እንኳን ደህና መጣሽ፣በእንግሊዝ አገር ስለምታደርጊው ከፍተኛ ትጥረትና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ እሰማለሁ፣ጌታ ይባርክሽ።

- ይህ ከርስዎ የተማርነውና ከርስዎ ዕውቀት ያገኘነው ነገር ነው።

- ጆርጅ እንኳ ደህና መጣህ . . ጃኖልካ ስለ ጥያቄዎችህና ስለ ብሩህ አእምሮህ ነግሮኛል። የምትፈልገውን ማቅረብ ትችላለህ።

- ጊዜዎን አላባክንም፣አራት ጥያቄዎች አሉኝ። አንደኛው እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንዴት እንደሚሆን አልገባኝም። ብዙ አንብቤያለሁ፣ብዙ ትንተናዎችንም አዳምጫለሁ፤ምንም ውጤት ላይ አልደረስኩም። ይቅርታ ደረግልኝና አንዳንዴ ክርስትና ከጣዖት አምላኪነት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው የሚሰማኝ!

የቄሱ ፊት ተለዋወጠ፤የጃኖልካና የካትሪናን ፊት ተመለከቱና ቀጥለው መሬት መሬት እያዩ . .

- ሁለተኛውስ?

- ኢየሱስ አምላክ ነው ወይስ ሰው ነው? አምልኮት የሚደረግለት አምላክ ነው ወይስ የተገደለ አገልጋይ ፍጡር ነው? የሰው ልጆችን ለማዳን አምላክ መሞት ያስፈልገዋል?! ሳይሞት በሕይወት እየኖረ ሰዎችን ማዳን አይቻልም?

- ሦስተኛውስ?

- መጽሐፍ ቅዱስን ብሉይ ኪዳንንም ሆነ አዲስ ኪዳንን ማነው የጻፈው? ማንስ ተረጎመው? ወደኛ ያስተላለፈውስ ማነው? በተለያዩ እትሞቹ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአንድ ተመሳሳይ እትም ውስጥ እርስ በርስ የሚጣረሱ ተጻራሪ ነገሮች ለምን ኖሩ? መጽሐፉ ውስጥ ካሉት ብዙዎቹን ምንባቦች ለማንበብ ልጆቼን እንኳ የማፍር ከሆነ ፈጣሪዬን ዘንድ አሳፋሪነቱ እንዴት ነው የሚሆነው?

- አራተኛውስ?

- የሃይማኖቶችና የነብያት ታሪክ የግድያ፣የአመጽና የብልግና ታሪክ ነው? አመጽና ግድያን እጠላለሁ፤ለአመጽና ለግድያ ጥሪ የሚያደርገውን ሁሉ እጠላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ ለነብያትና ለእግዚአብሔር መልእክተኞች ያለው አመለካከት ግን ይገርመኛል፤የግድያ የዝርፊያና የወሲብ ጥቅሶችም እንዲሁ ይገርሙኛል!

ቄሱ ራሳቸውን ቀና አደርገው ወደ ጃኖልካ ከመዞራቸው በፊት ጆርጅንና ካትሪናን ዓይን ዓይናቸውን ተመለከቱ . .

- ጃኖልካ አስቀድመህ የርሱን ጥያቄዎች ለምን አልነገርከኝም?

- እርሱም አልነገረኝም ነበር!

ቄሱ ለአፍታ የጆርጅን ዓይኖች ትኩር ብለው አዩ . . ከዚያም የድከመትና የቁርጠኝነት ምልክቶች ተጣምረው በሚስተዋልበት ፊት ወደላይ ተመለከቱ፤በመቀጠል በጥልቀት ለመናገር ተመቻቹ . . .

- አየህ ልጄ የነዚህን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲህ በቀላሉ መረዳት አትችልም፤ለማብራራትም ረዥም ጊዜ ይወስዳሉ። እናም ይህን ትተህ ወደ ጌታ አምልኮ ለምን አትሰማራም?

- ጌታዬ፣የመጣሁት ከርስዎ ተምሬ በዕውቀትዎ ለመጠቀም ነው። ረዥም ትንታኔ የሚያስፈልገውን ነገር ምሁራን ዐዋቂዎች አሳጥረው መግለጽ ይችላሉ።

- ደግ ነው ልጄ፣በሃይማኖታችን ውስጥ ልንወያይባቸውና ልንከራከርባቸው የማይገቡ ብዙ ምስጢሮች ይገኛሉ። አንተ ብቻህን በራስህ ልትረዳቸው የማይገቡ ብዙ ምንባቦችም እንደዚሁ አሉ።

- ጌታዬ፣ምስጢሮቹን በተመለከተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ ሃይማኖት እንድንከተል ታዘን ይህ ሃይማኖት ምስጢር ሊሆን እንዴት ይችላል? ለሁሉም ሰው ከእግዚአብሔር የተላለፉ ምንባቦችን ጥቂቶች ብቻ እንጂ ሌሎች የማይረዱት እንዴት ነው?!

በአነጋገሩ መከፋታቸው በቄሱ ፊት ላይ በግልጽ ታየ፤ወደ መሬት አዩና እንዲህ አሉ

- ከጆርጅ ጋር ብቻዬን እንድሆን ሁለታችሁ ገለል ልትሉልን ትችላላችሁ?

የጃኖልካ ፊት ተለዋወጠ፣በአነጋገራቸው መከፋቱ በግልጽ ተስተዋለበት፤አርሱ ራሱ ካመቻቸው ፕሮግራም በገዛ ወዳጁ መባረሩ ሊዋጥለት አልቻለም . .

- እኔና ካትሪና እንድንወጣልዎ ነው ሚፈልጉት? ለምን ይህም ሌላው ምስጢር ይሆን እንዴ?!

- ለርሱ ብቻ መንገር የምፈልገው ነገር ስላለ ብትወጡልኝ አመሰግናችኋለሁ።

- ካትሪና ወደ ማይክልና ሳሊ ሂጂና እዚያ ጠብቁኝ፣ከአፍታ በኋላ እቀላቀላችኋለሁ።

ካትሪና ቄሱን ተሰናበተች፤ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሚመሩት የቅዳሜ የቅዳሴ ሥርዓት እንዳትቀር አሳስበው በቡራኬ ሸኙዋት . . ከጃኖልካ ጋር ወደ መናፈሻው አመራች . . ሁለቱ ለቀው ሲወጡ ቄሱ ወደ ጆርጅ ፊታቸውን አዞሩ . .

- የኔ ልጅ አንተ በጣም ደፋር በጣም ጀግና ሰው ነህ፤ጀግንነት የጦር ሜዳው ሳይሆን ውስጣዊው ጀግንነት ነው።

- ጌታዬ አመሰግናለሁ።

- ልጄ ካንተ ጋር ስናገር እኔም ደፋር ጀግና ሆኜ ነው፤ምናልባትም የማትወደውን ነገር ከኔ ልትሰማ ትችላለህ።

- እሽ ይሁን፣ዋናው ነገር የምወደውን መስማቴ ሳይሆን የሚያስፈልገኝን መስማቴ ነው።

- ሊያስደንቅህ ይችል ይሆናል፣እያዘንኩ ለነዚህ ጉዳዮች ቁርጥ ያለ ምላሽ አይገኝም።

- ጌታዬ፣እምነትና ጥርጣሬ አንድ ላይ ሊሆኑ እንደማይችል አይታይዎትም?

- የምትናገረው ትክክል ነው። ቀርጥ ያለ መልስ ማግኘት ግን አልቻልኩም። ዕድሜዬን በሙሉ አንተ የጠቀስካቸውንም ለሚያጠቃልሉ ብዙ ጉዳዮች ምላሽ ስፈልግ ቆይቻለሁ። የሆነ ነገር መልስ ነው ብዬ ልነግርህ እችል ነበር፤ግና ደፋርና እውነተኛ ለመሆን ቃል ስለ ገባሁልህ እውነቱን ልንገርህና እስካሁን ድረስ ቁርጥ ያለ ምላሽ አላገኘሁላቸውም።

- ታዲያ መፍትሔው ምንድነው?

- እኔ አሁን ካለሁበት የተሻለ ነገር ስላላገኘሁ አሁንም ቄስ ነኝ። ለኔ በሁሉም ነገር ተጠራጣሪ ከመሆን መልስ ያላገኘሁላቸው አንዳንድ ጉዳዮች መኖራቸው ይመረጣል፤አይመስልህም?

- ልክ ነዎት፤ይሁን እንጂ በላጩ መልስ ብናገኝላቸው ነው።

- እውነት ነው፤ምናልባት አንተ መልሱን ታገኝ ይሆናል፤የማረጋግጥል ነገር ቢኖር መልሱ ከቤተክርስቲያን በኩል እንደማይሆን ነው። በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ በቄስነት ሰላሳ ዓመታት አሳልፌያለሁ፣መልስ ግን አላገኘሁም። እኔ ዘንድ ያለው ይኸው ብቻ ነው።

- አንድ ጥያቄ እንድጠይቅ ይፈቅዱልኛል?

- ጠይቅ።

- ጃኖልካና ካትሪና እንዲወጡ ለምን ፈለጉ?

- በምነግርህ ነገር ትገረም ይሆናል! ይህን ያደረኩት ድፍረትና ጀግንነት ስለሚጎድለኝ ነው። ማንም ቢሆን በሌሎች ሰዎች ፊት በተለይም ዐዋቂ ነው ብለው በሚተማመኑበት ሰዎች ፊት ደካማ አላዋቂ ሆኖ መታየት አይፈልግም። በተጨማሪም ካቶሊካዊነትን ወይም ክርስትናን ከነአካቴው ቢተውት ምንድነው የሚሆኑት? ለምሳሌ ኤቲስት ሊሆኑ ይችላሉ። በኔ እምነት በጥርጣሬና በውዥንብር ዓለም ከመኖር የተወሰኑ ጥርጣሬዎችን ይዞ መኖር የተሻለ ነው።

- ይቅርታ ይደረግልኝና ለመሆኑ ከቀሳውስትና ከመነኮሳቱ መካከል እርስዎ የሚሉትን ነገር በይፋ ለመናገር ድፍረቱ ያላቸው የሉም ማለት ነው?

- በክርስትና ታሪክ ውስጥ ይህን ያደረኩ ቀሳውስትና መነኮሳት በተለያዩ ዘመናት ተነስተዋል፤ሁሉም ግን ወይ ይገደላሉ፣ወይ ይሰወራሉ፣ወይ ይሸሻሉ። መጽሐፍ ቅዱስና የቫቲካን መንበረ ፓትርያርክ ሥርዓት ጨካኞች ናቸው።

እናም ኤሪክ ፊራቲኒ ‹‹ተቋሙ - የሰላይነት አምስት ምእተ ዓመታት›› በሚለው መጽሐፉ ውስጥ እንዳረጋገጠው በቫቲካንና በተለያዩ የዓለማችን የስለላ ድርጅቶች መካከል ያለውን ምስጢራዊ ግንኙነት እርስዎም ይደግፋሉ ማለት ነው?

- ፈጽሞ . . ይህ ትክክል አይደለም፤ከአሜሪካዊ ፕሮቴስታንት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ ስም ማጥፋት ነው።

- በመረጃ የተደገፉና ያነሳቸው እውነታዎችሳ?

- እያዘንኩ ብዞዎቹ እውነት ናቸው እለሃለሁ፤ዳሩ ግን ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን እና ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናውን ለማሳጣት በሚያስችል አቀራረብ ሆን ተብለው የተቀነባበሩ ናቸው።

- የስለላ ተቋማት ወደ ቫቲካን መስረግ ወይም በሌላ አገላለጽ የቫቲካን የስለላ ተቋም በመላው ዓለም መሰራጨቱ ግን እውነት ነው። ልክ አይደለም?

- እያዘንኩ አሁንም አውነት ነው፤ብዙ ጊዜ የሚሆን ቢሆንም አጠቃላይ የሆነ ጉዳይ ግን አይደለም ።

- ቫቲካንና መንበረ ፓትርያርኩ ጭካኔና ጡጫውን በካህናትና በመነኮሳት በኩል በሕጻናት ጭምር ላይ በሚፈጸሙ የወሲብ ቅሌቶች ላይ ለምን አላየንም?

- ሊታይ አይችልም፤ይህ ነገር በመካከላቸው በሰፊው የተሰራጨ ነው። ታዲያ ለሕጻናት ተብሎ ቤተክርስቲያኒቱ ትሰንጠቅ ብለን እንዴት እንጠብቃለን?! ደግሞም ከነዚህ ወሲብ ነክ ጉዳዮች ከፊሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ውስጥ ጭምር የሚገኘ ነው። አንተ አንባቢ ምሁር ነህና የኔ ልጅ ችሎታህን በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብታውለው የተሻለ ነው። ክርክሩን እዚህ ላይ ብንገታውስ?

- ጌታዬ ካቲሪና እና ጃኖልካ ለምን እንዳስወጧቸው ቢጠይቁኝ ምን ልበላቸው?

ቄስ ሎዊጂ በዝምታ ተውጠው እንዳቀረቀሩ፦

- ሁሌም ቢሆን እውነት ተመራጭ ነው።

- ጌታዬ አመሰግናለሁ፤በጌታ ፈቃድ አድርገዋለሁ፤ከርስዎ ብዙ እውቀት ገብይቻለሁ።

- እኔም አመሰግናለሁ፣ጌታ ይባርክህ፤በተከበረው የቅዳሜ የቅዳሴ ሥርዓት ላይ እንደማገኝህ ተስፋዬ የጠበቀ ነው፤እርግጠኛ መሆን ከጥርጣሬ የተሻለ ነው።

ጆርጅ ተሰናብቶ ከወጣ በኋላ ካትሪና እና ጃኖልካ ወደሚጠብቁበት መናፈሻ አመራ። እንደ ደረሰ ጃኖልካ ጠየቀው፦

- ለምንድነው እኛን ያስወጣን? ሎዊጂን ያልተገራ አድራጎት ሲፈጽም ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነው !

የጃኖልካ ቁጣና መከፋት ግልጽ በመሆኑ ጆርጅ በማስወጣቱ ጉዳይ ላይ መነጋገር አልፈለገም . .

- የምሳ ሰዓት ተቃርቧል፤አብረን በልተን ለመጨዋወት እንድንችል፣ከቤትህ አቅራቢያ ካለው አልፈኻማ ሬስቶራንት በቅርብ ርቀት ላይ ነን?

- አዎ፣ከዚህ በእግር የአምስት ደቂቃ መንገድ ነው።

- እንግዲያውስ ፍቀድልኝ . . ከልጆቼ ጋር ተጫውቼ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ወደ ሬስቶራንቱ እንቀሳቀሳለን . . ካትሪና ምን ትያለሽ?

- ጥሩ ነው፣በግማሽ ሰዓቱ ውስጥ ባንተና በቄሱ መካከል ስለ ነበረው ቆይታ እንድትነግረን ምኞቴ ቢሆንም፣ይሁን ችግር የለውም። ለማንኛውም ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሁሉንም ነገር ትነግረናለህ።

ጆርጅ ለጃኖልካና ለካትሪና ምን እላለሁ? ያበጠው ይፈንዳ የሆነውን ሁሉ ልንገራቸው? ምን ላደርግ? ብሎ ከራሱ ጋር እየተሟገተ ልጆቹ ወደሚገኙበት የመናፈሻው የሕጻናት ጥግ አመራ።
ከግማሽ ሰዓት በኋላ ጆርጅ ከሕጻናቱ ጋር ተመልሶ መጣ . .

- በጣም ርቦናል፣በሉ ወደ ሬስቶራንቱ እንሂድ።

- በሉ እንሂድ።

ከቄሱ ጋር (2)

ለአምስት ደቂቃ ያህል በእግር ከተጓዙ በኋላ ወደ አልፈኻማ ሬስቶራንት ደረሱ . . ጆርጆ ወደ ማይክልና ሳሊ ጎንበስ ብሎ፦

- ውዶቼ . . ከተማውን እያያችሁ በሬስቶራንቱ ሰገነት ላይ ብትመገቡ ምን ይመስላችኋል?

- አንተና ማማ የት ልትመገቡ?

- እኛ የጠበቀ ቀጠሮ አለን። እናንተ ለብቻችሁ ሆናችሁ እየተጨዋወታችሁና የከተማውን ውብ ገጽታ እያያችሁ ምሳችሁን ትበላላችሁ።

- በጣም ጥሩ፣ሳሊ በይ እንሂድ።

ጆርጅ ካትሪና እና ጃኖልካ መሀል ላይ ያለውን ጠረጴዛ ይዘው ተቀመጡ . . የምግብ ዝርዝሩን በማየት ላይ እያሉ ጆርጅ ፊቱን ወደ ጃኖልካ አዞረና . .

- ሙስሊሙ ወዳጅህ የት ነው?

- እሱም እኛን አስወጥቶን ካንተ ጋር ብቻ ለመነጋገር እንዳይጠይቅ እሰጋለሁ . . ለመንኛውም የምግብ ትእዛዞቹን ለመቀበል ከአፍታ በኋላ ይመጣል።

- ከቄሱ ጋር ትተኸኝ እንድትወጣ እኔ አልጠየኩህም፣የቄሱ ወዳጅህ ፍላጎት ነው።

- ይሁን እንጂ አንተም ወዲያው ነው የተስማማኸው።

- እህህ፣ታዲያ የሃይማኖት መሪዎችን መታዘዝ ግዴታ አይደለም እንዴ?! ዋናው ነገር . . ጥያቄዎቼ መልስ እንደሌላቸውና እናንተ ደግሞ ድክመቱንና አለማወቁን እንዳታዩ መፈለጉን ነው የነገረኝ።

ካትሪና ተከፍታ ወደ ጆርጅ ዓይኖች እየተመለከተች፦

- ቄስ ሎዊጂ ዘንድ እንዲህ ላሉ ቀላል ጥያቄዎች ምላሽ ሊታጣ አይችልም !

- ምላሽ እንደሌሉትማ በሚገባ አውቃለሁ፣ይህንን እንደማውቅም ያውቃል። የገረመኝ ለምን እንድንወጣ ፈለገ? በጉዳዩ ውስጥ ሌላ ነገር እንዳለ ነው የሚሰማኝ።

- ለማንኛውም ከኔ ይበልጥ ስለምትተዋወቁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፤እንደሚመስለኝ ካትሪናን ብቻ ማስወጣት ስለአሳፈረው ነው።

ለአፍታ ዝምታ ሰፈነ . . ዓይኖቿ ልታፍነውና ልትደብቀው የምትሞክረው ነውጥ ውስጧ መኖሩን የሚያሳብቁ ይመስል ጆርጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በባዘነ የካትሪና እይታ ውስጥ ግራ መጋባትና ጥርጣሬ መኖሩን አስተዋለ። ዝምታዋ ምናልባት የታፈነ እሳተ ገሞራ ዝምታ ዓይነት ሊሆን ይችላል። የጀኖልካ ዝምታ ግን በግልጽ በሚያውቀው ጉዳይ ላይ ወዳጁ ይህን ማድረጉ አስገርሞት ቢሆንም ጆርጅ ከነገረው ውጭ ከጀርባው የሆነ ነገር አለ የሚል ጥርጣሬ አሁንም አልለቀቀውም።
ትእዛዝ ለመቀበል አስተናጋጅ መጣና አስፈሪውን የዝምታ ድባብ ሰበረው . . ጃኖልካ የሬስቶራንቱ ባለቤት ሰሊም መኖሩን ጠየቀውና ከተቻለ ከርሱ ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ ነገረው . .

- ሰሊም ከወዳጆቹ ጋር እቢሮው ነው ያለው . . መልእክትዎን አደርሰዋለሁ . . ይቅርታ ለምሳ ምን ልታዘዛችሁ?

ትእዛዞቻቸውን ለአስተናጋጁ ተናገሩ። ጆርጅ ማይክልና ሳሊ የት እንዳሉ ለአስተናጋጁ ነግሮ ትእዛዙን እንዲያደርስላቸው ጠየቀው . . ወደ ጃኖልካ እያየ ጥያቄ ሰነዘረ . .

- ሰሊም የነገርከኝ ሙስሊም ነው?

- አዎ፣ለመጀመሪያ ጊዜ ስታየው ጣሊያናዊ ሊመስልህ ይችላል . . በነገራችን ላይ እንግሊዝኛን ጥርት አድርጎ ይናገራል።

- መልካም፣ከአፍታ በኋላ ይመጣና እንሰማው ይሆናል።

ከረዥም ዝምታ በኋላ ካትሪና ተናገረች . .

- አሁን ወደ ቄሱ ጉዳይ እንመለስ . . ለጥያቄዎችህ መልስ መስጠት አልቻሉም ነው ምትለው !

- አዎ አልቻለም፣ይህም ብቻ ሳይሆን ዕድሜውን በሙሉ ለነዚህና ለሌሎቹም ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሲጥር መኖሩንና አሳማኝ መልስ ማግኘት ያቃተው መሆኑን ነው የነገረኝ።

- ሊሆን የማይችል ነው !

- ካትሪና የምትናገሪው ቄስ ወዳጄ ነው፤መልሶቹን እንደማያውቅ በሚገባ አውቃለሁ። በነዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ ተከራክሬዋለሁ። የገረመኝ ግን ለምን እንድንወጣ እንደፈለገ ብቻ ነው ! የማላውቀው ነገር ቢኖር ይኸኛው ብቻ ነው !

- ቄስ ሎዊጂ እስቲያቬኖ እርግጠኛ እንድሆን ካገዙኝ ሰዎች መካከል ዋነኛው ናቸው። እንዴት ሆኖ ነው ይህ ጥርጣሬ እሳቸው ዘንድ ሊኖር የሚችለው?!

ጆኖልካ ለመናገር ተመቻችቶ አንጋጦ ተመለከተና፦

- የኔ ተሞክሮ እንዲህ ይላል ፦ የቄሱ ዕውቀት እየዳበረ በመጣ ቁጥር በግል በሚያደርገው ውይይት ይበልጥ እየተለሳለሰ ሲሄድ፣ለተራው አማኝ በጅምላ የሚሰጠውና የሚመጠናቸው ትምህርቱ ደግሞ ተጽእኖው እየጨመረ ይመጣ ነበር።

- ምን እያልክ ነው?

- አንቺ ከርሱ የሰማሽው ለተራው አማኝ የሚሰጠውን ትምህርት ነው። ለግለሰብ በዝግ የሚናገረው ግን ከዚያ የተለየ ነገር ነው። ለማንኛውም እኔ እረደዋለሁ፤ለሕዝብ በይፋ በሚሰጠው ትምህርት ምን እንዲል ነው የምትፈልጊው?! እኛ ጌታን አናውቅም፣ወይም መጽሐፍ ቅዱስ የተዛባ ወይም የሰዎች የገባበት ፈጠራ ነው እንዲል ትፈልጊ ኖሯል?!

ዓይኖቿ እንባ እየዘሩ ካትሪና እንዲህ አለች፦

- አይደለም፣ቸሩ ርህሩሁ ጌታ ሦስት አካላት ቢኖሩትም አንድ ነው፤መጽሐፍ ቅዱስም ከርሱ የተላለፈ ቃሉ ነው እንዲሉ ነበር የምፈልገው።

ጃኖልካ ካትሪናን በአዘኔታና በስስት ዓይን እያያት፦

- መጽሐፍ ቅዱስ ከገዛ ራሱ ጋር እርስ በርሱ ሲጣረስ ምን ማድረግ እንችላለን? አሳማኝ በሆነ ሎጂካዊ መንገድ ሦስት አንድ፣አንድ ደግሞ ሦስት እንዴት አንደሚሆን ልታብራሪልኝ ትችያለሽ?! በቤተክርስቲያን የሚሉትን እንደማይለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ያንን ሺህ ጊዜ ሰምቻለሁ፣ሊያሳምነኝ አልቻለም፤ይልቁንም ለብዙኃን ለሚሰጥ የጅምላ ትምህርት ብቻ እንጂ ለሌላ የሚረባ አይደለም የሚል እምነት አለኝ።

ጆርጅ የካትሪና ከባድ ውስጣዊ ነውጥና በውስጧ በመፈንዳት ላይ ያለው እሳተ ገሞራ ተሰማው። ለራሱ እንዲህ አለ፦
ስለ ቄሱ የሰማችው ነገር ንዝረቱ አቅሟ መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኖባት ሊሆን ይችላል አለና ርእሱን ለመለወጥ ሞከረ . .

- አሁን ወደኛ የሚመጣ ሰው ስላለ ውይይታችሁን ለሌላ ጊዜ ብታቆዩ ምን ይመስላችኋል?

- ኦ ሰሊም ነው . . ሰሊም እንኳን ደህና መጣህ፣ካንተ ጋር መተዋወቅ የሚፈልግ ሰው አለ።

- ሁላችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ . . ጃኖልካ ከእንግዶችህ ጋር እንኳን ደህና መጣህ።

- ሁለቱ እንግዶቼ ከዚህ በፊት ከሙስሊም ሰው ጋር ተቀምጠው አውርተው ስለማያውቁ ካንተ ጋር ትንሽ ማውጋት ይፈልጋሉ።

- ደስ ይለኛል፤እኔ ከግብጽ ነኝ። እናንተስ ከየት ናችሁ?

- ከእንግሊዝ ነን።

- በእንግሊዝ የሙስሊሞች ቁጥር በኢጣሊያ ካሉት በእጥፍ ይበልጣል።

- ልክ ነህ፤እኔ እንኳን የፈለኩት ስለ እስላም ካንተ ለማወቅ ነው። ቅዱስ መጽሐፋችሁ በብሉ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ያምናል?

- ስእስላም ሃይማኖት እምነቶች ያለኝ ዕውቀት በጣም ውስን ቢሆንም ለማንኛውም የማውቀውን እመልስላችኋለሁ . . አዎ፣ያምንባቸዋል፤ግን - ይቅርታ አድርጉልኝና - የተዛቡና የተበረዙ አድርጎ ይወስዳቸዋል።

- በሙሴና በኢየሱስ ታምናላችሁ?

- ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ነብያት ናቸው ብለን እናምንባቸዋለን።

- በጌታ ኢየሱስ ታምናላችሁ?

- አናምንም፣ሙስሊሞች የሚያምኑት ጌታ ሳይሆን የተከበረ የእግዚአብሔር ነብይ መሆኑን ብቻ ነው።

- ቅዱስ መጽሐፋችሁ ስሙ ምንድነው? እንዴት ነው ወደናንተ የደረሰው?

- ስሙ ቁርኣን ነው፤የደረሰን በነብዩ ሙሐመድ አማካይነት ነው . . ምንድነው የፈለጋችሁት?

- እስላምንና ትምህርቶቹን መተዋወቅ ነው የምንፈልገው።

- እኔ በበኩሌ እስላምን ብዙም አላወቅቀውም፤የማውቀው ንግድና ቱሪዝምን ነው። ለመሆኑ ከእስላም ምንድነው የምትፈልጉት?

- እናንተ ዘንድ ያለው አመጽና ሽብርተኝነት ስለሚያስገርመን ብቻ ነው።

- እኛ ዘንድ ያሉት አሸባሪ ሙስሊሞች በሃይማኖት ስም ሁሉንም ነገር ያወድማሉ።

- በሃይማኖት ስም ነው የምትለው? እንዲህ ያለ አመጽና ሽብር ያለበት ምን ዓይነት ሃይማኖት ነው?

- አዎ፣እስላም የሰላም ሃይማኖት እንጂ የሽብር ሃይማኖት አይደለም፤ሙስሊሞች ግን ኋላ ቀሮችና ግትሮች ናቸው።

- እንደገና ኋላ ቀሩ እስላም ነው ወይስ አሸባሪዎቹ ናቸው?

- እስላም ኋላ ቀር አይደለም፣ሙስሊሞች ግን ኋላ ቀር ናቸው። ሙስሊሞች ብትሆኑ ሚስትህ እንደዚህ ከኛ ጋር ቁጭ ብላ እንዲህ ማውራት የማይቻል ነበር። ታዲያ ይህ ኋላ ቀርነት አይደለም?

- ለምንድነው ከናንተ ጋር መቀመጥ የማይቻለኝ?

- መሸፋፈንና ከወንዶች መራቅ ስለሚኖርብሽ መቀመጥ አትችይም፤እውነቱን ለመናገር ግብጽን የተውኩት ከዚህ ኋላ ቀርነት ለመራቅ ነው።

- ዘመዶችህና መንግስትህም አቋማቸው ይህ ነው?

- እህህ . . አባቴ እናቴና ወዳጆቼ ሁሌም አመለካከትህ ከእስላም ያፈነገጠ ነው ይሉኛል።

- ለምን?

- እስላም ከክርስትና ሙለ በሙሉ ይለያል፤እናንተ ክርስቲያን ለመሆን አልፎ አልፎም ቢሆን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ መጸለይ ይበቃችኋል። እኛ ዘንድ ግን በቀን አምስት ጊዜ የማይሰግድ ሰው ከሃይማኖቱ ውጭ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል። እናንተ ብሉይና አዲስ ኪዳንን መተቸት ትችላላችሁ፣በኛ ግን ቁርኣንን የተቸ ሰው ከእስላም እንደ ተቀለበሰ ይቆጠራል።

- ከቤተሰቦችህ ውስጥ እዚህ ጣሊያን ውስጥ የሚኖር ሰው አለ?

- ከአስር ዓመታት ወዲህ ጣሊያን ውስጥ ለብቻዬ ነው የምኖረው፤ወደ አገሬ መመለስ እምቢ ብያለሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከሳምንት በፊት ወንድሜ፣እናቴና አባቴ መጥተው እዚህ ይገኛሉ፣ከሦስት ቀናት በኋላ ተመልሰው ይሄዳሉ።

- ላገኛቸው እችላለሁ?

- አዎ ይቻላል፣ነገር ግን እናንተ እነሱ ዘንድ ከሀዲዎች በመሆናችሁ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

- እንዴት?

- አንተ እግዚአብሔር ሦስት ነው ትላለ፤ህ፣ይህ ደግሞ ከርሱ ጋር ባእድ አምላክ መያዝ በመሆኑ አንድ እግዚአብሔርን ክደሃል፣ካፍር ነህ ማለት ነው።

- ምን አዲስ ነገር አለው?! እኛም በኢየሱስ አምላክነት ስለማያምኑ ከሃዲዎች ናቸው እንላለን፣ብናገኛቸው ምንም ችግር የለውም።

ካትሪና አሁንም ከቄሱ ጋር በሆነው ነገር ክፉኛ እንደበረገገች ናት፤በመሆኑም ተጨማሪ አንቀጥቃጭ ነገር የሚሸከም አቅም እንደሌላት ይሰማታል

- ጆርጅ ጊዚ የለንም፣ነገ የተከበረው የቅዳሜ የቅዳሴ ሥርዓት መሆኑን አትዘንጋ።

- እነሱ ጊዜ ካላቸው እኛ በቂ ጊዜ አለን . . መቼ ልናገኛቸው እንችላለን?

- ሙሉ ጊዜአቸውን ወይ ቤት ወይ እዚህ ሬስቶራንት ናቸው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይመጣሉ ብዬ አስባለሁ። ሌላ ጊዜ እንዲሆን ከፈለክም እንዲጠብቁህ አደርጋለሁ . . እደግመዋለሁ ስለሚናገሩት ነገር እኔ ተጠያቂ አይደለሁም።

ጆርጅ ነገሩን የምር በመያዙ ካትሪና ፊት ላይ ገልጽ የመከፋት ስሜት ይነበባል፣በምሬት እንዲህ አለችው፦

- ይቅርታ . . ጆርጅ ምን እንዳሰብክ አልገባኝም። ሞቼ እገኛለሁ ካልክ ተመልሰን ወደ ሬስቶራንቱ ለመምጣት እንዳንገደድ ጥቂት ደቂቃዎች እንጠብቃቸው።

- ወደ ላይ ወጥቼ ማይክልና ሳሊን አይቻቸው እመለሳለሁ።

- ቆይ፣ይኸውና መጥተዋል፣ከኛ ጋር እንዲቀመጡ ወደዚህ ልጥራቸው?

- ወደዚህ ጥራቸው፤ልጆቹን አይቼ በፍጥነት እመለሳለሁ።

- እጠራቸዋለሁ፣የናንተ ጥያቄ ነውና ኃላፊነቱን የምትወስዱት እናንተ ናችሁ . . እናቴ፣አባቴ፣ኻሊድ ወደዚህ ኑ . . ከናንተ ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው እዚህ አለ።

- ሳሊም ምድነው?

- ኻሊድ እነዚህ ወዳጆቼ ከናንተ ጋር መተዋወቅ ይፈልጋሉ። ላስተዋውቃችሁ ይህ ወንድሜ ኻሊድ ነው፣እሷ እናቴ ነች፣ይሄ አባቴ ነው . . ኻሊድ እንግሊዝኛ ይናገራል፣እናቴና አባቴ ግን በመጠኑ ብቻ ይረዳሉ እንጂ አይናገሩትም። ሁላችሁም ፍቀዱልኝና እኔ ከማዳመጥ ውጭ በውይታችሁ ውስጥ ጣልቃ አልገባም።

- ሁላችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ፤ኻሊድ እባላለሁ የሕንጻ መሀንዲስ ነኝ፣ሰሊም ወንድሜ ነው። ይህ አባቴ ዐብዱላህ ነው፣እሷ እናቴ ዓእሻ ናት።

- እኔ ጃኖልካ እባላለሁ በነጻ ንግድ ላይ የተሰማራሁ ኢጣሊያዊ ነኝ።

- ስሜ ካትሪና ነው፣እንግሊዛዊት ነኝ።

- ሁላችሁም እንኳን ደህና መጣችሁ።

ጆርጅ ከልጆቹ ዘንድ ተመልሶ መጣና ሰላምታ አቅርቦ ኻሊድና አባቱን ከጨበጠ በኋላ እናቲቱን ለመጨበጥ እጁን ሲዘረጋ ሳትጨብጠው ፈገግ ብላ ሰላምታውን መለሰችለት . .

- ይቅርታ . . እናቴ ወንዶችን አትጨብጥም፣ሰላም እንኳን ደህና መጣህ ትለሃለች።

- እኔም ይቅርታ እጠይቃለሁ፣እንዲህ መሆኑን አላውቅም ነበር።

- አንተ ከመምጣትህ በፊት ተዋውቀናል፤እኔ የሰሊም ወንድም ነኝ፣ስሜ ኻሊድ ነው፣የሕንጻ መሀንዲስ ነኝ፤እሷ እናቴ ነች፣ይህ አባቴ ነው።

- እኔ ጆርጅ እባላለሁ፣የኮምፒውተር መሀንዲስ እንግሊዛዊ ነኝ። የጥንታዊ ታሪክ የሃይማኖትና የጥበብ አገር የሆነችውን ሮምን እንዴት አገኛችኋት?

- የሕንጻ መሀንዲስ እንደ መሆኔ በጥበቡ ልጀምር መሰለኝ።ሮም በልዩ ጥበብ የተዋበች ናት፣አንዳንድ የማልወዳቸው ነገሮች ቢኖሩባትም የጥንታዊ ስልጣኔና የዘመናዊ ተሞክሮ ባለቤት የሆነች ግንባር ቀደም ከተማ ነች።

- ምኗን ነው ያልወደድከው?

- ቅርጻ ቅርጽ ጣዖታትና ሰዎች በአክብሮትና በቅድስና የሚመለከቷቸው መሆኑ አያስደስተኝም። እንዲህ ያለው ነገር ካደግንበት ሃይማኖታችን ጋር አይጣጣምም። ይህ ጣዖታዊነትና ከአንድ አምላክ ሌላ ባዕድ አማልክት ማምለክ ነው ብለን እናምናለን።

ጆርጅ ሐውልትና ቅርጻ ቅርጾችን በመጥላቱ ረገድ ከሙስሊሞች ጋር መመሳሰሉን አስታወሰ . . የሕንዱዎችና የቡድሂስቶች ቅርጻ ቅርጽና ጣዖታት አማልክትም ትዝ አሉት . .
ኻሊድ ቀጠለ . .

- ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ስለ ሮም ወደ ጠየከኝ ርእስ ይወስደኛል።

- በማቋረጤ ይቅርታ፣ያደግንበት ሃይማኖታችን ስትል ምን ማለትህ ነበር?

- በእስላም ውስጥ እኛ ማንንም ምንንም ከእግዚአብሔር ጋር አናጋራም። ምንም ሸሪክ የሌለው አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን አጥብቀን እናምናለን። ማንም ፍጡር ማንም ሰው ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ሊል አይገባም፣ፈጽሞ አይችልምም። ለዚህ ነው ነብያችን ሙሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ‹‹ከኔ በኋላ መቃብሬን የሚመለክ ጣዖት አድርጋችሁ አትያዙ፤እኔ የአላህ ባሪያና መልእክተኛው ብቻ እንጂ ሌላ አይደለሁምና›› ይሉ የነበረው።

- ከአነጋገርህ እንደምረዳው እኛ ጣዖታውን አጋሪዎች ነን ማለት ነው?

- እግዚአብሔር ሦስት አምላክ ነው ብሎ የሚያምን ሰው እኛ ዘንድ በአላህ የሚያጋራ ሰው ነው።

ቀስፎ የያዛትን ነገር የምታስተነፍስ ይመስል ካትሪና በከርክሩ ውስጥ ጣልቃ ገባችና . .

- ያንተ ታላቅ ሰሊም ግን ሀሳቡ ከዚህ የተለየ ነው፣አንተ የምትለውን ነገር አክራሪነት ነው ብሎ ነው የሚያምነው።

- ወንድሜ ሰሊም ታላቄ ነው፣አከብረዋለሁ፣ሰው ፊት እርሱን መጻረር አልወድም፤እኔ በግሌ ግን ባልኩት ነገር አጥብቄ አምናለሁ።

ጆርጅ አቋረጠና . .

- ይህ ማለት ሙሴና ኢየሱስ ውሸታሞች ናቸው ማለት ነው?

- እንዲህ ከማለት በአላህ እጠበቃለሁ ! እኛ በሙሴና በኢየሱስ (ሰላም በነርሱ ላይ ይሁንና) በፍጹምነት ነው የምናምነው። እናከብራቸዋለን፣እናልቃቸዋለንም። ከአላህ ዘንድ የተላኩ መልእክተኞች መሆናቸውንና ከአላህ ዘንድ መጽሐፎች የተላለፉላቸው መሆኑንም አጥብቀን እናምናለን . . ይልቁንም ብዙዎቹ የናንተ እምነቶች ደረጃቸውን አሳንሰው ያያሉ ብለን እናምናለን።

- እኛ የወልድን የኢየሱስን ደረጃ ዝቅ እናደርጋለን !

- እናንተ በሰው እጅ ተገድሏል ብላችሁ ታምናላችሁ፤እኛ ግን አልተገደለም ብለን እናምናለን። አንዳንዶቻችሁ ዘንድ ደግሞ ከጋብቻ ውጭ የተወለደ ተደርጎ ይታይ የለም? እናንተ አይደላችሁም ይህን ሁሉ የምታምኑት?

- እናንተስ . . በኢሱስና በድንግሏ ላይ ያላችሁ እምነት ምንድነው?

- ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሪያና መልእክተኛው መሆኑን እናምናለን፤ተመሳሰለባቸው እንጂ አልገደሉትም አልሰቀሉትም ብለን እናምናለን። አደም ያለ አባትና ያለ እናት እንደ ተፈጠረው ሁሉ ከእናቱ ከመርየም (ሰላም በርሷ ላይ ይሁንና) ያለ አባት በአላህ ተአምር የተወለደ ነው፤ለዚህም ነው በአንቀልባ ሆኖ በአራስነቱ የተናገረው፣ብዙ ተአምራትን አላህ የሰጠው፤መናገር የተሳነውንና በለምጽ የተያዙትን ሕሙማን ያድን የነረው፤በአላህ ፈቃድም ሙታንን ያስነሳ የነበረው፤ሰዎች በቤቶቻቸው የሚበሉትንና የሚያስቀምጡትንም ይነግራቸው የነበረው።

- እናም ስለ ኢየሱስ የተሟላ እሳቤ አላችሁ፣ታምኑበታላችሁ፣በብሉይና አዲስ ኪዳንም ታምላችሁ ማለት ነው?

- አዎ፣በኦሪትና በወንጌል በመሰረቱ ከእግዚአብሕር ዘንድ የተላለፉ በመሆናቸው እናምናለን።

- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው !

- በመሰረቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፉ መሆናቸውን ነገር ግን የተዛቡና የተከለሱ መሆናቸውን እናምናለን። እናንተ ዘንድም በአንዳንድ ወንጌሎች ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ወይም አምላክ ሳይሆን የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆኑ ተጠቅሶ የለም?

- የለም፣እንዲህ ያለ ነገር እኛ ዘንድ የለም።

ጃኖልካ ረዥም

ጸጉሩን ወደኋላ መልሶ እጁን አነሳና፦

- ስላቋረጥኳችሁ ይቅርታ፣የበርናባስ ወንጌል የሚባል ወንጌል አለ፤መኖሩ የታወቀው በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን ክርስትናን በከዳ ካቶሊካዊ መነኩሴ አማካይነት ነበር። ወንጌሉ ኢየሱስ ከርሱ በኋላ የሚመጣ ሌላ ተተኪ የእግዚአብሔር መልክተኛ ነብይ መኖሩን ያበሰረበትና ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልክተኛና ነብይ መሆኑን የሚያስተምር በመሆኑ፣ የተለያዩ የክርስትና ቡድኖች ግን ወንጌሉን አይቀበሉትም።

ጆርጅ በአድናቆት ዓይኖቹን አፈጠጠና፦

- እውነት ነው?! ታዲያ ካቶሊካዊ ቡድኖች ለምን ዕውቅና አልሰጡትም?!

- እርግጥ ነው ካቶሊኮችም ሆኑ ፕሮቴስታንቶች ባይቀበሉትም ሌሎች አንዳንድ የክርስትና ቡድኖች ተቀብለው አምነውበታል። ከዚያ በኋላ ብዙዎች እስላምን ተቀብለዋል፤በዚህ ምክንያትም ወንጌሉን የጻፈው ሙስሊም ነው ተብሎ ይተቻል።

ኻሊድ ፈገግ ብሎ፦

- ወንጌሉ ከሌሎቹ ይበልጥ ለእውነት የቀረበ ስለመሆኑ ማስረጃዎች አሉ።

- ይበልጥ ለእውነት የቀረበ ስትል ምን ማለትህ ነው? ትክክለኛ የሆነና ትክክለኛ ያልሆነ የሚባል ወንጌል አለ እንዴ?

- ከዓለማት ጌታ ከተላለፈው ወንጌል ጋር ይበልጥ የሚቀራረብ ማለቴ ነው። ይህም አዲስ በተገኙ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ወይም ግብጽ ውስጥ ከሚገኙ የበኒ መዛር ዋሻዎች በአንደኛው ውስጥ በተገኘው ወንጌል የተደገፈ ነው። ወንጌሉ ከነብዩ ሙሐመድ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) መምጣት በፊት በሦስተኛው ምእተ ዓመት መጀመሪያ የተጻፈ ሲሆን የይሁዳ ወንጌል ተብሎ ይጠራል፤በይዘቱ ከበርናባሳ ወንጌል ጋር ተመሳሳይ ነው።

ጃኖልካ በፌዝ ድምጸት፦

- የምትናገረው ሁሉ ትክክል ነው፣አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ግን በዚህም ሆነ በዚያኛው ወንጌል አያምኑም።

ኻሊድ ወደ ንድሙ ወደ ሰሊም እያየ፦

- ቅር አሰኝቻችሁ ከሆነ ይቅርታ አድርጉልኝ፣የምናገረው ነገር ሁሉ ለኢየሱስና (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ወደርሳቸው ለተላለፈው መጽሐፍ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር የመነጨ ነው።

ካትሪና ስሜቷ ተለዋወጠ፣ስለ ኢየሱስ ፍቅር ሲነሳ ዓይኖቿ እንባ አቀረሩ . .

- ሕይወቴ በሙሉ ለኢየሱስና ለፍቅሩ ቤዛ ይሁን፣ለዚህ ነው አዳኛችን በመሆኑ በርሱ የምናምነው፤ለዚህም ነው ክርስቲያኖች ተብለን የምንጠራው።

- እኔ የሕንጻ መሀንዲስ እንጂ የሃይማኖት ምሁር አይደለሁም፤ይሁን እንጂ ለዒሳ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ያለሽ ፍቅር እውነተኛ ይመስላል። ‹‹ለኢየሱስ ያለኝ ጥልቅ ፍቅር ወደ እስላም መራኝ›› የሚለውንና በቬንዙዌላዊው ካቶሊክ ክርስቲያን በሳይሞን አልፍሬዶ ካራቢሎ የተጻፈውን መጽሐፍ አንብበሻል?

- እንዲህ የሚባል መጽሐፍ መኖሩንም ሰምቼ አላውቅም፤ለኢየሱስ ያለኝ ፍቅርም ከካቶሊካዊነት በስተቀር ወደሌላ ይመራኛል ብዬም አልገምትም።

- ብታነቢው ምን ይጎዳሻል?! በካቶሊካዊነትሽ ትተማምኚ የለም?!

- አላየሁትም እንጂ አነበው ነበር።

- ይኸው ይህ ከኔ የተበረከተልሽ የመጽሐፉ እትም ነው። ይቅርታ ይደረግልኝና ከዓለማዊ ሕይወት የራቁና የናቁ መስለው የኢየሱስን ፍቅር ለግል ጥቅማቸው መገልገያ እንዳደረጉ አንዳንድ ቀሳውስትና መነኮሳት ሳይሆን ለኢየሱስ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ያለሽ ፍቅር ከልብ የመነጨ ሆኖ ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም።

- አመሰግናለሁ . . አነበዋለሁ፤ለኢየሱስ ባለኝ ፍቅር ላይም ሆነ በካቶሊካዊነቴ ላይ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ እርግጠኛ ነኝ።

- የሃይማኖት ምሁር አይደለሁም ትላለህ፣ስትናገር ግን የሃይማኖት ምሁር ቋንቋ ብቻ ሰይሆን ወደዚህ ሃይማኖት ጥሪ በሚያደርግ ሰው ቋንቋ ነው የምትናገረው።

- እስላም ሁላችንም ወደዚህ ሃይማኖት ጥሪ የምናደርግ ሰዎች እንደንሆን ይጠይቀናል። (ፈገግ ብሎ እናቱን አየና) እናቴ ወደዚህ አገር እንድመጣ ስታስገድደኝ እዚያ አገር ወደ እስላም ጥሪ የማድረግ አጋጣሚ ታገኝ ይሆናል ብላኝ ነበር፣እኔ ኢጣሊያንኛ ስለማላውቅ ለኔ ይህ የመጀመሪያ የደዕዋ አጋጣሚዬ ነው።

- ይቅርታ፣ሰው ሁሉ ወደዚህ ወደ ሰለጠነውና ወደ በለጸገው የምዕራቡ ዓለም ለመምጣትና ከኋላ ቀር አገሮች ለመውጣት ደስተኛ ነው። አንተ እንዴት ነው እናቴ አስገደደችኝ የምትለው?

- አውሮፓ ከኛ በጣም የሰለጠነች ናት። በየአገሮቻቸው በሚደርስባቸው ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊና ኢኮኖሚያዊ ጭቆና ምክንያት ስደተኞች ወደዚህ ሲደርሱ እንዲደሰቱ የሚያደርጋቸውም ይህ ነው። እኔ ግን በጥሩ ኩባንያ ውስጥ በመሀንዲስነት እሰራለሁ፣በቂ ገቢም አለኝ። እኛ ዘንድ በግብጽ አምባገነናዊው ሥርዓት ከወደቀ በኋላ ሁኔታችን ከበፊቱ የተሻለ ነው፣መጪው ጊዜ ደግሞ አላህ ካለ የበለጠ የተሻለ ይሆናል።

- እናንተ ዘንድ ላለው ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጭቆና መንስኤው ሃይማኖት አይደለም እንዴ?

- እስላም በምንም መንገድ የጭቆና ምክንያት ፈጽሞ ሊሆን አይችልም።

- በአሌግዛንደሪያ የሁለቱን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ያፈነዱት ሙስሊሞች አይደሉም?

- መጀመሪያ ላይ እንደዚያ ተብሎ ነበር፤ሁሉም ዓለም እኔም ጭምር በነገሩ ብገረምም እውነት ነው ብለን ተቀብለን ነበር። በምዕራባውያን ድጋፍ ሲገዛ የኖረው አምባገነኑ ሁስኒ ሙባረክ ከወደቀ በኋላ ግን ከፍንዳታው ጀርባ እሱና የስላላ ተቋማቱ እጅ እንደነበረበት ተረጋግጧል። የመጀመሪያውን ዜና ሰምተሃል፣በምዕራቡ ዓለም እንደተለመደው ሁለተኛውን ዜና አልሰማህም የሚል እምነት አለኝ።

- ይሁን እንጂ በሃይማኖታችሁ ምክንያት አሁንም ኋላ ቀሮች ናችሁ?

የኻሊድ እናት (ዓእሻ) ምልክት አሳይተውት፦

- ኻሊድ እንዲህ በለውማ ፦ የኔ ልጅ እኛ ወደኋላ የቀረነው በሃይማኖታችን ምክንያት ሳይሆን ከሃይማኖታችን በመራቃችን ምክንያት ነው!

ኻሊድ እናቱ ያሉትን ተርጉሞ ነገረው . . ምሳው ቀረበና ጠረጴዛ ላይ ተደረደረ፤ጆርጅ ግን የተጀመረውን ውይይት ለማስቀጠል ሞከረ . .

- አባትና እናትህ በመካከላችን የሚደረገውን ውይይት ይረዳሉ?

- አዎ፣በሚገባ ይረዳሉ፣እንግሊዝኛ መናገር ባይችሉም በሚገባ ይረዳሉ፤ሰሊም ከመጀመሪያው ነግሯችሁ ነበር፣ግና አንተ ከመምጣትህ በፊት ነው መሰለኝ።

- ጥያቄ ላቀርብላቸው እችላለሁ?

- እናቴ አቅርብ ትለሃለች፣መልሷን እኔ እተረጉምልሃለሁ።

- ኤቲስት ወይም አይሁዳዊት ወይም ክርስቲያን በሆንኩ ብለው አይመኙም?

- (እናት በኻሊድ ትርጉም) ፦ ልጄ በአላህ እጠበቃለሁ፣ብኩንነትንና ጥፋትን የሚመኝ ማንም ሰው አይኖርም።

- እኛ ያለንበት ጥፋትና ብክነት ነው ማለት ነው?

- (እናት በኻሊድ ትርጉም) ፦ ያ ጥፋትና ብክነት ካልሆነ ጥፋትና ብክነት ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፤እኔ በእስላም የተከበርኩ የታፈርኩ ኩሩና ደስተኛ ነኝ።

- ይህ ግን የርስዎ አመለካከት ብቻ ነው ወይስ የሁሉም ግብጻውያን አመለካከት ነው?

- (እናት በኻሊድ ትርጉም) ፦ ቢያንስ የኔ አመለካከት ነው። የሚያሳዝነው ግን ከኛም ዘንድ በናንተ ተጽእኖ ስር ወድቆቀው ሃይማኖትን ኋላ ቀርነት አድርጎ የሚመለከቱ አሉ።

ከዚያም ወደ ልጃቸው ወደ ሰሊም ተመለከቱ፣ራሱን አቀረቀረ . .

- ሴት ግን እስላም ውስጥ የተዋረደች ናት!

- (እናት በኻሊድ ትርጉም) ፦ ማነው እንዲህ ያለህ?! እኔ ዕድሜዬ ስልሳ አምስት ነው፣በዚህ ዕድሜም ልጄ ኻሊድ ሥራ የሚበዛበትና መምጣት የማይፈልግ ቢሆንም ትእዛዜን ተቀብሎ ከኔ ጋር እንዲመጣ ማስገደድ እችላለሁ። አርሱና ሴት ልጆቼም በየሳምንቱ ሦስትና አራት ጊዜ ይጠይቁኛል፣ስጦታዎች ያቀርቡልኛል፣እኔም ሆንኩ አባታቸው የሚያዛቸውን ነገር አንዲት ነገር መቃወም አይችሉም። እንዲህ ያለ አክብሮት አይተህ ታውቃለህ? አክብሮት ይህ ካልሆን አክብሮት ሚባል ነገር የለም ማለት ነው።

- እኔ አባትና እናቴን ከሦስት ወራት ወዲህ አላየኋቸውም።

ኻለድ የናቱን ምላሽ ከሰማ በኋላ ትንሽ እንደ መሸማቀቅ አለና ግልጽ የመሸማቀቅ ስሜት ወደሚስተዋልበት ሰሊም ተመለከተ . .

- ምንድነው ያሉት . . ?

- ላስከፋህ አልፈልግም . .

- ፈጽሞ አልከፋም፣ንገረኝ።

- ከናንተ እንደተማረውና ጸባያችሁን እንደወረሰው ሰሊም ነህ ትላለች።

- እዚህ እኛ አገር የሚገኙት ግን ብዙዎቹ ጠጭዎች፣ስነ ምግባር የጎደላቸውና ያልተገሩ ናቸው!

- (እናት በኻሊድ ትርጉም) ፦ አቅጣጫ ጠቋሚ ጠፍቶባቸው የሚባክኑ ሰዎች ሁሉም ቦታ ይገኛሉ፣አቅጣጫቸውን ሲያውቁ ግን ተጸጽተው ወደ ፈጣሪያቸው ይመለሳሉ።

ማይክልና ሳሊ ምሳቸውን ካበቁ በኋላ ከሰገነቱ ወርደው መጡ . .

- ባባ ከሃያ ደቂቃ በኋላ እመለሳለሁ ብለሀን ለአርባ አምስት ደቂቃ ጠበቅንህ፣ቃል በገባህልን መሰረት አንሄድም?

- ይቅርታ፣ልጆቻችሁን እንድትዘነጉ አደረግናችሁ።

- ኦህ፣ጊዜው መሄዱ ትዝ አላለኝም ነበር።

- ሰሊም፣ኻሊድ፣ዓእሻና ዐብዱላህ በጣም ነው የማመሰግነው . . ብዙ ጊዜ ተሸማናችሁ። ይህ የኔ ቢዝነስ ካርድ ነው የናንተን ልትሰጡኝ ትችላላችሁ?

- አባቴና እናቴ ምን ካርድ ይኖራቸዋል?! የኔ ይኸውና፣ኢሜይሌ አለበት፣ካትሪና ስለ መጽሐፉ ያለሽን አስተያየት ትልክልኛለሽ ብዬ ተስፋ ላድርግ?

- እሞክራለሁ፣አመሰግናለሁ።

ኻሊድ ከናቱና ከአባቱ ጋር ከሄደ በኋላ ሰሊም ይቅርታ ሊጠይቃቸው ወደ እንግዶቹ ፊቱን አዞረ . .

- እንዳልኳችሁ በዝምታ ነው የቆየሁት፣ለተሰማችሁ ማንኛውም ቅሬታ ይቅርታ እጠይቃለሁ። እኔ ግን ከመጀመሪያው ተናግሬ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፣እናንተ ናችሁ እምቢ ያላችሁ።

- በተናገሩት ነገር ብደናገጥም፣አቀራረባቸውም ትንሽ ጠንከር ያለ ቢሆንም ሁሉም ግን የተገራ አንደበት ያላቸው ጨዋዎች በመሆናቸው ምንም ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግህም . . እህህ፣ይልቅስ ለዓመታት ያልጎበኘሃቸውን ወላጆችህን ሄደህ ይቅርታ ጠይቅ።

ጃኖልካ ሁሉንም ተሰናብቶ ወደ ሥራው ሄደ። ጆርጅና ካትሪና ከሕጻናቱ ጋር ወደ ትሬቪ ፏፏቴ አመሩ . . በጣም ድንቅ የሆነ ፏፏቴ ነበር። በውብ እይታው በጣም ተማረኩ፤የዕለቱን ቀሪ ጊዜ በአካባቢው አሳለፉ . . ለቀው ከመሄዳቸው በፊት ካትሪና ሳንቲሞችን ወደ ፏፏቴው ወረወረችና ሳሊ ተገርማ ወደ እናቷ ተመለከተች . .

 

- በጣሊያኖች አፈተረት ሳንቲሞችን እዚህ የወረወረ ሰው ወደ ሮም ተመልሶ ይመጣል ይባላል።

- ባባ ሳንቲሞች ስጠኝ እኔም ልወረውር።

- የኔ ልጅ እውነት አይምሰልሽ፣ተረት ነው።

- አፈተረት መሆኑን አውቃለሁ፣ይሁንና ግን በትሬቪ ፏፏቴ ሳንቲም ወርወሬያለሁ ብዬ ለማውራት ብቻ ሳንቲም መወርወር እፈልጋለሁ።

- ይኸው ሳንቲሞች፣ ለራስሽና ለማይክልም ውሰጂለት። ካትሪና አንቺ ደግሞ አማኝ አፈተረተኛ እንዳትሆኚ ተስፋ አደርጋለሁ።

ካትሪናም ግልጽ በሆነ ምሬት መለሰች . .

- አንተም ውስብስብ ሰው እንዳትሆን ተስፋ አደርጋለሁ . . ነገሮችን አቅልላቸው፤ይህ ዝም ብሎ ሽርሽርና መዝናናት እንጂ ምንም አይደለም።

ከቄሱ ጋር (3)

- ካትሪና ምን ሆነሻል?

- ምንም።

- ፏፏቴውና በአካባቢው ያለው መናፈሻ አላስደሰተሽም?! . . ዛሬ እንደ ልማድሽ ስትስቂና ስትጫወቺ አላየሁሽም።

- በጣም ቆንጆ ነበር ግን አእምሮዬ ትንሽ ውጥረት ውስጥ ሳይሆን አልቀረም።

- በምን?

- ከተገናኘናቸው ዓይነት ሙስሊሞች ጋር መገናኘት የምትፈልገው ለምንድነው?

- አፈተረታቸውንና ኋላ ቀርነታቸውን አውቄ ቶም ስለ ሙስሊሞች ሲጠይቀኝ መልስ ላዘጋጅለት ነው።

- ግና ለንግገራቸው በጣም ጥሩ አዎንታዊ አቀባበል ነበረህ።

ማይክል ፈገግ ብሎ የካትሪናን ዓይኖች እየተመለከተ ፦

- እኔ ነበርኩ አዎንታዊ አቀባበል የነበረኝ?!

ካትሪና ማለት የፈለገውን ተረድታለች. .

- እኛ ለኢየሱስ ባለን ፍቅር ላይ ሊጨረት ይፈልጋል።

- በእርግጥም ኢየሱስንና እናቱን ከልብ የሚያፈቅሩ ይመስላሉ።

- ምንድነው የምትለው?!

- ልዩነቱ በኢየሱስ አምላክነት ላይ ነው። እነሱ ይህንን በእግዚአብሔር ማጋራት ባእድ አምልኮና ጣዖታዊነት አድርገው ነው የሚወስዱት።

- እኛ ግን የአምላክ አንድነትና አምልኮ አድርገን እንወስዳለን።

- እህህ፣መጽሐፉን ታነብዋለሽ?

- ማንበብ አልፈልግም።

- እህህ፣አነባለሁ ብለሽ ነው ቃል የገባሽለት፣አርሱ እንዳለሽ ሁሉ መጽሐፉን ለማንበብ ፍርሃት አለብሽ ማለት ነው?!

- ጆርጅ እንዴት እንዴት ነው ምትናገረው?! ምንም የማይጨምር ምንም የማይቀንስ መጽሐፍ ነው!

- ልክ ነሽ . . ታዲያ ለምን አታነቢውም? ምን ችግር አለው?

- ማንበብ ትፈልጋለች ያለህ ማነው?

- በማስረጃ አቀራረብና ከካቶሊካዊነት በመከላከል ረገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ደካማ ሆነሽ ነው ያገኘሁሽ፤ለመጀመሪያ ጊዜም በቀላል ንግግር ሰትፍረከረኪ ማየቴ ነው።

- መጽሐፉን አላነበውም።

- መጽሐፉን እንደምትፈሪው ለራስሽ እያረጋገጥሽ ነው ማለት ነው።

- እንግዲያውስ አነበዋለሁ።

- ካትሪና ምን ነካሽ? የምን ደካማነት ነው?!

- እኔ እንጃ፣ከቄሱ ጋር ከተገናኘንበት ጊዜ አንስቶ ውስጤ የተረጋጋ አይደለም፤እውነትም መጽሐፉን ማንበብ ፈርቼ ሳልሆን አልቀረሁም።

- አልፈራሽም፣ጠንካራ ነሽ፣አንቺ እርግጠኛ በመሆን ረገድ ለኔ ምሳሌ ነሽ። በጣም ትንሽ መጽሐፍ ነውና አሁኑኑ እንድታነቢ ነው የምጠይቅሽ፤ከትናንት ጀምሮ ስላላየሁ ኢሜይሌን አያለሁ።

ካትሪና ቁጭ ብላ መጽሐፉን ማንበብ ስትጀምር ጆርጅ በዓይኖቹ ካትሪናን እና በንባቡ ላይ ያላትን ተመስጦ እየተከታተለ ኢሜይሉን ከፈተ . . መልእክትና የብሉይ ኪዳን ጥቅስ ልኮላቸው ከነበሩት ሰዎች አስተያየታቸውን የሰጡባቸውን ምላሾች አገኘ . . ጠቅለል አድርጎ በማሳጠር እንደገና ለሁሉም ላከላቸው።

ቶምለበራድ ጭካኔ መነሻው ይህ ነው ማለትህ ነው?! ጥሩ አገላለጽ ይመስላል።

ሌቪበዚህ አረመኔያዊ ጭካኔ ላይ ያለኝን አቋም የምታውቀው ቢሆንም ሁላችሁም ግን ታምኑበታላችሁ፤ብሉይ ኪዳንን የሚተች ሁሉንም መለኮታዊ ሃይማኖቶች ይተቻል።

ሐቢብሙሉ በሙሉ እስማማበታለሁ፤ይሁን እንጂ የማልወዳቸውም ቢሆን ሙስሊሞች ግን በኦሪት ላይ ባላቸው እምነት ከሌሎች ይለያሉ።

አደምአደገኛ የሆነ አነጋገር ነው፤እንዲህ ያለው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ ሊሆን እንዴት ይችላል?

ቀጣዩን መልእክት ጻፈላቸው፦

‹‹ዛሬ ሃሳብ የምትሰጡት በጥቅስ ላይ ሳይሆን በእሳቤ ላይ ነው

በክርስትና ውስጥ ያለው የሥላሴ እምነት በእግዚአብሔር ሌላን ማሻረክ ነው፣ሊረዱት የሚያስቸግር ጽንሰ ሀሳብ ነው፤እግዚአብሔር አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ኢየሱስ የእግዚአብሔር አገልጋይና መልእክተኛው ነው። አጠር ያለ ምላሽና ሀሳባችሁን እጠብቃለሁ።

ጆርጅ››

ጆርጅ ኮምፒውተሩ ላይ የሚሰራውን አበቃ . . በጥልቅ ተመስጦ መጽሐፉን ማንበብ ወደ ቀጠለችው ካትሪና ፊቱን አዞረ . .

- ጨረስሽ?

- አልጨረስኩም፣ትንሽ ጠብቀኝ።

- በአንዳንድ ርእሶች ላይ ካንቺ ጋር ሀሳብ መለዋወጥ ስለምፈልግ መጽሐፉን ለነገ አቆይው።

- ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ፣ጨርሻለሁ።

- በመጽሐፉ በጣም የተመሰጥሽ ትመስያለሽ !

- መልካም ፈቃድህ ሆኖ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ።

- እንግዲያውስ እኔ እተኛለሁ።

ካትሪና መጽሐፉን አንብባ ጨረሰችውና አልጋው ላይ እንደተንጋለለ ወደ ጆርጅ ቀረብ አለች . .

- ይቅርታ ወደማገባደዱ አካባቢ ስለነበርኩ ልጨርሰው ብዬ ነው።

- አሳማኝ መጽሐፍ ይመስላል !

- በተወሰነ ደረጃ፣ማለፊያ ትረካ ነው።

- የነገው ሥራችንን ፈር ለማስያዝ ፈልጌ ነበር።

- ነገ ቅዳሜ ነው፤ቄሱ ነገ በቅዳሴ ሥርዓቱ ላይ እንድንገይ ጥሪ አድርጎልን የለም?

- አዎ ጠርቶናል፣ግን እንሄዳለን?

- አዎ እንሄዳለን፣ከሁሉም በላይ ቅዱስ በሆነ ቤተክርስቲያን የሚደረገውን ቅዳሴ እንተዋለን?

- እህህ፣እናም ለኢየሱስ ያለሽ ፍቅር ወደ ቤተክርስቲያን እንጂ ወደ እስላም አልመራሽም ማለት ነው።

- መጽሐፉ በከፍተኛ ደረጃ አሳማኝ ቢሆንም ነገ ግን በቤተክርስቲን ተገኝቼ እጸልያለሁ።

- ልጆቹን የትነው የምናቆያቸው?

- ከኛ ጋር ወደ ቅዳሴው እንወስዳቸዋለን።

- ቄሶቹን አትፈሪላቸውም?

- አልገባኝም።

- ልጆቼን ወደ ቅዳሴው ልወስዳቸው አልችልም፣ቀሳውስቱን እፈራላቸዋለሁ።

- ምናቸውን ነው የምትፈራው?

- በተደጋጋሚ ብሉይና አዲስ ኪዳንን በማንበባቸው ምክንያት የቀሳውስቱን አረመኔያዊ የጭካኔ ድርጊት እፈራላቸዋለሁ።

- ዛሬ የምትናገረው ሁሉ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል፣ማለት የፈለከውን ልታብራራልኝ ትችላለህ?

- ስለ አብያተ ክርስቲያናት ወሲባዊ ቅሌቶች አላነበብሽም? በታዳጊ ሕጻናት ቤተክርስቲያን ላይ ስለቀረቡት ክሶች አላነበብሽም? ሕጻናቱን አስገድደው ከደፈሩ ቀሳውስት መካከል ከአንደኛው ጋር የተደረገውን ቃለ መጠይቅ ሁሌም አልረሳም። ቀሳውስትና መነኮሳቱ አውሬዎች እንጂ ሰዎች ናቸው ብሎ ማመን ያስቸግራል፤እናም ማይክልና ሳሊ እንዲህ ላለው ነገር እንዲጋለጡ አልፈልግም።

- ጆርጅ ምን ነካህ? እኔ በየሳምንቱ ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ ቤተክርስቲን እሄዳለሁ፣እንዲህ ያለ ነገር ደርሶብኝ አያውቅም፣ይህ ሁሉ መረበሽ ለምን?

- ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያን ስለሚፈጸሙ ወሲባዊ ቅሌቶች ተወያይተሽ ወይም አንብበሽ ታውቂያለሽ?

- አላውቅም።

- እንግዲያውስ ወደ ዩቲዩብ ግቢና በዚህ ላይ የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን ተመልከቺና ነገ ልጆቹን ወደ ቅዳሴው መውሰድ አለብን ብለሽ ከጸናሽ እንወስዳቸዋለን።

- ላንተ ብዬ ቪዲዮዎቹን አሁን እመለከታቸዋለሁ፣ነገ ግን ሁላችንም ወደ ቤተክርስትያን ቅዳሴ እንሄዳለን . . ከኔ ጋርም የተገናኘነው ሙስሊም የሚጠቀመውን አነጋገር ስልት መጠቀም ጀምረሃል ማለት ነው!

- እህህ፣አነጋገሩ ተጽእኖ እንዳሳደረብሽ ሁሉ ቪዲዎቹም ተጽእኖ ያሳድሩብሻል፤የኔ ፍቅር ደህና እደሪ።

- ፍቅሬ አንተም ደህና እደር።

በረዥሙ ተቃቀፉ፣ጆርጅ ሲያንቀላፋ የቤተክርስቲያን ወሲባዊ ቅሌቶችን የሚመለከቱ ፊልሞችንና ጽሁፎችን ስትከታተል ቆየች፤ከዚያ ወሲባዊ ወዳልሆኑ የቤተክርስቲያን ቅሌቶች ተሸጋገረች፣ሳይታወቃት ረዥም ጊዜ አሳለፈች . . እንደገና ‹‹ለኢየሱስ ያለኝ ጥልቅ ፍቅር ወደ እስላም መራኝ›› ወደሚለው መጽሐፍ ተመለሰችና አንዱን የመጽሐፉን አንቀጽ በድጋሜ አነበበችው፤ይህን አንቀጽ ለምን እንደ መረጠች ግን አታውቅም

 
‹‹የቤዛነትና የስቅለት እምነት አእምሮንና ሎጂክን የሚጻረር ከመሆኑም ባሻገር፣መልካም ሥራን እርግፍ አድርጎ ለመተው፣ ኃጢአትና እንደ ግድያ፣ስርቆት፣አስገድዶ መድፈር፣ዝሙት ያሉና የመሳሰሉ እኩይ ተግባራትን ለመፈጸም በሩን ወለል አድርጎ የሚከፍት እምነት ነው። ኢየሱስ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ሊያሟሏቸው የመጡትንና ያስተማሯቸውን
የሕግን፣የትእዛዛትንና የመልካም ሥራዎችን አስፈላጊነት ጳውሎስ አጣጥሏል። በሮሜ ሰዎች መልእክቱ

(3፡28)

እንዲህ ብሏል፦
‹‹ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።›› አብርሃም (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) በሥራው አልጸደቁም

(4፡2)

። ጳውሎስ መዳን የሚገኘው በኢየሱስ መሰቀል በማመን ብቻ ነው የሚል ይዞ መጣ። የሰው ልጅ ጳውሎስን አምኖ ከተከተለው ፍጻሜው ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይከብዳል። ለጳውሎስ መልስ ከሚሆኑት መካከል ኢየሱስ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) የተናገሩትና ማቴዎስ

5፡19

ውስጥ የሰፈረው አንዱ ነው፦
‹‹እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤የሚያደርግ ግን ሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።››
አንቀጹን ደጋግማ አነበበች . . ምሽቱ ወደ ንጋት መቃረቡ ትዝ ሲላት መጽሐፉን ከጎኗ እንደተከፈተ አስቀምጣ አልጋው ላይ ተዘረጋች፤ ወደ ሀሳብ ዓለም እንደገባች እንቅልፍ ይዟት ጭልጥ አለ።
ጆርጅ አማልዶ ከእንቅልፉ ሲነቃ ካትሪና አላወቀችም። ተነስቶ ገላውን ታጠበና ልብሱን ቀየረ . . ልቀሰቅሳት ወደ ካትሪና ቀረብ ሲል ማታ ስታነበው የነበረውን መጽሐፍ ባቆመችበት ገጽ እንደተከፈተ በአቅራቢያዋ አገኘው . . አነበበውና መጽሐፉን እንደ ተከፈተ በነበረበት ሁኔታ ደፍቶ አስቀመጠው።
ወደ ልጆቹ ክፍል ሄዶ ተነስተው እንዲዘጋጁ ቀስሳቸው። በመቀጠል ወደ ካትሪና ተመልሶ ቀሰቀሳት . . ለቁርስ ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ሲያመሩ ጆርጅ ወደ ካቲሪና ዞረና . .

- የዛሬ ጉብኝታችን ወዴት ነው?

- ከቦታዎች ሁሉ እጅግ ውብና እጅግ ምርጥ ወደ ሆነው ቦታ ነው።

- ማማ ዛሬ ወዴት ነው የምንሄደው? ባባን ስጠይቅ የምንሄድበትን የምትመርጭው አንቺ ነሽ ብሏል።

- ከአፍታ በኋላ ከአባታችሁ ጋር አስደሳች ነገር እንነግራችኋለን።

ካትሪና ከጆርጅ ጋር ትንሽ ለመነጋገር ስለፈለገች ልጆቹ ቀድመው ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው . .

- ዛሬ ወዴትነው የምንሄደው?

- የቤተክርስቲያን ወሲባዊ ቅሌቶችን የሚመለከቱን አየሽ? አነበብሻቸው?

- ሁሌም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመሆኔ ጋር ያየሁትና ያነበብኩት ነገር ማሰብ ከምችለው በላይ ነው የሆነብኝ። ይህ እውነት ከሆነ እነዚህ ሰዎች ሳይሆኑ አራዊት ናቸው።

- ይህ የሚሆነው እምነትን ከመልካም ሥራ በሚነጥሉ የጳውሎስ ትምህርቶች ምክንያት ነው፣ክርስትና የቤዛነትንና የመድህንን እምነት የፈጠረው ለዚህ ነው ብለሽ ታምኚያለሽ?

- መጽሐፉን አንብበሃል እንዴ?

- ተከፍቶ የነበረውን ገጽ ብቻ እንጂ አላነበብኩም፤ባነበው ችግሩ ምንድን ነው?

- ችግር የለውም . . ስለገረመኝ ብቻ ነው። ብታነበው ጥሩ ነበር። እኔ አልፈራሁም፤ምናልባት ያነበብከው አንቀጽ በተለይ ለኔ ችግር ሊፈጥርብኝ ይችል ይሆናል፣ለሁሉም ወደፊት እንነጋገርበታለን። ዋናው ነገር ዛሬ ወዴት ነው የምንሄደው? ምን አሰብሽ?

- በቤተከርስቲያኑ ቅዳሴ ላይ የግድ መገኘት ይኖርብናል።

- ችግር የለውም፣ግና መጀመሪያ ወደ ቪላ ዶሪያ ባምቢሌ መናፈሻ ከሄድን በኋ ነው፤ከሮም መናፈሻዎች ትልቁ ብቻ ሳይሆን በውበትም ከዋነኞቹ አንዱ ነው።

- ከቅዳሴው እንዳንዘገይ እሰጋለሁ።

- እህህ፣መነኮሲቷ አንዘገይም።

- እንግዲያውስ ተስማምተናል።

ከቄሱ ጋር (4)

ቪላ ዶሪያ ባምቢሌ መናፈሻ ወደ ዘጠኝ ካሬ ኪሎ ሜትር በሚጠጋ ቦታ ላይ የተንጣለለ . . ውብና እጅግ የሚያስደስት ሰፊ አረንጓዴ ትእይንት ያለው . .
ማይክልና ሳሊ አይተው የረኩባቸው ብዙ ዓይነት አእዋፍ ያሉበት ማራኪ መነፈሻ ነው . .

- ማማ ምርጫሽ እጹብ ድንቅ ነው፤የዛሬው ቀን ከቀናት ሁሉ ድንቅ ቀን ነው።

- ቦታው በጣም ውብና እጅግ ማራኪ ነው፣ሳሊ አስደስቶሻል?

- አዎ በጣም ነው ያስደሰተኝ።

- የጉብኝታችን ውበት ዛሬ ለቅዳሴ ወደ ቤተክርስቲያኑ ስንሄድ ደግሞ ይበልጥ የተሟላ ይሆናል።

ማይክል ተነጫነጨና፦

- እኔ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ አልፈልግም።

ጆርጅ ትከሻውን ነቅንቆ ወደ ካትሪና አየና . .

- ይህ የእናትህ ምርጫ ስለሆነ እርሷን ጠይቃት።

- ከመደበኛው የቱሪስት ጉብኝት በኋላ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጉብኝት የግድ አስፈላጊ ነው።

- ማማ ይቅርታ፣እኔ ቤተክርስቲያን አልወድም !

- የፈጠረህን፣የመገበህንና የባረከህን አምላክህን ማምለክና ማመስገን አትወድም?

- አምላኬን ማምለክ እወዳለሁ፣ግን ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ሳይኖርብኝ ነው።

- አንድ ሰው አምላኩን በማምለክና በማመስገን ወደርሱ ፊቱን ካልመለሰ ዓለም ትጠበዋለች።

- አንቺ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ቆርጠሻል?

ጆርጅ ክርክሩን ማለዘብ ወደደ . .

- ፈጣሪህን ባታመልከውና ባታመሰግነው መታደልን አታገኝም፤አምልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ ጋር የተሳሰረ ነው የሚል ግምት የለኝም።

- የዚህን ውብ መነፈሻ ጉብኝት ከጨረስን በኋላ እንሄዳለን፣ጎብኝተህ ተዝናናበት፣የኔ ቆንጆ የፈጣሪህን አምልኮና ምስጋናውን ከመተው ግን ተጠንቀቅ።

- ማማ አመሰግናለሁ፤ባባ አመሰግናለሁ፤ነገር ግን አምልኮ ከቤተክርስቲያን ጋር ብቻ የተሳሰረው ለምንድነው?!

ካትሪና ክርክሩን መቋጨት ፈለገች . .

- ሳሊ ነይማ ያችን እዚያ ዛፍ ላይ ያለችውን ወፍ አየሻት? . . ኑ ወደዚያ እንሂድ . .

ማይክልና ሳሊ ወፍዋን ተከትለው ሮጡ . .

- የማይክል አነጋገር በጣም ጥሩ ነው።

- አዎ፣ግን ሕጻናቱ ለማይወዱት ነገር እኔን ምክንያት ለምን ታደርጋለህ?

- ወደ ቅዳሴው መሄድ ያንቺ ጥያቄ አይደለም?!

- አንተ ንጹሁ ፈላስፋ ንግግራችን አላበቃም ወደፊት ይቀጥላል።

ቤተሰቡ የጧቱን ጊዜ በመናፈሻው ውስጥ አሳልፈው ምሳቸውንም እዚያው በሉ . . ካበቁ በኋላ ካትሪና ወደ ልጆቿ ዞር አለችና፦

- አሁን ወደ ቅዳሴው እንሄዳለን፤በተመስጦ እንድትጸልዩና ራሳችሁን እንድትጠብቁ ይሁን።

- ከምንድነው ራሳችንን የምንጠብቀው?

- ከሚየውካችሁ ወይም ከሚያስቸግራችሁ ማንኛውም ነገር ወይም ማንኛውም ሰው።

- ምንን ከመሳሰለው?

- ከሚያውካችሁ ወይም ከሚያስቸግራችሁ ማንኛውም ነገር፤ማይክልና ሳሊ ያልኩት ግልጽ ነው?!

- ግልጽ ነው፣ ለምን እንደዚህ እንዳልሽን ግን አላውቅም?! ወደ ቤተክርስቲያን ነው ወይስ አጥቂ አራዊት ወዳሉበት መናፈሻ ነው የምንሄደው?!

ወደ ቤተክርስቲያኑ እንደተቃረቡ ካትሪና ወደ ጆርጅ ዘንበል ብላ በጆሮው አንሾካሾከች . .

- ተጠራጣሪ እንድሆን አደርገሀኛል፣ለማይክል ጥንቃቄ አድርግ እኔ ለሳሊ እጠነቀቃለሁ።

- እስከዚህ ደረጃም አይደለም፤በጣም የተወሰወስሽ ትመስያለሽ . . ለማንኛውም እሽ አደርጋለሁ።

ሁሉም ወደ ቤተክርስቲያኑ ገቡ፤አስፈሪው ቅዳሴ ተጀምሯል . . ጆርጅ ግን ግድ አልነበረውም፤ካትሪና በቅዳሴው ልቧ የተነካ ቢሆንም ጭንቀትና ደስተኛ ያለመሆን ስሜት ከፊቷ ይነበባል . .
እንደወጡ ማይክል በእናቱ ተንጠለጠለና . .

- ማማ አመሰግናለሁ፣ድንቅ የሆነ ቅዳሴ ነበር፤ኢየሱስን በጣም እወዳለሁ!

- ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ልጅ ከኃጢአት መዳን ምክንያቱ እርሱ ነው።

በሕጻን ንጽሕናና የዋህነት ሳሊ ጠየቀች . .

- ማማ . . ቸሩ አምላክ እኛን ከኃጢአቶቻችን ለማዳን ኢየሱስን ከመግደል ውጭ ሌላ መንገድ አልነበረውም እንዴ? በጣም ስለምወደው የኢየሱስ ወልድ ሞት በጣም ያሳቅቀኛል፤በርሱ ምክንያት በየዓመቱ የገና ስጦታዎች ይመጡልኛል።

ማይክል አከለ . .

- ሳሊ እኔም እንዳንቺ ነኝ . . ምናልባት ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ የማልወደው በዚህ ወይም ቀሳውስትና መነኮሳቱን ስለማልወዳቸው ሊሆን ይችላል።

- ለኢየሱስ ያለህ ፍቅርህ ነው የሚያድንህና ነጻ የሚያወጣህ።

- ማይክል መልካም መሥራትን አትርሳ፤ኢየሱስ ባስተማረን መሰረት ማመን ብቻ በቂ አይደለምና።

የቅዳሴ ሥርዓቱ ካበቃ በኋላ ቤተሰቡ ወደ ሆቴሉ ተመለሰ፤ልጆቹ ወደ ክፍላቸው አመሩ . . በዚህ ጊዜ ጆርጅ መሰሪ ፈገግታ እያሳያት ለካትሪና እንዲህ አለ፦

- ቤተክርስቲያን ውስጥ ውጥረት ይታይብሽ ነበር።

- አንተ ደግሞ ግድ የለሽነት በግልጽ ይስተዋልብህ ነበር።

- ልክ ነሽ፣አሳማኝ ሆኖ ባልታየኝ ነገር ግድ እንዲኖረኝ እንዴት ትጠብቂያለሽ? ዋናው ነገር የመልስ ጉዟችን ተነገወዲያ ነው፤ቀሪውን የጉብኝት ጊዜ ባለፈው እንዳደረግነው ሁሉ አስደሳች ሆኖ ማሳለፍ ይኖርብናል።

- እኔ በጣም ደክሞኛል፤ትናንት በጣም ዘግይቼ ነበር የተኛሁት፤እናም አሁን እተኛለሁ።

- እኔም ኢሜይሌን አይቼ እተኛለሁ። ሙስሊሙ ሰውየ የሰጠሸን መጽሐፍ ልትሰጭኝ ትችያለሽ?

- ልታነበው ነው?!

- ምናልባት፣ባነበው ምን ችግር አለው?

- ምንም፣እንካ . . ደህና እደር።

ጆርጅ ኮምፒውተሩን ከፍቶ ለላከላቸው መልእክት ባልደረቦቹ የላኩትን ምላሽ ለማየት ወደ ኢሜይሉ ገባ፦

ሐቢብየዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቼን የአምላክን ሦስትነት ከአንድነቱ ጋር (ሥላሴን) ለማስረዳት ብዙ ደክሜ ሳይሰካልኝ ቀርቷል፤ምናልባት እኔ ራሴ ስላልተረዳሁት ሊሆን ይችላል። የጠቀስከው በአጠቃላይ በጣም ጥንታዊ በሆኑ ወንጌሎች ውስጥ ይገኛል።

ቶምማቴማቲክስ 3 ≠ 1 ይለናል። የሎጂክ ምሁራን ‹‹ያንድ ነገር ተከፋይ ክፍል በብያኔው የዋነኛው ክፍል ተከታይ ነው›› ይላሉ። አባቴ ‹‹ያልገባህን ነገር አትናገር›› ይል ነበር። እኔ ደግሞ ‹‹መልስ እንድሰጥህ ልረዳው የምችለውን ነገር ብቻ ንገረኝ›› ባይ ነኝ፣እህህ።

አደምኢየሱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንጂ የእግዚአብሔር ሸሪክ ወይም ልጅ አይደለም ብንል ይህ ፈጽሞ የኢየሱስን ክብር ማሳነስ ማለት አይደለም።

ሌቪይህ እኛ ዘንድ በአይሁዳዊነት ውስጥ ‹‹ዕዝራ የእግዚአብሔር ልጅ ነው›› እንደሚባለው ዓይነት ነው። ሁለቱም መረዳት የማይቻል አነጋገር ነው የሚል እምነት አለኝ።

የተሰጡትን ሀሳቦች ስሞችን ሳይጠቅስ መልሶ ለሁሉም ላከላቸው። ከዚያም የሚከተለውን መልእክት ጻፈ፦

‹‹ሦስተኛው ዙርአዲስ ኪዳንን ያዛበውና የበረዘው ጳውሎስ ሊሆን ይችላል?

ጆርጅ››

ቀሪዎቹን መልእክቶች በማየት ላይ እያለ የሚከተለውን ከካኽ የተላከ መልእክት አገኘ፦

‹‹ውድ ወዳጄ ጆርጅ . . በመልካም ጤንነት ላይ እንደምትሆን ተስፋዬ የጸና ነው። ሁሉም ሠራተኞች እየጠበቁህ ነው፤በቅርቡ እንደምንገናኝ ተስፋችን ነው።››

ካኽ››

* ማስታወሻ እስካሁን ድረስ ከአንድ ሳምንት በላይ ከሥራ ቀርተሃል።››

ኮምፒውተሩን ለመዝጋት ሲያስብ የአደም የፌስቡክ ገጽ ትዝ አለው፤ሳይጎበኘው ረዥም ጊዜ ሆኖታል፤ወደ ገጹ ሄደና ስለሱ የተጻፈ አዲስ መጣጥፍ አገኘ፦
‹‹መታደልን በመፈለግ ላይ ከተሰማራው ወዳጄ የሚቀሰሙ ትምህርቶች

3››፦

‹‹መታደልን በመፈለግ ላይ የተሰማራው ወዳጄን በዚህ ሰሞን እንግዳ የሆነ የጤና ችግር ገጥሞታል። ከርሱ የተማርኩትን ከማውሳቴ በፊት በሕመሙ ወቅት በተከሰተው ነገር ላይ ጥቂት ነጥቦችን ላስፍር

1. በሽታ እንደ ተለመደው ድካም ማስከተሉ የታወቀ ነው፣ወዳጄንም ይኸው አጋጥሞታል። የመታደል መንገድ ፍለጋውን ከፍጻሜ አያደርስም የሚል ስጋት አድሮብኝ ነበር፤እርግጠኝነቱና ቁርጠኝነቱ ግን ስጋቱን በሰላም እንዲያልፍ አድርጎታል። በመሆኑም አስተዋይ ሰው ወሳኝ ትላልቅ ውሳኔዎችን በድክመት ሁኔታ ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት መወሰን አይገባውም።

2. በአንድ ወቅት ላይ ድክመቱን ሳስተውል ሂደቱን ተራምጄ የመታደል መንገድ ይኸኛው ነው ብዬ ልነግረው ምንም ያህል አልቀረኝም ነበር . . ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አትርፎኛል።

3. መጪው ወቅት ለወዳጄ ከሁሉም ይበልጥ በጣም አስቸጋሪው ወቅት እንደሚሆንበት እርግጠኛ ሆኛለሁ፣ውጤቱን ተከታታዬ አሳውቃችሁ ይሆናል።

ወደ ትምህርቱ ስንመለስ ወዳጄ የመታደልን መንገድ ፈልጎ ለማወቅ አሁንም ጽናትና ቁርጠኝነቱን እንደሰነቀ ነው። የሚከተሉትን ትምህርቶች ከርሱ መገብየት ችያለሁ

1. በዙሪያህ የሚገኙ ሰዎች ወይ ተጽእኖ ታሳድርባቸዋለህ ወይ ባንተ ላይ ተጽእኖ ያሳደራሉ፣ወይም ደግሞ ትታገላቸዋለህ። ይህን የሚወስነው የእሳቤና የእምነት ትግሉ ነው። በወዳጄ ዙሪያ የሚገኙ ሰዎቹ ብዙዎቹ በርሱ ተጽእኖ ስር መዋል ጀምረዋል። ይህም የጽናቱንና የቁርጠኝነቱን ብርታት የሚያመለክት ነው። በጥቅሉ ሲታይ አሁን ካንድ በላይ የሆኑ በመታደል መንገድ ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ሰዎች እንዳሉ ነው የምገምተው። ማን ያውቃል በቅርቡ ሁሉም የመታደልን መንገድ ለማወቅ መቻላቸውን ላበስራችሁ እችል ይሆናል።

2. በመታደል መንገድ ፍለጋ ጉዞ ላይ ለሁሉም አመለካከቶች ሚዘናዊ መሆንና ከስሜታዊነት መራቅ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፤አንዳንድ ጊዜ በጫናዎች ውስጥ ሲሆን የሚያጣው ቢሆንም ወዳጄ ይህን ሚዘናዊነት ታጥቋል።

3. የመማር አስፈላጊነት፤የምታውቀው ምናልባት ትክክል ላይሆን ስለሚችል፣ አውቃለሁ ብለህ የምታስበውን እንኳ ቢሆን መማር አስፈላጊ ነው። በወዳጄ ላይ አድናቆቴን የሳበው ከልጅነቱ ጀምሮ ያደገባቸውን ነገሮች እንኳ በክፍት አእምሮ ለመማር የሚያሳየው ቁርጠኝነት ነው።

4. የሚያሳዝነው ወዳጄ ሁነቶችን ንባቦቹንና ውይይቶችን እርስበርስ የማስተሳሰርና የማቀናጀት ችሎታው ውስን መሆኑ ነው። ይህ የተለያዩ እሳቤዎችንና አመለካከቶችን አነጻጽሮ የማየት ብቃት ወደ መታደል መንገድ ለመድረስ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

ወዳጄ የመታደልን መንገድ ለማወቅና ለታላላቆቹ የሕይወት ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በሚያደርገው ፍለጋ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል የሚል እምነት አለኝ። ለማንኛውም ቀጣዩን ትምህርት በቅርቡ ይዤላችሁ እመለሳለሁ።

አደም››

ጆርጅ ከፌስቡክ አንባቢዎች የተሰጡትን አስተየቶች አነበበ፤ያንደኛው አስተያት ትኩረቱን ሳበው፦
‹‹ወዳጅህን በጣም የምትወደው
ትመስላለህ፤ለዚህ ነው
አርአያ
አድርገህ የምታቀርበው።›› የአደም መልስ እንዲህ የሚል ነበር፦
‹‹አዎ ለሰዎች ሁሉ በጎውን እንደምመኝ ለርሱም እመኝለታለሁ፤እግዚአብሕር ለሰው በጎውን እንድንወድላቸው ያዘናል።››
በመቀጠል ስለ አመለካከት ለውጥና ሽግግር በአደም የተጻፈ ሌላ መጣጥፍ አነበበ። የሚከተለው ነበር፦

‹‹አንድን እሳቤና አመለካከት ትቶ ወደ ሌላ መሸጋገር አስቸጋሪ ነገር ቢሆንም ዛሬ ያጋጠመኝ ግን እንግዳ የሆነ ተሞክሮ ነው። ዛሬ በጣም ብልህና ብሩህ አእምሮ ያለው ፈላስፋ ከሆነ የስነ ልቦና ሐኪም ጋር ተገናኘሁ። ይሁን እንጂ በተለያዩ እምነቶችና እሳቤዎች መካከል ሲዘዋወርና ካንዱ ወደ ሌላው ሲሸጋገር ነው የኖረው። ክርስቲያን ነበር ወደ ኤቲስትነት ተለወጠ፤በስነምግባሩ የወረደ ኢአማኝ ሆነ። ቡድሂዝምን፣ሂንዱይዝምን፣አይሁዳዊነትንና ክርስትናንም አጥንቷል። አሁን እስላምን ለማጥናት ይፈልጋል። ሁለት ችግሮች ያሉበት ሲሆን አንደኛው ፍልስፍናን በሁሉም ነገር ላይ ፈራጅና መለኪያ አድርጎ ይወስዳል፤ፈራጅና መመዘኛው ዕውቀት እንጂ ያንተ ዘመናዊ የፍልስፍና መርህ አይደለም ስለው በአነጋገሬ እንደገና እንደሚያስብበት ቃል ቢገባም አምኖ መቀበል ግን አልቻለም። ሁለተኛ ችግሩእያንዳንዱን ሃይማኖት የሚመለከተው ከኤቲስትነቱና ስለአጠናቸው ሃይማኖቶች የመዛባትና የመምታታት ሁኔታ ያለው ጥልቅ ዕውቀቱ ካሳደረበት የሁሉም ሃይማኖቶች ጥላቻው መጥፎ ስሜት በመነሳት መሆኑ ነው። ከርሱ ጋር በሚኖረኝ ግንኙነት ምን ትመክሩኛላችሁ?

አደም››

የተባለው ሐኪም ቶም መሆኑን ጆርጅ አውቋል። የቶምን የፌስቡክ ገጽ ሲከፍት ግን ምንም አዲስ ነገር አላገኝም፤ይልቁንም ከአምስት ቀናት ወዲህ ቶም ገጹን ከፍቶ አያውቅም፣ይህ ደግሞ ልማዱ አልነበረም . . ኮምፒውተሩን ዘጋና መጽሐፉን አነሳ። እንቅልፍ ስለመጣበት ቶሎ ቶሎ አየት አየት አደረገ።
አንደኛው ገጽ ላይ ዓኑይ ያረፈበት ጽሑፍ ትኩረቱን ሳበውና በተመስጦ አነበበው። ጽሑፉ የተለመደ ዓይነት ቢሆንም አርሱን ለምን እንዳስደነገጠው ግን አላወቀም። በአምልኮ፣መድህን በማግኘትና በሕይወት መካከል ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ንጥጥሎሽ ባለበት ክርስትና ውስጥ እንዲህ ያለውን የማያውቀው በመሆኑ ይሆን? ወይስ ተናጋሪው ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ይሆን?
‹‹አሜሪካዊው ጸሐፊ ማይክል ኸርት በመጽሐፉ የታላላቆች ዝርዘር ውስጥ በቁጥር አንድ ላይ ካስቀመጣቸው በኋላ እንዲህ ይላል፦
መሐመድ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) በታሪክ ውስጥ በሁለቱም በሃይማኖታዊውና በዓለማዊውም መስኮች ጎልተው የወጡና በላቀ ደረጃ ስኬታማ የሆኑ ብቸኛው ሰው ነበሩ . . ይህ በዓይነቱ ልዩና አቻ የማይገኝለት ውህደትና ጥምረት ሙሐመድን በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ከማንም በላይ ኃያል ተጽእኖ የሚፈጥር ታላቁ ሰብእና እንዲሆኖ ያስችላቸዋል።››
ጆርጅ በጀርባው ተኝቶ ለሀሳብ ዓለም እጁን ሰጠ፤ራሱን ያወቀው ጧት ካትሪና እንዲህ ስትለው ብቻ ነበር፦

- ተነስ ንቃ፣እህህ፣ይህ ሁሉ በመጽሐፉ ጦስ ነው።

- ኦህ . . የፈራሽልኝ ትመስያለሽ፣አይዞሽ ተረጋጊ መጽሐፉን ገና አላነበብኩትም።

- እህህ፣ ይህ ሁሉ መጽሐፉን ሳታነበው ከሆነ አንብበህ ቢሆን ኖሮ ምን ትሆን ነበር! በል ንቃ።

ከቄሱ ጋር (5)

- በሉ ፈጠን በሉ . . ዛሬ ሮም ውስጥ የመጨረሻ ቀናችን ነውና በተቻለ መተን ብዙ ቦታዎችን መጎብኘት አለብን።

በሁነቶች የተሞላ ግሩም ቀን ነበር . . ቤተሰቡ መናፈሸዎችንና መዝናኛ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል። በሰው ሰራሽ ሐይቅ ላይ በጀልባ ተጉዘዋል . . ጉብኝታቸውን ያገባደዱት ወደ ገበያ ማዕከል በመሄድ ነበር . . ከገበያው ሲወጡ ጆርጅ ካትሪናን ድንገት ነካ አደረጋትና መልእክት ያለው ፈገግታ አሳያት፦

- መስቀል ሳትገዢ ቀረሽሳ ! ኢየሱስን መውደድ ተውሽ?

- እንዳውም ፍቅሬ ጨምሯል፣ፍቅር ግን ትእዛዛትን በመፈጸምና መልካም በመሥራት እንጂ በመስቀል ብቻ አይደለም።

- እኔም ከረዥም ጊዜ አንስቶ ስነግርሽ የቆየሁት ይህንኑ ነው። ፍቅር በመስቀል፣በሥዕልና በቅርጻ ቅርጽ፣በመነኮሳትም ሆነ በቀሳውስት አይደለም።

- አንተ አክራሪ ፕሮቴስታንት አሁን ይህን ተወን።

- መጽሐፉን ገና ያላነበብኩት ቢሆንም ማን ያውቃል ለኢየሱስ ያለኝ ጥልቅ ፍቅር አሸባሪ ሙስሊም ያደርገኝ ይሆናል።

- አሸባሪ ለመሆንም ሆነ ላም የሚያመልክ ህንዱ ለመሆን ብቁ ትመስለኛለህ።

- እህህ።

አመሻሹ ላይ ቤተሰቡ ቴቭራ ወንዝ ዳርቻ ወደሚገኝ ዝነኛ ሬስቶራንት አመሩ . . ማራኪውን የከተማይቱን ገጽታ እየተመለከቱ አሰደሳችና አነቃቂ በሆነ አየር ውስጥ እራታቸውን በሉ . .

- ስለ ሃማኖት ስታወሩ ብዙ ጊዜ እሰማችኋለሁ፣ሃይማኖት ለሰው አስፈላጊ ነገር ነው?

- አዎ ማይክል፣ ያለ ጥርጥር አስፈላጊ ነው።

- አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ግን ፦ ቀዳሚው መሰረት ኤቲዝም ነው፣እኛን የፈጠረን ተፈጥሮ ነው፤ሃይማኖታዊ እሳቤና ስለ ሃይማኖት ማሰብም ያረጀ ያፈጀ አፈተረት ነው፣ይላል።

- ያንተ ሀሳብስ?

- በሃይማኖት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ነገሮች አፈተረት ናቸው ብዬ አስባለሁ።

- ሃይማኖት ራሱ አፈተረት በመሆንና በአንዳንድ ሃይማኖቶች ውስጥ አፈተረት በመኖር መካከል ልዩነት አለ።

- ጓደኛዬ እንደሚለው ግን በሃይማኖት ውስጥ ያሉት አፈተረታዊ ጉዳዮች ብዙ ናቸው።

- ማሙሽዬ ምን የመሳሰሉ ናቸው?!

- የትምህርት ቤት መምህሬ ብዙ ጊዜ ቢያብራራውም፣የሥላሴን እምነት ምንነት፣የኢየሱስን ቤዛነትም . . መረዳት አልቻልኩም።

- ምናልባት ዕድሜህ ትንሽ ስለሆነ ይሆናል፣ትልቅ በምትሆንበት ጊዜ ትረዳቸዋለህ።

- የነገርኩሽ ጓደኛዬ፣‹‹የምትጠይቀው ሰው ሁሉ አንተ ገና ትንሽ ልጅ ነህ ይለሃል፣ግን እመነኝ ሁሉም ለራሳቸው አይረዱትም›› ነበር ያለኝ፤አንቺ እነዚህን ነገሮች ትረጂያለሽ?!

- አዎ፣በተወሰነ ደረጃ።

- ባባ አንተሳ?

- እህህ፣አይገባኝም፣በተወሰነ ደረጃ አልረዳም።

- ነገሩ አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፤አምላክ እንድንረዳው እኛን ማድከም ይፈልጋል እንዴ?

ካትሪና ተቆጣች . .

- ኡፍ፣አንተ ደግሞ እንደ አባትህ ነገሮችን ታካብዳለህ፤ማሙሽዬ ነገሩ ከዚህ በጣም የቀለለ ነው።

ጆርጅ በቁርጠኝነት መንፈስ አከለ . .

- ግሩም ነው ማይክል፣እግዚአብሔር የሰው ልጅ አእምሮ መረዳት የሚሳነውን ነገር አያስተላልፍም። እንደዚህ መስሎ የታየህ ነገር ካለ ለመረዳት የበለጠ መማር ያስፈልገሃል ማለት ነው። ከዚህ ውጭ ነገሮች ወደማይታወቁ ሚስጥሮች ይለወጣሉ የሚለውን አትቀበል።

- እናም ባባ አንተ ከኤቲስቱ ጓደኛዬ ጋር ትስማማለህ ማለት ነው?

- ፈጽሞ አልስማማም፤ኤቲዝም ከአእምሮ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጋጭ አፈተረት ነው።

- ባባ አልገባኝም።

- ዓለም በአጋጣሚ የተፈጠረ፣ሰዎችም በአጋጣሚ የተፈጠሩ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ?!

- ባባ ኤቲስቶች እንደዚያ አይሉም፣አንዳንዶቹ በባዮሎጂ ትምህርት ስለተማርነው የዳርዊን ንድፈሀሳብ በሳይንሳዊ መንገድ ያወራሉ።

- ልክ ነው፣የዳርዊን ንድፈሀሳብ ጊዜ ያለፈበት ንድፈሀሳብ ነው፤በአሁኑ ዘመን ግን ስህተተኛነቱ በሳይንስና በምክንያትም ተረጋግጧል።

- እንዴት?

- የሳይንስ መምህርህን መጠየቅ ትችላለህ፤ከኔ በተሻለ ሁኔታ ዝርዝሩን ያውቃል፤ወይም ይህንን በዝርዝር የሚያስረዳ መጽሐፍ ልገዛልህ እችላለሁ። መመርኮዝ ያለብን ሳይንሳዊ መስለው ቢታዩ እንኳ በአፈተረቶች ላይ ሳይሆን በሳይንስና በዕውቀት ላይ መሆን ይኖርበታል።

- ችግሩ ግን ሃይማኖት ከሳይንስ ጋር የሚጋጭ መሆኑ ነው።

- ሊሆን አይችልም፤አንደኛው ከሌላው ፈጽሞ መብቃቃት አይችልም።

- እንዴት?

- ይህን በአይንስታይን አባባል ላጠቃልልህ እችላለሁ፦ ‹‹ሳይንስ ያለ ሃይማኖት አንካሳ ነው፤ሃይማኖምት ያለ ሳይንስ እውር ነው›› ይላል።

- ኤቲስቶች ዕውቀታቸው አንካሳ ነው ማለትህ ነው?!

- እንዳውም ማይምነታቸው ከዕውቀታቸው የበዛ ነው። ሃይማኖት ያለ ሳይንስ ወደ አፈተረትና ወደ ምስጢሮች ሊለወጥ ስለሚችል የእውር መደናበር ነው . .

ማይክል ዝም ሲል ጆርጅ ከልጁ ዕድሜ በላይ የገዘፉ የሚመስሉትን እነዚህን ጥያቄዎች ሲያሰላስል ቆየ . . የአእምሮውን ብሩህነት የሚያመለክት ይሆን ወይስ የጥርጣሬ በሽታ ትንሹ ሥዕል?
ቤተሰቡ ወደ ሆቴሉ ሲመለስ ጃኖልካ እንግዳ መቀበያ ውስጥ እየጠበቃቸው ነበር፤ገና ሲያያቸው ተነስቶ ሰላምታ አቀረበላቸው . .

- ድንገተኛ ጉብኝት፣እንኳን ደህና መጣህ።

- የቄሱ ወዳጅ እንደምነህ፣ቅዳሴው ላይ አላየንህም!

- ቅዳሴ ላይ መገኘት ከተውኩ ዓመት ሊሆነኝ ነው።

- ታዲያ የቄሱን ወዳጅነት እንዴት መጠበቅ ትችላለህ?!

- ጥያቄዎችህን መመለስ ቢያቅተውም ቄሱ አንተ ዘንድ በጣም የተባረከ ሰው ይመስላል፤የሆነውን ነገር ከርሱ ማረጋገጥ ችያለሁ።

ጆርጅ በአንክሮ

- ትዋሸኝ ነበር?

- በፍጹም፣ለማረጋገጥ ብዬ ነው፤የዚያ ቀን አድራጎቱ ለኔ በጣም እንግዳ ነገር ነበር፤ነገሩ አንተ እንዳልከው ነው፤ቄሱ ካትሪናን ብቻ ማስወጣት አልፈለገም ነበር።

ካትሪና በመገረም አፈጠጠች . .

- በተለይ እኔን ለምን?!

- ሰውየው አንቺ አንዱ ተጠቃሚ የሆንሽውንና ለተራው ሕዝብ በይፋ የበሚናገረውና በዝግ በር ከምሁራን ጋር በሚናገረው መካከል ልዩነት ያደርጋል ብየሽ ለም? . . ለማንኛውም አላራዝምባችሁም፤ነገ ነው መሰለኝ የምትሄዱት?

- አዎ ነገ ነው።

- ልሰናበታችሁ ነው የመጣሁት፤ግንኙነታችን እንዲቀጥል እሻለሁ፣ከናንተ ጋር በመገናኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል።

- እኛም እንዲሁ ደስተኞች ነን . . እናመሰግናለን።

- ትንሽ ጥያቄ አለኝ፣መጽሐፉን ልትሰጭኝ ትችያለሽ? ወዳጄን ጠይቄው የቀረው የመጨረሻ ኮፒ ላንቺ የሰጠው መሆኑን ነገረኝ።

- መጽሐፉ እስከዚህ ድረስ አንተ ዘንድ አስፈላጊነት አለው ማለት ነው?!

- የዚያ ቀን ውይይታችሁ ስለ እስላም ከተራ ነገር ወይም ከዜና ዘገባዎች ባለፈ ውሃ የሚቋጥር ምንም ዕውቀት እንደሌለኝ አረጋግጦልኛል። ስለሆነም ይህን ሃይማኖት ለማወቅ ወስኛለሁ፤የመጽሐፉ ርእስም ስለሳበኝ ማንበብ ፈለግሁ።

- ከልጆቹ ጋር ወደ ክፍላችን ልውጣና መጽሐፉን ይዤልህ እመለሳለሁ . . ማይክል፣ሳሊ በሉ ኑ።

ጆርጅ ሳቅ እያለ . .

- እህህ፣እናም እስላምን ለማጥናት ወስንሃል ማለት ነው?

- አዎ ወስኛለሁ።

- ሙስሊም ትሆናለህ?

- ለምሳሌ እንደ ቀድሞው የሊብያ መሪ እንደ ቀዛፊ ይሆናል ብለህ ትጠብቀኛለህ? . . እኔ ያለ ምንም ልዩነት ሁሉንም አመለካከቶች አጠናለሁ። በዚያ ቀን ስለ እስላም ምንም አለማወቄን መገንዘብ ችያለሁ። በእስላም ላይ ብዙ ግርፍ መረጃዎች ቢኖሩኝም ሁሉም አስተማማኝ አይደሉም።

- እኔ ገና ስለ እስላም አላነበብኩም . . በሚቀጥለው ዙር እሱን አጠናለሁ። እያዘንኩ መጽሐፉንም አላነበብኩትም፣ለማንበብ ፍላጎት ነበረኝ።

- መጽሐፉ ለናንተ ይሁን፣ጥያቄዬን አነሳለሁ።

ካትሪና መጸሐፉን ይዛ መጣችና ለጃኖልካ ሰጠችው። መጻፊያውን አውጥቶ አንዳንድ መረጃዎችን ከመጽሐፉ ገልብጦ ከወሰደ በኋላ አመሰግኖ መጽሐፉን መልሶ ሰጣት . .

- መጽሐፉን አትፈልገውም እንዴ?

- መጽሐፉ የሚገኝበትን የኢንተርኔት ድረ ገጽ አድራሻ ወስጃለሁ፤ይህ በቂ ነው፣አመሰግናለሁ ደህና ሁኑ።

ጆርጅና ካትሪና ወደ ክፍላቸው ሄዱ . . ጆርጅ የወዳጆቹን ምላሽ ሲጠባበቅ ስለነበር ኮምፒውትሩን ከፈተ። ‹‹ጳውሎስ መጽሐፍ ቅዱስን በተለይም አዲስ ኪዳንን በርዞታል፣አዛብቶታል ትላላችሁ?›› የሚል ትያቄ ልኮላቸው ነበር። ያልተጠበቀው አስገራሚ ጉዳይ ሁሉም መልሶች የመዛባትና የመምታት አደጋ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ መከሰቱን በሙሉ ድምጽ የተስማሙበት መሆኑ ነው። የመበረዝና የማዛባት ድርጊቱ የተፈጸመበትን መንገድ በተመለከተ ግን ልዩነት አላቸው . . ሁሉንም ምላሾች እንደገና ጽፎ ለሁሉም ላከላቸው . .

ሐቢብ እያዘንኩ ከታሪክ አኳያ በትክክል ተከስቷል።

ቶም መዛባቱ፣መከለሱና መምታታቱ እስከተረጋገጠ ድረስ ማን እንደፈጸመው ማወቅ ለኔ ቁምነገር የለውም።

አደምፈንጂ ያዘለ ጥያቄ ነው። ማን እንዳዛበውና እንደ ለዋወጠው አላውቅም።

ሌቪ ታዲያ ብሉይ ኪዳንን ያዛባውና ያምታታው ማን ይሆን?! ምናልባት ችግሩ የተከሰተው በገልባጮችና በጽሑፍ መዝግቦ የማጠናቀሩ ሥራ በጣም በመዝግየቱ እንጂ ሆን ተብሎ ለማዛባት ዓላማ ላይሆን ይችላል።

የሚከተለውን ጻፈላቸው

‹‹አራተኛው ዙር ፦ በግልጸኝነት ለመናገር እስላምን ለማወቅ እውነተኛ ፍላጎት አላችሁ? ከሆነስ ለምን?

መልካም ፈቃዳችሁ ሆኖ አጭር መልስ ነው የምፈልገው . . ነገ ምሽት ለንደን እገባለሁ።

ጆርጅ - ሮም››

ለሁሉም ባልደረቦቹ ላከላቸው

። በዚህ ዙር ካትሪናን እና

ጃኖልካን በዝርዝሩ ውስጥ አካቷል

. . ኢሜይሉን ማንበብ ቀጥሎ ከቶ

ም የተላከለትን መልእክት አገኘ ፦

‹‹ይድረስ ለሁሉም ወዳጆቼ፣የፌስቡክ ገጼ የተሰረቀብኝ መሆኑን እሳውቃችኋለሁ፤እንዲመለስልኝ ከፌስቡክ አመራር ጋር በመደራደር ላይ ነኝ። በገጹ ላይ ሊታይ ለሚችል እኩይ የሆነ ማንኛውም ነገር አስቀድሜ ይቅርታ እየጠየቅሁ እኔን የማይወክል መሆኑን እገልጻለሁ።

ቶም››

ጆርጅ የቶምን ፌስቡክ ገጽ ሲከፍት ቶም ከበርካታ ሴቶች ጋር ኢሞራላዊ በሆነ አሳፋሪ ሁኔታ የሚታይባቸው ፎቶዎች ተለጥፈው አገኘ

። በቶምና በበራድ መካከል ጦርነቱ ተጀመረ ማለት ነው? ሲል ራሱን ጠየቀ። አደም ስለ ሐኪሙ የአመለካከትና እሳቤ ሽግግርና ካንዱ ወደሌላው መረማመድ የጻፈው መጣጥፍ ወዲያው ትዝ አለውና አደም እውነቱን ነው ቶም ዝቅጠት ውስጥ ነበር አለ። ጆርጅ ፎቶዎቹን መመልከት ቀጠለ፣ከሴቶቹ ፎቶዎች መካከል ካትሪናን እየፈለገ መሆኑ ከአፍታ በኋላ ታሰበውና ይህ ለርሱም ሆነ ለርሷ ተገቢ ያልሆነ ጥርጣሬ እንደሆነ ተገነዘበ። ኮምፒውተሩን ዘግቶ አልጋው ላይ በጀርባዋ ወደተኛችው ካትሪና ሄደና ሳማት፤በእንቅልፍ ልቧ መልሳ ሳመችው፤ዓይኖቿን ከፍታ ፈገግ አለች . .

- እወደሃለሁ።

- እኔም እወድሻለሁ . . ወደኔ ቀረብ በይ።

ቀጣዩ ቀን በፍጥነት ነጎደ . . ወደ አይሮፕላን ማረፊያ ለመንቀሳቀስ የቀራቸው የተወሰኑ ሰዓታት ብቻ ናቸው . . ወደ ገበያ ሄዱና ካትሪና ስለ አደም ስጦታ ጆርጅን አስታወሰችው። ከፍተኛ ጥራት ያለውና ዋጋው በጣም ርካሽ የሆነ የቆዳ ቦርሳ . . በግብይታቸው መሀል በአንዳንድ ምርቶቹ ላይ የማጣሪያ ሽያጭ በማካሄድ ላይ የሚገኝ ውድ የቆዳ ምርቶች መሸጫ ሱቅ በድንገት አጋጠማቸው። ያንዳንድ ምርቶቹ የቅናሽ ዋጋ እስከ80
በመቶ የሚደርስ ነበርና ጥራት ያለው የቆዳ ቦርሳ በርካሽ ዋጋ ለአደም ተገዛ . . በአስገራሚው የአደም ጥያቄና ፍላጎቱን እውን ለማድረግ ባስቻላቸው ያልተጠበቀ አጋጣሚ እየሳቁ ሱቁን ለቀው ወጡ።
ከገበያው ማእከል አቅራቢያ በሚገኝ ሬስቶራንት ምሳቸውን በሉና ሸንጣዎቻቸውን ለመውሰድ ወደ ሆቴሉ ተመለሱ . . ከዚያ ወደ አይሮፕላን ማረፊያው አመሩ።