ጭንብሉ ሲወልቅ

ጭንብሉ ሲወልቅ

ጭንብሉ ሲወልቅ (1)

ጆርጅ ከሮም ጉዞው መልስ የበለጠ መነቃቃትና እፎይታ ተሰምቶታል።
ብዙ
ጭንቀትና
ጫናዎች
የተቃለሉለት
ሆኖ የተሰማው ከመሆኑ የተነሳ የነበረበት ውጥረት በሥራ ብዛትና አብዛኛውን ጊዜውን ይወስድበት በነበረው ንባብ ምክንያት ይሆን? ወይስ ከወንጌልና ከአምላክ ጋር ብቻ ሳይሆን ከክርስትና እና ከሁሉም ፈለጎቹ ጋር በጥቅሉ በተያያዙ አሉታዊ እሳቤዎችና ግራ በመጋባት ምክንያት ይሆን? ብሎ ራሱን ጠየቀ። አልያም አሁን የተሰማው እፎይታ መጫወቻ አሻንጉሊቱን ሰብሮ ከሚደሰት ሕጻን ደስታ ያላለፈ ይሆን? ቤተክርስቲያን፣ ጳጳሳዊ ሥርዓቱና ወንጌሉ በውስጡ ከተንኮታኮቱ በኋላ ሌላ አዲስ መጫወቻ ከየት ያገኝ ይሆን?! ወይስ ለመንፈሱ ለሕይወቱና ለደስታው ምንም ትርጉም ያጣ ኤቲስት ሆኖ ይቀመጥ? ከዚያም ኦ አምላኬ
! ኦ አምላኬ
! ኦ አምላኬ
! ብሎ ጮኸ . .
ካትሪና እንኳ ሳትቀር ጉዞውን ወዳለች፤የተለየ መንፈስ ይዛ ነው የተመለሰችው . . ደስታዋ በባሏና በልጆቿ ደስታ በመደሰቷ ይሆን? ወይስ አጥልቃው የነበረውን ጭንብል በማውለቋ ሕይወትን ከተለየ አቅጣጫ መመልከት መጀመሯ ያሳደረባት ደስታ ይሆን? የቄሱን ግራ መጋባትና ደካማነቱን ስታውቅ የደረሰባትን ከባድ ድንጋጤ፣በግብጻዊው ሰውየና በሰጣት መጽሐፍ ፊት ተሸናፊ መሆኗን፣ጃኖልካንና ማስረጃዎቹን መሞገት የተሳናት መሆኑን . . ታስታውሳለች። መለስ ትልና ‹‹ግን እኮ ከአስፈሪ ጥርጣሬ የሚሻለውን እርግጠኝነት እውስጤ ይዣለሁ›› ትላለች። እንደገና ራሷን ‹‹ከበፊቱ ይበልጥ አሁን ለምን ደስተኝነት ይሰማኛል?!›› ስትል ትጠይቃለች።
ቤት ደርሰው እቃዎቻቸውን ካደራጁና ራሳቸውም ከተረጋጉ በኋላ፣የባልደረቦቹ ምላሾች መድረስ አለመድረሳቸውን ለማየት ጆርጅ ኢሜይሉን ከፈተ። የሁሉንም ምላሾች አገኘና ኮፒ አድርጎ ባለፈው ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ ለሁሉም መልሶ ላከላቸው።

ሌቪ አባቴን የገደሉ ሙስሊሞችን የምጣላቸው ቢሆንም እስላምን አጠናለሁ፤የማጠናው ግን የተሸከሙትን ክፋት ለማወቅና እንዴት ከዚያ መዳን እንደሚቻል ለመረዳት ስል ነው።

ሐቢብ አዎ መለኮታዊ ሃይማኖት ነውና አጠነዋለሁ፤ስለሱ ያለን መረጃ ግን በጣም አናሳ ነው።

ቶም አዎ፣ሌላው ዘንድ ያላገኘሁትን ምናልባት እርሱ ዘንድ ላገኝ ስለምችል አጠናዋለሁ ነው።

አደምበእርግጠኝነት አዎ፤መርሃችንና ሚዘናዊነታችን ሁሉንም መለኮታዊ ሃይማኖቶች እንድንመረምር ያስገድዱናል።

ሐጃኖልካ አዎ እመረምረዋለሁ፣እኔ ሁሉንም ነገር መማርና ማወቅ ደስ ይለኛል።

ወደ ሮም ከሄዱበት ጊዜ አንስቶ ኢሜይሏን ከፍታ ስለማታውቅ ከመልሶቹ መካከል የካትሪናን አላገኘም . . አምስተኛውን ዙር ጻፈና ለሁሉም ላከ . .

‹‹አምስተኛው ዙር ምክንያታችሁ የተለያየ ቢሆንም የሁላችሁም መልስ ‹‹አዎ›› መሆኑ አስገራሚ ሆኖብኛል። በመሆኑም የዛሬው ጥያቄ እያንዳንዱ ሰው በሦስቱ መለኮታዊ ሃይማኖቶች መጻሕፍት (ብሉይ ኪዳን፣አዲስ ኪዳንና ቁርኣን) መካከል ንጽጽሮሽ ያድርግ የሚል ነው።

ጆርጅ - ለንደን››

መልእክቱን ልኮ የተወሰኑ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ ስልኩ አቃጨለ፣ደዋዩ ቶም ነበር፤ድምጹ ውጥረትና ጭንቀት ውስጥ መኖሩን ያሳብቅበት ነበር . .

- ሰላም ነው አይደለም?

- ሰላም ነው መግባታችሁን ለማወቅ ፈልጌ ነው፤ላገኝህ እፈልጋለሁና መቼ መገናኘት እንችላለን?

- ገና ከ45 ደቂቃ በፊት ነው ቤት የደረስነው፣አሁን በጣም ስለመሸ ነገ ጧት ይመቸሃል? ካልሆነም አሁን መምጣት ትችላለህ።

- አዝናለሁ ጊዜው እንዲህ መምሸቱን ልብ አላልኩም ነበር፣ ይቅርታ። ነገ ጧት አራት ሰዓት ላይ እቤት እመጣለሁ።

- እጠብቀሃለሁ፣አይዞህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር በጎ ይሆናል።

- ጆርጅ አመሰግናለሁ፤ደግሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

የቶም ጥሪ ያሳሰበው ጆርጅ የቶም የፌስቡክ ሂሳብ መሰረቁና ከበራድ ጋር ችግር ውስጥ መኖሩ ወዲያውኑ ትዝ አለውና ኮምፒውተሩን እንደገና ከፍቶ ወደ ቶም ፌስቡከክ ገጽ ሄደ።
ያጋጠመው ግን ያልጠበቀው ነበር . . ካትሪና በአስነዋሪ አለባበስ ከቶም ጋር ሆና የምትታይባቸውን ፎቶዎች ተለጥፈው አየ! አስተውሎ መመልከት ሞከረ፣በፎቶግራፎቹ ላይ ንጽሕናና የዋህነትን የተላበሰው የካትሪና ፊት በግልጽ ተለይቶ ይታያል። ፎቶዎቹ የሮም ጉዞ ደስታውንና እፎይታውን የሚያስረሳው ከባድ ድንጋጤ አሳደሩበት። ለራሱ እንዲህ አለ፦

- የዋህነትንና ንጽሕናን ጨምሮ ሁሉም ነገር ማታለልና ማጭበርበር ነው ማለት ነው !

ለቶም መልሶ መደወል አሰበ፣ግን ምን እንደሚሆን ለማየት እስከ ነገ አራት ሰዓት መታገስን መረጠ . . ለመተኛት ሞከረ ግን አልቻለም። ካትሪናን ከቶም ጋር ባየበት ሁኔታ ማየትን ማሰቡ አስጨንቆታል፤ትእይንቱን ከአእምሮው ፈጽሞ ማራቅ አልቻለም። ቶምና ካትሪና ተስማምተው ስለ ንጽሕናቸው የዋሹትን ውሸት እንዴት አምኖ እንደ ተቀበለ ገርሞታል። ሕይወት ገደል ትግባ . . ሰዎች ውሸታቸውን አሉ የሚሏቸው መልካም የስነ ምግባር እሴቶችም ገደል ይግቡ . . ጊዜውስ ምነው አልነቃነቅ አለ
! ጊዜ ራሱም ማጭበርበርና ማስመሰል አሳምሮ ያውቅበታል፣በሁለቱም ሁኔታ አንድ ቢሆንም ራሱን አንዴ ረዥም አድርጎ ሲያቀርብ ሌላ ጊዜ ደግሞ አጭር ሆኖ ይታያል።
ካትሪና ጧት ሦስት ሰዓት ላይ ነቃች፤ጆርጅ ግን ያንቀላፋ መስሎ አደባ . . ወደርሱ ቀረብ ብላ ሳመችውና በጆሮው አንሾካሾከች፦

- ውዴ የቤት አስቤዛ ለመግዛት መሄዴ ነው፤ለቤት የሚያስፈልጉን ነገሮችን ለመሸመት መሄዴ ነው ፍቀድልኝ።

ካትሪና ወጥታ እንደ ሄደች ጆርጅ ከመኝታው ተነስቶ ልክ አራት ሰዓት ላይ የደረሰውን ቶምን ጨፍገግ ባለ ፊት ተቀበለው . .

- ስለ ረበሽኩህ አዝናለሁ፣ነገሩ በጣም ቀላል ነው፣ግን በጣም አሳሳቢ ነው።

- በል ንገረኝ።

- ከበራድ ጋር ያለው ጦርነት በአስከፊ ሁኔታ ተጀምሯል።

- አልጠበቅክም ነበር?

- ጠብቄአለሁ፣ግና ቆሻሻ ጦርነት ነው።

- ከበራድ ከዚህ የተለየ ነገር ትጠብቅ ኖሯል?

- አልጠበቅኩም፣ፍቀድልኝና ልጨርስ። ከአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ማፍያ ቡድናቸው ጋር ተባባሪ ሆኜ እንድሰራ አለበለዚያ ለውርደት እንደሚያጋልጠኝ አስጠንቅቆኝ አልተባበርም አልኩት። ደጋግሞ ቢያስጠነቅቀኝም እምቢ አልኩት። ከጥቂት ቀናት በፊት የፌስቡክ ሂሳቤን ለመክፈት ስሞክር አልከፈት አለኝ፣የቴክኒክ ችግር ይሆናል ብዬ ሳስብ ባልተጠበቀ ሁኔታ የፌስ ቡክ ገጼ ኢሞራላዊ በሆኑ የቀድሞ ፎቶዎቼ ተሞልቶ አገኘሁት።

- ይህ መቶ በመቶ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀ ነው፣አይደለም እንዴ?

- እባክህን አስጨርሰኘ፣ፎቶዎቼን መለጠፍ ከጀመረ በኋላም እንድተባበረው ደጋግሞ ጠየቀኝ፣እኔም እምቢታዬን ደጋግሜ ነገርኩት። በዚህ ጊዜ ነው ከበፊቱ ይበልጥ አስቀያሚ የሆነ ሥራ መስራት የጀመረው። እውነት ያልሆኑ ፎቶዎችን በቴክኒካዊ ዘዴ እያቀነባበረና ቆርጦ እይገጣጠመ ገጼ ላይ መለጠፉን ተያያዘው።

- እናም ከኔ ምንድነው የምትፈልገው . . ?

- ምን እንደምልህ አላውቅም፤ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን ካትሪና ራቆቷን ሆና ከአጠገቤ የምትታይበትን ፎቶ አቀነባብሮ አስቀምጧል።

- በፌስቡክ ገጽህ ላይ ያሉት የክህደት ፎቶዎችህ እውነተኛ አይደሉም ማለት ነው የምትፈልገው?

- በእርግጥ እውነተኛ አይደሉም።

- የምትላት ሴት እኮ ባለቤቴ ነች፣ፎቶግራፎቹ የራሷ ስለመሆናቸው እርግጠኛ ነኝ።

- ልክ ነህ የራሷ ፎቶዎች ናቸው፣ግን በቴክኒክ የተቀነባበሩ እንጂ እውነተኛ አይደሉም።

- ቶም ይበቃል . . በኔ መሾፉ ይብቃህ !

- ፎቶዎቹን አስተውለህ መርምራቸው፣ከተለያየ ቦታ ተወስደው የተቀጣጠሉና በእጅ የተቀነባበሩ መሆናቸውን በግልጽ ማየት ትችላለህ።

- ከቤቴ ውጣልኝ . . ውጣልኝ !

- ጆርጅ እኔን በድለህ ካትሪናንም አትበድላት።

- ውጣ . . በቃ ውጣ።

ጆርጅ የሚያደርገው ነገር ጠፍቶት በሳሎኑ ሶፋ ላይ ተዘረገፈ፣በከፍተኛ ስሜታዊ ሁኔታ ውስጥ ነበር . . ስልኩ ሲጮህ ቁጥሩን ተመለከተ፣አደም ነበር። ሁሉም በኔ ላይ ድራማ እየተወኑ መሰለኝ፣በትወናው ውስጥ እኔ ብቻ ነኝ ሞኝ ተላላው . . ይሀ ደግሞ አሁን ምን ይፈልግ ይሆን?! ብሎ አጉረመረመ።

- ሃሎ አደም !

- ሃሎ ጆርጅ ናፈቅከን እኮ።

- ምን ፈለግህ?

- ምንም፣እንዲሁ ሰላም ልበል ብዬ ነው።

- አመሰግናለሁ፣ደህና ሁን።

ከደቂቃዎች በኋላ ለምትመጣው ካትሪና ምን እንደሚላት እያሰበ መነጋገሪያውን አስቀመጠ። ውርደት ተሰምቶታል፤የክህደት ውርደት፣የማሞኘትና ድክመትን የመጠቀም ውርደት . . ካትሪና ፈገግ እያለች ስትመጣ ሲያይ ትንሽ ለመረጋጋት ሞከረ . .

- እንደ ሮሙ ሆቴል ዝግጁ የሆነ ቁርስ እዚህ የለም፤ቁርስ በልተሃል ወይስ የሆነ ነገር ላዘጋጅልህ?

- ምንም አልፈልግም።

- እንግዲያውስ አንድ ፍንጃን ወተት ወይም ሻይ ትጠጣለህ።

- አመሰግናለሁ።

- ትንሽ ነገርም ቢሆን ተጋራኝ።

- ምንም አልፈልግም አልኩሽ እኮ አይገባሽም?

- ጆርጅ ምን ተፈጠረ?

- ካትሪና ጭምብሉ ነው የተገለጠው፣ጭንብሉ ወልቋል።

- የትኛው ጭንብል?

የቶምን የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ ከፊቷ አኖረ . . እየተራገመና እያጉረመረመ ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ . .

- አንቺ አጥባቂ ሃይማኖተኛዋ፣ተመልከቺው፤አንቺ ትንሽቱ አውሬ እይውማ! ብትመነኩሽ ኖሮ እንደ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና መነኮሳት ሁሉ ትልቅ አውሬ በሆንሽ ነበር፤ተመልከቺ . .

ካትሪና ፎቶዎቹን ተመለከተች፤እያለቀሰች ጆርጅን ተከትላ ሄደች . .

- ቶም ውሸታም ባለጌ ሰው ነው፤ይህ በፍጹም እኔ አይደለም።

- አንቺ የተዋጣልሽ ተዋናይ አሁንም ድራማውን መቀጠል ነው የምትፈልጊው? ነገም አብራችሁ ልትተኙ . .

- እመነኝ እኔ ይህን ምሰራ ሰው አይደለሁም፣ይህ የቶም ተራ ብልግና እና የርሱ ውሸት ነው። ብዙ ጊዜ ስነ ምግባር የጎደለው ኤቲስት ሰው ነው ስትለኝ አልነበረም?

- ለሕክምና ወደርሱ እንድሄድ በተለይ የጎተጎትሽኝ አንቺ አልነበርሽም? ሃይማኖት ያስተማርሽውስ አንቺ አይደለሽም? ተለውጧል የምትይውስ አንቺ አይደለሽም? !

- እኔን ትጠረጥረኛለህ ብዬ ፈጽሞ አልጠበቅኩም ነበር . .

ካትሪና በለቅሶ ፈነዳች . . ከዚያ ራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ዳግም ወደ ኮምፒውተሩ ሄደች፤ቶምን እየተሳደበችና እተራገመች ፎቶዎቹን ትኩር ብላ በአስተውሎት አየቻቸው። በዚህ ጊዜ ከተለያየ ቦታ ተወስዶ እንዲገጣጠም የተደረገ መሆኑ በግልጽ በሚታይ አንድ ፎቶ ላይ ዓይኖቿ አረፉ። በችኮላ ኮምፒውተሩን ይዛ ወደ ጆርጅ ሄደች . .

- ተመልከት፣ፎቶው ተቆርጦ የተቀነባበረና እውነተኛ አለመሆኑ በግልጽ የሚታይ ነው። አሁን እስኪ እንዴት ሆኖ ነው ይህ ራስ ከዚህ ደረት ጋር ሊጣጣም የሚችለው?!

- ይህ ልክ የቶም አነጋገር ነው፤‹‹ተቆርጦ የተለጣጠፈ ፎቶ›› የተውኔቱ አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ነው?

- በደንብ አስተውለህ ተመልከተው።

- ምናልባት ሊሆን ይችላል፤ትወናችሁን ተቀብዬ በድጋሜ እንድታሞኙኝ ግን አልፈልግም !

- ቶም እርሱ ራሱ ገጹ ላይ ለጥፎ በውሸት የተቀነባበረ ፎቶ ነው እንዴት ማለት ይችላል?!

- ቶም ከአፍታ በፊት መጥቶ በራድ የፌስቡክ ሂሳቡን እንደ ሰረቀበትና እርሱን ለመበቀል ብሎ ፎቶዎቹን አቀነባብሮ የለጠፋቸውም ራሱ በራድ መሆኑን ነግሮኛል።

- በራድ ! ለምንድነው የሚበቀለው?

- የተውኔቱን ትረካ ለማሟላት ያህል፣አደንዛዥ እጽ ከነርሱ ጋር ተባብሮ ለመሸጥ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው።

- የምትናገረው ልገባኝ አልቻለም፤ለማንኛውም ግን ፎቶዎቹ ተቆራርጠው የተቀነባበሩ ብቻ ሳይሆኑ ውሸት መሆናቸው በግልጽ የሚስተዋል ሰለመሆኑ ፍጹም እርግጠኛ ነኝ።

- በውሸት የተቀነባበሩ ሊሆኑ፣አውነትም ሊሆኑ ይችላሉ። የፌስቡክ ሂሳቡ የተሰረቀበት መሆኑን የሚገልጽ መልእክት ቶም አልላከልሽም ነበር? ወይስ አሁንም የተውኔቱን ሌላ አዲስ ምዕራፍ መጀመራችን ይሆን?!

- ወደ ሮም ከተጓዝንበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ኢሜይሌን ከፍቼ አላውቅም፤ኮምፒውተሩን ስጠኝና ከፍቼ ልረዳ።

ካትሪና ኢሜይሏን ስትከፍት ከቶም የተላኩ ሁለት መልእክቶችን አገኘች . . የመጀመሪያው ሂሳቡ መሰረቁን የሚገልጽ ሲሆን ሁለተኛው አስነዋሪ ፎቶ የያዘ ነበር። በፌስቡክ ገጹ ላይ ያለው የቶም ፎቶ ራሱ ሆኖ ‹‹ይህ የንጽሕና እና የእውነተኝነት ማስረጃ ነው›› የሚል መግለጫ ከስሩ ተጽፎአል። ፎቶውን አስተውላ ስትመለከት ከቶም ጎን ያለው ሰው እርሷ ሳትሆን ጆርጅ ነው . . !

- ይልቅስ አንተ ነህ ክህደት የምትፈጽምብኝ፤ናማ ፎቶውን ተመልከት።

- እኔ? ከማን ጋር ነው ክህደት የምፈጽምብሽ?!

- ከቶም ጋር፤ይኸ ፕሮቴስታንታዊ ግብረሰዶማዊነት አይደለም?!

ጆርጅ ፎቶዎቹን አስተውሎ ተመለከታቸው፤ተቆርጠው የተቀነባበሩ መሆናቸው በግልጽ የሚታይ ነበር . . ጆርጅ ለተወሰነ ጊዜ ራሱን አቀርቅሮ ቆየና ቀና ብሎ በተረበሸ ቅላጼ . .

- ቶምን ከቤት አባርሬው ነው የሄደው።

- ጆርጅ እኔን ትጠረጥረኛለህ?!

- ከቶም ጋር በመስማማት ትወናውን እያካሄደብኝ ነው ብዬ በማሰብ በአደም ላይም ስልክ ዘግቼበታለሁ !

- ጆርጅ ይህ ሁሉ ለምን?!

- በምናደድበት ጊዜ ወይም በድክመት ሁኔታ ላይ ሆኜ በአንድ ነገር ላይ እንዳልወስን አደም ከአንድ ጊዜ በላይ መክሮኛል። አሁን ምን እንደማደርግ አላውቅም?! ካትሪና አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጊልኝ።

- ከዚህ ሁሉ በኋላ ‹‹አጥፍቻለሁ ይቅርታ›› ብቻ ! !

- ምን እንዳደርግ ትፈልጊያለሽ?

- አላውቅም፣የይቅርታ ጥያቄው በጥፋቱ ልክ ነው የሚሆነው።

- ይቅር እንድትይኝ እማጸንሻለሁ፤ቶምና አደምን በተመለከተ ምን ማድረግ እንደምችል አስብበታለሁ።

- ካንተ ባማልጠብቀው ሁኔታ በጽኑ ያቆሰልከኝ ብትሆንም፣አሁን የተናገርከውን የአደም ምክር ከመተግበር ግዴታ ጋር ይቅር ብየሃለሁ።

- ካትሪና አመሰግናለሁ፣አንቺ ሁሌም ልብሽ የጠራ ሳፊ ነው። እንዴት እንደማመሰግንሽና ያጠፋሁብሽን ትልቅ ጥፋት እንዴት እንደማስረሳሽ አላውቅም . . (ብሎ ተነስቶ አቀፋትና ቀጠለ) ፦ ከቶምና ከአደም ጋር ያለውን ነገር መፍትሔ ለመፈለግ ለአጭር ጊዜ ለብቻዬ እንድሆን ትፈቅጂልኛለሽ?

- ይሁንልህ፣ብቆስልም የጌታ ረድኤት ካንተ እንዳይለይ እጸልያለሁ።

ጆርጅ ኮምፒውተሩ አጠገብ ቁጭ አለ፤ኢሜይሉን ከፈተና የሚከተለውን መልእክት ጻፈ፦

‹‹ውድ ወዳጄ ቶም

በኔና በአንተ መካከል ሳናስበው በተፈጠረው ነገር ጥፋተኛ በመሆኔ ይቅርታ እጠይቀሃለሁ . . አንተ በበኩልህ ወደ ቤቴ መጥተህ ይቅርታ ጠይቀሃል፣ይቅር እንድልህም ጠብቀህ ነበር፤እናም በኔም ተመሳሳይ ነገር አድርግ . . ከፈለግህ ወደ ክሊኒክህ እመጣና ብታባርረኝ ደስተኛ ነኝ . . ደጋግሜ ይቅርታ እንድታደርግልኝ እለምነሃለሁ።

ጆርጅ››

በመቀጠል ይቅርታ ለመጠየቅ በቀጥታ ለአደም ደወለ

. .

- አደም፣ በጣም ምርጥና በጣም ርካሽ የሆነውን ቦርሳ አምጥቼልሃለሁ።

- አገኘህ? በዚህ መመዘኛ አግኝተህ አመጣህ?

- አዎ፣መቼ መጥተህ ትወስዳለህ?

- እህህ፣ዛሬ ባናገርከኝ ሁኔታ እንዳታናግረኝ ላንተ በሚመች ጊዜ።

- በተመቸህ ጊዜ አድርገው፤ቅድም ስትደውል በድክመትና በውጥረት ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩ ይቅርታ አድርግልኝ፣የሆነውን ነገር ሳገኝህ አጫውተሃለሁ።

- እንግዲያውስ እዚህ መጥተህ ሳትጎበኘኝ ረዝም ጊዜ በመሆኑ ወደ ካፌቴሪያው ብቅ በል።

- መልካም፣ዛሬ ወይም ነገ እጎበኘሃለሁ።

ጥሪውን ካበቃ በኋላ ቶም ምላሽ ጽፎለት ከሆነ ለማወቅ ወደ ኢሜይሉ ተመለሰ

. .
ቶም ለካትሪና ልኮት የነበረውን መልእክት ለርሱም ተልኮለት አገኘ፤በማንበብ ላይ እያለ ከቶም ምላሽ መጣለት . .

‹‹ይቅር እንድልህ ከፈለግህ አዳምጠህ ትእዛዞቼን ፈጽም

1- ነገ ማታ አንድ ሰዓት ላይ ወደ ክሊኒኬ ትመጣለህ፣ከዚያ በኋላ አባርረሃለሁ አላባርርህም የሚለውን እኔ እወስናለሁ

2- እንዲህ ያለውን ጋጠ ወጥ ድርጊት ዳግም ከመፈጸም ተቆጠብ

3- ይህን እንዳነበብክ ለትእዛዞቹ ተገዥ መሆንህን የሚያረጋግጥ ቀጥተኛ መልእክት ጻፍ።

ዶክተር ቶም››

ምላሽ

ጻፈለት . .

‹‹ውድ ወዳጄ ቶም ስመጣ ብታባርረኝ እንኳ ጥፋተኛ ስለሆንኩ ተስማምቻለሁ።

ጆርጅ››

መልሱን እንደ ላከለት ለቶም ስልክ ደወለ . .

- ሃሎ።

- ሃሎ፣በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ተናድጄ ስለነበር ነው።

- ምንም አይደለም፤አንድ ሳልጠቅሰው የረሳሁትና ልትስማማበት የሚገባ ግዴታ ግን አለ . .

- ምንድነው?

- እህህ . . ጆርጅ ቀልዴን ነው ሁሉም ነገር አልቋል፤ነገ በጣም አስፈላጊ የሆነ ቀጠሮ ይኖረናል።

- ቶም በጣም አመሰግናለሁ።

- ትቀርና ወየውልህ . . እህህ፣ተዘጋጅቼ እጠብቀሃለሁ።

- እንድታባርረኝ በቀጠሮው ከች እላለሁ . . አሁንም ደግሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ጭንብሉ ሲወልቅ (2)

የስልክ ጥሪውን እንዳበቃ ከአደም ጋር ቀጠሮ እንዳለው

አስታወሰ . .

- አሁን አደምን ለመጎብኘት ወደ ካፌቴሪያው እሄዳለሁ።

- አደም አስተዋይ ጥበበኛ ሰው ነው፤ጉዳዮች ባይኖሩኝ ኖሮ ካንተ ጋር በሄድኩ ነበር።

- ልክ ነሽ፣ከኔ በመወዳጀቱ ምን እንደሚጠቀም አላውቅም !

- ወዳጅነት ቁሳዊ መጠቃቀምን የማይሻ ራሱን የቻለ ትልቅ እሴት ነው።

- ለብቻው የሚኖር በመሆኑ አብረን ምሳ እንበላ ይሆናል፣ከኔ የሚያገኘው ነገር ካለ ምናልባት ይህች ብቻ ናት።

ጆርጅ ወደ ካፌቴሪያው ስደርስ አደም ሞቅ ያለ አቀባበል አደረገለት። የሥራ ተራው ከግማሽ ሰዓት በኋላ እንደሚያበቃ ነግሮት እስከዚያ ድረስ ቡና እየጠጣ እንዲቆይ ነገረው። አደም ከሥራ ሲወጣ በቀጥታ ወደ ጆርጅ መጣና ምሳቸውን በሰዓዳ ሬስቶራንት ለመብላት ወስነው ሄዱ።

- ለደርሶ መልስ ጉዞና ምሳችን ለመብላት የአንድ ሰዓት ጊዜ አለንና የካቶሊኮች መናኸሪያና ማዕከላቸው እንዴት እንደነበረ አሁን ልታወጋኝ ትችላለህ?

- ብናገር አትቆጣም?

- ጆርጅ ስሜታዊ የሆንክ ትመስላለህ፣ምን ያስቆጣኛል?!

- ብሉይ ኪዳንን እውነት ነው ብዬ መቀበልም ሆነ በርሱ ማመን አልችልም፤በመሆኑም አይሁዳዊነት፣ካቶሊካዊነት፣ ፕሮቴስታንትነትም ሆነ እስላም ለኔ አመቺ አይደለም።

- አንደኛ - በብሉይ ኪዳን ላይ ይህን ሁሉ መጫንህ ለምንድነው? ለኛ በላክልን ጥቅሶች ምክንያት ነው?

- ይህ አንዱ ምክንያት ነው፤መጽሐፉ የተምታታና የተዛባ ስለ መሆኑ ሌሎች መቶ ተመሳሳይ ምክንያቶች አሉኝ።

- አዲስ ኪዳንሳ?!

- ከብሉይ ሻል ያለ ቢሆንም ያው ተመሳሳይ ናቸው።

- ቁርኣንሳ?!

- በብሉይና አዲስ ኪዳንም የሚያምን እንደ መሆኑ እሱም እንደዚያው ነው።

- በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ችኩል እንዳትሆን ምኞቴ ነው።

- ከዚህ ሁሉ ጋር ለጥያቄዎቼ ምላሽ እንደማገኝ የሚሰማኝ እንጥፍጣፊ ስሜት አሁንም አለኝ።

- በእርግጠኝነት መልሱን ታገኘዋለህ።

- ችግሩ'ኮ አንዱም ሃይማኖት ትክክለኛ ሆኖ ካልተገኘ መፍትሔው ኤቲዝም ሊሆን ነው ማለት ነው !

- ኤቲዝም የመታደል መንገድና የሕይወት ጥያቄዎች ምላሽ ሆኖ አያውቅም፣ወደፊትም ሊሆን አይችልም።

- ታዲያ መንገዱ የቱ ነው?

- ፍለጋህን ቀጥልበት ታገኘዋለህ።

- እህህ፣ምናልባት እስላም ወይም የሽብር ሃይማኖቱ ይሆናላ !

- እስላምን ማጥናት እንፈልግ እንደሆነ በመጠየቅ መልእክት ስትልክልን የተለያየ ሃይማኖት ያላቸው ከመሆኑ ጋር የሁሉም መልስ ‹‹አዎ እንፈልጋለን›› የሚል ነበር፤አንተ ራስህ ግን እስላምን ማጥናት የማትፈልገው ለምንድነው?!

- እናንተ ከጠቀሳችኋቸው በሚበልጡ ብዙ ምክንያቶች፤ከሁላችሁም ይበልጥ እስላምን ለማጥናትና ለማወቅ የምጓጓው እኔ ነኝ። እስላም ትክክለኛ ሆኖ ካልተገኘ ሌላ የትኛውም ሃይማኖት ትክክለኛ ሊሆን አለመቻሉ ብቻ በቂ ምክንያት ነው።

- የትኛውንም ሃይማኖት በዚህ መንገድ ማጥናት አይታየኝም !

- ወደ ሰዓዳ (መታደል) ሬስቶራንት ደርሰናል፣ወደ መታደል መንገድም ምነው በደረስን ! ለማንኛውም እንግባና ወጋችንን እንቀጥል።

የሚመች ጠረጴዛ መርጠው ሲቀመጡ አስተናጋጁ የምሳ ትእዛዛቸውን ተቀብሎ ሄደ . . አደም በቁርጠኝነት ስሜት ጆርጅን እያየ . .

- ከፈቀድክልኝ ስናገረው የነበረውን ልጨርስ፤ለሮም ጉዞ ስትዘጋጅና ስለ ክርስትና በጥልቀት ማንበብ ስትጀምር ምን ብየህ ነበር?

- ለሁሉም ሀሳቦች አእምሮህን ክፍት አድርገህ ያለ ምንም ቅድመ ውሳኔ ነገሮችን መርምራቸው ነበር ያልከኝ።

- ዛሬም ያንኑ ደግሜ እለሃለሁ፤እስላምን ከዚህ ውጭ በሌላ መንገድ እንድታጠናው አልፈልግም።

- ገና አይሮፕላን ላይ እያለሁ ነው እስላምን ለማወቅ ማንበብ ስለሚገቡኝ መጻሕፍት ማሰብ የጀመርኩት።

- የኔን ምክር ትፈልጋለህ?! ከየትኛውም መጽሐፍ በፊት ቁርኣንን በማንበብ ጀምር።

- አይሁዳዊነትንና ክርስትናን ሳጠና ለምን በመጽሐፎቻቸው በብሉይና አዲስ ኪዳን አልጀመርኩም?

- አይሁዳዊነት ብሉይ ኪዳንን እንድታነብ የማይጠይቅህ ብቻ ሳይሆን ሆን ብሎ አንዳንድ ጥቅሶቹን እንዳይነበቡ ስለሚደብቃቸው ነው። ክርስትናም መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ራስህ አንብበህ እንድትረዳ አይጠይቅህም፤ካህናትና ቀሳውስት በሚረዱበት መንገድ ብቻ መረዳት አለብህ ይላል።

- ቁርኣንስ?!

- እስላምን አልተረዳህም ብየህ የለም? እስላም ለሙስሊምም ሆነ ሙስሊም ላልሆነው የማስተማሪያ፣የማብሰሪያ፣የማስጠንቀቂያና የጥሪው ማድረሻ ዋነኛ መሰረት ያደረገው ቁርኣንን ነው።

- አደም ስለ እስላም ጥልቅ ዕውቀት ያለህ ትመስላለህ፣በሃይማኖቶች ጥናትና ምርምርህ ውስጥ አጥንተሃል ማለት ነው?

- አዎ።

- በግልጸኝነት በርሱ ላይ ያለህ አስተያየት ምንድነው?

- አንተን በመሰለ ሰው ላይ ማንም የራሱን ሀሳብ ሊጭንበት አይገባም፤ቁርኣንን ራስህ አንብበውና የራስህን ውሳኔ በራስህ ወስን።

- በግልጸኝነት ሃይማኖትህ ምንድነው? መጀመሪያ ላይ አይሁዳዊ መሰልከኝ፣ከዚያ ካቶሊካዊ፣አሁን ደግሞ ሙስሊም !

- ቡድሂዝምንና ሂንዱይዝምን እወቃቸው ባልኩህ ጊዜ ቡድሂስት ወይም ህንዱ ሊመስልህ እችል አልነበረም? የሰው ልጅ አእምሮውን ክፍት አድርጎ ከተቆለፈበት ሳጥን ራሱን አውጥቶ በነጻ ማሰብ እስካልቻለ ድረስ ፈጽሞ መሻሻል የማይችል መሆኑን ላረጋግጥልህ እፈልጋለሁ። ሃይማኖቴንና የምከተለውን እምነትም የመታደልን መንገድ ለማግኘት የሚያስፈልግህን ሁሉ ካወቅህ በኋላ እነግረሃለሁ፤ምናልባት ይህ መንገድ ሁሉንም ሃይማኖቶች የሚተካ ሊሆን ይችላል።

- ሃይማኖቶችን ሁሉ የሚተካ እምነት ይኖራል ብዬ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም።

- ቁርኣንን አንብብ፤ቀጥለህ ስለ እስላምና ስለ እስላም ነብይ የተጻፉ መጽሐፎችን አንብብ። ሃይማኖቶችን ሁሉ በንጽጽር ለመመልከት ሞክር። ርእሰ ጉዳዮችንና መረጃዎችን የማገናዘብና የማነጻጸር ችሎታ ለስኬት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

- ጉዳዮችን እንዴት ነው የማስተሳስራቸው?

- የምትጓዝበትን አቅጣጫ ላለመሳት በቡድሂዝም ወይም በህንዱ ሃይማኖት ውስጥ የጠላሃቸውን ነገሮች አስታውስና በአይሁዳዊነት ውስጥ ስለ አለመኖራቸው እርግጠኛ ሁን፤ከዚያም በክርስትና ውስጥ መኖር አለመኖራቸውን አረጋግጥ። በመጨረሻም እስላም ውስጥ ስለ አለመኖራቸው እርግጠኛ ሁን። በተመሳሳይ መልኩ በቡድሂዝም ውስጥ የወደድከው ነገር በአይሁዳዊነት በክርስትና ወይም በእስላም ውስጥ መኖር አለመኖሩን አረጋግጥ። በዚህ ሁኔታ ነው ርእሰ ጉዳዮችን በማነጻጸረና በማገናዘብ የምታያይዛቸው።

- የምፈልገውንና የማልፈልገውን አያይዞ በማነጻጸር የሚያየው የተሟላ ወጥ ምልከታ ደስ ይለኛል።

- በሃይማኖቶች መካከል ያሉትን ተመሳስሎና ልዮነቶቻቸውንም አስተውለህ መርምር።

- የሚያሳዝነው በመካከላቸው ካሉት ልዩነቶች ይልቅ በመካከላቸው ያለው ተመሳስሎ ነው የሚታየኝ !

- ነገሮችን አገናኝቶ መመልከት አእምሮና አስተሳሰበን ያጎለብታል። ዝርዝር ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሆኑትንም እርስ በርሳቸው አያይዘህ ማየትህን አረጋግጥ።

- ተመሳስሎአቸውን በተመለከተ ሁሉም በብሉይ ኪዳን የሚየምኑ መሆናቸውን አስተውያለሁ፤በመሆኑም በዚህ መጽሐፍ የሚየምን በእውነት እብድ ነው የሚል እምነት አድሮብኛል።

- ክርስቲያኖች አዲስ ኪዳን የመጣው ብሉይ ኪዳንን ለማሟላት ነው ብለው ያምኑበታል። አይሁዶች ግን በአዲስ ኪዳን አያምኑም። ሙስሊሞች ደግሞ በመሰረቱ በሁለቱም የሚያምኑ ቢሆንም፣ሁለቱም የተዛቡና የተበረዙ በመሆናቸው ዛሬ ያሉት ከእግዚአብሔር የተላለፉ ነባሮቹ አይደሉም የሚል አቋም አላቸው። የሚያምኑት በቁርኣን ሲሆን ከበፊቱ የነበሩትን መለኮታዊ መጽሐፎች ሁሉ የሚሽር ነው ይላሉ። ታድያ ልዩነቶቻቸው የሰፉ መሆናቸው አይታይህም?

- ልክ ነህ . . ልዩነቶቹ በጣም ሰፊ ናቸው። በተፈጥሮዬ ከልዩነቶች ይልቅ በሚመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ አተኩራለሁ፤ነገሮችን እምብዛም አያይዤ አልመለከታቸውም።

- መልካም፣ችግርን ነቅሶ ማውጣት የመፍትሔው መጀመሪያ ነውና ወደ እልባቱ ደርሰሃል፣እናም በተሟላና በተሰናሰለ መልኩ ታየዋለህ ማለት ነው። በልተህ ጨርሰህ ከሆነ ከሥራ እንዳልዘገይ መንቀሳቀስ አለብኝ።

- አዎ ጨርሻለሁ፤በል እንሂድ። በጣም ምርጡና በጣም ርካሹ ቦርሳህ መኪና ውስጥ ነው፣እንዳልረሳው።

- ስጠይቅህ ስቀህብኝ የነበረ ቢሆንም በመመዘኛው መሰረት ነው ያመጣኸው።

- በአጋጣሚ በአንዳንድ የቦርሳ ዓይነቶች ላይ የማጣሪያ ሽያጭ የሚያካሄድ መደብር ነበር፣በዚህ የጥራት ደረጃ በመደብሩ የቀረው የመጨረሻው ቦርሳ ይህ ነበር።

- አጋጣሚ እግዚአብሔር ሊወስነው የሚችለውን ነገር የሰው ልጆች ማወቅ እንደማይችሉ ያመለክታል። የሚያሳዝነው ግን ‹‹አጋጣሚ›› የሚለውን ቃል ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው አንድ ነገር እንዴት እንደ ተከሰተ ሳናውቅ በምንቀርበት ጊዜ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በፍጥረተ ዓለሙ ውስጥ ያለውን ሁሉ የምናውቅ ይመስል የማናውቀው ነገር ሲያጋጥመን ‹‹አጋጣሚ›› ነው ብለን እንወስዳለን ማለት ነው። እኛ ስላልደረስንበት ብቻ ዕውቀቱ የለም የማለት ያህል ሲሆን፣ ይህም የተወገዘው በራስ አጉል መመካትና መመጸደቅ መሆኑ ጥርጥር የለውም . . አልያም ልብ ሳንለው በኤቲዝም ተጽእኖ ስር ከመውደቅ የተነሳ ሊሆንም ይችላል።

- በፍልስፍናህና በተራቀቁ ቴክኒካዊ ቃላትህ አንገላታኸኝ። እህህ፣የእግዚአብሔር ቅድመ ውሳኔ ሆነና አንዱ ቦርሳ ብቻ ሲቀር ወደ መደብሩ ደረስኩ ማለት ነው፤ፈተናውን አልፌ ይሆን?

- እህህ፣ቦርሳው ከፍተኛ ጥራት ያለውና በጣም ርካሽ ከመሆን ግዴታ ጋር።

- እንግዲያውስ አልፌአለሁ፣ቦርሳው ይኸውና ተቀበል።

- በጣም ድንቅ ነው፣ፈተናውን አልፈሃል። ይህም አንዳንድ ጊዜ እውነታን በአእምሮአችን ብቻ ላንገነዘብ እንደምንችል የሚያመለክት ነው።

- ይሁንና ተጨባጩ እውነታ ከአእምሮ እውነታ ጋር የማይጻረር እንደ መሆኑ፣እውነታ ከአእምሮ ጋር የሚቃረን መሆን አይችልም፤አለበለዚያ ከሁለት አንዱ እውነታ አይደለም።

- ልክ ነህ፤የረቀቀ ልዩነት አለ፤ታድያ ፈላስፋው ማነው? !

- እባክህን ዛሬ ቶምን ከቤቴ አባርሬ አስቀይሜዋለሁ፤ይቅርታ ጠይቄው ይቅር ብሎኛል። በነገራችን ላይ ነገ ከርሱ ጋር ቀጠሮ አለኝ።

- ከቤትህ አባርረህ ይቅርታ ጠየቅህና ይቅር አለህ ! ይህ የመጠቀ ስነ ምግባር ነው፣ምስጉን ጠባይ ነው። ቶም በዚህ ፍጥነት እዚህ ደረጃ ይደርሳል ብዬ አልጠበኩም ነበር !

- ምን ማለትህ ነው?

- እንደ ነገርከኝ ቶም መሻሻልን እያሳየ ነው፤ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ከወራዳነት ወደ ምጡቅ የስነ ምግባር ደረጃ በፍጥነት መነሳት አይችልም።

- በሆስፒታሉ ከተዋወቃችሁ በኋላ ከቶም ጋር አልተገናኘህም ነበር?

- ከአንድ ጊዜ በላይ ተገናኝተናል።

- ከአንድ ጊዜ በላይ?!

- አዎ፣እውነቱን ለመናገር ተመችቶኛል፣እኔም የተመቸሁት ይመስለኛል።

- እንዴት መዘንከው?

- ብልህ፣አስተዋይ፣በትልቅ የሽግግር ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ ሰው ነው።

- ከዬት ወዴት ነው ሽግግሩ?

- ከነበረበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ሁኔታ እየተሸጋገረ ነው።

- የተሻለ ሁኔታ ምንድነው?

- አንተ የተሰማራህበት የመታደልን መንገድ ፍለጋ ሊሆን ይችላል።

- እኔ አላገኘሁት . . እርሱ ያገኘዋል? !

- አንተም እንደሱ በከፍተኛ የሽግግር ጊዜ ውስጥ አይደለህም እንዴ? እንዳያገኝ የምትፈልግና የቀናህበት ትመስላለህ !

- ዋናው ነገር ከርሱ ጋር ያለኝ የነገው ቀጠሮ ምን መልክ መያዝ አለበት?

- እንደ ተለመደው መሆን አለበት።

- የተለመደው ምንድነው?

- ከኔ ይልቅ አንተ ታውቀዋለህ።

- የተለመደው ስለላፉት ንባቦችና ውይይቶች ይጠይቀኝና ቀጣዩን አዲስ ዙር እንጀምራለን።

- እናም የሚጠበቀውም ይህ ነው ማለት ነው።

- ስለ ተዛባውና ስለ ተበረዘው ክርስትና ከርሱ ጋር ትወያያለህ፣ ወይም ኋላ ቀሩን እስላም ስለ ማጥናት ከርሱ ጋር ትከራከራለህ ብለህ ትገምታለህ?

- አዎ ሁሉም ይሆናል የሚል ግምት አለኝ።

- ምድራዊ ሃይማኖቶችን፣አይሁዳዊነትንና ክርስትናን በተመለከተ እንዳደረኩት ሁሉ ሚዘናዊ በሆነ ተመሳሳይ ሁኔታ እስላምንም ለማጥት ወደ ቶራ ቦራ ተራሮች ልጓዝ? አደም ምን ነካህ?

- እህህ፣አዎ . . ምንም አልነካኝም፣ሌሎች ሃይማኖቶችን ለማጥናት እንደተጓዝክ ሁሉ እስላምን ለማጥናት መጓዝን አንተ እንዳልከው የፍትሐዊነትና የሚዘናዊነት ግዴታ ነው . . እህህ፣ይሁን እንጂ የግድ ወደ ቶራ ቦራ አይደለም።

- ሙስሊም ነኝ ብዬ አስመስዬ መሄድ ካልሆነ በስተቀር ወደ መካ መጓዝ እንኳ አልችልም።

- በውሸት ወደ መታደል መንገድ እደርሳለሁ ብለህ ታስባለህ? !

- እስላም ውስብስብ ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ? ካቶሊክ ሳልሆን ወደ ሮም ሄጃለሁ፤ሌላው ቀርቶ ኤቲስት እንኳ ብትሆን ወደ ቫቲካን መግባት ትችላለህ።

- ማለት የፈለከው ይገባኛል፤ግና አንድ የመካ ነዋሪ የሆነ ሰው ለመግቢያ ቪዛ የሚጠየቁትን ነገሮች ሳያሟላ ወደ እንግሊዝ መግባት ይችላል?

- እኔም ማለት የፈለከው ገብቶኛል፤ግን ጉዳዩ የተለያየ ነው።

- ምንም ልዩነት የለውም፣የመግቢያ መመዘኛዎችን ሳታሟላ በዓለም ላይ የትም ቦታ መግባት አትችልም። ምንም የሌለው ደሃ ወደ መታደል ሬስቶራንት ገብቶ እኛ እንደበላን መብላት ይችላል?

- ትክክል ነው . . ግና ሙስሊም የመሆን ግዴታ ላይኖርብኝ ይችላል።

- ማን ያውቃል፣ሊኖርብህ ይችል ይሆናል።

- ዛሬ ደግሞ በጣም የተለየህ ሰው ሆነሃል፤ወደ ካፌቴሪያው ተቃርበናል፣በቅርቡ ግን ካንተ ጋር ቀጠሮ ይኖረኛል።

- እህህ፣በደስታና በጉጉት ነው ስልክህን የምጠባበቀው . . አለዚያም ቶራ ቦራ እንገናኛለን።

ጭንብሉ ሲወልቅ (3)

ጆርጅ በቀጠሮው መሰረት ወደ ቶም ሲሄድ ክለኒኩ ተዘግቶ አገኝ፤በሩን አንኳኳና ቶም ከፍቶለት ሞቅ ካለ አቀባበል ጋር ተቀበለው።

- በል ግባ . . አዝናለሁ በራድ ያስነሳው አውሎ ነፋስና ችግሮቹ ጋብ እስኪሉ ድረስ ክሊኒኩ ተዘግቷል። በራድ ሁሉንም ግለሰባዊ፣ሞያዊና መንግስታዊ ባለ ድርሻዎችን አሁንም እያነሳሳብኝ ነው።

- ምን ማድረግ አሰብክ?

- አላወኩም፣እዚያም አለ እዚህ መፈታቱ አይቀርም።

- ለምን አትደራደርም?

- በምን ላይ ነው ከርሱ ጋር የምደራደረው?

- እኔ እንጃ፣ዋናው ነገር ከሸርና ተንኮሉ መገላገል ነው።

- እርሱ የሚፈልገውን ከመቀበል ሸርና ተንኮሉ ይመረጣል። በጣም የሚገርመው አብዝቶ ቢያስቸግረኝም፣የሰጠኝ አገልግሎትም ትልቅ ቢሆንም፣ቀደም ሲል ከነበረው አሁን በጣም ደስተኛ ነኝ !

- ሕይወት በተቃርኖና በአስደናቂ ነገሮች የተሞላች ነች። ዝሙት የሚፈጽም መነኩሴ፣ገበናውን የማይሸፍን የተራቆተ ነብይ፣ገዳይ የሆነ አምላክ፣ይህ ሁሉ ሆኖ ግን መቃወምና መተቸት አይፈቀድም !

- ይህን ትተን ወደ ጉዳያችን እንግባና በግልጸኘነት የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን እንዴት አገኘሃት?

- በግልጸኝነት እውነቱን ተናገር ካልከኝ የሰው አእምሮ ሊቀበለው በማይችል ሁኔታ ላይ ነው ያገኘኋት !

- ምናልባት ይህ ሊሆን የቻለው ፕሮቴስታንት በመሆንህ ይሆናል !

- የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያንም በብዙ ነገር ተመሳሳይ ናት። ችግሩ በዚህ ወይም በዚያኛው ነው የሚል እምነት የለኝም ችግሩ . .

- ችግሩ ምኑ ላይ ነው?

- በግልጽ ለመናገር ችግሩ ጣዖት አምላኪነት ነው።

- ጣዖታዊነት? ! ባዕድ አምልኮ? !

- ይህን ማሰብ በጣም ጎድቶኛል፣እውነታው ግን ይኸው ነው። የጳጳሳዊ ሥርዓት ጣዖታዊነት፣የሥላሴ እምነት ጣዖታዊነት፣የቅርጻ ቅርጽና የሥዓሎች አምልኮ ጣዖታዊነት የ . . ጣዖት አምልኮ . .

- የችግሩ ምንጭና መሰረት ራሷ ቤተከርስቲያኗ ናት ማለት የፈለክ ትመስላለህ?

- አይደለም፣ተጨባጭ የሆነ እውነተኛ ችግር ያለው ብሉይና አዲስ ኪዳንን አጠቃሎ በያዘው በራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። ይህን ቋጠሮ ለመፍታት ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የታያት መፍትሔ ከቤተ ክርስቲያኗ መነኮሳትና ቀሳውስት ውጭ ሌላው ተራ አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነብ መከልከል ነበር። ካህናቱ ብቻ ናቸው መጽሐፉን መረዳት፣ማስረዳትና ማብራራት የሚችሉት። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መፍትሔ ደግሞ ማንበብና እንዳሻቸው ተገዥ አለመሆን ነው።

- የረቀቀ ትንተና ነው። በአንተ አመለካከት የዚህ መንስኤ ምን ይመስለሃል?

- ምክንያቱ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው ወገን እንዳሻው የለዋወጠውና እንደ መሰለው ያሻሻለው መሆኑ ነው። ከዚ በኋላ ቀሳውስት በየዘመኑ እየተሰበሰቡ በተደጋጋሚና በቋሚነት ሲለዋውጡትና ሲያሻሽሉት መኖራቸው ነው። በመሆኑም አእምሯዊና ሎጂካዊ እውነታዎችን የሚጻረረውና እርስ በርሱ የሚፋለስ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ ቃሉ ሆኖ መቀጠል አልቻለም።

- ወንጌል በኢየሱስ ዘመን እንዲጻፍ ለምን አልተደረገም ነበር?

- በዘመኑ ክርስቲያኖች በከፍተኛ ጭቆና ውስጥ የነበሩ ተሳዳጆች ስለነበሩ ሊጻፍ አልቻለም። አዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት በኋላ ረዥም ዘመናት ቆይቶ ከታሪክ አንጻር በውል በማይታወቁና በማንነታቸው ላይ ከስምምነት ባልተደረሰ ግለሰቦች አማካይነት ነበር የተጻፈው። የተጻፈበት ቋንቋም ኢየሱስ ካስተማረበት ቋንቋ የተለየ ሌላ ቋንቋ ነበር። ዋናው ነገር ችግሩ ስር ሰደደና ፈጽሞ ሊፈታ የማይችል ቋጠሮ መሆኑ ነው። ለዚህም ነው በተለያዩ ቅጂዎቹ ውስጥ ብቻ ሳሆይን በራሱ በአንድ ተመሳሳይ ቅጂ ውስጥ እጅግ የበዙ መፋለሶችና የርስ በርስ ግጭቶች የሚስተዋሉት። አንዱ ትርጉም ከሌላው፣አንዱ እትም ከሌላው የሚጋጭ፣ከሰው ልጅ አእምሮ፣ከሎጂክ፣ከተጨባጭ እውነታና ከሳይንስ ጋር የሚጻረረውም በዚህ ምክንያት ነው . .

- ይኸ በቂ ነው፤ግና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጫን ያልክ ትመስላለህ !

- ፈጽሞ አልተጫንኩም፤እመነኝ እውነቴን ነው የምነግርህ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተገዥ ለመሆንና በርሱ ለመመራት ጥረት ባደርግም አልቻልኩም !

- እንዴት? አብራራልኝ።

- ሁለት ምሣሌዎችን ልስጥህ ፦ አንደኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው ሁሉ አላምንም፤እዚያ በሰፈረው ሁሉ ማመን ማለት አእምሮዬን ውድቅ አድርጌ አውልቄ ማስቀመጥ ማለት ነው። አእምሮዬን ውድቅ ካደረኩ ደግሞ ምንም መረዳት አልችልም ማለት ነው።

- ጥሩና ተጨባጭ የሆነ ፍልስፍና ነው . . ድንቅ እሳቤ ነው።

- ሁለተኛው ደግሞ ፦ አእምሮዬን ውድቅ አድርጌ ለመረዳትና ለማመን ብወስን እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እኔ ለአንተ አልሆንም ይለኛል !

- እንዴት ለአንተ አልሆንም ይላል? አብራራው።

- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረው የኢየሱስ ቃል ፦ ‹‹ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።›› አይደለም የሚለው? እናም እኔ እስራኤላዊ ስላልሆንኩ ኢየሱስ በጭራሽ ለኔ የተላከ አይደለም።

- ስለዚህ አንተ ክርስቲያን አይደለህማ?!

- ሊሆን ይችላል፣አውነቱን ነው የምልህ አላውቅም . . በአንተ ምክንያት ኤቲስት እንዳልሆን እሰጋለሁ!

- ኤቲስት እንድትሆን ቀደም ሲል የዘየድኩት መላ ይህ ነበር፤ተሳክቶልኝ እንዳይሆን እፈራለሁ። አሁን ግን ከነበረኝ አቋም ሙሉ በሙሉ ተለውጫለሁ። ቢያንስ ኤቲዝምን በሚመለከት ከአንተ የበለጠ ዕውቀት ያለኝ ከመሆኑ አንጻር፣ከመሰል ጉዳዮች ለመገላገል የሚደረግ ሽሽት እንጂ የምር የሆነ ኢአማኝነት አለመኖሩን ደጋግሜ አረጋግጥልሃለሁ። የከፋ ብልሹ ሕይወት ለመምራት ወደ ኤቲዝም፣አስካሪ መጠጥ፣ዝሙትና ወይም ሌላ ማንኛውም ነገር መሸሽ ማለት ነው። ሽሽቱ ውስጣዊ አውነታ ከመሆን ይልቅ ከራሱ ከእውነታ የሚደረግ ፍርጠጣ ነው።

- ልክ ነውህ፣እያዘንኩ የዘየድከው መላ የያዘልህ ይመስላል፤ወደ መታደል መንገድ የመድረስ ተስፋዬ እንዳይጨልም ስጋት አለኝ።

- ምናልባት ባለማወቅ ሳንመረምረው ወይም ሳንረዳው ያለፍነው ነገር ሊኖር ይችላል። ለማንኛውም ሳናጠናቅቅ ውሳኔ ላይ ላለመድረስ ተስማምተናል።

- ሳንመረምረው ወይም በደንብ ሳንረዳው የዘለልነው ነገር ሊኖር ይችላል ስትል ምን ማለት ነው?! ይህማ ራሱ የካቶሊኮች ሎጂክ ነው።

- በተወሰነ ደረጃ ትክክል ነው፤ይሁንና አእምሮና ሎጂክ እኛ የሳትነውን ሊቀበሉ ወይም ቢያንስ እኛ ለስህተት ልንጋለጥ አንችልም?

- ልክ ነው አእምሮ ያንን ሊቀበል ይችላል ብቻ ሳይሆን የዚህ ተቃራኒ ተቀባይነት የለውም። ሁልጊዜ ትክክለኛው እኔ ነኝ ብሎ ማሰብ ራሱ ከአእምሮ ጋር የሚጻረር ነው።

- እህህ፣በጀ . . እናም ካቶሊካዊነት ከሰው ልጅ አእምሮ ጋር ይጣጣማል ማት ነዋ ! . . ዋናው ነገር ሳናጠናቅቅ ውሳኔ ላይ ላለመድረስ ተስማምተናል።

- እንደ ልማድህ እስላምን ማጥናት እንጀምር ለማለት ይህ መንደርደሪያ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

- በትክክል ነው . . ይህንኑ ነው የምልህ፤እንድያውም እኔ በበኩሌ እስላምን ማጥናት ጀምሬአለሁ። በነጻ አእምሮ ያለ ምንም ቅድመ ውሳኔ ለማጥናት ከራሴ ጋር እየታገልኩ ነው። እኔም ካንተ ጋር በመታደል መንገድ ፍለጋ ላይ መሰማራቴን ነግሬህ የለም?

ጆርጅ አንደኛውን እጁ በሌላኛው መታና ፦

- ማለቂያ የሌለው መንገድ የጀመርን መሰለኝ።

- ከትናንት አንስቶ የሙስሊሞችን ቅዱስ መጽሐፍ ቁርኣንን ማንበብ ጀምሬአለሁ።

- እህህ፣እኔም ብሆን አደም እንዳነበው ሊያሳምነኝ ሞክሯል፣ግን መልስ አልሰጠሁትም፤ይሁን እንጂ ጊዜ እያባከንኩ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።

- የእንግሊዝኛ ትርጉሙን የሰጠኝ አደም ነው . . ካነበበ እስላምን ሊቀበል ይችላል ብሎ ይጠብቃል መሰለኝ።

- እስላምን እንድትቀበል ይፈልጋል! ብትቀበል እርሱ ምን ይጠቀማል?

- ሰዎች ሁሉ ወደየራሳቸው ሃይማኖቶችና አመለካከቶች ነው ጥሪ የሚያደርጉት።

- ማለት የፈለከው አልገባኝም።

- ምኑ ነው ያልገባህ? አደም ወደራሱ ሃይማኖት ሊያስገባኝ ይፈልጋል፤ግልጽ ያልሆነልህ ምኑ ነው?

- አደም ሙስሊም ነው ! ! !

- አዎና፣ዐረብ መሆኑን ገጽታውና ተክለ ሰውነቱ ይናገር የለም? ይህን አታውቅም ነበር?

- አዎ አላውቅም ነበር፤ስሙ የዐረብ ስም አይደለም፣የሕንድ ዝርያ ያለው ካቶሊካዊ ነው የሚል ግምት ነበረኝ፣አደም እያሾፈብኝ እንዳይሆን ፈራሁ።

- ስሙ እንኳ የመላው የሰው ልጆች አባት ስም ነው፣እኛ ዘንድም አለ፣ዐረቦች ዘንድም እንዲሁ የተለመደ ስም ነው። ያሾፍብኛል ያልከው ገን ትክክል ኤመስለኝም፤ዋሽቶህ ያውቃል?! ጠይቀኸው እውነት ያልሆነ ነገር ነግሮህ ያውቃል?

- ካንዴም ሁለቴ ጠይቄው መልስ አልሰጠኝም። ዋናው ነገር ወደ እስላም ሊወስደኝ ከኋላ እየገፋፋኝና ወደዚያ ሲመራኝ ኖሯል? ሞኝ ተላላ መሆን አልፈልግም።

- ወደራሱ ሃይማኖት ቢጠራህ ሞኝ ተላላ ትሆናለህ?!

- አልሆንም ግን . . እፈራለሁ።

- ወደ እስላም መግባትን የምትፈራ ካልሆንክ በስተቀር ምንም የሚያስፈራህ ነገር የለም?!

- አዎ ያለ ዕውቀትና ያለ ማስተዋል ወደ አንድ ነገር መነዳትን እፈራለሁ።

- ቀሳውስቱም ሆኑ ሌሎች ሊነዱህና ሊያሳምኑህ ያልቻሉትን አደም ነድቶህ እስከያሳምንህ ድረስ ደካማ ሆነህ ነው?! ወይስ አደም በከፍተኛ ደረጃ ጠንካራ በመሆኑ አስፈርቶህ ነው?

ጆርጅ በእጆቹ እያመላከተ ፦

- ሁለቱም አይደለም፤ግን ለምንድነው እንደዚህ የምታናግረኝ? !

- በሁሉም ሃይማኖቶች ላይ አንበሳ ከመሆን እስለምን ወደምትፈራ ጥንቸል ስለተለወጥክ።

- ፈሪ አይደለሁም፤እስላምንም አጠናለሁ፣እመረምረዋለሁም . . ስለኔ መለወጥ ስትናገር ትዝ አለኝ፣አደም ስለ አንተ መለወጥና ሽግግር ይጽፋል።

- ስለኔ መለወጥና ሽግግር? ! ከበራድ ጦስ ገና ሳልገላገል ይኸኛው ደግሞ ምን ጽፎ ይሆን?

- ወደ ፌስቡክ ገጹ ግባና የጻፈውን አንብብ።

- እሽ አደርጋለሁ፣ይህን ተወውና ዋናው ነገር ከርሱ በፊት የነበሩትን እንዳጠናሃቸው ሁሉ እስላምን በክፍትና ነጻ አእምሮ ታጠነዋለህ?

- አዎ አጠናለሁ፣ተስማምተናል።

- ከርሱ በፊት የነበሩትን እንደተቸህ ሁሉ ትተቸዋለህ?

- አዎ፣እንዲያውም ይበልጥ የጠነከረና የሰላ ትችት።

- ይኸማ የምናወራው በክፍትና ነጻ አእምሮ ማጥናት አይደለም። ይበልጥ የጠነከረና የሰላ ትችት ማለትህ ከቅድመ ሁኔታ ባልጸዳ ዝግ አእምሮ ማለት ነው። ምድራዊ ሃይማኖቶችን፣አይሁዳዊነትንና ክርስትናን ባጠናህበት መንገድ ክፍት በሆነ ነጻ አእምሮ አጥናው።

- እናም ሳልተቸውና የሰላ ሂስ ሳልሰነዝርበት እንድሰልም ነው የምትፈልገው? !

- ከቅድመ ውሳኔ ነጻ በሆነ ሚዘናዊ አእምሮ ለእውቀት ትኩረት ሰጥተህ ካጠናኸው በኋላ፣ልክ አይሁዳዊነትን፣ክርስትናን ወይም ቡድሂዝምን እንደተቸሃቸው ሁሉ በሙሉ ልብ እንድትተች ነው ፍላጎቴ።

- ባልካቸው እምነቶች ላይ ግን ጠንካራ ትችት አቅርቤ ቢያንስ ለኔ ስህተት ሆኖ የታየኝን ሁሉ ነው ያጋለጥኩት።

- እኔ የምልህም ይህንኑ ነው፣የነሱን ስህተተኛነት እንዳጋለጥከው ሁሉ የእስላምን ስህተተኛነትም አጋልጥ። መማርንና ውሳኔን ከዚያ በኋላ ማድረግ ምርጫዬ ቢሆንም ያላሰብነውና አእምሯችን ውስጥ የሌለ ነገር ሊገለጥልን ይችል ይሆናል።

- የእስላምን ስህተተኝነትና እርስ በርስ መጣረሱን ካጋለጥን በኋላ ምንድነው የምንሆነው? ወደ ኤቲዝም ነው የምንመለሰው? !

- እኔ እንጃ ! የማውቀው ነገር ቢኖር እንዳልኩህ ሁሉ ያልጠበቅነው ነገር ሊታየን ይችል ይሆናል የሚለውን ነው።

- ቁርኣንን ማንበብ እንደመጀመርህ እስካሁን እንዴት አገኘኸው?

- ትናንተ ነው የጀመርኩት፣እጅግ በጣም ትንሽ ነገር ብቻ ነው ያነበብኩት፣ግን አስደሳች ነው።

- እህህ፣ኦህ መወስወስ የጀመርኩ መሰለኝ፣አንተም ሙስሊም እንዳትሆን እሰጋለሁ።

- አይደለሁም . . እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፣እኔ ሙስሊም አይደለሁም።

- ታድያ አንተ ምንድነህ? !

- እኔ እንዳንተው ነኝ፤እኔ እንጃ በፍጥነት የምገለባበጥ ሆኖ ይሰማኛል።

- አደምም ስለ አንተ ሲጽፍ ያለው በለውጥ ሂደት ውስጥ መሆንህን ነው።

- ምናልባት ያለው ነገር እውነት ሊሆን ይችላል፣ዛሬ ስለኔ የጻፈውን አነባለሁ። ለመሆኑ ፌስቡክ ላይ እንዳገኘው ሙሉ ስሙ ማነው?

- ኢሜይሉ ስላለህ ሙሉ ስሙን ደብዳቤዎቹ ውስጥ ታገኛለህ፣በዚያም የፌስቡክ ገጹን ማግኘት ትችላለህ።

- መልካም፣ዋናው ነገር እስላምን በነጻ አእምሮ እንመረምራለን።

- እናም ወደ አፍጋኒስታን ወይም ወደ ቶራ ቦራ ያለ ቅድመ ውሳኔ በነጻ አእምሮ እንሄዳለና !

- ወደ ሙስሊምነት እንደምትለወጥ እርግጠኛ የሆንክ መስለህ ለምን እንደምትናገር እኔ እንጃ።

- እየቀለድኩብህ ነው።

- በነገራችን ላይ በካቶሊካዊነት ላይ ባለህ አቋም ምክንያት ከካትሪና ጋር አልተወዛገባችሁም?

- አልተወዛገብንም፣እጅ ሰጠች መሰለኝ።

- ወደ ቤተ ክርስቲያን በሄድኩበት ጊዜ እውነተኛ አምላኪና ለኢየሱስ ጥልቅ ፍቅር ያላት መሆኗን መገንዘብ ችያለሁ።

- የኔም ስሜት ይኸው ነው። ከካቶሊካዊነትና ከእምነቶቹ በኩል ያጋጠማት አስደንጋጭ ሁኔታ ግን ብርቱ ነው . . ሮም ውስጥ ከአንድ ሙስሊም ጋር በተገናኘን ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤና የመፍረክረከ ሁኔታ ነበር ያሳየችው !! እምነትና እርግጠኝነትን ያስተማራት ቄስ ለኔ ጥያቄዎች መልስ መስጠት እንዳልቻለ ስታውቅም እንደዚሁ ተፍረክርካሎች !

- በሃይማኖት አጥባቂነቷ በጣም አደንቃታለሁ።

- ታድያ ወደ ካቶሊክነት ለምን አትለወጥም?

- እርስ በርስ መጋጨትንና ሳይንስን መጻረር በጣም ስለምጠላ።

- እህህ፣እንግዲያውስ ወደ እስላም ግባና ወደ ቶራ ቦራ ተራሮች አቅና።

- እስላምን አሳማኝ ሆኖ ባገኘውና የመግቢያ መመዘኛው ወደ ቶራ ቦራ መሄድ ቢሆን እንኳ በእርግጠኝነት አደርገዋለሁ።

- ጽኑ ቁርጠኝነትን እወዳለሁ፣ግና መውጫ መንገዱ አይታየኝም።

- እኔም እንዲሁ ነኝ፤ይሁን እንጂ በድንገትም ቢሆን መገለጹ አይቀሬ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ ነኝ፣እንዴት ብለህ አትጠይቀኝ፤በቃ እርግጠኛ ነኝ።

- እኔም ተመሳሳይ የሆነ የእርግጠኝነት ስሜት ነው ያለኝ።

- ለላክንልህ መልሶች እንዳስለመድከን ማጠቃለያ ለምን አልተላከለንም?

- ልክ ነህ . . በአንተ ፎቶዎች ምክንያት ትናንት ኢሜይሌን አላየሁም ነበር። ዛሬ ሁሉንም አይና የአደም መልሶች ሙስሊም መልሶች መሆን አለመሆናቸውን ልብ ብዬ ለማየት እሞክራለሁ።

- ቀደም ሲል ከላካቸው መልሶቹ ውስጥ ግልጽ አልነበረም?

- ሊሆን ይችላል፤ሆኖም ልብ አላልኩም ነበር። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ነገሮችን፣ሁነቶችን፣ውይይቶችንና መረጃዎችን እርስ በርሳቸው አዛምጄ በማነጻጸር ያለ መመልከት ችግር እንዳለብኝ የጻፈው።

- ነገሮችን አዛምዶና አነጻጽሮ መመልከት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

- አነጋገርህ በትክክል ከአደም አነጋገር ጋር ተመሳሳይ ነው፤አድናቂው ሳትሆን አልቀረህም።

- አቋሙ ይህ መሆኑን አላውቅም ነበር፤እውነቱን ለመናገር አድናቆቴ ከዚህ አቋሙ ይበልጥ ለውስጣዊ ሚዘናዊነቱ ነው።

- ለውስጣዊ ሚዛናዊነቱ ያለህን አድናቆት እኔም እጋረሃለሁ፤የአመለካከቱ አድናቂም ነኝ። በነገራችን ላይ በራድ ቢሮህ ውስጥ የተከለውን የስለላ ሲስተም አስወግደሃል?

- አዎ፣ከበራድና ከጣጣው ለመገላገል ያለኝን ጉጉት ልነግርህ አልችልም፤ከዚያ አስቄያሚ የቀድሞ ሕይወቴ ጋር ያስተሳስረኛል!

- በቅርቡ ትገላገለዋለህ፤እንድሄድ ትፈቅድልኛለህ??

- አዎ ትችላለህ፣የዛሬውን ጨርሰናል፣በኔ እምነት በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ከሆኑ ቀጠሮዎቻችን ይህ ዋነኛው ነው።

- እናም እስላምን ማጥናት እንጀምራለን፣ወደ ሥራ እመለስና ካኽን አገኘዋለሁ፣እንዴት እንደምጠላቸው ልነግርህ አልችልም!

- ምኖቹን ነው የምትጠላቸው?

- እሰላምና ካኽን።

- እንደገና ወደ ኢሚዛናዊነቱ ተመለስን!

- ኦህ . . ልብ አላልኩም ነበር፣ማለት የፈለኩት ካኽንና ሥራውን ነው።

ጭንብሉ ሲወልቅ (4)

ጆርጆ ማታ ወደ ቤቱ ከደረሰ በኋላ ኢሜይሉን ከፈተ . . ሦስቱ መለኮታዊ መጽሐፎችን በንጽጽር እንዲመለከቱ ለላከላቸው መልእክት ከባልደረቦቹ የተላኩትን ምላሾች አገኘ

ሌቪቁርኣንን አላነበብኩትም፣ይሁንና ግን ሦስቱ ሃይማኖቶች በጣም ይመሳሰላሉ የሚል ግምት አለኝ።

ሐቢብሁሉም ከእግዚአብሔር ዘንድ ከመሆናቸው አንጻር ተመሳሳይ ናቸው። ቁርኣን ግን ተአማኒነት ባለው መንገድ በጽሑፍ ተጠናቅሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ በመሆኑ ይለያል። ይሁን እንጂ በጽሞና አላነበብኩትም።

አደምበመሰረቱ ሁሉም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፉ ናቸው፤የሚያሳዝነው ግን ብሉይ ኪዳንና ወንጌሎች የተዛቡና የተከለሱ መሆናቸው ነው።

ቶምቁርኣንን ስላላነበብኩት ከኦሪትና ከወንጌል ጋር አላነጻጸርኩም።

ካትሪናብሉይና አዲስ ኪዳኖች ከእግዚአብሔር የተላለፉ ናቸው። እሰካሁን ያላነበብኩት ቢሆንም ቁርኣን ግን እንደዚያ አይመስለኝም።

ጃኖልካትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርኣንን ማንበብ ጀምሬለሁ፤በምን እንደሆነ ባላውቅም ከብሉይ ኪዳንና ከአዲስ ኪዳን ይለያል የሚል አስተያየት አለኝ።

ጆርጅ የአደምን ምላሽ ከወትሮው በተለየ ትኩረት አነበበ፣የሚጠቀመውን የአጻጻፍ ስልት አስተዋለ

. .
ሁሉም
ወዳጆቹ ቁርኣንን እንዳላነበቡ ወይም በጨረፍታ ብቻ ያነበቡ መሆናቸውን በግልጽ ሲናገሩ ይህንን ያላለው አደም ብቻ ነበር። ሁሉንም መልሶች ለሁሉም ወዳጆቹ መልሶ ከላከ በኋላ የሚከተለውን ስድስተኛ ዙር ጻፈላቸው

 

‹‹ስድስተኛው ዙር ፦ ከናንተ መካከል ቁርኣንን አንብቦ በመረዳት በተረጋገጠና ተኣማኒነት ባለው ሁኔታ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ አለመተላለፉን፣መዛበትና መከለስ የደረሰበት መሆን አለመሆኑን መመርመር የሚችል ሰው ያድርግ። ትችታችሁን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እጠብቃለሁ።

ጆርጅ››

መልእክቱን ከላከ በኋላ በቀጥታ ለአደም ደወለ. .

- የተገናኘን ቢሆንም አሁንም ደግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ፤ነገ ይመቸሃል?

- ችግር የለውም፤የሥራ ሰዓቴ ነገ እስከ ሁለት ሰዓት ስለሆነ የሚሆነው ግን ከዚያ በኋላ ነው፣እህህ እራት አብረን እንበላለን።

- ይስማማኛል፣እኔም ነገ ወደ ሥራ የምመለስበት የመጀመሪያው ቀን ነው፤ከሦስት ሳምንታት ወዲህ የካኽን ፊት አላየሁም።

- እንግዲውስ እጠብቀሃለሁ፣ደህና ሁን።

ካትሪና ወደ

ቤት ስትመለስ ጆርጅ ኮምፒውተሩ መስኮት ላይ እንዳፈጠጠ ቁጭ ብሎ አገኘችውና ስማው ትከሻውን መታ መታ አደረገች . .

- የኔ ፍቅር በመዘግየቴ ይቅርታ፣የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመሸመት ወደ ገበያ ማእከል ሄጄ ነው። ከጉዞ ከተመለስን ወዲህ ቤት ውስጥ ምንም አልነበረም . . ግሩም ትዝታ ጥሎ ያለፈ ጉዞ ነበር።

- እውነትሽን ነው የማይረሳ ድንቅ ጉዞ ነበር፣ዋነኛው የጉብኝቱ ድንቅ ነግር ግን አንቺው ነሽ።

- ለውብ አገላለጽህ አመሰግናለሁ፣ፈጥኖ ያለፈ ጉዞ ነበር።

- ሁሉም መልካም ነገሮች የሚያልፉት በፍጥነት ሲሆን አሳዛኝ ጊዜያት ግን ረዥምና አሰልቺ ይሆናሉ። አስደሳች መጽሐፍ እንኳ አንዳንድ ጊዜ በአንዴ ተነቦ ያልቃል፣አሰልቺ መጽሐፍ ግን ብዙ ቀናት ወይም ሳምንታት እጅ ላይ ይቆያል . . ለዚህ ነው ኻሊድ የሰጠሸን መጽሐፍ በአንድ ምሽት ያነበብሽው።

- ‹‹ለኢየሱስ ያለኝ ታላቅ ፍቅር ወደ እስላም መራኝ›› የሚለውን መጽሐፍ ማለትህ ነው?! በጣም አነጋጋሪ የመሆኑን ያህል አስደሳች አልነበረም።

- ለዚህ ነው በላክሽው መልእክትሽ እንደጠቀስሽው ቁርአንን ለማንበብ የምታስቢው?

- በትክክል፤ለማንበብ ቆርጬ ትናንት የቁርኣን መጽሐፍ ገዝቻለሁ።

- እህህ . . ኦ ካትሪና ይህማ መሰረታዊ ለውጥ ነው፣ካትሪና ቁርኣንን ልታነብ ! ሙስሊም ልትሆንም ትችላለች ማለት ነው?

- አነበዋለሁ፤ሂስ ልሰነዝርበት፣እንከኑንና እርስ በርስ መጣረሱን ለማጋለጥ ዓላማ አነበዋለሁ።

- ሁላችንም ቁርአንን እንድናነብ የሚጠይቅ መልእክት ከአፍታ በፊት ለሁላችሁም ልኬ ነበር፤የሚገርም መገጣጠም ነው። እኔ የቁርአን መጽሐፉን ነገ ከአደም እወስዳለሁ።

- ለምን በተለይ ከአደም?

- መጽሐፍ ቅዱሳቸው ስለሆነ።

- አደም ሙስሊም ነው?! ካቶሊክ ነው ብለህ አልነበረም?!

- እውነቱን ለመናገር ሙስሊም መሆኑን ሳውቅ ነገሩ ለኔም ያልጠበኩት አስገራሚ ሆኖብኛል። በተለይ ለዚሁ ጉዳይ ብዬ ነገ ከርሱ ጋር ቀጠሮ ይዣለሁ።

- በአደም ደስተኛ ብሆንም ሙስሊሞች ግን ፈጽሞ አያስደስቱኝም። ካቶሊክ ነው ብዬ ስላሰብኩ ይሆናል የተመቸኝ።

- የምትናገሪው ነገር ከፍትሐዊነትና ከስነ አስተሳሰብ ጋር አይጣረስም? እምነቱን ትተን ማንነቱን መመዘን አይደለም ተገቢው?

- አይደለም፤ከመመዘኛ መስፈርቶች ሁሉ ዋነኛው ሃይማኖት ነው። አንድን አማኝ ካቶሊክ ከአንድ አሸባሪ ሙስሊም ጋር በአንድ ዓይን እንዳይ ነው የምትጠብቀው?! ምሁርን ከማይም በተለየ ዓይን እንመልከት የለም? በመልካም ስነ ምግባር ለታነጸው ከወራዳው በተለየ አክብሮት እንቸር የለም? እናም መልካም ስነ ምግባር፣ዕውቀትና ሃይማኖት የመመዘኛ መስፈርት መሆናቸው ጥርጥር የለውም።

- ሊሆን ይችላል፤ይህ ትክክል የሚሆነው ግን ልክ እንደ መልካም ስነ ምግባርና እንደ ዕውቀት ሁሉ ሃይማኖትሽም ምንም ጥርጣሬ የሌለበት እውነት ቢሆን ኖሮ ነው። አይመስልሽም?

- በተወሰነ ደረጃ፤ይሁንና አንተ ዘንድ ሃይማኖት ከመልካም ስነ ምግባርና ከላቀ እውቀት ያነሰ ደረጃ አለው ማለት ነው?! . . እህህ፣ጆርጅ አሁንም የኤቲዝም ብክለት ያለብህ ትመስላለህ።

- ምናልባት፣ግና ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ለሳሊና ለማይክል ለምን ነበር የፈራሽው? አንቺም የኤቲዝም ብክለት አለብሽ ማለት ነው?

- ምንም የፈራሁት ነገር አልነበረም፤አንተ እንዳው የሆነ ነገር ታስብና ራስህን ታሳምናለህ፤ደሞስ ምኑን ነው የምፈራው?

- እየቀለድኩ ነው፤ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ለልጆቹ ስጋት አላደረብሽም፣ሙስሊሙ የሰጠሸን መጽሐፍ ማንበብም አልፈራሽም። ለመሆኑ መጽሐፉ የታለ? እኔ አላነበብኩትም።

- አንደምታውን በሚገባ እረዳለሁ፤ማንም ሰው ቢሆን የሚሰማው፣የሚያነበውና የሚያስበው ነገር ተጽእኖ ያሳድርበታል።

- አንድ ጥያቄ እጠይቅሻለሁ፣በግልጽነት እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ።

- ጠይቅ . .

- የካቶሊክ እምነትን መተው ትችያለሽ?

- ካቶሊካዊነት እተዋለሁ?! ትቼው ወዴት ልሄድ?

- ወደ ፕሮቴስታንት፣አይሁዳዊነት፣እስላም ወይም ወደ ማንኛውም እምነት።

- ከወር በፊት ጠይቀህ ቢሆን ኖሮ ያለ ምንም ማመንታትና በሙሉ ልብ አልተውም ባልኩህ ነበር . . አዝናለሁ አሁንም ቢሆን አልተውም እለሃለሁ። ግና እምነቴ ከቀድሞው ለምን በጣም እንደ ደከመ አላውቅም። አንተም በጥያቄዎችህ የምታፋጥጠኝ ብትሆንም ከራሴ ጋር ይበልጥ ግልጽ እንድሆን አድርግሀኛል።

- አንቺ ለኔ የእምነት ተምሳሌት ነሽ። ያልሽው ለውጥ ምናልባት እምነትሽ ለመጨመሩ ማስረጃ ሊሆን ይችላል። እኔ ፕሮቴስታንት እንጂ ካቶሊክ ባልሆንም የእምነትሽ ልባዊነት ይሰማኛል፣አንቺ ለኔ የመንገድ ፋና ነሽ።

- አንተ ነህ እንጂ የእውነት ፍለጋ ተምሳሌት፣ደሞም ትደርስበታለህ፤ጆርጅ እወደሃለሁ።

ጭንብሉ ሲወልቅ (5)

ጧት

ላይ ጆርጅ ተለይቶት ወደ ነበረው ሥራው ሄደ፣ካኽን ማግኘት ስላልፈለገ በቀጥታ ወደራሱ ቢሮ አመራ . . በካኽ ላይ የጥላቻ ስሜት አድሮበታል። ይሁዲ በመሆኑ፣በስግብግብነቱ፣ በወራዳ ጠባዩ ምክንያት ይሆን ወይስ ሁሉንም አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ? የሚያውቀው ነገር ቢኖር ሃይማኖተኛ አይሁዳዊት ከመሆኗ ጋር ሌቪን የሚወዳት መሆኑን ነው . . በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት
ማንንም
አይጠላም፣የሚጠላው
የሃይማኖቶችን መፋለስና አፈተረቶቻቸውን ብቻ ነው።

ለማንኛውም ግን ካኽን ማግኘት የግድ ነው፤በመሆኑም ካኽ መምጣቱን አውቆ ከመደወሉ በፊት ሊደውልለት ይገባል. .

ስለ
ካኽ በማሰላሰል ላይ እያለ ለኩባንያው

ላበረከተው የላቀ አገልግሎት

ጠቀም ያለ ጉርሻ የተፈቀደለት መሆኑን የሚገልጽ ወረቀት ጠረጴዛው ላይ ከፊቱ ተቀምጦ ተመለከተ። ወረቀቱ የፈጸማቸውን ስኬታማ ሥራዎች፣በሕንድና በቴል አቪቭ ያደረጋቸውን የውል ስምምነቶች የሚዘረዝርና በካኽ የተፈረመ ነበር። ለካኽ የነበረውን ጥላቻ ከልክ አሳልፎ ይሆን? ወይስ መሸለሙን ሲያውቅ ለርሱ የነበረውን ገንቢ ያልሆነ አስተያት ለዘብ አድርጎ ይሆን?

የተሰጠው ጉርሻ

የበጎነቱ
መገለጫ
ይሆን?
ወይስ
እርሱ በኢየሩሳሌም ለብንያሚን ያቀረበው ዓይነት ጉቦ ይሆን?!
የቢሮ ስልኩ አቃጨለና መነጋገሪያውን አነሳ፤በሌላው ጫፍ ካኽ ነበር . .

- ሃሎ ጆርጅ፣መምጣትህን ሳውቅ ወደ ቢሮዬ ትመጣለህ ብዬ ጠብቄ ነበር፤ትመጣለህ ወይስ እኔ ልምጣልህ?

- ወረቀቶቼን እያስተካከልኩ ነበር፣ከደቂቃዎች በኋላ እመጣለሁ።

- እሽ እጠብቀሃለሁ።

ጆርጅ አንዳንድ ወረቀቶችን ሰብሰብ አድርጎ ለማስተካከል ቢችልም ካኽ ባሳየው አክብሮት የተጠመደ አእምሮውንና ሀሳቡን መሰብሰብ ሳይችል ወደ ካኽ ቢሮ አቀና። ሲገባ ሞቅ ያለ አቀባበል አደረገለት . .

- ጆርጅ እንኳን ደህና መጣህ፣ናፈቅንህ እኮ እንደምነህ ጃል? ሮምስ እንዴት ነበረች? ቴል አቪቭም ጭምር እንጂ?

- በጣም ደህና ነኝ፤ከሕመሙ ተፈውሻለሁ። የቴል አቪቩን ጉዞ በተመለከተ ሁሉንም ውሎች አጠናቅቄ ልኬላችሃለሁ። የሮሙ ጉዞ ግን ግሩም ድንቅ ነበር። እናንተስ እንዴት ከረማችሁ? ኩባንያውስ?

- የቴል አቪቩ ውል ለኩባንያው ትልቅ የስኬት እርምጃ ተደርጎ የሚቆጠር ነው። የአይሁዶች ሎቢ በብዙ አገሮች ውስጥ ስር የሰደደ ተጽእኖ ፈጣሪ ነው። ከቴል አቪቭ ጋር ውል መፈራረማችን የሁሉንም ያውሮፓ አገሮችና የአሜሪካን በር መክፈቻ ቁልፋችን ነው። በዚህ ምክንያት የሥራ አመራር ቦርዱ የገንዘብ ጉርሻ እንዲሰጥህ ወስኗል፣አይተሃል?

- ካኽ ለዚህ በጎ አስተያየትህ አመሰግናለሁ፣የተለየ ነገር አልሰራሁም፣መፈጸም ያለብኝን ነው ያደረኩት።

- መሰናክሎችን እንዴት ማለፍ እንደምትችል ሳስብ ይገርመኛል፤ድንቅ የሽያጭ ኤክሰፐርትም ነህ !

- ምንም መሰናክል አልነበረም፣ወዲያው ነበር የተፈራረምነው።

- ለርሱ በግል የሚሰጠውን ገንዘብ አልጠየቀም ነበር? !

- ጉቦውን ማለትህ ነው? ወስዷል።

- ሌላ ነገር አልጠየቀም?

- ሌላ ምን?

- ተወው፣ከሌቪ ጋር ስንት ሌሊት አደርክ? ሃይማኖተኛ ስለሆነች አንዳንድ ጊዜ እምቢተኛ መሆኗን አውቃለሁ።

- ፈጽሞ አብሬአት አልተኛሁም፤ይህን ማድረግም አልችልም።

- ብንያሚን ቆሻሻ ነው . . አላግባባት ማለት ነው?

- ቆሻሻነቱ ግን ጉቦ በመቀበሉ ነው። እንዲያግባባልኝ አልጠየኩትም። ብንያሚን ከኔ ጋር ወሲብ እንድትፈጽም እንዲያስገድዳት እፈቅዳለሁ ብለህ ትጠብቃለህ? !

- እህህ፣ዋናው ነገር ውሉን መፈረሙ ነው። አንተ እንድትደሰትና እንድትዝናና ነበር ምኞቴ፣አንተ ግን እሽ አላልክም። ባንተ ቦታ ብሆን ኖሮ ከርሷ ጋር እንጂ አላድርም ነበር፤አልማረከችህም?

- ካኽ እኔ ባለትዳር ነኝ፣በባለቤቴ ላይ ክህደት እንድፈጽም ትፈልጋለህ? እኔ መርሆዎቼን መጣስ አልችልም።

- መርህ የምትለውን ነገር ወዲያ በልልኝ። እኛ የምንጠቀምበት ከግቦቻችን ውስጥ አንዱን ማሳካት ስንፈልግ ብቻ ነው።

- ስለ መርህ ሳይሆን ስለ ሌላ ነገር እየተናገርክ ነው የሚመስለኝ፣መርህ ግን ሊጣስ አይችልም።

- ወደ ቴል አቪቭ ስሄድ ሌቪ ሁሌ ከኔ ጋር ታድር እንደነበረ ታውቃለህ? እሷም ከማንም በላይ ነው ስለ መርህ የምትናገረው።

- ሰብአዊ ድክመት እንጂ ሌላ አይደለም።

- ይህ የመርህ ፍልስፍና ነው። አንድን ዓለማ ማሳካት ስንፈልግ መርህ ነው እንላለን፤ሌላ ነገር ስንፈልግ ደግሞ የሰው ልጅ ድክመት ነው እንላለን።

የካኽ አነጋገር የጆርጅን ልቦና ነክቷል፤ትክክለኛ አነጋገር ነው። እርሱ ራሱ ለብንያሚን ጉቦ አቀብሎ በሰብአዊ ድክመት አመካኝቷል፤እናም እርሱ ራሱ ካኽ በመርህ ላይ የሚከተለውን ንድፈ ሀሳብ ተከትሎ እየሄደ ይሆን?

- ሊሆን ይችላል፤ይሁን እንጂ ፍላጎቴን እስካላረካልኝ ድረስ መርህ ለምኔ የሚለው አቋም አደገኛ ነው። መርህ የሌላት ሕይወት ከሁሉም የከፋች እኩይ ሕይወት ናት። በዚህ ሁኔታ ከእንስሳት ብዙ የተለየን አንሆንም።

- እህህ፣ይቅርታ አድርግልኝና እንስሳት ከሰው ልጆች የተሻሉ ናቸው፤ከፈለግህ መርህ በለው የማይለወጡ ቋሚ ተፈጥሯዊ ነገሮች አሏቸው።

- ልክ ነህ . . መርህና ስነ ምግባራዊ እሴት የሌላቸው ሰዎች ከእንስሳትም የከፉ ናቸው። ከሀብት፣ከወሲብና ከሥልጣን ውጭ ምንም ወደማያሳስባቸው አውሬነት ይለወጣሉ።

- የመርህ ጠበቃው፣ድንቅ ሌክቸር ነው። አሁን ይህን እርሳውና ለሥራ ተሰናዳ፤ውል ለመፈራረም ወደ ስዊድን አዲስ ጉዞ ለማድረግ ዝግጁ ነህ?

- ወደ ስዊድን አዲስ ጉዞ?

- አዎ . . ከአንድ ሳምንት ያህል በኋላ። የሥራ አመራር ቦርዱ ካንተ በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይሄድ በሙሉ ድምጽ ተስማምቷል፤ለዚህ ነው አንተ እስክትመለስ ብሎ ካንድ ጊዜ በላይ ቀኑን ያራዘሙት።

- የምን ውል ነው?

- ከሞላ ጎደል ከቴል አቪቩ የኮንትራት ውል ጋር ተመሳሳይ ነው፤የሚፈረምበት ሁኔታም በጣም የተመሳሰለ ነው።

- እንዴት? አልገባኝም !

- ካንተ ዲፕሎማሲያዊ ክህሎት ጋር ለቴክኒካል መምሪያ ኀላፊው በግል የሚሰጥ ገንዘብ ይኖራል፤ነገሩ በዚሁ ያበቃና ስምምነቱ ይፈረማል።

- የፈለከው ገብቶኛል፤እዚያ ያለው የቴክኒክ መምሪያ ኀላፊ ሌላው ብንያሚን ነው ማለት ነው። ግና ሌላ ሌቪ በስዊድን ትኖር ይሆን?

- እህህ . . ከሌቪ ጋር አልተዝናናሁም ብለህ የለም? ለምንድነው ሌላዋን የስዊድን ሌቪ የምትፈልገው? መርህስ የት ገባ?

- እንደዚያ ማለቴ አይደለም፣የሚያመሳስሉ ነጥቦችን መፈለጌ ነው።

- አዎ . . ስዊድንም ሌቪን የመሰለች አለችልህ፣ስሟ እንግሪድ ነው፤እርግጠኛ ሁን ልክ እንደ ሌቪ በጣም ውብ ቆንጆ ናት።

- መልካም፣እምቢታዬ በቆንጆዋ ምክንያት ነው ብለህ አታስብ።

- አልገባኝም።

- አልሄድም፤ችግሩን ግን ቀያይ የጭፈራ ምሽቶች አለመኖር አድርገህ እንዳትረዳ።

- ለምንድነው የማትሄደው?

- የመርህ ጠበቃ የሚል ስያሜ ሰጥተሀኝ የለም? ጉቦ ከኔ መርህ ጋር ይጻረራል።

- የመርህ ጠበቃው፣ውሉን እንዲፈርም ለብንያሚን ገንዘቡን ሰጥተህ የለም? !

- አዎ፣ግን ተሳስቻለሁ፤ካሻህ ሰብአዊ ድክመት ነው በለው።

- ግቦቻችንን ለማሳካትና ጥቅሞቻችን ለማስከበር ብቻ ነው መርህን የምንገለገልበት አላልኩህም ነበር? ምንድነው የምትፈልገው?

- ምንም አልፈልግም፤በቃ መሄድ አልፈልግም።

- በቀጣይ የሚሰጥህ ጉርሻ ያለፈው እጥፍ ይሆናል ብልህስ? የሦስት ወር ደሞዝ ያህል ነው።

- ችግሩ እሱ ሳ . .

- አሁን መልስ እንድትሰጠኝ አልፈልግም። እንድታስብበት ሁለት ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ይህን መልካም አጋጣሚ እንደማታበላሽ እርግጠኛ ነኝ።

- መልካም አጋጣሚው ምን ይሆን?

- ጉዞ፣ጠቀም ያለ ጉርሻና የሥራ እድገት።

- የሥራ እድገት? !

- አዎ፣በአዲሱ መዋቅር መሰረት - የስዊድኑን ውል ፈርመህ ከመጣህ - የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ትሆናለህ፣የኔን ቦታ ትይዛለህ። የሥራ አመራር ቦርዱ ለሥራ ክንውንህ ከፍተኛ አድናቆት አለው።

- አንተሳ? !

- የኩባንያችን ባለንብረት ለሆነው እናት ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ልሆን እችላለሁ። ረጋ ብለህ አስብበት፤ይህን መልካም አጋጣሚ እንደማታበላሽ እርግጠኛ ነኝ። የጉዞ ሰሌዳውን እንደሚመችህ ማስተካከል ይቻላል። እህህ፣መርህ ማለትም የሚሰጠውን ገንዘብ ማድረስ ወይም በአንተ ትርጓሜ ጉቦውን መስጠት ይሆናል።

- ባልሄድስ? !

- በዚህ ኩባንያ በራስህ ላይ ወንጀል የፈጸምክ ትሆናለህ። አንተን የመሰለ አስተዋይ ይህን ያደርጋል ብዬ አላስብም። እመነኝ እኔ ራሴ ለመሄድ እፈልግ ነበር፤የሥራ አመራር ቦርዱ ግን በአንተ ላይ ከፍተኛ እምነት በመጣሉ ትላልቅ ኮንትራቶችን ለመፈራረም አንተ መሄድ አለብህ በሚል አቋሙ ገፍቶበታል።

- በቀናት ውስጥ መልስ እሰጥሃለሁ።

- በአእምሮህና በአስተዋይነትህ እተማመናለሁ፤በመሆኑም የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ካሁኑ አስፈላጊውን የጉዞ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግልህ አዛለሁ። የኮንትራት ሰነዶቹና አስፈላጊ ወረቀቶች ከተሟላ ዝርዝር የውል ስምምነት ረቂቆች ጋር ወደ ቢሮህ ይደርሳሉ።

- ፍቀድልኝና ወደ ሥራ ልመለስ።

‹‹ካኽ እንዳለው እውን

መርህና መልካም ስነ

ምግባር
አስፈላጊ ሆነው ሲገኙ የምንለዋውጣቸው መጠቀሚያና መገልገያ ናቸው? ወይስ የምንመራባቸውና መንገድ የሚያሳዩን ቋሚ የብርሃን ማማዎች ናቸው? እንዲህ ከሆነ ለብንያሚን በቴል አቪቭ ጉቦውን ለምን ሰጠሁ? የጉዞው ጉዳይ ካኽ ዘንድ በጣም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን በሥራው ለመቀጠል ወይም ለመልቀቅም ወሳኝ ነጥብ ሳይሆን አልቀረም . . መርሆ እውነት ዋጋ የለሽ ከሆነ እርስ በርሳቸው ወደሚባሉ አራዊትነት እንለወጣለን ማለት ነው። ዋይ . . ፈጣሪ እነዚህን ነገሮች ለምን አላደራጀም? ወይስ ሰዎች እርሱን አግልለው ጉዳዮቻቸውን በገዛ ራሳቸው እንዲያደራጁ ነው የተወላቸው?!›› ብሎ ራሱን እየጠየቀ ጆርጅ ወደ ቢሮው ተመለሰ።

በሀሳብ

ተጠምዶ እያለ ጉዞውን የሚመለከቱ ሰነዶችና የጉዞ ወረቀቶች ተጠቃለው ወደ ቢሮው ተላኩለት። ለርሱ ይበልጥ አስፈላጊው ጉዳይ እጓዛለሁ ወይስ አልጓዝም? የሚለው ውሳኔ በመሆኑ ወረቀቶቹን በግድ የለሽነት አየት አየት አደረጋቸው። የማይጓዝ ከሆነ ለማንበብ ለምን ይደክማል?
ጆርጅ ወደ ቤት ተመልሶ በጉዞው ውሳኔ ላይ ካትሪናን ለማማከር፣ከተለመደው በላይ በጣም ረዝሞ የታየውን የዕለቱን የሥራ ሰዓት ማብቂያ ሲጠብቅ ቆይቶ ወደ ቤቱ ሄደ። ካትሪናን በከፍተኛ ተመስጦና በጢሞና በማንበብ ላይ ሆና አገኛት . .

- የምታነቢው መጽሐፍ በጣም አስደሳች ሳይሆን አይቀርም!

- በተወሰነ ደረጃ፣የሙስሊሞችን መጽሐፍ ቅዱስ ነው የማነበው።

- ማንበቡን ጀመርሽ ማለት ነዋ!

- አዎ፣በጢሞና ያነበብኩትና የተረዳሁት ቢሆንም ያንዱን ምዕራፍ ትርጉም ካንድ ጊዜ በላይ ደጋግሜ ሳነብ ነው ራሴን ያገኘሁት።

- ለምን?

- እኔ እንጃ፤ምናልባት ከለመድኩት ዓይነት ሙሉ በሙሉ የሚለይ በመሆኑ ሊሆን ይችላል . . !

- መልካም . . ይህን ርእስና መጽሐፉን ለጊዜው ተወት እናድርግና የማማክርሽ ብርቱ ጉዳይ አለኝ።

- መቀጠል ትችላለህ።

- ካኽ ሌላ አዲስ የሥራ ጉዞ እንዳደርግ ጥያቄ አቅርቦልኛል።

- በዚህ ኩባንያ ሥራ ከጀመርክበት ጊዜ ወዲህ የሥራ ጉዞዎች እንዲህ ተከታትለው ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ለመሆኑ ወዴት ነው?

- ወደ ስዊድን ነው።

- ስዊድን ማራኪ አገር ነች።

- ችግሩ ይኸ አይደለም።

- ታዲያ ችግሩ ምንድነው?!

- የኮንትራት ውሎችን ለመፈራረም ወደ ኢየሩሳሌም በተጓዝኩበት ወቅት እዚያ ለሚገኘው ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ ውሉን በቀላሉ ይፈርም ዘንድ ትልቅ ጉቦ ይዤለት ነበር የሄድኩት። በዚህ የስዊድን ጉዞም ይህንኑ ዳግም እንዳደርግ ነው የሚፈልጉት።

- ጉቦን የማወግዝና የምጠላው ከመሆኑም ጋር ምኑ ነው አዲስ የሆነብህ?! ቀደም ሲል ሰጥተህ የለም?

- ይህማ ቃል በቃል የካኽ አነጋገር ነው።

- ያን አለቃህን እጠለዋለሁ፤ግና . .

- በመጀመሪያው ዙር ተሳስቼ ብሆን ስህተቱን አሁንም መድገም አለብኝ?! ሰዎች ከጥፋቶቻቸው መታረም የሚችሉበት መንገድ የለም እንዴ?

- በክርስትና ውስጥ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ብሎ ራሱን በመሰዋቱ እኛን ከኃጢአት ነጻ አድርጎን አጸድቶናል።

- ይህ ለአንድ የተለየ ግለሰብ ሳይሆን ለአጥፊውም ለሌላውም ነው።

- አልገባኝም።

- ማለት ሁላችንም በኢየሱስ ደም አንዴ ከኃጢአት ነጻ ወጥተናል፤የመድህን ዋስትና እስከተሰጠን ድረስ ኃጢአት መሥራትን ለምን እንተዋለን?! ይህ ለምህረት ምስክር ወረቀት ንግድ ጥሩ መግቢያ ይመስለኛል።

- ማለት የፈለከው ገብቶኛል፤በክርስትና ዘንድ ነገሩ እንዲህ ነው። በእስላም ዘንድ ግን በፈጸመው ኃጢአት ተጸጽቶ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ምህረት ያገኛል።

- እንዴት ያለ ፈጣን እርምጃ ነው? ስለ እስላም መናገር ጀመርሽ? ይህ ሁሉ አንድ መጽሐፍ ብቻ ካነበብሽ በኋላ?! ሙስሊሞች ንስሐ የሚገቡት በመነኮሳትና ቀሳውስቶቻቸው ዘንድ ነው? ከኋጢአት የመንጻት ቅዳሴ የሚደረገው እንዴት ነው?

- ምንም ዓይነት ቅዳሴ የለም፤በቀጥታ ወደ ፈጣሪ አምላክ ተመልሰህ ምህረት እንዲያደርግልህ መለመን፣ኃጢአቱን እርግፍ አድርገህ መተውና ሁለተኛ ላትመለስበት በቁርጠኝነት መወሰን ብቻ ነው።

- እንዲህ በቀላሉ!

- አዎ።

- ይህን ሁሉ ያገኘሽው ሙስሊሙ ሰውዬ ሮም ላይ ከሰጠሸ መጽሐፍ ነው?!

- ቁርኣን ብለው ከሚጠሩት የሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ።

- መልካም፣ወደ ካኽ ጉዳይ እንመለስ።

- እኔ እንጃ፣አስቸጋሪ አመራጮች ናቸው፤መርህን ጥሰህ ያሉህን በመቀበል ለገዛ ህሊናህ ተጠያቂ ተወቃሽ መሆን ነው፣አልያም እምቢ ብለህ ሥራህን ማጣት ነው።

- አዎ አስቸጋሪ ምርጫ ነው፣ምላሽ ለመስጠት የሁለት ቀን ጊዜ አለኝ። በኔ ቦታ ብትሆኚ ግን ምን ታደርጊ ነበር?

- እኔም በበከሌ እንዳንተው በግራ መጋባት ሁኔታ ውስጥ ነኝ፤እኔን በሚመለከት የግል ጉዳይ ላማክርህ ነበር፤ስለ ቀደምከኝ ግን በሁለት ግርታዎች ላስጨንቅህ አልፈልግም።

- እንዴት?

- ትምህርት ቤት የማስተምረውን ነገር እንደ በፊቱ አሳማኝ ሆኖ አላገኘሁትም፤በመሆኑም ሥራዬን ለመልቀቅ እያሰብኩ ነው።

- ሥራሽን ትለቂያለሽ?!

- አንተ መርህን መጣስ እንደማትወድ ሁሉ እኔም መርሆዬን መጣስ አልሻም። በማስተምረው አብዛኛው ነገር እምነት አጥቻለሁ፣ወይ የማላምንበትን ነገር ለሌሎች በማስተማር መርሆዬን መጻረር፣አልያም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብና ከነሱ የማገኘውን የወር ገቢ ማጣት ነው።

- ይህ ከፍተኛ ለውጥ ነው፣ባለፉት አስር ዓመታት ይህንኑ ስታስተምሪ አልነበረም? ምኑ ነው አዲስ? ሁለታችንም ሥራ ከለቀቅን በእንግሊዝም ሆነ በዓለም ደረጃ እየተባባሰ በመጣው የሥራ አጥነት ሁኔታ ውስጥ እንዴት መኖር እንችላለን?

- አዲሱ ነገር በካቶሊካዊነት ላይ ያለኝ እምነት የተናጋ መሆኑ ነው። ይህን አይደለም የፈለከው?! ለማንኛውም ግን እስካሁን አልወሰንኩም።

- አስከፍቼሽ ከሆነ አዝናለሁ፣ለቀልድ ያህል ነው።

- ማስከፋት ሳይሆን በተቃራኒው ከዓይኔ ላይ ያለውን ግርዶሽ ነው ያስወገድክልኝ። የበለጠ ግራ እንዳላጋባህ ልነግርህ አልፈለኩም ብየህ አልነበረም?

- ልክ ነሽ፣በግርታዬ ላይ ግርታ ነው የጨመርኩት . . ደጋግሜ አስብበትና በሁለት ቀናት ውስጥ እወስናለሁ። አንቺም ከውሳኔ ላይ መድረስ አለብሽ። እውነቱን ለመናገር ሕይወት በጥቅሉ ውሳኔ ናት . .

- ጆርጅ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰዎችን ማማከር ይኖርብሃል።

- በሥራ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ከውስጥ መረዳት የሚችል ማን ይኖራል?

- ከወዳጆችህ መካከል አንድ ሊኖር ይችላል። በመደበኛ የኢሜይል መልእክት ዝርዝር ለሁላችንም ለምን ጥያቄ አትልክልንም?

- ድንቅ ሀሳብ ነው፣አሁኑኑ እልካለሁ።

ጆርጅ ወደ ቢሮ ክፍሉ ሄዶ ኮምፒውተሩን ከፈተ፤ለወዳጆቹ ምክር ይለግሱት ዘንድ መልእክት ላከላቸው፦

‹‹ሰባተኛው ዙርአንድ ችግር ስለ አጋጠመኝ ለስድስተኛው ዙር ምላሽ ከመስጠታችሁ በፊት ምክር እንድትሰጡኝ ወደድኩ። ችግሩ በአጭሩቁሳዊ ሕይወቴ ቢጎዳም ለመርሆዎቼ ታማኝ ልሆን? ወይስ መርሆዎቼን ረግጬም ቢሆን ለጥቅሜ ትኩረት ልስጥ? ራሳችሁን በኔ ቦታ አድርጋችሁ በመውሰድ መልሳችሁ ግልጽና ቀጥተኛ እንዲሆን ምኞቴ ነው። ግላዊ ጥቅሞችና መርሆዎች የማይጋጩበትና የሚጣጣሙበት መንገድ ይኖር ይሆን?

ጆርጅ››

መልእክቱን ከላከ በኋላ የቶምን የፌስቡክ ገጽ ከፈተ፤ወደ ቀድሞ ቦታው ተመልሶ አገኘው። በገጹ ላይ ታትመው ለነበሩ ሐሰተኛና ቆርጦ ቀጠል ፎቶዎች ይቅርታ የሚጠይቅ ጽሑፍ ተለጥፎአል . . ቶም የፌስቡክ ሂሳቡን ለማስመለስና ከበራድ ጋር የነበረውን ችግር ለመፍታት የቻለ መስሎ ስለታየው ትንሽ እፎይታ ተሰማው። ከዚያም የአደምን ገጽ ከፈተ፤‹‹የመታደልን መንገድ ለመገለግ ከተሰማራው ወዳጄ የሚቀሰሙ ትምርቶች 4›› በሚል ርእስ አዲስ መጣጥፍ ተለጥፎ አገኘ

‹‹ወዳጄ ከሁሉም እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ላይ ይገኛል።አሁን ባለበት የፍለጋ ደረጃ ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል ይቻላል

1.የሰው ልጅ ማወቅ የሚያስፈልገው ነገር ከማወቅ ይልቅ የማያስፈልገውን ነገር ማወቅ ይቀለዋል። የመታደልን መንገድ ከማወቅም ያለ መታደልን መንገድ ማወቅ ይቀለዋል። አዲስና መሰረታዊ ለውጥ ውስጥ ማለፍ ለማንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው።

2.የትኛውም ብርቱ ውሳኔ ድፍረትና ጀግንነትን ይጠይቃል። ጀግንነት ለማንኛውም አመለካከታዊ፣ወታደራዊ ወይም ስነ ምግባራዊ ስኬት ወሳኝ ነጥብ ነው። ወዳጄ ያለ ጥርጥር ጀግና ነው፣ነገር ግን አሁን ከቀድሞው የበለጠ ጀግንነት ያስፈልገዋል። እናም እንደዚያ መሆን ይችል ይሆን?

3. ወዳጄና በዙሪያው ያሉት ብዙም ትኩረት በማይሰጡትና ልብ በማይሉት የለውጥ ሂደት ውስጥ ናቸው። ይህም አስገራሚ ነገር ነው። እስካሁን ድረስ እኔ ሙስሊም መሆኔን አያውቅም። በጣም የሚቀርቡት ሰዎችም እንደሱ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆናቸውን ሲያውቅ መገረሙ አይቀሬ ነው።

4. ወዳጄ ለመማር ጉጉና ታታሪ ቢሆንም እስላምን የማወቅና የመመርመር ውሳኔ ላይ በቀላሉ አልደረሰም። ምናልባት ለዚህ መንስኤው በመገናኛ ብዙኃን በእስላም ላይ የሚነዛው ሰፊ ውዥንብር ሊሆን ይችላል። በከፊል ደግሞ ሙስሊሞች ራሳቸው ማድረግ የሚገባቸውን ባለ ማድረጋቸውና በስህተቶቻቸው ምክንያት ሊሆንም ይችላል።

አሁንም ቢሆን ወዳጄ በመታደል መንገድ ፍለጋ ጉዞውና ለትላልቆቹ የሕይወት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ላይ ነው የሚል እምነት አለኝ። ቀጣዩን ትምህርት በቅርቡ ይዤላችሁ እመለሳለሁ።››

አደም››

ጆርጅ በአደም የተጻፈውን በድጋሚ በጢሞና አነበበው። ‹‹አደም የመታደል መንገድ እስላም ብቻ ነው ብሎ ያምናል ማለት ነው?! ከሆነስ ከመነሻው ለምን አልነገረኝም ኖሯል? እያፌዘብኝ ይሆን? ወይስ እስላም በማታለል ላይ ይመሰረታል? እስላም እውን የመታደል መንገድ ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ ለምን ይደብቃል? ለምንስ ከኔ ይሸሽጋል?! የሚሸሹት አሳፋሪ ነገር ሆኖ ነው? ወይስ የቤተ ክርስቲያንን ሚስጥራት የመሰለ ሌላው የሃይማኖት ሚስጥር ይሆን?›› ሲልም ራሱን ጠየቀ። በዚህ የሀሳብ ማዕበል ውስጥ እያለ ካትሪና መጣች . .

- ነይማ አደም ስለኔ የጻፈውን አንብቢ። ይህን ግለሰብ መጠራጠር ጀምሬአለሁ።

- ምንድነው የጻፈው?

- ይኸው አንቢቢው።

ካትሪና መጣጥፉን በከፍተኛ ተመስጦ አነበበችውና ወደ ጆርጅ ዞር ብላ . .

- ጥርጣሬህ ምኑ ላይ እንደሆነ አልገባኝም !

- እርሱ ሙስሊም ነው፣ለኔ ታላላቅ የሕይወት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጠው የመታደል መንገድ እስላም ነው የሚል እምነት አለው።

- ልክ ነው፣ይኸ የተለመደ ነው፤የራሱን እምነት የመታደል መንገድ ነው ብሎ ማመኑ ተፈጥሯዊ ነው።

- ግና . . ለምን አስቀድሞ አልነገረኝም፣ለምን ያታልለኛል?

- ያልሆነ ነገር ነገሮህ አታልሎህ ያውቃል?

- የለም፣ግን ሃይማኖቱንና እምነቱን ከኔ ሸሽጓል።

- በግልጽ የነገረህ ይመስለኛል፣አንተ ነህ ልብ ያላልከው።

- እንዴት?

- በፌስቡክ ገጹ መረጃ ላይ ሃይማኖቱን ጽፎአል። ፈጽሞ አልደበቀም፣እንዲያውም ይኮራበታል። ሃይማኖት በሚለው ላይ ‹‹በእምነቱ የሚኮራ ሙስሊም›› ብሎ ጽፎታል።

- ታቂያለሽ ገጹን ብዙ ጊዜ እየከፈትኩ ይህን ልብ ብዬ አላውቅም። አደም እውነቱን ነው፣በበቂ ሁኔታ ነገሮችን አላገናዝብም።

- በላክልን መልእክት ሁላችንም ቁርኣንን አንብበን አስተያየት እንድንልክልህ ጠይቀህ አልነበረም? አንተ ራስህ ማንበብ ጀምረሃል?!

- ካኽ በችግሮቹ ወጥሮኝ ስለነበረ ገና አልጀመርኩም። ዛሬ ከአደም ጋር እገናኛለሁ፣ቁርኣንን ማንበብም ዛሬ እጀምራለሁ። በኩባንያው ሥራ መቀጠል አለመቀጠሌን ዛሬ ወይም ነገ ለመወሰን እሞክራለሁ።

- አደም ከኛ የተሻለ አዋቂ አይሆንም፣ይበልጥ ጠንከር ባለ ሁኔታ ምላሽ እንድንሰጠው ረጋ ብለህ የሚልህን አዳምጥ . . ምናልባት ሰልመን ከርሱ ጋር እስላምን እንድከተል ይፈልግ ይሆናልና ክርስትና ተነስቶ ከኛ ጋር እንዲሆን እናደርገው።

- ምናልባት ሊሆን ይችላል። አሁን ወደርሱ እሄድና በእርጋታ አዳምጬው ከርሱ ለመማር እሞክራለሁ፤እራትም አብረን ሳንበላ አንቀርም።