ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . .

ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . .

ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . . (1)

የጆርጅ ጤንነት ቀስ በቀስ መሻሻል እያሳየ ነው። የቀዶ ጥገናው ስኬታማነት ምልክቶች በጉልህ እየተንጸባረቁ ነው። ከማግስቱ ጀ
ምሮ የሕክምና መሳሪያዎቹ ስለተነሱለት መንቀሳቀስ ችሏል። በግሉኮስ ከሚሰጠው ፈሳሽ ምግብ ውጭ ግን ገና መብላት አልጀመረም . . ካትሪና ከሕጻናቱ ጋር ሊያዩት መጡ። በመልካም ጤንነት ላይ ሆኖ በደስታና በፍካት ሲያዋራቸው ስላገኙት በጣም ተደሰቱ። ደስታው ትናንት መልእክት ልኮላቸው እንዲጸልዩለት ጠይቋቸው ለነበሩ ሁሉ የምስራች መልክት ማስተላለፉን አላስረሳውም። ምናልባት ቀዶ ጥገናው የተሳካው በአንደኛቸው ጸሎት ምክንያት ሊሆን ይችላል . . ምናልባት!
ጆርጅ ስለ ክርስትና እና ስለ ተለያዩ ፈለጎቹና ጎራዎቹ በተቻለ መጠን የበዛ መረጃ ሰንቆ ለሮም ጉዞው ለመዘጋጅት ወደ ጥልቅ ንባቡ ተመልሷል። ፕሮቴስታንት ሆኖ ተወልዶ ስለ ሃይማኖቱ የሚያውቀው እጅግ በጣም ጥቂት ብቻ መሆኑ ሁሌም ይገርመው ነበር። ከሚያውቀው ውስጥ አብዛኛው ከካቶሊኳ ካትሪና ወይም ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ በነበረበት ጊዜ ከካቶሊኩ ሐቢብ ወይም ለመታደል መንገድ ፍለጋው ጥረት በቅርቡ ካደረጋቸው ንባቦች የተማረው ነው። የማያውቁትን ሃይማኖት እንደሚከተሉት ብዙኃኑ ክርስቲያን መሰሎቹ ሁሉ ከዚህ ቀደም ይህ ነው የሚባል ሃይማኖትን የማጥናት አጋጣሚ ተመቻችቶለት አያውቅም። እንዲያውም ብዙዎቹ እንደሱው ከስሙ ባለፈ ስለ ሃይማኖታቸው የሚያውቁት ነገር የለም።
በክርስትና ላይ ያደረገው ንባብ በተለይም በክርስትና ጎራዎችና ቡድኖች መካከል ያሉ እምነትን፣አፈጸጸምን፣አምልኮን የሚመለከቱ ከፍተኛ ልዩነቶች፣የተደረጉ ጦርነቶችና ታላላቅ ግጭቶች በእጅጉ የሚያስደነግጡ ነበሩ። ይህ ሁሉ ቅራኔና ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? በሚለው ላይ ብዙ ያሰላስል ነበር። ካቶሊካዊነት ቀዳሚ በመሆኑ ችግሩ የመጣው ከፕሮቴስታንት ነው ያለችው ካትሪና እውነቷን ይሆን? ሆኖም በክርስትና ታሪክ ኦርቶዶክስ ከካቶሊክ ቀዳሚ መሆኑን አስታወሰ። በቅርበት መርህ ከተኬደ ለኢየሱስ ዘመን ይበልጥ የሚቀርበው የእምነቱ ጎራ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነው ተብሎ ይገመታል፤ይሁን እንጂ ወንጌሎች በኢየሱስ ሕይወት ዘመን ተጽፈው አልተቀመጡም . . ታዲያ የትኛው የክርስትና ጎራ ነው ትክክለኛው? በጉዳዩ ላይ ከሌላ ሰው ጋር የመነጋገር ፍላጎት አደረበትና ለአደም ለመደወል ወሰነ . .

- ሃሎ አደም እንደምነህ?

- ሃሎ እንደምነህ ጃል . . እንኳን በሰላም ወጣህ።

- አደም አመሰግናለሁ፤በተቻለ መጠን በቅርብ ጊዜ ብንገናኝ ምኞቴ ነው።

- የሚመችህ ከሆነ ነገ መምጣት እችላለሁ።

- በጣም ጥሩ፣ግን ጥያቄ አለኝ፤ከቶም ጋር የጀመርኩትን ልግፋበት ወይስ ላቁም?

- ቀጥልበት የሚል ሀሳብ አለኝ፤ይሁንና ጥያቄው ለምን ተነሳ? ለምንስ አሁን?

- እኔ እንጃ፣ምናልባት አንዳንዴ ምንም አዲስ ነገር የለም የሚል ስሜት ስለሚሰማኝ ሊሆን ይችላል።

- አዲስ ነገር የለም ስትል?

- እንጃ፣እንዳው የሆነ እንግዳ ስሜት ነው በቃ።

- እኔም አላውቅም፤የማውቀው ነገር ቢኖር አዲስ ነገር ካልታየህ በስተቀር መቀጠል እንዳለብህ ነው። በተለይም አንተ ብዙ እየተጠቀምክ ከመሆኑም በተጨማሪ እንደምትለው ቶም ራሱ ጥሩ መሻሻል አሳይቷል።

- ልክ ነህ፤ለምን እየተመቸኝ እንደመጣና እንደ ሐኪም ሳይሆን እንደ ወዳጅ ማየት ለምን እንደ ጀመርኩ አላውቅም። ለማንኛውም ይህ የሚሰማኝ ነገር እንጂ ሌላ አይደለም፤ቀጠሮ ለመውሰድ እደውልለታለሁ፤መልካም ፈቃድህ ከሆነ ግን ከዚያ በፊት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ነገ ካንተ ጋር መወያየት እሻለሁ።

ጆርጅ የስልክ ጥሪውን አበቃና ለቶም ደውሎ ወደ ሮም ከመጓዙ በፊት ቀጠሮ እንዲይዝለትና ቦታው በሆስፒታሉ እንዲሆንለት ጠየቀው። ቶምም ላስቸግርህ አልፈልግም በማለት እርሱ ራሱ ወደ ሆስፒታሉ ለመምጣት ተስማማ።

- ተነገወዲያ ጧት ይሁን። ሐኪሙ ከሦስት ቀናት በኋላ ትወጣለህ ብሎኛል።

- ጆርጅ አንተን ደስ እንዳለህ ይሁን።

ጆርጅ በንባብ ተጠምዶ እያለ ካትሪና መጣች . . ፊቷ በደስታ ፈክቶ ከፍ ባለ ድምጽ ሰላምታ አቅርባ ወደ ክፍሉ ገባች። ከጎኑ ቁጭ አለችና ጉንጩን ሳመች . .

- በጣም ደስ ብሎኛል፣ሐኪሙ እንደነገረኝ የጤንነትህ ሁኔታ አመርቂ ነው።

- አዎ ደህ ነኝ፣የሮም ጉዞ ጉዳይስ?

- ከሞላ ጎደል ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው። ትኬቶች ኦኬ ተደርገዋል፤ሆቴል ተይዟል። ከአንዳንድ ግለሰቦች ጋር የሚኖሩት ቀጠሮዎችና ከአስጎብኚዎች ጋር የሚደረጉ የጉብኝት ፕሮግራሞችም ተመቻችተዋል።

- በጣም ጥሩ፣ግና ከአንዳንድ ግለሰቦች ጋር የሚኖሩ ቀጠሮዎችን ስትይ ምን ማለትሽ ነው?

- የምትፈልገውን አውቃለሁ፤ከአንዳንድ ቀሳውስት ጋር ተገናኝተህ እንድትወያይና ቫቲካንን እንድትጎበኝ አመቻችቻለሁ።

- ይህ እኔ የምፈልገው ሳይሆን አንቺ የምትፈልጊው ነው።

- አዎ፣እኔ እምፈልገው ነው፤ፕሮግራም ያስያዝኩት ግን ያንተም ፍላጎት መሆኑን ስለማውቅ ነው።

- ልክ ነሽ፣የኔ ፍቅር አመሰግናለሁ።

- ከሐኪም ቶም ጋር ቀጠሮ የምትወስደው ከጉዟችን በፊት ነው ወይስ ከዚያ በኋላ?

- ከዚያ በፊት፣ነገ እዚህ ሆስፒታል እንዲሆን ተስማምተናል . . ለሕክምና ቀጠሮው ትኩረት የምትሰጭ ትመስያለሽ?

- ልክ ነህ፣ቶም ዘንድ ለሕክምና ቀጠሮ መሄድ ከጀመርክበት ጊዜ አንስቶ ይበልጥ ደስተኛ እንደ ሆንክ መስሎ ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም።

- በዚህ ምክንያት ብቻ ነው?!

- አዎ በዚሁ ምክንያት ብቻ . . ለምን እንደሆነ ባላውቅም ምናልባት ቶም ራሱም ከነበረበት ሁኔታው አሁን የተሻለ ሆኖ ስለሚሰማኝም ሊሆን ይችላል።

- እኔም እንደዚሁ ዓይነት ግንዛቤ ብኖረኝም እያጭበረበረኝ ነው የሚል ስጋት ግን አለኝ።

- ሁሉም ሊሆን ይችላል፣እኔ ግን እውነተኛ መለወጥ ነው ወደሚለው አደላለሁ።

- ይሁንና እያታለለን ከሆነ ዓላማው ምንድነው?

- እኛን በማታለል የሚያገኘው ጥቅም አለ ብዬ አልገምትም፤ለዚህ ነው መለወጡን እውነት ብዬ የማምነው።

- የቢሮው ኃላፊ በራድ ባይኖር እኔም እንደዚያ ነው እምነቴ።

- ያን ሰውየ በጣም እጠለዋለሁ፤ፈጽሞ የማይመች እኩይ ሰው አድርጌ ለምን እንደማየው አላውቅም።

- ቶም ራሱም እንዲሁ ተማሮበታል!

- ሊሆን ይችላል ግን አሳማኝ አይደለም! ከሚማረርበት ከሥራ አሰናብቶት መገላገል ይችላል።

- ልክ ነው፤እኔ እንጃ ምናልባት ሌላ ምክንያት ሊኖር ይችላል! ለማንኛውም ከርሱ ጋር ያለኝን ሕክምና ለማቆም ሳስብ ነበር።

- ይህ ተገቢ መስሎ አይታየኝም . . ውሳኔው ግን ያንተ ነው።

- ሀሳብሽ በትክክል ከአደም ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ ነው። አንዴ የጀመርከውን መንገድ መጨረስ ይጠበቅብሃል ነው የሚለኝ፤የቶምን መሻሻል እየጠቆመ መጥፎ በነበረበት ጊዜ አብረህ ቀጥለህ መሻሻልና መለወጥ ሲጀምር እንዴት ትተወዋለህ ባይ ነው።

- ሎጂካዊ አነጋገርና ጠንካራ መከራከሪያ ነው።

- ሁልጊዜ በሀሳብ መጣጣማችሁ አደምን ፕሮቴስታንት ሳይሆን ካቶሊክ ነው ብዬ እንድደመድም ያደርገኛል።

- እህህ፣ምናልባት ደግሞ ካቶሊካዊነት ከፕሮቴስታንትነት ይልቅ ለእውነት የቀረበ ለመሆኑ አስረጅ ሊሆንም ይችላል።

- ሊሆን ይችላል፤ሮም ላይ አንስተን እንወያይባቸዋለን ብዬ ብዙ ጥያቄዎችና ንጽጽሮችን ሰብስቤ አዘጋጅቻለሁ።

- ግሩም ሀሳብ ነው፤የምናመራው ወደ ካቶሊካዊነት ማዕከል ብቻ ሳይሆን ወደ ዓለም አቀፍ የክርስትና ማዕከል ነውና።

- ምናልባት የካቶሊካዊነት ማእከል ቢሆን እንጂ በእርግጠኝነት የክርስትና ማእከል ግን አይደለም። በአሳዛኙ ፓፓዊ ሥርዓት እኛ አናምንም።

- እንዲህ ያለውን አባባል ሁለተኛ እንዳትናገር፤በተስማማነው መሰረት እነዚህን ርእሰ ጉዳዮች ሮም ስንደርስ እንወያይባቸዋለን። ካቶሊካዊነት ላይ ጫን ያልክ አይመስልህም? በአፈንጋጩ ፕሮቴስታንት ላይ ያሉንን ትችቶች እንዳነሳ ነው የምትፈልገው?

- አፈንጋጩ!! ለፕሮቴስታንት ቆንጆ አገላለጽ ነው! አንቺ በተናገርሽው እኔ እንዳንቺ አለመቆጣቴን አታስተውይም?!

- እህህ፣ፕሮቴስታንትን የሚገልጽ ተጨባጭ አገላለጽ መሆኑን ስለምታውቅ ሊሆን ይችላል። ሃማኖታችሁን እንዳሻችሁ አይደለም የምትደርሱትና እየጠፈጠፋችሁ የምትሰሩት? መጽሐፍ ቅዱስንም እንደመሰላችሁ አይደለም የምትረዱት? ማለት የፈለኩት አፈንጋጭነትም ይኸው ነው!

- ምናልባት እንዳልሽው ሊሆን ይችላል፣አልያም ከሮማዋ ቤተክርስቲያን ጥመትና ከምትቸበችበው የምህረት ማስገኛ ምስክር ወረቀት ነጻ በመሆናችን ሊሆን ይችላል።

- ይህን ሁሉ ሮም ላይ ልንወያይበት ተስማምተናል። እናም አሁን ክርክሩን ብናቆም ምን ይመስለሃል?

- እህህ፣ተስማምተናል። በቀጠሮአችን መሰረት ለመጓዝ ምናልባት የሚፈለግ ነገር ካለ ሐኪሙን ጠይቀሽ እንድታረጋግጭ እፈልጋለሁ፤ለጉዞው በጣም ጓግቻለሁ።

- ኤጲስ ቆጶሱን ለመገናኘት ጓግቻለሁ ማለትህ ነው!!

ጆርጅ ተመቻችቶ ተቀመጠና ፈገግ ብሎ፦

- አዎ፣ሃይማኖቱ የተሳሳተ መሆኑን እፊትሽ ላሳምነው።

- ያን ሹፈትህን የማውቀው ብሆንም በዚህ ጉዞ በእውነት ገለልተኛና ሚዛናዊ ለመሆን ከራሴ ጋር እታገላለሁ፤ ስለዚህ የኔ ፍቅር ልታግዘኝ ትችላለህ?

- የኔ ፍቅር መቼም ልቤን እንዴት እንደምታሸንፊው ታውቂያለሽ። በማስረጃ ሳሸንፍሽ በፍቅር ትረቺኛለሽ። አዎ፣የምችለውን ሁሉ እንደማደርግ እርግጠኛ መሆን ትችያለሽ።

- ጆርጅ እወደሃለሁ፤አሁን ስለ አንተ ሁኔታና ስለ ጉዞው ጉዳይ ሐኪሙን ለመጠየቅ ልሂድ።

ከአንድ ሰዓት በኋላ ካትሪና ስትመለስ ጆርጅን በንባብ ተጠምዶ አገኘችው . .

- ኦህ አምላኬ . . የምታነበው ነገር እስከዚህ ድረስ አስፈላጊ ነው ማለት ነው?!

- አዎ፣ስለ ማርቲን ሉተርና ስለ ጆን ካልቪን ነው የማነበው፤ሁለቱ በፕሮቴስታንት ላይ ተጽእኖ ካሳደሩት ሰዎች ዋነኞቹ ናቸው።

- የፕሮቴስታንትን ሃይማኖት ደረሱት፣ፈለሰፉት፤ማለትህ ነው?

- በአብዛኛው እውነት ተናግረሻል፤ይሁን እንጂ ያንን ያደረጉት ከካቶሊክ በሽታዎችና ከብልሹ ልማዶቹ ለመገላገል ሲሉ ነው . .

- እናም ፕሮቴስታንት ልቦለድ ድርሰት መሆኑን አምነህ ትቀበላለህ ማለት ነው?!

- አንዳንድ ሰዎች ዘንድ ሃይማኖትን ከኋላ ቀርነትና ከአእምሮ ደነዝነት ጋር የተያያዘ አድርገው እስከማየት ደረጃ ድረስ፣ካቶሊካዊነት በሚስጥሮቹና በፓፓዊ ሥርዓቱ የፈጠረውን የኢ-አማኝነት (ኤቲዝም) ማእበል ለመገደብ ሲባል የተደረገ በመሆኑ እያዘንኩ አዎ እልሻለሁ! በዚህ ላይ አሁኑኑ እንድንከራከር ትፈልጊያለሽ?

- ኦህ . . ጉዳዩ በቀጥታ በካቶሊካዊነት ላይ ነው የተደፈደፈው፤ፕሮቴስታንታዊነት ልቦለድ ድርሰትና የክርስትና ሃይማኖት ብረዛ መሆኑን አምነህ እስክትቀበል ድረስ ሮም ላይ እንከራከርበታለን።

- እውነትሽን ነው፣ፕሮቴስታንት ከካቶሊክ የተዛነፈና ያፈነገጠ ነው፤ለዚህም ነው አንዱ ሌላውን ከክርስትና የወጣ ከሃዲ አድርጎ የሚያየውና የሚዋጋው . . ሌላው ቀርቶ የፕሮቴስታንት ጎራዎችም አንዱ ሌላውን ከሃዲ አድርገው ይመለከታሉ። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችና ጎራዎች ቁጥር ስንት እንደሆነ ታውቂያለሽ?

- አላውቅም፣ወደ መቶ ይደርሳሉ?

- ይህ ዜና ምናልባት ሊያስደምምሽ ይችላል። የቤተክርስቲያኖቹና የጎራዎቹ ቁጥር ከሃያ ስምንት ሺህ እስከ አርባ ሺህ ነው።

- አርባ ሺህ ቤተክርስቲያኖችና ጎራዎች?!

ጆርጅ በመከፋት ስሜቱ ተለዋወጠ፤ፊቱን ቅጭም አደረገ፣ቀና ብሎ ተመቻችቶ በመቀመጥ እንዲህ አለ

- በጣም እያዘንኩ አዎ፣ይህም መለኮታዊ ያልሆኑና ሕንድ ውስጥ ያየኋቸውን የመሳሰሉ ቡድኖችን እንዳስታውስ ያደርገኛል። አሁንም እያዘንኩ ግልጽ መሆንና ለራስ መታመን በእውነት አስቸጋሪ ነገር ነው!

- የፕሮቴስታንት እምነት የፈጠራ ድርሰት ነው ብየህ የለ ! (ፈገግ ብላ ቀጠለችና) ፦ ይሁንና በስምምነታችን መሰረት ሮም ላይ ነው የምንከራከርባቸው።

- ከአንድ ጊዜ በላይ የፈለግሽውን እየተናገርሽ ሮም ላይ እንወያይባቸዋለን ትያለሽ። (ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ ግዴለም ላንቺ ሲባል ይሁንልሽ፤ሐኪሙ ምን አለ?

- ጆር እወደሃለሁ . . ሐኪሙ የነገረኝ የጤንነትህ ሁኔታ እጅግ በጣም ጥሩ መሆኑን፣ የቀዶ ጥገና ሕክምናው መቶ በመቶ የተሳካ በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከሆስፒታል የምትወጣ መሆኑን፣ከወጣህ በኋላ ከሁለት እስከ ሦስት ቀናት ብቻ ዕረፍት ማድረግ በቂህ መሆኑንና ከዚያ መደበኛ ሕይወትህን መቀጠልም ሆነ ያለ ምንም ስጋት ጉዞውን ማድረግ እንደምትችል ነው።

- በጉዞው ወቅት የሚደረጉ የተለዩ ጥንቃቄዎች አሉ?

- ጠይቄው ራስህን አለማንገላታትን ለአደጋና ለአስቸጋሪ ሁኔታ አለመጋለጥን ከመሳሰሉና ከቀዶ ጥገናው ጋር ግንኙነት ከሌላቸው አጠቃላይ የጤና ምክሮች ውጭ የተለዩ ጥንቃቄዎች ፈጽሞ አለመኖራቸውን ነግሮኛል።

- መልካም።

- ግሩም ድንቅ ጉዞ ይሆናል፤የጋብቻችንን የመጀመሪያዎቹን ቀናት ዳግም እናድስበታለን።

- የጋብቻችን የመጀመሪያዎቹ ቀናት ድንቅ ነበሩ! እናድሳቸዋለን፣በጉዞውም ተደሳቾች እንሆናለን፤በተጨማሪም አዲስ ነገር ያለበት ጉዞም ይሆናል . .

- ምን አዲስ ነገር?

- የማይክልና ሳሊ ከኛ ጋር መኖር።

- ለነሱ ስንል የጉብኝቱን አንዳንድ ይዘቶች ለመለወጥ ብንገደድም ደስታችንን እጥፍ ድርብ ስለሚያደርጉ በጣም እወዳቸዋለሁ።

- እነሱን በሚመለከት ማድረግ የሚገባኝን እንዳላደረግሁ አውቃለሁ፤ሳላስበው ድንገት እንዳደጉ ነው የሚሰማኝ።

- የነፈግናቸውን በቂ ጊዜ ወደፊት እንክሳቸዋለን፤አይመስልህም?

- አዎ፣የማበረክትላቸው ከሁሉም የላቀ ስጦታ የመታደልን መንገድ እንዲያውቁ ማድረግ ነው የሚል እምነት አለኝ።

- አሁንም የመታደል መንገድ!

- ለሁለተኛም ለሦስተኛም ጊዜ እንጂ፣ወደዚያ ለመድረስ እንደተቃረብኩ ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም።

- ማን ያውቃል ሮም ውስጥ አብረን እንደርስበት ይሆናል።

- እህህ፣ሁላችንም እንደገና ካቶሊክ እንሆናለን ማለትሽ ነው?!

- ምናልባት . . ወይ ደግሞ ሌላ ሊሆንም ይችላል።

- ካቶሊካዊነትን ትለቅያለሽ ማለት ነው?!

- ማን ያውቃል? አንተ ራስህ ፕሮቴስታንትን ትለቅ ይሆናል።

- ሌላው ይሆናል ብለን እንገምትና ካቶሊካዊነትን የመልቀቅ ድፍረትና ወኔ ይኖርሻል?

- ይህን ለመወሰን ረዥም ጊዜና ትግል ጠይቆኛል . . ዛሬ ግን አስቸጋሪ ውሳኔ ቢሆንም አዎ ማለት እችላለሁ።

- የኔ ፍቅር ኮርቼብሻለሁ።

- ተልእኮህን ሳትወስን፣ለሕይወትህ ትርጉምና ዓለማ ሳታኖርለትና ለታላላቅ ጥያቄዎችህ ምላሽ ሳታገኝ ለመኖር ያልወደድክ በመሆንህ እኔ ነኝ እንጂ በአንተ የኮራሁት።

- እህህ፣እንግዲያውስ አንቺ ፕሮቴስታንቷ እንኳን ደስ አለሽ።

- እህህ፣አምነህ ወደ ግንዱ ወደ ጥንተ መሰረቱ ወደ ካቶሊካዊነት የተመለስከው አንተ አፈንጋጭ ፕሮቴስታንት እንኳ ደስ አለህ ልበል እንጂ።

ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . . (2)

ከካትሪና መሄድ በኋላ ጆርጅ ወደ ንባቡ ተመለሰ። ስለ ማርቲን ሉተር ስለ ጆን ካልቪንና ስለሌሎቹም፣እንደዚሁም በክርስትና ሃይማኖት ውስጥ ስለተስተዋሉ አዳዲስ ለውጦች የጀመረውን ንባብ ቋጨ። በነርሷ ድምጽ እስከባነነ ድረስ ጊዜው አልታወቀውም ነበር

 

- ከወጣህ በኋላ ፈተና አለብህ?

- አዎ፣ወሳኝ ፈተና አለብኝ።

- በየትኛው የትምህርት እርከን?

- አላውቀውም።

- እንድንነጋገር የምትፈልግ አይመስለኝም፣ከንባብህ ስለ ረበሽኩህ ይቅርታ አድርግልኝ። እኔ እንኳ የመጣሁት ግሉኮሱን ላላቅቅልህ ነው፣ከነገ ጀምሮ መደበኛውን አመጋገብ ትጀምራለህ።

- ይቅርታ፣ማለት የፈለኩት አንቺ እንደተረዳሽው አይደለም።እውነቱን ለመናገር ፈተና ላይ መሆኔ ይሰማኛል፣ግን የትምህርት ፈተና አይደለም።

- የምትናገረው ምንም አልገባኝም !

- ሃይማኖትሽ ምንድነው?

- እኔ በሁሉም ሃይማኖቶች ብዙም አልተማመንም፣ሆኖም ግን ፕሮቴስታንት ነኝ . . ካልቪናዊ።

- የጆን ካልቪን ተከታይ ነሽ ማለት ነው?

- አዎ፣ይዞት የመጣው አዲስ ነገር ምን እንደሆነ ባላውቅም የርሱ ተከታይ ነኝ። የማውቀው ነገር ቢኖር ለአእምሮ የቀረበ መሆኑን ብቻ ነው።

- ይዞት የመጣውን አዲስ ነገር ካላወቅሽ ይህን እንዴት አወቅሽ?

- እኔ ነርስ እንጂ መነኩሲት አይደለሁም። በካቶሊኮችና በፕሮቴስታንቶች መካከል የነበሩትን ደም አፋሳሽ ግጭቶች የፈታ መሰለኝ።

- የአንድ ሃይማኖት አማኞች ሆነው እርስ በርስ መፋጀትና መተላለቅ ለማሰብ አይከብድም?! እንደ ካልቪን ያለ አንድ ግለሰብ መጥቶ ሃይማኖትን ዳግም ጠፍጥፎ መስራቱስ ለማሰብ አያስቸግርም?!

- ለዚህ ነው በፕሮቴስታንትም ሆነ በካቶሊካዊነት ከነአካቴውም በሁሉም ሃይማኖቶች ላይ እምብዛም አልተማመንም ያልኩህ። ሃይማኖት የሚያስፈልገኝ ባይሆን ኖሮ ፕሮቴስታንታዊነትን ባልተቀበልኩ ነበር።

- ይቅርታ አድርጊልኝና ሃይማኖት የሚያስፈልገኝ ባይሆን ኖሮ ስትይ ምን ማለትሽ ነው?

- ያለ ሃይማኖት መኖር አልችልም፤ሕይወት ያለ ሃይማኖት ስቃይና እርግማን ነው። ኤቲስት ነበርኩ፣ከዚያ ወደ ዓለማዊነት (ሴኩላሪዝም) ተለወጥኩ። ስመራው በነበረው የጭንቀት ሕይወት ምክንያት ራሴን ለማጥፋት ተቃርቤ ነበር። ያለሁበት መንገድ የተሳሳተ መሆኑን ውስጤ ያውቀው ነበርና ያለ ምንም ዝርዝር ማብራሪያ ፕሮቴስታንት ለመሆን ወሰንኩ . . ካንተ ጋር ሀሳብ መለዋወጥ በጣም አስደሳች ነው፣ግና ሥራ ስላለብኝ ፍቀድልኝና ልሂድ።

- ንጹህ ሕሊናሽ አንቺ እንዳልሽው ፕሮቴስታዊነትን ያለ ምንም ዝርዝር ማብራሪያ እሽ ብሎ ይቀበላል? ከገዛ ራስሽ ለመሸሽ ያደረግሽው ነው የሚል እምነት አለኝ፣ግን ወዴት?

የጆርጅ አነጋገር ያሳደረባት ተጽእኖ ከፊቷ ጎልቶ ታየ። ጭንቀቷንና መንፈሰ ባዶነቷን ለመሸሸግ እየሞከረች፦
 

- ምናልባት ልክ በነፋስ እንደሚነዳ ላባ ወደማላውቀው መሸሼ ሊሆን ይችላል፤ይሁን እንጂ አንድ ቀን ወደምፈልገው ለመድረስ እችል ይሆናል፤ደህና ሁን ልሂድ።

ጆርጅ

በተከታዩ ቀን አማልዶ ከእንቅልፉ ተነሳ። ከፍተኛ የሆነ ረሃብና የምግብ ፍላጎት አድሮበት ስለነበር ቁርስ እንደ ቀረበለት በጉጉትና በአምሮት በላና ወደ ንባቡ ተመለሰ። የትናንትናዋ ነርስ ሙቀቱን ለመላካት መጣች . .

- በጣም ጥሩ ነው፣በጎ ሆነሃል።

- ትናንት ረብሼሽ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

- አልረበሽከኝም፤ለትሕትናህ አመሰግናለሁ። ያለ ምንም ግብ ከገዛ ራሴ በመሸሽ ላይ ስለመሆኔ የተናገርከው ነገር ትክክለኛ ይመስለኛል። ታዲያ ኤቲዝምና ሴኩላሪዝም ስቃይ፣ሃይማኖተኛ መሆን ደግሞ ሽሽት ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ?

- ሃይማኖተኛ መሆን ሽሽት አይደለም፤አንቺ ግን ከራስሽ ሃይማኖት ነው የምትሸሽው።

- ከእግዚአብሔር የተላለፈ ሳይሆን አንተ እንዳልከው የሚደረስ ፈጠራና ተጠፍትፎ የሚሰራ ሃይማኖት በመሆኑ ነው። በየጊዜው ሃይማኖቱ የተሻለ እንዲሆን ለማሻሻልና ለመከለስ የሚመጡ ሰዎች ይኖራሉ።

- ግንኮ መለኮታዊ ሃይማኖት ማለትም ከእግዚአብሔር የተላለፈ ነው።

- ከኔ ይበልጥ አንተ ስለ ሃይማኖት ታውቃለህ፤ይሁንና ካልቪን ወይም ሉተር ወይም ሌላው ሰው እንዳስፈለገው የሚለዋውጠው ሃይማኖት እንዴት ሆኖ ነው መለኮታዊ ሃይማኖት የሚሆነው?! እንዲያውም ኢየሱስ ራሱ አዲስ ኪዳን በጽሐፍ ከመጠናቀሩ በፊት የተገደለ በመሆኑ የተጻፈው በደቀመዛሙርቱ ደቀመዛሙርት አማካይነት ነው።

- የሃይማኖት ፈላስፋ ሳትሆኚ አልቀረሽም !

- እንዳልከኝ ሁሉ ከገዛ ራሴ የምሸሽ ፈርታጭ ነኝ እንጂ።

- በአንቺ አመለካከት መፍትሔው ምንድን ነው?

- መፍትሔው አንተ የምትተችብኝ ከራስ መሸሽ ነው።

- ከችግሮች መሸሽ መፍትሔ ያስገኛል ብዬ አላስብም።

- ታዲያ በአንተ አመለካከት መፍትሔው ምንድን ነው?

- ወደ ሃይማኖት ዝርዝር ጉዳዮች ገብተን እውነታውን ማወቅ ነው ።

- ቀሳውስትና መነኮሳት ልንሆን?! እነርሱ ራሳቸው ትልቅ ጥርጣሬ አላቸው፣ለዚህ ነው በማያቋርጥ ሁኔታ በሃይማኖት ላይ ለውጥ የሚያካሄዱት።

- መንገዱን ማወቅ ማለት ቀሳውስትና መነኮሳት ሆን ማለት አይደለም። እኔ ለቀሳውስትና ለመነኮሳት አክብሮት አለኝ፣ ከነሱ አንዱ መሆን ግን አልፈልግም። ጥርጣሬ እርግማንን ሲያመጣ እርግጠኝነት ግን እርጋታን ያላብሳል።

- ካቶሊካዊ ትመስላለህ፣ለቀሳውስትና ለመነኮሳት ያለ ምንም ጥያቄ እጅ ሰጥተን እንድንገዛ ብቻ ሳይሆን፣ለራሳችን መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን እንዳንረዳ ነው የሚፈልጉት።

- በኔና በፈጣሪ አምላኬ መካከል አገናኝ ሰው እንዲኖር ለማድረግ አእምሮዬን አውልቄ አሳልፌ መስጠት አይቻለኝም፤እኔ ፕሮቴስታንት ነኝ።

- ታዲያ አንተ እንደኔው ነህና ለምንድነው የምትተቸኝ?! ሉተራዊ ካልሆንክ በስተቀር።

- እህህ፣እውነቱን ለመናገር የካልቪን ወይም የሉተር ወይም የሌላው ተከታይ ሆኜ እንደሆነ አላውቅም፤የማውቀው አባቴና እናቴ ፕሮቴስታንቶች ስለነበሩ ብቻ ፕሮቴስታንት መሆኔን ነው።

- እናም አንተ በትክክል እንደኔው ነህና ከራስ በመሸሽ እንዴት ነው የምትገልጸኝ?!

- እኔ ራሴ ከራሴ የሸሸሁ ፈርጣጭ በመሆኔ ነው።

- ወዴት ነው ሽሽትህ?

- ወደ መታደል መንገድ።

- እህህ፣ፈላስፋው ወዴት ነው መንገዱ?

- አላውቅም፣ግን አገኘዋለሁ።

- የፍልስፍናዊ እንቆቅልሾች ባለቤት ትመስላለህ። በውይይቱ ደስተኛ ብሆንም ለመሄድ እገደዳለሁ። በነገራችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጽናትና ቁርጠኝነት ስላለህ እንደምታገኘው እኔም እርግጠኛ ነኝ፤ስታገኘው ግን አሳውቀን።

- ምኑን?!

- የመታደልን መንገድ !

ነርሷ ከሄደች ከአፍታ ቆይታ በኋላ የጤንነቱን ሁኔታ ለማየት ሐኪሙ ወደ ጆርጅ ክፍል መጣ። በጥሩ ጤንነት ላይ ስለሚገኝ ከፈለገ ነገ ምሽት መውጣት እንደሚችል ነገረው።

- አመሰግናለሁ።

- ባለቤትህ ወደ ሮም እንደምትሄዱ ነግራኛለች፣እንኳን ደስ አለህ እለሃለሁ፣ውብና ታሪካዊት አገር ናት።

- አዎ፣እኔ አሷና ልጆቻችን አብረን ልንጓዝ ነው፤ከቀዶ ጥገናው በኋላ የምትሰጠኝ ተጨማሪ የጤና ምክር ይኖራል?

- ፈጽሞ የለም፤በጣም ጥሩ በሆነ የጤንነት ሁኔታ ላይ ነህ።

ከማምሸቱ

ጥቂት ቀደም ብሎ አደም ደረሰ . . ጆርጅን በዙሪያው የሚሆን ነገር በማይሰማው ሁኔታ በተመስጦ ሲያነብ አገኘው። ቀረብ ብሎ ሰላም አለው፦
 

- በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር እያነበብክ መሆን አለበት፣ሌላው ቀርቶ አጠገብህ ሰው መኖሩ እንኳን እየተሰማህ አይደለም !

- አደም . . ! እንኳን ደህና መጣህ፣ምን ጊዜ ገባህ? ስለ ጥንታዊው የክርስትና ታሪክ ሳነብ ነበር።

- መልካም፣ምን አገኘህ።

- ስለ ጥንቱና አዲሱ የክርስትና ታሪክ ስታነብ በጣም አስገራሚ የሆነ የመደናበር ሁኔታ ታስተውላለህ !

- ወደ ሮም እንኳ ከመጓዝህ በፊት ካቶሊካዊነትን ለመተቸት የተቻኮልክ አይመስልህም?

- እኔ ካቶሊካዊነትን አልተችም።

- ተረድቼ ካልሆነ ማለት የፈለከው ምንድነው?

- እኔ የምተቸው ካቶሊካዊነትን፣ፕሮቴስታንትንና ሁሉንም የክርስትና ቡድኖችንና ጎራዎችን ነው።

- ወደ ሮም መጓዝህ ነውና ከጉዞህ በኋላ ነገሮች የበለጠ ግልጽ ስለሚሆኑልህ አትቸኩል። ማን ያውቃል ምናልባት አሁን አእምሮህ ውስጥ የሌለ አዲስ ነገር ሊታይህ ይችል ይሆናል።

- ላማክርህ የፈለኩትም ይህንኑ ነበር።

- አልገባኝም፣ልታማክረኝ የፈለከው ጉዳይ ምንድነው?

- በሰጠኸኝ ሀሳብ መሰረት ለቶም ደውየለት ነገ ለመገናኘት ቀጠሮ ወስጃለሁ፤ምን እንደሚለኝ ግን አውቃለሁ !

- በጣም ጥሩ፣ቀጥል ምን ሊል ይችላል?

- በሮም ጉብኝትህ ክርስትናን በደንብ አጥናው፣በቅርበት ለማወቅ ሞክር ይለኛል። እኔ ግን ከንባቤም ሆነ ከኢየሩሳሌም ጉዞዬ ወይም ፕሮቴስታንት እንደ መሆኔ ከሕይወቴ በበቂ ሁኔታ አውቄዋለሁ የሚል ስሜት አለኝ። ስለዚህም በጉዞዬ የምጨምረው አዲስ ነገር ይኖራል የሚል ግምት የለኝም።

- ጆርጅ ዕድሜህ ስንት ነው?

- ሰላሳ ሰባት ወይም ስምንት ነኝ፤ለምን ጠየከኝ?

- ሰላሳ ስምንት ዓመት ታግሰህ ኖረሃል፤ወደ ሮም ተጉዘህ በውሳኔህ እርግጠኛ ሆነህ እስክትመለስ መታገስ እንዴት ያቅተሃል? የተቻኮልክ አይመስልህም?

- ምናልባት ሊሆን ይችላል፤ግና ስለ ፕሮቴስታንት ቡድኖችና ጎራዎች ይበልጥ ባወቅሁ ቁጥር ይበልጥ እየተውኩትና እየጣልኩት ነው።

- እናም ምናልባት ወደ ካቶሊክ ወይም ወደ ኦርቶዶክስ ልትለወጥ ትችላለህ ማትለ ነው።

- አንተ ካቶሊክ ነህ ብየህ የለ? ግና እመነኝ ከፓፓዊው ካቶሊካዊነት ያለኝ ርቀት ከፕሮቴስታዊነት ካለኝ ርቀት የበለጠ ነው።

- ከጉዞው በኋላ ሀሳብህ ምናልባት ይለወጥ ይሆናል፤ለማንኛውም ከቅድመ ውሳኔ ርቀን ሀሳቦችን በክፍትና ነጻ አእምሮ መመርመር አስፈላጊ ነው።

- ምንም ዓይነት ቅድመ ውሳኔ አልገደበኝም። የካቶሊክና የፕሮቴስታንት መጽሐፎችና ሕትመቶቻቸውን፣ታሪካቸውንና ውጤታቸውን በጥልቀት አንብቤያለሁ፤ይሁን እንጂ ምንም አሳማኝ ነገር አላገኘሁም።

- መልካም፣ይበልጥ ነጻ ለመሆንና ይበልጥ አስተውለህ ለማስተንተን ሞክር እንጂ አትቸኩል። ይህን ካደረክ ከጉዞህ በኋላ በምትወስደው ውሳኔህ የበለጠ እርግጠኝነትና የአእምሮ እርጋታ ይኖረሃል።

- ለመሆኑ ሃይማኖት ከአእምሮ ወይም ከሳይንስ ጋር ሊጋጭ ወይም ተጻራሪ ሊሆን ይችላል?

- በጭራሽ . . ሃይማኖቱ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ

የተላለፈ ከሆነ ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም።

- አንድ ሃይማኖት ከአእምሮ፣ከተጨባጭ እውነታ ወይም ከሳይንሳዊ ዕውቀት ጋር የሚጻረር መሆኑ እውነተኛ ሃይማኖት ላለመሆኑ ማስረጃ አይደለምን?

- ነው፣ይሁን እንጂ የሰው ልጅ አእምሮ ውስን በመሆኑ ያልደረስክበት ነገር ሁሉ ከአእምሮ ወይም ከሳይንስ ጋር ይጻረራል ማለት አይደለም፤ይህ የሚያመለክተው የሰው ልጅ አእምሮ ውስን መሆኑን ነው።

- እንዴት ማለት? አብራራው።

- እግዚአብሔርን ፍጹማዊ የሆነ ዕውቀት አለማወቃችን እግዚአብሔር የለም ማለት አይደለም። ይህ ማለት በተለመደው ሰብአዊ ድክመታችንና ውስንነታችን ምክንያት እውቀታችን ገደብ አለው ማለት ነው።

- ብዙ ብለፋና ብባዝንም አምላክ አንድም ሦስትም ነው የሚለውን የሥላሴ ጽንሰ ሀሳብ እስካሁን ድረስ መረዳት አልቻልኩም። ቤተክርስቲያኗ ያለ ጥያቄና ያለ ክርክር እንዳምንበት የምትፈልገውና ከቤተክርስቲያን ምስጢሮች አንዱ የሆነ ካቶሊካዊ ምስጢር ይሆን?

- አንድን ነገር መገንዘብ ባለመቻልና ያ ነገር ከአእምሮ ጋር የሚጻረር በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፤የትኛውን ማለትህ ነው?

- ሁለተኛውን ማለቴ ነው፤የሥላሴ ጽንሰ ሀሳብ ከአእምሮዬ ጋር ስለሚጻረር ልረዳውና ልተረጉመው አልችልም።

- ቀጥተኛ፣ሚዘናዊና ትክክለኛ ከሆነ አእምሮ ጋር የሚጻረር ሃይማኖት ትክክለኛ ሃይማኖት ወይም እውነተኛው ሃይማኖት መሆን አይችልም።

- እናም በዚህ ኦርቶዶክስን፣ካቶሊክንና ፕሮቴስታንትን ውድቅ እናደርጋለን ማለት ነው።

- ከሮም እስክትመለስ ድረስ ለምን አትታገስም?

- ይህንኑ ይዤ የምመለስ ከሆነ ኤቲስት ወይም ሴኩላሪስት እሆናለሁ ማለት ነው።

- ኤቲዝምና ሴኩላሪዝም አንተ ዘንድ ከሰው አእምሮ ጋር አይጻረሩም ማለት ነው?

- ከአእምሮ ጋር በቀጥታ ይጻረራሉ፤ለዚህ ነው ትቼው ወደ ሃይማኖት የሸሸሁት። በመቀጠልም ከሰው ሰራሽ ምድራዊ ሃይማኖት ወደ መለኮታዊ ሃይማኖት ሸሸሁ። ከዚያም አይሁዳዊነትን አሁን ባለበት ሁኔታው ጠላሁት። ክርስትናንም መጥላት ጀመርኩ፣የቀረኝ ቢኖር አሸባሪ ሙስሊም መሆን ብቻ ነው።

- ምናልባት ልትረዳና አሳማኝ ሆኖ ልታገኝ ስለምትችል ከሮም እስክትመለስ ውሳኔ ላይ አትድረስ።

- አሳማኝ ሆኖ ባላገኘውስ?

- ምናልባት የመታደል መንገድ እርሱ ሊሆን ስለሚችል እስላምን መርምር፣አጥናው !

- ታዲያ አንተ እስላምን አጥንተህ አሸባሪና ኋላ ቀር የሴቶች አሳዳጅ ለምን አልሆንክም ?

- አሁን የምንገኘው በክርስትና ጥናት እርከን ላይ ነው፤ከሮም ከተመለስክ በኋላ እነግረሃለሁ።

- አንተና ካትሪና ሮም አእምሮዬን እንድጻረር የምታሳምነኝ፣ከሎጂክና ከሰብአዊ አእምሮ ጋር የሚጋጨውን እውነት ብዬ እንዳምን የምታደርገኝ ይመስል ለምን ሮም ሮም እንደምትሉ አላውቅም !

- እኔ አእምሮህን አውልቀህ አስቀምጥ፣ሎጂክን ተጻረር አላልኩህም። አትቸኩል፣አእምሮ አለህ ታስባለህና አሳማኝ ሆኖ ካላገኘህ የምትፈልገውን አድርግ ነው ያልኩህ። ደሞም እኔ የመጣሁት ባንተ ጥያቄ ነው፣ምንም ነገር አልጫንኩብህም፤እናም ይህ ውርጅብኝ በኔ ላይ ለምን ?

- አደም ይቅርታ፣እኔ በተፈጥሮዬ ችኩል ነኝ። እመነኝ ፍላጎቴ በተቻለ መጠን ቶሎ የመታደልን መንገድ ማግኘት ነው። ከቀዶ ጥገናው በፊት ይበልጥ ያስፈራኝ የነበረው ትልቁ ነገር የመታደልን መንገድ ሳላውቅ እንዳልሞት ነበር።

- በእግዚአብሔር ፈቃድ ትደርስበታለህ፣ታገኘዋለህ። አንተ ያልዘገየህ ብቻ ሳትሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዝክ ብትሆንም ጭራሽ ከማጣት ዘግይቶ ማግኘት የተሻለ ነው።

- አደም ደጋግሜ ይቅርታ እጠይቀሃለሁ፣ምናልባት ችኩል ሆኜ ይሆናል፤ወይም ደግሞ በነዚህ ርእሰ ጉዳዮች ተሰላችቼ ሊሆንም ይችላል።

- ቶሎ ለመድረስ በመጓጓት ተቻኩለህ ከሆነ አንድ ነገር ነው፣መሰላቸት ግን ሳያጠናቅቁ መቆም ማለት በመሆኑ አደጋ ነው።

- አደጋ ! ትንሽ ያጋነንክ አይመስልህም ? !

- ጽናትና ቁርጠኝነት የሌለው ሰው የትም አይደርስም፣ምንም ነገር አያሳካም። መሰላቸት ማለት ደግሞ ቁርጠኛ አለመሆን ማለት ነው፤የመጓኋትህ ውጤት የሆነው የችኩልነት ስነ ልቦና ከዚህ ጋር እንዳይጋጭብህ።

- እስማማለሁ፣ስሜትህ ግን ቶሎ ይገነፍላል፣ይህን አላስተዋልክም ?

- ሊሆን ይችላል፣ዓላማህ እኔን ለማስበርገግ መሆኑ ግን አልታየህም ?

- እህህ አልፎ አልፎ . . አንተ ቶሎ ቱግ ትላለህ።

በዚህ ወቅት . . ካትሪና ወደ አባታቸው አልጋ ከሚሮጡት ማይክልና ሳሊ ጋር ወደ ክፍሉ ገባች። በናፍቆት አቀፋቸው . . ለጥቂት ጊዜ አደምን ተወት አድርጎ ከነርሱ ጋር በማውራት ተጠመደ . . አደም ለደቂቃዎች ከጠበቀ በኋላ ለመሄድ ወሰነ . .

- አስተማማኝ ጤንነት ላይ መሆንህ አስደስቶኛል፣አሁን እንድሄድ ፍቀድልኝ።

ካትሪና ፈገግ ብላ ለአደም ፦

- ይቅርታ አደም፣ማይክልና ሳሊ ከቀዶ ጥገናው በኋላ አባታቸውን አላዩም፣ቀደም ሲልም ጉዞ ላይ ስለነበር ሳያገኙት ብዙ ጊዜ ሆኗቸዋል።

- ስለምን ይቅርታ ትጠይቂያለሽ?! ጭውውታችንን ጨርሰናል፣ወዳጄ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን አይቼ ተጽናንቻለሁ፣እኔም ሥራ ስላለብኝ መሄድ እፈልጋለሁ።

- አደም ምስጋናዬ የላቀ ነው፤ከመጓዜ በፊት አገኘሃለሁ?

- ካንተ ጋር መገናኘት ደስታዬ ነው፣ባንገናኝ እንኳ ቢያንስ እንደዋወላለን። ፍቀዱልኝ ልሂድ።

አደም ከወጣ በኋላ ካትሪና ሀሳብ ሰነዘረች ፦

- ይህን ወዳጅህን እዚህ ሆስፒታል እንጂ አላየሁትም፤ነገር ግን የላቀ ስነ ምግባር ያለው በጣም የተገራ ድንቅ ሰው ነው፣ሲያዩት እኔ እንጃ በጣም ቀለል ያለና የሚመች ነው።

- ምናልባት እንዳንቺው ካቶሊክ ስለሆነ ሊሆን ይችላል !

- ሁሉም ካቶሊኮች የተገራ ጸባይ ያላቸው ድንቅ ሰዎች ናቸው፤ግና ቀደም ሲል ሃይማኖቱን እንደማታውቅ ነግረኸኝ ነበር።

- እስካሁንም ድረስ አላውቅም፤ይሁን እንጂ ወደ ሮም እንድሄድና ካቶሊካዊነትን በጥልቀት እንዳውቅ ያለው ጉጉት በአተያዩ መንገድ ሁሌ ካንቺ ጋር የሚስማማ መሆኑ ካቶሊክ መሆኑን ያረጋግጥልኛል። ታውቂያለሽ ዛሬ ደግሞ ካቶሊካዊነትን ያለ ቅድመ ውሳኔ በነጻ አእምሮ እንዳጠናው ሊያሳምነኝ ይፈልጋል።

- እህህ፣መልካም ነው፣ምናልባት ስታጠናው ዝግ ሆነህ ይሆናል፤ምናልባት ደግሞ ከባለቤትህ ያላገኘኸውን መረጃ ከወዳጆችህ ታገኝ ይሆናል . . በነገራችን ላይ ወደ ሮም መጓዛችን መረጋገጡን ለልጆቹ አሳውቄአለሁ፣እነሆ ከፊትህ ናቸውና የሚጠይቁትን አዳምጣቸው።

- በሉ ጠይቁ . . ምንድነው የምትፈልጉት?

- ባባ ረሳህ እንዴ?

- ምንድነው የረሳሁት?

- የቅዱስ አንጅሎን አምባ ለማየት እንደምፈልግህ ነግረህ ነበር፤ሳሊ ደግሞ የትሬቪን ፏፏቴ ለማየት ነው የጠየቀችው።

- ይቅርታ፣እውነትም ረስቼ ነበር።

- ጉብኝቱ ሆቴል ቁጭ ብሎ ማንበብ፣ኮምፒውተር ላይ መስራትና ሙለውን ጊዜ በመወያየት ማሳለፍ ብቻ እንዳይሆን ስጋት አለኝ።

- ለናንተ የተለየ ጊዜ እንደምሰጥ ቃል እገባላችኋለሁ።

- ባባ ቃል ነው?

- እናታችሁ ምስክር ነች፣ቃል ገብቻለሁ።

- እኔም ቃል እገባላችኋለሁ፣አባታችሁ ምስክሬ ነው።

ቤተሰባዊው ጭውውት ሞቅ ያለና አስደሳች ነበር፤የምሳ ሰዓት ሲደርስ ካትሪና ለልጆቹ እንዲህ አለች

 

- አሁን ብንሄድና በጣሊያን ሬስቶራንት ምሳ ብጋብዛችሁ ምን ይመስላችኋል?

- ድንቅ ነው !

- በሉ እንሂድ።

ካትሪና ከልጆቹ ጋር ስትሄድ ጆርጅ ምሳውን በልቶ ወደ ንባቡ ተመለሰ . . ሆስፒታል ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በጥልቀት ሲያነበው የነበረውን ሲያስታውስ ሀሳብ ገባው . . ብዙ ባነበበ ቁጥር እርስበርስ የሚጋጩ ጉዳዮች እየበዙ ይመጣሉ፣በተለይም እርሱ የክርስትና ጣዖታዊነት፣ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱንና የሃይማኖት መሪዎችን አማልክት አድርጎ መያዝ ብሎ የሚጠራውን በተመለከተ
! ይህን ሁሉ ተቃርኖ በአንድ ጉዞ ማስወገድ ይቻላል . . ! ይህ እውን መሆን ከቻለ ምናልባት ፓፓዊው ሥርዓት ትክክለኛ ሊሆንና እሱም እንደ ካትሪና እና እንደ አደም ካቶሊካዊ ሊሆን ይችላል . . !

ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . . (3)

ጆርጅ ከእንቅልፉ አማልዶ ተነሳ። ቁርሱን ከበላ በኋላ እንደ ልማዱ ወደ ንባብ ገባ። ሊነበብ የሚገባ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ይዟል፤‹‹አይነኬ ትረካዎች በኦሪት›› የተሰኘውና በጆናታን ክሪች የተደረሰ መጽሐፍ። በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ ስለ መጽሐፉ የቀረበውን ሐተታ አነበበ

፦ ‹‹

በዚህ አስገራሚ መጽሐፍ ውስጥ ደራሲው፣ብሉይ ኪዳን በምዕራቡ ዓለም ስነ ጽሑፍ ውስጥ አስደንጋጭ ትረካዎች በመሆናቸው በዘመን ርዝመት ምክንያት በተደበቁና ከሁሉም ይበልጥ አስበርጋጊና ግልጽ በሆኑ ትረካዎች የተሞላ መሆኑን ይነግረናል። . . ›› ቀሳውስትና መነኮሳት ለሰው ልጅ ይበልጥ የሚበጀውንና የማይበጀውን ነገር ከእግዚአብሔር በላይ ያውቃሉ ተብሎ እንዴት ሊታሰብ ይችላል? በብሉይ ኪዳን ውስጥ የማያውቃቸው ታሪኮች የትኞቹ እንደሆኑ ራሱን ጠየቀ። ትረካዎቹ ለምንና እንዴት ሊደበቁ ቻሉ? ቀደም ሲል ከሌቪ ጋር ከተነጋገሩባቸው ታሪኮች ይበልጥ በግድያና በአመጽ የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ? ዛሬ ቀጠሮ ስላለው ቶም ከመምጣቱ በፊት ለማንበብ ወሰነ።

መጽሐፉ አንዳንድ ርእሰ ጉዳዮችን ለመደበቅ በትርጉም

አማካይነት ማጭበርበር ብቻ ሳይሆን ከኦሪጂናሉ የዕብራይስጥ ቅጂ ለአንባቢ እንዲመች ተደርገው የቆርጦ መቀጠል

ሥራዎች እንዴት እንደተከናወኑ

በስፋት ያጋልጣል። ይህን የሚያደርጉትም እነዚህን የወሲብ፣የእርቃነ ገላና የአመጽ ትረካዎች ሕጻናት እንዲያነቧቸው እንዴት እንተዋለን? በሚል ማመካኛ ነው። ሌላ ጊዜ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን አይልም፣ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው የሚለውን የሓኻሞች አባባል በምክንያትነት ያቀርባሉ። ሁሉም ግን ታሪኮቹን ለመደበቅ ወይም ለማዛበትና ለማጭበርበር የሚደረግ ከንቱ ሙከራዎች ናቸው። ታዲያ ይህን ሁሉ እነሱ ከፈጣሪ አምላክ ይበልጥ ያውቃሉ ማለት ነው? ወይስ መጽሐፉ ከእግዚአብሕር ዘንድ የተላለፈ አይደለም ማለት ነው? ወይ ደግሞ ያሁኑ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር የተላለፈው የጥንቱ ቅጂ የተበረዘ የተከለሰና የተምታታ አዲስ ቅጂ ወይም ድርሰት ብቻ ነው?
ጆርጅ በከፍተኛ የመረበሽና የመደናገጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ንባቡን ቀጠለ። በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን) ሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች (አይሁዳዊነት፣ክርስትና እና እስላም) ያምኑበታል። በመሆኑም
መጽሐፉን
መተቸት
ሁሉንም መለከኮታዊ ሃይማኖቶች መተቸት ማለት ሊሆን ይችላል
! በዚህ የጆናታን ክሪች መጽሐፍ ውስጥ ሰክሮ እርቃኑን ስለሆነው

ኖሕ

፣በሎጥና በሁለት ሴት ልጆቹ መካከል ስለ ተፈጸመውና እንዴት ተራ በተራ ከአባታቸው ጋር እንደተኙ ስለሚያወራው ወራዳ ወሳባዊ ትረካ፣በያዕቆብ ልጅ በሮቤል እና በአባቱ ቁባት መካከከል ስለተፈጸመው ወሲባዊ ቅሌት . . አነበበ። በሥጋ ዘመዳ

ሞች መካከል እንኳ ሳይቀር የተፈጸሙ የወሲብ ቅሌቶችን የሚተርኩ ጥቅሶችን እያቅለሸለሸው አነበባቸው።

ጤናማ ሰብአዊ አእምሮ የሚጠየፋቸው እነዚህ ወሲባዊ ቅሌቶች እንዴት ሆነው ስለ እግዚአብሔር ነብያትና መልእክተኞች የሚተርኩ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመጠየቅ

ጆርጅ በእጅጉ ተገረመ። እነዚህን አጸያፊ ትረካዎች አንብቦ መጨረስ

ፈተና

ሆነበት . . እንደ ምንም ብሎ፦

‹‹ተለዋዋጭ ባሕርይ ያለው ባዙቃዊ አምላክ፣ሕይወት ሰጭ ከመሆን ይልቅ በአብዛኛው አውዳሚ የሆነ . . ››

በማለት የእግዚአብሔርን ባህርያት ወደሚገልጸው ክፍል ደረሰ።
ተገቢ ያልሆኑ አስቸጋሪ ባሕርያት መሆናቸው ተሰምቶት እንዲህ
ያለውን አምላክ ማምለክ ፈጽሞ አይቻልም ሲል ደመደመ!
እንዲህ ያለውን ድፍረት በፈጣሪ አምላክ ላይ መፈጸም እንዴት ተደርጎ ሊታሰብ ይችላል?! መጽሐፍ ቅዱስ ፈጣሪ አምላክን ከሚያከብርና ከሚቀድሰው በበለጠ ላም የሚያመልኩ ወገኖች
ላሚቱን አምላካቸውን ያከብራሉ፣ይቀድሳሉ።
ስለ ቅድስቷ ዝሙተኛ ስለ ታማራ ታሪክ እያነበበ ጆርጅ በጀርባው ተኝቶ ሳቁን ለቀቀው
! በቤተመቅደስ ውስጥ እስከ ተፈጸመ ድረስ ዝሙት የተቀደሰ ተግባር መደረጉ አስገረመው። እንዳውም አንዳንዶች ቅድስት ዘማዊት መነኩሲት አልያም ይሁዳ ዝሙት የፈጸመባት የልጁ ሚስት ሳትሆን አትቀርም ይላሉ። ጆርጅ እያነበበ ያለው ነገር አቅለሸለሸው፤እነዚህን የቅሌት ትረካዎች አንብቦ መጨረስ ተሳነው። በየጊዜው መገናኛ ብዙኃንን የሚያጣብቡና በካቶሊክ ካህናትና መነኩሴዎች የሚፈጸሙ የወሲብ ቅሌቶችን የሚመለከቱ ዜናዎች ትዝ አሉት።

መጽሐፉን

ዘግቶ ኮምፒውተሩን ከፈተ፤ወደ ዩትዩብ ድረገጽ ገባና ‹‹የቤተክርስቲያን ወሲባዊ ቅሌቶች›› ብሎ ጻፈ። በድምጽና በምስል ማስረጃዎች ተደግፈው የመጡ የቤተክርስቲያን ወሲባዊ ቅሌቶች መረጃ ብዛትና ዓይነት አስበረገገው። ሁለቱ ካቶሊኮች አደምና ካትሪና እንደ መከሩኝ ወደሮም የማደርገውን ጉዞ ገፍቼበት የካቶሊክን ሕጸጾች መመርመሩን ልቀጥልበት? ወይስ ጉዞውን ለሽርሽር ብቻ አድርጌ የመታደልን መንገድ ልርሳ? ሲል ራሱን ጠየቀ። ይሁን እንጂ የመታደልን መንገድ ቢረሳ ወደ ነበረበት የእርግማንና የጥርጣሬ መንገድ እንደሚመለስ ወይም አእምሮንና እውቀትን በሚያወድም ኃይሉ የሰው ልጅ ሰብእና አውዳሚ ወደሆነው ኤቲዝም እንደሚያመራ ያውቃል። ሀሳቦች አእምሮው ውስጥ ሲፋጩ፤እያንዳንዱ ሀሳብ ሌላውን ሀሳብ አሽቀንጥሮ ከመጣሉ በፊት የገዛ ራሱን መንፈስና ልቦና አሽቀንጠሮ ሲጥልና ጥያቄዎቹን መልሶ ሲያመጣበት ተሰማው። ከሀሳቡ የባነነው በሐኪሙ ድምጽ ነበር፦

- ጆርጅ . . ኧረ አንተ ጆርጅ ! አትሰማም እንዴ?

- ወይ . . አዎ፣ኖር ዶክተር።

- እኔ አናግረሃለሁ አንተ ሌላ ዓለም ውስጥ ነህ፤ስለ ምንድነው የምታስበው?

- የማልወደውንና የምጠላውን ርእሰ ጉዳይ እያሰብኩ ነበር።

- ምን ይሆን? !

- አርስበርስ የሚጋጩና ሎጂክና አእምሮን የሚጻረሩ ጉዳዮችን እጠላለሁ።

- እንዴት ማለት?

- ስለ ቀሳውስትና መነኩሳት ወሲባዊ ቅሌቶች ሰምተሃል? !

- ኦህ . . አዎ።

- ሕጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚፈጽሙና አስገድደው የሚደፍሩ ሰዎች ለእግዚአብሔር አምልኮና ለአገልግሎቱ ራሳቸውን በታማኝነት ማዋል ይችላሉ ተብሎ እንዴት ይታሰባል? !

- ጉዳትና አደጋውን እያወቀ አስካሪ መጠጥ ወይም አደንዛዥ እጽ እንደሚጠቀመው ሐኪም ማለት ነው !

- ሔሮዊን የሚጠቀም የጤና ባለሞያና ሐኪም እናንተ ዘንድ እንዴት ነው የሚታየው?

- በሥራው ስኬታማ ያልሆነ ሐኪም ነው፤ከሞያውም ሊባረርና ሊጋለጥ ይገባል !

- ስለ ሐኪሞቹ ኃላፊነት ያለበት ወገን ዕድገት የሚሰጣቸው፣ የሚሸልማቸውና ጥፋታቸውን አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን፣እነሱንና አደንዛዥ እጻቸውን የሚያስተዋውቅ፣ ስልቱንም ጭምር የሚያስተምራቸው፣ሥርዓታቸውና ሕጋቸው ይህንኑ የሚየበረታታ ከሆነሳ !

- ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፤ይሁንና ንግግራችንን እንቀጥልና እንዲህ ያለው ወገን ተባባሪና እኩይ በመሆኑ ሰዎች ሐኪሞችን፣ሆስፒታሎችንና ሕክምናንም በጥቅሉ በጥርጣሬ ዓይን እንዲመለከቱ የሚያደርግ ነው፤ምን ለማለት ፈለግህ?

- የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች መነኩሳቱንም ጭምር ወሲብ፣ዝሙት፣ብልግና እና አስገድዶ መድፈርን አይደለም የሚያስተምሩት? መጽሐፍ ቅዱስ ነብያትንም ጭምር በሚያካትት መልኩ እንዲህ ባሉ ትረካዎች የተሞላ አይደለም ወይ?

- ምንም አልገባኝም፤ይበልጥ ትክክለኛ ልሁንና ካንተ ምንም ነገር እንዲገባኝ አልፈልግም። ታዲያ ኢአማኝ እንድንሆን ነው የምትፈልገው?! በሕክምናው ዓለም ብዙዎቹ ኤቲስት ሐኪሞች የላቀ ቦታ ያላቸውም ጭምር የስነ ልቦና ሕሙማን ወደመሆን የቀረቡ መሆናቸውን በሚገባ እናውቃለን፣ ወይም ቢያንስ በሕይወታቸው ደስተኞች አይደሉም። የኔን ምክር የምትፈልግ ከሆንክ ከራስህ ሽሽ፣አሳማኝ ሆነው ብታገኘው እንኳ ከዚህ አመለካከት ራስህን አግልል፤በሆነ መንገድ ሽሽ . . በጫወታ፣በመጠጥ፣በሴት፣በሥራ ወይም በሆነ ነገር፣ብቻ ሽሽ።

- ከራሳችን ሸሽተን ደስተኝነትን ማግኘት እንችላለን? !

- አዝናለሁ ያንን መታደል ፈጽሞ አይቻልም። ከኤቲዝምና ከእግዚአብሔር ከመራቅ መርገምት አንጻር ይኸኛው መርገምት ግን መታደል ተደርጎ ይወሰዳል . . አስደሳቹን ጭውውት በማቋረጤ አዝናለሁ። የመጣሁት ዛሬ ማምሻውን ስለምትወጣ ስለ ጤንነትህ ሁኔታ ብቻ ጥያቄዎች ካሉህ ለመመለስ ነው። በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት የሰውነትህን የሙቀት መጠን እንድትከታተል እንመክረሃለን። ጥያቄ ይኖረሃል? ከሕክምና ጋር የተያያዘ ጥያቄ ብቻ ማለቴ ነው? !

- የለኝም አመሰግናለሁ . . ከሁለት ቀን በኋላስ የሙቀት መጠኑን መከታተል ያስፈልገኛል?

- አያስፈልግም . . ሁለቱ ቀናትም ለተጨማሪ ጥንቃቄ ብቻ ነው። የሙቀት መጠኑ ከተረጋጋ ጤንነትህ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል ማለት ነው።

ቶም ገባ . . ለሐኪሙና ለጆርጅ ሰላምታ አቀረበ . . ሐኪሙ ወደ ሥራው ለመሄድ ለቆ ሊወጣ ሲል ጆርጅ ቀደመውና . .

- ከሕክምና ጋር ያልተያያዘ አንድ ጥያቄ እንዳቀርብ ትፈቅድልኛለህ?

- በፍጥነት መሆን አለበት፣ቀጥል።

- ሽሽት መታደልን የማያስገኝ መሆኑን የምታውቅ እስከሆንክ ድረስ ለምን ትሸሻለህ?

- ኤቲዝምን በመፍራት፤ቢያንስ በኔ አመለካከት ኢአማኝነት መርገምት ነው።

- ኤቲዝም ወይ ሽሽት? ! ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም? !

- እኔ አልደረስኩበትም እንጂ ሦስተኛ አማራጭ ምናልባት ሊኖር ይችላል። አንተ ከደረስክበት ንገረኝና ባለውለታዬ ትሆናለህ . . አሁን ልሂድ፣ከመውጣትህ በፊት ጤና ነክ ጥያቄ ካለህ እንድትደውልልኝ ለነርሷ ንገራት፣ደህና ሁን።

ሐኪሙ

ሲወጣ ቶም አይቶ ወደ ጆርጅ ፊቱን አዞረና . .

- ጆርጅ በሁለታችሁ መካከል ሲካሄድ የነበረው ውይይት ምን እንደሆነ አላውቅም፤የኤቲዝምን መርገምትነት፣የሚያስከትለውን ጭንቀትና ውጥረቱን ግን ከማንም በላይ አውቃለሁ።

- ኤቲዝም ለምን መርገምት ሆነ ትላላችሁ?

- የምትጠጋበትን፣ጉዳይህን ሰጥተኸው የምትመካበትንና የምትተማመንበትን አለማግኘት፣መንገድና አቅጣጫ እንዲያሳይህ የምትጠይቀውን አለኝታ ማጣት ከሁሉም በላይ አስቸጋሪ ነገር ነው።

- መንገዴን እንዴት ነው ከርሱ የማውቀው?

- ወደኛ በላካቸው ነብያት፣መልእክተኞችና መጽሐፎቹ አማካይነት ማወቅ ትችላለህ።

- ዝሙተኛ መነኩሲት ወይም አስገድዶ የሚደፍር ካህን ወይም መነኩሴ መንገዱን ይመሩኛል ብዬ እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

- አልገባኝም።

- ሰክሮ ዝሙት የሚፈጽም ነብይ ወይም በወሲባዊ ትረካ የታጨቀ ቅዱስ መጽሐፍ እንዴት መንገድ ይመራኛል?

- ጆርጅ ምን ነካህ? ዛሬ ለምንድነው እንዲህ የምትናገረው?

- ወዳጄ ቶም ታከተኝ፣ወደ ሮም ላለመጓዝ ከተጓዝኩም ለሽርሽር ብቻ እንዲሆን ከምር እያሰብኩበት ነው።

- ለምን . . ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?

- አዲስ ነገር የለም፣በብሉይና አዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ወሲብና ስለ አመጽ ብዙ ብዙ ነገሮችን አነበብኩ፣አየሁ።

- ታዲያ ይኸ ካቶሊክን ብቻ የሚመለከት ነው?!

- ምን ማለትህ ነው?

- የፕሮቴስታንቶች የአመጽና የነውጥ ሥራ ተመሳሳይ እንዲያውም ከዚያ የከፋ አይደለም ወይ? በታሪክ ውስጥ ታይተው በማይታወቁ አስከፊ አረመኔዊ ጭፍጨፋዎች የጀርመንና የሌሎች አገሮች ካቶሊክ ሕዝቦችን ማን እንደፈጀ ታውቃለህ?

- አዎ ፕሮቴስታንቶች ናቸው። ግና ታክቶኛል፣ምናልባት ፕሮቴስታዊነትም ጭምር ዋጋ ቢስ ነው።

- ጆርጅ እንዳስለመድከን ጠንካራ ሁን። ደካማ ተሸናፊ እንዳትሆን ተጠንቀቅ። ጽናትና ቁርጠኝነት ካለህ ወደ መታደል መንገድ ትደርሳለህ። ደካማ ተሸናፊ ከሆንክ ግን መድረሻህ ወደ ጭንቀትና ውጥረት እርግማን ይሆናል።

- ምን ላድርግ?

- እኔ እንጃ፣የማውቀው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ወደርሱ የሚያደርሰውን መንገድ የማይደብቅ መሆኑን ብቻ ነው።

- ይህ መንገድ የት ነው ያለው? ክርስቲያኖች ሙስሊሞችም በዚያ በወሲብና በአመጽ ትረካዎች በተሞላው መጽሐፍ በብሉይ ኪዳን ያምኑ የለም? ስለዚህ ጉዳይ ስትነግረኝ ሌቪን ማመን ቸግሮኝ ነበር። አሁን ግን በዓይኔ በብረቱ አይቼ የነገረችኝ ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁ። ከብሉይ ኪዳን ማስረጃ እንድጠቅስልህ ትፈልጋለህ?!

- ፈጽሞ አያስፈልገኝም፤ይልቁንም ተጨማሪ ካስፈለገህ ከአዲስ ኪዳንም ጭምር ማስረጃ ልሰጥህ እችላለሁ።

- ታዲያ ሁለቱም በዚያው ተመሳሳይ መንገድ የሚሄዱ እስከሆኑ ድረስ ክርስትና እና እስላምን በመመርመር ለምን እንደክማለን?

- ከመጀመሪያው መንገዱን ፈልገን ለማወቅ ነው የተስማማነው። ወደ መንገዱ ለመድረስ መቃረባችን ለምን እንደሚሰማኝ አላውቅም። በእሽቅድምድሙ መጨረሻ ላይ እጅ አትስጥ . . ጆርጅ አንተ ለራስህ ብቻ አይደለም ፍለጋ የምታካሄደው፣እኔም ንባቤና ምርምሬ ካንተ ጋር ሆኗል፣እርግጠኛ ነኝ የመታደልን መንገድ እናገኘዋለን፣ግን እንዴት ብለህ አትጠይቀኝ።

- የኔም ስሜት ተመሳሳይ ነው፤ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ በራሴና በስሜቴ እየቀለድኩ ይሁን ብዬ እጠይቃለሁ። ሁሉም ማስረጃዎች መባዘንንና ከመንገድ መዛነፍን የሚያመለክቱ ቢሆንም በውስጤ ግን ከመንገዱ በቅርብ ርቀት ላይ መሆኔ ይሰማኛል።

- ወደ ሮም ተጓዝና ካቶሊካዊነትና ፕሮቴስታዊነትን በቅርበት መርምር። ያነበብካቸውን ጉዳዮች ተመልከት፣ተወይይባቸው፤ሁሉንም መለኮታዊ ሃይማኖቶች በጥናት ከማዳረስህ በፊት የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አትድረስ።

- እስላምንም እናጠናለን?!

- አዎ ያለ ምንም ጥርጥር፤አንድን ነገር ማጥናትና መመርመር ማለት በዚያ ነገር ማመን ማለት አይደለም። ስለቡድሂዝም፣ህንዱይዝምና አይሁዳዊነት አንብበህ የለም? አጥንተህ የለም? ታዲያ ምኑ ነው አዲስ? ሁሉንም መለኮታዊ ሃይማኖቶች መርምረን ከማወቃችን በፊት ላለመወሰን ቀደም ብለን ተስማምተን የለም?!

- እቀጥልበታለሁ፤የመታደልን መንገድ እንደማገኝ በውስጤ እርግጠኛ ብሆንም እስካሁን ባየኋቸው አመለካከቶችና ሃይማኖቶች ውስጥ ያጋጠሙኝ ተግዳሮቶች አፈተረት፣አመጽ፣ወሲብ፣መበረዝ፣መዛባትና እርስ በርስ መምታታት ናቸው።

- ወደ መታደል መንገድ ለመድረስ አሁንም አጥብቀህ አስብ። ፍለጋውና መድረሱ እንዲሁ ቀላል ቢሆን ኖሮ ይህን ሁሉ ጥረትና ድካም ባላስፈለገን ነበር!

- እደርስበታለሁ፤ምናልባትም መፍትሔው ቀላልና ግልጽ ሆኖ ከአጠገቤ እያለ ለማየት ሳልችል በመቅረቴ እገረም ይሆናል።

- መንገዱ ምናልባት ካቶሊካዊነት ወይም ፕሮቴስታንታዊነት . . ወይም እስላም ሊሆን ይችላል።

- እነዚህ መንገዶች ሁሉ በአፈተረት፣በማጭበርበር፣ሃይማኖትን ለሥልጣን፣ለገንዘብና ለወሲብ በመገልገል የተሞሉ ናቸው የሚል እምነት ቢኖረኝም የፍለጋ ጉዞውን እንቀጥልበታለን። ለመሆኑ አንተ ምን ትመክረኛለህ?

- ብዙ አንብበሃል?

- አዎ ማንበቤ እንጂ ያታከተኝ ምን አለና! በነገራችን ላይ ካቶሊካዊነት ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማብራሪያ ጋር ካልሆነ መጽሐፍ ቅዱስን እንኳ እንድናነብ አይፈልግም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ነገር መረዳት ያለብን ፓፓው በሚረዳበት መንገድ ብቻ ነው። አእምሯችንን አውልቀን እንድናስቀምጥ ይፈልጋሉ!!

- ልክ ነህ፤ፕሮቴስታንት ግን በሚፈልጉት መንገድ አዲስ ሃይማኖት ጠፍጥፈው መስራት ይፈልጋሉ። በሚፈልጉት መንገድም ይረዱታል። በዚህ ምክንያት ነው ለዘመናት ብዙ ቦታ ሲከፋፈልና ሲሰነጣጠቅ የኖረው።

- ፓፓው በሚፈልገው መንገድም ሆነ እኛ በምንፈልገው መንገድ ብረዳው አዲስ ኪዳን በመሰረቱ ለመበረዝና ለመምታታት የተጋለጠና በስህተቶች የተሞላ በመሆኑ የተዛባ ነው። እነዚህ ሃይማኖቶች አይረቡም፣አፈተረት ናቸው ብየህ አልነበረም?

- መልካም፣የበለጠ አንብብ፣የበለጠ እወቅ፣የበለጠ ተወያይተህ ተከራከር፣የበለጠ ክፍትና ነጻ አእምሮ ይኑርህ። ይህን ስታደርግ መንገዱ ይታየሃል።

- ካቶሊካዊነት ግን ለምን የሚል ጥያቄ በማይቀርብባቸውና ውይይት በማይካሄድባቸው ምስጢሮች ላይ የተመሰረተ ነው። ከመነኮሳት ውጭ ማንም የማያውቃቸው ሰባቱ የቤተክርስቲያን ምስጢሮች!! አእምሮንና ሎጂክን የሚጻረሩ ከመሆናቸው ጋር እነዚህን መከራከር፣ማስተንተን ወይም መቃወም ከእምነቱ ጎራ የሚያስወጣ ክህደት ነው!!

- ፕሮቴስታንቶችም እንኳ ከሰባቱ ምስጢሮች በሁለቱ ያምናሉ።

- አንድ ነገር ባልኩህ ቁጥር ‹‹ፕሮቴስታንትም እንደዚ ነው›› ማለትህን አስተውልሃል? ከካትሪና ጋር ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመሄድህ ካቶሊካዊ ሆነሃል ልበል? የምትለውን ሁሉ በሚገባ አውቃለሁ፣የምናገረው ግን ስለ ካቶሊካዊነት ነው።

- ያለ ዕውቀትና ያለ ምክንያት በአንድ ሃይማኖት ላይ እንድትጫንና ወገንተኛ እንድትሆን አልፈልግም። በዕውቀትና በምክንያት ላይ ተመስርተህ ከሆነ ግን ያለ አድልዖ በሚዛናዊነት የፈለከውን በል።

- የምናገረው በዕውቀትና በምክንያት ላይ ተመስርቼ ነው።

- እኔም እንደዚያው ነኝ፤የፈለኩት የበለጠ ሚዘናዊ እንድትሆን ብቻ ነው።

ኦህ . . ልክ ነህ፤ስለነሱ የምናገራቸው አብዛኞቹ ጉዳዩች በአይሁዳዊነትና በፕሮቴስታንትም ውስጥ እያሉ ምናልባት በካቶሊካዊነት ላይ ይበልጥ ጠንከር ብዬ ይሆናል። አስላም ውስጥም እንደዚሁ ወደፊት ያጋጥሙኛል ብዬ እጠብቃለሁ።

- ስለዚህም ነገሮች ግልጽ እስኪሆኑልን ድረስ የምርምርና የፍለጋ ጉዞአችንን እንደ ጀመርነው በተረጋጋ መንፈስ እናጠናቅቅ . . አንተ አይደለህም እንዴ ‹‹ሳይወሳሰብ ቀለል ባለ ሁኔታ›› የምትለኝ?

- አዎ፣ይህች የታወቀች የአደም አባባል ናት።

- እናም የሰው ልጅ የተረጋጋ ሲሆን የበለጠ ሚዘናዊና የበለጠ ምክንያታዊ ይሆናል። ከመጀመሪያው እንደ ነገርኩህ ነገሮች ግልጽ ሆነውልህ እስክታውቃቸው ድረስ ወሳኔ ላይ እንዳትደርስ እጠይቀሃለሁ። ምናልባት ውሳኔህ ለምሳሌ ያህል አይሁዳዊነት ሊሆን ይችላልና ለምን ትቸኩላለህ?

- በቀላሉ ልንገርህና በምንም ዓይነት ውሳኔዬ አይሁዳዊነት ሊሆን ይችላል የሚል እምነት የለኝም። እኔ አመጽን እጠላለሁ፣ብሉይ ኪዳን ደግሞ በአመጻ ታሪኮች የተሞላ ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰፈሩትን እነዚህን ጥቅሶች እስኪ አስተውላቸው ፦ ‹‹ . . ሰይፉንም ከደም የሚከለክል ርጉም ይሁን፡፡› ‹‹እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፣በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፣የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው።›› እስኪ ከዚህ የከፋ ምን ዓይነት ሽብርተኝነት ይኖራል?!

- ክርስቲያኖችና ሙስሊሞችም በብሉይ ኪዳን ያምኑ የለም?! እናም የበለጠ ተለሳለስና ነገሮች ሙሉ በሙሉ ፍንትው ብለው እስኪገለጹልህ ድረስ ውሳኔ አታስተላልፍ። ወደ መታደል መንገድ እንደምትደርስ እኔ እርግጠኛ ነኝ።

- በኔ ግምት ይህ ትልቁ ችግር ነው። ክርስቲያኖች አዲስ ኪዳንን የብሉይ ኪዳን ማሟያ አድርገው ይወስዱታል፤ገና ባላጠናውም ሙስሊሞችም እነደዚያው ይመስሉኛል። ስለዚህም ሁሉም የአመጽና የሽብር ሃይማኖቶች ናቸው።

- እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦች አሉ ፦ አንደኛ በነዚህ ጉዳዮች ውስጥ የይሆናል ግምት ቦታ የለውም። ሀሳብህ መመስረት ያለበት በዕውቀትና በማስረጃ ላይ ብቻ ሊሆን ይገባል። ሁለተኛ ይበልጥ እርግጠኛ እንድትሆን እፈልጋለሁ። አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ማሟያ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ያምኑበታል ማለት ነው ወይስ አይደለም?

- ባልከው ነገር እስማማለሁ፣‹‹ይመስለኛል›› ግምት እንጂ ዕውቀት አይደለም። የበለጠ ማንጓለልና ማንጠርም ከዋነኛ ጉዳዮች አንዱ ነው። አሳዛኙ ነገር ክርስቲያኖች ‹‹ማሟያ›› የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ በሚገባና ግልጽ በሆነ ሁኔታ አላነጠሩትም፤ያላነጠርኩት እኔ አይደለሁም። ለምሳሌ ያህል ካቶሊኮች ተከታዮቻቸው አዲስ ኪዳንን በቀጥታ አንብበው እንዳይረዱ ይከለክላሉ። ለራሳቸው ተረድተው እንደ እኔና እንደ አንተ ላለው ተራ ሰው ማስረዳት የሚገባቸው መነኮሳት ብቻ ናቸው ብለው ያምናሉ። ያለዚያማ የሚከተሉትን የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች ማንም በቀጥታና በግልጽ ይረዳል ፦ ‹‹በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም፡፡›› ‹‹ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግስ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው፡፡›› ጥቅሶቹ ግን ማንም ሊረዳው በሚችል ግልጽና ቀላል ቋንቋ የተጻፉ ናቸው።

- ክርስቲያኖች ለነዚህ ጥቅሶች ቀጥተኛ ያልሆኑ ንጽጽራዊ ትርጉሞች እንዳላቸው መቼም ታውቃለህ።

- ልክ ነህ ቀጥተኛ ያልሆኑ ንጽጽራዊ ትርጉሞች አሉን። ለነዚህ ጥቅሶች ተቃራኒ የሆኑና ለርህራሄና ለፍቅር ጥሪ የሚያደርጉ ጥቅሶችም አሉን። ቀጥተኛ ያልሆነ ንጽጽራዊ ትርጉም ሎጂካዊ ባይሆንም ከንጽጽራዊነት የሚያልፍ አይደለም። ንጽጽራዊ ትርጉሞቹ በዚህ በተሞላው ብሉይ ኪዳን ካለን እምነታችን ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም። በሚያሳዝን መልኩ ከሌሎች ጋር ብቻ ሳይሆን እርስ በራሳችን መካከልም ተግባራችን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። ስለ አረመኔያዊ የጭካኔ ተግባሮቻችን ምሳሌዎችን እንድጠቅስልህ ትፈልጋለህ?

- ለአሁኑ ይህ ርእሳችን አይደለም፤ነገሮችን በቦታቸው እናስቀምጥና ጠቅለል ባለ መልኩ እንመልከታቸው። ማንኛውንም ሃይማኖት ለማጥናት በአምላኩ፣በነብዩ፣በመጽሐፉ፣በእምነቶቹ፣በሕግጋቱ፣በታሪኩ እና በገሃዳዊ ሁኔታው ላይ ማተኮር ተገቢ ይሆናል። በዚህ ጥናት ተመራጭ የሚሆነው በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ሳይሆን በአጠቃላይ መርሃዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ነው።

- መልካም፣እንዴት ማለት ነው?

- በብሉይ ወይም አዲስ ኪዳን ውስጥ በአንድ የተወሰነ ጥቅስና በንጽጽራዊ ትርጉሞቹ ላይ ከማተኮር ይልቅ፣ከተአማኒነቱና በትክክል ከመተላለፉ አንጻር፣ከጸሐፊዎቹና ከትምህርቶቹ አንጻር፣እግዚአብሔርንና ነብያቱን አስመልክቶ ከሚያራምዳቸው እምነቶቹ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ በሆነ እይታ እንመልከት። የተቀሩት ዝርዝር ጉዳዮች መሰረታዊውን ጉዳይ ለማረጋገጥ የሚቀርቡ ምስክሮች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም።

- በጣም ጥሩ፤በዚህ ላይ ብዙ ያነበብኩ ቢሆንም የበለጠ እስካነብና የበለጠ እስክወያይባቸው ድረስ ማቆየት እችላለሁ።

- የበለጠ ለማብራራት እንዳልከው የአይሁዳዊነት ጥናትህን ከብሉይ ኪዳን ጨርሰሃል እንበልና ትምህርቶቹ ምንድናቸው? ስለ እግዚአብሔር ነብያት ያለው አመለካከትስ ምንድነው?

- ከእግዚአብሔር የተላለፈ ነው ተብሎ ይገመታል።

- እግዚአብሔር ነው የጻፈው? ሙሴ ነው የጻፈው? አሮን ነው የጻፈው? ጸሐፊው ማን እንደሆነ ታውቃለህ?

- አዲስ ኪዳንን በተመለከተም ይህንኑ የምትጠይቅ ይመስለኛል?

- ያለ ጥርጥር፤ባላደርግማ ሚዘናዊ አልሆንኩም ማለት ነው። እንዲህ ዓይነቱ የእሳቤ ስልት ወደ መታደል መንገድ ሊያደርሰን የሚችልና ሰጥቶ መቀበልን በሚያስተናግዱ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳንጠመድ የሚያደርገን ስልት ነው።

- ግሩም ሀሳብ ነው፣እስማማበታለሁ።

- ከሮም ከተመለስክ በኋላ ሁለት ዋና ዋና መለኮታዊ ሃይማኖቶችን ገምግመን ለመጨረስ እንችላለን፤የሚቀረን አንዱ ብቻ ይሆናል። እናም አጠቃላዩ ሥዕል ግልጽ ስለሚሆንልን የመታደል መንገድ ፍለጋ ጉዞአችንም ይጠናቀቃል ማለት ነው።

- ሁሉም የማይረቡ መሆናቸው ግልጽ ቢሆንልንስ ?!

- ቀደም ሲል በነበርኩበት ሁኔታ ላይ ብሆን ኖሮ ወደ ኤቲዝም እንመለሳለን እልህ ነበር። ይህን የፍለጋ መንገድ እንድትከተል የፈለኩት ዞረህ ወደ ኤቲዝም እንድትመለስ ነበር። አሁን ግን ሁሉም ሃይማኖቶች የማይረቡ ሆነው ቢገኙ እንኳ እንደገና ወደ ኋላ ተመልስን ሥራችንን ሙሉ በሙሉ እንገመግማለን። ሃይማኖት አስፈላጊ ነው? ከሆነ ሃይማኖትን የምንመርጠው እንዴት ነው? ብለን በመነሳት እንደ አዲስ እንጀምርና አሁን እስካለንበት ድረስ እንቀጥላለን፤ይህን ስናደርግ ነገሮች የበለጠ ግልጽ ይሆኑልናል።

- በጣም ረዥም መንገድ ነው!

- እንደገና ወደ ኋላ አንመለስም ብዬ አስባለሁ፣ምኞቴም ነው። ጉዳዩ ከዕውቀት ጋር የተሳሰረ ነው፣ማለትም ዕውቀት በጨመርን ቁጥር አርቆ ማሰብና ግንዛቤያችን ይጨምራል። በተቃራኒው ደግሞ ብዥታዎች በጨመሩ ቁጥር አለማወቃችን ጨምሮ ከጥያቄዎቻችን ምላሽ የሚኖረን ርቀት ይጨምርና ከመታደል መንገድም እንርቃለን። እንደምትደርስ እኔ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ፣ግና ትንሽ ታገስ።

- ያለ ምንም ጥርጥር እደርሳለሁ፣(ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ ከሁሉም በላይ የሚያንገላታኝ ወደ መንገዱ የሚወስደውን መንገድ አለማየቴ ነው።

- ወደ መንገዱ የሚያደርሰው መንገድ ግልጽ ነው፣ገና ያላየኸው ግን መንገዱን ራሱን ነው። ሰዎች ብዙ ጊዜ ወደ መንገድ የሚወስደውን መንገድ፣የሚፈልጉትና ያላዩት መንገድ አንዱ አካል አድርገው ያስባሉ።

- ጥሩ ፍልስፍና ነው፤ወደ መንገድ የሚወስደው መንገድ እንዴት ግልጽ እንደሆነ ግን አብራራልኝ።

- ከመጀመሪያው አንስቶ የኤቲዝምንና የሴኩላሪዝምን መንገድ ውድቅ ማድረግህን ታውቅ የለም? ከዚያም የሰው ሰራሽ ምድራዊ ሃይማኖቶችን መንገድ ውድቅ አድርገሃል። በመቀጠልም ከመለኮታዊ ሃይማኖቶች ውስጥ አንዱን ለመምረጥ ማነጻጸርና ማመዛዘን ጀምረሃል። ልክ ነኝ?

- ሙሉ በሙሉ ልክ ነህ ። ለኔ ግልጽ ያልሆነልኝ ግን እንዴት ወደዚያ መድረስ እንደምንችል ነው።

- ያልኩህም ይህንኑ ነው። ያልተገለጠልህ ራሱ መንገዱ ነው እንጂ ወደ መንገዱ የሚያደርሰው መንገድ አይደለም።

- እህህ፣ደግ ነው፤ለማንኛውም ይህን እንለፈውና ለሮም ጉዞዬ ምን ትመክረኛለህ?

- በመጀመሪያ የምመክርህ በጉዞው ተደሳች እንድትሆንና ልጆቹንም በሽርሽር እንድታዝናናቸው ነው። አእምሮህን አሳርፈህ በንባብና በውይይት ያከማቸኸውን ግዙፍ መረጃህን ማቀናጀትና ማቀናበር ያስፈልገሃል። ሁለተኛ ንባብና ውይይትህን በነጻ አእምሮ ቀጥልበት። ትኩረትህን በቅርጻዊ ጉዳዮች ላይ ሳይሆን በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አድርግ። ሦስተኛ መረጃዎችህን ለማቀናጀትና ለመተንተን የሚያግዝህን የማስተዋል ስልት አብዝተህ ከተጠቀምክ በመሰረታዊ ጉዳች ላይ ብቻ ለማነጣጠር ይረዳሃል።

- መልካም፣በጣም ጠቃሚ ምክር ነው፣እጠቀምበታለሁ።ለጥያቄዎቼ መልስ ፍለጋ በመነሳቴ ብቻ እፎይታ ባገኝም በሂደቱ ውስጥ የበለጠ ስሜታዊ ሆኜ ነው ራሴን ያገኘሁት።

- የስሜታዊነትህ መንስኤ በአእምሮህ ላይ ያለው ተከታታይ ጫና ነው፤የመረጃዎችና በአካባቢህ ያሉ ሰዎች ጫና ነው። ለዚህ ነው ጭነትህ የገዘፈው፤እናም በነገርኩህ ራስህን የማዝናናት ምክሮች ጭነትህን አቃልል።

- እሽ አደርጋለሁ፤ለልጆቼም በዚህ ቃል ገብቻለሁ።

- መልካም ጉዞ እንዲሆንልህ ምኞቴ ነው። ከጉዞህ መልስ ጭነትህ ተቃሎ፣መረጃዎችህ ደርጅተውና ተቀነባብረው አእምሮህም የበለጠ ነጻ ሆኖ እንገናኝ።

- ቶም፣የበራድ ነገርስ እንዴት ሆነ?

- ጉዳዩ መባባስ የጀመረ ይመስላል። እርሱ ዘንድ ባሉት ፎቶግራፎችና የቀረጻ ቅጂዎች በግልጽ እኔን ማስፈራራት ጀምሯል።

- አንተን ማስፈራራት!

- አዎ፣ኢሞራላዊ የሆኑ የኔና ያንዳንድ ታካሚ ሴት ደንበኞቼ የቆዩ ፎቶግራፎች በእጁ ይገኛሉ። ካንዳንድ ታካሚዎች ጋር ያደረኳቸው የሕክምና ምክክር ቅጂዎችንም ይዟል። በነዚህ በኔ ላይ ጫና መፍጠር ጀምሯል፣ካልተደራደርኩ ለሕክምና ኮሚቴዎች ምክር ቤትና ለሕክምና ባለሞያዎች ማህበር አሳልፎ ለመስጠት እያስፈራራኝ ነው።

- ለሕክምና ማህበራቱ አሳልፎ ቢሰጥ ምን ጉዳት ያስከትልብሃል?

- ስሜ በአደባባይ ከመጉደፉም በላይ የሞያ ብቃት ምስክር ወረቀቴን እነጠቃለሁ።

- በምን ላይ ነው እንደራደር የሚልህ?

- ከርሱ ጋር እንድሰራ ለማድረግ።

- ከርሱ ጋር ምን መስራት?

- እህህ፣አደንዛዥ እጽ በመሸጥና ከኔ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ መፈጸም።

- የአደንዛዥ እጽ አሻሻጭ ከምትሆን ለሙያ ማህበራቱ ቢናገር ይሻላል።

- ልክ ነህ . . ግና ከሙያዬ መባረርም ከባድ አደጋ ነው።

- ታዲያ ምን ታደርጋለህ?

- አላወኩም፣ገና አስብበታለሁ። በል ደህና ሁን።

ጆርጅ ከቶም ጋር በነበረው ቆይታ ተዳሳች ሆኖ ወደ ንባቡ ተመለሰ . . ከርሱ ጋር ከተገናኘ በኋላ የመረጋጋትና የእፎይታ ስሜት ተሰምቶታል። በአነጋገሩም ተደስቷል። በተቻለው መጠን ምክሩን ተግባራዊ ለማድረግም ወስኗል። ይሁን እንጂ ከበራድ ጋር ባለው ችግር ቶምን እንዴት መርዳት እንደሚቻል በማሰብ አእምሮው ተጠምዷል . . በቶም መለወጥ እርግጠኛ ከሆነ በኋላ ችግር ሲገጥመው ብቻውን መተው አልፈለገም። ዳሩ ምን ማድረግ ይቻለዋል?
የቶምን ችግር በማሰላሰል ላይ እያለ . . ኢ-ሜይሉን ከፈተና ከሐቢብና ከሌቪ ጤንነቱን ለመጠየቅ የተላኩ ሁለት መልእክቶችን አገኘ። ቀጣዩን መልስ ጻፈላቸው፦

‹‹ውድ ሐቢብ

የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደርጎልኛል። በመልካም ጤንነት ላይ መሆኔን አበስረሃለሁ። ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ሮም እሳፈራለሁ። እዚያ በሆንክና በዕውቀትህና በክፍት አእምሮህ ካቶሊካዊነትን አስመልክቶ የሚያጋጥሙኝን እንዳንድ ችግሮች ብታብራራልኝ እንዴት በወደድኩ።

ወዳጅህ ጆርጅ››

‹‹ወዳጄ ሌቪ

የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደርጎልኛል። በመልካም ጤንነት ላይ መሆኔን አበስርሻለሁ። ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ሮም እሳፈራለሁ። እዚያ በሆንሽና በዕውቀትሽና በክፍት አእምሮሽ ኦሪትንና አይሁዳዊነትን አስመልክቶ የሚያጋጥሙኝን እንዳንድ ችግሮች ብታብራሪልኝ እንዴት በወደድኩ።

ወዳጅሽ ጆርጅ››

የኢሜይል መልእክቶቹን በማገባደድ ላይ እያለ ካትሪና መጣች . .

- የመውጫ ሂደቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይጀመራል።

- ቤት፣ሰዎችና መኪኖችም ጭምር በጣም ናፍቀውኛል።

- ከኛ ተለይተህ ያሳለፍከው ቆይታ ለኔና ለልጆቼ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር . . አንተ እንኳ በንብህና በውይይቶችህ ተጠምደህ ነበር። ቶም ዛሬ መጥቶ ነበር እንዴ?

- አዎ፣ከርሱ ጋር ድንቅ ቆይታ ነበረን።

- አላልኩህም ነበር?

- ምክሮችሽ ሁሌም የሚመቹ ናቸው፤ዋናው ነገር መቼ ነው የምንወጣው?

- ከአፍታ በኋላ፤አንዳንድ ወረቀቶችን መጨረስ ብቻ ነው የቀረኝ። አሁን እሄድና አጠናቅቄ እመለሳለሁ። መንገድ ላይ ዛሬ ባንተና በቶም መካከል የሆነውን ታወጋኛለህ።

ወደ አብያተ ክርስቲያናት አገር . . (4)

ቤተሰቡ ከበረራው ሁለት ሰዓት አስቀድሞ ወደ አይሮፕላን ማረፊያ አመራ . . በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ወደ ታሪካዊቱ ሮም ጉዞ ተጀመረ . . ለዚህ ጉዞ በጥንቃቄ ያቀደችው

ካትሪና

ከፒያሳ ናቮና አደባባይ ብዙ የማይርቀውን ራፋይል ሆቴል ነበር የያዘችው። ሆቴሉ የሮምን ከተማ ገጽታ፣ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያንን እና የፓንቲኦን ቤተ መቅደስ ቁልቁል የሚያሳይ ነው። ራፋይል ሆቴል ከአውቶቡስ መስመሮች ጋር በሚገባ የተሳሰረ ከመሆኑም ባሻገር አብዛኞቹ የሮም ከተማ ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ ቦታዎችም በእግር ጉዞ ከሆቴሉ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛሉ . .

- ካትሪና ምርጫሽ በጣም ድንቅ ነው።

- ማሚ አመሰግናለሁ፣ታቂያለሽ ማየት ከምፈልገው አምባ የቀረበ ሆቴል ነው የያዝሽልን።

- ሳሊ ማየት ከምትፈልገው ፏፏቴም ብዙ አይርቅም።

- አሁን ከምሽቱ አንድ ሰዓት ነው፤ሆቴሉ ውስጥ ብንዝናና እራታችን በልተን ብናርፍ ጧት የጉብኝት ፕሮግራማችንን በንቃት ለመጀመር ይረዳናል፤አይመስላችሁም?

- ባባ በጣም ጥሩ ነው . .

ቤተሰቡ በማለዳ ተነሳ . . ቁርሳቸውን በሆቴሉ ሬስቶራንት በሉ። ከአስጎብኚ ጋር በታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ወደ ተሞላውና በአቅራቢው ወደሚገኘው አደባባይ አመሩ። የሮምን ጥንታዊ ሕንጻዎች ድንቅ ሐውልቶቿን፣የኪነ ሕንጻ ጥበብ፣ ጥልቅ ታሪካዊነትና ግርማ ሞገስ የሚንጸባረቅባቸው የተዋቡ አብያተ ክርስቲያናትን ሲመለከቱ ወደር የሌለው ደስታና እርካታ አገኙ።

የምሳ

ሰዓት ሲደርስ በጥንት ሮማውያን ሞዴል ወደ ተዘጋጀው የኢጣሊያ ሬስቶራንት ሄዱ . .

- ባባ የሮማውያን ሥልጣኔ ይህን ያህል ጥልቀትና ውበት አለው ብዬ አላሰብኩም ነበር !

- ማይክል፣የሮማውያን ሥልጣኔ ድንቅ የሆነ ጥንታዊ ሥልጣኔ ነው። ከግሪክ ሥልጣኔ ቀጥሎ ታላቁ የአውሮፓ ሥልጣኔ ነው። ከልደት በፊት በ275 መላውን የኢጣሊያ ባህረ ገብ ምድር የተቆጣጠረ ሥልጣኔ ነበር። በቀጣዮቹ ሁለት ተከታታይ ምእተ ዓመታት ሮማውያን መላውን አውሮፓና ሰሜን አፍሪካን ያጠቃለለ፣የግሪክን ሥልጣኔም እውስጡ ያካተተ ኢምፓይር መገንባት ችለዋል።

- ሮምን ልዩ የሚያደርጋት ውጭ ያሉት ሐውልቶችና ቅርጻቅርጾች ብቻ ሳይሆኑ ይህ ፒሳም ጭምር ነው።

- ማይክል በሐውልቶቹ ተደንቀሃል?

- አሰራራቸው ያምራል።

ከትሪና ፈገግ ብላ

- የኢየሱስና የድንግሏ ሐውልቶች ምንኛ ያምራሉ !

- እነዚህ ሐውልቶችና የኢየሱስ ሐውልቶችም ጭምር በሕንድ ያየኋቸውን የቡድሃና የሌሎች አማልክት ቅርጾችን እንዳስታውስ ለምን እንደሚያደርጉኝ አላውቅም። ለኔ ሁሉም ተመሳሳይ ነገሮች ሆነው ይታዩኛል።

- አሁን ይህን ተወንና ምሳችንን ከበላን በኋላ ወደ ሌላኛው የአደባባዩ ክፍል እናመራለን።

ካትሪና በዚህ ጉዳይ ላይ ልጆቹ ፊት መከራከር እንደማትፈልግ የተረዳው ጆርጅ ሀሳቧን አክብሮ ተቀበለ። ይሁን እንጂ አእምሮው የኢየሱስን ሐውልቶች ከቡድሃ ሐውልቶች ጋር ማስተሳሰር ብቻ ሳይሆን የጣዖት አምላኪዎችን እምነት ከካቶሊኮች እምነት ጋር አይይዞ መመልከቱን አላቆመም።
ቤተሰቡ የዕለቱን የጉብኝት መርሐ ግብር አጠናቆ ጸሐይ ከጠለቀች ከአጭር ጊዜ በኋላ ወደ ሆቴላቸው ተመለሱ። እራታቸውን በሆቴሉ ሬስቶራንት አንድ ላይ በሉና ወደ መኝታ ክፍሎቻቸው አመሩ . . ጆርጅ ኢሜይሉን ከፈተና ከሐቢብ የተላከለትን መልእክት አገኘ

‹‹ጆርጅ

ይህን መልእክት የምጽፍልህ ከሌቪ ጋር አብረን በመሆን ነው። መልእክተህን አንብበን ቀዶ ጥገናው ስኬታማ በመሆኑ በእጅጉ ተደስተናል። ቀዶ ጥገናው የተሳካልህ መሆኑን ምክንያት በማድረግም ከአፍታ በኋላ ከሌቪ ጋር የደስታ መግለጫ ዝግጅት ይኖረናል። ካቶሊካዊነትን ወይም አይሁዳዊነትን በተመለከተ ግልጽ ያልሆነልህን ነገር ካንተ ጋር ለመወያየት ደስተኞች ነን። በፕሮቴስታንትና በእስላምም ጭምር ለመወያየት ደስተኞች ነን። በነዚህ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ካንተ ጋር ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተን እንጠብቃለን።

ሐቢብና ሌቪ››

ማሳሰቢያ ከሐቢብ ብቻ በቅዳሜ ዕለቱ ቅዳሴ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን መጎብኘት እንዳትረሳ።

መልስ ጻፈላቸው፦

‹‹ሐቢብና ሌቪ ሠላም ለናንተ ይሁን

አሁን ያለሁት በካቶሊኮች አገር በሮም ነው፤ከካቶሊካዊው ቫቲካንም በቅርብ ርቀት ላይ እገኛለሁ። ስለኔ በመደሰታችሁ ተደስቻለሁ። ግልጽ ያልሆኑልኝን ነገሮች በሚመለከት አንዱን ጥቅስ ብቻ አስተላልፍላችሁና በጣም አጠር ያለ አስተያየት እንድትሰጡበት እጠብቃለሁ . . ‹‹አይነኬ ትረካዎች በኦሪት›› የተሰኘውና በጆናታን ክሪች ከተጻፈው መጽሐፍ አንዱን አንቀጽ እጠቅስላችኋለሁ። አንቀጹ ስለ ኦሪት ወይም ብሉይ ኪዳን ሲናገር እንዲህ ይላል

ሚሸል ቪንቶራ እንዳስቀመጠው - ብሉይ ኪዳን ውስጥ በተመለከተው ነገር ስሜቱ ክፉኛ የተጎዳ ጋዜጠኛ ነው - ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ አፍራሽ አረመኔያዊ የጭካኔ አድራጎት የሚተርክ መጽሐፍ ነው። ‹‹ዘንዶ የሚያገቡ ሴቶች፣እርስ በርሳቸው የሚገዳደሉ ወንድማማቾች፣ሙሉ በሙሉ የሚታረድና የሚፈጅ ሕዝብ፣በረሃ ውስጥ የሚንከራተቱ ነገዶች፣የሚጋዙ አራስ ሕጻናት፣ወንጀልን የሚከተል ነብይነት፣ነብይነትን የሚከተል ወንጀል፣የነብያት አንገት ተቆርጦ እንዲመጣላቸው የሚጠይቁ ዘፋኞች›› ቫንቱራ ሲያጠቃልል ኦሪትን ወደ ቅዱስ መጽሐፍነት ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ማንኛውም ሕብረተሰብ ለእብደት የተጋለጠ ነው ይልና ‹‹ይህን በመሰለ መጽሐፍ ላይ የሚመረኮዝ ሥልጣኔ ሕብረተሰቡ አረመኔያዊ ጭካኔ የሌለውና አውዳሚ ያልሆነ ሕብረተሰብ ይሆናል ብሎ መጠበቅ›› አስቂኝ ነው በማለት ያክላል። እናም ከቬንቱራ ጋር ትስማማላችሁ ወይስ አትስማሙም? ሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ መሆናቸውን ግንዛቤ ውስጥ ከማስገባት ጋር! አስተያየት ስጡበት።

ከአክብሮት ሠላምታና ከናፍቆት ጋር

ጆርጅ››

ጽሑፉን በአንድ መልእክት ለአደምና ለቶምም ለመላክ ወሰነ . . ከዚያ ቁጭ ብሎ ማሰላሰል ያዘ . . እርሱ ራሱ ቬንቱራ በሚለው ነገር ይስማማል?! ካትሪና ባሰናዳችው መሰረት ነገ ከማገኛቸው ሰዎች ጋር ይህን ሀሳብ አንስቼ እወያይበታለሁ . .
ጧት ከቁርስ በኋላ ካትሪና ልጆቹን ይዛ ለግብይት ወጣች . . ጆርጅ ግን ካትሪና ባመቻቸች ቀጠሮ መሰረት የጃኖልካ ፍራንኳን መምጣት ቁጭ ብሎ ጠበቀ . . ጃኖልካ ካትሪና እንዳስተዋወቀችው
በካቶሊካዊነትና
በፕሮቴስታንት ላይ የጋዜጠኝነት ምርመራዎችን ያካሄደ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ነው። በተያዘለት ቀጠሮ ልክ ከጧቱ አምስት ሰዓት ላይ ከሆቴሉ ደረሰ። ጆርጅ በሰላምታ ተቀበለው፣በትህትና ሰላምታውን መልሶ፦

- ከቀሳውስት ወዳጆቼ ከአንደኛው በደረሰኝ መሰረት ለታላላቆቹ ጥያቄዎች ምላሽ ፍለጋ ላይ የተሰማራህ ተመራማሪ ነህ። ካህኗ ባለቤትህ ለወዳጄ ለቄስ ሎዊጂ እስቲያቬኑዋ ደውላ ይህንኑ ነግራቸዋለች። ለማንኛውም ራሴን ላስተዋውቅህ።

- ባለቤቴ ካህን አይደለችም፤ከአፍታ በኋላ ትመጣለች፣ካንተ ጋር መተዋወቅ ደስታዬ ነው፣እባክህን ቀጥል።

- እኔ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ነኝ። በዩኒቨርሲቲ ያጠናሁትን ፍልስፍና በጣም እወደዋለሁ። የፈላስፋዎች - ፈገግ ብሎ ቀጠለና - በእርግጥ የብሩህ አእምሮ ባለቤቶችም ዋነኛ ጥያቄዎች የሕይወት ዋነኛ ጥያቄዎች ናቸው። ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ስመራመር አያሌ ዓመታትን አሳልፌያለሁ።

- ካትሪና የደወለችላቸው ቄስ ለዚህ ነው አንተን ያናገሩት?

- አዎ።

- የዓመታት ምርምርህ ውጤት ምን ነበር?

- እህህ . . አስፈላጊ በሆኑ ውጤቶችና የተወሰኑ ነጥቦች ላይ ደርሻለሁ።

- በጣም ጥሩ፣ምንድናቸው?

- በቀላሉ . . ‹‹ምንም›› ነው መልሱ ! ያለኝ በአሳፋሪው የሃይማኖቶች ሁኔታ ላይ የተሰነዘሩ ትችቶች እንጂ የተቀናጀና ተሟልቶ የተጠናቀረ እሳቤ አይደለም።

- የምርምርህ ውጤት ‹‹ምንም›› ከሆነ ዘንዳ በምን ልትረዳኝ ትችላለህ?!

- እውነቱን ለመናገር አንተን ሊጠቅሙ የሚችሉ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ተሞክሮዎች አሉኝ። እኔም በተራዬ ካንተ ልምድ መቅሰም እችላለሁ። አዝናለሁ፣ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት ግን ውጤት አልባ ነው !

- መልሱ ‹‹መልስ የለውም›› ማለት ሊሆን ይችላል ብለህ ታምናለህ?

- አንተ ጥልቀትንና ማቅለልን አጣምረህ የተላበስክ ነህ፣ግሩም ነው አሟላው።

- ምኑን ነው የማሟላው? እኔ ጠያቂ ነኝ፣አንተ መልስ እንጂ።

- መልሱ ግልጽ ነው፤ስለሆነም መመለስ አያሻኝም። መልሱ ‹‹መልስ የለውም›› ሊሆን የማይችል መሆኑ እርግጥ ነውና፣ ቀጥል።

- እናም አንተ ያልደረስክበት መልስ ይኖራል ማለት ነው?

- አእምሮዬ መልስ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል ባይ ነው።

- አእምሮ መልስ ላይኖር ይችላል ብሎ ይገምታል የሚል እምነት የለኝም። ይህ ማለት የሰው ልጆች በብኩንነት ውስጥ ይዳክራሉ ማለት ሲሆን፣ይህም በተራው ወደ ከንቱነትና ምንምነት መደዴ አመለካከት ያደርሳል።

- አንተ ድንቅ ፈላስፋ ነህ፤የኔም ሀሳብ ይኸው ነው። ቅድም ያልኩህ ምን እንደምትል ለማየት ነው . . ይሁንና በአንተ አመለካከት ለጥያቄዎቼ ምላሽ የማገኘው ከወዴት ነው?

- በፍለጋ ላይ ነኝ፣እስካሁን አላገኘሁትም። ያንተስ ሀሳብ?

- ብዙ ወዳጆቼ ኤቲስቶች ናቸው፣ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንደሌላት፣የጥያቄዎቹ ምላሽ በሳይንሳዊ ተግባራዊ ዘዴ ወይም በአጋጣሚ ብቻ ሊሆን እንደሚችል ሊያሳምኑኝ ይፈልጋሉ።

- መልካም፣ለጥያቄዎችህ መልስ ሰጡ?

- ኤቲዝም ወራዳ ፍልስፍና ነው፤በሳይንሳዊነትና በእሳቤነት ለመታየት ቢጥርም ከተራ አፈተረትና ከኋላ ቀር ቀባጣሪነት የሚያልፍ አይደለም። እመነኝ ኤቲዝምን በሚገባ አውቃለሁ፣ከብዙ ኤቲስቶች ጋር ሰፊ ክርክር አድርጌያለሁ።

- በኤቲዝምና በሴኩላሪዝም አመለካከት ላይ ጫን ያልክ ትመስላለህ።

- ኤቲስት እንዳትሆን ስጋት አለኝ፣ለዚህ ነው መሰለኝ የምትከራከርላቸው። ፍቀድልኝና እኔ ግን ካንተ ጋር በግልጽነትና በዝርዝር ነው የምናገረው። እያንዳንዱ ኤቲስት ስህተተኛ መሆኑን በውስጡ አምኖ ይቀበላል። እኔ ኤቲስት ነበርኩ፤ለተወሰነ ጊዜ ኤቲዝም ውስጥ ኖሬያለሁ። ኤቲዝም ከሃይማኖቶች ችግር ለመራቅ የሚደረግ አንድ ዓይነት ሽሽት እንጂ ሌላ አይደለም። ምንም ዓይነት ፍልስፍና፣ንድፈ ሀሳብ፣ሕሊናዊም ሆነ ሳይንሳዊ ማስረጃ የለውም። ሴኩላሪዝም ግን በሃይማኖት ያምናል፤ነገር ግን ከኤቲዝም መነሻ በመነሳት ሃይማኖትን ከሰው ልጆች ሕይወት መነጠል ይፈልጋል።

- እንዴት?

- በሃይማኖትና በሳይንስ መካከል ያለው ቅራኔና ትግል ስር የሰደደ ዘመን ተሸጋሪ ችግር ነው። በሁለቱ መካከል ግጭት ሲኖር በሰዎች ዘንድ የሳይንስ እውነታ ከሃይማኖት እውነታ የላቀ ነው።

- የኛ ዕውቀት ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተላለፈው ዕውቀት የበለጠ ሊሆን ይችላል?

- በእርግጥ አይችልም፤ይሁንና ከእግዚአብሔር ዘንድ ስህተት ወይም ሊሆን የማችል ነገር ሊመጣ ይችላል?

- ምን ማለትህ ነው?

- ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምሳሌ ያህል ሌሎችን እንዲገድሉ ወይም ዝሙት እንዲፈጽሙ ወይም አስካሪ መጠጥ እንዲጠጡ የሚያበረታቱ ጥቅሶችን ሲያነቡ ወይም ሲሰሙ፣እነዚህ ነገሮች ከአእምሮ ከሞራልና ከዕውቀት አንጻር ጎጂዎች ለመሆናቸው እርግጠኞች እየሆኑ ምን እንዲያደርጉ ነው የምትፈልገው?

- እንግዲያውስ ከታላላቆቹ ጥያቄዎች መልስ ፍለጋ ድካም እፎይታ ለማግኘት ወደ ሴኩላሪዝም ደርሰሃል ማለት ነው።

- አዝናለሁ . . ሴኩላሪዝም ፈጽሞም እፎይታ አያስገኝም። እኔ የምናገረው ስለ ሴኩላሪዝም አማኝ ተከታዮች ነው፤ሴኩላርዝም በሃይማኖትና በሳይንስ መካከል ያለውን ተቃርኖና የታሪክን ችግር ይፈታል፤እንዲያውም እውነቱን ከፈለክ ሴኩላሪዝም ከክርስትና ሃይማኖት ጋር በብዙ መንገድ ይጣጣማል።

- መልካም . . የመጨረሻውን ነጥብ አብራራልኝ።

- ፓፓዊው ሥርዓት የምህረትና የስርየት ምስክር ወረቀቱን ላንተ ለመሸጥ ሲል የፈለከውን ነገር እንድትሰራ የሚያደርግህ መንገድ ነው። እናም ሃይማኖትን ወደ ጎን ብለህ ያሻህን ሰርተህ የስርየት ማረጋገጫውን ከቫቲካን መግዛት ብቻ በቂህ ነው።

- ፕሮቴስታንቶች ግን በዚህ አያምኑም፤አይደለም እንዴ?

- ያን የሚያደርጉት ግን ሃይማኖትን ከሰው ሕይወት ስለማይነጥሉ ሳይሆን ሃይማኖተኝነታቸው አነስ ያለ በመሆኑ ሊሆን ይችላል። ሃይማኖትን በይፋ ነው ከሰው ልጅ ሕይወት የሚነጥሉት። በኔ እምነት ለሱኩላሪዝምና ለኤቲዝም ዋነኛው መረማመጃ ቤተክርስቲያን ነች !

- አንተ በምን ላይ ነህ? ! የምን ሃይማኖት ተከታይ ነህ? ! አንዴ ለኤቲዝም ትከላከላለህ፣አንዴ ደግሞ ለሴኩላሪዝም ትሞግታለህ፣ሌላ ጊዜ ለካቶሊካዊነት ትከራከራለህ !

- እኔ ምንም አይደለሁም፤ውጤቱ ምንም አይደለም አላልኩህም ነበር? አንተስ ምንድነህ?

- አባትና እናቴ እንደዚያ ስለነበሩ እኔ ፕሮቴስታንት ነኝ፣ከዚያም ምንም !

- እህህ . . እናም አንዳችን እንደሌላችን ነው ማለት ነው።

- ወደ ምንም ውጤት በደረስክ ጊዜ ደስተኛ ነበርክ? ደርሻለሁ ብለህስ ታስባለህ?

- ‹‹ምንም›› የሚደረስበት ነገር አይደለም ! ምናልባት እዚህ እኛ ዘንድ በምዕራቡ ዓለም የተለያዩ ከንቱና መደዴ አመለካከቶች፣ ጎራዎችና ቡድኖች እንዲነሱና እንዲስፋፉ መነሻ ምክንያቱ ይህ ሳይሆን አልቀረም።

- ከንቱና መደዴ አመለካከቶች?

- እህህ፣አዎ ሃይማኖታቸውን በምንም ላይ ወይም ከሃይማኖት በራቁ ተራ ነገሮች ላይ የሚመሰርቱ የአመለካከት ጎራዎች።

- እንግዲያውስ ይህን የ‹‹ምንም›› አደጋ ነው እንበላ? !

- ይልቅስ አደጋው የሕይወት ጥያቄ መልስ ያላገኘ መሆኑ ነው።

- ለምን ተዘናግተህ አትሸሸውም?

- አልቻልኩም፤አንድ ብልህ ወይም አርቆ አስተዋይ ሰው ይህን ማድረግ ይችላል ብዬ አላምንም።

- አብዛኛው ሰው እብድ ወይም ጅል ነው ማለትህ ነው?

- አብዘኞቹ ሰዎች ሕይወታቸው እየደፈረሰና ደስተኝነት እየራቃቸው ሊዘናጉት አይችሉም ማለቴ ነው።

- አንተ ፈላስፋ ነህ፤ግና ተስፈኛ አይደለህም። ወደ አልቦ ውጤት እንጂ የትም መድረስ አልቻልክም፤ታዲያ መፍትሔው ምንድነው?

- ለኔ መፍትሔው ለጥያቄው መልስ እስክናገኝ ድረስ ፍለጋውን መቀጠል ነው . . አንተሳ መፍትሔው ምንድነው ትላለህ?

- መፍትሔው አንተ ያልከው ብቻ ነው። ካንተ የምለየው ግን በጣም ቅርብ በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደ መልሱ እንደምደርስ የሚሰማኝ በመሆኑ ነው።

- ተስፋ መሰነቅ ከአምላክ የሚሰጥ ጸጋ ነው፤ተስፋህ በተገቢ ቦታው እዲሆን ምኞቴ ነው። ይሁን እንጂ ተስፋ ለመሰነቅ አመላካች ነገር ሊኖርህ የግድ ይላል።

- አመላካች ማስረጃው መንገዱን ተስፋ ሳትቆርጥ በጽናት፣ያለማመንታትና ያላንዳች ጥርጣሬ በቁርጠኝነት መጓዝ ነው።

- ድንቅ ነው . . በጣም ግሩም ነው፣በጉዞህ የት ደርሰሃል?

- ኤቲዝምንና ምድራዊ ሰው ሰራሽ ሃይማኖቶችን መርምሬ አልፌያለሁ። እንዳልከው ሁሉ የሚጠቅሙ አይደሉም። ከዚያ መለኮታዊ ሃማኖቶችን ተራ በተራ መመርመር ጀመርኩ፣አሁን ክርስትናን በማጥናት ላይ እገኛለሁ።

- እኔ ከቤተሰብ መነሻ ካቶሊክ ነኝ፤ሆኖም ከካቶሊካዊነት ምኑንም እውነት ነው ብዬ አልቀበልም እለሃለሁ። ካቶሊካዊነት የግብስብስ ምስጢሮችና እርስ በርስ የሚጣረሱ ጉዳዮች ስብስብ ነው።

- ታዲያ ለምን ፕሮቴስታንት አትሆንም?

- አንተ ፕሮቴስታንቱ ይቅርታ አድርግልኝ፤በራሴ ሃይማኖት ነው የጀመርኩልህ። ፕሮቴስታንታዊነት ከካቶሊካዊነት ግብስብስ አፈተረቶችና ምስጢሮች ለመሸሽ የተደረገ ጥረት ነው። ይሁን እንጂ ባለቤቱ ሃይማኖተኝነቱ እምብዛም የሆነ ያልተሳካ ጥረት ነው። በመሆኑም የካቶሊካዊነትን ግብስብስ አፈተረቶችና ምስጢሮች ከፊሉን ልል ከሆነ ሃይማኖተኝነት ጋር ያጣመረ አዲስ ጎራነው።

- የበለጠ ብታብራራልኝ፤አንዳንዴ ድብቅ ትመስላለህ።

- ሁለቱም ማለቴ ካቶሊክና ፕሮቴስታንትም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አይደለም የሚመረኮዙት? ብሉይና አዲስ ኪዳን ደግሞ የአፈተረቶችና የምስጢሮች መነሻ ናቸው።

- ከአምላክ ዘንድ ስለ ተላለፈው መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንዲህ ትናገራለህ ? !

- ልክ እንደ ቄሱ ወዳጄ ትናገራለህ። ለርሱ የሰጠሁትን መልስ ነው ላንተም የምሰጠው . . እስኪ በልበ ሙሉነት መልስልኝና አሁን በእጃችን የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ቃሉ መሆኑን ማረጋገጥ ትችላለህ? እኔ ግን ቢያንስ ከፊሉ ከእግዚአብሔር የተላለፈ ቃሉ አለመሆኑን በማስረጃ ላረጋግጥልህ እችላለሁ።

- እንዴት ነው የምታረጋግጠው?

- በብዙ ተጨባጭ ማስረጃዎች። ከነዚህ መካከል ከፈለክ መጽሐፍ ቅዱስ መቼ እንዴትና በነማን በጽሑፍ እንደ ተጠናቀረ ታሪኩን አንብብ። ከእግዚአብሔር የተላለፈ ቃሉ ነው ብሎ የሚያምን ሰው እንኳ ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር ፊት ለፊት ይላተማል። በተለያዩ ቅጂዎች፣እትሞች፣ትርጉሞች መካከል ብቻ ሳይሆን በአንድ ተመሳሳይ ቅጂ ውስጥ ያሉትን ቅራኔዎችና የርስበርስ ግጭቶች አንብብ። ከእግዚአብሔር ዘንድ አለመሆናቸው ቁልጭ ብሎ የሚታዩ አንዳንዳንድ ትረካና ሁነቶቹን አንብብ። አምላክን በጨካኝ ተንኮለኛነት የሚገልጹ ትረካዎችን ተመልከታቸው . . ሌላ ማስረጃ ትፈልጋለህ? ዝርዝር ማስረጃዎችን ትሻለህ?

- በዚህና በሌላውም ጉዳይ ላይ የሚሉትን ለመስማት ከቄሱ ጋር መወያየት ፍላጎቴ ቢሆንም፣ባልከው ነገር በአብዛኛው እስማማለሁ።

- የምትደንቅ ሰው ነህ፤ታዲያ በዚህ ላይ ለምን ትጨቀጭቀኛለህ?

- ሁኔታው አንተ እንዳልከው ከሆነ መፍትሔው ምንድነው?

- እኔ ምንም ውጤት ላይ አልደረስኩም ብየሃለሁ።

- ይቅርታ፣ምንም ነገር ስትል ምንም አለማወቅ ማለት ነው። እኔ የምፈልገው ዕውቀትና ግንዛቤ ያለውን ሰው ነው።

- የምትለው ነገር ትክክል ነው፤እኔ ግን የለኝም።

- ባንተ ግምት መልሱን መስጠት የሚችለው ማነው?

- ባውቅ ኖሮማ ድካሜ ከረዥም ጊዜ በፊት ባበቃ ነበር።

- መልካም ፈቃድህ ሆኖ ተጨማሪ ከቀሳውስት ማግኘት እፈልጋለሁ። ለነዚህና ለሌሎችም የሚሰጡትን ምላሽ መስማት እፈልጋለሁ።

- ቀሳውስት ወዳጆቼ ብዙ ናቸው። ዝግ የሆኑትን ወይስ ለሁሉም ነገር ክፍት የሆኑትን ነው የምትፈልገው? የዕውቀት ባለቤቶችን ወይስ ዐዋቂ መሰሎቹን?

- ማማረጥ የሚቻለኝ ከሆነ ያለ ጥርጥር ከዝጉ በክፍት አእምሮ የሚያናግረው የተሻለ ነው። ዋናው ግን የበለጠ ዕውቀት ያለው መሆኑ ነው፤ዝግም ይሁን ክፍት እኔ የበለጠ ዕውቀት ያለውን ነው የምፈልገው።

- አይዞህ ተማመን፣ያንድ ሰው ዕውቀት በጨመረ ቁጥር ለተለያዩ ሀሳቦች ክፍትነቱ የበለጠ ይጨምራል። ባለቤትህ ካናገረችው ከወዳጄ ቄስ ሎዊጂ እስቲያቬኖ ጋር እንድትገናኝ ቀጠሮ እይዝልሃለሁ፤ካየኋቸው ቀሳውስት ሁሉ የበለጠ እውቀት ያለውና ከሁሉም ይበልጥ በክፍት አእምሮ የሚናግር ቄስ ነው። ለነገ ወይም ለተነገ ወዲያ ቀጠሮ እወስድልሃለሁ።

- በጣም አመሰግናለሁ።

- የምትፈልገውን በሚገባ እገነዘባለሁ፣በምችለው ሁሉ ልረዳህ ደስተኛ ነኝ።

ጆርጅ እየሳቀ፦

- እንዳስቸገርኩህ ይሰማኛል፣ግና አንድ ጥያቄ አለኝ፣እስላምን አጥንተሃል?

- አላጠናሁም . . እንዳው ጥቂት ንባብና አጭር ውይይት ብቻ እንጂ . . ።

- ለምን?

- እስላም የአመጽ፣የጦርነት፣የሴት ልጅ ጭቆና፣የኋላ ቀርነትና የመሳሰሉ ሌሎች ብዙ ነገሮች ሃይማኖት ነው።

- ታዲያ እስላምን አላጠናሁም፣አልመረመርኩም እያልክ ይህን ሁሉ እንዴት ማወቅ ቻልክ?

- ከመኖሪያ ቤታችን ጎረቤት ያለው ሬስቶራንት ባለቤት ግብጻዊ ሙስሊም ነው፣አንዳንዴ ከርሱ ጋር እወያያለሁ።

- ስለራሱ ይህንኑ ነው የሚናገረው?

- ስለራሱ ይህንን የሚናገር ማንም ሰው አይኖርም፤ግና እንደ ሌሎቹ ኋላ ቀር ሙስሊሞች ሳይሆን ስልጡን ሙስሊም ነው። ለሙስሊሞች ኋላ ቀርነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ስጠይቀው ለግትርነት፣ተቃራኒን ለመግደል፣ሴትን ለማጨቆን እና ለመምታትም ጭምር ጥሪ የሚያደርግ በመሆኑ ምክንያቱ ሃይማኖቱ ራሱ መሆኑን ነው የነገረኝ።

- በጣም የሚገርም ነው፤እሱንም ማግኘት እችላለሁ?

- አንተ ራስህ በጣም ትገርማለህ፣ከርሱ ምን ትፈልጋለህ? ለማንኛውም ግን ቤታችን አቅራቢያ ባለው ሬስቶራንት በማንኛውም ቀን ምሳ ወይም እራት በልተህ ከርሱ ጋር ትንሽ ማውጋት እንችላለን።

- መልካም፣ከፈቀድክልኝ አሁንም ሌላ ጥያቄ አለኝ።

- እሽ ቀጥል።

- በካቶሊካዊነት ላይ ያለህን አቋም እያወቁ ቄሱ አንተን እንዴት ወደኔ ላኩህ?

- ክፍት አእምሮ አለው አላልኩህም? ብዙ ጊዜ እኔ የምናገራቸውን ነገሮች አሳማኝ ሆነው እንዳገኘው ይሰማኛል፤የተሻለው አማራጭ ግን ምን እንደሆነ አያውቅም !

- ብልጥ አቋም ነው፤ለጥያቄዎቻችን መልስ የምናገኝበት መንገድ ግልጽ ሳይሆንልን ከቀረ ከብኩንነትና ከባዶነት ያለንበት ነገር የተሻለ ይሆናል።

- ልክ ነህ፤እኔም ያለሁበት ብኩንነትና ባዶነት እንዳይሆን ተስፋ አደርጋለሁ፣ይሁን እንጂ አሁንም ፍለጋውን እንደቀጠልኩ ነኝ።

- ይቅርታ፣ፈጽሞ አንተን ማስከፋት አላሰብኩም።

- አውቃለሁ።

ካትሪና ከማይክልና ከሳሊ ጋር ተመለሰች፤ከጃኖልካ ጋር ተገናኝተው ሰላምታ ተለዋወጡ . .

- ጌታ የተመሰገነ ይሁን ከመሄድህ በፊት ደረስኩ፣ከተከበሩ ቄስ ሎዊጂ እስትያቪኖ ዘንድ አይደለም የመጣኸው?

- አዎ፣እናም አንቺ የጆርጅ ባለቤት ነሽ ማለት ነው፤ ምንኩስናን ባትቀበይም ከእንግሊዝ ሃይማኖት አጥባቂ ካቶሊኮች አንዷ መሆንሽን ነው ቁሱ የሚናገረው።

- ላንተም ለሎዊጂም ምስጋና ይድረሳችሁ፤የሚሰጡትን ትምህርቶችና ሌክቸሮቻቸውን በማደማጥ የምከታተላቸው መምህሬ ናቸው።

- ለነገ ወይም ለተነገወዲያ ከርሱ ጋር እንድትገናኙ ቀጠሮ እይዝላችኋለሁ።

- ጆርጅ ከተስማማ ግሩም ነው።

- ጆርጅ ራሱ ነው ጥያቄ ያቀረበው፤ወደ አልፈኻማ ሬስቶራንትም ጎራ ትላላችሁ።

- በጣም ጥሩ ነው፣ከመምህሬ ጋር እገናኛለሁ . . ግን ያልከው ሬስቶራንት በተለይ ለምን ተመረጠ?

- ጃኖልካ ንገራት . .

- ከሙስሊሞች አንዱን ለማግኘት።

- ለምን?

- አላውቅም፣ግን ስለ እስላም ኋላቀርነትና ስለ አረመኔነቱ ከርሱ መስማት ይፈልጋል።

- ይህ ሙስሊም ያልነገረህን ብዙ ነገር እኔ እነግረሃለሁ። የሃይማኖታቸውን ኋላ ቀርነት ለማወቅ ኋላ ቀር ሀገሮቻቸውን መመልከት ትችላለህ።

- ለማንኛውም ይህ የአድራሻ ካርዴ ነው። ማንኛውም ዓይነት ሃይማኖታዊ ወይም ቱሪስት ነክ ጥያቄ ካላችሁ ብትደውሉልኝ ደስተኛ ነኝ። ከወዳጄ ቄስ ሎዊጂ እስትያቬኖ ጋር ቀጠሮውን አረጋግጬ እደውልላችኋለሁ፤ደህና ሁኑ።

ጃኖልካ ወጥቶ ሄደ፤ካትሪና እየሳቀች ወደ ጆርጅ ዞራ . .

- ውይይታችሁ እንዴት ነበር? በጊዜ ተመልሰን ባገኘው ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር።

- በጣም ጥሩ ነበር፤አመሰግንሻለሁ።

- እንዲህ ነውና . . ቄሱ ምሁርና ሃይማኖተኛ የሆነ ካቶሊክ ሰው እንጂ ሌላ አይልኩም።

- አዎ . . ፈላስፋና ምሁርም ነው፤እንዳልሽው አጥባቂ ካቶሊክ ሃይማኖተኛ ግን አይደለም።

- ይገርማል ! ወዳጃቸው መሆኑን ነው የነገሩኝ።

- ልክ ነው ወዳጃቸው ነው።

- አንድ ቄስ ሃይማኖተኛ ካልሆነ ግለሰብ ጋር ወዳጅነት ሊኖረው ይችላል? ! ዋናው ነገር ሊጠቅሙን ስለሚችሉ ከቄሱ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ እንዲይዝልኝ ነው።

- ከማንኛውም ግለሰብ የሚጠቅም ነገር መቅሰም መልካም ነው፤በተለይም ቄስ ከሆነ። ለመሆኑ ገበያ ሄዳችሁ ምን ሰራችሁ?

- አስደሳች ሽርሽር ነበር። ሕጻናቱ በገበያውው ማጫወቻ ስፍራ ተጫውተው ካበቁ በኋላ ለአጨር ጊዜ ተዘዋውረን አንዳንድ ነገሮችን ሸምተናል . . የመንገዱ መጨናነቅ ነው ያቆየን።

- ከከተማዋ የቱሪስት መዳረሻዎች ውስጥ የቱን ነው ዛሬ የምንጎበኘው?

- ለማይክል ስንል የቅዱስ አንጅሎን አምባ እንጎበኛለን፤በጣም ውብና በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ አምባ ነው። አሱንና በአካባቢው ያሉትን ለመጎብኘት ሙሉ ቀን ይወስድብናል።

- በሉ አሁን እንሂድ፤ማይክልና ሳሊ የት ናቸው?

- በክፍላቸው ናቸው፣አዲሱን ጫማቸውን እያደረጉ ነው፤እንንቀሳቀስ።

ቤተሰቡ ወደ ቅዱስ አንጅሎ ለመሄድ ተያይዘው ወጣ . . ጆርጅ የቶምን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ አእምሮውን ነጻ አድርጎ ከቤተሰቡ ጋር ለመንሸራሸርና ለመዝናናት ፈለገ። ስለ መታደል መንገድ ፍለጋው ብዙ ላለማሰብና ለጥያቄዎቹ ምላሽ ወደሚያገኝበት መንገድ ለመድረስ ብዙ ላለመጨነቅ፣ጉዞውንም በእርጋታና በዝግታ ለማድረግ ወሰነ . .