ተስፋና ስጋት

ተስፋና ስጋት

ተስፋና ስጋት (1)

ጆርጅ በክርስትና ላይ የሚያደርገውን ጥልቅ ንባብ ቀጥሎበታል። ትኩረት ያደረገው በብሉይና አዲስ ኪዳኖች ትክክለኛነትና በደረሰባቸው የመበረዝ፣ የመምታታት፣የመዛባትና የጭማሬዎች ጉዳይ ላይ ነው። ይህ ርእስ ስ
ሜት የሚኮረኩር ከመሆኑ አንጻር ወደዚህ ለመግባት ሲያቅማማ መኖሩ ታሰበው። ይሁን እንጂ የራሴ የሚለው ቅዱስ መጽሐፍ ምን ያህል ከመበረዝና ከመለወጥ የተጠበቀ ትክክለኛና ተአማኒ መጽሐፍ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ርእሱን በጥልቀት ማጥናት የግድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ዘንድ ጥርጣሬ የሚነሳበት ሆኖ መኖሩ በጣም አሳሳቢና አስቸጋሪ ነገር ነው። ምሳ እስከ መጣለት ጊዜ ድረስ ንባቡን የቀጠለው ጆርጅ ምሳውን የበላው እያነበበ ነበር . . በንባቡ ተጠምዶ እንዳለ ሙቀቱን ለመለካት የመጣችው ነርስ እንዲህ አለችው፦

 - ፈተና ያለበት ተማሪ ትመስላለህ!

- አህህ፣አዎ የሕይወት ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ። የምፈተነው ፈተናውን አልፌ መታደልን ለማግኘት ወይ ደግሞ ወድቄ ዕድለ ቢስነትን ለመቀበል ነው።

- ፈላስፋ ትመስላለህ!

- ቁም ነገሩ ፈተናውን ማለፌ ነው።

- የሕይወትን ፈተና ማለፍ አስቸጋሪ ነው። የሚያሳዝን ነው አብዛኞቹ ሰዎች ፈተናውን ይወድቃሉ።

- ለምን?

- ለመውደቅ ስለሚፈልጉና ማለፍ ስለማይሹ።

- ወይ እየተፈላሰፍሽ ነው፣ወይ ደግሞ በአስገራሚ ሁኔታ ገሃዱን ሁኔታ እየተጻረርሽ ነው።

- እንግዲያውስ እየተፈላሰፍኩ ነኝ፤ሥራ ስላለብኝ ፍቀድልኝ ልሂድ።

በአነጋገሯና ጥልቅ የሆነ ፍልስፍና እንደ ዘበት ወርወር ካደረገች በኋላ እንዴት ፈጥና እንደ ሄደች ገርሞት ጆርጅ ፈገግ አለ. .

አብዛኛው ሰው የሕይወትን ፈተና ለመውደቅ ይፈልጋል ማለት ምን ማለት ነው?

እንዴትስ ሊሆን ይችላል?!

ለማንኛውም እዚሁ ሆስፒታል ውስጥ አብራው ስለላለች ሲያገኛት ማብራሪያ ይጠይቃታል. .

ጆርጅ በንባብ ተጠምዶ እያለ ቶም መጣ. .

ጆርጅ ግን ቶም ገብቶ አጠገቡ እስከ ቆመበትና እየሳቀ ትከሻውን መታ መታ እስካደረገበት ጊዜ ድረስ መምጣቱን አላስተዋለም ነበር ..

- አሁን ክርስትናን ከነፈለጎቹ በሚገባ የግድ አውቀሃል ማለት ነው።

- ቶም . . እንኳን ደህና መጣህ።

- ዛሬ እንዴት ነህ?

- እንደምታየኝ ዛሬ ደህና ነኝ፤ዛሬ ትመጣለህ ብዬ አልጠበኩም ነበር።

- ካትሪና ላትኖር ትችላለች ብዬ ያሰብኩትን ጊዜ መርጬ ነው የመጣሁት።

- ለምን?

- ስለ ሳምኳት የጥፋተኝነት ስሜት የምሰማኝ በመሆኑ ነው፤ለምን እንዳደረኩት አላውቅም፤ከርሷ መገናኘቴ አያስደስትህም ይሆናል፣የምናገረውንም አምነህ አትቀበልኝም ብዬ አስባለሁ፤ይህን ብታደርግ እውነት አለህ።

ጆርጅ

ፈገግ አለና፦

- ነገሩ ቀላል ነው፤ግና ለበራድ ካትሪናን እንደምትወዳት፣ሁሌም እንደምትስማትና እንደምትደሰትባት ለምን ትናገራለህ?

- እኔ እንደዚህ ብየው?!

- ይህ ከኔ ሳይሆን የቢሮህ ኃላፊ በራድ ዛሬ ሊጠይቀኝ መጥቶ የነገረን ነው።

- ፊትም አላመንከኝም፣አሁን እንዴት አድርገህ ታምነኛለህ? እርሱ እኮ ውሸታም ወራዳ ነው።

- ይህን የሚናገረው የቢሮህ ኃላፊ ነው። ዛሬ ጧት ካትሪና ባለችበት ነው የተናገረው። እኔ ወደ ቶራ ቦራ እንደምሄድስ አልነገርከውም? ወይስ ይህንንም ፈጥሮ ነው ያወራው?

- ኦህ፣ፍላጎቴ አልነበረም ግን አንዳንድ ነገሮችን ልነግርህ እገደዳለሁ።

- በል ንገረኝ።

- የቢሮዬ ኃላፊ ወይም የኔ ጸሐፊ እኩይና ስነ ምግባር የጎደለው ሰው መሆኑን አውቃለሁ። ቀደም ሲል በሴቶች ስጫወትባቸው ያግዘኝ ስለ ነበረ ዝም ብዬ አልፈው ነበር። እመነኝ ካንተ ጋር ከተገናኘሁበት ቀን ጀምሮ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ተለውጫለሁ። ከዚያን ቀን ጀምሮ ንባቤ፣ውይይቴና ምርምሬ ሁሉ በሃይማኖቶችና መታደልን በሚያመጡ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኗል። አዲሱ የኔ ሁኔታ በራድን ያላስደሰተው በመሆኑ ብዙ ጊዜ የጨቀጨቀኝ ከመሆኑም በላይ በእጁ የሚገኙና ከአንዳንድ ሕሙማን ሴቶች ጋር የተነሳኋቸውን የቆዩ ፎቶግራፎች ይፋ ለማድረግ አስጠንቅቆኛል። . . በተጨማሪም በኔ ክፍል ውስጥ በምስጢር ካሜራና ድምጽ መቅጃ ማጥመዱን ዘግይቼ ደርሼበታለሁ። በዚህም ለሰዎች የምናገረውን፣የስልክ ጥሪዎቼንና የማደርገውን ሁሉ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በድምጽና በምስል ይቅርጽ ነበር። ይህን የደረስኩበት ከሦስት ቀናት ወዲህ ብቻ ሲሆን የመረረ ጠብ በመካከላችን ተፈጥሮ ከሥራ ለማባረር ስዝትበት እርሱም ፎቶገግራፎቹን ከነድምጼ በቀጥታ ኢንተርኔት ላይ ለመልቀቅ ዝቶብኛል፡፡ ይህም የሕክምና ፈቃዴን መነጠቅ ማለት ነው፡፡ አሁን ምናባቴ እንደማደርግ ቸግሮኛል። የምናገረውን ታምናለህ?! ባታምነኝም ምክንያት አለህ . .

- በከፍተኛ ደረጃ ልቦለድ ትረካ ቢመስልም እውነት መሆኑን የሚመሰክሩ ማስረጃዎች አሉኝ።

- የምን ማስረጃ?

- ካንተ ጋር በነበረኝ የመጨረሻው ቀጠሮ ከቢሮህ ወዲያው እንደወጣሁ በራድ አግኝቶኝ ስለ ቶራ ቦራ ነግሮኝ ነበር፤አብረን በነበርንበት ጊዚ አንተ ፈጽሞ እንዳልወጣህና እርሱም ወደ ክፍሉ እንዳልገባ እርግጠኛ ነኝ።

- ለምን አልነገርከኝም?

- ነገሩ ከፍተኛ አግራሞት ነበር የጫረብኝ፤ግና ምናልባት አስደናቂ አጋጣሚ ወይም ከሩቅ መናበብ የሚሉት ይሆናል ብዬ ዝም አልኩ።

- እንግዲያውስ ሙሉውን እውነት ነግሬሃለሁ፣ማመን አለማመኑ ያንተ ፈንታ ነው።

ነርሷ

በሩን አንኳኳችና በችኮላ ገባች . .

- በማቋረጤ ይቅርታ፣ሐኪሙ ካንተ ጋር በአስቸኳይ መነጋገር ስለሚፈልግ አሁን ወዳንተ እየመጣ ነው።

- ጥሩ ይምጣ፣ግን ነገሩ ምን ይሆን?

ሐኪሙ መጣ . .

- ጆርጅ እንደምነህ? ለድንገተኛ ጉብኝቴ ይቅርታ፣ጉዳዩ አጣዳፊ በመሆኑ ነው።

- እሽ፣ግባ።

- ቀሪዎቹ የምርመራ ውጤቶች ከአፍታ በፊት ደርሰዋል። በጣም አስቸኳይ የሆነ ቀዶ ጥገና ያስፈልገሃል። ነገ በዚህ ሰዓት መደረግ ይኖርበታል።

- ነገሩ አሳሳቢ ሳይሆን አልቀረም መሰለኝ።

- እውነቱን ለመናገር አዎ ለማለት እገደዳለሁ፤በዚህሰዓት የመጣሁትም በዚህ ምክንያት ነው። ከነገ ስድስት ሰዓት በፊት በጉዳዩ ላይ አስበህበት ስምምነትህን በፊርማህ ለማረጋገጥ ጊዜ አለህ።

- ማሰብና መፈረም . . ማረጋገጥ!

- በዝርዝርና በግልጽ ላብራራልህ ይገባኛል። የሙቀት መጠንህን ከፍ የሚያደርገው ቫይረስ ከያንዳንዱ ከፍታ ጋር ከአንጎልህ ሕዋሳት የተወሰኑ ክፍሎችን እያበላሸ መሆኑን ደርሰንበታል። ትኩሳቱ ነገ ማታ ከሁለት ሰዓት በኋላ ይመጣብሃል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ቀዶ ጥገናውን ከጀመርንልህ በኋላ እንጂ አይመጣም ማለት ነው። የቀዶ ጥገናው የስኬታማነት ዕድል 60% ብቻ ነው።

- ቀሪው 40% ምን ይሆናል?!

- በአንዳንድ የአንጎል ክፍሎች ውስጥ እንከን ይኖራል ማለት ነው።

- ይህ ምን ማለት ነው?

- አዝናለሁ ውጤቱን አሁን መተንበይ አልችልም . . ምንም ነገር ላይከሰትም ይችላል፤ማንኛውንም ሌላ ነገር ሊያስከትልም ይችላል።

አሁን ከኔ የሚፈለገው መስማማቴን ገልጬ በፊርማ ማረጋገጥ ነው!

- አዎ።

- ቀዶ ጥገናው እንዳይደረግልኝ ባልስማማ ምንድነው የሚሆነው?

- ስምምነትህ ተጠይቆ እምቢ ማለትህን በማረጋገጥ ትፈርማለህ . . ሁኔታው ለኛ አዲስ ቢሆንም ቀዶ ጥገናውን ማድረጉ ላንተ ተመራጭ ነው የሚል እምነት አለኝ። ሌላ ጥያቄ ይኖረሃል?

- በጉዳዩ ላይ ሌሎች ተጨማሪ አስፈላጊ መረጃዎች ከሌሉ ጥያቄ የለኝም።

- ሌላ ነገር የለም፤ያነጋገርኩህ የሕክምና ቡድኑ ተሰስቦ ከወሰነ በኋላ ሲሆን ይህ የሁሉም የጋራ አቋም ነው። ሌላ ጥያቄ ካለህ በማንኛውም ጊዜ ለነርሶቹ ብትነግራቸው ወዲያውኑ ደውለው ስሚነግሩኝ ምላሽ ማግኘት ትችላለህ። በጉዳዩ አስበህበት ከነገ ስድስት ሰዓት በፊት የስምምነት ማረጋገጫ ፍርማህን እንደምታኖር ተስፋ አደርጋለሁ።

- አስቤበትና ተማክሬ መልስ እሰጠሃለሁ።

- እንደ ልማድህ ነገሮችን በማቅለል ሳትጨነቅ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ሕይወት፣ሞትም ሆነ ሕመም የሰው ልጆችን ሚያጋጥሙ የተለያዩ ሁኔታዎች በመሆናቸው እንደ ሁኔታው ልንቀበላቸው ይገባል። አሁን ልሂድ፣ ጧት ሦስት ሰዓት ላይ እመጣለሁ፤ካዚያ በፊት ጥያቄ ካለህ ለነርሷ ንገራትና ይደውሉልኛል።

- አመሰግናለሁ ዶክተር።

ዶክተሩ

ወጣ፤የቶም ድምጽ እስካቋረጠው ድረስ ጆርጅ በዝምታ ተዋጠ . .

- ጆርጅ . . የታደልን ደስተኞች ካልሆን በስተቀር ሕይወት ትርጉም የላትም። በዳግም ሕይወትና በምርመራ የማናምን ከሆነም ሞትም ትርጉም የለውም። የሞትና የሕይወት ፍልስፍና ምንኛ አስደናቂ ነው!

- ይልቁንም የመኖርና የሕልውና ፍልስፍና እራሱ በጣም አስገራሚ ነው! ለምን ዓለማ ነው የተፈጠርነው? መጨረሻችንና መመለሻችንስ ወዴት ነው?!

- ታዲያ ምኑን ነው የምታስበው?!

- ሕይወትን ነው ወይስ ሞትን ነው? የምፈልገው ብዬ ሳስብ ነበር።

- ማሰብ አያስፈልግህም፤ሕይወትን የማይፈልግ ማንም ሰው የሌም።

- ታዲያ ሰዎች ለምን ራሳቸውን ይገድላሉ? በዓለም ላይ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ አይደለም ወይ? እኔ ራሴ ባንድ ወቅት ይህንኑ ተመኝቼ አልነበረምን?

- በተለይ ያንተው አስገራሚ ነው። ራሱን የሚገድል ሰው እድለቢስነቱን ነው በሌላ እድለቢስነት የሚቋጨው። መታደልን ላገኘ ሰው ግን ይህ ፈጽሞ አስፈላጊው አይደለም።

- ራሴን ለመግደል በሄድኩበት ጊዜ ፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ ነው የጠበበኝ፤መጠን በሌለው ጭንቀትና የእድለቢስነት ስሜት ውስጥ ነበርኩ። ልክ አንተ እንዳልከው መከፋቴን በመከፋት ለማክተም እፈልግ ነበር።

- መሞት ነው ወይስ መኖር ነው ምፈልገው ብለህ ለማሰብ አሁንም ባለመታደል ሁኔታ ውስጥ ነህ?

- እውነቱን ለመናገር በመታደል መንገድ ፍለጋ ላይ ከተሰማራሁበት ጊዜ ጀምሮ የመታደል ስሜት እየተሰማኝ ነው። መንገዱን ጀምሬ እንዲህ ከተሰማኝ ጉዞውን ጨርሼ ስደርስበት እንዴት ይሆን? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ።

- እናም ወደ መታደል ለመድረስ ሕይወትን የሙጥኝ ብለህ ያዝ።

- እኔ ሕይወትን እፈልጋታለሁ፤ጥያቄው ግን ሕይወትስ ትፈልገኛለች ወይ? ነው። ልጃችን ማሪ ከሞት ጋር ስትታገል አየኋት፣ግና ሞት አሸነፋት . .

- እምነትህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፣እርሱ ይረዳሃል።

- እህህ፣ቶም የሚተማመን ሃይማኖተኛ ወጥቶሃል ማለት ነው!

- ተለውጫለሁ ብየህ የለ? እመነኝ እኔ ራሴ እለወጣለሁ ብዬ ጠብቄ አላውቅም ብቻ ሳይሆን ለመለወጥም እቅድ ኖሮኝ አያውቅም። እንዴት እንደ ተለወጥኩ አላውቅም፣ግን በእርግጠኝነት ተለውጫለሁ።

- በምታየው ሁኔታ ላይ ብሆንም እንኳ ጥያቄ አለኝ፦ ቀደም ሲል በነበርክበት ነው ወይስ አሁን ባለህበት ሁኔታ ነው ይበልጥ ደስተኛ የሆንከው?

- ባለፈው ጊዜ የአካልና የመንፈስ ደስታን አስመልክተህ በኢ-ሜይል ለላክልኝ ጥያቄ መልስ ልሰጥህ እችላለሁ። መንፈሴን ዕድለቢስ በማድረግ ነበር አካሌን ሳስደስት የነበረው፣ይህን በማድረጌም ሁለቱንም መንፈሴንም አካሌንም ለእድለቢስነት እዳርግ ነበር!

- አሁንስ?

- አሁንም ለመታደል አልበቃሁም፣ይሁን እንጂ ቢያንስ ቀደም ሲል በነበርኩበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ አይደለሁም።

- በኔ ቦታ ብትሆን ኖሮ መሞትን ነው ወይስ መኖርን ነው የምትመኘው?

- ያለ ጥርጥር ሕይወትን ነው የምመርጠው። ምናልባት ቀደም ባለው ጊዜ ብትጠይቀኝ ኖሮ መሞትን እመርጣለሁ . . የመሞት መርገምት ለመኖርን መርገምት እልባት ይሰጣል እልህ ነበር።

- ራሴን ለመግደል ስሄድ መንገድ ላይ ያገኘሁት ሽማግሌ በጣም የታደለና ከሕጻን አያቱ ጋር በመጫወት በጣም ደስተኛ እንደነበረ አስታውሳለሁ። አድራሻውን ወስጄ ቢሆን ኖሮ እያልኩ ሁሌ እቆጫለሁ።

- ዋናው ነገር አሁን ሐኪሞች ከኛ የተሻለ ስለሚያውቁ፣ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ ተስማምተህ መፈረም አለብህ የሚል ሀሳብ አለኝ። መጀመሪያ ግን ከካትሪና ጋር እንድትመካከር ነው የማሳስብህ።

- ያለ መሳካት ዕድሉ 40% በመሆኑ አንዳንድ ጉዳዮችን ማስተካከል የግድ ቢሆንም የኔም ሀሳብ ይኸው ነው . .

- ወዳጄ መልካሙንና ስኬቱን ብቻ አስብ፣የተመኘኸው ብቻ ነው የሚያጋጥምህ። ሁላችንም ለሁሉም ሁኔታዎች ራሳችንን ማዘጋጀት ችግር የለውም . . ከዚህ በሽታ ተገላግለህ የመታደል ፍለጋ ጉዞህን በድል ታጠናቅቃለህ፤ወደ መታደል ስትደርስ ግን እኔንም መውሰድ እንዳትረሳ . . በጉዳዩ ላይ እንድታስብበት አሁን ትቼህ እሄድና ነገ መጥቼ እጠይቀሃለሁ፣ደህና ሁን።

ጆርጅ በጀርባ ተኝቶ ዓይኑ እያየ ልጁ ማሪ የተጋፈጠችውንና ምናልባትም እርሱም በቅርቡ ሊጋፈጠው ስለሚችለው ሞት ምንነት ማሰላሰል ጀመረ። ለመሆኑ ሞት ራሱ ምንድነው? ሕይወትስ ምንድነው? ሞት ከዚህ ዓለም ጣጣዎች መገላገያ ነው? ወይስ የዚህ ዓለም ደስታ ፍጻሜ ነው? የመጀመሪያው ከሆነ አያ ሞት እንኳን ደህና መጣህ፣ሁለተኛው ከሆነ መታደልን አግኝቶ ምንነቱን አውቋል ማለት ነው። እንዲህ በማሰብ ላይ እያለ በፌዝ ፈገግ አለና ‹‹ወዴትም የማያደርስ ፍልስፍና እየተፈላሰፍኩ ልሞት ነው መሰለኝ›› አለ ለራሱ . .

የስልክ

ጩኸት ከሀሳቡ አባነነው። አደም ነበር የደወለው . .

- ሃሎ፣እንደምነህ አደም?

- ጆርጅ እንዴት ነህ? ልጠይቅህ ፈልጌ ነው የደወልኩት። አሁን እንዴት ነው?

- በመኖርና በመሞት መካከል ነኝ፤ለማንኛቸው ይበልጥ ቅርብ እንደሆንኩ አላውቅም።

- አልገባኝም፣እንዴት ማለት?

- 60% ሕይወት 40% ደግሞ ሞት ወይም ዘላቂ ጉዳት።

- ምንም አልገባኝም፤እየቀለድክ ከሆነ እኔ ይህን ቀልድ አልወደውም።

- ቀልድ በሆነ፣ግና እውነት ነው . . ምናልባት የመሳካት ዕድሉ 60% የሆነ ቀዶ ጥገና ነገ ሳይደረግልኝ አይቀርም።

- በማንኛውም ሁኔታ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ።

- ዛሬ ብንገናኝ ምኞቴ ነበር።

- አሁን የሕሙማን መጠየቂያ ሰዓቱ ስላለፈ ዛሬ የሚሆን አይመስለኝም፤በጊዜ ለምን አልደወልክልኝም ነበር?

- እኔ እንጃ፣ነገ በጧቱ የመጠየቂያ ሰዓት ልትመጣ ትችላለህ?

- አዎ በሚገባ፣አሁን መምጣት ብችል እንኳ በመጣሁ ነበር። የማረጋግጥልህ ነገር ቢኖር ግን ዕድሜ በእግዚአብሔር እጅ እንጂ አስፈላጊ ምክንያት ቢሆኑም በሐኪሞች እጅ አለመሆኑን ነው።

- ሞትን ፈርቼው ወይም ምንም ቁብ ሳልሰጠው ቀርቼ እንደሆነ አላውቅም። የማውቀው ነገር ቢኖር የሕይወትን ቅደም ተከተል ሙሉ በሙሉ የሚለውጥ ግዙፍ እውነታ መሆኑን ብቻ ነው።

- አይዞህ አትፍራ፣ተስፋ አትቁረጥ፣እግዚአብሔር ከኛ ከራሳችን እንኳ ይበልጥ ለኛ ርህሩህ አዛኝ ነው።

- እመነኝ ፈርቼ ይሆን ወይስ ተረብሼ? ምን እንደሆንኩ አላውቅም። የሚሰማኝ ነገር ቢኖር ሕይወቴን ዳግም ሥርዓት ማስያዝ እንዳለብኝ ብቻ ነው . . በራሴ ሳሾፍ አታይም? . .

- የምን ሹፈት ነው?

- ሞትን ስፈራ ሕይወቴን ሥርዓት ለማስያዝ ወሰንኩ። ገና ወደ ሕይወት በማምራት ላይ እያለሁ እንጂ ሕይወትን ለቅቄ ስሄድ አልነበረም ሕይወቴን ሥርዓት ማስያዝ ይበልጥ ተገቢ ይሆን የነበረው?

- ቀደም ብሎም ሕይወትህን ሥርዓት ለማስያዝ ጥረት በማድረግ ላይ ነበርክ፣ምን ያህል እንደቀረ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም የማያውቅ ቢሆንም፣ ቀሪውን ሕይወት ሥርዓት ማስያዝም የግድ ነው . . እኔ ተስፋ ማድረግ፣በጎውን መመኘትና መጠበቅ ነው ደስ የሚለኝ። ተስፋ መቁረጥና በጎ በጎውን አለማየትን እጠላለሁ።

- ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ነኝ፣እሞታለሁ ብለህ ትጠብቃለህ?

- በእግዚአብሔር ፈቃድ ትኖራለህ፣በፍለጋ ጉዞህም ወደ መታደል ትደርሳለህ፤ከዚያ በኋላ የዓለማዊ ሕይወትንና የሞትን ትርጉም ትረዳለህ።

- ‹‹ከሞት በኋላ ያለው ሕይወታችን›› የሚለው አገላለጽ ውብ አገላለጽ ነው። በዚህ ላይ ነገ ካንተ ጋር እወያያለሁ። ይቅርታ አድርግልኝና ላሳውቃት አሁን ለካትሪና ለመደወል እገደዳለሁ።

- ልክ ነህ . . ባለቤትህን ማማከር ይኖርብሃል። አራዝሜብህ እንደሆነ አዝናለሁ፤እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፣በሰላም ያገናኘን።

- አደም ላንተ ያለኝ አክብሮት ወሰን የሌውም፣ጧት እጠብቀሃለሁ፣ደህና ሁን።

የአደም ቃላት ጭንቅላቱ ውስጥ እየደወሉ የስልክ ጥሪውን አበቃ። ‹‹ዕድሜ በእግዚአብሔር እጅ እንጂ በሐኪሞች እጅ አይደለም››፣‹‹እግዚአብሔር ከኛ ከራሳችን እንኳ ይበልጥ ለኛ ርህሩህ አዛኝ ነው››፣‹‹ተስፋ ማድረግ፣በጎውን መመኘትና መጠበቅ ነው ደስ የሚለኝ። ተስፋ መቁረጥና በጎ በጎውን አለማየትን እጠላለሁ››፣‹‹በፍለጋ ጉዞህም ወደ መታደል ትደርሳለህ፤ከዚያ በኋላ የዓለማዊ ሕይወትንና የሞትን ትርጉም ትረዳለህ።›› የሚሉትን የአደም አባባሎች ሳያስብ ሲደጋግማቸው ራሱን አገኘ . . የአደም ቀላል ግን ጥልቅ ቃላት ውስጡን ለምን ሁሌ እንደሚያንቀጠቅጡ አያውቅም። ምስጢሩ በራሳቸው በቃላቱ ምክንያት ነው? ወይስ እውነተኛ በመሆናቸው? ወይስ እንዴት እንደሚቆጣጠረው በማያውቀውና አሁን በሚገኝበት ያልተረጋጋ ሁኔታው ምክንያት ይሆን? . .
ጆርጅ እየተግተለተሉ የመጡ ሀሳቦቹን ገታ አደረገ። ለካትሪና ደውሎ ስለ ጉዳዩ ማማከር የግድ ነበር . .

- ሃሎ ካትሪና፣ናፈቅሽኝ፤ዛሬ ትመጪያለሽ ብዬ ጠብቄ ነበር።

- ልመጣ ነበር፣ዳሩ ቀላል ጉዳይ አጋጥሞኝ ቀረሁ እንጂ።

- በሰላም ነው?

- ሰላም ነው፣ሳሊ የቤት ሥራ ስለነበራት የኔ እገዛ አስፈልጓት ነው።

- አሁን የት ነሽ?

- እቤት ነኝ፣ጆርጅ ችግር አለ እንዴ?

- ኣይ፣አንድ ነገር ላማክርሽ ፈልጌ ነው። እኔ ከተስማማሁበት ነገ የቀዶ ጥገና ሊደረግልኝ እንደሚችል ሐኪሙ ነግሮኛል።

- ነገ ነገ ! ጥድፊያው ምንድነው? የምን ቀዶ ጥገና ነው?

- ሐኪሙ የነገረኝ ነገ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ማድረጉ ተመራጭ መሆኑን ነው።

- የኔ ፍቅር . . ምን እያሰብክ ነው? አሁኑኑ ወደ ሆስፒታል እመጣለሁ።

- ነገ ጧት ብትመጪ የሚሻል ይመስለኛል።

- ቀዶ ጥገናው የምንድነው?

- የአንጎል ቀዶ ጥገና ነው።

- የአንጎል!! አደገኛነት አለው?

- ምናልባት። ዋናው ነገር የመሳካት ዕድሉ 60% ብቻ ቢሆንም መደረጉ ተመራጭ ነው የሚል አቋም አለው ሐኪሙ፤አንቺስ ምን ታስቢያለሽ?

- የምለውን አላውቅም፣ሌሊቱን በሙሉ ስላንተ እጸልያለሁ፤ማይክልና ሳሊን ይዤ ጧት እመጣለሁ።

- የኔ ፍቅር እጠብቅሻለሁ . . ደህና ሁኚ።

ካትሪና ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ተከናንባ ተኛች። የጆርጅን በድንገት ከሕይወቷ ውስጥ አለመኖር መሳብ ከበዳት . . ቀዶ ጥገናው ሳይሳካ ቢቀርስ? . . ዘላቂ አካለ ስንኩልነት ቢገጥመውስ? . . እንደገና ተነሳችና ለጆርጅ መጸለይ ጀመረች . .
ጆርጅም ስለ ካትሪና እና ስለ ሁለቱ ልጆች በማሰላሰል ተጠመደ። በዋነኛነቱ ያሳሰበው የገንዘብ ጉዳይ ነው . . ለካትሪና እና ለልጆቹ ጠቀም ያለ ገንዘብ ሊሆን የሚችለውን የሕይወት መድህን ዋስትናውን ማደሱን አስታውሶ ፈገግ አለ። ከሚሰራበት ኩባንያ ጋር የገባው የሥራ ውልም ጥሩ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል መሆኑና በተለይም ለሕመም የተጋለጠው ለኩባንያው ሥራ ጉዞ ላይ እያለ መሆኑን ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን በማሰብ አሰበ፤ይሁን እንጂ ስለራሱ እንጂ ለማንም ግድ የሌለው ካኽ ከሞትኩ ምንም ነገር አይሰጥም የሚል ጥርጣሬረ አደረበት . . መሰል የሀሳብ ግጭቶችን በማስተናገድ ላይ እያለ እንቅልፍ ይዞት ሄደ . .

ተስፋና ስጋት (2)

ጆርጅ አማልዶ ከእንቅልፉ ነቃ፤ባስተናገዳቸው የሀሳብና የጥያቄ ማእበሎች የተጨናነቀው ጭንቅላቱ እየከበደው ቁርሱን በላ። በአብዛኛው ቀዶ ጥገናው እንዲደረግ ወደ መወሰኑ ያደላ ቢሆንም ጭንቀት ጠበቅ እያለበት ነው . . ከቀዶ ጥገናው በፊት ምን ማድረግ ይኖርበታል? . . ካትሪና እና ልጆቹ ፈጽሞ ከአእምሮው ሊርቁ አልቻሉም . .
የጧቱ የሕሙማን መጠየቂያ ሰዓት እንደደረሰ አደም በፈገግታ ወደ ክፍሉ ከተፍ ሲል አየው . .

- የምሥራች ንገረኝማ . . እንዴት ነህ?

- ደህና ነኝ . . አዲስ ነገር የለም፤ምንም ነገር በርሱ እጅ ባይኖርም ሐኪሙን እየጠበቅሁ ነኝ፤ከአፍታ በኋላ ይደርሳል።

- ልክ ነህ፣በሐኪም እጅ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሰው ልጅ እጅ ምንም ነገር የለም።

- ታዲያ ነገሮች ሁሉ በማን እጅ ናቸው?!!

- ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ናቸው።

- አደም አምላክህ ማነው?

- የኔ አምላክ ያንተና የዓለማት ሁሉ አምለክ ነው፤አሁን ይህን ተወኝ።

- እናም አንተ ፕሮቴስታንት ነህ ማለት ነው?!

- መታደልን ፍለጋ ፕሮጄክተህ ተሳክቶ ለመታደል ስትበቃ ካንተ ጋር እሆናለሁ።

- ያ ከቀዶ ጥገናው በኋላ በሕይወት ተርፌ ከኖርኩ የሚሆን ነው!

- ተስፋ አድርግ . . በጎ በጎውን ብቻ አለማሰብ ያስጠላኛል!

- ዓለማዊ ሕይወት በቀቢጠ ተስፋ የተሞላች ናት፣ለምን አልቀበልም ትላለህ?

- ዓለማዊ ሕይወት በምንም ላይ ሳይሆን የቆመችው በተስፋ ላይ ብቻ ነው፤አፈተረቶቹን ወዲያ በላቸው።

- እውነቱን ነገረኝና . . በቁጥር 13 ገደቢስነት አታምንም?

- በጭራሽ አላምንም። ዩኒቨርሱን የሚያቀነባብረውና የሚመራው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። በነገራችን ላይ የቁጥሩ የንበት ድምጽ በነሱ ቋንቋ ‹‹መኖር አለብኝ›› ከሚል አገላለጽ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው ቁጥር 13 ቻናውያን ዘንድ የመልካም ዕድል ገድ ነው። የመጥፎ ገድ ነገር በጥቅሉ ከአፈተረትነት ያለለፈና ከእግዚአብሔር መንገድ ያፈነገጠ ጥመት ብቻ ነው።

- ፕሮቴስታንት እንደመሆንህ የወሩ 13ኛ ቀን ዓርብ ላይ ቢውል እንኳ ቀኑን ገደቢስ አድርገህ አትወስደውም? በክርስትና ታሪክ ውስጥ ይሁዳ ክህደት ፈጽሞ አሳልፎ ሳይሰጣቸው ኢየሱስና ሐዋርያዎቹ በምስጢር የተሰበሰቡት ዓርብ ቀን መሆኑንና የተሰብሳቢዎቹም ቁጥር 13 መሆኑንስ አታውቅምን?

- እኔ በአፈተረቶች አላምንም። የመጣሁት ስለ ገደቢስነትና ስለገዳምነት ካንተ ጋር ለመከራከር ሳይሆን አንተን ለመጠየቅ ነው። ወዳጄ ሁሌ መልካም ገድንና ተስፋን ሰንቆ እንዲኖር ነው የምመኝለት።

- የቀዶ ጥገናው የመሳካት ዕድል 60% ብቻ እየሆነ ተስፋ እንድሰንቅ እንዴት ትፈልጋለህ?!

- ጌታችን ርህሩህና ቸር አዛኝ ጌታ ነው፤ሁሉም ነገር በርሱ እጅ ነው። ሐኪሞች ምክንያት ብቻ ናቸው። ተስፋ ስታደርግ የበለጠ ደስተኛ ትሆናለህ፣የተሸለ ለመኖር ትችላለህ፤የቀዶ ጥገናው የመሳካት ዕድልም በጣም ጥሩ ነው። ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ካደረብህ ግን ሁኔታህ የባሰ የከፋ ይሆናል፤ሕይወትህም የከፋ ይሆናል፣ርህሩሁ ፈጣሪ ጌታ የጻፈልህ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ጆርጅ ምን ነካህ በፊት እንደዚህ አልነበርክም'ኮ?

- አንተን ለመፈተንና የምትለውን ማወቅ ፈልጌ ነው፤ተስፋ ማድረግን ካንተ መማር ፈልጌ እንጂ እንደምታውቀው አፈተረትና አጉል አምልኮን አልወድም . . ይሁንና እኔ ባለሁበት ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሰው ተስፋ መሰነቅ የሚችለው እንዴት ነው?

ካትሪና ማይክልና ሳሊን አስከትላ መጣች፣በሀዘን ተውጠው በጥድፊያ ወደ ጆርጅ አልጋ ደረሱ . .

- ጆርጅ አይዞህ፣አሁን እንዴት ነህ?

- ባባ እንዴት ነህ? በጣም አሳሰብከን።

- ባባ ምን ሆነህ ነው?

ከቀዶ ጥገናው በፊት ቤተሰቡ ከአባታቸው ጆርጅ ጋር አብሮ የመሆን ዕድል እንዲኖረው ለማድረግ አደም ክፍሉን ለቆ መሄድ መረጠ . .

- ፍቀዱልኝ እኔ ልሂድ፣ስለ ረበሽኳችሁ ይቅርታ።

- ኦህ . . መኖርህን አላስተዋልኩም ነበር፣ይቅርታ እንደምነህ አደም?

- የለም፣የለም አትሂድ፤ቸኩለህ ካልሆንክ በስተቀር እንድትቆይ ነው የምፈልገው።

- የሚያስቸኩለኝ ነገር እንኳ የለም፣እንዳላውካችሁ ስለፈለኩ ብቻ ነው።

- ምንም የሚያውከን ነገር የለም፣በመኖርህ ደስተኞች ነን።

ጆረጅ ማይክልና ሳሊን ቀረብ አድርጎ አልጋው ጫፍ ላይ አስቀመጣቸውና ስለ ትምህርት ቤትና ስለ ቤት ጠየቃቸው . .

- ባባ እኛ ደህና ነን፤መቼ ነው ወደ ቤት የምትመለሰው?

- እናቴ ከሦስት ቀን በኋላ ትመጣለህ ብላ ነበር፤ስትመጣ በቀጥታ ወደ ሮም እንደምንጓዝም ነግራን ነበር።

- የአይሮፕላን ትኬት ገዝቻለሁ፣የምንጓዘው ከአስር ቀናት በኋላ ነው።

- ትኬቶች ገዛሽ?! እንዴት?! ያለሁበት ሁኔታ ይህን የሚፈቅድልኝ አይመስለኝም።

- አትስጋ፣ድነህ ትሄዳለህ።

- አደም ምን ትላለህ?

- የተባረከ ውሳኔ ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድም እውን ይሆናል፤ይህ ለጥያቄህ መልስ ነው።

- የትኛው ጥያቄ?

- በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ተስፋ መሰነቅ እንዴት ይቻላል? ብለህ ጠይቀኸኝ አልነበረም?

- ነገሮችን ለቸሩ ርህሩህ ጌታ ሰጥቶ ሁሉንም ለርሱ መተው በሕይወታችን ደስተኞች እንድንሆን ያደርገናል።

- ካትሪና እንባ እየተናነቃት ፦ ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስና ስላንተ ስጸልይ ነው ያደርኩት፤እርግጥ ጸሎቴ እንጂ ለቅሶዬ ምንም እንደማይጠቅምህ አውቃለሁ። ጧት ትንሽ የዘገየሁት የገዛሁትን የአይሮፕላን ትኬት የጉዞ ቀን ኦኬ ለማስደረግ ብዬ ነውን፤ጆርጅ ምን ትላለህ?

ካትሪና ባንቺ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ልገልጽልሽ አልችልም፣ተስማምቶኛል . . ቆንጆዋ ሳሊ እስኪ ንገሪኝማ ፦ ወደ ሮም ለመሄድ ጓግተሻል?

- ባባ በጣም በጣም ነው የጓጓሁት። የትሬቪን ፏፏቴ ማየት እፈልጋለሁ።

- የትሬቪ ፏፏቴ ደግሞ ምንድነው?!

- በጂኦግራፊ ትምህርት የተማርነው ትልቅ ፏፏቴ ነው።

- እኔ ደግሞ የቅዱስ አንጅሎን አምባ ማየት እፈልጋለሁ፤ለአጼዎቹ ቅሪተ አጽም ማሳረፊያ የተገነባ አምባ ሲሆን በጂኦግራፊ እንደተማርነው በኋላ ሙዝየም ሆኗል።

- እኔ ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስን ካቴዴራል መጎብየት ነው ምፈልገው።

- ነገሮች በሚገባ የተቀነባበሩ ይመስላል፤እውን እንደሚሆኑመም ተስፋ አደርጋለሁ . .

ሕጻናቱ በደስታ ፈንድቀው አባትና እናታቸውን ላይ ተጠመጠሙ . . በጉጉትና በተስፋ ስለ ጉዞው መነጋገር ከቀጠለው ልዩ ቤተሰባዊ ቆይታ ራሱን ገለል ለማድረግ አደም ወደ ክፍሉ አንድ ጥግ ፈንጠር ብሎ ወንበር ላይ ተቀምጧል . . ካትሪና ሰዓቷን አየት አድርጋ ለሕጻናቱ እንዲህ አለች

- አሁን ሦስት ሰዓት ሆኗል፣ሾፌሩ ውጭ እየጠበቃችሁ ነው።

- እሽ . . ባባ ቻው ቻው፣ ደህና ሁን . .

- ውዶቼ በሰላም እንገናኝ፣ደህና ሁኑ . .

ጆርጅ ለብቻው ወደ ተቀመጠው አደም ፊቱን አዞረ . .

- አደም ይቅርታ፣አልተከፋህም?

- ምኑ?

- የሮም ጉዟችን፤አንተ ፕሮቴስታንት እንጂ ካቶሊክ አይደለህምና።

- አልከፋኝም፤እንዲያውም እንድትጓዝ ነው የማበረታታህ፤የክርስትናን ሃይማኖት ከተለያዩ ጎራዎቹና ጭፍራዎቹ ጋር በይበልጥ እንድታውቅ መሄድህ በጣም የሚደገፍ ነው።

- አደም አንተ እኮ የምትገርም ሰው ነህ!!

- በየመታደል መንገድ ፍለጋ ጥረታችን ላይ ፍጹም እውነተኞች ከሆን እያንዳንዱ ተጨማሪ ጥረትና ዕውቀት ለመንገዱ መገለጽ አንድ ዓይነት ማሳያ በመሆኑ ትኩረት ልንቸረው ይገባል። ቀደም ሲል ወደ ሕንድና ኢየሩሳሌም እንድትጓዝ አበረታትችህ አልነበረም? ምን አዲስ ነገር አለ?

- አዲስ ነገር በኛና በካቶሊኮች መካከል በቀልና ጦርነት መኖሩ ነው . . እናንተ ፕሮቴስታንቶች በሰላሳ ዓመቱ ጦርነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ካቶሊኮችን ገድላችሁ የለም?

- በዚህ ዓይነት አረመኔያዊ መንገድ መገዳደልን ማንም አይወደውም። ደግሞም እኔን ፕሮቴስታንት ነው ያለህ ማነው? ምናልባት ካቶሊክ ሊሆን ስለሚችል ከጉዞህ መልስ እነግረሃለሁ።

- ካቶሊክ ትመስላለህ፤አንተና ካትሪና የምትጋሩት ነጥብ አለ . . በዚህ ሰሞኑ ንባቤና በጉዞዬ ካቶሊካዊነትን በይበልጥ ለማወቅ ጥረት አደርጋለሁ። የመጀመሪያ እምነቴ ግን እንግዳ የሆነ ጣዖት አምላኪነት አለበት የሚል ነው። ልክ እንደ ጣዖት አምላኪዎቹ ቤተመቅደሶች በቅርጻ ቅርጾችና በሥዕሎች የተጨናነቁ ቤተክርስቲያኖቻቸውን አልወድም።

- ሰዎችን የሚገድለውን ፕሮቴስታዊነትን ግን ትወዳለህ።

- ይህ ካቶሊክ መሆንህን ያረጋግጥልኛል።

- ማለት የፈለኩት ይህን ሳይሆን በመታደል መንገድ ፍለጋ ጥረትህ ወቅት በየትኛውም ቡድንና በማንኛውም ፈለግ ውስጥ እውነትን ፈልግ፣መርምር ማለቴ ነው። ይህን ስታደርግ መታደልን፣የሕሊና እርካታና መረጋጋትን ታገኛለህና።

ካትሪና ሁለቱን ሕጻናት ከሸኘች በኋላ ወደ ክፍሉ

ተመለሰች .

.

- በመዘግየቴ ይቅርታ፣ማይክልና ሳሊ ከሾፌሩ ጋር ከመሄዳቸው በፊት ጭማቂና ሳንድዊች ፈልገው አቆዩኝ።

- ካትሪና ለዚህ ጉዞ መሰናዶ በማድረግሽ ከልብ ነው የማመሰግነው፤አእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው የሞት ፍራቻ ከኔ እንዲርቅ ለማድረግ ችለሻል።

- የሰው ልጅ መንፈሱ ሲጠራና ሲመጥቅ እውነታዎች ተገልጠው ከፊቱ ይዘረገፋሉ። ሞት ምንጊዜም ከርሱ ጋር የሚኖርና በማንኛውም ወቅት ሊከሰት የሚችል እውነታ መሆኑንም ይገነዘባል። በመሆኑም ለሕይወት መሸንገያዎችና ለመደሰቻዎቿ እስረኛ መሆኑ ያበቃል። ሀሳቡና ትኩረቱ በዚህ ዓለም ጉዳዮች ተወጥሮ የሚያዝ አይሆንም . . የተፈጠረበትን ዓለማና መመለሻውን የሚያውቅ ሰው የሚኖረው ለመሞት፣የሚሞተውም ለመኖር መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይችላል።

- ‹‹ለመሞት እንኖራለን፣ለመኖርም እንሞታለን›› የሚለው ድንቅ ፍልስፍና ነው፤ግና ችግሩ ጣዕረ ሞትና ስቃዩ ነው።

- ኢየሱስ ለሰው ልጆች ብሎ ስቃይ ተቀብሏል፤ስቃይ ለዘላለማዊው መድህን መሰረታዊ ነገር ነው፤ስቃይን መቀበላችን ለኢየሱስ ላለን ፍቅር ማሳያ ነው።

- ታዲያ ዓለማዊ ሕይወት አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ ነው?

- ጥቅሟ ጌታን ለማገልገልና ለማገልገል ብቻ እንድንጠቀምባት ነው።

- አደም በዚህ ላይ ምን ትላለህ?

- በየትኛው?

- ሕይወት በጥቅሉ ለአምላክ አገልግሎትና እርሱን ለማስደሰት ብቻ መሆን ይገባል በሚለው ላይ።

- ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ . . እግዚአብሔርን ማገልገል ግን መጸለይ ብቻ አይደለም።

ካትሪና በአድናቆት

- በጣም ጥሩ፣በዚህ ላይ ቀሳውስትም ሳይቀሩ ብዙ ጊዜ እንዘነጋለን። ሕይወታችን በሙሉ ለእግዚአብሔር መሆን የሚገባ አምልኮ ነው።

ጆርጅ በስላቅ እየሳቀ፦

- ተደጋጋሚው ጥያቄ ግን ርህሩሁን አምላክ በፍጹምነት የሚያመልክ ሰው ማነው? ቁሳቁስ ወይም ጣዖትን አምላኩ አድርጎ የሚይዝ ማነው? የሚለው ነው።

አደም በቁርጠኝነት መንፈስ፦

- ምናልባት ይህ በታሪክ ውስጥ አሳሳቢውና አደገኛው ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም።

- ጆርጅ፣አምላክን በሚመለከት በኛ መካከል ስላለው ልዩነት ጠቆም ማድረግህ መሰለኝ።

- ምን ለማለት ነው የፈለግሽው?

- እኛ ሁሉም ክርስቲያኖች በሥላሴ ማለትም እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው በሚለው እምነት ላይ ሙሉ በሙሉ እንስማማለን። ሥላሴዎቹም አንደኛው አብ ሁለተኛው ወልድ ሦስተኛው መንፈስ ቅዱስ ነው። በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ባህርያት ላይ ልዩነቶች ቢኖሩንም በሥላሴ እምነት ላይ ልዩነት የለንም።

- ይህን ማለቴ አይደለም፣ይህን አላሰብኩም፣ላለማሰብም ነው የምጥረው። ሦስቱ አንድ፣አንዱም ሦስት በባህሪ የሚለያዩ አማልክት እንዴት እንደሚሆኑ ሊገባኝ አይችልም!

- በክርስትና ውስጥ ከሁሉም አስቸጋሪው ጉዳይ ይህ ነው። ሮም ስትሄድ በዚህ ላይ በስፋት እምድትወያይ ሀሳብ አቀርባለሁ፣እጅግ በጣም የተወሳሰበ አስቸጋሪ ርእስ በመሆኑ እዚህ ባለንበት ቦታ መተንተን አይቻልም።

- ሕይወታችንን ለርሱ አምልኮና ለአገልግሎቱ አሳልፍን የምንሰጠውን በሚገባ እንዴት እንደማናውቀውና እንዲያውም ማወቁ እንዴት አስቸጋሪ እንደሚሆን ሊገባኝ አይችልም። ይልቁንም አንዳንዴ በኛና በጣዖት አምላኪዎች መካከል ምንም ልዩነት አላይም!!

- እመነኝ ከጥያቄው መሸሼ አይደለም፣የሚከተለው ቤተክርስቲያን የፈለገውን ቢሆን ይህ የያንዳንዱ ክርስቲያን ችግር ነው፤ስለዚህ ሮማ ላይ በጥልቀት እንወያይበታለን።

አደም በፈገግታ ፦

- እኔ በበኩሌ በካትሪና ሀሳብ እስማማለሁ፤ይህ ከባድ ርእስ ነው፣እንዲያውም ከሁሉም ጉዳዮች ዋነኛው ነው። ስለዚህም በዚህ ሁኔታ በችኮላ መወያየቱ ተገቢ አይደለም። አእምሮ ያለው ሰው ጣዖታዊ ነው ብሎ በሚያስበው ሃይማኖት ውስጥ መቀጠል የማይችል ሲሆን፣ አንድ መለኮታዊ ሃይኖትም ከጣዖት አምላኪ ሃይማኖቶች አንዱ ሊሆን አይችልም።

- እህህ፣ሁሉም ክርስቲያኖች አንዳንዴ ጣዖታዊነት ይጠናወታቸዋል የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ እናንተ ሁለት ካቶሊኮች እኔም ከናንተ ጋር እስማማለሁ!

ካትሪና በመገረም ፦

- አደም አንተ ካቶሊክ ነህ እንዴ?

- አንዳንዴ ካቶሊክ ነህ ይለኛል፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ፕሮቴስታንት ነህ ይለኛል።

- አሃ፣በቃ አሁን ካቶሊክ መሆኑን አረጋግጫለሁ . .

ጆርጅ በመሳቅ ላይ እያለ ሐኪሙ ገባ . . ፈገግ እያለ ወደ ጆር አልጋ ተጠጋ

. .

- እንዲህ ነው እንጂ፣የነገርኩህ ነገር እንዳለ ሆኖ እንደዚህ ደስተኛ ሆነህ እንደማገኝህ እርግጠኛ ነበርኩ።

- ዶክተር ኖር እንኳን ደህና መጣህ፣እንደዚህ እርግጠኛ የሆንከው ግን ለምንድነው?

- ማንኛውም ምሁርና ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው ከሌላው ይበልጥ ራሱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ማስረከቡ የግድ ነው።

- ለመሆኑ እግዚአብሔር ማነው?

- ቀድሞውኑ አንተ ፈላስፋ ነህ ብያለሁ። እኔ ክርስቲያን ነኝና ይህን ርእስ እሸሻለሁ፣ከፍተኛ ጥረት ባደርግም ሊገባኝ አልቻለም። ርህሩህ ቸርና ቻይ የሆነ ፈጣሪ አምላክ ስለመኖሩ ግን እርግጠኛ ነኝ፣ይኸ በቂዬ ነው።

- እኔ ግን ይህ ብቻ በቂዬ ነው ብዬ ፈጽሞ አላስብም፣የማላውቀውን አምላክ እንዴት ነው የማመልከው?

- አንተ ትፈላሰፋለህ፣ለማንኛውም ቀዶ ጥገናው እንዲከናወንልህ በፊርማ አረጋግጠሃል?

- አላደረኩም፣ለመፈረም ግን ዝግጁ ነኝ፤ካትሪና እንደዚያ አይደለም እንዴ?

- የቀዶ ጥገናውን ስኬታማነት የበለጠ ከፍ የሚያደርጉ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ? ወይም ቀዶ ጥገናውን ለማከናወን የተሻለ ቦታ ይኖር ይሆን?

- ይህን ቀዶ ጥገና ለማከናወን ተመራጩ ሆስፒታል ጀርመን አገር ነው የሚገኘው፤ይሁን እንጂ አሁን ወደ ሌላ ሆስፒታል መዛወር የሚቻልበት ሁኔታ የለም። ቀዶ ጥገናው ዛሬውኑ መደረግ ይኖርበታል። ትናንት ጀርመን ከሚገኘው እሰቴሽያሊስት አማካሪ ጋር ግንኙነት አድርገን በጣም አበረታቶናል። የስኬታማነቱን ዕድል ከፍ የሚያደርገውን ነገር በተመለከተ ይህ ነው ብዬ መጥቀስ የምችለው የተለየ ነገር አላውቅም።

- ምን ትመክረናለህ?

- በአስቸኳይ ስምምነቱን እንድትፈርሙ ነው። የቀዶ ጥገናውን የመጨረሻ ምርመራ አስራ አንድ ሰዓት ላይ እንጀምራለን፣ቀዶ ጥገናው ዛሬ ሁለት ሰዓት ይከናወናል።

- ቀዶ ጥገናውን ማነው የሚደርገው?

- የቀዳጅ ሐኪሞች አምበል ዶክተር እስቲቭ ማይክ ነው፣እስቴሽያሊስት አማካሪ ሐኪም ናቸው።

- እንፈርም ዘንድ ወረቀቱን ልትሰጠን ትችላለህ፣የምትመክረን ሌላ ነገር ካለም ጥሩ ነው።

- ሌላ ነገር የለም፣እስከ ቀዶ ጥገናው ድረስ እንዲሁ ደስተኛ ሆነህ እንድትቀጥል እሻለሁ፣በሳይንሳዊ መንገድ ባልተረጋገጠ ተሞክሮዬ እንደማውቀው ተስፋ በሰነቀ አዎንታዊ ስነ ልቦናዊ ሁኔታ ላይ ያሉት ሰዎች ቀዶ ጥገና ከሌሎች ይበልጥ ስኬታማ ነው።

- መልካም ነው . . ተስፋ መሰነቅንና በጎ በጎውን በመጠበቁ ረገድ ከአደም ጋር ሳትስማሙ አትቀሩም።

- አንተንም ጨምሮ አርቆ አስተዋይ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በዚህ የሚስማሙ ይመስለኛል።

- ካትሪና ከቀዶ ጥገናው በኋላ ለምናደርገው ጉዞ ትኬቶችን ገዝታ የጉዞ ዝግጅቱን ያጠናቀቀችው ካትሪና በዚህ ረገድ ከሁላችንም ልቃ ሳትገኝ አልቀረችም።

- ግሩም ነው፣ከቀዶ ጥገናው በኋላ ለዕረፍትና ለክትትል ከአንድ ሳምንት ጊዜ በላይ አያስፈልግህም፤ከዚያ በኋላ መውጣት ትችላለህ . . ይሁን እንጂ ከቀዶ ጥገናው አስር ቀን በኋላ እንጂ ጉዞ ማድረግን አንመክርም።

- እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣የአይሮፕላን ቦታ የተያዘው ከዛሬ አስር ቀን በኋላ ነው፣ግምቴ በደንብ ይዞልኛል ማለት ነው . .

- አዎ፣ድንቅ ሥራ ነው የሰራሽው . . ጆርጅ የተባረከች ሚስትና ግሩም ድንቅ ወዳጆች አሉህ፣እንኳን ደስ አለህ እለሃለሁ። የሚፈረሙ ወረቀቶች ከአፍታ በኋላ ይደርሱሃል፤የቀዶ ጥገናውን ቅድመ ሂደቶች አሁን እጀምራለሁ፤ፈጣን ፈውስም እመኝልሃለሁ።

ሐኪሙ ከወጣ በኋላ ጆርጅ ወደ ካትሪና ዞሮ እንዲህ አለ . .

- እንግዲህ ነገሮች ቀዶ ጥገናው ይደረግ ወደሚለው ያደሉ ይመስላል፤ከዚያ በፊት ያለው አጭር ጊዜ ብቻ በመሆኑ አንዳንድ ነገሮችን መልክ ማስያዝ ያስፈልገኛል።

- ጥሩ፣ምን ማድረግ ፈለክ?

- ከሞትኩ ሳይታወቁ ጠፍተው እንዳይቀሩ ያለኝን ንብረት ሁሉ በዝርዝር መዝግቤያለሁ፣ያለኝን ሀብት በሙሉ ላንቺና ለሁለቱ ልጆቼ ብቻ እንዲከፋፈል ነው የጻፍኩት።

- ጆርጅ እባክህ እንደዚህ አትበል . . ገና ትኖራለህ፣በሰላም ድነህ ትወጣለህም።

- በማቋረጤ ይቅርታ አድርጉልኝ፣ድነህ በሰላም እንደምትወጣ እርግጠኛና ባለ ሙሉ ተስፋ ከመሆኔም ጋር፣አሁን እርሱ የሚለው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህን ባታደርግ ኖሮ ምናልባት ንብረትህ ሳይታወቅ ሊቀር ይችላል። ከይቅርታ ጋር እንዲያውም አንዳንድ የቤተክርስቲያን መመሪያዎችን ተግባራዊ አድርገህ ቢሆን ኖሮ ባለቤትህን ተገቢ መብቷን ታሳጣት ነበር።

- የምትለውን መረዳት አልቻልኩም፣አንተ ሃይማኖተኛ እየሆንክ እንዴት እንዲህ ትላለህ?

- አባትና እናትህስ?

- ሳላያቸው አስር ዓመት ያህል ይሆነኛል።

- ይህን ለመናገር አሁን ጊዜው ላይሆን ይችላል . . ይሁን እንጂ ይህ ያለ ጥርጥር ጥፋት ነው።

- ካንተ ጋር እስማማለሁ፣ስለ ወላጆቹ ጉዳይ ካንድ ጊዜ በላይ ነግሬዋለሁ። የኔ ወላጆች በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ እንዴት በተደሰትኩ ነበር።

- ዛሬ ሁለታችሁም በሁሉም ነገር በኔ ላይ የተስማማችሁ ይመስላል። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ስነቃ ከመጓዛችን በፊት ወላጆቼን ልጎበኛቸው ቃል ገብቼላችኋለሁ . . ቀዶ ጥገናው በሕይወቴ ውስጥ መለያ ነጥብ ሳይሆን አይቀርም።

- በኑዛዜህ ውስጥም ብትጠቅሳቸው መልካም ይሆናል።

- ልክ ነው፣መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹እግዚአብሔር፡- አባትህንና እናትህን አክብር፤ . . ብሎአልና፤›› በማለት ለወላጆች ደግ እንድንሆን አዟል።

- የሚያሳዝነው የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዞች አንዳንዴ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መሆናቸው ነው፤አሁን የጠቀስሽውን አንብቤ ‹‹ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እህቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፣ደቀ መዝሙሬ መሆን አይችልም፡፡›› የሚለውን ሉቃስ ወንጌል ውስጥ ሳነብ ግራ ይገባኛል።

- በኛ በካቶሊኮች ዘንድ አንተ አሁን የጠቀስከው ዓይነት ግጭት አእምሯችን ውስጥ ሲፈጠር ውሳኔ እንዲሰጡበት ጉዳዩ ወደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይተላለፋል፤ፕሮቴስታንቶች ግን በዚህ ላይ ብዙ ይቸገራሉ።

- ለጣዖታዊነት ወደ ቀረበውና አእምሮን አውልቆ ወዳስቀመጠው አስከፊ ፓፓዊ ሥርዓት ልትመልሽን ነው። ዋናው ነጥብ ይህንን በኋላ እንመለስበታለን፣አሁን ይበልጥ ወደሚያሳስበንና ወደነበርንበት ጉዳይ እንመለስና ወላጆቼን በምክራችሁ መሰረት በዝርዝሩ ውስጥ እጨምራለሁ። ከአፍታ በኋላም በምስክርነት ትፈርሙበት ዘንድ የኑዛዜ ወረቀቱን እሰጣችኋለሁ ።

- በእግዜአብሔር ፈቃድ በሰላም እንደምትወጣ እርግጠኛ ብሆንም ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ።

- የሕይወት ዋስትና እንሹራንስ ውሌን ከአንድ ወር በፊት አሳድሻለሁ፣ከሞትኩ በኋላ ለናንተ ዋስትና ይሆናል ።

- የመድህን ዋስትና የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ይህ ምክንያት ብቻ ነው ።

- ቤቱን በተመለከተ . .

- የምትፈልገውን ሁሉ በኑዛዜው ላይ ማስፈርህ አስፈላጊ ነው፤አሁን ከዚያ ይበልጥ አስፈላጊው እንዲፈውስህና ቀዶ ጥገናውን ስኬታማ እንዲያደርገው እግዚአብሔርን መለመንና መጸለይ ነው . . (ፈግ ብሎ ቀጠለና) ፦ ከሮማ ስጦታ እንድታመጣልኝ እንደምፈልግም እንዳትረሳ።

ካትሪና ሳትፈልገው ጥሶ መጉረፍ የጀመረውን እንባዋን ጠራረገችና በአደም የስጦታ ጥያቄ ፈገግ አለች . .

- ልክ ነህ . . ከሁሉም በላይ በጸሎታችን እግዚአብሔርን መለማመን ነው፤ከሮማ እንዲመጣልህ የምትፈልገው ስጦታ ግን ምንድነው ?

- እህህ፣እንግዲህ የሕንድም ይሁን የጣሊያን ዑድ ሽቶ ሮማ አይገኝ፣ከቫቲካን ካቶሊካዊ ስጦታዎችን አላመጣልህ . .

- ሁለቱንም አልፈልግም፤የምፈልገው ሁለት ስጦታዎችን ነው። አንደኛው በጣም ግሩምና በጣም ርካሽ የሆነ የኪስ ቆዳ ቦርሳ ነው፤ርካሽ ካልሆነ ግን አልፈልገውም። ሁለተኛው የኢጣሊያ እግር ኳስ ታላቅ ኮከብ የካርኒቫሮን ትልቅ ሬክላም እንድታመጣልኝ ነው።

- በጣም ግሩም የሆነ ውብና ርካሽ የቆዳ ቦርሳ! ይህ የማይመስል ነው . . እህህ፣ሙጢዕ አርረሕማንን ጣሊያን ውስጥ ካለገኘነው በስተቀር የሚቻል አይመስለኝም ።

- ሕንድ ውስጥ ሙጢዕ አረሕማንን የገራልህ ጌታ ጣሊያን ውስጥም ሌላ ሙጢዕን መቻችልሃል።

- ለመጀመሪያ ጊዜ እስፖርተኛ መሆንህን ማወቄ ነው!

- ካርኒቫሮ ያለፈው የዓለም ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ነው። እንደ ብዙዎቹ የጣሊያን ስፖርት ተንታኞች ግምት የቀድሞው ዝነኛ ኮከብ የፍራንኮ ባሬዚ ተተኪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ለማንኛውም እኔ ስፖርትን ከመመልከት ይልቅ መስራትን ነው የምወደው፣ጥያቄዬ ግን ይኸው ነው።

- ከቫቲካን መስቀል እንዲመጣልህ ከፈለክ ጆርጅ ካላመጣልህ እኔ አመጣልሃለሁ።

- በኔ ላይ በቃ ሁሌም አንድ ናችሁ ማለት ነው።

- አመሰግናለሁ፣በወዳጄ እየቀለድኩ ነው፤እንድሄድ ትፈቅዱልኛላችሁ?

በዚህ አፍታ . . ቶም ደረሰና ክፍሉን የሞላውን ፈገግታና ሳቅ ተመለከተ . .

- ጆርጅ አዲስ ነገር የተገኘ ይመስላል፣እስቲ አብስረን።

- አዲስ ነገር እንኳ የለም፤ወዳጄ አደም በጣም ውብና በጣም ርካሽ የሆነ የጣሊያን የቆዳ ቦርሳ ስጦታ ከሮማ እንዳመጣለት ጠይቆኝ ስንስቅበት ነበር።

- ከሮማ?! ቀዶ ጥገናውን እዚያ ለማድረግ ወደ ሮማ ልትጓዝ ነው?!

- መጀመሪያ ከወዳጄ ከአደም ጋር ላስተዋውቅህ፤አደም ይህ ወዳጄ ሐኪም ቶም ነው . . ቀዶ ጥገናውን ዛሬ አድርጌ ከአስር ቀን በኋላ ከውድ ባለቤቴ ከካትሪና እና ከልጆቻችን ጋር ወደ ሮማ እንሄዳለን። ቦርሳውን እንዴት እንደማመጣለት ግን አላውቅም።

- እንዲህ ያለው ግሩም ድንቅ በተስፋ የተሞላ ብርቱ መንፈስ የትም የማይገኝ ነው፤ቀዶ ጥገናውን በተመለከተ የተለወጠ ነገር አለ?

- የለም፣የተለወጠ ነገር ቢኖር ካትሪና ይዛ ባመጣችልኝና ከአደም በተማርኩት በተስፋ የተሞላ ብርቱ የመንፈስ ጥንካሬ ለሕይወት ያለኝ አመለካከት ነው።

- በተስፋ የተሞላ መንፈስ ከምንም በላይ አስፈላጊያችን ነው፤የብዙዎቹ የአእምሮ ሕመሞችና የስነ ልቦና ችግሮች መፍትሔ በዚህ ውስጥ ነው ያለው። መማሩ ግን አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል።

- ከአደም ጋር ቁጭ በል፣በዚህ ረገድ ተዝቆ የማያልቅ ሀብት ስላለው ያስተምረሃል።

- እናም የርሱ ተማሪ ሆኜ ከርሱ በመማር መታደል ይኖርብኛል።

- ግልጽ ለመሆን ካንተ ጋር ስቀመጥ ከምፈላሰፍባቸው መልሶች መካከል ብዙዎቹን የሚወስደው ወይ ከርሱ ነው፣ወይ ደገሞ ከካትሪና ነው . . ‹‹ነገሮችን ሳናካብዳቸውና ሳናወሳስባቸው ቀለል አድርገን መውሰድ አለብን›› የሚለውን ደጋግሜ ሳነሳልህ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ይህን የወሰድኩት ከአደም ነው።

- በጣም ግሩም ነው፣በተለይ ይህ አባባል ካንተ ከሰማሁት በኋላ አመለካከቴንና ባህሪዬን በከፊል ቀይሯል። ቀደም ሲል ተፈጥሮዬና ንባቤም ነገሮችን ወደ ማቅለል ሳይሆን ወደ ማወሳሰብ አቅጣጫ ያዘነበለ ነበር።

- አይምሰልህ ጆርጅ የወጣለት አሟካሽ ነው፣ከርሱ ለመማር አብሬው የምቀመጠው እኔ ነኝ፤እኔ ተራ የካፍቴሪያ አስተናጋጅ ስሆን እርሱ ግን አስተማሪዬና መምህሬ ነው።

ካትሪና በፈገግታ

- ማሞከሻሸት ከጀመርን ዘንዳ ይህ ሁሉ የጆርጅን የግርታ ጥያቄዎች እንቆቅልሽ የፈታው የቶምም ጥረት ውጤት ነው።

ቶም በመገረም ስሜት

- ይቅርታ . . እርግጠኛ ለመሆን ብቻ፣እውን ቀዶ ጥገናው ዛሬ ይካሄዳል?

- አላመንከኝም መሰለኝ፣ አዎ . . የተስፋ መሰነቅ ትምህርት መልመጃዎች አሁንም ገና የሚያስፈልጉህ መሰለኝ። ሁሉንም ነገሮች መልክ መልክ አስይዣለሁ፣የሚቀረኝ አንዳንድ ማስታወሻዎችን ለመጻፍ ግማሽ ሰዓት ብቻ ነው። ሞትም ሆነ ሕይወት ያለው በአላህ እጅ ብቻ ነው።

- ቀዶ ጥገናው መች ነው የሚደረገው?

- ሂደቱ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ይጀምራል፣ቀዶ ጥገናው ደግሞ ሁለት ሰዓት ነው።

አደም ሰዓቱን ተመለከተ . .

- አሁን ፍቀዱልኝ፣የግድ ወደ ካፌቴሪያው መሄድ አለብኝ።

- አደም የምስጋና ቃላት ያጥሩኛል፣አንተ ምርጥ ወዳጅ ነህ።

- አደም አንዴ፣ይህ ቢዝነስ ካርዴ ነው፣ ካንተ ጋር በደንብ መተዋወቅና ካንተ ጋር መወያየት ምኞቴ ነው።

- የግድ ልትገናኙ ይገባል . . አደም ሐኪም ቶም ቀደም ሲል ከነገርኩህ አሁን የተለወጠ ይመስላል።

- ካንተ ጋር በመተዋወቄ ክብር ይሰማኛል፣ቢዝነስ ካርድ ስለ ሌለኝ ግን ይቅርታ . .

ከኪሱ ቁራጭ ወረቀት አውጥቶ ስሙንና ስልክ ቁጥሩን ጻፈና ለቶም ሰጥቶት ተሰናብቶት ሄደ . .

- ከተዋወቅኩት አጭር ጊዜ ብቻ ቢሆንም አደም ከወዳጆቼ ሁሉ ምርጡ ወዳጅ ነው።

- በጣም ጨዋ የሆነ ሰው ነው። አንተ ራስህን ስተህ በነበረበት ጊዜ ካኽ ሊጠይቅህ መጥቶ አደምን አስተናጋጅ በመሆኑ አፌዞበት ነበር፤እርሱ ግን ምንም ክፉ ቃል አልመለሰለትም፤ያለው ነገር ቢኖር ‹‹የኔ ማንነት ከውስጤ የሚመነጭ እንጂ ከውጭ የማመጣው አይደለም›› የሚል ብቻ ነበር።

- ላገኘውና ልተዋወቀው ይገባል . . አንተ ጆርጅ የኔን መለወጥ አምነህ መቀበልህም መልካም ነገር ነው።

የጆርጅ ስልክ ሲያቀጨል ቶምና ካትሪናን ይቅርታ ጠይቆ መነጋገሪያውን አነሳ። አለቃው ካኽ ነበር . .

- አሁን ደህና ትመስላለህ፣ራስህን ስተህ በነበረበት ጊዜ ልጠይቅህ መጥቼ ነበር። የካፌቴሪያ አስተናጋጁ አንተ ዘንድ ነበር፤አሁን እንዴት ነህ?

- እኔ ደህና ነኝ፣አስተናጋጁ ወዳጄ በመሆኑ ማንም ሰው የሚያስከፋውን ነገር እንዲናገር አልፈቅድም።

እህህ፣የምሥራች ልንገርህ . . በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ሦስት ታላላቅ የውል ስምምነቶችን ለመፈረም በመቻልህ የዳይሬክተሮች ቦርድ እንድትሸለም ወስኗል።

- አንተንም እነሱንም አመሰግናለሁ፤ሽልማቱ ምናልባት ጉቦ ስላቀበልኩ ሊሆን ይችላል።

ይህን ተውና ሥራ መቼ ነው የምትጀምረው? የእረፍት ፈቃድ አልወሰድክም እኮ።

- አላወኩም፣ዛሬ የቀዶ ጥገና አደርጋለሁ፣ከዚያ ለዕረፍት ወደ ሮማ እሄዳለሁ። ስመለስ የሥራ ፈቃድ እጽፍልህና ሥራውን መቀጠል አለመቀጠሌን እወስናለሁ።

- ስሜታዊ ወይ በጣም የተሰላቸህ ትመስላለህ፤እንዲዚህ ስትናገር ሰምቼህ አላውቅም።

- አዝናለሁ፣የራሴን መርህ ረግጬ ለቤንያሚን የጉቦ መሳሪያ ነው የሆንኩት።

- በቀዶ ጥገናው ምክንያት የተረጋጋህ አይደለህምና ሌላ ጊዜ እደውላለሁ፣ደህና ሁን።

- ደህና ሁን . .

- የኔ ፍቅር ምንድነው ነገሩ . . ?

- ያ ካኽ ነው፣የአደም ተጻራሪ ምስል፤አደብ የለው፣ጸባይ የለው፣መርህ የለው!

- ከልክ ባለፈ ቁሳዊነት፣በኤቲዝምና ከሃይማኖት በመራቃቸው ምክንያት በሕብረተሰባችን ውስጥ የርሱ ዓይነቶች እጅግ ብዙ ናቸው።

ቶም

አከለ፦

- በኔ እምነት የሰው ልጆች ዋነኛ ችግር ከእግዚአብሔር መራቃቸው ነው። የጭንቀት የውጥረት የብክነትና የአደጋዎች ሁሉ ዋነኛ ምክንያትም ይኸው ነው።

- ይህን ከካትሪና ብሰማው እረዳለሁ፣ከቶም መሰማቱ ግን እንግዳ ነገር ነው የሚሆንብኝ!!

- እህህ፣መለወጥህን ተቀብያለሁ ብለህ አልነበረም? በሌላ በኩል የከፋውን አደጋ የሚጋርጡት የሃይማኖት መሪዎች ነን ባዮች ስለሆኑ እንጂ ሁሉም ሳይንሳዊ ጥናቶች ያልኩትን ያረጋግጣሉ።

- የካቶሊኮችን ፓፓዊ አመራር ማለትህ ነው።

- አንደምታው ይገባኛል፣ለማንኛውም የመጣሁት ልጠይቅህ ነውና ፍቀዱልኝ ልሂድ፤ነገ መጥቼ አየሃለሁ።

- ቶም በጣም አመሰግናለሁ፤በጉብኝትህ እጅግ ረክቻለሁ።

ቶም

እንደ ወጣ . . ካትሪና ወደ ጆርጅ ዞር አለችና . .

- እውነቱን ለመናገር ቶም በጣም ነው የተለወጠው!

- ልክ ነሽ፣ሃይማኖት በሰው ውስጥ ያለውን ሁሉንም ነገር ይለውጣል።

- ድንቅ ነው፣ጆርጅ አንተም'ኮ ተለውጠሃል

- ሊሆን ይችላል!

- ልጆቹ ዘንድ ወደ ቤት እሄድና ጊዜውን ለአንተ በመጸለይ አሳልፋለሁ፤አስራ አንድ ሰዓት ላይ ወዳንተ እመለሳለሁ።

- ወረቀቶቹን ጨርሼ ስለማስረክብሽ የግድ መመለስ ይኖርብሻል።

ተስፋና ስጋት (3)

ጆርጅ ኑዛዜውን በማዘጋጀት ተጠምዶ ንብረቶቹን በዝርዝር አሰፈረ። በአንድ ሰዓት ውስጥ ሁሉንም አዘጋጅቶ ጨረሰ . . በመቀጠል የሚደረግለትን የቀዶ ጥገና ሕክምና በመንገር
በጸሎታቸው እንዲያስቡት ለሁሉም ወዳጆቹ መልእክት ለመላክ ወሰነ። ከመካከላቸው በትክክለኛውና በእውነተኛው መንገድ የሚጓዝ ሰው አምላክ ዘንድ ተሰሚነት ሊኖረው ይችላል ከሚል በመነሳት ጸሎቱ ከሁሉም ሃያማኖቶችና የእምነት ፈለጎች ተከታይ ወዳጆቹ እንዲሆን ወደደ . . ለሁሉም ኢ-ሜይል ላከ። በተለይም ለካቶሊኩ ሐቢብ፣ለአይዳዊቱ ሌቪ . . ከወዳጆቹ መካከል ሙስሊም ስለ መኖሩ ሲያስብ ሙጢዕ አረሕማን ትዝ አላለው፣ለርሱም ጸፈ። ሕንድን ሲያስታውስ ቡድሂስቷ ጆስቲና ትዝ አለችው፣ግና እነዚህ ጣዖታውያን ራሳቸው ጠፍጥፈው ወይም ጠርበው የሚሰሩት አምላካቸው ይጠቅማል ወይም ይጎዳል ብዬ አላምንም፣ጣኦታዊነት አስጠሊታ ነው . . ሲል ደምድሞ ኮምፒውተሩን ዘጋ።

ስልኩ

ጮኸ፣እንግዳ ቁጥር ነበር፣አነሳው . .

- ሃሎ።

- ሃሎ ጆርጅ፣ስለ ጤንነትህ አጽናናን።

- ሃሎ ማን ልበል?

- ረሳኸኝ መሰለኝ፣ሌቪ ነኝ ከቴል አቪቭ።

- ሌቪ እንደምነሽ . . እንዴት ልረሳሽ እችላለሁ፤ደግ የዋለችልኝን ብዙ ያስተማረችኝን ሰው እንዴት እረሳለሁ? ሌቪ ናፍቀሽኛል፤ድምጽሽን መለየት ባለመቻለ ይቅርታ፤ትደውያለሽ ብዬ አልጠበኩም ነበር።

- የቀዶ ጥገናው ነገር እንዴት ነው? በጣም ነው ያሳሰበኝ።

- ለበጎ ስሜትሽ ምስጋናዬ የላቀ ነው፤ቀዶ ጥገናው ዛሬ ይደረጋል፣ስኬታማ ይሆናል የሚል ትልቅ ተስፋ ሰንቄያለሁ፤የጻፍኩላችሁ እንድትጸልዩልኝ ብቻ ነው።

- እጸልይልሃለሁ፣ግና እያዘንኩ ጸሎቴ በአይሁዳዊነት መንገድ ነው።

- ለምን አዝናለሁ ትያለሽ?!

- ከአንተ ጉብኝት ወዲህ የመታደልን መንገድ ለመፈለግ በሃይማኖቶችና በእምነት ፈለጎች ላይ ንባብ እያካሄድኩ ነው። ወደ የመታደል መንገድ ለመድረስ ምክርና መመሪያህን በመጠባበቅ ላይ ነኝ።

- ትንሽ ያጋነንሽው መሰለኝ፤ካንቺ የተማርኩት እኔ ነኝ፣በተለይም ግልጸኝነትንና ለራስ መታመንን ካንቺ ተምሬያለሁ . . በነገራችን ላይ የጓደኛችን የሐቢብ ወሬስ?

- ይኸው አጠገቤ ነው ያለው፣ሊያናግርህ ይፈልጋል።

- እህህ፣ጥበቃውና ዘበኝነቱ በስልክም ጭምር ነው በይው . . ሐቢብ ድንቅ ሰው ነው . . ሌቪ ጉድኝታችሁን ይበልጥ ለማጥበቅ ሞክሩ፣ለሰው ልጅ ጓደኛ በጣም ወሳኝ ነው።

እህህ፣ ምናልባት ሐቢብ የሚነግርህ ነገር ሊኖር ይችላል . . ዋናው ነገር ሁላችንም ስላንተ እንጸልያለን። ፈጣን ፈውስ እመኝልሃለሁ፣ቀዶ ጥገናው ከተጠናቀቀ በኋላ ደውልልን፣ሐቢብን እንካ።

- ሃሎ ጆርጅ፣ዘበኛው ነኝ፤ምንድነው ነገሩ? አሁን እንዴት ነህ?

- ዛሬ የቀዶ ጥገና ሕክምና ይደረግልኛል፤ተፈውሼ በመልካም ሁኔታ ላይ እሆናለሁ። አንተስ እንዴት ነህ? ናፍቀሃለሁ።

- እኛ በጣም ደህና ነን፣እኛ የበለጠ ናፍቀንሃል፤ጉብኝትህ በእርግጥ የውይይት መክፈቻ ቁልፍ ነበር . .

- ዶክተር ይህ ያንተ ትህትና ነው . . ካንተ ብዙ ነው የተማርኩት፣ስለ ክርስትና የተለያዩ ፈለጎች የተናገርከው እስካሁን ጆሮዬ ውስጥ እንዳቃጨለ ነው። በነገራችን ላይ የነገርከኘን ለማረጋገጥ በመጪው ሳምንት ሮምና ቫቲካንን እጎበኛለሁ።

- ግሩም ነው፣መታደልን የመፈለግ ጉዞህን ቀጥልበት፣የምትደርስበትን ውጤት እንደምታሳውቀን የገባህን ቃልም አትዘንጋ።

- ፈጽሞ አልረሳም፤የመታደል መንገድ ፍለጋው የት እንደደረሰ አሳውቃችኋለሁ፣ለሌቪም ቃል ገብቻለሁ።

- አስደሳች ዜና ልንገርህ . . ከሌቪ ጋር ሳንጋባ አንቀርም።

- ዋው! . . የተባረከ ይሁን፣እንኳን ደስ አላችሁ . . ካቶሊካዊ ወይስ አይሁዳዊ ጋብቻ?

- እህህ፣ጋብቻው ከወራት በኋላ እንጂ አይፈጸምም፣ገና ያልተፈቱ አንዳንድ ጉዳዮች አሉ። አይሁዳዊም ይሁን ወይም ካቶሊካዊ ወይም ፕሮቴስታንታዊ ወይም ሌላ ግን ወደ መታደል መንገድ በሚያደርስ መንገድ ነው ሊሆን የሚችለው።

- ወደርሱ የሚያደርሰውን መንገድ ለማወቅ ይረዳን ዘንድ ፈጣሪ አምላክን እንለምነዋለን።

- ጌታ ካንተ ጋር ይሁን። ስለ ጤንነትህና ስለ መታደል መንገድ ፍለጋው ለማወቅ በጉጉት እንጠብቃለን። ደህና ሁን።

ጆርጅ

የሆነ ነገር በማሰላሰል ላይ እያለ የነርሷ ድምጽ አቋረጠው . .

- አንዳንድ ምርመራዎችን ለማካሄድ አሁን መሄድ አለብን።

ጆርጅ ሰዓቱን ተመለከተ፤ልክ አስራ አንድ ሆኗል። የተለያዩ ምርመራዎች ከተደረጉለት በኋላ ወደ ክፍሉ ተመለሰ . . ሰዓቱ አስራ ሁለት ተኩል ነው፣ካትሪና ገና አልመጣችም ነበረና ደወለላት። ሆስፒታሉ መግቢያ በር ላይ መሆኗን ነገረችው። ከደቂቃዎች በኋላ ካትሪና መኪናዋ ተበላሽቶ በሕዝብ ማመላለሻ ለመጠቀም በመገደዷ ስለዘገየች እያዘነችና ይቅርታ እየጠየቀች ገባች።

- ስትቆዪ ምን አገኝቷት ይሆን ብዬ አሰብኩ።

- መኪናዋ መንገድ ላይ ስትበላሽብኝ የበለጠ እንዳልቆይ መንገድ ዳር አቁሜ በአውቶቡስ ተሳፈርኩ።

- ይህን ፖስታ ያዥው፣ክፉ ነገር ቢያጋጥም የሚያስፈልጉሽ ወረቀቶችና ሰነዶች ሁሉ ተካተውበታል።

- በእግዚአብሔር ፈቃድ ክፉ አያገኝህም፣ተፈውሰህ ትወጣለህ።

- አንድ ያልጻፍኩት ነገር አለ።

- ምንድነው?

- ላንቺም ይሁን ለልጆችሽ የመታደል መንገድ ፍለጋውን እንድትቀጥዪበት እፈለጋለሁ።

- የመታደል መንገድ ፍለጋውን አንተው ራስህ ታሟለዋለህ፤ወደምትፈልገውም ትደርሳለህ . . የመልካም ስነ ምግባርና የመርህ ባለቤት ነህና እግዚአብሔር ፈጽሞ አያሳፍርህም።

- እንባሽን ጥረጊ . . ካቲ ቃል ግቢልኝ።

- በእግዚአብሔር ፈቃድ ካንተ ጋር በመሆን የመታደል መንገድ ፍለጋ ጉዞውን እቀጥልበታለሁ፤ለዚህም ቃል ገብቼልሃለሁ። የመጀመሪያው ፍለጋም አብረን ወደ ሮማ በምናደርገው ጉዞ ይሆናል።

- ካትሪና እወድሻለሁ . .

ወደርሷ ቀረብ

ብሎ እቅፍ አደረጋት . . በለቅሶ ፈነዳች . .

- ጆርጅ እኔም እወደሃለሁ።

- እንደ ልማድሽ በተስፋ የተሞላሽ ሁኚ፤በሮም የምናርፍበትን ሆቴል ይዘሽልናል?

- አዎ።

ቀሪ ምርመራዎችን ያጠናቅቅ ዘንድ ጆርጅን ለመውሰድ ነርሷ መጣች . . የካትሪናን እጅ ጠበቅ አድርጎ በመያዝ ወደ ቤት እንድትሄድና እንድትጸልይለት ለመናት . .

- የኔ ፍቅር ወደ ቤት ሂጂ። ከአፍታ በኋላ ለማደንዘዣ ይወስዱኛል፣ቀዶ ጥገናውም ሦስት ሰዓት ይወስዳል . . እናም እዚህ መቆየትሽ አስፈላጊ አይደለም። ሁሉም ነገር ስለሚሳካ ተረጋጊ . .

- እንዲህ አትበል፣ጆርጅ እወደሃለሁ፣ካንተ ጋር ወደ ሮም እንጓዝና የመታደለን መንገድ እናገኘዋለን።

- የኔ እመቤት መሄድ ትችያለሽ፤ቁጥርሽ ስላለ ከቀዶ ጥገናው በኋላ እንደውልልሻለን።

- ጆርጅ እንግዲያውስ ጌታ ይጠብቅህ፣ዕድሜህንና ሕይወትንህም ይባርክ።

ለራሱ ፈጽሞ ፍርሃት የሚባል ነገር ዝር ባይልበትም ልቡ

ለካትሪና እና ለልጆቹ በፍርሃት እየራደ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍሉ አመራ። የእያንዳንዱ ሰው ጭንቀትና ሀሳብ ለገዛ ራሱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህች ዓለም ምን ትሆን ነበር? ሲል ራሱን ጠየቀ። በእርግጥ የማይታሰብ አደጋ ነበር የሚሆነው፣የሌሎችን ሕመም፣ሀሳብና ጭንቀት መጋራት የራስን ሕመምና ጭንቀት ለማቅለልና በተዕግስት ለመቋቋም አጋዥ ነው . . ሕይወትም እንደዚሁ፣ሰዎችን ለመጥቀም ለማስደሰት የሚኖር ሰው ደስተኛ ይሆናል፣መታደልንም ያገኛል። ለራሱ ብቻ የሚኖር ሰው ደግሞ መንገዱን ይስታል . . እየተግተለተለ የሚመጣ ሀሳቡን ሐኪሙ አቋረጠው . .

- አሁን በከፍተኛ የመረጋጋትና የሕሊና ሰላም ላይ እንድትሆን እፈልጋለሁ። የምርመራህ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት በጣም አመርቂ ስለሆነ ሁሉም ነገር ስኬታማ ይሆናል።

ተስፋና ስጋት (4)

ቀዶ

ጥገናው እኩለ ሌሊት ላይ ተጠናቀቀ፤አራት ሰዓት ነበር የፈጀው። ካትሪና በየሰዓቱ ወደ ሆስፒታሉ ስትደውል ነበር የቆየችው። ቀዳጅ ሐኪሙ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ ወጥቶ እስከ ደወለላት ጊዜ ድረስ አልተረጋጋችም ነበር። ነገሮች ሁሉ በተፈለገው መንገድ መከናወናቸውን፣ የቀዶ ጥገናው ውጤት ከአስራ ሁለት ሰዓቶች በኋላ የሚታይ መሆኑንና ከዚህ ጊዜ አካባቢ በፊት እንደማይነቃ ነገራት . .

- የኔ እመቤት አይዞሽ ተረጋጊ። የስልክ ጥሪዎች ወደ ሆስፒታሉ እየጎረፉ ናቸውና ሌሎች የሚደውሉ ሰዎችንም አረጋጊያቸው።

- እነማን ናቸው የሚደውሉት?

- አደም፣ቶም . . የምታውቂያቸው ከሆነ እባክሽ ደውይላቸው።

- እሽ . . እንዲጸልዩለት እነግራቸዋለሁ።

በተከታዩ

ቀን አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ . . ጆርጅ መንቃት ጀምሮ እጁን ባልተለመደ ሁኔታ እያንቀሳቀሰ ግልጽ ያልሆኑ ቅዠት መሰል ቃላትን እያሰማ ነው። መንቃቱን ለመጠበቅ አጠገቡ ተቀምጠው የነበሩት ካትሪና አደምና ቶም በቅዠት ከሚናገራቸው ውስጥ . . የመታደል መንገድ፣ለምን ተፈጠርን . . ሕይወት . . ሞት . . የሚሉትን ከመሳሰሉ ውስን ቃላት በስተቀር የገባቸው ነገር አልነበረም።

ጆርጅ

ያለበትን ሁኔታ ለማየት ሐኪሙ ሲመጣ ካትሪና በመጣደፍ ብድግ ብላ ተቀበለችው . . በፈገግታ ተቀበላት . .

- የኔ እመቤት ጭንቀትሽን እረዳለሁ . . ሁሉም የምርመራ ውጤቶች በጣም አመርቂ መሆናቸውን ላበስራችሁ እፈልጋለሁ፤ከአፍታ በኋላ ይነቃል ብለን እንጠብቃለን።

- ዶክተር . . የማይታወቅ ነገር ሲናገር ነበር!

- አታስቡ! ገና ሙሉ በሙሉ አልነቃም፤ይህ የተለመደ ነገር ነው። የማደንዘዣው ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ ከተወገደና ግልጽ የሆነ ነገር መናገር ከቻለ ለቀዶ ጥገናው ስካታማነት የመጀመሪያው ምልክት ነው። ነገ መሳሪያዎቹን ከርሱ ማላቀቅ እንጀምራለን፤መንቀሳቀስና ተነስቶ መቆም ከቻለ ቀዶ ጥገናው መቶ በመቶ ስኬታማ ሆኗል ማለት ነው . . ሲነቃ በየሦስት ሰዓቱ የሕመም ማስታገሻ እንሰጠዋለን። ከዚያ በኋላ ሙሉ ጤናማ ሆኖ ታገኙታላችሁና አይዟችሁ።

- እናመሰግናለን ዶክተር፣እግዚአብሔር ይጠብቀው።

- በነገራችን ላይ ቀዶ ጥገናው ከመጀመሩ በፊት በማደንዘዣው ወቅት ‹‹የመታደል መንገድ›› የሚል ቃል ይደጋግም ነበር፤ የመታደል መንገድ ምን ይሆን?

- ሁሉንም ነገር ትቶ ለማግኘት በፍለጋው ላይ የተሰመራበት መንገድ ነው።

- እዚህ ሆስፒታል ገብተው ከታከሙት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ደስተኛ ሰው እርሱ ነው፤የመታደልን መንገድ ለምንድነው የሚፈልገው?

- የመታደል መንገድ ፍለጋውን ሲጀምር እንጂ ደስተኛ አልሆነም።

- በሰላም ተፈውሶ ከተነሳ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዱን ያገኘዋል፤ፍቀዱልኝና ልሂድ።

ሐኪሙ

እንደወጣ . . ቶም ከላዩ በተጠመዱ የሕክምና መሳሪያዎች ስር ወደ ተኛው ጆርጅ ፊቱን አዞረ . . በአዘኔታም አጉተመተመ . .

- አንተ ጆርጅ፣በእርግጠኝነት የመታደልን መንገድ ታገኘዋለህ፤እኔም ካንተ ጋር አገኘዋለሁ። የመረገም መንገድ የሆነውን የኤቲዝምን መንገድ ሞክሬያለሁ፤ጭንቀትና ውጥረት ብቻ እንጂ ያተረፍኩት ነገር አልነበረም፤ይሁን እንጂ የፈጠረን ርህሩህ ጌታ እኛን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ሊመራን እንደሚችል እርግጠኛ ብሆንም እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ግን የትኛውንም ሃይማኖት አምኜ አልተቀበልኩም።

- ቶም አንተም እንደምታገኘው እርግጠኛ ነኝ።

- አደም እንዴት ነው የማገኘው?

- አንተ ያልከውን ልድገምና ርህሩሁ አምላክ ወደርሱ ለመቅረብ የፈለገውን አያርቅም፤ስለዚህም እኔም አንተም ጆርጅም ለመፈለግ የምንጥረውን እናገኘዋለን።

- አንተም ጭምር በመታደል መንገድ ፍለጋ ላይ ነህ?

- ምናልባት!!

ጆርጅ ዓይኖቹን በግድ መክፈት ጀመረ . . ካትሪና አወቀችና ወደርሱ ቀረብ አለች . .

- ጆርጅ የኔ ፍቅር ትሰማኛለህ?

- አዎ።

- በሰላም በመንቃትህ ጌታ የተመሰገነ ይሁን። በጣም ተጨንቀንልህ ነበር፤ይኸውና አደምና ቶም አንተን ለማየት መጥተው እዚህ ይገኛሉ።

- አመሰግናለሁ።

- ፈጣን ፈውስ እመኝልሃለሁ።

- እኔም ፈጣን ፈውስ እመኝልሃለሁ። ሐኪሙ ቀዶ ጥገናው ስኬታማ መሆኑን አብስሮናል።

- የኔ ፍቅር የምትፈልገው ነገር ይኖራል?

- የለም።

- ጫና ልንፈጥርበት አይገባም፤በቀስታና በእርጋታ እንዲነቃ አሁን ልንተወው ይገባል።

- ልክ ነው . . ስለዚህም እኔና አደም እንሂድና አንቺ ከአጠገቡ ሁኚ።

- ሁለታችሁንም እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ፤እርሱ ራሱ ዛሬ ደውሎላችሁ ያለበትን ሁኔታ ይነግራችኋል።

- አደም መኪና አለህ ወይስ እንዳደርስህ ትፈልጋለህ?

- መኪና የለኝም፣አንተንም ማስቸገር አልፈልግም፣በሕዝብ ትራንስፖርት እሄዳለሁ።

- ካንተ ጋር ትንሽ ማውራት ስለምፈልግ ግባ አብረን እንሄዳለን . . ካትሪና ደህና ሁኚ።

- ደህና ሁኑ።

ቶምና አደም ከወጡ ከግማሽ ሰዓት ያህል በኋላ . . አጠገቡ ያለችው ካትሪና በሀሰብ ዓለም ጭልት እንዳለች ጆርጅ እንደገና ዓይኖቹን ከፈተ . .

- ካትሪና . .

- ጆርጅ የኔ ፍቅር . . አሁን እንዴት ነህ?

- ደህና ነኝ . . ቶምና አደምን ያየኋቸው መስሎኝ ነበር ልበል?

- ሁኔታህ አስተማማኝ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ከአፍታ በፊት ነው የሄዱት፤ከማለዳ አንስቶ እዚህ ነበሩ . . የኔ ፍቅር አንተ እንዴት ነህ?

- አሁን ስንት ሰዓት ነው? . . ራስ ቅሌ ውስጥ ሕመም እየተሰማኝ ነው።

- ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ ነው፤አትጨነቅ አሁኑኑ ሐኪም አስጠራለሁ።

ነርሷ እንደጠራችው ሐኪሙ ወዲያውኑ ከተፍ አለ . .

- ጆርጅ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነህ።

- ራስ ቅሌ ውስጥ ከባድ ሕመም ይሰማኛል።

- ችግር የለውም፣አሁን ማስታገሻ ትወስድና ይተወሃል፤የራስ ቅል በከፊል ተከፍቶ ስለነበር ይህ የተለመደ ነገር ነው። ነገሮች ሁሉ መልካምና አበረታች ናቸው።

- ትንሽ ከበድ ቢለውም በግልጽ መናገርም ጀምሯል።

- ይህ የቀዶ ጥገናው ስኬታማ መሆን ምልክት ነውና ሀሳብ አይግባሽ፤ጆርጅ አንተም ሀሳብ አይግባህ።

- አመሰግናለሁ።

ሐኪሙ የሕመም ማስታገሻ መርፌ ወጋው . . ወደ ካትሪና ዞሮ ጆርጅ ከመርፌው በኋላ በትንሹ ለሁለት ሰዓት የሚተኛ በመሆኑ ወደ ቤት እንድትሄድ መከራት . .

- እዚሁ ሆኜ እጠብቀዋለሁ።

- ከነቃ በኋላም ሁለት ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ የሚቆይ ሌላ መርፌ ይሰጠዋል፤ለማንኛውም ውሳኔው የራስሽ ነው።

- የኔ ፍቅር ሂጂ።

- ቀኑ ሙሉ ስላንተ ስጸልይ እውላለሁ።

ጧት አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ጆርጅ ነቅቶ ከነርሷ ጋር በጥሩ ሁኔታና በግልጽ ለመነጋገር ቻለ። ይሁን እንጂ ገና ምግብ አልተፈቀደለትም አሁንም የሚመገበው በግሉኮስ ነው . .
ለካትሪና ደውሎ በመነጋገር አጽናናት። ለአደምና ለቶምም እንዲደውል ጠየቀችውና ደወለላቸው፤ ከዚያም ለሌቪ ደወለ . . በመቀጠል ስለ መታደል መንገድ ፍለጋውና ስለ ሮም ጉዞው ማሰላሰሉን ቀጠለ . .