ነቢዮች ከሰው ልጆች ምርጦችና ፈርጦች ናቸው

ነቢዮች ከሰው ልጆች ምርጦችና ፈርጦች ናቸው

‹‹የአላህን ነቢያትና መልክተኞቹን በተመለከተ ከተላለፉት የተዛቡና ተአማኒነት ከጎደላቸው ዘገባዎች መካከል መስከራቸውን፣ወይም ዝሙት ላይ መውደቃቸውን፣ወይም ሰዎች እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠታቸውን . . የሚያወሩ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ በአላህ ለተመረጡ ምርጦችና የሰው ልጆች ፈርጦች ከሆኑ የአላህ ነቢያት ቀርቶ በመልካም ስነምግባር ለታነጸ ተራ ሰው እንኳ የማይገባ መሰረት የለሽ ተረት ነው። ከመሰል ተረቶች መካከል ነቢዩ ዳውድን  አስመልክቶ (ሳሙኤል ካልዕ 11፣2-26)፤ስለ ኢያሱ ወልደ ነወዌ  የቀረበው (ኢያሱ 6፣24)፤ነቢዩ ሙሳን  አስመልክቶ የሰፈረው (ዘኁልቁ 31፣14-18) እና ሌሎቹም መሰል ጥቅሶች ለአላህ ክቡራን ነቢያት ፈጽሞ የማይገቡ ናቸው።››


Tags: