ምርጥ ሥርዓት

ምርጥ ሥርዓት
‹‹ዘመናት ማቅረብ የቻሉት የተሻለ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓት በመሆኑ እስላም ድል ማድረግ ችሏል። በደረሰበት ቦታ ሁሉ በፖለቲካ ኋላ ቀር የሆኑ፣ግፍና ምዝበራ የሚፈጸምባቸው፣በፍርሃትና በስጋት ውስጥ የሚኖሩ፣ዕውቀትም ሆነ ሥርዓት የሌላቸው ሕዝቦች ያጋጥሙት ስለነበረ እስላም መሰራጨት ችሏል። በተመሳሳይ መልኩም ከሕዝባቸው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ጤናማ ያልሆኑ ራስ ወዳድ መንግሥታትን ያገኝ ስለነበረም እስከዚያን ጊዜ ድረስ በዓለም ላይ የተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገጽታ የነበረው፣ከሁሉም ይበልጥ ስፋት ያለው፣ይበልጥ ዘመናዊና ይበልጥ ጽዱ የሆነ ፖለቲካዊ እሳቤ ነበር። ከማናቸውም ሌላ ሥርዓት የተሻለ ሥርዓትም ለሰው ልጆች ያቀርብ ነበር። በሮማውያን ግዛተ አፄ የነበረው የባርያ አሳዳሪ ካፒታሊስታዊ ሥርዓት፣በአውሮፓ የነበረው ስነ ጽሑፍ፣ስልጣኔ፣ማሕበራዊ ወግና ልማድም፣እስላም ከመመስረቱ ቀደም ብሎ ከስመውና ሙሉ በሙሉ ወድመው ነበር።››


Tags: