ሄርበርት ጆርጅ ዌልዝ

quotes:
  • ከመሰናበቻው ሐጅ ትምሕርቶች
  • ‹‹ሙሐመድ የመሰናበቻውን ሐጅ ከመዲና ወደ መካ ያደረገው ከመሞቱ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ነበር። በዚህ የሐጅ ሥርዓት ላይ ለሕዝቦቹ ታላቅ መካሪ ዲስኩር ያደረገ ሲሆን የንግግሩ የመጀመሪያ አንቀጽ ብቻውን በሙስሊሞች መካከል ያለውን ዝርፊያና ንጥቅያ፣የበቀልና የደም ጉዳዮችን ሁሉ ነቅሎ የመጣል አቅም ነበረው። የዲስኩሩ የማጠቃለያ አንቀጽ ደግሞ ጥቁሩን ሰው ከሙስሊሞች መሪ ኸሊፋ ጋር ፍጹም እኩል የማድረግ ኃይል ነበረው። በእውነትም በዓለም ላይ ፍትሐዊ ለሆነ በይነሰባዊ ግንኙነት ታላቅ መሰረትን ጥሏል።››


  • ጎሐ እስላም
  • ‹‹ታሪክ በጥቅሉ ወደርሱ ያነጣጠረ የሚመስለው ታላቁ የእስላም አዲስ ጎሕ ከመቅደዱ በፊት ስንት ትውልዶች በፍርሃትና በዕድለ ቢስነት ይጠቁ ይሆን! በዚያን ቀን ሰላም ምድሪቱን ያጥለቀልቃል። በዚያም ቀን ሰላም ልቦችን ያጥለቀልቃል።››


  • ምርጥ ሥርዓት
  • ‹‹ዘመናት ማቅረብ የቻሉት የተሻለ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓት በመሆኑ እስላም ድል ማድረግ ችሏል። በደረሰበት ቦታ ሁሉ በፖለቲካ ኋላ ቀር የሆኑ፣ግፍና ምዝበራ የሚፈጸምባቸው፣በፍርሃትና በስጋት ውስጥ የሚኖሩ፣ዕውቀትም ሆነ ሥርዓት የሌላቸው ሕዝቦች ያጋጥሙት ስለነበረ እስላም መሰራጨት ችሏል። በተመሳሳይ መልኩም ከሕዝባቸው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ጤናማ ያልሆኑ ራስ ወዳድ መንግሥታትን ያገኝ ስለነበረም እስከዚያን ጊዜ ድረስ በዓለም ላይ የተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገጽታ የነበረው፣ከሁሉም ይበልጥ ስፋት ያለው፣ይበልጥ ዘመናዊና ይበልጥ ጽዱ የሆነ ፖለቲካዊ እሳቤ ነበር። ከማናቸውም ሌላ ሥርዓት የተሻለ ሥርዓትም ለሰው ልጆች ያቀርብ ነበር። በሮማውያን ግዛተ አፄ የነበረው የባርያ አሳዳሪ ካፒታሊስታዊ ሥርዓት፣በአውሮፓ የነበረው ስነ ጽሑፍ፣ስልጣኔ፣ማሕበራዊ ወግና ልማድም፣እስላም ከመመስረቱ ቀደም ብሎ ከስመውና ሙሉ በሙሉ ወድመው ነበር።››




Tags: