የዕውቀት ጥማትና የስልጣኔ ፍቅር

የዕውቀት ጥማትና የስልጣኔ ፍቅር

‹‹በስልጣኔ ታሪክ ውስጥ በመላው የሙስሊም ዓለም ከተከሰተው ድንገተኛ የዕውቀት ጥማትና የስልጣኔ ፍቅር ይበልጥ ውብና ድንቅ የሆነ ንቅናቄ ታይቶ አያውቅም። ከመሪው ኸሊፋ ጀምሮ እስከ ተራው ለፍቶ አዳሪ ድረስ እያንዳንዱን ሙስሊም የዕውቀት ጥማትና ተጉዞ የመማር ጉጉት በድንገት የተጠናወተው ይመስል ነበር። ይህም እስላም በሁሉም አቅጣጫ ካቀረበው ምርጡ ነገር ነበር። እንደ በግዳድ ወዳሉትና ከዚያም በኋላ የስነ ጽሑፍና የተለያዩ የዕውቀት ዘርፎች ማዕከሎች ወደነበሩት የትምሕርት ተቋማት የሚጎርፉት ተማሪዎች፣ዘመናዊውን ሳይንስ ለማጥናት በአውሮፓውያን ሊቃውንት ይጥለቀለቁ እንደነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ይበልጥ ድንቅና አስደማሚ ነበር።››


Tags: