የከበሬታ ሃይማኖት

የከበሬታ-ሃይማኖት

‹‹እስላም የሰላም፣የእኩልነት፣የነጻነት፣የወንድማማችነት፣የክብርና የልዕልና ሃይማኖት ነው። ይህ ሁሉ በሕግጋቱ፣በመርሆዎቹና በስነምግባሮቹ ውስጥ በግልጽ ይታያል። እስላም ውስጥ ያለው ጾም በሌሎች ሃይማኖቶች ውስጥ ካለው ጾም የተለየ ነው። የሰው ልጆች ችግር መነኩሳት እንደሚያደርጉትና አንዳቸው ተንቀሳቃሽ የአጥንት መዋቅር እስከሚመስል ድረስ የአካል ፍላጎትን ማፈን አይደለም። በመሆኑም እስላም ሥጋዊ ፍላጎቶችን በመግራት ይቆጣጠራቸዋል እንጂ አያፍናቸውም። በእስላም ዘንድ ያለው የጾም ዓለማም የተከለከሉና ሐራም የሆኑ ሥጋዊ ፍላጎቶችን መርታት ትችል ዘንድ ነፍሲያን መታገል፣ቁጡብ መሆንንና በመታገስ ራስን መግዛት መለማመድና ራስን ማሰልጠን ነው። በግልጽና በስውርም አላህ እንደሚያን አውቀን መጠንቀቅ፣ላጡትና ለተራቡት እናዝን ዘንድ የማጣትና የመራብን ስሜት መረዳት መቻል ነው። በተጨማሪም ጾም ሰውነት ከምግብ አለመፈጨት ችግር ዕረፍት እንዲያገኝ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ነው። ጾም ለግለሰብ ጤንነት ለመንፈሱና ለአእምሮው ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ለሕብረተሰብ ደግሞ ለመቀራረብ፣ለተራድኦና ለአንድነት ፋይዳው የጎላ ነው።››


Tags: