ጃክ ሪሳር

quotes:
  • ቁርኣንና ሐዲስ መሳ ለመሳ
  • ‹‹የነቢዩ ሙሐመድን ሥራዎችና መመሪያዎች የሚመለከቱ ንግግሮች ስብስብ ተደርጎ የሚቆጠረው ሐዲስ የቁርኣን መሙያ (ማብራሪያ) ነው። አንድ ሰው ሐዲስ ውስጥ ከሕይወት ተለዋዋጭ እውነታዎች አንጻር የስነምግባሩ መሰረታዊ አካል የሆነውንና በነቢዩ ሙሐመድ አእምሮ ውስጥ ይመላለስ የነበረውን ነገር ያገኛል። ሱንና የቁርኣን ማብራሪያ በመሆኑ አስፈላጊነቱ የግድ ነው።››


  • የነቢያዊው ሱንና አሰባሰብ
  • ‹‹በስብስባቸው ሱንናን የሚመሰርቱት እነዚህ ሐዲሶች በአመራረጣቸው ላይ ጥብቅ የሆነ ከፍተኛ ፍተሸ ከማድረግ ጋር በነቢዩ ባልደረቦች ተዘግበው ወይም ከነሱ ተላልፈው የተጠናቀሩ ናቸው።››


  • የጥቃቅን ዝርዝር ጉዳዮች መሰረቶች
  • ‹‹ቁርኣን ለሁሉም ጉዳዮች መፍትሔዎችን ያቀርባል። ሃይማኖታዊውን ሕግ ከሞራላዊው ሕግ ጋር ያስተሳስራል። ማሕበራዊ ሥርዓትና አንድነትን ለመፍጠር፣ተስፋ የለሽነትን ጭካኔንና አፈተረትን ለማቃለል ጥረት ያደርጋል። የጎስቋሎችን እጅ ለመያዝ ጥረት በማድረግ ደግነትን ይመክራል፤በመተዛዘንና በርህራሄ ያዛል። በሕግ አወጣጥ ረገድ ለዕለታዊ ተራድኦ ለጥቃቅን ዝርዝር ጉዳዮች መሰረቶችን ያኖራል። ለውሎችና ለውርስ ጉዳዮች ሥርዓት አብጅቶላቸዋል። በቤተሰብ መስክ እያንዳንዱ ግለሰብ በሕጻናት፣በአገልጋዮችና በእንስሳት አያያዝ፣በጤናና በአባበስ ጉዳዮች ላይ መከተል ያለበት ወስኖ አስቀምጧል . . ወዘተ. ››
Tags: