እስታንሊ ሊይን ፓውል

quotes:
  • መስጊድ . . ዩኒቨርሲቲ ነው
  • ‹‹መስጊዶች የእስላም ዩኒቨርሲቲዎች ነበሩ - አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ ናቸው። ዕውቀትን በተጠሙ ተማሪዎች የተጨናነቁ ነበሩ። እነዚህ ተማሪዎች፣ሊቃውንት በሃይማኖት፣በሕግ፣በፍልስፍና፣በሕክምና እና በሒሳብ ሳይንሶች ላይ የሚሰጡትን ሌክቸሮች ለማዳመጥ ይመጡ ነበር። ሊቃውንቶቹ ራሳቸው ዐረብኛ ይናገሩ ከነበሩ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ነበሩ። ተማሪው ዜግነቱ የፈለገውን ቢሆን ሙሉ አቀባበል ይደረግለት ነበር።››


  • የዕውቀት ጥማትና የስልጣኔ ፍቅር
  • ‹‹በስልጣኔ ታሪክ ውስጥ በመላው የሙስሊም ዓለም ከተከሰተው ድንገተኛ የዕውቀት ጥማትና የስልጣኔ ፍቅር ይበልጥ ውብና ድንቅ የሆነ ንቅናቄ ታይቶ አያውቅም። ከመሪው ኸሊፋ ጀምሮ እስከ ተራው ለፍቶ አዳሪ ድረስ እያንዳንዱን ሙስሊም የዕውቀት ጥማትና ተጉዞ የመማር ጉጉት በድንገት የተጠናወተው ይመስል ነበር። ይህም እስላም በሁሉም አቅጣጫ ካቀረበው ምርጡ ነገር ነበር። እንደ በግዳድ ወዳሉትና ከዚያም በኋላ የስነ ጽሑፍና የተለያዩ የዕውቀት ዘርፎች ማዕከሎች ወደነበሩት የትምሕርት ተቋማት የሚጎርፉት ተማሪዎች፣ዘመናዊውን ሳይንስ ለማጥናት በአውሮፓውያን ሊቃውንት ይጥለቀለቁ እንደነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ይበልጥ ድንቅና አስደማሚ ነበር።››
Tags: