አላህ ተጋሪ የለውም

አላህ ተጋሪ የለውም
‹‹ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፣እርሱ አንድና ምንም ተጋሪ የሌለው ነው። እርሱ እውነት ነው፣ከርሱ ውጭ ያለው ሁሉ ሐሰት ነው። ፈጥሮናል ይመግበናልም። እስላም ነገሮችን ሁሉ ለአላህ ሰጥተን መስለም ማለት ነው። ወደርሱ መጠጊያ መያዝ ነው። በርሱ ላይ መተማመን ነው። ሁሉም ኃይል ያለው ለርሱ ጥበብ ቀጥ ብሎ በመግገዛት ውስጥ ነው። ድርሻችን የፈለገውንም ቢሆን አላህ የሰጠን ዕጣ ፈንታችን - አስበርጋጊውን ደራሽ ሞት ቢሆን እንኳ - ወደን በቀና ስሜት መቀበል ነው። መልካሙ እርሱ የመረጠው መሆኑንና ሌላው መልካም አለመሆኑን ማወቅ ነው። የሰው ልጅ ኢምንት አንጎሉን የዓለማትና የሁኔታዎቻቸው መመዘኛ አድርጎ መውሰዱ የከፋ ጅልነት ነው።ማድረግ ያለበት ከርሱ ግንዛቤ በላይ ቢሆንም ይህ ዩኒቨርስ ፍትሐዊ የሆነ ሕግ እንዳለው ማወቅ፣በጎ ነገር የዩኒቨርሱ መሰረት መሆኑን፣ሰናይነት የዩኒቨርሱ መንፈስ መሆኑን መረዳት ነው . . ይህን ሁሉ አውቆ አምኖበት በእርጋታና በጽድቅ ስሜት በዚህ መጓዝ ይኖርበታል።››


Tags: