ቶማስ ካር ላይል

quotes:
  • ነቢያዊ ስነምግባር
  • ‹‹ተፈጥሮው ከታይታና ከማስመሰል የጸዳ በመሆኑ ሙሐመድን ከልብ እወደዋለሁ። ይህ የምድረበዳ ተወላጅ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው ነበር። በራሱ ላይ እንጂ በማንም ትከሻ አይንጠለጠልም፤ያልሆነውንና የሌለበትን ነገርም ፈጽሞ አይናገርም። ኩራተኛም አልነበረም፤ግን ደግሞ ተዋራጅም አልነበረም። አላህ እንደ ፈጠረውና እንደሻለት በተጣፈ ልብስ ይሄድ ነበር። ግልጽ በሆነው ነጻ ቃሉ የሮምን ቄሳሮችና ዐረብ ያልሆኑ ነገስታትን ለዚህች ዓለምና ለወዲያኛው ዓለም ሕይወት ማድረግ ስላለባቸው ነገር ያሳውቃቸው ነበር። የራሱን ልክና ደረጃም ያውቅ ነበር። የዛሬን ሥራ ለነገ የማያቆይ ጽናትና ቁርጠኛነትን የተላበሰ ሰውም ነበር።››


  • አላህ ተጋሪ የለውም
  • ‹‹ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፣እርሱ አንድና ምንም ተጋሪ የሌለው ነው። እርሱ እውነት ነው፣ከርሱ ውጭ ያለው ሁሉ ሐሰት ነው። ፈጥሮናል ይመግበናልም። እስላም ነገሮችን ሁሉ ለአላህ ሰጥተን መስለም ማለት ነው። ወደርሱ መጠጊያ መያዝ ነው። በርሱ ላይ መተማመን ነው። ሁሉም ኃይል ያለው ለርሱ ጥበብ ቀጥ ብሎ በመግገዛት ውስጥ ነው። ድርሻችን የፈለገውንም ቢሆን አላህ የሰጠን ዕጣ ፈንታችን - አስበርጋጊውን ደራሽ ሞት ቢሆን እንኳ - ወደን በቀና ስሜት መቀበል ነው። መልካሙ እርሱ የመረጠው መሆኑንና ሌላው መልካም አለመሆኑን ማወቅ ነው። የሰው ልጅ ኢምንት አንጎሉን የዓለማትና የሁኔታዎቻቸው መመዘኛ አድርጎ መውሰዱ የከፋ ጅልነት ነው።ማድረግ ያለበት ከርሱ ግንዛቤ በላይ ቢሆንም ይህ ዩኒቨርስ ፍትሐዊ የሆነ ሕግ እንዳለው ማወቅ፣በጎ ነገር የዩኒቨርሱ መሰረት መሆኑን፣ሰናይነት የዩኒቨርሱ መንፈስ መሆኑን መረዳት ነው . . ይህን ሁሉ አውቆ አምኖበት በእርጋታና በጽድቅ ስሜት በዚህ መጓዝ ይኖርበታል።››


  • ፈጠራ ወሬና ማጠልሸት
  • ‹‹ጭፍንና ጠባብ ወገንተኞች፣ሙሐመድ ከግለሰባዊ እውቅና ፍለጋ፣ከዝና እና ከሥልጣን ውጭ ሌላ ፍላጎት አልነበረውም ይላሉ። ፈጽሞ አይደለም፤በእግዚአብሔር ይሁንብኝ በዚያ የታላቅ ሰብእና ባለቤት በሆነው፣በእዝነት፣በሰናይነት፣በአዘኔታ፣በደግነትና በጥበብ በተሞላው በዚያ የምድረበዳ በረሃ ታላቅ ሰው ልብ ውስጥ ከዓለማዊ ሕይወት ስግብግብ ፍላጎት ውጭ የሆኑ ሀሳቦች፣ከሥልጣንና ዝና ፍለጋ የራቁ ቅን ፍላጎትና ዓላማዎች ነበሩ። እንዴታ! ያ የጠራች ነፍስ ባለቤት የሆነ ከነዚያ ቅኖች፣ፍጹሞችና የምሮች ከመሆን ውጭ ሌላ ምንም መሆን ከማይችሉ ሰዎች አንዱ ነውና!››




Tags: