ነቢያዊ ስነምግባር

ነቢያዊ ስነምግባር
‹‹ተፈጥሮው ከታይታና ከማስመሰል የጸዳ በመሆኑ ሙሐመድን ከልብ እወደዋለሁ። ይህ የምድረበዳ ተወላጅ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው ነበር። በራሱ ላይ እንጂ በማንም ትከሻ አይንጠለጠልም፤ያልሆነውንና የሌለበትን ነገርም ፈጽሞ አይናገርም። ኩራተኛም አልነበረም፤ግን ደግሞ ተዋራጅም አልነበረም። አላህ እንደ ፈጠረውና እንደሻለት በተጣፈ ልብስ ይሄድ ነበር። ግልጽ በሆነው ነጻ ቃሉ የሮምን ቄሳሮችና ዐረብ ያልሆኑ ነገስታትን ለዚህች ዓለምና ለወዲያኛው ዓለም ሕይወት ማድረግ ስላለባቸው ነገር ያሳውቃቸው ነበር። የራሱን ልክና ደረጃም ያውቅ ነበር። የዛሬን ሥራ ለነገ የማያቆይ ጽናትና ቁርጠኛነትን የተላበሰ ሰውም ነበር።››


Tags: