በሕይወትና በሞት መካከል . .

በሕይወትና በሞት መካከል . .

በሕይወትና በሞት መካከል . . (1)

ጆርጅ ልቡ በሌቪ ሀሳብ እንተወጠረ ወደ አይሮፕላኑ ገባ። ቆይታው ከአራት ቀናት ያላለፈ ቢሆንም ልቡን መቆጣጠር ችላለች . . ለመሆኑ ምስጢሩ ምን ይሆን?! ጨካኝና ግፈኛ በሆነ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚኖር የተቀደሰ ንጹሕ መልአክ ሆና ነበር ለርሱ የታየችው። ሴቶችንና አይሁዳዊነት ውስጥ የሚፈጸምባቸውን አስከፊ ጭቆና አስመልክቶ ከሌቪ ጋር ያደረገውን ውይይት በምሬት አስታወሰ። ሴት ልጅ እንደ እቃ እንዲትወረስ የሚያደርግ ሃይማኖት ምን የሚሉት ነው
! የሕብረተሰቡን ግማሽ አካል እንደ ቆሻሻ፣እንደ ውሻና እንደ እርኩስ ነገር የሚመለከት፣የመውረስ መብት የሚነፍጋትና መብት አልባ ፍጡር የሚያደርጋት ሃይማኖት
! . . ስለ ብሉይ ኪዳን መዛባትና ተአማኒነት ማጣት ያደረጉት ውይይት፣ለአባቷ ገዳይ ሙስሊሞች ያላት የከረረ ጥላቻ፣‹‹የሴሎን ልጆች›› ስለሚገድለው፣ስለሚዘርፈውና ስለሚሰርቃቸው ምርጡ ኤሁዳዊ ሕዝብ ያነሱት ሁሉ ትዝ አለው። በአካባቢው ላይ ለአይሁዶች ባለመብትነት ማስረጃ ይሆናሉ የተባሉትንና ግን የሌሉ ቅርሶችን በሚመለከት የተለዋወጡት ሀሳብ . . ታወሰው። ሌቪ ከአይሁዳዊ ውስብስብነት ወደ ካቶሊካዊ ውስብስብነት እንደማትሸጋገር የተናገረችው ትዝ ብሎት ፈገግ አለ። ከትውስታው ዓለም ባኖ የተመለሰው ከጎኑ የተቀመጠው ተሳፋሪ ሲያቋርጠው ነበር፦

- ወዳጄ በእጅህ የያዝከው መርፌ ምንድነው?

- ድንገተኛ ትኩሳት ሊያጋጥመኝ ስለሚችል አይሮፕላን ውስጥ በእጄ እንድይዘው በጥብቅ አሳስቦኝ ሐኪም ነው የሰጠኝ ነው።

- እንዳየው ትፈቅድልኛለህ?

- እንካ፣ሐኪም ነህ?

መርፈውን ተቀብሎ አየው፣አብሮት ያለውን የአጠቃቀም መምሪያ ወረቀት አነበበ።

- እኔ ፋርማሲስት ነኝ፣ይህ መርፌ ላንት እጅግ አስፈላጊ ሳይሆን አይቀርም፣አልፎ አልፎ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውል መድኃኒት ነው።

- ሐኪሙ አልነገረኝም፣ለምን ሕመም ነው የሚየገለግለው?

- አላውቀውም፣ይህ መርፌ ግን መጥፋት የማይችሉ ቫይረሶችን ለማስታገስ እጅግ በጣም አጣዳፊ ለሆኑ ድንገተኛ ሁኔታዎች ነው የሚታዘዘው።

- ወዳጆቼ ለኔ በመጨነቅ ያደረጉት እንጂ እኔ እንኳ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነኝ።

- ሊሆን ችላል፣ግን አይመስለኝም፣ይህ መርፌ በልዩ የሐኪም ትእዛዝና በድንገተኛ ሁኔታዎች ብቻ እንጂ የማታዘዝና የማይሸጥ ነው።

- ሊሆን ይችላል፣አላውቅም፤እኔ ግን በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ነኝ።

- በእርግጥ ጤንነት ከታመሙ ሰዎች በስተቀር ሌሎች የማያዩትና ጤነኞች ብቻ በራሳቸው ላይ የደፉት ዘውድ ነው። ረብሸህ እንደሆን ይቅርታ።

- ፈጽሞ . . አመሰግናለሁ።

ጆርጅ ዳግም ለትውስታዎቹ እጁን ሰጠ . . ልቡ አሁንም ለሌቪ እየተጨነቀ ነው። ዐረብ ቢሆንም አብሮት በመሆን ብዙ ያስደሰተውንና የተመቸውን ሐቢብን በአድናቆት ሲያስታውስ ደስ አለው። ሙስሊሞችን አስመልክቶ ከርሱ ጋር ባደረገው ውይይት ለሐቢብ ‹‹አንተ የካቶሊክ ጭንብል ያጠለቅህ ሙስሊም ነህ›› ማለቱን አስታወሰ . . ይህ ጉዞ ለርሱ በሁነቶች የተሞላ እጅግ በጣም አስደሳች ጉዞ ነበር . . አስተናጋጇ አቋረጠችው፦

- ይቅርታ፣ምን መመገብ ይመርጣሉ? ሥጋ ወይስ ዶሮ?

- ሥጋ።

አጠገቡ ያለው መንረገደኛ ወደሱ ዞረና፦

- አእምሮህ ሙሉ በሙሉ በሀሳብ የተወጠረ ትመስላለህ !

- ኦህ . . አዎ፣ያሁኑ ጉዞዬ ግሩም ድንቅና በመረጃዎች የበለጸገ ነበር።

- ኢየሩሳሌም ምን ያህል ቆየህ?

- ለአራት ቀናት።

- ብቻ !

- አዎ፣ግን ብዙ ወራት የቆየሁ ያህል ነው። ያገኘኋቸውን ድንቅ ሰዎች መቼም ቢሆን አልረሳቸውም።በዚች ቅድስት አገር ውስጥ ከነሱ ብዙ ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁ።

- አይሁዳዊ ነህ?

- አይደለሁም . . ለምን?

- እኔ አይሁዳዊ ነኝ . . ይቅርታ አድርግልኝና አገሩ ለነሱ የተዘጋጀ በመሆኑ በተለምዶ ኢሩሳሌም ውስጥ እርካታ የሚያገኙት አይሁዶች ብቻ ናቸው። ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ግን ያሉበት ሁኔታ የሚያስደስት አይደለም።ስላገኘሃቸው ሰዎች ደስታህንና አድናቆትህን ስትገልጽ አይሁዳዊ መሰልከኝ? !

- ኢየሩሳሌም ውስጥ ኤሁዶችንና ክርስቲያኖችንም አግኝቻለሁ፣ሁሉም ድንቅ ሰዎች ናቸው።

- ምናልባት ይህ አባባል እንግሊዝ አገር ቢነገር አግባብነት ይኖረዋል፣ቴልአቪቭ ውስጥ ግን የሰዎች አንቀሳቃሽ ሞተር ሃይማኖት ነው።

- አንተ አይሁዳዊ ነህና አንድ ጥያቄ እንዳቀርብልህ ትፈቅድልኛለህ?

- ጠይቅ።

- የኦሪት ትምህርቶች ላንተ አሳማኝ ናቸው?

- አይደሉም፣ኦሪትን መረዳት የሚቻለው በቴልሙድ ትምህርቶች አማካይነት ብቻ ነው።

- መልካም፣የቴልሙድ ትምህርቶችስ ላንተ አሳማኝ ናቸው?

- እህህ፣አሁንም አይደሉም፣ግና በዚህ መልካቸው ነው ወደኛ የደረሱት።

- ይቅርታ፣በውስጥህ ያለው ይህ ግጭት አያስጨንቅህም?

- ማንንም ቢሆን ያስጨንቃል፤ዳሩ ግን ሰዎች በሚያስጨንቃቸው ነገር ላይ የሚኖራቸው አያያዝ ይለያያል።

- እንዴት?

- እኔ ከዚህ ውስጣዊ ግጭት የምሸሸው ራሴን በሥራዬ በመጥመድ ነው። ከዚህ ግጭት በመጠጥ ወይም በወሲብ ውስጥ ራሳቸውን የሚደብቁ ሰዎችም ይኖራሉ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ የሚሸሹና ይበልጥ ሃይማኖተኛ በመሆን የሚሸሹ ሰዎችም ይገኛሉ።

- በጣም ጥሩ፣ከራስህ ጋር በጣም ግልጽ ሰው ትመስላለህ።

- አመሰግናለሁ።

- ይሁንና ‹‹ሽሽት መታደልን ያስገኛል? ወይስ አያስገኝም?›› የሚለው ጥያቄ ይቀራል።

- ያለ ሃይማኖት የሚኖር ሰው የስነ ልቦና ሕመምተኛ ነው በሚለው ላይ ሁሉም አስተዋዮች የሚስማሙ ይመስለኛል። በመሆኑም ሽሽቱ ከኤቲዝም በሽታና ከጽልመቱ፣ በሃይማኖት ውስጥ ካለው ተቃርኖም ለመራቅ የሚደረግ ሽሽት ነው።

- በነዚህ ጉዳዮች ላይ በሚደረግ ሳይንሳዊ ትናት ውስጥ ከሚደበቀው ሰው በስተቀር፣በዚህ እንስማማለን?

- አዎ፤ግና ለሀሳብ፣ለጭንቀትና ለአእምሮ መዋዠቅ የሚዳርግ በመሆኑ አልወደውም።

- ከሽሽት በስተቀር ሌላ መፍትሔ የለም የምትል ትመስላለህ።

- አዎ፣አይደለምም።

- እህእህ፣እንዴት?

- አዎ የምለው ከሽሽት በስተቀር ሌላ መፍትሔ ስለማላውቅ ነው። አይደለም የምለው ደግሞ ፈጣሪ አምላክ እንዲሁ ለብኩንነት፣ለውስጣዊ ግጭትና ለሽሽት አሳልፎ ሰጥቶ ሊተወን የማይችል በመሆኑ ነው።

- ፋርማሲስት ሳትሆን ፈላስፋ ትመስላለህ።

- ድካሜ ሁሉ እውነታን ለመፈለግ የማደርገው ምርምር ነው። ሳይንሳዊው ስልት ከምናገረው ጋር ይቃረናል፤ከፋርማሲ የተማርኩት በሳይንሳዊ መንገድ እንጂ እንዳልናገር ነው።

- ለእውነታ የሚደረገው ፍለጋ ወይም እኔ በምወደው ስያሜ ‹‹የመታደል መንገድ›› ተድላና ደስታን ያጎናጽፋል እንጂ ለእርግማን አይዳርግም።

- ‹‹የመታደል መንገድ›› ጥሩ አገላለጽ ነው።

- ይቅርታ ላቋርጥህና አይሮፕላኑ እየበረደ ነው? ኃይለኛ ብርድ እየተሰማኝ ነው።

ፋርማሲስቱ ትኩሳቱን ለማየት እጁን ጆርጅ ግንባር ላይ አደረገ፣ሙቀቱ ከፍ ብሏል . .

- የያዝከው መርፌ የተሰጠህ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፣አሁን እንዴት ነህ?

- ቅዝቃዜው እየጨመረ ነው፣ድካም ይሰማኛል፤አታስብ ከአፍታ በኋላ ይሻለኛል። የመታደል መንገድ ትኩረትህን ስቧል?

- ስለ መታደል መንገድ ተውና መርፌውንና የሕክምና መግለጫ ወረቀትህን ልትሰጠኝ ትችላለህ?

- ይኸው እንካ።

ፋርማሲስቱ አይሮፕላኑ ላይ ሐኪም ይኖር እንደሆነ አስተናጋጇን ጠየቃት፣አለመኖሩን ነግራ መኖር ነበረበት በመዘግየቱ አልደረሰም፣አለችው . .

- ግዴለም፣መርፌውን እኔው ራሴ እሰጠዋለሁ፤ፋርማሲስት ከመሆኔም ጋር የከፍተኛ ደረጃ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና ወስጄያለሁ። ይሁንና ራሱን ይስታል፣የሚነቃውም ከደረስን በኋላ ስለሚሆን የአንቡላንስ መኪና አይሮፕላን ጣቢያ እንዲጠብቀን አድርጉ።

- ነገሩ አሳሳቢ ይመስላል፣ባለቤቴ በአንቡላንስ መኪና እየጠበቀችኝ ስለሆነ መኪናው አስፈላጊ አይደለም፣አንተም ትንሽ ያጋነንክ መሰለኝ።

- አላጋነንኩም፣ግና በነገሮች አያያዝ ላይ ሳይንሳዊ ስልቶችን ረግጬ ማለፍ አልሻም።

በሕይወትና በሞት መካከል . . (2)

ጆርጅ ራሱን ከሳተበት ተመልሶ ሲነቃ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ራሱን አገኘ። ካትሪናንም ፈገግ ብላ አጠገቡ አያት . .

- የኔ ፍቅር በሰላም በመምጣትህ ጌታ የተመሰገነ ይሁን።

- አሁን የት ነኝ? ፋርማሲስቱስ የት ነው?

- አንተ ለንደን ሆስፒታል ውስጥ ነህ፣ፋርማሲስቱ ደግሞ ማን ይሆን? !

- - ሆስፒታል ውስጥ ነኝ? ! አይሮፕላኑ ውስጥ ከጎኔ የነበረው መንገደኛ የትነው ያለው?

- ኦ ገባኝ፣በአንቡላንስ መኪና ውስጥ አንተን አስረክቦኝ ያለህበትን ሁኔታ ካረጋገጠ በኋላ አድራሻህን ወስዶ ነው የሄደው። ደህና በመሆንህ ጌታ የተመሰገነ ይሁን።

- ኣህ . . የኔ ፍቅር አንቺ እንዴት ነሽ? በጣም ነው የናፈቅሽኝ፣ስለ አለፋሁሽና ስለ ረበሽኩሽ ይቅርታ አድርጊልኝ። ነገሮች ወደዚህ ደረጃ ይደርሳሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር።

- ሐኪሙ የቀድሞ የሕክምና ወረቀቶችህን አንብቦ የደም ናሙና ወስዷል። ኤክስሬይም አስነስተው የምርመራ ውጤቱን ነገ እናየዋለን ብለዋል።

- መቼ ነው ወደ ቤት የምንሄደው?

- አላወኩም፣የምርመራ ውጤቱ ከታየ በኋላ መሆን ያለበትን እንወስናለን ነው ያለኝ። ለማንኛውም እምደሚገምቱት ከአንድ ሳምንት ላላነሰ ጊዜ እዚህ ትቆያለህ።

- ሳምንት? !

- ዋናው ነገር ቆይታህ ሳምንት መሆኑ ሳይሆን፣ጤንነትህ አስተማማኝ መሆኑንና እዚያ ሆፒታል እንድትቆይ ባለመደረጉ መገረማቸውን መናገራቸው ነው።

- ሆስፒታሉ እንኳ እንዳልወታጣ ለማድረግ ጠይቆኝ ብዙ ሞክሯል፣እኔ ነኝ አሻፈረኝ ያልኳቸው . . ሌላ ምን አለ?

- የሥራ ፈቃድ ወስጄ ካንተ ጋር እሆናልሁ፤ካንተ ጋር መቀመጥ ስለናፈቀኝ አብረን ለመሆን ይህ መልካም አጋጣሚ ሳይሆን አይቀርም።

- እኔም በጣም ናፍቄሻለሁ። የምፈልገው ግን ካንቺ ጋር ወደ ቤት መሄድ ነው።

- የኔ ፍቅር አትጨነቅ በቅርቡ ትወጣለህ . . የትንሣኤ ቤተክርስቲያንን ጎብኝተሃል?

- አዎ . . ለመጎብኘት ቃል ገብቼልሽ የለ? የማርያምን ቤተክርስቲያንም ጎብኝቻለሁ።

- በነዚህ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኖች ጸሎት ያደረሰ ሰው ምነኛ ታደለ ! የትንሣኤ ቤተክርስቲያንን መጎብኘት የዕድሜ ልክ ምኞቴ ነው።

- ቃል በገባሁልሽ መሰረት ገብቼ ስላንቺ ጸሎት አድርሻለሁ፣ግና ምኑ ላይ ነው ደስታው?

- ለኔ ወደ እግዚአብሔር አምልኮ ከመቀላቀልህ የሚበልጥ ደስታ የለም።

- አምልኮዎቻቸውና በዓሎቻቸው የሀዘንና የለቅሶ ከመሆናቸውም ጋር ሃይማኖተኛ አይሁዶችም እንዲህ ይላሉ።

- ልክ ነህ፣እነሱ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት በተሻረና በኢየሱስ መገለጽ ሕልውናው ባበቃ ሃይማኖት ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን ተዋግተውታል፣ገድለውታልም፣ተከታዮቹንም አሰቃይተዋል።

- ለመሆኑ ክርስቲያኖች ኦሪትን በብሉይ ኪዳንነቱ ያምኑበታል?

- አዎ ያምናሉ።

- ታዲያ በኢየሱስ መገለጽ ያበቃለት ሃይማኖት ነው የምትይው እንዴት ነው?

- ለአይሁዳዊነት በጥብቅ የወገንክ ትመስላለህ፣እንደ ሃይማኖት አብቅቷል፣ልንመራባቸው ዘንድ የኦሪት ትምህርቶች ግን ቀሪ ናቸው።

- እንዴት አድርገሽ ነው በተዛባና ተአማኒነት በጎደለው ትምህርቱ የምታምኚውና የምትመሪበት?

- የተዛባና ተአማኒነት የጎደለው ! ማነው እንዲህ ያለህ?

- ብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ የሴሎ ሴት ልጆች የሚከተለው ጥቅስ ሰፍሯል ፦ ‹‹የብንያምንም ልጆች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው ፦ ሂዱ በወይኑም ስፍራ ተደበቁ፤ተመልከቱም፣እነሆም፣የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘፈን ሲወጡ ከወይኑ ስፍራ ውጡ፣ከሴሎም ሴቶች ልጆች ለየራሳችሁ ሚስት ንጠቁ፣ወደ ብንያም ምድርም ሂዱ።›› የሴሎ ሴት ልጆች እነማን እንደሆኑ ታቂያለሽ? እንዲህ ያለው ነገርስ ከእግዚአብሔር የተላለፈ ነው ብለሽ ታምኚያለሽ?

- የሴሎ ሴት ልጆች እነማን እንደሆኑ በሚገባ አውቃለሁ፤በዚህ ላይ መናገር ግን አልፈልግም። ይህንና የመሳሰለውን ለኛ ማብራራት ያለባቸው ቀሳውስትና ሊቃነ ጳጳሳቱ ናቸው።

- በተጨማሪም ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚከተለውን እናገኛለን ፦ ‹‹የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፣በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፣የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው።›› እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ እንዴት ሆኖ ከእግዚአብሔር የተላለፈ ሊሆን ይችላል?

- መልካም ፈቃድህ ሆኖ አርእስቱን እንድትለውጥ እፈልጋለሁ። እነዚህንና ሌሎች ብዙ መሰል ጥቅሶችን አውቃቸዋለሁ፤ይሁን እንጂ በነሱ ላይ ክርክር መክፈት አልሻም። ደሞም አሁን እረፍት እንድታደርግ ነው የምፈልገው።

- ለምን?

- በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ መከራከር አልፈልግም ብየሃለሁ . . በሆስፒታል ቆይታህ ለጥናትና ለንባብ ጥሩ ጊዜ ያለህ ይመስለኛል።

- ልክ ነሽ። ዋናው ነገር ላፕቶፔ ከኔ ጋር መሆኑ ነው። ስለ ክርስትና እና ስለ ጎራዎቹ ማንበብ ስለምፈልግ አንዳንድ መጽሐፎችን መግዛትም ያስፈልገኛል።

- በጣም ጥሩ፣ምናልባት ወደ ካቶሊክነት ትለወጥ ይሆናል።

- ምናልባት ሊሆን ይችላል።

- ያሁኑ ንባብህ ለጉዞአችን መልካም ቅድመ ዝግጅት ሊሆን ይችላል፣ውዴ ረሳህ እንዴ?

- አልረሳሁም፣በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሆን ነገ ከሐኪሙ ጋር እነጋገርበታለሁ። ቆይታዬን ራሴን በንባብ ለማጥመድ እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም እሞክራለሁ።

- ቆይታህ ሊያስጨንቅህ አይገባም። እኔ ካንተ ጋር እዚሁ ስለምሆን አብረን በመሆንና በመወያየት አስደሳች ጊዜ እናደርገዋለን።

- ካትሪና በጣም አፈቅሪሻለሁ።

- እኔም እንደዚሁ ነኝ። አሁን ሄጄ ነገ እንድመለስ ትፈቅድልኛለህ? ከትናንተት ጀምሮ አዚህ ነኝ፣አሁንም እየመሸ ነው።

- አዝናለሁ፣ከኔ ጋር ለፋሽ፤የኔ ፍቅር ነገ እጠብቅሻለሁ። ዋናው ነገር አንዳንድ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ኮምፒውተሬና ስልኬ ከአጠገቤ እንዲሆኑ እፈልጋለሁ።

- ኮምፒውተርህንና ስልክህን በአቅራቢያህ ባለው ጠረጴዛ ላይ አደርጋለሁ፣ግና ራስህን ካላማድከም ግዴታ ጋር ነው።የኔ ፍቅር እረፍት እንድትወስድ ነው ፍላጎቴ፤ለማንኛውም እስከ ነገ ደህና ሁንልኝ።

ጊዜው ገና በመሆኑ ጆርጅ መተኛት አልፈለገም። ትንሽ ለማንበብ ወስኖ ኢ-ሜይሉን ሲከፍት ስለ ጤንነቱ ሁኔታ እንዲያሳውቃት የሚመማጸነውን የሌቪ መልእክት አነበበ። የደረሰውን ሁሉ ነግሯት ለመርፌው፣ለተደረገለት አቀባበልና ላደረገችለት ሁሉ ልባዊ ምስጋናውን በመግለጽ መልስ ላከለላት። ቃሉን ያልዘነጋ መሆኑን፣ሆኖም ኮምፒውተሩንና ስልኩን የተቀበለው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ብቻ መሆኑንም ጻፈላት። የመታደልን መንገድ ፍለጋ በተመለከተ የደረሰበትን ለማሳወቅ የገባላቸው ቃል እንደ ተጠበቀ መሆኑን አረጋግጦ ለሐቢብም ምስጋናውን እንድታደርስለት ጠየቃት።

 

 

ሌላ መልእክት ከአደም የደረሰው ሲሆን መንፈስን ለጉዳት በመዳረግ ሥጋዊ ደስታን ስለማግኘት ጽፎለት ለነበረው የላከለት መልስ ነበር፦

‹‹መንፈስና ገላ አብረው ደስተኛ መሆን ካልቻሉ የአካል ደስታ ብለህ የሰየምከው የገላና የመንፈስም እርግማን ነው፡፡ ሕይወትን ደስተኝነት የሌለበት መርገምት አድርጎ የሚወስደው ይህ ፍልስፍና ጽልመታዊ ፍልስፍና ነው። ለመሆኑ ለእርግማን ነው? ወይስ ለደስታ ነው የተፈጠርነው?! ለእርግማን ነው የተፈጠርነው የሚለው አመለካከት ለሁሉም ነገር አምላክን ማማረር ለሚቃጣው የኤቲስቶች አመለካከት የቀረበ ነው። ወይም የአምላክን ባህርይ፣የሰውን ልጅ ተፈጥሮና የሃይማኖትን ባህሪ ከመረዳት ለራቁ ምድራዊ ጣዖታዊ ሃይማኖቶች የቀረበ ነው። አልያም በመበረዛቸውና መዛባታቸው ምክንያት በጣኦታዊነት ተጽእኖ ስር ወደ ወደቁ ሃይማኖቶች የተጠጋ ነው። በአጠቃላይ አነጋገር ይህ አመለካከት ከሳይንሳዊ፣ፍልስፍናዊ ወይም ሃይማኖታዊ . . አመለካከትነት ይልቅ የባለቤቱን ውስጣዊ ቅራኔና ግጭት የሚያመለክት ነው። አሁን ተመልሰህ መጥተሃል ብዬ ስለምገምት እረፍት ከወሰድክ በኋላ ተገናኝተን መወያየት እንችላለን።››

ጆርጅ ደብዳቤውን በድጋሜ ካነበበው በኋላ ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ፦
ይኸ አደም ትልቅ ፈላስፋ ነው? ፕሮቴስታንት ነው? ወይስ ይሁዲ? ዕድሜው ገና ወጣት ከመሆኑና የተሰማራበት ሥራ ተራ ከመሆኑ ጋር በአነጋገሩ ውስጥ ነገሮችን ሳወሳስቡ አቅልሎ ማየትና ጥልቅነት አንድ ላይ የተጣመረበት ነገር ለምን እንደሚታየኝ አላውቅም። አደም እውነቱን ነው፣መንፈስም ሆነ አካል ለብቻቸው መታደል አይችሉም፣የሰው ልጅ ወጥና የተሟላ አንድ አሃድ ነውና። ይህን ወጥ አንድ አሃድ መከፋፈል ጥልቅነት ያላቸውን ጉዳዮች ተራ አድርጎ የማየት ያህል ነው። የአካል ጊዜያዊ ደስታ የመንፈስና የገላን በሽታ ያስከትላል። እንደ ቡድሂስቶች ዓይነት በምናኔና ከዓለማዊ ደስታ በመራቅ የሚገኘው ማንኛውም የመንፈስ ደስታም የስነ ምግባር እነጻ ወይም የመንፈስ ምጥቀት ተብሎ ቢጠራ እንኳ፣ የመንፈስና የገላን በሽታ ያስከትላል። የመታደል መንገድ መንፈስና ሥጋ የሚጣመሩበት፣አካልና አእምሮ የሚቀላቀሉበት፣ተድላና ደስታን እንጂ እርግማንና ብኩንነትን በማያስከትል ሁኔታ ሁለቱ የሚዋሐዱበት ጥምረት ነው። አንዳንድ ሃይማኖቶች ገላን በማሰቃየት የመንፈስ ተድላና ምጥቀት ለማግኘት በሚል ከአካላዊ ደስታ ብዙ ይርቃሉ። ሌሎቹ ደግሞ በተገላቢጦሽ ለአካላዊ ደስታ ብቻ ብለው ከመንፈሳዊ ደስታ ብዙ ይርቃሉ። ሁለቱም ግን አካላዊ ደስታንም ሆነ መንፈሳዊ ደስታን ሳያገኙ፣ለነፍስም ሆነ ለሥጋ መታደልን ሳያመጡ በከንቱ ይቀራሉ።
ጆርጅ ሰዓቱን ሲመለከት ሁለት ሰዓት ሆኗል፤ለአደም ደወለ።

- ሃሎ አደም፣ለንደን ገብቻለሁ፣ግን ሆስፒታል ነኝ፤ስለዚህ ላገኝህ አልችልምና ፍልስፍናህንና ውይይታችንን ለመቀጠል ልትጎበኘኝ ትችላለህ?

- ይማርህ . . እጎበኘሃለሁ። በውይይቶቼም ሆነ አንተ እንደምትለው በፍልስፍናዬ ላስቸግርህ ግን አልፈልግም።

- እንደዚያ ማለቴ አይደለም፣እውነቱን ለመናገር ያንተ ውይይትና ፍልስፍናህ የተለየ ደስታ ይሰጠኛል፤በተሳሳተ መንገድ ተረድተሀኝ እንደማይሆን ተስፋ አድርጋለሁ።

- እኔም በአነጋገርህ ቅር ተሰኝቻለሁ ማለቴ አይደለም። ነገሩ በጣም ቀላል ነው፣እኔ ማቅለልን ነው የምወደው። ነገ ምሽት ልጎበኝህ እሞክራለሁ።

- አደም እጠብቀሃለሁ፣ውይይቶችህን ናፍቄያለሁ።

- እህህ፣ነገ እንገናኝ። የውይይት ናፍቆትን ከማሰናዳልህ ቡና ናፍቆት ጋር እየቀላቀልክ እንዳትሆን፣ደህና ሁን።

ጆርጅ ወደ አደም እንዲህ የሚስበው ምስጢር ምን እደሆነ እያሰበ ስልኩን ዘጋ . . ከገጽታውና ከተክለሰውነቱ እንግሊዛዊ አለመሆኑ ግልጽ ነው። ግሪካዊ ወይም ጣሊያናዊ ሊሆን ይችላል
። አልያም ከላቲን አሜሪካ ሊሆን ይችላል።ለማንኛውም ግን ትልቅ ምቾትና ደስታ የሚሰጠው ሰው ነው። ሌቪ ከአደም ጋር ብትገናኝ ኖሮ እንዴት ታየው ይሆን? እህህ፣ አደም ሰማያዊ ዓይኖቿንና ወርቃማ ጸሯን እያየ መታገስ ይችል ይሆን? ወይስ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ እንደኔም ጭምር ወርቃማ ምክሮቹ ባዶ ቃላት ይሆኑና ሌላው ካኽ ይሆን ነበር? ለማንኛውም ነገ ይመጣና ያሳለፍኩትን ሁሉ እተርክለታለሁ . .

በሕይወትና በሞት መካከል . . (3)

 
ነርሷ ቁርሱን ጠረጴዛው ላይ ስታድርግለት ጆርጅን በማለዳ ቀሰቀሰችው . .

- ሐኪሙ መቼ ነው የሚመጣው?

- ጧት ሦስት ሰዓት ላይ በክፍሉ የሚገኙ ታካሚዎችን ሁሉ ያያል። ዋናው ነገር ትኩሳት ከተሰማህ በፍጥነት ንገረን፣የወሰድከው መርፌ ውጤት ከሚያበቃበት ከሁለት ሰዓት ጀምሮ በየሰዓቱ ሙቀትህን እንለካለን።

- አመሰግናለሁ፣የትኩሳቱ ጉዳይ አደገኛና አዙሪቱም ቀጣይ ይመስላል።

- ዋናው ነገር የገላህ ሙቀት ከፍ ካለ ወይም ብርድ ከተሰማህ በፍጥነት እንድትነግረን ይሁን።

- እሽ፣መልካም።

ጆርጅ ቁርሱን ከበላ በኋላ ነርሷ የተናገረችውን ነገር ቁጭ ብሎ አሰላሰለ። ሌቪ መርፌውን በእጁ ይዞ እንዲገባ ለማድረግ ያደረገችበትን ግፊት አስታወሰ . . ሐኪሙ ሦስት ተኩል ላይ ወደ ክፍሉ ሲደርስ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን የሚል ስጋትና ጭንቀት ተሰማው . . ።

- ዶክተር መልካም ፈቃድህ ሆኖ የጤንነቴን ሁኔታ በግልጽ ልታስታውቀኝ ትችላል?

- የኛ የምርመራ ውጤት ኢየሩሳሌም ከተሰጠህ የምርመራ ውጤት የተለየ አይደለም።

- ይቅርታ፣እዚያ የተሰጠውን ውጤት አላውቅም፣ምን ያሳያል?

- ያለ ምንም ቀዳሚ ምልክት በድንገት ወደ አንጎል ሕዋሳት የደረሰ እንግዳ የሆነ ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የትኩሳት ደረጃህን ከፍ እያደረገ ነው። ምንም ችግር ሳይኖርብህ በተለመደው ሁኔታ ላይ የምትገኝ ብትሆንም ሆስፒታል ውስጥ እንድትቆይ ለማድረግ የምንገደደው በዚህ ምክንያት ነው። የሰውነትህ ትኩሳት በድንገት ከፍ ሲል ከአንድ እስከ ሁለት ቀን እየሰራ የሚቆይ የሙቀት መቀነሻና የማስታገሻ መርፌ ልንሰጥህ እንገደዳለን።

- እሰከ መቼ ነው ሆስፒታል የምቆየው?

- አሁን ማወቅ አልችልም። ለማንኛውም ገና የምንጠብቃቸው የምርመራ ውጤቶች በመጪዎቹ ሁለት ቀናት ውስጥ ይደርሳሉ። አዲስ ነገር ካልተከሰተ ቆይታህ በጣም ቢበዛ ከሁለት ሳምንት በላይ አይሆንም።

- የዚህ ቫይረስ መነሻ ምክንያት ምንድነው?

- እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፤ይሁንና ማንኛውንም ነገር ስለምናሟላልህና በየጊዜው መረጃዎችን ስለምንሰጥህ የሚያሳስብህ ነገር አይኖርም። ስለ ሕመምህ እስካሁን የምናውቀው ነገር ይኸው ብቻ ነው።

- ለመልካም አቀራረብህ በጣም አመሰግናለሁ።

ሐኪሙ ተሰናብቶት ሄደ . . ጆርጅ ለረዥሙ የሆስፒታል ቆይታ እቅድ ለማውጣት ኮምፒውተሩን ከፈተ። የመታደልን መንገድ ፍለጋ ላይ እንደመሆኑ ስለራሱ ሃይማኖት ይበልጥ ለማወቅ አብላጫውን ጊዜ ለንባብ ለማዋል ወሰነ። ‹‹ሃይማኖቴን ልወቅ
! ክርስትናን እና ጎራዎቹን ልወቃቸው
›› ብሎ በማጉረምረም በራሱ ላይ አፌዘ። ቀሪውን ጊዜ ደግሞ የክርስትና ምሁር
ከሆነችው ካትሪና፣እንደዚሁም ከአደምና ከቶም ጋር ለመወያየት፣ከተቻለም ከሌቪና ከሐቢብም ጋር የኤሌክትሮኒክስ ውይይት ለማካሄድ እቅድ ነደፈ። ከዚያም በኦርቶዶክስ፣በካቶሊክና በፕሮቴስታንት እምነቶች ላይ ንጽጽራዊ ንባብ በማድረግ ላይ ይሰማራል። እነዚህ ሦስቱ ዋነኞቹና ታዋቂዎቹ የክርስትና ጎራዎች ሲሆኑ፣ሁሉንም የክርስትና ጎራዎች አንድ በአንድ ለማጥናት ቢፈልግ እድሜ ልኩን ማዳረስ አይችልም።
ከእኩለ ቀን በኋላ ካትሪና ማይክልና ሳሊን ይዛ መጣች። ናፍቋቸው ስለነበር በመምጣታቸው በጣም ተደሰተ . . ከጎኑ አስቀምጧቸው ሲያጫውታቸው፣ሲያስቃቸውና ሲያስቁት ደስታው ወደር አልነበረውም . . መንፈስና አካልን አንድ ላይ የሚያረኩ መደሰቻዎች ታወሱት . . ከልጆቹ ጋር ጊዜውን ሲያሳልፍ ይህን ጥምር ደስታ እንደሚያገኝ ተገነዘበና አካልና መንፈስን አንድ ላይ ደስተኛ የሚያደርጉትን ነገሮች ሁሉ ምነው ባወቅሁ ሲል ተመኘ። ይህን ማድረግ መቻል የግድ ወደ የመታደል መንገድ መድረስ ማለት መሆኑ ተሰማው . .
ለሁለቱ ሕጻናት በአእምሮው የሚጉላላውን ጥያቄ አቀረበላቸው . .

- ማይክል በሕይወትህ ከሁሉም በላይ የሚያስደስትህ ነገር ምንድነው?

- ባባ ካንተ ጋር መጫወት ነው፣እግር ኳስንም እወዳለሁ።

- ሳሊ አንቺስ?

- እኔም ባባ ካንተ ጋር መጫወት እወዳለሁ፤በአሸንጉሊት መጫወትም ያስደስተኛል።

- እኔም ከናንተ ጋር መጫወት ያስደስተኛል፣ግና ከጨዋታ በስተቀር የሚያስደስታችሁ ሌላ ነገር አለ?

ማይክል በመገረም፦

- አንዳንድ ጊዜ ደስታ ይሰማኛል፣ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ይከፋኛል፣ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም። ባባ ለምን ይሆን?

- ማይክል፣ ምክንያቱ ላንተ ምን ይመስለሃል?

- የመደሰቴ ምክንያት ምናልባት ባልደረባዬን ወይም ጓደኛዬን በማገዜ ሊሆን ይችላል። መከፋቴ ደግሞ በፈጸምኩት መጥፎ ተግባር ምክንያት ሊሆን ይችላል።

በዚህ ድንቅ ቤተሰባዊ ውይይት ካትሪና በሰፊው ፈገግ ብላ
የኔ ቆንጆ ልባችን በደስታ የሚሞላው ሰዎችን ሁሉ ስንወድና መልካሙን ሁሉ ስንመኝላቸው ሊሆንም ይችላል፣አለች።

- ምንም ነገር ባንሠራም እንኳ ለሰዎች መልካሙን መመኘት ብቻ ማለትሽ ነው ማማ?

- አዎ፣በተቃራኒውም ምንም ነገር ባናደርጋቸውም እንኳ ሰዎችን መጥላትና ለነሱ ክፉ መመኘት እኩይ ነገር ነው።

ጆርጅ ውይይቱን ይበልጥ ማጎልበት ወደደና፦
ታዲያ አንተ ማይክል፣አንቺም ሳሊ፣ይህ ከሆነ ዘንዳ ሰዎች ለምንድነው ራሳቸውን ደስተኞች የማያደርጉት? ለምን መከፋትን ይመርጣሉ?

- ማይክል ፦ ሞኞች ስለሆኑ ነው።

- ሳሊ ፦ ወይም ስለማያውቁ ነው።

- ካትሪና ፦ የኔ ውዶች፣ ወይም በሁለቱም ምክንያት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ወደ መልካም ነገር መመራትና ለሰናይ ተግባርና ለደስታ መታደል የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።

- ጆርጅ ፦ ስለዚህ የመታደልን መንገድ ገልጎ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ይሆናል።

- ማይክል ፦ የመታደልን መንገድ ለመፈለግ ወደ ኢሩሳሌም እጓዛለሁ ብለህ ለናቴ ስትናገር ሰምቻለሁ፤የመታደል መንገድ የሚገኘው ኢየሩሳሌም ብቻ ነው?

እህህ፣ የኔ ልጅ አይደለም፣እኔ እውነትን ለማግኘት በፍለጋ ላይ ነኝ። በአጋጣሚ ኮንትራት ለመፈራረም ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዝኩ፤እዚያ ከሰዎች ስማርና ጠቃሚ ዕውቀት ስገበይ ነበር።

ሳሊ በሕጻን የዋህነት፦

- የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን አልወዳቸውም።

ጆርጅ በአግራሞት፦

- ለምን?

- የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ቤተሰቦቿ ወደ እስራኤል እየሩሳሌም እንደሚሄዱና እስራኤል በሰዎች ግድያ፣በእስራትና በማሰቃየት፣እንዲሁም በፍንዳታዎች የተሞላች መሆኗን ትናገራለች። ስለዚህ እስራኤልን አልወዳትም፣የኢየሩሳሌም ሰዎችንም አልወዳቸውም።

ካትሪና በሴት ልጇ አነጋገር ተገረመችና
፦ ሽብርተኝነትንና ግድያን የሚወድ ጤነኛ ሰው የለም። ሁሉም ምድራዊና መለኮታዊ ሕጎች ለፍትሕና ለሰናይ ተግባራት ጥሪ ያደርጋሉ፣አለች።
የካትሪና አነጋገር ጆርጅን ስለ ቡድሂዝም የመደብ ሥርዓት፣መግደልን ሴቶችንና የሴሎ ልጆችን ስለሚመለከቱ የብሉይ ኪዳን ሕግጋት እንዲያስታውስ አደረገው። ፈገግ እያለ፦

- ኢየሩሳሌም ውስጥ ከሁሉም ሃይማኖቶች ከሙስሊሞች፣ከክርስቲያኖችና ከአይሁዶችም በጣም ጥሩ የሆኑ ሰዎች ይገኛሉ።

- ሳሊ ፦ ስለዚህ አይሁዳዊቷ ሌቪ ይህን ግድያና እስራት ስለምትወድ እኔ አልወዳትም።

- ጆርጅ ፦ ሌቪ ማን ናት?

- አይሁዳዊቷ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ናት።

- ጆርጅ ፦ ጥሩ አርገሻል፤ልጆቼ በቅርጻቸው ወይም በአገሮቻቸው ምክንያት ሳይሆን፣ሰዎችን መውደድና መጥላት የሚገባን በመርሆዎቻቸውና በመልካም ስነ ምግባራቸው ምክንያት መሆኑ በጣም ጥሩ ነገር ነው።

- ማይክል ፦ እኔም ጓደኛዬን ዴቪድን አልወደውም፤ስለ መጠጥ እንጂ ሌላ ወሬ የለውም።

ጆርጅ በጨረፍታ ካትሪናን አየና ፈገግ አለ . .

- ማይክል፣ መጠጥ ምን ችግር አለው?

- አላውቅም፣የማውቀው የሚጠጣ ሰው አእምሮውን የሚስት መሆኑን ብቻ ነው።

ካትሪና በመረበሽ ስሜት ለልጇ ምላሽ ለመስጠት ተጣደፈች . .

- ማይክል ደግ አድርገሃል፣አስካሪ መጠጥ በሃይማኖታችን በአዲስ ኪዳንም እርም ተደርጓል ፦ ‹‹የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤›› . .

ካትሪና በጆርጅ ገጽታ ላይ የመገረም ስሜት አስተውላ ርእሱን ለወጠች፦

- ጆርጅ ከሐኪሙ ጋር ተገናኝተሃል?

- አዎ ።

- ምን አዲስ ነገር አለ?

- አዲስ ነገር የለም፤ከቴልአቪቭ ሆስፒታል የምርመራ ውጤት ጋር ተመሳሳይ ነው አለኝ። የቴልአቪቩ ምርመራ ውጤት ራሱ ምን እንደሆነ ግን እኔ አላውቅም ።

- ይገርማል፣እዚያ ያለው ሐኪም የምርመራ ውጤቱን አልነገረህም ነበር?

- የሄድኩበት ኩባንያ በሰጠኝ አገልግሎት አንዷ ሰራተኛቸው የሕክምናዬን ጉዳይ እንድትከታተል ስለተደረገ፣የምርመራ ውጤቱን ያወቀችው ሌቪ ናት ። ውጤቱን ለማወቅ ጥረት ባደርግም እንዳልረበሽ በማሰብ መሰለኝ ሊታሳውቀኝ አልፈለገችም ።

- የካትሪና ፊት በቅናት ተለዋወጠ፤ያች ሌቪ ቆንጆና ስሜትህ እንዳይጎዳ በጣም የምታትሳሳልህ ትመስላለች ! !

- ሳሊ ፦ ባባ እንደ ጓደኛዬ ሌቪ ዓይነት ከሆነች ግን ቆንጆም ጥሩ ሰውም አይደለችም ።

- ጆርጅ ፦ ያችኛዋ ሌቪ ግን ቆንጆና ጥሩ ሰውም ነች።

- ካትሪና ፦ አይሁዳዊያት ሴቶች በብሉይ ኪዳን እንዳለው ሁሉ ወሲብ ለነሱ በቀላሉ የሚፈጸም ተራ ነገር ነው።

- ማይክል፦ ማማ ብሉይ ኪዳን ወሲብን ያበረታታል?

- ካትሪና ፦ ማይክል እየቀለድኩ ነው፤(ወደ ጆርጅ ዞር አለችና) ፦ ጆርጅ አይደለም እንዴ?

- ልክ ነሽ . . እናትህ ብዙ መቀለድ ትወዳለች . . ሰዎችን መግደል፣ወይም አስካሪ መጠጥን መጠጣት ወይም ልቅ ወሲብን የሚያበረታታ ትክክለኛ የሆነ ሃይማኖት ፈጽሞ የለም።

ጆርጅ ማይክልን ሲያናግር ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት ካትሪና ስለተረዳች፣እንደገና አርእስቱን ለመለወጥ ሞከረች፦

- ጆርጅ፣ስለዘገየን አሁን ልጆቹን ወደ ቤት አድርስና በቀጥታ ወዳንተ እመለሳለሁ።

- የኔ ፍቅር እጠብቅሻለሁ . . (ወደ ሁለቱ ሕጻናት ዞር አለና) ፦ የኔ ጀግኖች! ቢያንስ በየሁለት ቀኑ እንድትጎበኙኝ ይሁን፣እወዳችኋለሁ . . አላቸው።

በሕይወትና በሞት መካከል . . (4)

 
ካትሪና ልጆቹን ይዛ ከሄደች በኋላ ብቻውን ሲቀር ጆርጅ ለሀሳቦቹ እጁን ሰጠ። እንዲህ ሲልም ራሱን ጠየቀ
፦ ዕድሜዬን በሙሉ በአመለካከቶች በፍልስፍናና በሃይማኖቶች ግጭቶች ውስጥ እኖራለሁ ማለት ነው?
! መላው የሰው ዘር ይታደል ዘንድ እነዚህ ሃይማኖቶች እርስ በራሳቸው የተጣጣሙ ለምን አይሆኑም?
! የሰው ልጆች በመላ ውስጣዊ ሰላም አግኝተው ለምን አይኖሩም?
! እርስ በርሳቸውስ ለምን በሰላምና በመቻቻል አይኖሩም?
! (ፈገግ አለና ቀጠለ)
፦ ምናልባት በድንገት ታምኔታዊ ሆኜ ይሆናል፣አስደናቂዋ ሕይወት አንዳንዴ ከአእምሮ ውጭ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ሕልውና ወደሌላቸው ባዶ ተምኔታዊ ምኞቶች ትለውጠናለች
!
ጌታ ሰዎችን ሁሉ ያለ ልፋት ወደራሱ ቢያደርሳቸውስ እላለሁ . . ምናልባት ሕይወት አሰልቺ ሳትሆን አልቀረችም። ሰብአዊ ድክመት የሌለባቸው ሌላ ፍጡር ሆነንም ሊሆን ይችላል። ብንሆን ኖሮ ክፋት ብቻ ሳይሆን ደግነትም ጭምር አይኖርም። እንዲያውም የሁለቱ ጎን ለጎን መኖር በዚህ ዓለም ላይ እየኖርን ስለመሆናችን ማስረጃ ነው። ኣህ . . የሰው ልጅ የመኖሩን ትርጉም፣የመሞቱን ፍቺና መጨረሻው ወዴት እንደሆነ የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር በፍልስፍናዎቹና በአመለካከቶቹ ማዕበል ውስጥ ባክኖ መቅረቱ ነው . .
ከሄደች ምንም ያህል የቆየች ባይሆንም የካትሪናን መመለሰና የወዳጁን የአደምን ጉብኝት ሲጠብቅ ነበር . . ኮምፒውተሩን ከፍቶ ኢ-ሜይሉን ሲያይ ሥራውን በስኬት በመጨረሱ አመስግኖት መታመሙን ከባለቤቱ መስማቱን በመንገር ዛሬ ወይም ነገ መጥቶ እንደሚጎበኘው የገለጸለበትን የከካኽ መልእክት አገኘ። በመቀጠል የአደምን የፌስቡክ ገጽ ጎበኘ። ስለርሱ የሚጽፈውን ነገር ማንበቡን አደም እንዳይነቃ የጓደኝነት ጥያቄ አላቀረበም . . ‹‹የመታደል መንገድን ፍለጋ ላይ ከተሰማራው ወዳጄ የተቃረመ ትምህርት 2›› በሚል ርእስ ስር የተጻፈ መጣጥፍ አገኘ፦

‹‹በመታደል መንገድ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ወዳጄ አሁንም የደስተኝነትን መንገድ ለማግኘት ጥረቱን በቁርጠኝነትና በጽናት እንደ ቀጠለ ነው። የሚከተሉትን ትምህርቶች ከርሱ ለመገብየት ችያለሁ ፦

 

1 - መታደልን ፍለጋ የመሳሰሉ ትላልቅ ጉዳዮች ከፍተኛ ጥረትና ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ ይጠይቃሉ።

2 - ጽናትና ቁርጠኝነት መልካም አጋጣሚዎችን ይፈጥራሉ። ወዳጄ ጽናትና ቁርጠኝነቱ በጨመረ ቁጥር የመማርና የማወቅ ዕድል ተመቻችቶለታል።

3- የመታደልን መንገድ ለመፈለግ የሚነሳ ሰው የሚያረጋግጠው ትልቁ ስኬትና ድል፣ የገዛ ራሱን ማሸነፍ እንጂ በሕይወት ሁነቶች ላይ ድል መቀዳጀት አይደለም።

4 - ከጽናቱና ከቁርጠኝነት ኃይሉ ጋር ለወዳጄ የሚሰጋለት ነገር የማያሳፈልገውን ነገር ሁሉ ያውቃል፣ይሁን እንጂ በሚያስፈልገው ነገር ላይ በበቂ ሁኔታ ትኩረት የማያደርግ መሆኑን ነው።

የተቀሩትን ትምህርቶች በቅርብ ቀን ይዤላችሁ እመለሳለሁ . . ሠላም ለሁላችሁም ይድረስ። አደም››

ጆርጅ ጽሑፉን እንደገኛ በጥሞና አነበበው። አደም አእምሮው ውስጥ የሚመላለሰውን የሚያውቅ መስሎ ተሰማው። ትልቁ ፈተና ሲል ምን ማለቱ ይሆን? በራስ ላይ ድልን መቀዳጀት ማለቱስ? ሲል ራሱን ጠየቀ። ወዳጁ ፈተና መውደቁን፣መርሆውን ሽጦ ጉቦ ማቀበሉን አደም ያውቅ ይሆን? ቆንጆ ሴት መሳሙንና ማቀፉንስ? ከርሷ ጋር በሚስቱ ላይ ክህደት ለመፈጸም መፈለጉንስ? ካኽን የመሰለ ስነ ምግባር የጎደለው ብልሹ ሰው ከሚመራው ኩባንያ ለመልቀቅ አለመወሰኑንና ይልቁንም ጉቦ በማቀበል ተባባሪው መሆኑን ያውቅ ይሆን? የመጨረሻው ነጥቡ ትርጉምስ ምን ማለት ይሆን? የማያስፈልገኝን በማወቄና ለሚያስፈልገኝ በቂ ትኩረት ባለ መስጠቴ ለምን ይሰጋልኛል? የማልፈልገውን ሁሉ ማወቅ ማለት የግድ የምፈልገውን ሁሉ ማወቅ ማለት አይደለም ወይ? እርግጥ ነው ወዳጁ ብኩን ኤቲስት፣በአፈተረት ውስጥ የሚኖር ቡድሂስትም ሆነ ላም ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ቁሳቁሶችን የሚያመልክ ሕንዱ መሆን አይፈልግም። ውስበስብ ይሁዲም አይሆንም . . ታዲያ የሚፈልገው ምን ይሆን? የአደም ስጋት ተገቢ ሳይሆን አልቀረም። ነጻ ሆኖ መጻፉን እንዲቀጥልበት የፌስቡክ ገጹን ያነበበው መሆኑን ሳይነግረውና ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ዛሬ በጉዳዩ ላይ ከርሱ ጋር ለመወያየት ይሞክራል።
ጆርጅ የክፍሉ ቅዝቃዜ የጨመረ መስሎ ተሰማውና የሙቀት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ብድግ ሲል ድካም ተሰምቶት ተንገዳገደ። ነርሷ አየችውና በፍጥነት መጣች . .

- ብርድ ብርድ አለህ?

- አዎ ትንሽ፣የሙቀት መጠኑ ዝቅ ብሎ ይሆናል መሰለኝ።

- የሙቀቱ መጠን አልተለወጠም፣ የተረጋጋ ነው። አልጋህ ላይ አረፍ በል፣ለሐኪሙ እደውልና በፍጥነት መርፌውን ይዤልህ እመለሳለሁ።

ነርሷ ወጥታ ሄደችና መርፌውን ልትወጋው ፈጥና ተመለሰች . .

- ይህ ሐኪሙ ያዘዘልህ አዲሱ መርፌ ነው

- አዲሱ? !

- አዎ አዲሱ፣ከመጀመሪያው ይበልጥ ብዙ ጊዜ የሚሰራ ሲሆን ራስህን ግን ያስተሃል። ይቅርታ አድርግልኝና በአስቸኳይ ልትወጋ የሚገባ ነው፣ክንድህን መዘርጋት ትችላለህ?

ነርሷ መርፌውን ወጋችው፤በጥቂት በደቂቃዎች ውስጥ ሙሉ በሙሉ ራሱን ሳተ።
ካትሪና ስትመለስ ጆርጅን በዚህ ሁኔታ ላይ አገኘችውና እስኪነቃ ድረስ ከአጠገቡ ቁጭ ብላ ጠበቀች። አልጋው ላይ ለጥ ብሎ ሲተኛ ተመለከተችው። በካቶሊካዊቷ እምነት እርሷን ከመከራከር ባይገታም፣በጌታ አምኖ እጁን ለመስጠት የማይፈልግ ቢሆንም፣ደግነቱንና ለርሷ ያለውን ፍቅር አስታውሳ ፍቅሩ እነደ አዲስ በውስጧ ይቀሰቀስ ጀመርር . . እያሰበችው ቁጭ አለች . . መልስ እያጠራት የመፋጠጥ ሁኔታ የሚያጋጥማት ቢሆንም ክርክሮቹን በጣም ትወዳለች። ለብዙ ጥያቄዎቹ ግልጽ ምላሽ የላትም። ከነዚህ ጥያቄዎችና ክርክሮች ለመገላገል በደፈናው ጌታን አምኖ መቀበል ብቻ በቂ አይደለም? ወይስ ያለ ጥያቄ አምኖ መቀበል ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ጥያቄውን ላለመመለስ የሚደረግ አንድ ዓይነት ሽሽት ይሆን? እርግጥ ነው የካቶሊክ እምነት ውስብስብነት አንዳንድ ጊዜ ያስቸግራታል። አይሁዳዊነትና ፕሮቴስታንታዊነትም እንዲሁ በተመሳሳይ ውስጣዊ ግጭቶች የተሞሉ ናቸው፣ምናልባትም ከካቶሊካዊነት በከፋ መልኩ
! ሽሽት ቢሆንም እንኳ ያለ ጥያቄና ያለ ክርክር አምኖ መቀበሉ ለሁለቱም ይበልጥ አትራፊ አይሆንም? በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ሽሽት ኪሳራ ከሚያስከትል መጋፈጥ ተመራጭ ይሆናል። ኦህ . . አንተ ኢየሱስ ሆይ ይቅር በለኝ፣አንተ አላዳንከንም ማለቴ አይደለም፣ግና . .
ስለ ቆንጆዋ አይሁዳዊት ስለ ሌቪ የተናገረውን አስታወሰች . . በጆርጅ ላይ ጽኑ አመኔታ አላት። ያለው መርህና የታማኝነት ደረጃው ምን ያህል እንደሆነም ታውቃለች። ይሁንና ከኢየሩሳሌም ወሲብ ነክ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን ብቻ አግበስብሶ የመጣው ለምንድነው?
! ባሳደረባት የቅናት ስሜት ፈገግ አለችና ቶም በሳማት ጊዜ ይህ ቅናት ዬት እንደነበረ ራሷን ጠየቀች። ታዲያ በዚህ ረገድ ጆርጅ እውነት የለውም? አዲስ ኪዳን የሚከለክል መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ለልጆቼም እያስተማርኩ መጠጥ እንዴት ነው እምጠጣው?
! አምላኬ በዚህ ሁሉ ቢከራከረኝ ምን እመልስለታለሁ . .
ካትሪና በራሷ የሀሳብ ዓለም በመዋኘት ላይ እያለች ነርሷን ‹‹አንቺ ቆንጆ ጆርጅ የት ነው?›› የሚል ሰው ድምጽ ሰማች።ነርሷን የሚያይበት ሁኔታ ከቃላቱ ይበልጥ አስቀያሚ ነበር . . ነርሷ ክፍሉን አመላከተችውና ገብቶ ካትሪናን ጨበጣት።

- እንዴት ነሽ፣የጆርጅ ባለቤት ነሽ?

- አዎ፣ካትሪና እባላለሁ፤እንኳን ደህና መጣህ፣አንተ ማነህ?

- እኔ የጆርጅ የሥራ ባልደረባ ካኽ ነኝ። ትናንት ደውዬ ሆስፒታል መሆኑን ነግረሽኝ ነበር፣አሁን እንዴት ነው ያለው?

- ደህና ነው . . ትኩሳት አለበት፣የሰውነት ሙቀቱ መጠን ከፍ በማለቱ ሙቀቱን የሚቀንስና የሚያስታግስ መርፌ ስለሰጡት ራሱን ስቶ ተኝቷል።

- አንቺ እንግሊዛዊት አትመስዪም !

- ሕንዳዊ የዘር ግንድ ያለኝ እንግሊዛዊት ነኝ።

- እህህ፣የምሥራቆች ውበት በግልጽ ይታያል፣ጆርጅ ወደ ሕንድ ሲሄድ ያላስፈለገው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም።

- ምንድነው ያላስፈለገው?

- የሕንድ ቆነጃጅት ኮረዶች፤እህህ፣ለማንኛውም እንኳን ደስ አለሽ እላለሁ፣ጆርጅን በፍቅርሽ ማርከሽ ሳትፈትኚው አልቀረሽም።

የካትሪና ፊት በከፍተኛ የመከፋት ስሜት ተወረረ . .

- ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ነው ያየሁሽ። ጆርጅ ውበትሽን ከኔ ይደብቅ ነበር ማለት ነው። ለማንኛውም ካንቺ በመተዋወቂቄ ዕድለኛ ነኝ። በፈለግሽው ነገር ለመታዘዝም ዝግጁ ነኝ። ከኛ ጋር ኩባንያችን ውስጥ ለመስራት ከፈለግሽ ታዛዦች ነን።

- አመሰግናለሁ፣እኔ የሃይማኖት መምህርት ስሆን የቤተክርስቲያን የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ነኝ።

- የኛ ሥራ የሚያስገኘው ቁሳዊ ጥቅም የተሸለ ነው፣የበለጠ እርካታም ያጎናጽፋል የሚል ግምት አለኝ።

- ሙሉ ጊዜዬን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሰጠሁ በመሆኔ ሥራዬን መለወጥ አልፈልግም።

- አስቢበት ውሳኔው ያንቺ ነው። እውነቱን ለመናገር ጆርጅ ኩባንያውን በጣም ነው የጠቀመው። የዳይሬክተሮች ቦርድ ባከናወነው ከፍተኛ ጥራት ያለው ስኬታማ ሥራ ጥልቅ ምስጋና እና አድናቆት ቸሮታል፤በተለይም በመጨረሻ ባደረገው የቴል አቪቭ ጉዞው። ታውቂያለሽ . . በሁለት ተከታታይ ጉዞዎች በያንዳንዱ ተፈላጊውን የውል ስምምነት በላቀ ብቃትና ሁሉንም ደንበኞች ባረካ መልኩ ለመፈራረም ችሏል።

- አንተ አለቃው ስለሆንክ ምናልባት ይህን ማሳካት የቻለው ከአንተ በተሰጠው መመሪያና ድጋፍም ጭምር ሊሆን ይችላል።

- ሊሆን ይችላል፣ግን አይመስለኝም፤በተለይም ሴቶችን በሚመለከት።

በዚህ አፍታ . . አንድ ሰው የክፍሉን በር አንኳኳ . .

- ይቅርታ . . ይህ የጆርጅ ክፍል ነው?

- አዎ፣የተኛው እርሱ ነው፣ራሱን አያውቅም፣እኔ ባለቤቱ ነኝ፣ግባ አንተ ማነህ?

- እኔ ወዳጁ አደም ነኝ፣ዛሬ ደውሎልኝ ነበር፣በጥሩ ጤንነት ላይ ነበረ፣አሁን ምን አግኝቶት ነው?

- ሕመሙ እየሄደ በድንገት ይመለስበታል። ትኩሳቱ ከፍ ስለሚል ማስታገሻና የትኩሳት መቀነሻ መርፌ ለመውሰድ ስለሚገደድ ሙሉ በሙሉ ራሱን ስቶ ይቆያል።

- በጣም ነው የማዝነው፣ወዳጄን መርዳት የምችልበት ነገር ይኖር ይሆን?

- ለጥልቅ ስሜትህ አመሰግናለሁ፣አረፍ በል።

- አመሰግናለሁ።

አደም ካኽን ለመጨበጥ እጁን ሲዘረጋ ካኽ በኩራት ተወጣጥሮ ጨበጠው፤አደም በትህትና እንዲህም አለው . .

- ይቅርታ . . አልተዋወቅንም።

- እኔ ካኽ ነኝ፣በኩባንያው የጆርጅ አለቃ ነኝ፤አንተስ ሥራህ ምንድነው?

- አደም እባላለሁ፣በአንድ ካፌቴሪያ አስተናጋጅ ስሆን የጆርጅ ወዳጅ ነኝ።

- አስተናጋጅ? !

የአደም ፊት ቀላ፣ግን ንዴቱን ዋት አደረገውና በተረጋጋ ቅላጼ

- ሲነቃ ልትጠይቀው ትችላለህ ! ወዳጅነት በስነ ልቦናዊ፣መንፈሳዊና ርእዮታዊ ቅርርብ ላይ እንጂ በሀብትና በገንዘብ ላይ አይመሰረትም የሚል እምነት አለኝ !

በካኽ አነጋገር የተከፋች መሆኗ በግልጽ የሚስተዋልባት ካትሪናም በፍጥነት ጣልቃ ገባች፦

- አደም ምንም አይደለም፣ጆርጅ ስላንተ በዙ ነገር ነግሮኛል . . በአንተ ወዳጅነት፣በአመለካከትህና በጥበብህ እጅግ በጣም ደስተኛ ነው።

- ይህ የጆርጅ መልካም ስነ ምግባርና የተገራ ባህሪው ማሳያ ነው . . (ወደ ካኽ እያየ ቀጠለ) ፦ ባይሆንማ እርሱ ትልቅ ኢንጂነርና የስነ ቴክኒክ ባለሞያ ሲሆን እኔ አንድ ተራ አስተናጋጅ ነኘ !

ካኽ በኩራት እንደ ተወጣጣረ፦

- በትክክል !

- ካኽ እባክህን ለጆርጅ ወዳጅ አክብሮት እንድትሰጥ እፈልጋለሁ።

- እህህ፣ገቢው ከኔ የጽዳት ሰራተኛ ገቢ ለማይበልጥ ሰው ብለሽ ነው እንደዚህ የምትናገሪው?

- የጆርጅ ወዳጅ ነው፤ደሞም ገንዘብ ሁሉም ነገር ማለት አይደለም። የሰዎች ማንነት በገንዘብ ይለካል ብለህ ነው የምታምነው?

- ጆርጅን መሰልሽኝ . . ለኔ ግን ከአስተናጋጅ ጋር መቀመጥ ውርደት ነው። ካትሪና ዋናው ነገር እኛ ዘንድ እንድትሰሪ ያቀረብኩልሽ ግብዣ አሁንም እንደተጠበቀ ነው . . ይህ ቢዝነስ ካርዴ ነው፣ስልኬ አለበት። የሚያስፈልግሽ ነገር ሲኖር ደውይ፤በይ ደህና ሁኚ . . ለጆርጅ ፈውስ እመኝለታለሁ።

- አደም፣ ሰውየው ለተናገረው ሁሉ ይቅርታ እጠይቀሃለሁ።

- ይቅርታ የሚያስጠይቅ አይደለም፣የኔ ማንነትና እሴት ያለው ከውስጤ እንጂ ማንም ስለኔ በሚናገረው ውስጥ አይደለም። ደግሞም አንቺ ምንም ስላልተናገርሽ ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግሽም።

- ጆርጅ ስላንተ የነገረኝ ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው።

- አመሰግናለሁ፣ይህ ትህትናውና መልካም ስነ ምግባሩ ነው።

- ስለ ሃይማኖተኛነትህ፣ስለአስተዋይነትህና ስለ ምክሮችህ ብዙ ነገር ነግሮኛል።

- ጆርጅ በፍጹም ልቦና እውነታን በመፈለግ ላይ የተሰማራ ሰው ነው፤ካሰበበት መድረሱም አይቀሬ ነው። ቸሩ ፈጣሪ አምላክ ደግሞ ወደርሱ ለመድረስ የሚፈልግን ሰው አያሳፍርም።

- በእግዚአብሔር ላይ መተማመንና መመካትን በተመለከተ ጥልቅ አነጋገር ነው፤ሆኖም ግን እርስ በርስ መጋጨታቸውን ሲመለከት ሃይማኖቶችን ሁሉ እርግፍ አድርጎ እንዳይተው አያስፈራህም?

- አይመስለኝም።

- ይህ ሁሉ በራስ መተማመን ለምንድነው?

- በእውነተኛ ሃይማኖት ውስጥ እርስበርስ የሚጋጭና የሚቃረን ነገር የለም፤ስለዚህህም መድረሱ አይቀሬ ነው።

- አንተ ካቶሊክ ነህ ወይስ ፕሮቴስታንት?

- መልስ እንዳልሰጥ ትፈቅጂልኛለሽ?

- ዝም ብዬ ነው የጠየኩት፣ውሳኔው ያንተ ነው።

- ጆርጅን ሌላ ጊዜ መጥቼ እጠይቀዋለሁ፣አሁን ፍቀጂልኝና ልሂድ።

- ነገ መጥተህ ብታየው ጆርጅ በጣም ደስተኛ ይሆናል፣እባክህን እንዳትቀር።

- ነገ ወይም ተነገወዲያ ለመምጣት እሞክራለሁ። ለማንኛውም ያለበትን ሁኔታ ለመጠየቅ ነገ እደውልለታለሁ፤ደህና ሁኚ።

የሚያስተኛው መርፌ ሥራውን ቀስ በቀስ እየቀነሰ በመምጣቱ ጆርጅ በጥቂቱ ራሱን ማወቅ ጀምሯል፤ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሆነ የመጫጫን ስሜት ስለሚሰማው ዓይኖቹን የሚከፍታቸው በግድ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ በካትሪና በካኽና በአደም መካከል ከነበሩት ምልልሶች ከፊሉን የሰማ ቢሆንም ከፊሉ ተደበላልቆበታል። ከአደም መሄድ በኋላ ትንሽ ሻል ስላለው ዓይኖቹን ለመክፈት ፈለገ፣ወደ ክፍሉ የሚያመራ ጎብኚ ኮቴ ሲሰማ ግን አለመክፈቱን መረጠ። ጎብኚው ሰላምታ አቅርቦ ተቀመጠ፣ሐኪም ቶም ነበር . .

- የፈላስፋችን ጤንነት አሁን እንዴት ነው?

- ቶም እንኳን ደህና መጣህ፣ድንገተኛ ትኩሳት መጥቶበት የማስታገሻ መርፌ ሰጡት፣አሁን ራሱን አያውቅም።

- መልካም ጤንነትና የተሟላ ፈውስ እመኝለታለሁ። ጆርጅ በጣም አልፎ አልፎ ብቻ የሚገኝ ልዩ ሞዴል ነው። ብዙ የምጨቃጨቀው ብሆንም እኔ ከምጠቅመው ይበልጥ ከርሱ በብዙ ነገር ተጠቃሚ ሆኛለሁ።

- አንተ የርሱ ሐኪም ነህ፤አንተ ዘንድ ሕክምና መከታተል ከጀመረ ወዲህ ብዙ መሻሻል አሳይቷል።

- ይልቁንስ መሻሻል ያሳየሁት እኔ ነኝ። ምናልባት አንቺም ሆንሽ ጆርጅ አታውቁትም እንጂ እኔ ቀልደኛ ሐኪም ነበርኩ። ዋነኛ ፍላጎቴ ሴቶችን ማጥመድና መዝናናት ነው። በዚህ ሰሞን የጆርጅ ፍልስፍና በሃይማኖቶች ላይ ያደረኳቸው ንባቦችና ካንቺ ጋር ቤተክርስቲያን መጎብኘቴ ሕይወቴን ለምን እንደለወጠ አላውቅም። በነገራችን ላይ ባለፈው ጊዜ ስለ ሳምኩሽ ይቅርታ እጠይቃለሁ፣እመኚኝ ሆን ብዬ አቅጄ አልነበረም፣ለምን እንዳደረኩትም አላውቅም።

- ነገሩ አልፏል፣የተረሳ ነገር ነው። ምናልባት ትልቁ ስህተት ከኔ ለከራሴ ሳይሆን አይቀርም። በዚያን ዕለት ያን እርጉም መጠጥ አብዝቼ ነበር።

- ለማንኛውም ሰዎች ስንባል ለስህተቶቻችን ‹‹ሳናውቀው ነው ወይም ተገደን ነው›› እያልን ማመካኛ መደርደር እንወዳለን። ይህን ተይውና ስለ ጆርጅ ጤንነት ሐኪሞች ምን እንዳሉ ንገሪኝ።

- ነገሮች ሙሉ በሙሉ ግልጽ የሆኑ አይመስልም። የሐኪሞች ቡድን በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥ ጥርት ያለ ውሳኔ ላይ ይደርሳል የሚል ተስፋ አለኝ።

- ይሻለዋል፣ጌታም ይጠብቀዋል።

ጆርጅ አሁን ገና የነቃ መስሎ አጠገቡ ያሉትን በመጠየቅ ዓይኖቹን ከፈተ . .

- ጆርጅ የኔ ፍቅር ነቅተሃል።

- ከመቼ ጀምሮ ነበር እንደዚህ የነበርኩት?

- ከሦስት ሰዓት ጀምሮ ነው። ነርሷ እንደ ነገረችኝ እኔ ከመምጣቴ ጥቂት ቀደም ብሎ ነበር መርፌውን የሰጡህ። በሰላም በመንቃትህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን . . (ወደ ቶም ዞረችና) ፦ ያንተ ሐኪም ሊጠይቅህ መጥቶ ይኸው እዚህ ይገኛል።

- ጆርጅ እንዴት ነህ?

- ደህና ነኝ፣ዶክተር እንደምን አለህ?

- ደህና ነኝ፣ስለጤንነትህ ካትሪናን ጠይቄ ጥሩ ሁኔታ ላይ መሆንህን ነግራኛለች፤አሁን ላደክምህ አልፈልግም፣ተመልሼ እጠይቀሃለሁ።

- እኔ እንግዲህ ሆስፒታል ነኝ፣መጪው ቀጠሮአችን መቼ ነው የሚሆነው?

- አንተ በፈለከው ቀን፣እዚህ ክፍልህ ውስጥም ሊሆን ችላል።

- መልካም፣እንግዲ;ያውስ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ይሆናል።

- በሆስፒታል ቆይታህ ጊዜ ካለህ፣ውይይታችን ይበልጥ ጠንከር ያለ እንዲሆን በመለኮታዊ ሃይማኖቶች ላይ የምታደርገውን ንባብ ቀጥልበትና አጠናቅቅ።

- ጥሩ፣ተስማምተናል።

ካትሪና ጆርጅ አጠገብ ከተደረደሩት መጽሐፎች አንዱን አንስታ ፈገግ እያለች

- ከትናንት አንስቶ ጀምሮታል።

- ጆርጅ፣ ጥሩ አድርገሃል።

- እዚህ ያለኝን ረዥም ቀሪ ወቅት በውይይት ላይ ለማዋል እሞክራለሁ . . (ወደ ካትሪና ዞር ብሎ ፈገግ አለና) ፦ እርሷ ውይይትና ክርክር ስለማትወድ ቶሎ ትዘገዋለች እንጂ።

የካትሪና ፊት ቀላ . .

- ውይይት ላለማቋረጥ ቃል እገባላችኋለሁ።

- እህህ፣በጣም ጥሩ፤ካንተ ጋር ለመወያየትና ሀሳብ ለመለዋወጥ ከተመቸኝ ደጋግሜ እጎበኘሃለሁ። ፈጣን ፈውስ እመኝልሃለሁ፣ፍቀዱልኝና ልሂድ።

ቶም ወጥቶ ሲሄድ ካትሪና ፈገግ ብላ ወደ ጆርጅ ዞረች

- የኔ ፍቅር ውይይቶችን በማቋረጤ ይቅርታ አድርግልኝ፣ ይህን እንዳላደርግ ግን አግዘኝ።

- መቀለዴ ነበር።

- ሆኖም እውነትም አለህ . . ያንተ አለቃ ነኝ የሚለው ቅሌታም ባለጌ ካኽ ማነው? ብዬ ልጠይቅህ ነበር።

- ካኽ ምን አደረገ?

- ዛሬ እዚህ መጥቶ ነበር፤በጸባዩ፣በስነ ምግባሩም ሆነ በድርጊቱ ጫፍ የነካ ቅሌታም ነው፤አንተን ባላስብ ኖሮ አባርረው ነበር።

- እኔን በማሰብ . . ! ማበረር ትችይ ነበር። እንዴት እንደምጠላው ልነግርሽ አልችልም። ግን ምን አድርጎ ነው?

- ዓይኑ፣እይታው፣አነጋገሩ፣አድራጎቶቹ፣መንፈሱ፣ሁለመናው ቅሌታም ወራዳ ነው። ይታይህ፣እርሱ ማኔጀር ነውና አደምን አስተናጋጅ በመሆኑ አብጠልጥሎ ሲያዋርደው ! ነርሷንም በብልግና ያናገር ነበር !

- አደም መጥቶ ነበር? !

- አዎ፣ካኽ አስከፍቶታልእንጂ። እርሱ ግን እጅግ የላቀና የተገራ ጨዋነትን ነው ያሳየው።

- አንዳንድ ጊዜ አደም ሙሉ በሙሉ የካኽ ተቃራኒ የሆነ ሰብእና ሆኖ ነው የሚታየኝ።

- ትልቅ ከማይመስለው ዕድሜውና ከተሰማራበት ሥራው በተቃራኒ አነጋገሩ እንደ ዕድሜ ባለጸጋና እንደ ፈላስፋ ነው።

- እናም አስቀድሜ ስለ አደም የነገርኩሽን ማረጋገጥ ችለሻል ማለት ነው?

- ጆርጅ ስለርሱ የነገርከኝን ብቻ ሳይሆን ያልነገርከኝንም እውነት አድርጌ እወስዳለሁ። ካኽ በተለይ በሴቶች ነገር ላይ ያንተ ተቃራኒ ነኝ ብሎ ነው የነገረኝ፣የርሱን ቅሌታምነትና ያንተን ጨዋነት ግን እርሱ አይነግረኘም።

- ፈታኟ ኦርሜላ፣ውቧ ሌቪስ?

- የኔ ፍቅር እኔ ባንተ በጣም ነው የምተማመነው። እመነኝ በስነ ምግባርህና በጨዋነትህ ጽኑ እምነት አለኝ። አንተሳ በኔ ትተማመናለህ?

- አዎ።

- ከቶም ጋር ያሳለፍኳቸውን ምሽቶችስ?

- በመጨዐረሻው ምሽት ላይ በመካከላችሁ ስለተከሰተው ነገር ቶም ነግሮኛል።

- እመነኝ ያ ነገር እንዴት እንደተከሰተ አላውቅም።

- ኦህ . . ብዙ ስህተቶችን እንፈጽማለን፣ግን እንዴት እንተከሰቱ አናውቅም። የኔ ፍቅር በእምነትሽና በጨዋነት ባህሪሽ እተማመናለሁ።

- ጆርጅ አፈቅረሃለሁ።

ሰዓቷን ተመለከተችና

- አሁን መሄድ አለብኝ፣ነገ እመለሳለሁ።

ነገ ልጠብቅሽ? ለውይይትና ለክርክር ቃል ጋበተሽልኛል። ካንቺ ጋር ከማነሳቸው ነገሮች ውስጥ ወንጌል ውስጥ የሰፈረውና ፦ ‹‹የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤›› የሚለው ጥቅስ አንዱ ይሆናል።

- የኔ ፍቅር ተስማምተናል፣በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ ሆኘልህ እቀርባለሁ።

- ፍቅሬ ተስማምተናል።

በሕይወትና በሞት መካከል . . (5)

 
ካትሪና ወጥታ ሄደች . . መጀመሪያ ሲነቃ የሰማቸውን ድምጾች ለማስታወሰ እየሞከረ ዓይኖቹን ጨፈነ። ከሌላው ይበልጥ ቶም የተናገረውና ስለ መለወጡና ከጆርጅ ብዙ ፋይዳ ማግኘቱን የገለጸው በጉልህ ታወሰው፤መረጃው ብርቱና አሳማኝ ሆኖ ተሰማው።
ካኽ አደምን በማብጠልጠል ከተናገራቸው ግርድፍና ያልተገሩ ቃላት ጥቂቶቹ ትዝ አሉት። የአደም ጨዋነትና ትሁት አነጋገሩ ታወሰው። ውሉን በስኬት በመፈራረሙ ምክንያት ከካኽ በቀረበለት ምስጋና እና ከኩባንያው ቦርድ በተቸረው አድናቆት በውስጡ ፈገግ አለ። ከሆስፒታሉ ከወጣ በኋላ ኩባንያውን ለመተውና በካኽ እጅ የሚሽከረከር ኢሞራላዊ መሳሪያ መሆኑን ለማብቃት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለማቅረብ በቂ ድፍረት ይኖረው ይሆን? ወይስ የገንዘብና የስልጣን ፍቅር በመርሆዎቹ ላይ ድል ይቀዳጅ ይሆን?
በሀሳብ ባህር በመዋኘት ላይ እያለ የነርሷን ድምጽ ሰማ

- እንደምን ነህ፣የሙቀት መጠኑ አሁን እንዴት ነው?

- አህ፣አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነኝ፣ይሻለኛል።

- ከጊዜው በፊት ትነቃለህ ብለን ጠብቀን ነበር።

- በትክክል . . ከአፍታ በፊት ነው የነቃሁት፣ይሁን እንጂ በጣም ደክሞኝ ስለነበር ዓይኔቼን እንደጨፈንኩ ቀጥዬ ነበር።

- ግድ የለም፣የሰውነትህ የሙቀት መጠን አሁን ቆንጆ ነው፤ደህና ሁን።

- አመሰግናለሁ፣ከእንግዳዬ በኩል ለደረሰብሽ ተገቢ ያልሆነ ነገር ይቅርታ አድርጊልኝ፣የሆነውን ነገር ባለቤቴ ነግራኛለች።

- እኔ ሳልሆን ባልደረባዬ ነበረች። ለማንኛውም እንደሱ ያሉ ያንዳንድ ሰዎች ጋጠወጥነት ስለሚያጋጥመን ለምደነዋል። በዚህ ራስህን አታስጨንቅ፤ለጨዋነትህ አመሰግነሃለሁ . . ስሜ ዚንታ ነው፣የሚያስፈልግህ ነገር ካለ በማናቸውም ጊዜ ልታስጠራኝ ትችላለህ።

- ዚንታ ስሜሽ ትንሽ እንግዳ ነገር ይመስላል !

- የዘር ግንዳችን ከነምሳ እንጂ ከእንግሊዝ አይደለም።

- እንዳንች ያለች ደግና ትሁት ነምሳዊት አውቃለሁ።

- ይገርማል፣እንግሊዝ ውስጥ የነምሳውያን ቁጥር በጣም ትንሽ ነው።

- ሌቪን እንግሊዝ ውስጥ ሳይሆን ቴልአቪቭ ነው የተዋወኳት።

- ይሁዳ ናት ! አይሁዶች አውሮፓን ስለበከሉ ፍልስጥኤምና ኢየሩሳሌምን ሰጥተናቸው ነው ከነሱ የተገላገልነው።

- በአይሁዶች ላይ ያለሽ ስሜት ጠንከር ያለ ይመስላል !

- ሊሆን ይችላል፣ግና አንተ ከአይሁዶች ጋር ብዙ ስላልኖርክ ነው . . ለማንኛውም ከፈለከኝ በማንኛውም ጊዜ አስጠራኝ፤አሁን እራት ስላልበላህ ይመጣልሃል፣በልተህ ማረፍ ይኖርብሃል።

- ስለትህትናሽ አመሰግናለሁ።

- ሚስተር ጆርጅ ምንም አይደለም።

በቀጣዩ ቀን ሰሞኑን አጥቶ የከረመው ንቃትና ብርታቱ ተመልሶለት አማልዶ ከእንቅልፉ ተነሳ። እዚ መሰንበቱ ስለ ሰለቸው ከሆስፒታሉ መውጣት በቻልኩ ብሎ ተመኘ። በጧት የቀረበለትን ቁርስ በልቶ እስከ ዶክተሩ መምጫ ሰዓት ድረስ ጥልቀት ባለው ንባብ ራሱን ለማጥመድ ወሰነ። በዚህም በአይሁዳዊነትና በክርስትና መካከል አንዳንድ ንጽጽራዊ ምልከታ ያደርጋል። አይሁዳዊነት ውስጥ ካላት ስፍራ ጋር ለማነጻጸር ሴት በክርስትና ውስጥ ስላላት ስፍራ ያነባል። በዚህ ርእስ ላይ ከካትሪና ጋር ለመወያየትና ከሐቢብና ከሌቪ ጋር ለመላላክም ይችላል ማለት ነው።

 

ሐኪሙ መጥቶ ገና ሰላምታ ሲያቀርብለት ጆርጅ ጠየቅ፦

- የምርመራ ውጤቱን በተመለከተ አዲስ ነገር አለ?

- የለም፣አንዳንዱ ውጤት ሲደርስ አንዳንዱ ደግሞ ገና አልደረስም፣አትጨነቅ ተረጋጋ።

- እንዲሁ ለመጠየቅ እንጂ ፈጽሞ አልተጨነኩም፣የደረሱት የምርመራ ውጤቶችስ?

- ከመወሰናችን በፊት የቀሩትን ውጤቶች እንጠብቃለን፤አንተን ማስበርገግ አልፈልግም፣ይሁን እንጂ ምናልባት ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግህ ይችል ይሆናል።

- ቀዶ ጥገና? !

- አታስብ ብየሃለሁ፣የሚያድነው እግዚአብሔር ነው፣ፈውስም በርሱ እጅ እንጂ በኛ እጅ አይደለም፣እኛ ምክንያት ብቻ ነን።

- ሁኔታዬ እስከዚህ ደረጃ መድረሱ በጣም አስገርሞኝ እንጂ እመነኝ ፈጽሞ አልተጨነኩም።

- አውቃለሁ፣ሁሌ በንባብና በውይይት ተጠመድህ እንጂ ስትጨነቅ ጭራሽ አይታህ እንደማታውቅ ነርሷ ነግራኛለች። ይኸ እጅግ በጣም ጥሩ ነው . . ውጤቱ ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ይደርሳል ብለን እንጠብቃለን።

- ውጤቱን እጠብቃለሁ፣ጥሩ ነገር ይዞ እንደሚመጣ እተማመናለሁ።

- ድንቅ ነው፣ይህ ጥልቅ መተማመን ከምን እንደመጣ ልታብራራልኝ ትችላለህ?

- እግዚአብሔር አምላካችን ከኛ ይበልጥ ለኛ ርህሩህ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

- እናም አንተ ሃማኖተኛ ነህ ማለት ነው። በጥቅሉ ሲታይ ሃይማኖተኞች ለደስተኝነትና ለሕሊና መረጋጋት የበለጠ ብቃት አላቸው። የሚያስቸግሩን እጣ ፈንታቸውን ይህቺ ዓለማዊ ሕይወት ብቻ መሆኑን የሚያምኑ ኤቲስት ሕሙማን ናቸው።

- ይቅርታ፣ማለት የፈለኩት አንተ ያልከውን አይደለም።ጌታችን በዚህ ዓለም ላይ ከሁሉም በላይ ለኛ ርህሩህ ነው ማለቴ ነው። በእርግጥ የተናገርከው በጣም ጥልቅ የሆነ ትርጉም አለው። አማኝ ሰው ከወዲያኛው ዓለም ሕይወት ጋር ራሱን ስለሚያያይዝ ሕይወቱ ቀጣይነት አለው። ይህ ግን የመለኮታዊ ሃይማኖቶችን ተከታዮች ብቻ የሚመለከት ነው።

- ፈላስፋ መሰልከኝ፤ወዳጄ እኔ ሥራ አለኝ . . ይሁንና ያኛው የቡድሂዝም ወይም የሕንዱ እምነት ተከታይ ይህን ማድረግ ለምን እንደማይችል በአጭሩ ንገረኝ።

- ስንሞት ነፍሳችን ወደሌሎች ፍጡራን ትዛወራለች ብለው ስለሚያምኑ ሌላ መጪ ሕይወት አለ ብለው አይቀበሉም።

- እህህ፣ጥልቀት የሌለው ጥሬ እምነት ነው፤አነጋገርህ ማራኪ ቢሆንም ለመሄድ እገደዳለሁ፤ ደህና ሁን።

ጆርጅ በንባቡና በትንተናው ውስጥ እንደሰመጠ ቀጠለ። ያቋረጠው ከአደም የተደወለለት ስልክ ነበር . .

- አደም እንደምን አለህ? መጥተህ እንደነበረ ካትሪና ነግራኛለች፣በጣም አመሰግናለሁ።

- ወዳጄ ሆይ ! ላግዝህ ወይም ላቀርብልህ የምችለው ነገር ይኖራል?

- ወዳጄ የምትለው ውብ ቃል ነች። ወዳጄ ላንተ ያለኝ ምስጋና የበዛ ነው። እመነኝ ካንተ የምፈልገው ነገር ቢኖር እጠይቅህ ነበር . . ኦ ! አዝናለሁ ካንተ የምፈልገውን ነገር አስታወስኩ።

- በል ንገረኝ፤እውነተኛ ወዳጆች መሆናችን እንዲሰማኝ ስለምታደርግ ታስደስተኛለህ።

- የምፈልገው ካንተ ጋር መገናኘት ነው፣ካንተ ጋር የምወያይባቸው ብዙ ርእስ ጉዳዮች አሉኝ።

- ይቅርታ አድርግልኝና ዛሬ ሳይሆን ነገ እመጣለሁ። ዛሬ አንድ ሰራተኛ ከሥራ ስለቀረ በካፌቴሪያው ድርብ ሥራ አለብኝ።

- መልካም . . ግዴለም ነገ እጠብቀሃለሁ።

ጆርጅ የስልክ ጥሪውን እንዳበቃ ካትሪና ደረሰች። በደስተኝነት ስሜት ፊቷን በፈገግታ አድምቃ ወደ ክፍሉ ገባች . .

- የኔ ፍቅር ዛሬ እንዴት ይሆን ያደረው?

- ደህና አድሬያለሁ፣በጥሩ ሁኔታ ላ;ይ ነኝ፤አንቺስ እንዴት ነሽ?

- እግዚአብሔር ለፀጋው የተመሰገነ ይሁን።

- ላንቺ የእግዚአብሔር ፀጋ የትኛው ነው?

- የሃይማኖት ፀጋና በቤተክርስቲያን ሥራ መጠመዴ . . እና . . አንተ ባሌ የመሆንህ ፀጋ።

- እናም ሃይማኖተኝነት በአንቺ አመለካከት ፀጋ ነው? !

- ጥርጥር አለው? የምትጽናናበትን ፈጣሪ የሌለህ አምላክ አልባ ከመሆን የከፋ ነገር የለም !

- በአንቺ እምነት የኤቲስቶች ነገር እንዴት ነው?

- በግልጽነትና ያለምንም ዘለም ወለም . . በኔ አመለካከት ኤቲዝም እምነት ሳይሆን ደዌ ነው። የመንፈስና የልቦና በሽታ ነው። የተዛባ አእምሮና ኢምክንያታዊነት ነው። ለፍጥረትና ለፍጡርም በሽታ ነው።

- ሙሉ በሙሉ ካንቺ ጋር እስማማለሁ። ግና ባለቤትሽ በሽተኛ በመሆኑ ፀጋው ምኑ ላይ ነው?

- አንተ ባለቤቴ በመሆንህ ለኔ ፀጋ ነው ማለት እንጂ ያንተ መታመም ፀጋ ነው ማለቴ አይደለም።

- ያም ቢሆን ፀጋነቱ ምኑ ላይ ነው?

- ለሴት ተገቢውን ክብር የማይሰጡና በንቀት ዓይን የሚመለከቱ ብዙ ወንዶች ይገኛሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹ ወንዶች እንደ አንተ እንደኔ ፍቅር ለሴቶቻቸው ታማኞች አይደሉም።

- የሴቶችን ክብር ማሳነስና መጨቆን ከሃይማኖተኝነት ጋር በቀጥታ የተዛመደ አይደለም ወይ?

- እንዴት?

- ሃይማኖተኝነት በጨመረ መጠን ሴትን አሳንሶ ማየት ይጨምራል።

- አሁንም ልድገምና ይህን ያለህ ማነው?

- የአይሁድ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ሴቶችን የሚገልጹት እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ነው።

- ማለት የፈለከው አይሁዳዊነትን ከሆነ ክርስትናን በዚህ ውስጥ ለምን ታጠቃልላለህ?

- ጳውሎስ በቆሮንቶስ 1 ውስጥ ፦ ‹‹ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ፤ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።›› አላለም ወይ?

- ዛሬ ደግሞ የስነ መለኮት ሊቅ ሆነሃል !

- በሆስፒታል ቆይታዬ በክርስትና ላይ ጥልቅ ንባብ አካሄዳለሁ ብየሽ የለ? ቶምም እንዲሁ አንቺ እያለሽ ይህንኑ ብሎ አልነበረም?

- መልካም . . ይህ ሃይማኖተኝነትህን ይጨምራል . . ምናልባትም ከፕሮቴስታነት ወደ ካቶሊካዊነት ሊለውጥህም ይችላል።

- ሊሆን ይችላል፤ይሁንና ወደ ርእሳችን እንመለስ። በግልጽ እንነጋገርና የሴት ሁኔታ ክርስትና ውስጥ በአይሁዳዊነት ውስጥ እንዳለው ሁሉ አስከፊ አይደለምን?

- ግልጽ ለመሆንና ውይይቱን ለመቀጠል ቃል ስለገባሁልህ ብጠላውም እቀጥላለሁ።

- የምትጠይውን ነገር እንድትቀጥዪ አልፈልግም፣እርግጠኛ ሁኚ እኔ ምንም ቅር አይለኝም።

- የለም፣ እቀጥላለሁ፤ ለአንተ በጌታ አምነህ እጅ መስጠት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ለኔ ደግሞ አእምሮና ምክንያታዊ አመለካከት ያስፈልገኛል የሚል ሀሳብ አለኝ።

- ካንቺ ጋር እስማማለሁ። ለእግዚአብሔር ወደው እጅ ሳይሰጡ እምነት ሊኖር አይችልም። ይሁን እንጂ ፍትሕ አስተካካዩ ጌታ ግን እርስ በርስ የሚጣረሱ ወይም አእምሮ ሊቀበላቸው የማይችል ግዴታዎችን ሊጥልብን አይችልም።

- እንዴት?

- እውነተኛ የሆነ ሃይማኖት አእምሮ የማይቀበለውን ነገር ይዞ ሊመጣ ይችላል?

- ምንን የመሰለ ነገር?

- እግዚአብሔር ደካማ ነው፣ወይም ፍጡራን ያስፈልጉታል፣ወይም ሰዎች እንዲገደሉ ያዛልና የመሳሰሉ ነገሮች። እንዲህ ያለው እንዴት አምላክ ሊሆን ይችላል? !

- አንደምታው አደገኛ ቢሆንም አፍ የሚያስዝ አስረጅ ነው።

- የትኛውን አንደምታ ማለትሽ ነው?

- ይህ እንኳ ከርእሳችን ውጭ ነው። ርእሳችን የሴት ስፍራ በክርስትና ውስጥ የሚለው ነው፣አይደለም እንዴ?

- ልክ ነሽ . .

- ግልጽጹን ለመናገር . . ወንድ በሆንኩ ብዬ ብዙ ተመኝቻለሁ። በእርግጥ ሴት ክርስትና ውስጥ ደረጃዋ ከወንዱ ዝቅ ያለ ነው።

- ኦህ፣ልክ እንደ አይሁዳዊነት ማለት ነው?

- ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ከዚያ ቀለል ያለም ሊሆን ይችላል። የተዛቡና ተአማኒነት የሚጎድላቸው ኦሪትና ተልሙድ በጣም አስከፊ የሆኑ ትምህርቶችን አካተዋል፤እንዲያውም ለማሰብ እንኳ በሚከብዱ ወሲባዊ ልቦለዶች የተሞሉ ናቸው . . ወንጌል ውስጥ ግን ሴት ከወንድ ያነሰች መሆኗና የሴቶችን መብት በሚመለከት አንዳንድ መጥፎ ነገሮች ቢኖሩም የአይሁዳዊነትን ያህል የከፋ አይደለም።

- ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚያስበረግጉ ጥቅሶች አጋጥሞኛል።

- እንዴት ያሉ?

- ሴት እንደ ንብረት ትወረሳለች ፦ ‹‹ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፣አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፣የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፣ከእርስዋም ጋር ይኑር።›› ወንድ ወራሽ ከሌለ በስተቀር ሴት ልጅ መውረስ አትችልም ፦ ‹‹ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ፦ ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው፣ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ፤›› የወር አበባ ያለባትን ሴት አስመልክቶም፦ ‹‹በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው። . . መኝታዋንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፣በውኃም ይታጠባል፣እስከ ማታም ርኩስ ነው።›› . . ይበቃል ወይስ ልጨምር?

- ይበቃል፣ይበቃል፣ . . እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ ዘንድ የሚስተዋለው የሴቶች አስከፊ ሁነታ እንዳለ ሆኖ፣ ክርስትና ሴትን በአይሁዳዊነት ውስጥ ከነበረችበት ብዚ አስቸጋሪ ነገሮች ነጻ አውጥቷታል፤ሁኔታችንም በአይሁዳዊነት ውስጥ ከነበረው ተሻሽሏል።

- እንዴት?

- ለሴት መብቷን አስከብሯል። ለምሳሌ አይሁዶች በኢየሱስ ዘመን በተራ ምክንያቶች የሰራችው ምግብ ያልጣፈጠ በመሆኑ እንኳ ቢሆን ፍች ይፈጽሙ ነበር። በዝሙት ምክንያት ብቻ እንጂ ፍች እንዳይፈጸም ኢየሱስ አስተማረ። በዚህም በማንኛውም ምክንኛያትና በማንኛውም ጊዜ ይፈታት ከነበረው ወንድ ሥልጣን ነጻ አውጥቷት መዘባበቻው እንዳትሆን አድርጓታል።

- መልካም . . ሌሎች ምሳሌዎችን ማቅረብ ትችያለሽ?

- መጽሐፍ ቅዱስ አንተ በገለጽካቸው ዓይነት ጥቅሶች እንደተሞላ ሁሉ ለሴት አክብሮት በሚሰጡ ሌሎች ጥቅሶችም የተሞላ ነው።

- የሚጋጩና እርስ በርስ የሚቃረኑ እየሆኑ ትክክለኞች ይሆናሉ ተብሎ አይታሰብምና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፉ ትክክለኞቹ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?

- አስቸጋሪ ነጥብ ነው ያነሳኸው። የውይይቱ መራዘም አድክሞኛል፤ባይሆን ኖሮ ግን እመነኝ ከመወያየት አላፈገፍግም ነበር።

- ሌላ ጊዜ እንወያይበታለን፣ግን አስቸጋሪው ርእስ የቱ ነው?

- ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፉት የትኞቹ ናቸው? የሰዎች የብረዛና የማዛባት እጅ የገባባቸውስ የትኞቹ ናቸው? የሚለው ነው።

- ለአሁኑ ውይይቱን እንቋጨውና ሌላ ጊዜ እንቀጥልበታለን።

- ስለ ትንሣኤ ቤተክርስቲያን አሁን ትነግረኛለህ?

- እንደፈለግሽ፣ቃል እንደገባሁልሽ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሄጃለሁ። የሄድኩት ዓርብ ቀን ስለ ነበረ መንገዱ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ነበረበት . .

ጆርጅን ለመጠየቅ የመጣው በራድ አቋረጣቸው . .

- ጆርጅ እንደምን አለህ? . . ካትሪና ሠላም።

- እንኳን ደህና መጣህ !

- መታመምህን ሰምቼ ልጠይቅህ መጣሁ፤ምናልባት አስፈልግህ ይሆናል።

- አመሰግናለሁ።

በራድ ፊቱን ወደ ካትሪና መልሶ መሰሪ ፈገግታ እያሳየ

- ኦ ካትሪናም እዚህ ናትና፣ከቶም ጋር ያለች መስሎኝ።

- ምን ማለት ፈለክ?

- ምንም፣የኔ እመቤት አትቆጪ።

ጆርጅ ተመቻችቶ ተቀመጠና

- ይህ ያንተ ሥራ ወይም አንተን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም።

- ሊሆን ይችላል፤ግና ቶም ስለ ካትሪናና ስለ ውበቷ ብዙ ጊዜ ስለሚናገር እርሱ ዘንድ ትሆናለች ብዬ ገምቼ ነው።

ጆረትጅ ተናደደ፦

- አንተ ውሸታም ጋጠወጥ ነህ።

- ቶም ወደ ቶራ ቦራ መሄድ እንደምትፈልግ ነግሮኛል፣እርሱም ይዋሻል ማለት ነው?

ካትሪና በአግራሞት ዓኖቿን አፍጥጣ፦

- ቶራ ቦራ?!

- ከተፈጥሮ ጸባዬ እንድወጣ አታድርገኝማ። በራድ ለጉብኝትህ አመሰግነሃለሁ፤ሠላም እፈልጋለሁና በል ቶሎ ከዚህ ጥፋልኝ።

- እኔስ እሄድልሃለሁ፣ነገር ግን ቶም ማር በተቀቡ ቃላቶቹ እንዳይሸነግላችሁ፤በቃላት ሽንገላ ኤክስፐርት ነው። ከፈለጋችሁ የተጫወተባቸውን ሴቶች መጠየቅ ትችላላችሁ . . ጆርጅ እንደምታውቀው ሁሉ ለሁሉም ችግሮችህ ፈውሱ እኔ ዘንድ ይገኛልና ስልክህን እጠብቃለሁ፤ደህና ሁኑ።

በራድ እንደወጣ ካትሪና መናገር እየቃጣት ሶፋው ላይ ተመቻችታ ተቀመጠች . .

- ይህን ሰውየ እጠለዋለሁ።

- እኔንም እንደዚሁ ያስጠላኛል። መርህም ሆነ ሰብእና የጎደለው ሰው ነው።

- ግና ማለት የፈለገው ምንድነው?

- በየትኛው ጉዳይ?

- እውን ወደ ቶራ ቦራ መሄድ ትፈልጋለህ?

- እህህ፣ቶራ ቦራን ታውቂያለሽ?

- አዎ . . በፓኪስታንና በአፍጋኒስታን የሚገኝ የአሸባሪዎች ተራራ ነው፤ጉዳዩ ምንድነው?

- አንድ እንግዳ ነገር ተከስቶ ነበር። ከቶም ጋር ስለ ሃይማኖቶችና ስለ እስላም ስንናገር ከሰለምክ ወደ ቶራ ቦራ ትሄዳለህ ብሎ ቀለደብኝ። ወዲያው ከቶም ዘንድ ስወጣ በራድ ሳላስበው ‹‹ወደ ቶራ ቦራ ትሄዳለህ?›› ሲለኝ ተገረምኩ።

- ጆርጅ፣በራድና ቶም ውሸታሞች ስለሆኑ ስለኔ የሚናገሩትን አትመን።

- የበራድን ውሸታምነት አውቃለሁ። ቶም ግን አንቺን እንደ ሳመሽ ነግሮኝ ሆን ብሎ ፈልጎ አለማድረጉን ገልጾልኛል።ለምን እንዳመንኩት ግን አላውቅም።

- አዝናለሁ፣ ቶም የተናገረው አውነት ነው። ይህ ተከስቷል፤ጥፋቱን ከርሱ ይበልጥ የምሸከመው እኔ ነኝ። ጠጥቼ ባልሰክር ኖሮ ደፍሮ ያደረገውን ባላደረገ ነበር።

- ቶም የፈጸመውን ምናልባት ሳያስበውና እንዴት እንዳደረገው ሳያውቅ ያደረገው ነው ብዬ ልረዳ እችላለሁ። በጣም የሚገርመው ግን አስካሪ መጠጥ መውሰዱን አሁንም የቀጠልሽበት መሆኑ ነው !

- እውነቱን ለመናገር . .

- ከዚህ ይበልጥ አስገራሚው ደግሞ ፦ ‹‹የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤›› የሚለውን ጥቅስ ለልጃችን ለማይክል መንገርሽ ነው።

- የሰው ልጅ ለሁሉም ጥፋትና ስህተቱ ፍልስፍናዊ ወይም ምክንያታዊ ትንተና ቢያንስ ለራሱ ለመስጠት ይችላል። እኔ ግን ለራሴና ላንተም ይበልጥ ግልጽ ሆኜ እናገራለሁ።

- በማቋረጤ ይቅርታ፣ለጥፋትና ስህተቱ ፍልስፍናዊና ምክንያታዊ ትንተና መስጠት ስትዪ ምን ማለት ነው?

- እኛ የማናውቃቸው የሃይማኖት ትምህርቶች ብዙ ናቸው። የማናውቃቸውና የማንከተላቸው ትምህርቶችም እንደዚሁ በርካታ ናቸው። ችግሩ ግን ስህተታችንን አምነን መቀበል የማንወድና ጥፋተኞች መስለን እንዳንታይ ሎጂካዊ ወይም ፍልስፍናዊ እንዲያውም ሃይማኖታዊ ትንተና ለመፈለግ የምንባዝን መሆናችን ነው። ለዚህ ጉልህ ምሳሌ የሚሆነው በክርስትና ውስጥ ያለው የአስካሪ መጠጥ ጉዳይ ነው።

- ይበልጥ ግልጽ ልታደርጊልኝ ትችያለሽ?

- አስካሪ መጠጥ በብሉይና በአዲስ ኪዳንም እርም ተደርጎ የተከለከለ ነው። በብሉይ ኪዳን ውስጥ ፦ ‹‹ . . ነገሥታት የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አይገባም፣መሳፍንትም ፦ ብርቱ መጠጥ ወዴት ነው? ይሉ ዘንድ፤እንዳይጠጡና ሕግን እንዳይረሱ፣የድሀ ልጆችንም ፍርድ እንዳያጎድሉ “። የሚል ሰፍሯል። በአዲስ ኪዳን ደግሞ ፦ “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ“ የሚል ተጽፏል።

- በጣም ጥሩ፣እናም በመሰረቱ አስካሪ መጠጥ እርም ነው ማለት ነው። ግና ከዚህ ክልከላ ውጭ የሆነ እገዳው የማይመለከተው ልዩ ሁኔታ አለ?

- አታሹፍብኝ፤ግልጽ ሆኜልህ ነው የምናገረው። በእርግጥ ነቢያት አስካሪ መጠጥ ይጠጣሉ የሚል ጥቅስም ሰፍሯል። እናም ቤተክርስቲያን ውስጥ አስካሪ መጠጥ እንጠጣና ኢየሱስ ዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ስለራሱ ሲናገር “እውነተኛው የወይን ግንድ እኔ ነኝ“ ብሏል። ስለ ተከታዮቹም ሲናገር ፦ “እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ “።ብሏል እያልን ፍልስፍናዊ ማመካኛ እንደረድራለን ።የወይን ውሃ ተክሉን ለመመገብ ወደ ቅርንጫፎች እንደሚሰራጭ ሁሉ፣ቅዱስ ደሙ ደማችንና የሰራ አካላችንን ቅዱስ ለማድረግ በደም ሥራችን ውስጥ መሰራጨቱን ለማመልከት ኢየሱስ የወይን ጠጅን በምሳሌነት ተጠቅሟል፣እያልን እንጎነጫለን። ኢየሱስ ግን የወይን ጠጅን እንድንደሰትበትና እንድንሰክርበት አልሰጠንም። የሰጠን አማኞች ብቻ እንጂ ሌሎች የማይረዱትና የሚያነጻ ምስጢራዊ ዓለማ አድርጎ ነው ብለን እንፈላሰፋለን።

- ኦህ . . ድንቅ ፍልስፍናዊ ፈጠራ ነው !

- በኔ መዘባበትህን አቁም፣አለዚያ ውይይቱን አቆማለሁ።

- አህሀ፣መልካም እንግዲያውስ አስካሪ መጠጥ መጠጣት የተቀደሰ ተግባር ሆኗል ማለት ነው !

- ሃይማኖት እንዲሆን ለምንፈልገው ነገር እንዴት ፍልስፍናዊና ምክንያታዊ ትንተና እንደምንሰጥ አየህ?

- እንዲህ ዓይነቱ ነገር ተከታዮቹ ያሻቸውን ነገር ባሻቸው ጊዜ ሊሚፈጥሩለት ሰው ሰራሽ ሃይማኖት እንግዳ ነገር አይደለም። ከእግዚአብሔር ለተላለፈ መለኮታዊ ሃይማኖት ግን ተቀባይነት የለውም።

- ወየው፣አንተ መቼም ክርክር አይሰለችህም፣እኔ ግን ማይክልና ሳሊ መምጫቸው ስለሆነ ወደ ቤት ለመሄድ እገደዳለሁ። እንደገና ተመልሼ ለመምጣት እሞክራለሁ . . ውይይቱንም እንቀጥላለን። ግን እኔ ከውስጥ ራሴን ስለምሟገት በተለይ ደግሞ ግጭቱ በሃይማኖታችን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በገዛ ራሳችን ውስጥ ጭምር ስለሆነ ይደክመኛልና ክርክርህን ቀለል አድርግልኝ።

- የኔ ፍቅር መመለስሽን እጠብቃለሁ። አስቀይመሽ ከሆነም ይቅርታ አድርጊልኝ፣ራስሽን እንድታስጨንቂም አልፈልግም። ዛሬ መመለስ ካልተመቸሽም ችግር ለውም።

ካትሪና ግንባርና ግንጮቹን ስማ ወጥታ ሄደች . . በተካሄደው ውይይት በጣም ተደስታለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ራሷን እንደ ገለጸችና አእምሮዋ ስሜቷን እንደረታ ታምናለች። ጆርጅም በእጅጉ ተደስቷል። ካትሪና ዝም ብሎ አምኖ በመቀበል ካባ የተሸፈነና ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የፍልስፍና፣የሎጂክና የዕውቀት . . አቅም እንዳላት ለመገንዘብ ችሏል። ጆርጅ ካትሪና ከሄደች በኋላ በጀርባ ተኝቶ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ
፦ ጥልቅ ውይይትና ክርክር ነበር። ካትሪና አስካሪ መጠጥ ለምን እንጠጣለን ከሚለውን ጥያቄ ሳትፋጠጥ በግሩም ስልት እንዴት ማምለጥ እንደ ቻለች አስታውሶ ፈገግ አለ።