አላህ ሰውን ክቡር ፍጡር ማድረጉ

አላህ ሰውን  ክቡር ፍጡር ማድረጉ
‹‹የአላህ ሕግ የሆነው እስላም በዙሪያችን ስላለው ተፈጥሮ ግልጽ ሆኖ እናገኘዋለን። ተራሮች፣ባሕሮች፣ፕላኔቶችና ከዋክብት በአላህ ትእዛዝ ብቻ ይሄዳሉ፤በጉዞአቸውም በርሱ ብቻ ይመራሉ። ሁሉም ለፈጣሪያቸው ትእዛዝ ተገዥዎች ናቸው። በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለችው እያንዳንዷ አቶም ግኡዝ አካላትን ጨምሮ እንደዚሁ የግድ ለርሱ ታዛዦችና ተገዥዎች ናቸው። የሰው ልጅ ግን አላህ የመምረጥ ነጻነት የሰጠው በመሆኑ ከዚህ አጠቃላይ ሕግ ለየት ይላል። እናም ለአላህ ትእዛዛት የመገዛት ወይም የራሱን ሕግ ለገዛ ራሱ ደንግጎ በመረጠው እምነቱ መሰረት የመጓዝ ምርጫ አለው። የሚያሳዝነው ግን በአብዛኛው ሁኔታ ሁለተኛውን መንገድ የመረጠ መሆኑ ነው።››


Tags: