ድክመት . . !

ድክመት . . !

ድክመት . . ! (1)

ጆርጅ ወደ ሆቴሉ ሲደርስ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ነበር። ወደ ክፍሉ ገብቶ ቶሎ ሸውር ከወሰደና ልብሱን ከቀየረ በኋላ ለምሳ ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ለመሄድ ወሰነ። ከክፍሉ ሊወጣ ሲል ስልኩ ጮኸ። ካትሪና ነበረች . .

- ሃሎ . . የኔ ፍቅር እንዴት ነሽ።

- ጆርጅ እንደምነህ፣የድንቃድንቆቹ አገርስ እንዴት ናት?

- ግሩም ድንቅ ናት፣እኔ እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ። ሥራዬንም አሳክቻለሁ። ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው የቀሩኝ፣ ይህችን ውብ ከተማ የበለጠ ለማወቅ እጠቀምባቸዋለሁ።

- በጣም ጥሩ፣የሐኪሙን ጥያቄዎችስ እንዴት አደረግህ?

- ኣህ፣ቶም ወደ ሃይማኖቶች ቀረብ ብለህ ስትመለከታቸው ሁሉንም ችላ ትላቸዋለህ ማለቱ፣አንዳንዴ እውነቱን ነው የሚል ስሜት ያድርብኛል። ቢሆንም ግን በተወሰነ ደረጃ ነገሮች ግልጽ መሆን የጀመሩ ይመስለኛል።

- ካቶሊክ ክርስትና ወደርሱ በቀረብክ ቁጥር የበለጠ ያስደስተሃል፣መንፈስ ቅዱስም ይረዳሃል።

- ይህን እንኳ ተይኝ፣አጥባቂ ክርስቲያኑ ማይክል ነው እንድረካባቸው ኮረዶችን የሚያቀርብልኝ። ማይክልም ካኽም ሁሉም ያው ናቸው፣ከእንግዲህ ማናቸውንም አላምንም።

- ያንድ ክፉ ምሳሌ መኖር ማለት መሰረታዊው እሳቤ ስህተት ነው ማለት አይደለም። እንዲያውም መሰረታዊው እሳቤ ስህተተኛ ላለመሆኑ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል። አንድ ክፉ ምሳሌ ቢገኝ በተቃራነው በአስርቶች የሚቆጠሩ መልካም ምሳሌዎች ይገኛሉና !

- ልክ ነሽ፣ዋናው ነገር ልጆቻችን ማይክልና ሳሊ እንዴት ናቸው?

- በጣም ደህና ናቸው፣ሁላችንም በጣም ናፍቀህናል።

- እኔም እንደዚሁ በጣም ናፍቄያችኋለሁ።

በሆቴሉ ሬስቶራንት ምሳው ምርጥ ምርጡ በያይይነቱ የተትረፈረፈበት ክፍት ቡፌ ነበር። ሬስቶራንቱ ከተለያዩ አገሮች በመጡ ቱሪስቶች ተጨናንቋል። ጆርጅ ፈንጠር ብሎ በሚገኝ ጠረጴዛ ምሳውን ለመብላት ለብቻው በተቀመጠበት፣ዓይኑ ውብና ማራኪ በሆነች ሕንዳዊት ኮረዳ ላይ አረፈ። ዕድሜዋ በሃያዎቹ መጀመሪያ አከባቢ ይመስላል። ሐር የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጥቁር ጸጉር፣የተኳሉ ዓይኖች፣ብርቱካን የመሰሉ ስርጉድ ጉንጮች፣ በፈገግታ የተሞላ ውብ ገጽታ . . በዓይኖቻቸው የሚያሳድዷትን ቱሪስቶች ትቃኝ ነበር። አንድ ጊዜ ፈገግታ ትለዋወጣለች፣ሌላ
ጊዜ ደግሞ በመሽኮርመም ፊት ትነሳቸዋለች።
በውበቷና በመሽኮርመሟ ለምን እንደተማረከ አላወቀም፣ በተደጋጋሚ እይታውን ተክሎባታል። ከወጥመዷ ለመራቅ በምግቡና ኢንተርኔት ላይ በሚጠብቀው ሥራ ሃሳብ ለመጠመድ ወሰነ። ግና ሳያስብ ያችን ውብ ኮረዳ ከጎኑ ቁጭ ብላ አገኛት . .

- ስሜ ኦርሜላ ነው፣ የዴልሂ ልጅ ነኝ። የስሜ ትርጉም ፈታኟ ወይም ማራኪዋ ማለት ነው . . ለብቻህ ተቀምጠህ በዓይኖችህ ስትበላኝ ሳይ አሳዘንከኝ፣ብቸኝነትህን እንዳቃልልህ ትፈልጋለህ?

 

ጆርጅ ራሱን ቀና አድርጎ ተመለከታት። በከፊል ራቆቷን ነች፣ ሆዷ ሙሉ በሙሉ ተገልጧል። ገላዋን ምንም ያህል የማይሸፍን በጣም አጭር የሆነ ጉርድ ነው የለበሰቸው። ፊቷ ሙሉ ጨረቃ ነው፣ ጸጉሯ የሐር ነዶ። ፈገግታዋ መብረቅ ነው። ሌሎችን እምቢ ስትላቸው ወደርሱ ጠረጴዛ መጥታ ስትቀመጥ ለምን ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው አያውቅም . .

- ስሜ ጆርጅ ነው፣ከእንግሊዝ አገር ነው የመጣሁት። ለበጎ አስተያየትሽ አመሰግናለሁ። ከዚያም ራሱን ለማሸነፍና ውስጣዊ ትግሉን ለመቋጨት በመፈለግ ዝም አለ። አብሯት መቀመጥ ውስጡ ይመኛል፣መቀመጡ ግን ሌሎች ጉዳዮችን ማስከተሉ ግልጽ ነው . . አዝናለሁ፣የበዛ ሥራ አለብኝ፣ወደ ሕንድ ከደረስኩ ወዲህ ለብቻዬ ስቀመጥ ይኸ የመጀመሪያዬ ነው።

- ትሕትናህ፣አለባበስህና ገጽታህ ውብ ነው፣አብረን ብንደሰትስ ?

- አቀራረብሽም ውብ ነው፣አሁን ካንቺ ጋር በመነጋገር እየተደሰትኩ ነው፣ከአፍታ በኋላ ግን በሥራ መጠመዴ ነው።

- ይቅርታ . . በተፈጥሮህ ጅል ነገር ትመስላለህ፣እኔ ከኤድስ ነጻ መሆኔን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት አለኝ።

እጇን ዘርግታ እጁ ላይ አሳረፈችና ጠበቅ አድርጋ ያዘችው። የኤሌክትሪክ ንዝረት ያህል እስከ ልቡ ድረስ ቢሰማውም፣ ልቡንና ስሜቱን አሸንፎ እጁን ከእጇ በቀስታ አስለቀቀ።

- ገብቶኛል . . አመሰግናለሁ፣አመሰግናለሁ፣እኔ ባለትዳር ነኝ።

- ሚስትህ እዚህ ሕንድ ውስጥ ካንተ ጋር ነች ? !

- አይደለችም፣እንግሊዝ አገር ናት።

- ከአውሮፓና ከአሜሪካ የሚመጡ የተለያየ ሃይኖት ያላቸው ቱሪስቶች አብዛኞቹ ባለትዳሮች ናቸው። ይሁን እንጂ ሁሉም እዚህ መደሰትና መዝናናትን ይወዳሉ . . ሕንዳዊ ውበት ከሌላው የተለየ ነው።

- አመሰግናለሁ . . አንቺ በእርግጥ ውብና ማራኪ ነሽ። ግና አመሰግንሻለሁ።

- አንተተ ለየት የምትል ውስብስብ ሰው ነህ። በሕይወቴ እንዳንተ ያለ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም። ራሴን ለወንድ አቅርቤ እምቢ አልፈልግም ስባል ይህ የመጀመሪያዬ ነው።

ኦርሜላ
ወዲያውኑ
ተነስታ ሄደች። ጆርጅ ለራሱ አጉረመረመ፣ የሚገርም
ነው . . ሚስቱን የማይክድ ሰው፣ ለመርህ ተገዥ የሆነ ሰው ውስብስብ ነው፣እህህ ምናልባት . . ሕይወት
በየቀኑ ትርጉማቸውን
የማናውቃቸው፣ወይም በየራሳችን መንገድ የምንተረጉማቸው ድንቃድንቆችን ታሳየናለች። ካኽ በኔ ቦታ ቢሆን ኖሮ የቆንጆዎች ቆንጆ ከሆነች ኮረዳ ጋር ምርጥ ሌሊት በማሳለፍ በተደሰተ ነበር!!

ድክመት . . ! (2)

ጆርጅ ምሳውን አብቅቶ ሰዓቱን ሲመለከት በሕንድ አቆጣጠር አስር ሰዓት ተኩል ነው። በለንደን አቆጠጠር ሲያሰላ ከጧቱ አምስት ሰዓት ነው። ካትሪና ከአራት ሰዓት በፊት ማለትም ከጧቱ አንድ ሰዓት ላይ መደወሏን አስታወሰ። እንዲህ አማልዶ ከእንቅልፍ መንቃት የካትሪና ልማድ አይደለም!
ወደ ክፍሉ ሄደና የሚጠብቁትን ሥራዎች ለማጠናቀቅ፣ ኢሜሉንና የፌስቡክ ገጹን ለማየት . . ኮምፒውተሩን ከፈተ። ከሁለቱ ኩባንያዎች ጋር ውሉ በተሳካ ሁኔታ መፈረሙን በማብሰር ለካኽ ኢሜል ላከ። የተላኩለትን መልእክቶች አየት አየት ካደረገ በኋላ ከሦስት ቀናት ወዲህ ወዳላየው የፌስቡክ ገጹ ገብቶ በርካታ ቁጥር ያላቸው መጣጥፎች፣ምስሎችና ከወዳጆቹ የመጡ ሊንኮችን አገኘ። ሐኪም ቶም ወዳጅነት ጠይቆት አገኘውና ከወዳጆች ዝርዝር ውስጥ ከጨመረው በኋላ ወደ ገጹ ሲሄድ አዳዲስ ፎቶግራፎችን የጨመረ መሆኑን ተመለከተ። ሲከፍታቸው ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ምስል ተመለከተ። ቶምና ካትሪና አብረው የሚታዩባቸው ፎቶግራፎች!
አብረው ሲመገቡና ሲሲቁ የሚያሳይ ከሥሩ ‹‹ከካትሪና ጋር›› የሚል የተጻፈበት አንደኛው ነበር። ፌስቡክ ላይ መቼ እንደ ተደረገ ሲያስተውል በለንደን አቆጣጠር አስራ ሁለት ሰዓት

ሆኖ አገኘው

። በአንዳንዶቹ ላይ 5፡25 ሰዓት የተጻፈባቸው ሲሆን ቀኑ ግን ያው 15/17 . . ነበር።
ግራ ተጋባ። ካትሪና የደወለችው ገና ከማለዳው ነበር፣እስከ አስራ አንድ ተኩል ድረስ ከቶም ጋር ነበረች፣እናም እስካሁን አልተኛችም ማለት ነው
! ደሙ ፈላና ለካትሪና ደወለ። ስልኳ ዝግ ነው። ለቶም ሲደውል በተዳከመ ድምጽ መለሰለት፦

- ሃሎ ጆርጅ፣እንዴት ነህ ? ሁሉንም ሃይማኖቶች ችላ ማለት መጀመርህን ካትሪና ነገረችኝ !

- መቼ ነገረችህ ? ! !

- ስትደውልልህ አብረን ነበርን። ከዚያ በኋላ ወደ ቤት አደረስኳት፣ታድለሃል። በጣም ድንቅ ሴት ነች።

- ምን ስታደርጉ ነበር ?

- በቤተክርስቲያን የድግስ ሥርዓት ላይ ነበርን። በሃይማኖተኞች ላይ ጥናት አካሄዳለሁ ብየህ የለ !

ጆርጅ የስልክ ጥሪውን አበቃና በዚህ ሀፍረተ የለሽ ቅሌት ተገርሞ አልጋው ላይ ተዘረጋ . . ሳያስብ ኮረዳዋን ኦርሜላን ሲፈልግ ራሱን እንግዳ መቀበያው ውስጥ አገኘ። ሲያጣት የእንግዳ መቀበያ ሰራተኛውን ጠየቀ። ፈገግ አለና ዛሬ ፈላጊዋ በጣም ብዙ ነው፣ከአፍታ በፊት ወደ ቻይናዊ ቱሪስት ክፍል ሄዳለች፣አለው።
ግንፍል ብሎ በግብዝነት ጠየቀው፦
 

- ምን ያደርጋሉ ? !

- እህ፣ምን እንደሚያደርጉ እንዴት ልወቅ ?

ጆርጅ በጥያቄው ተመልሶ አፈረ፣በከፍተኛ
ውጥረት ላይ መሆኑን ተገነዘበ። የሚያደርገው ነገር ጠፋው . . ወደ ክፍሉ ተመልሶ ሄደ . . በዚህ አፍታ የሚታየው ነገር ከሃዲዋን ካትሪና በማንኛውም መንገድ ቢሆን መበቀል ብቻ ነው። እነዚያን በሬስቶራንቱ ድግስ ላይ እምቢ ብሎ የተዋቸውን ሁለቱን ቆነጃጅት ኮረዶች እንዲያመጣለት ለማይክል ለመደወል ወሰነ። እስኪ መርሆህ ይጥቀምህ፣እንደ ካኽ ወይም እንደ ቶም ለምን አትሆንም፣እነዚህ መርሆዎች ምን ጠቀሙህ . . ምንም . . ምንም
. . አለችው፣ነፍሲያው።

- ሃሎ . . ማይክል።

- ሃሎ ጆርጅ፣ በሰላም ነው ? በዚህ ጊዜ ደውለህ አታውቅም።

ጆርጅ ባንኖ ሰዓቱን ሲመለከት ገና አንድ ሰዓት ተኩል ነበር . .

- ኦህ፣ይቅርታ እንዲሁ ሰላም ለማለት አስቤ ነው . . በቃ ነገ እደውላለሁ፣ አመሰግናለሁ ማይክል።

- በመደወልህ አመሰግናለሁ፣ነገ እደውልልሃለሁ።

ጆርጅ እየተነጫነጨና በንዴት እያጉረመረመ፣ አንዳንድ ስድብና እርግማን ካፉ እያመለጡ ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ቀጠለ። የሚያደርገው ጠፍቶታል። በሚስቱ ላይ ያደረበት ጥርጣሬና ግራ መጋባት ሰብእናውን ደካማ እንዲሆን አድርጓል . . ከኦርሜላ ጋር ሊበቀላት ቢፈልግም ሊያገኛት አልቻለም። ከርሱ
ያነሰ
ግትርና እንዲቆጠብ በሚያደርጉት በነዚያ መርሆዎች ላይ ከርሱ ይበልጥ የሚለሳለስ ሌላ ግለሰብ አንደወሰዳት እርግጠኛ ሆኗል። እርሱን ቀፍድዶ በመያዝ ሌሎች መጥተው በማራኪ ውበትና በደስታ
እንዲዝናኑ በሚያደርገው አጉል የመርህ ተገዥነቱ ተበሳጨ።
በዚህ አፍታ ውስጥ ካትሪና ቀደም ሲል ከቶም ጋር አምሽታ የነበረችበትን አስታውሶ ኢንተርኔት ላይ ገብቶ የቶምን ድረ ገጽ ከፈተና የቆዩ ፎቶገግራፎችን መፈለግ ያዘ። የዚያን ምሽት ፎቶግራፍም ቶም ድረ ገጽ ላይ ተደርገው አገኛቸው። ፎቶግራፎቹ ከሞላ ጎደል ከመጨረሻው የምሽት ድግስ ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ ቦታውም ራሱ መሆኑንና ምናልባትም ቤተክርስቲያኑ መሆኑን የሚያመለክቱ ነበሩ። እንዲህ ያለውን ጋጠ ወጥነት የምትፈቅድ ምን ዓይነቷ ቤተክርስቲያን ትሆን
? ስል ራሱን ጠየቀ!!
የቀድሞውን ማምሸቷን በምን መልኩ ይዞት እንደነበረና በራድ የአደንዛዥ እጽ ሱሰኛ ሊያደርገው እንዴት እንደ ሞከረ ትዝ አለው።
‹‹ለዋነኞቹ ጥያቄዎችህ እልባት ስታገኝ ችግሮችህን በተሻለ
ሁኔታ
መያዝ
ትችላለህ፣መንፈስህም
ጫናዎችን ለመቋቋም የበለጠ ጥንካሬ ያገኛል››። ‹‹ጥርጣሬህን የወንጀሏ ማስረጃ አድርገህ አትውሰድ፣ ምናልባት ከቶም ጋር የሆነችው እሱን ወደ ክርስትና ለመጥራት ሊሆን ይችላል
!››። ‹‹ቅለትና ጥልቀት ባለው ስልት በዋነኛው ጉዳይህ ላይ አትኩር፤ ያን
ስታደርግ
ደስተኝነት ከውስጥህ ከራስህ መንፈስ ይመነጫል፣ ይህ ሲሆን ለችግሮችህ ሁሉ መፍትሔ ታገኛለህ››።
‹‹በካትሪናና በቶም ላይ ከተለመደው የተለየ ነገር ላለማሳየት ሞክር፣በቅርብ ወደ ሕንድ መሳፈርህ ነውና ከጉዞው ስትመለስ የሚሆነው ይሆናል። ነገሮችን የምትወስዳቸው ቀለል አድርገህ ሳታወሳስብ፣ በደስተኝነት መንፈስ እንጂ በትካዜ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን።›› የሚሉትን የአደምን ምክሮች አስታወሰ። ለመሆኑ ይኸ አደም ከካትሪና
ገር
ተስማምቷል
? ወይስ እንደሱ ሃይማኖተኛ ስለሆነች ለርሷ እየተሟገተ ነው
? በማለት ራሱን በራሱ ጠየቀ። ይህ ሰው ከኔ የሸሸገው ምን እንደሆነ ለማወቅ እደውልለታለሁ!!

- ሃሎ ማን ልበል ?

- ጆርጅ ነኝ፣ ከሕንድ ነው የምደውለው።

- ከምስራቅ የሚደውለው ምዕራባዊ ሰው ! እንደምን አለህ ?

- መጥፎ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት። ካትሪና እስከ ዛሬ ጧት ድረስ ሌሊቱን ሙሉ ከቶም ጋር ነው ያመሸችው።

- እንዴት ማረጋገጥ ቻልክ ?

- ከራሱ ከቶም ነው ያረጋገጥኩት፣ፎቶግራፎቹን በፌስቡክ ገጹ ላይ አሰራጭቷል፣ለራስህ ገብተህ ማየት ትችላለህ።

- ታዲያ ምኑ ነው አዲስ ?ባለፈው ጊዜም ከርሱ ጋር ማምሸቷን አረጋግጠህ አልነበረም ?

- አዎ ግን . .

- ዋናው ነገር ምን ለማድረግ አስበሃል ? በጥርጣሬና በግራ መጋባት ወቅት ደካማ አትሁን። ትኩረትህን በሥራህ ላይና የጉዞህ ዓላማ በሆነው በጥያቄዎችህ ምላሽ ፍለጋ ላይ ብቻ አድርግ።

- በማንኛውም መንገድ ቢሆን ካትሪናን መበቀል እፈልጋለሁ።

- በግራ መጋባትና በጥርጣሬ ላይ በምትሆንበት የድክመት ሁኔታ ውስጥ ማንም ሰው እንዲጫወትብህ አታድርግ ብየሃለሁ አስቀድሜ። አሁንም ደጋግሜ የምልህ በድክመት ሁኔታ ላይ በምንገኝበት ወቅት መርሃችንን መጠበቅ ይሳነናል፣መርሃችንን አጥብቀን በያዝን ቁጥር ደግሞ ይበልጥ ጠንካሮች እንሆናለን።

- በአንድና ከዚያም በላይ በሆኑ የሕንድ ኮረዶች እደሰታለሁ፤ ልቤን እንዳነደደች ልቧን ለማንደድ ከኮረዶቹ ጋር ሆኜ ፎቶግራፎችን እልክላታለሁ።

- በዚህ ራስህን ነው የሚታቃጥለው፣በዚህ መንገድ መበቀል የደካሞች አድራጎት ነው። ካትሪናን ከምትጎዳት ይበልጥ ራስህንና መርሆህን ነው የምትጎዳው። ላይሆን ቢችልም ከቶም ጋር ክህደት ፈጸመች ብንል እንኳ ይበልጥ ተጎጂው አንተ ነህ ወይስ እሷ ?

- እኔ ነኝ።

- አይደለም እሷ ነች። ራሷን መርሆዋን፣ሃይማኖቷንና ስሟን ያቃጠለችው እራሷ ናት። እኔ አሁንም አንተ እንደ ጠረጠርካት አትሆንም የሚል እምነት ቢኖረኝም አንተ በምንም ነገር ተጎጂ አትሆንም።

- ለምንድነው የምትሟገትላት ? እንዳንተው ሃይማኖተኛ ስለሆነች ነው ?

- አንተ እንደምትለው ክህደት ፈጽማብህ ከሆነች መስላ ለመታየት ብትሞክር እንኳ ሃይማኖተኛ አትመስለኝም። ክህደት ያልፈጸመችብህ ከሆነ ሌላ ነገር ነው። እኔ በጭራሽ የማላውቃት እየሆንኩ ለምን ብዬ ነው የምሟገትላት ? ሃይማኖተኛ መሆኗንም አሁን ነው ካንተ የምሰማው። የነገርከኝ የሚትጠጣና የሚታመሽ መሆኗን ብቻ ነበር። ሃይማኖተኛ ነች አላልከኝም። ደሞም በዚህ ምን ጥቅም አገኝበታለሁ ? በተጨማሪም የጠየከኝ አንተ እንጂ እኔ አልደወልኩም !

- አደም ይቅርታ አድርግልኝ፣በጣም ስለተረበሽኩ እንጂ አንተን ማስቆጣት ፈልጌ አይደለም። ከኦርሜላ ጋር ካትሪናን መበቀል የወሰንኩት በጣም ስለጨነቀኝ ብቻ ነው።

- እኔን ለማስከፋት እንዳላሰብክ አውቃለሁ። ዳሩ ግን ውጥረቶች ከመርሆዎቻችን ሊያዘናጉን አይገባም። ኦርሜላ ደግሞ ማን ናት ?

- በጣም የሞማርክ ቁንጅና ያላትና ዛሬ ራሷን አቅርባልኝ እምቢ ያልኳት ኮረዳ ነች። አሁን ላገኛት ምን ያህል እንደጓጓሁ ልነግርህ አልችልም።

- ለምንድነው እምቢ ያልካት ?

- ለሥጋዊ ፍላጎት፣ለጊዜያዊ ስሜት ወይም ለአላፊ ደስታ ብዬ መርሆዬን ማዋረድ ስላልፈለኩ . . ወይም ሞኝ ተላላ በመሆኔ !

- አሁን መርሆህን ለማራከስ ዝግጁ ነህ ማለት ነው ? !

- ምን ላድርግ ?

- ወደ መርሆህ ተመለስ። ለታላላቆቹ ጥያቄዎችህ ምላሽ ፈልግ። በደስተኝነት ጎዳና ተጓዝ። ከግብህ ትደርሳለህ፣ ፈተናውንም ታልፋለህና !

- ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ለንደን ስለምመለስ ላገኝህ ይገባኛል።

- እኔም እጠብቀሃለሁ።

የሚያደርገውን ያጣው ጆርጅ ስልኩን እንደዘጋ ኮምፒውተሩን ከፈተ። የአደምን የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ የማየት ሀሳብ አደረበት። በጣም የተለመደው ዓይነት ገጽ
ነበር። መጣትፎቹ በአንጻራዊነት ረዣዥሞች ናቸው። እንዲህ ያሉ መጣጥፎችን ማንበብ በሚፈቅድለት የስነ ልቦና ሁኔታ ላይ ባይሆንም ‹‹ደስተኝነትን ፍለጋ ከሚኳትነው ወዳጄ የሚቀሰሙ ትምሕርቶች›› በሚል ርእስ ሥር የተጻፈው መጣጥፍ ትኩረቱን ሳበው። ከአራት ቀናት በፊት በአደም የተጻፈ ነበር. .

ደስተኝነትን ፍለጋ ከሚኳትነው ወዳጄ የሚቀሰሙ ትምሕርቶች

በቅርቡ የ ደስተኝነትን መንገድ በጉጉት በመፈለግ ላይ ከሚገኝ መርህ ካለው ግለሰብ ጋር ተዋውቄያለሁ። ፍለጋው ከልብ የመነጨ እውነተኛ ፍለጋ ነው የሚል እምነት አለኝ። ያለበት ጫና ግን በጣም ከባድ ነው። ከርሱና ከታሪኩ ትምሕርት ያገኘሁ በመሆኔ የሚከተሉትን ጠቃሚ ነጥቦች ከናንተ ጋር መጋራት ወደድኩ

1. ደስተኝነትን የሚፈልግ ሰው ወደዚያ የሚያደርሰውን መንገድ ይዞ ለመጓዝ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። በገንዘብ፣ በሥልጣንም ሆነ በውርስ ወደዚያ መድረስ አይቻልም። ደስተኝነትን ለማግኘትና ወደዚያ ለመድረስ ጽኑ ጥረትና የማያቋርጥ ፍለጋ ማድረግ የግድ ነው።

2. በሕይወቱ ውስጥ ለታላላቆቹ ጥያቄዎች መልስ መስጠት የማይችል ሰው ደስተኛ መሆንም ሆነ ደስተኝነትን ማግኘት ፈጽሞ አይችልም። ጥያቄዎቹ ማነው የፈጠረን ? ለምን ዓለማ ነው የተፈጠርነው? ለምንድነው የምንኖረው? መጨረሻችንስ ወዴት ነው? የሚሉ ናቸው። ለነዚህ ጉዳዮች እልባት መስጠት ያልቻለ ሰው ፈጽሞ ደስተኝነትን መጎናጸፍ አይችልም።

3. አንዳንድ ሰዎች ወደ ደስተኝነት የሚያደርሰውን መንገድ ውስብስብነና አስቸጋሪ ያደርጉትና ተግዳድሮቶቹን ማለፍ አልቻልንም ይላሉ። ነገሮችን ገርና ቀላል አድርገው ቢወስዱ በቀላሉ መድረስ በቻሉ ነበር።

4. አንዳንድ ሰዎች በመለስተኛ ችግሮችና በጥቃቅን የቅርብ ዓላማዎች ዋናኛ ዓላማቸውን ይዘናጋሉ። ይህን ሲያደርጉ መሀል መንገድ ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ በጭራሽ ወደ ደስተኝነት አይደርሱም።

 

5. በጉዞው ወቅት መርሆዎቻችንን መጣስ ተገቢም ትክክለኛም አይደለም። መርሆዎች መሪ የብርሃን ማማዎች ስለሆኑ መጣስ የለባቸውም። ረግጦ ሊያልፋቸው የሚሞክር ሰው የሚያፈርሰው የገዛ ራሱን ሲሆን እነሱ ግን ባሉበት ይኖራሉ።

6. በፍለጋው ላይ የተሰማራ ሰው ፍለጋው ከልብ የመነጨ እውነተኛ ፍለጋ እስከሆነ ድረስ፣ቁርጠኛና የማያቋርጥ ጥረት በትእግስትና በጽናት ካደረገ መንገዱን ብሩህ የሚያደርጉለት ነገሮች ገር ይሆኑለታል።

ትምህርቶቹ ብዙ ስለሆኑ በሚቀጥለው ጽሑፌ ምናልባት በቅርቡ ለማሟላት እሞክራለሁ።

 

ከአክብሮት ጋር ፡- አደም

ድክመት . . ! (3)

ጆርጅ የአደምን ጽሑፍ ካነበበ በኋላ ዘና ያለ ቢሆንም አደም ሳይነግረውና ስሙን እንኳ ሳይጠቅስ ስለርሱ ለምን እንደ ጻፈ ግራ በመጋባት ራሱን ጠየቀ። አደም በጻፈውና ለኔ በነገረው መካከል ምንም ግጭት የለም። ከኔ ጋር ግልጽና ቁርጠኛ ነበር። ለተጎዳ ስሜቴና ላለሁበት የስነ ልቦና ሁኔታዬ ግን ግድ የለውም
! የሄሮዊን እንክብል ብወስድ ወይም ኦርሜላን ባገኝ ኖሮ ያለሁበትን ሁኔታ እረሳ ነበር፣መርሳት የደስተኝነት መንገድ ነው . . አወይ፣እውን እነዚህ ዘዴዎች ከራስ ወደፊት መሸሽ ናቸው
? ወይስ አጋጣሚዎችን የማያበላሹ አስተዋዮች የሚጠቀሙበት ትክክለኛ መፍትሔ ናቸው?
ግራ መጋባቴና
መባዘኔ ምነው ከፋ!
የክፍሉ ስልክ አቀጨለና መነጋገሪያውን አነሳ። የእንግዳ መቀበያ ሰራተኛው ነበር የኦርሜላን መምጣት ሊነግረው የደወለው . .

- ወደ ክፍልህ እንድትመጣ ትፈልጋለህ ?

ጆርጅ ምላሽ ጠፍቶት ለረዥም ጊዜ ጸጥ አለ . .

- አላውቅም !

- ማለት ?

- እኔ ራሴ መጣሁ።

ከክፍሉ ወጥቶ ወደ እንግዳ መቀበያው ወረደ። መውረዱ ካትሪናን ለመበቀል ነው
? ወይስ አደም እንደሚለው የገዛ ራሱን ለመበቀል
? ካኽና ቶምን ልታዘዛቸው
? ወይስ አደምን ልታዘዝ
? እያለ ከራሱ ጋር በመሟገት ላይ እያለ አሳንሰሩ እንግዳ መቀበያው ላይ ቆመ። በሩን ከፍቶ ሲወጣ ኮረዳይቱ ኦርሜላ ከፊትለፊቱ ቆማለች . . አይታው በሰፊው አፈገገች፣ፊቷ ፈክቶ የፈነዳ ጽጌሬዳ መስላለች።

- ሰላም ኦርሜላ፣እዚያ መቀመጫ ላይ ብንቀመጥ ምን ይመስልሻል ?

- አህ፣ይቻላል።

እንደተቀመጠች በፈገግታ ቀደመችው . .

- የእንግዳ መቀበያው ሰውየ ስለኔ እንደጠየክና እንደፈለከኝ ሲነግረኝ ከፍተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ።

- ለምን ?

- እምቢ ብለህ ስትመለሰኝ ያዋረድከኝና ባንተ ዓይን የምማርክ ውብ ቆንጆ እንዳልሆንኩ ስለተሰማኝ ነው።

- አመሰገንኩሽ እንጂ አልዋረድኩሽም። ቆንጆ አይደለሽም አላልኩምም። አንቺ እንደ ስምሽ ውብና ማራኪ ልጅ ነሽ።

- ታዲያ አብረን እንድንደሰት ወደ ክፍልህ ሄደን ለምን አንዝናናም . . ብላ በዓይኗ ጠቀስ አደረገችው።

- መጀመሪያ መነጋገር እፈልጋለሁ።

- ስለምንድነው የምንነጋገረው ?

- በጣም ቀላል የሆነ ለኔ ግን ትልቅ ትርጉም ያለው ጥያቄ ልጠይቅሽ እችላለሁ ? ግን ከኔ ጋር ፍጹም እውነተኛ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ።

- ካንተ ጋር የመጨረሻው ፍጹም እውነተኛ እሆናለሁ፣የሆነ ነገር ወዳንተ ለምን እንደሚስበኝ አላውቅም።

- በሕይወትሽ ደስተኛ ነሽ ?

ለአፍታ ጸጥታ ሰፈነ። ኦርሜላ መሬት መሬቱን እያየች ዝምታውን አቋረጠችና . .

- እውነተኛ ለመሆን ቃል ገብቼልሃለሁና ቃሌን አከብራለሁ። እንዲህ ያለውን ጥያቄ አልጠበኩም ነበር። ደስተኝነት ሳቅ ፈገግታና ጫወታ፣ገንዘብና ቁንጅና ከሆነ በጣም በጣም ደስተኛ ነኝ።

- ማለት በውስጥሽ፣የሕሊና ሰላም፣ውስጣዊ ደስታና የመንፈስ እርካታ አለሽ ወይ ? ማለቴ ነው። አንዳንድ ሰው እውስጡ የትየሌለ ሀዘንና ጭንቀት ተሸክሞ በጥርሱ ይስቃል።

- እውነቱን ለመናገር ቃል ገብቼልሃለሁና ልክ እኔን እየገለጽከኝ ነው። በገንዘብ፣በሳቅና በጫወታ፣በጭፈራና በወሲብ ከራሴ፣ ከውስጣዊ ሀዘኔና ከጭንቀቴ እየተሸሸግሁ ነው የምኖረው።

- ውበት ገንዘብና ጤንነት እያለሽ የዚህ ሀዘንና ጭንቀት መንስኤ ምንድነው ?

- አላውቅም። ምናልባት የምመራው ትርጉም አልባ ኑሮ ይሆናል፣ሕይወቴ ፈጽሞ ትርጉም የለሽ የሆነ የከንቱነት ሕይወት ነው።

- ሕይወትሽ ትርጉም እንዲኖረው ለማድረግ ጥረት ታደርጊያለሽ ? ወይስ ጉዳዩ አያሳስብሽም ?

- አይደለም፣እኔ መልሱን ለማግኘት ምንም ብቃት የለኝም። መልስ ማለት ደስተኝነት ማለት ነው፣ያ ደግሞ እንደኔ ላለ የሚገባ ነገር አይደለም

- ለምን ተገቢሽ አይሆንም ?

- እኔ ቱሪስቶች የሚጫወቱበትና እኔም ለጊዜያዊ ደስታ የምጫወትባቸው ቆንጆ አሻንጉሊት እንጂ ሌላ አይደለሁም።

- ሌላ ሰው ሳይሆን እኔ እየፈለኩሽ መሆኔን ስታውቂ ለምን ደስ አለሽ ?

- ባንተ ላይ ጫወታዬ ስለከሸፈብኝና በዚህ ረገድ ሽንፈት ፈጽሞ አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ብቻ ነው።

- ለምን ስፈልግሽ እንደነበረ ታውቂያለሽ ?

- አላውቅም፣ፈገግ አለችና ፡- ይህን ጥያቄ ልጠይቅሽ ነው የፈለኩሽ እንዳትለኝ ብቻ? !

- አይደለም፣ለዚህ እንኳ አይደለም። ባለቤቴ ከሌላ ወንድ ጋር ክህደት ፈጽማብኛለች ብዬ በመጠራጠሬ ካንቺ ጋር በመዝናናት ልበቀላት ፈልጌ ነው።

- እህህ፣እኔ የመጫወቻ አሻንጉሊት ነኝ ብየህ የለ ! ባለቤትህን በመሰሪነት በኔ ልትበቀል ነው ማለት ነዋ፣የኔ ዝቅጠት እስከዚህ ድረስ ነው ማለት ነዋ ? !

- አዝናለሁ፣አንቺኮ እጅግ በጣም ውብና ማራኪ ቆንጆ ነሽ፣ግና መርሆዬ መልካም ጸባዬንና ስነ ምግባሬን የሚጻረር ነገር እንዳልፈጽም ያግደኝ ስለነበረ ብቻ ነው።

- አሁን ግን ለመበቀል ስትል መርሆዎችህን ረስተሃል ማለት ነዋ ! ወይኔ በሰው ዓይን ይህን ያህል ውዳቂ ርካሽ ነኝ ማለት ነው !

- እኔ አንቺን ለማዋረድ አልፈለኩም፣ግን ይኸ የተሰማራሽበት ሥራ ነው።

- ውሸት አልተናገርክም ! የሰው ልጅ አንዳንድ ጊዜ ራሱን ቆም ብሎ አይመለከትም፣በዚህ ሥራ ላይ ከተሰማራሁ ሁለት ዓመት የሞላኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ራሴን አቅርቤለት እምቢ ያለኝ ወንድ አልነበረም። መጀመሪያ ላይ ለውበቴ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት በመግለጽ ሲቀባጥሩ ጉዳያቸውን ጨርሰው ለመሄድ ስነሳ በሚናገሩት ቃላትና በሚፈጽሙት ድርጊት ውርደቴና ዝቅጠቴ ምን ያህል እንደሆነ ሲሰማኝ ኖሯል . . ይህን በቀጥታ የሚገልጽልኝና ራሴን በራሴ እንድጋፈጥ የሚያደርገኝ ሰው ሲያጋጥመኝ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው።

 

- ይቅርታ . . አንቺን ለማዋረድ ወይም ስሜትሽን ለመጉዳት ፈልጌ አለመሆኑን ደግሜ ደጋግሜ ላረጋግጥልሽ እፈልጋለሁ።

- ምናልባት ሊሆን ይችላል . . ይሁን እንጂ እውነታው ይኸው ነው !

- ምን ማለትሽ ነው?

- አንዳንድ ጊዜ ከገዛ ራሳችን እንሸሻለን፣ እውነተኛውን ማንነታችንን ባለበት ሁኔታ ማየትን እንፈራለን።

- አልገባኝም !

ጆርጅ እጁን ዘርግቶ እጇን ያዝ አደርጎ ወደራሱ ሊስባት ሲሞክር፣ቀስ ብላ እጇን አላቀቀች። ዓይኖቿ አነቡና እንዲህ አለች

- አልባሌነት፣ከንቱነትና ከሕይወት ሽሽት የፈለገውን ያህል ጀግንነት ቢመስሉ መናጢነት ናቸው።

- ይህን ተይውና በተናገርኩት ነገር ይቅርታ አድርጊልኝ።

- እህህ፣ሚስትህን በኔ ለመበቀል ብለህ መርሆዎችህን አሽቀንጥረህ ትጥላቸዋለህ፣እስከዚህ ድረስ ወራዳ ነኝ ማለት ነው? !

- ምንድነው የምትፈልጊው? ወደ ክፍሌ ወጥተን ከሀዘናችንና ከውስጣዊ ጭንቀታችን ለመሸሸግ አብረን እንድንዝናና አትፈልጊም ማለት ነው?

- አዎ፣አሁን እኔ በተራዬ እምቢ ብያለሁ።

- ሃይማኖትሽ ምንድነው?

- ሃይማኖት የለኝም፣ትክክለኛ ሃይማኖት የሚከተል ሃይማኖተኛ ሰው እኔ የምሰራውን ነገር ይሰራል?

- ባለቤቴ ሃይማኖተኛ ነች፣ከሌላ ወንድ ጋር ክህደት ትፈጽምብኛለች የሚል ጥርጣሬ አለኝ !

- ጥርጣሬና ግምትህ ያለ ቦታው ነው፣አሊያም እርሷ ሃይማኖተኛ ሳትሆን ዋሾ አስመሳይ ናት፤ወይም የተሳሳተና የተዛባ ሃይማኖት ትከተላለች ማለት ነው። የሚያየኝና የሚጠይቀኝ አምላክ እያለኝ ቁጭ ብዬ ወንዶችን የማጠምድ ይመስለሃል? . . በነገራችን ላይ አባትና እናቴ ቡድሂስቶች ናቸው፣እኔ ግን እርስ በርሱ የሚቃረን በመሆኑና በአስቀያሚ መደባዊነቱ ምክንያት ቡድሂዝምን እርግፍ አድርጌ በመተው ሃይማኖት የለሽ ሆኜያለሁ።

- ስለ አያቶሽ ሃይማኖት እንዴት እንዲህ ትናገሪያለሽ?

- ቡድሂዝም ሃይማኖታችን ነው እንደፈለግን እንጨምርበታል፣ እንቀንስበታለን፣እናሻሽለዋለን። ስለዚህም ከፈለክ ሃይማኖት የለሽነትን አዲሱ የቡድሂዝም ማሻሻያ አድርገህ መውሰድ ትችላለህ ! ብዙዎቹ አዳዲስ ፋሽኖች በነባሩ ሃይማኖት ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ናቸው። ፈጠራ በመጥፎ ጎኑ ቢሆንም እንኳ ድንበር የለውም . . አሁን ሆቴሉን ለቅቄ እሄዳለሁ፣ምናልባትም ሁለተኛ ወደዚህ አልመለስም።

- ለምንድነው የማትመለሺው?

- ለሕይወቴ ትርጉም የሚሰጠኝና ራሴን እንዳከብር የሚያደርገኝ ምክንያት እስከማገኝ ድረስ አልመለስም፤ዳግም አመሰግነሃለሁ።

- ወዴት ትሄጅያለሽ ?

ኦርሜላ ተነስታ ወጣች፣ለጥያቄው መልስ አልሰጠችም።

ድክመት . . ! (4)

ጆርጅ የማይክል ጥሪ ሲያቃጭል ከእንቅልፉ አርፍዶ ተነሳ . . ድካም በተሞላበት ድምጽ ጥሪውን ተቀበለ . .

- እስካሁን ተኝተሃል? ምን ሆነሃል? ትተኛለህ አርፍደህ ትነሳለህ፣ከካኽ ነው የተማርከው?

- እባክህን ይህን ተወኝና ሕንድ ውስጥ አንድ ቀን ተኩል ቀርቶኛል፣ምንትመክረኛለህ?

- አያሌ መናፈሻዎች፣አብያተ ክርስቲያናት፣ቤተመቅደሶች፣ ሙዝየሞችና ገበያዎች፣ . . ይገኛሉ። የቱን ነው የምትፈልገው?

- አብያተ ክርስቲያናትንና ቤተ መቅደሶችን።

- የቅዱስ ጄምስን ቤተክርስቲያን መጎብኘት አትርሳ፣በጣም ታዋቂና ማራኪ ቤተ ክርስቲያ ነው።

- የሙስሊሞች፣ የሕንዱዎችና የሌሎች የአምልኮ ቦታዎችስ የሉም?

- እኔ ባልወደውም ግንባታው ስድስት ዓመታት የፈጀው ታላቁ የደልሂ ዐቢይ መስጊድም ኪነ ሕንጻው እጅግ ግሩም ነው።

- አመሰግናለሁ፣ቁርሴን በልቼ እነዚህን ሁለት መዳረሻዎች እጎበኛለሁ።

- ከቁርሱ ላይ ከመነሳትህ በፊት ከሆቴሉ እደርሳለሁ።

- አትልፋ፣ ታክሲ እይዛለሁ።

- ኣይ፣የውል ስምምነት ፊርማውን ያጠናቀቅን በመሆኑ ይህ ጉቦ አይደለም፣ከግማሽ ሰዓት በኋላ አንተ ዘንድ ነኝ፣ደህና ሁን።

ጆርጅ፣በሚስቱ
ላይ
ያደረበትን
ጥርጣሬ
ለመርሳትና ጥርጣሬውን የሚቀሰቅስበትን ከኦርሜላ ጋር ያደረገውን ምልልስ ለመዘናጋት እየሞከረ ቁርሱን በልቶ ተነሳ። ወዲያውኑ ማይክል ደውሎ እንግዳ መቀበያ ውስጥ እየጠበቀው መሆኑን ነገረው። የቀረውን ሻይ ጨለጠና ወደ ማይክል አመራ . . ሰላምታ ተለዋውጠው ወደ መኪና ገቡና ወደ ቤተክርስቲያኑ አመሩ።

- ትናንት ከሕንዱው የሬስቶራንት ሰራተኛ ጋር ስነጋገር አንተን አስታውሼህ ነበር።

- ሕንዱው እኔን እንድታስታውስ እንዴት አደረገህ?

- አህ፣ስለ ቡድሂስቷ ጂዮስቲና የተናገርከው ትዝ አለኝ። ከዚህ ለበለጠ ጊዜ ከርሷ ጋር ቁጭ ብለህ ኖሮ ሁለተኛ ወደ ሕንድ ለመመለስ አታስብም ነበር፣ብለሀኝ ነበር !

- አህ፣ትክክል . . ትክክል ነው፣እነዚህ ሃይማኖቶች ሰዎች በስልጣኔና በዕውቀት እጅግ ኋላ ቀር በነበሩበት ዘመን የፈጠሯቸው ናቸው። እያንዳንዱ ሃይማኖት የታለመው አንድ የተወሰነ ችግር ለመፍታት ወይም የተወሰኑ መደቦችን ጥቅም ለማስከበር ነበር። ዛሬ ላይ ሲታዩ ግን የተሻሻሉ አዳዲስ እትሞች ቢሯቸውም . . የዘቀጡ ናቸው። እነዚህን ሃይማኖቶች ወዲያ በላቸውና ከአፍታ በኋላ የምንደርስበትን የቅዱስ ጄምስ ቤተክርስቲያን ላስተዋውቅህ። የታነጸው በ1836 በጄምስ ሰክነር ነበር። በቀጠናው ጥንታዊና ልዩ የሆነ የስነ ሕንጻ ጥበብ የሚስተዋልበት ሲሆን አደባባዩም ከውብ አደባባዮች አንዱ ነው።

- በአካባቢው ጥንታዊ የሆነ ቀዳሚ ቤተክርስቲያን ነው? !

- አዎ፣ከ200 እስከ 300 ዓመታት አካባቢ ይሆነዋል።

- ከ300 ዓመታት በፊት ሕንድ ውስጥ ክርስትና አልነበረም? !

- ክርስትና ወደ ሕንድ የደረሰው በሁለት መንገድ ነው። አንደኛው በቶማስ አማካይነት በአንደኛው ምእተ ዓመት ሲሆን፣ቶማስ በዮሐንስ ወንጌል ከአስራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነው። ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ከ1500 እስከ 1975 ባሉት ዓመታት በምዕራባውያን ዘመቻዎች አማካይነት ነው። በሕንድ ውስጥ ከሕንዱና ከእስላም ቀጥሎ ሦስተኛው ሃይማኖት ነው። የክርስቲያኖች ቁጥር በ24 ሚሊዮን ይገመታል።

- ብቻ ! ከሕንድ የሕዝብ ቁጥር አንጻር ትንሽ ነው።

- ልክ ነው፣ክርስቲያኖች ከጠቅላላው ሕዝብ 2.3% ናቸው። ሕንዱዎች ክርስትና ከውጭ በገንዘብ ይጫንብናል ብለው ስለሚያስቡ በዚህ አነስተኛ ቁጥር ላይ እንኳ በቁጣ የተሞሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ያካሄዱበታል።

- አንድን ሃይማኖት በገንዘብ ኃይል በሰዎች ላይ መጫን ተገቢ ነው ?

- ኣሀ፣በተወሰነ ደረጃ ተገቢ ነው፣ሰዎችን ከበሰበሱ የሕንዱ እምነቶች ነጻ እስክናደርጋቸው ተገቢ ይሆናል።

ከቤተክርስቲያኑ
ደርሰው
የኪነ
ሕንጻ
ውበቱን ሥዕሎቹን፣ ቅርጻቅርጾቹን፣ጉልላቶቹን እየተመለከቱ ማድነቅ ጀመሩ። በእርግጥም በጣም የሚማርክ ነበር። ይሁን እንጂ ለጉብኝት የተዘጋጀ ታሪካዊ ቅርስ ብቻ ይመስል፣የማምለኪያ ስፍራነቱን የሚያሳይ ምንም ዓይነት የአምልኮ ገጽታ አይታይበትም። ማይክል ሁሉንም ነገር ከፍ ባለ የደስታ ስሜት ለጆርጅ ሲያስረዳ ቆይቶ ጉብኝቱ ተጠናቀቀና ለመሄድ ወደ መኪና ሲገቡ

- እንዴት አገኘኸው ? አለው።

- በእውነት ግሩም ድንቅ ነው።

- ብየህ አልነበረም ? አሁን ወዴት ነው የምንሄደው ?

- ወደ ደልሂ ዐቢይ መስጊድ ለመሄድ ነው የተስማማነው።

- መልካም ! ቦታውን እኔ ባልወደውም፣ፍላጎትህን ለማክበር ይሁን።

- ለምንድነው የማትወደው ?

- ሙስሊሞች ጨካኝ አረመኔዎች ናቸው።

- እንዴት ማለት ? ሰዎችን በኃይል ወደ እስላም እንዲገቡ ያስገድዳሉ ?

- እውነቱን ለመናገር ወደ አረመኔያዊ ሃይማኖታቸው እንዲገባ ማንንም አላስገደዱም።

- ታዲያ እንደክርስትና በገንዘብ ያታልሏቸዋል ማለት ነው? !

- ማለት የፈለከው ይገባኛል፣ግን ይህንንም አያደርጉም።

- ታዲያ ሰዎች ወደዚህ ሃይማኖት የሚገቡት እንዴት ነው ?

- አህ . . ሰዎች ይህን ሃይማኖት መጀመሪያ የተቀበሉት፣ ለንግድ ወደ ሕንድ ከመጡት ዐረቦች ነበር።

- ማለትም ሰዎች እስላምን የተቀበሉት ወዶና ፈገልገውት እንጂ ተገደው አልነበረም ማለት ነው !

- አዝናለሁ፣ይህ እውነት ነው። ሰዎችን ማታለልና ማጭበርበር ቀላል ሳይሆን አልቀረም። ከዐረብ ነጋዴዎች ጋር መገናኘት በጀመሩበት ጊዜ ከአስቀያሚው የሕንዱ መደባዊነት በመሸሽ ወደ እስላም ይገቡ ነበር። ከዚያ በኋላ በወራሪነት መጡ።

- በወራሪነት? !

- አዎ፣ከዘመቻዎቹ የመጀመሪያው በ700 ዓመተ ልደት አካባቢ ሙሐመድ ብን አልቃሲም አስሠቀፊ በሚባል ግለሰብ የተመራ ነበር።

- ከአንድ ሺ ሦስት መቶ ዓመታት ጀምሮ ማለት ነው !

- እየተበራከቱ መጥተው በሕንድ ሁለተኛው ሃይማኖት ለመሆን ቻሉ።

- ቁጥራቸው ምን ያህል ይሆናል ?

- ቁጥራቸው ከ180 ሚሊዮን ወይም ከሕዝቡ 14.5% ይበልጣል።

- ትልቅ ቁጥር ነው ! ይህ ማለት ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ባይገነጠሉ ኖሮ ሙስሊሞች በሕንድ አብላጫውን ቁጥር ይይዙ ነበር ማለት ነው? !

- ልክ ነው፣በሕንዱዎች እንጨቆናለን በማለታቸው ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ተጠናክረው በፓኪስታን መገንጠል ተደመደመ። ፈገግ ብሎ ቀጠለና ፦ ለኛ የሚሻለው ይህ ነው። መስሊሞች ከ1001 ዓመተ ልደት ጀምሮ ለ300 ዓመታት ያህል ሕንድን ገዝተዋል።

- በዚህ ጊዜ ውስጥ ሰዎች እስላምን እንዲቀበሉ አስገድደዋል ?

- አላስገደዱም። ግን ግፈኞች ነበሩ፣በድሆችና በደካሞች ጉልበት ታላላቅ ድንቅ ሕንጻዎችን ገንብተዋል።

- ታጅ መሐልን ስንጎበኝ ሙጢዕ አረሕማን ይህን አንስቶልኝ ነበር !

- ይህ የሙጢዕን ሚዘናዊነት ያመለክታል። ሃማኖታቸውን እንዲቀበሉ ባያስገድዱም በሕዝቡ ላይ በደል ፈጽመዋል። በእርግጥ ሕንድን የገዙት ስርወ መንግሥታት ሁሉ ግፍና ጭቆና ፈጽመዋል፣ምናልባትም ሕንድን ከገዙት ሁሉ የሙስሊሞቹ አገዛዝ የተሻለ ፍትሓዊነት የነበረው መሆኑን መግለጽ ሚዘናዊነት ነው። መንግስታቸውን ያስወገዱት የተለየ ዓይነት ምዝበራና አረመኔነት በነበረውና የምሠራቅ ሕንድ ኩባንያ በሚል ሽፋን ወራሪዎቹ እንግሊዞች ነበሩ። በእንግሊዞቹ ቅኝ አገዛዝ ላይ ሕንዱዎችና ሙስሊሞች በጋራ አምጸዋል።

ሕንዱዎች የሙስሊሞችን አገዛዝ ይወዱ ነበር ማለት ነው ?

- እህህ፣እያዘንኩ አዎ ይወዱ ነበር። ሁሉም የሙስሊም ገዥዎች ግፈኞች አልነበሩም፣ግፉ የታየው በመጨረሻው የአገዛዝ ዘመናቸው ነበር። ግፍ ይፈጽሙ የነበሩ ሙስሊም ገዥዎችም ቢሆኑ ከእንግሊዞቹ የምስራቅ ሕንድ ኩባንያ ግፍና አስከፊ ምዝበራ ጋር ሲነጻጸሩ ፍትሐዊ ገዥዎች ነበሩ . . ይህ ቅር እንደማያሰኝህ ተስፋ አደርጋለሁ።

- ታሪክ መነገር ያለበት እንዳለ ነው እንጂ እኛ በምንፈልገው መንገድ ተቀነባብሮ አይደለም።

- እንግሊዞች ሙስሊሙን ንጉሥ ማርከው ልጆቹን ከገደሉ በኋላ ጭንቅላቶቻቸውን ቆርጠው ምግብ ማዕድ ላይ እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስ፣በበእንግሊዞች ላይ የተነሳሳው ሕዝባዊ አመጽ ቀጠለ። ከዚያ በኋላ እስላማዊ ሃይማኖትን መዋጋት፣ትምህርቶቹን ማገድ፣የሕንድን ሀብት መመዝበር በሰፊው ተያያዙት።

- ምን ዓይነቱ ጭካኔና ኢሰብአዊነት ነው . . የሚዘመርለት ሰብአዊ መብት የትገባ? !

- ስለ ሰብአዊ መብት የምንሰማው በጉባኤዎች ላይ፣ በስብሰባ አደራሾች ውስጥና በሕትመተች ላይ ብቻ ነው። ተግባርና ተጨባጭ እውነታው ግን ሌላ ነገር ነው። ዋናው በእንግሊዞች ላይ በተደረገው አመጽ ዋነኛ የመሰባሰቢያ ማእከል ወደ ነበረው ትልቁ መስጊድ ተቃርበናል። በዚህ መስጊድ ነው የሙስሊም ሊቃውንት በእንግሊዞች ላይ የጅሃድ ፈትዋ ያስተላለፉትና በፈትዋው መሰረት ሕዝቡ የተንቀሳቀሰው . . የጅሃን ነማ ወይም ጃማ መስጊድ ተብሎ ይጠራል። ግንባታው ረዥም ጊዜ የፈጀ ሲሆን የተጠናቀቀው በ1656 ዓመተ ልደት ነው። እንዲገነባ ያዘዘው መንጎሊያዊው ንጉሥ ነገስት ሻህ ጂሃን ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 25000 ሰጋጆችን የሚይዝ የኤስያ ክፍለ አህጉር ትልቁ መስጊድ ነው ።

- ጥንታዊና ታሪካዊ መስጊድ ነው ማለት ነው !

- ምናልባት ይሆናል፣በመንጎላዊ ስነ ሕንጻ ሞዴል የተገነባና ሦስት ጉልላቶች ያሉት ነው። ይኸው ከፊትህ የሚታየው ነው፣ ደርሰናል።

ወረዱና የኪነ ሕንጻ ውበቱን በአድናቆት ተመለከቱ . . እሱን ላለማስከፋት ብሎ እንጂ በማይክል ፊት ላይ ያለ መደሰት ስሜት ይስተዋል ስለነበረ፣ጆርጅ የተባበረውን የማይክል ስሜት ለመጠበቅ ሲል የመስጊዱን ጉብኝት ቶሎ አጠናቀቀ።

- ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ትፈልጋለህ ?

- አመሰግናለሁ፣አሁን ጊዜው ትንሽ የሄደ ይመስለኛል።

- ግና ሚዘናዊ አልሆንክም !

- ለምን ?

- ቤተክርስቲያኑን አየህ፣ መስጊድም አየህ፣ የሕንዱዎችን ቤተመቅደስ ግን አላየህም !

- ማየት እወድ ነበር፣ግን ብዙ አለፋሁህ።

- ቤተመቅደሱ ከምንሄድበት መንገድ ቅርብ ነው፣ማየት ትፈልጋለህ ?

- በትክክል፣ከሥራ የማያስተጓጉልህ ካልሆነ ደስ ይለኛል። ጉዞዬ ነገ ስለሆነ ካሁን በኋላ ጓዜን ስለማዘጋጅ ብዙም አልወጣም።

- የቤተ መቅደሱ ስም አክሻርዳም ነው። በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ያገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ይጎበኙታል። በደልሂ ውስጥ ትልቁ የሕንዱ ቤተ መቅደስ ነው። ግንባታው በ2000 ተጀምሮ በ2005 ነው የተጠናቀቀው። አዲስ ቤተ መቅደስ ሲሆን የኪነ ሕንጻ ውበቱ ድንቅ ነው። በግድግዳዎቹ ላይ የአማልክቶቻቸው ምስሎች ተቀርጸውበታል።

- እንስሳቱና ሌሎቹም አማልክት ተቀርጸውበታል ?

- አህ፣አዎ እንስሳትንና ዘፋኞችን የመሳሰሉ ሁሉም አማልክት የተቀረጹበትና የ20000 አማልክት ቅርጾች ያሉበት ቤተ መቅደስ ነው። ሰው ሰራሽ ምድራዊ ሃይማኖቶች አስቂኝ ናቸው ብየህ የለም ? እንደሚመስለኝ ደስ የሚላቸውን ወይም የሚገርማቸውን ነገር ባዩ ቁጥር አምላክ ያደርጉታል። የምትገኘው በድንቃድንቆቹ አገር ነው። አይጦችን ቤተ መቅደስ ሰርተውላቸው የሚያመልኩ አሉ። እባብና ዘንዶዎችን ቤተ መቅደስ ሰርተውላቸው የሚያመልኩ አሉ። ለማንኛውም ወደ ሕንዱው ቤተ መቅደስ ደርሰናል።

- በጣም ውብ የሆነ ሕንጻ ይመስላል።

- ልክ ነህ። የተገነባው በጽጌሬዳማ የአሸዋ ድንጋይ (ሳንድስቶን) ሲሆን ብረትም ሆነ ኮንክሪት አገልግሎት ላይ አልዋለም። በተለያዩ የተረቀረጹ ጌጦች በከፍተኛ ደረጃ አጊጧል። እንዳይረፍድብህ ቶሎ እንውረድ።

በውስጡ የታጨቁት የአማልክት ቅርጻቅርጾች ብዛት ቢያሸማቅቁትም ጆርጅ በሕንጻው ውበት በጣም ተደንቋል . . በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ፈጣን ጉብኝት አድርገው ወጡ። በመልስ ገዟቸው ላይ፦
 

- ሕንጻው ግሩም ድንቅ የሚባል ነው፤ቅርጻቅርጾቹና ብዛታቸው ግን አስጠሊ ነው !

- ልክ ነው . . እውነትህን ነው።

- የገረመኝ ነገር ግን ቤተክርስቲያኑም ጭምር ቅርጻቅርጾች አሉበት። መስጊዱ ግን ምንም ምሥልም ሆነ ቅርጻቅርጽ የለበትም !

- የቤተክርስቲያኑ ምሥልና ቅርጻቅርጽ ግን የኢየሱስ እንጂ የእንስሳት አይደለም።

- አህ፣ ልክ ነህ። ለማንኛውም በጣም ነው የማመሰግነው፣ የዛሬው ጉብኝት እጅግ በጣም የተዋጣለት ነው።

በዛሬ የጉብኝት ፕሮግራሙ ድባብ ውስጥ ጆርጅ የካትሪናና የቶምን ጉዳይ ትንሽ የረሳ ከመሆኑም በላይ መጠነኛ የደስታና የመረጋጋት ስሜት ተሰምቶታል። ‹‹በዋነኛ ጉዳይህ ላይ አትኩር›› . . የሚለው የአደም ቃል ወለል ብሎ ታይቶታል። ይህ ጉብኝት ለርሱ ወደ ደስተኝነት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነበር። ሰው ሰራሽ ምድራዊ ሃይማኖቶች ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለመስጠት ፋይዳ የሌላቸው መሆኑ ግልጽ ሆኖለታል። የሌላቸውንና የማያውቁትን ነገር እንዴት ሆኖ ሊመልሱ ኖሯል? ሌላው ቀርቶ ወደሚፈልጉት ሃይማኖታዊ መረጋጋት ለመድረስ እንኳ ራሳቸውን እንደ ሁኔታውና እንደ አስፈላጊነቱ የሚያሻሽሉና የሚለዋውጡ ናቸው . .
ለአደም መልእክት የመላክ ሀሳብ መጣለትና ኮምፒውተሩን ከፈተ፦

‹‹ወዳጄ አደም . . ስለ ምክርህ አመሰግናለሁ፣ላልተገባ አነጋገሬ ይቅርታ አድርግልኝ።

አውነቱን ልንገርህና በምክርህ ብዙ ብዙ ተጠቅሜያለሁ። ሕሊናዬን ተቆጣጥሮ የነበረውን የብቀላ ፍላጎትም መርታት ችያለሁ። ትኩረቴን በዋነኛው ጉዳዬ ላይ በማድረጌ ሀሳቤ በንኡሳን ጉዳዮች ላይ ከመበታተን ድኗል። ሙሉውን ቀን በቁርጠኝነትና በጽናት በዚህ ላይ በማተኮሬ ያንተንና የሐኪሙን ጥያቄ በግልጽ መመለስ ችያለሁ። ምድራዊ ሃይማኖቶች ለየትኛውም ጥያቄ ምላሽ የላቸውም። እኛን ያልፈጠሩን ሰብአዊ ፍጡራን ሀሳቦች ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደሉምና ለምን እንደ ተፈጠርን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ? . . ምስጋናዬ በድጋሜ ይድረስህ። ነገ ወደዚያ ስለሚመለስ እንገናኛለን፣ አሁንም አመሰግናለሁ።

ወዳጅህ ጆርጅ።

ከዚያም በሳለፈው ቀንና ወደ ዐቢይ ግቡ ጉዞ በመጀመሩ ደስተኝነት እየተሰማው አልጋው ላይ በጀርባው ተንጋለለ . .

ድክመት . . ! (5)

ጆርጅ አማልዶ ከእንቅልፉ ተነሳና የሚያነቃቃ ሙቅ ሻወር ወሰደ . . ሰዓቱን ሲመለከት ወደ አይሮፕላን ማረፊያ ለመሄድ አራት ሰዓት ቀርቶታል። በቀሪው ጊዜ ምን ማድረግ እንደምችል አያለሁ፣መጀመሪያ ግን ቁርሴን ልብላ . .
ለቁርስ በተቀመጠበት ትናንት አነጋግሮት የነበረውን ሕንዱ አስተናጋጅ ካቡርን አየና ጠራው . .

- አቤት ጌታዬ ! ሠላም አደሩ?

- እንደምነህ፣ባለፈው ጊዜ አራዝሜብህ ነበር፣አሁንም መልካም ፈቃድህ ከሆነ ሌሎች ጥያቄዎች አሉኝ ?

- ችግር የለውም። ለሕንዱ ሃይማኖት ብዙ ትኩረት የሰጡ ይመስላል . . ይህ አዲሱ የምዕራባውያን ፋሽን ነው።

- ሕንዱይዚም ፋሽን ነው ?

- አዎ፣ሕንዱይዚምና ቡድሂዝም እናንተ ዘንድ በአውሮፓና በአሜሪካ ፋሽን ሆነዋል። በመሰረቱ ወደዚህ የሚመጡት ሰዎችን ወደ ግዑዝ መሳሪያነት ከለወጠው እርጉሙ ማቴሪያሊዝም ለመሸሽ ነው፡፡ ከግዑዝ ቁሳዊነት ሸሽተው የሆነ መንፈሳዊነትና ሞራላዊነትን ለመፈለግ እንጂ ስለ ሃይማኖቶቹ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም።

- ጥሩና ግልጽ ነው። እኔ ግን አንድ ጥያቄ ላቀርብልህ እፈልጋለሁ። አንተና ሕንዱዎችም በአጠቃላይ ደስተኞች ናችሁ ?

- ምናልባት ሰዎችን የሚጨቁኑና የሚመዘብሩ በራህማዎች፣ ናቸው ብዬ ባላስብም ደስተኞች ይሆኑ ይሆናል። እኔ ግን ከመደቦች አንጻር ከሾደሮች ማለትም ከአገልጋዮች መደብ ነኝ። እምነትን በተመለከተ እኛ ከሃይማኖታችንና ከአማልክታችን ብዛት፣ከዓለማዊ ሕይወትም ሆነ ከአምላክ ጭምር ነጻ በሆኑ መንፈሳዊ ሞራላዊ ክንውኖች ራሳችንን እናሸሻለን። ስለ ጋንዲ ሰምተህ አታውቅም ?

- ሰምቻለሁ፣ድንቅ ሰብእና ነበር።

- በሕንዱይዚም ላይ ማመጽ ፈልጎ አክራሪ ሕንዱዎች የገደሉት አመጺ ሰብእናም ነበር።

- ለምንድነው በገዛ ሃይማኖቱ ላይ የሚያምጸው ?

- ሃይማኖታችን እንዳለ ሆኖ እኩል ሆነን መኖር ስለማንችል ነው። ግን ይቅርታ ምናልባት - እንደ ፋሽኑ - በሕንዱይዝም ተማርከህ ከሆነ እያበላሸሁብህ እንዳልሆን።

- ሃይማኖትህን ለምን አልለወጥክም ?

- አባቴና እናቴ ሕንዱዎች ናቸው፣ሕንዱ ሆኜ ነው የተወለድኩት . . በመቀጠል ፈገግ አለና ፦ እኔም ሌላው ጋንዲ እንዳልሆን ማመጽ አልፈልግም።

- ይህችን የገንዘብ ስጦታ ተቀበለኝ፣ ጊዜህን ብዙ ተሻምቻለሁ።

- አመሰግናለሁ።

ወደ ክፍሉ ተመልሶ ሄደና ዕቃዎቹን መሰብሰብና ጓዙን ማዘጋጀት ጀመረ። ይህን በማድረግ ላይ እያለ ስልኩ አቃጨለና አነሳው፡፡ ከሪሙሏህ ነበር . .

- ጆርጅ እንደምነህ፣ከሪሙሏህ ነኝ።

- ሃሎ፣ከሪሙሏህ።

- ትናንት ሠላም ልልህ መጥቼ አላገኘሁህም። በተስማማነው መሰረት ሕንድ በሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ የተረጋገጠውን የውሉን ሰነድ እንድግዳ መቀበያ አስቀምጫለሁ። መቼ ነው የምትሳፈረው ?

- በጣም አመሰግናለሁ፣ልረሳው ነበር። አሁን እቀበለዋለሁ፣ ጉዞዬ ከሁለት ሰዓት በኋላ ነው . .

- ወደ አይሮፕላን ማረፊያ እንዳደርስህ ትፈልጋለህ ?

- አመሰግናለሁ። መኪና እንዲያዘጋጅልኝ ከሆቴሉ ጋር ተስማምቻለሁ።

- ይቅርታ፣ለንደን በሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ የተረጋገጠውን የውሉን ቅጂ እጠብቃለሁ፣ደህና ሁን።

ጆርጅ መነጋገሪያውን አስቀምጦ ወዲያውኑ ወደ እንግዳ መቀበያ ደወለና ወረቀቶቹን እንዲያመጡለት ጠየቀ . . መነጋገሪያውን አስቀምጦ አሰበ

ምንም መጥፎ ነገር ሳያይበት በከሪሙሏህ ውስጡ የማይደሰተው ለምን ይሆን
? እብን ላዴንን በመምሰሉ ምክንያት ይሆን
? ወይስ በድርድር ላይ ንቁና በጥበብ የተካነ በመሆኑ
? ወይስ ስለ አለቃው ስለ ካኽ በመናገሩ? ወይስ ገና ባላወቀው ሌላ ምክንያት ይሆን
? አስገራሜ የሆነ እንግዳ ስሜት ነው . . ምናልባት የለንደኑን ሜትሮ የባቡር ፍንዳታዎችን መርሳት አልቻለም። ምናልባት ደግሞ መገናኛ ብዙኃን በሳደሩበት ተጽእኖ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ አያስደስተኝም፣ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም . .
ከእንግዳ መቀበያ ክፍል የመጣው ወረቀት ሲደርስ ከነጎደበት የሀሳብ ዓለም ተመለሰ . . አገላብጦ አያቸው። በትክክል እንደፈገው ሆነው አገኛቸው። የቀረው ነገር ቢኖር ለንደን ቢገኘው የሕንድ ኤምባሲ እንዲረጋገጥ ማስደረግ ብቻ ነበር። ሰዓቱን ሲመለከት ወደ አይሮፕላን ማረፊያ የመሄጃ ሰዓት ደርሷል።
ለእንግዳ መቀበያ ክፍል ደወለና የመውጫ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁለትና ያልተጠበቀ ነገር ወይም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥመው፣ ቢቻል መኪናው ግማሽ ሰዓት አስቀድሞ እንዲዘጋጅለት ጠየቀ . .
ወደ አይሮፕላን ማረፊያው ሲጓዝ በመኪናው መስኮት የደልሂን መንገዶች እየቃኘ ነበር። ጎዳናዎቹ በቅርጻቅርጾች የተሞሉ ናቸው። ድንጋዮችን ወይም ሰብአዊ ፍጡራንን ማምለክም ሆነ ለጥያቄዎቼ ከነሱ ምላሽ ማግኘት ሊሆን የማችል ጉዳይ ነው . . ወደ መጀመሪያው የደስተኝነት መንገድ ለመራችኝ ሕንድ ምስጋና ይድረስ። ካሳለፍኳቸው ነገሮች ሁሉ ጋር አስደሳች ጉዞ ነበር . . እያለ ከራሱ ጋር እያወራ ተጓዘ።