ዴል ካርኒጄ

quotes:
  • በአላህ ታገዝ
  • ‹‹ያለ ረዳትና ያለ ደጋፊ ብቻቸውን የሕይወትን ፍልሚያ ከሚጋፈጡ፣ መለኮታዊ ረድኤት እገዛን ቢለምኑ ኖሮ ምናልባት ካሁኗ አፍታ ጀምሮ በአእምሮ ሕሙማን ሆስፒታሎች ውስጥ በመጯጯህ ላይ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሰቃዮችን ማደን ይቻል ይሆናል።››


  • ሃይማኖተኛና ሕሙማን
  • ‹‹ሰዎች ስለ ሳይንስና ሃይማኖት መራራቅ እንጂ ሌላ ነገር የማያወሩበት ጊዜ ትዝ ይለኛል። ይህ ክርክር ግን ላይመለስ አብቅቷል። በጣም አዲስ የሆነው የስነልቦና ሕክምና ሳይንስ በሃይማኖት መርህ ያበስራል፤ለምን?! የስነልቦና ሐኪሞች ጠንካራ እምነት፣ሃይማኖትና ጸሎትን አጥብቆ መያዝ፣ጭንቀትን፣ስጋትንና ውጥረትን ለማስወገድና ከግማሽ በላይ የሚሆኑ በሽታዎችን ለመፈወስ አመርቂ ውጤት እንዳላቸው ስለሚገነዘቡ ነው። ዶክተር ኤ፣ኤ፣ብሬል ‹ሃይማኖተኛ ሰው በእርግጥ በስነልቦና በሽታ ፈጽሞ አይጠቃም› እስከማለት ደርሰዋል።››


  • ጥልቅ ሁን
  • ፈላስፋው ፍራንሲስ ቢኮን ፦ ‹‹ጥቂቱ ፍልስፍና ሰውን ወደ ኤቲዝም ሲቀርብ፣የፍልስፍና ጥልቅ ዕውቀት ግን ወደ ሃይማኖት ይመልሰዋል›› ማለቱ በጣም ትክክል ነበር።


  • ሃይማኖተኝነት ለበሽታዎች ፈውስ ነው
  • ‹‹ጠንካራ እምነትና ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝ፣ጭንቀትን፣ስጋትንና ውጥረትን ለማስወገድና እነዚህን በሽታዎች ለመፈወስ አመርቂ ውጤት እንዳላቸው የስነልቦና ሐኪሞች ይገነዘባሉ።››


  • የመንፈስ እርካታ
  • ‹‹ልክ ኤሌክትሪክ፣ጥሩ ምግብና ንጹሕ ውሃ የሚሰጠኝ ጸጋ እንደሚያሳስበኝ ሁሉ፣እኔ አሁን የሚያሳስበኝ ሃይማኖት ለኔ የሚሰጠው ጸጋ ነው። እነዚያ የተመቻቸ ሕይወት እንድንኖር ያግዙናል፤ሃይማኖት ግን ከዚህ የበለጠ ነው የሚሰጠኝ፤የመንፈስ እርካታ ያጎናጽፈኛል፤ወይም በዊልያም ጄምስ አነጋገር ‹ሕይወትን መኖር እቅጠል ዘንድ ጠንካራ ግፊት ይሰጠኛል› . . የተሟላና ጥልቀት ያለው፣የደስተኝነት፣የመታደልና የእርካታ ሕይወት። እምነት፣ተስፋና ጀግንነትነም ይመግበኛል። ፍርሃትን፣ስጋትንና ጭንቀትን ያባርርልኛል። ሕይወቴ ዓላማና ግብ እንዲኖረው ያደርገኛል። የደስተኝነትን ሰፊ አድማስም ይከፍትልኛል። በሕይወታችን ምድረበዳ ውስጥ ለምለም ኩሬ ለመፍጠርም ያግዘኛል።››




Tags: