ዲቦ ራፖርተር

quotes:
  • አላህ ሰውን ክቡር ፍጡር ማድረጉ
  • ‹‹የአላህ ሕግ የሆነው እስላም በዙሪያችን ስላለው ተፈጥሮ ግልጽ ሆኖ እናገኘዋለን። ተራሮች፣ባሕሮች፣ፕላኔቶችና ከዋክብት በአላህ ትእዛዝ ብቻ ይሄዳሉ፤በጉዞአቸውም በርሱ ብቻ ይመራሉ። ሁሉም ለፈጣሪያቸው ትእዛዝ ተገዥዎች ናቸው። በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለችው እያንዳንዷ አቶም ግኡዝ አካላትን ጨምሮ እንደዚሁ የግድ ለርሱ ታዛዦችና ተገዥዎች ናቸው። የሰው ልጅ ግን አላህ የመምረጥ ነጻነት የሰጠው በመሆኑ ከዚህ አጠቃላይ ሕግ ለየት ይላል። እናም ለአላህ ትእዛዛት የመገዛት ወይም የራሱን ሕግ ለገዛ ራሱ ደንግጎ በመረጠው እምነቱ መሰረት የመጓዝ ምርጫ አለው። የሚያሳዝነው ግን በአብዛኛው ሁኔታ ሁለተኛውን መንገድ የመረጠ መሆኑ ነው።››


  • ከነብይነት ማረጋጋጫ ማስረጃዎች አንዱ ነው
  • ‹‹በማይም ሕህብረተሰብ ውስጥ ያደገውና ያልተማረው ሰው ሙሐመድ፣ዘመናዊው ሳይንስ እስከ ዛሬው ዘመናችን ድረስ ለማግኘት ጥረት የሚያደርግባቸውንና ቅዱስ ቁርኣን የገለጻቸውን የዩኒቨርስ ተአምራት እንዴት ማወቅ ቻለ?! ስለዚህም ይህ ንግግር የግድ የኃያሉ አላህ ቃል መሆን ይኖርበታል።››


  • የጠራ ስረ መሰረት
  • ‹‹እስላም ከሙሐመድ ዘንድ የሆነ አዲስ ሃይማኖት አይደለም። አልመሲሕ [የአላህ ሰላም በርሱ ላይ ይሁን] ወደ ሰማይ ካረገ ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ምድር ላይ በተሰራጨ ጊዜ ቀደም ሲል በነበሩት መለኮታዊ ሃይማኖቶች ውስጥ የሰፈረውን መለኮታዊ ራእይ ዳግም አሰራጨ፤ወደ ጠራ ጥንታዊ ስረ መሰረቱም መለሰው። እግዚአብሔር የላካቸው ነቢያት ሁሉ መስሊሞች ነበሩ፤መልክቶቻቸውም ሁሌም አንድ ነበሩ።››


  • የአላህ ቃል
  • ‹‹ቅዱስ ቁርኣንን አንብቤ ስጨርስ፣ይህ ፍጥረትን ለሚመለከቱና ለሌሎቹም ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሾችን ያካተተ እውነታ ነው የሚል ስሜት ውስጤን አጥለቀለቀው። በተቀሩት ሃይማኖታዊ መጽሐፎች ውስጥ እርስ በርስ ሲጣረሱ የምናገኛቸውን ሁነቶች ሎጂካዊ በሆነ መንገድ ያቀርብልናል። ሁነቶቹ ቁርኣን ውስጥ ሲቀርቡ ድንቅ በሆነ ቅንጅትና መጣጣም፣እውነታው ይህ ስለመሆኑና ይህ ንግግር የግድ ከአላህ ዘንድ ብቻ የተላለፈ ስለመሆኑ ለጥርጣሬ ምንም ቦታ በማይተው ቁርጥ ባለ የአቀራረብ ስልት ነው።››


  • የዩኒቨርስ ተአምራት
  • ‹‹ያልተማረውና በማይማን አካባቢ ውስጥ ያደገው ሰው ሙሐመድ፣ቅዱስ ቁርኣን የገለጸቸውንና ዘመናዊው ሳይንስ እስከ ዛሬው ዘመናችን ድረስ ሊደርስባቸው የሚጥረውን የዩኒቨርስ ተአምራት እንዴት ማወቅ ቻለ?! እናም ይህ ንግግር የግድ የአላህ (ሱ.ወ.) ንግግር መሆን ይኖርበታል።››




Tags: