የማሳረጊያው ቃል

የማሳረጊያው ቃል

ሦስቱ ወዳጆች እንግዳ ማረፊያ ማእከሉ መግቢያ በር ላይ በቀጠሯቸው መሠረት ተገናኙ . . ራሽድ ‹‹መቶ ታላላቅ ሕያው የታሪክ ሰዎች - ሙሐመድ የታላቆቹ ታላቅ›› በሚል ርእስ የታተመው መጽሐፍ አዲስ እትም ወደሚገኝበት መጽሐፍት መሸጫ ይዟቸው ሄደ። በጋዜጦች መሸጫ ጥጉ ቆሞ ርእሶችን ያነብ የነበረው ማይክል በድንገት ራሽድን በመጣራት እንዲህ አለው፦

ራሽድ . . ይህን አሰገራሚ ርእስ አንብብማ . . ዛሬ ከምናደርገው ውይይት ጋር ተያያዥነት አለው . . ‹‹እስራኤል ውስጥ በሚገኝ አንድ ቤተ መጽሐፍ ውስጥ በእጅ የተጻፈ ጥንታዊ የብራና ቁርኣን ተገኘ›› ይላል . .

ራሽድ፦ ጥንታዊ የብራና ጽሑፉ ወደ እስራኤሉ ቤተ መጽሐፍት እንዴት እንደ ደረሰ መጠየቅህ ነው? . . ይህን ዜና ትናንትና በአንድ ድረገጽ ላይ አንብቤያለሁ . . ይህ ጥንታዊ ቅርስ በአሜሪካ መራሹ ጦር ከተወረረች በኋላ ከዕራቅ የተሰረቀ መሆኑን አንዳንድ ትንተናዎች ያመለክታሉ።

ማይክል፦ አይደለም . . አይደለም . . ማለት የፈለግሁት ዛሬ በእጃችሁ ከሚገኘው ቁርኣን ጥንታዊነት ጋር ያለውን ግንኙነት፣ከቁርኣን ተአማኒነትና ከትክክለኛነቱ ጋር ምን ተያያዥነት እንዳለው ነው። ዜናው እንደሚለው ጽሑፉ ከ1200 ዓመታት ያህል በፊት የተጻፈ ነው፤ይህም የመጀመሪያው የቁርኣን ቅጂ በጽሑፍ ከተጠናቀረ ከ200 ዓመታት በኋላ ብቻ ሲሆን አሰደናቂ ዜና ነው።

ራሽድ፦ አንደኛ- ይህ እስካሁን ከተገኙት የቁርኣን ጥንታዊ ቅጂዎች በጣም ጥንታዊው አይደለም። ሩሲያውያን በዓለም ላይ በጣም ጥንታዊ የሆነው የቁርኣን ቅጂ በነርሱ እጅ እንደሚገኝ ይናገራሉ። ሩሲያዊው ተመራማሪ የፊም ሪድዋን ሆላንድ ውስጥ በተደረገ የካርቦን ጨረር ትንተና፣በእጃቸው የሚገኘው የቁርኣን ቅጂ ዘመኑ ስምንተኛውና ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሆኑን እንደሚያሳይ አረጋግጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ ግብጻውያን እጅግ ጥንታዊ የሆነው የቁርኣን ቅጂ እነርሱ ዘንድ በካይሮው የሑሰይን መሳለሚያ የሚገኘው ነው ይላሉ። የቅጂው ዕድሜ ወደ 1400 ዓመት የሚቃረብ ሲሆን፣በሦስተኛው ኸሊፋ በዑሥማን ብን ዐፋን  ትእዛዝ፣ቁርኣንን በቋሚነትና ወጥ በሆነ ሁኔታ ለማስጠበቅ ሲሉ እንዲጻፉ ከተደረጉት ስድስት መጽሐፎች አንዱ ነው።

በየመን ደግሞ በ1972 ሰንዓ የሚገኘው ታላቁ መስጊድ እድሳት ሲደረግለት በመጀመሪያው ኸሊፋ በአቡ በክር አስሲዲቅ ዘመን የተጻፈ ጥንታዊ የቁርኣን ቅጂ ነገኘቱን ይናገራሉ።

ተጽፈው ወደየአገሩ የተላኩ የቁርኣን ቅጂዎች ብዙ የነበሩ በመሆናቸው፣ይህ ሁሉ ትክክለኛ ሊሆን ይችላል።

ሁለተኛ- ዛሬ በሙስሊሞች እጅ የሚገኘው በነቢዩ ዘመን የነበረው ያው አንድና ተመሳሳይ ቅጂ መሆኑ በሃይማኖቶች ተመራማሪ ሊቃውንት ዘንድ የጸና እና የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ኦሪየንታሊስቶችም አምነው ይቀበሉታል፤ከአላህ ዘንድ የተላለፈ መሆኑን ግን አይቀበሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ዛሬ ባሉት በሁለቱም ኪዳኖቹ ታኣማኒነቱና ስረ መሰረቱ የተረጋገጠና ጸና አይደለም።

ፈረንሳዊው ኦሪየንታሊስትና የሕብረተሰብ ሳይንስ ሊቅ አርነስት ሬይናን ፦ ‹‹ቁርኣን ምንም ዓይነት መለዋወጥም ሆነ መዛባት አልደረሰበትም . . ›› ይላል።

አሁን መጽሐፉን ለመግዛት የመጣነው አሜሪካዊው ዶክተር ማይክል ሃርት ደግሞ ፦ ‹‹በሃይማኖቶች ታሪክ ውስጥ ቃላቱንና ፊደላቱን ሳይዛቡና ሳይታረሙ እንዳሉ ጠብቆ የቆየ ብቸኛ መጽሐፍ፣ሙሐመድ ያስተላለፈው ቁርኣን ብቻ ነው።›› ብሏል። ጀርመናዊው ባለቅኔ ጎቴህ ግን ከዚህ አልፎ በመሄድ ፦ ‹‹ቁርኣን የመጽሐፎች ሁሉ መጽሐፍ ነው፤እያንዳንዱ ሙስሊም እንደሚያምነው ነው እኔም በዚህ የማምነው›› ብሏል። ጎቴ በዚህ ብቻ ሳይወሰን ዕድሜው ሰባ ዓመት በሞላ ጊዜ ቅዱስ ቁርኣን ወደ ነቢዩ ሙሐመድ የወረደባትን ያችን የተቀደሰች ሌሌት በጽሞና እና በተመስጦ ለማክበር መቁረጡን በአደባባይ አውጇል።

ራጂቭ፦ ይህ የዛሬው ርእሳችን ነው . . ቁርኣን በእርግጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ ለመሆኑና እስላም ከሰማይ የመጣ መለኮታዊ ሃይማኖት ስለመሆኑ ማረጋገጫው ምንድነው?

ራሽድ፦ ከአላህ ዘንድ የተላለፈ ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን . . ዛሬ ያለው ብቸኛው ትክክለኛ ሃይማኖትም ጭምር ነው . .

ማይክል፦ በድምጻችን የመጽሐፍ ቤቱን ደንበኞች እንዳንረብሽ ወደዚያ ገለል እንበል።

ራጂቭ (ተያይዘው ለውይይት ወደተመደው ጥግ ሲያመሩ ራሽድን እያናገረ)፦ ያልከው ነገር ይሁንልህና ማረጋገጫው ምንድነው?!

ራሽድ፦ ጊዜው እስከበቃን ድረስ ማረጋገጫውን እሰጣችኋለሁ። እውነቱን ለመናገር ቁርኣን የአላህ ቃል እንጂ የሙሐመድ ቃል አይደለም። የሰውንና የዘመንን ወሰን ጥሶ የሚያልፈውን የአላህን ሁለንተናዊ ፍጹማዊ ዕውቀት የሚያሳየውን አንዳንድ ተአምራዊ ጎኖቹን አብራራላችኋለሁ።

ማይክል፦ እኛ የምናምንበትንና የተስማማንበትን ነው የምትነግረን። በዕውቀት በአእምሮና በምክንያት ላይ ብቻ ተንተርሰህ ንገረን።

ራሽድ፦ የአብያተ ክርስቲያናት ተከታዮች የሃይማኖታቸውን መጽሐፍ፣መጽሐፍ ቅዱስ ብለው ይጠራሉ። ቅድስና ደግሞ ከስህተትና ከእርስ በርስ መፋለስ ጋር ይጋጫል። የመጽሐፉ መዛባትና እርስ በርሱ መፋለስም ለአምላክነት ተገቢ ይሆን ዘንድ፣ከእንከንና ከጉድለት ሁሉ የጠራ ምሉእ መሆን ከሚገባው የእውነተኛው አምላክ ባሕርያት ጋር ይጋጫል . . ቤተክርስቲያ በሳይንስ ላይ ያላትን አቋምና፣የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ከሳይንስ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት በርሷና በሳይንቲስቶች መካከል ስለነበረው ትግል አላወራም። ግና በዚህ መስክ ቁርኣን ያለውን አቋም እንመልከት፦

ከዘመናችን ሙስሊም ዑለማእ አንዱ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱልመጂድ አዝዘንዳኒ፣በአሜሪካው የኖርዝ ዊስቶን ዩኒቨርሲቲ የሴቶች በሽታዎችና የስነ ተዋልዶ ፕሮፌሰር ከሆኑት ጆሊ ሳምሶን ጋር፣ስለ ጽንስ የመጀመሪያዎቹ የዕድገት ደረጃዎች፣ቁርኣን ሰው የሚጸነሰው ከሁለቱ የዘር ፍሬዎች ውሕደት በኋላ መሆኑን፣ከዚያ ቀጥሎ ያሉትን የሰው የጽንሰት ዕድገት ዝርዝር ጉዳዮችን፣የዓይን ቀለም፣ የቆዳ ቀለም፣የጸጉር ቀለም . . እንዴት እንደ አረጋገጠ ተነጋግረዋል። ዘመናዊው ሳይንስ የሰው ልጅ ጂኖች ዝርዝር ሳይጸነስ ገና የዘር ጠብታ ደረጃ ላይ እያለ ተለይቶ የሚወሰን መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ይህም ቀጥሎ ከሰፈረው የአላህ ﷻ ቃል ጋር የተጣጣመ ነው ፦

{ሰው ተረገመ፤ምን ከሓዲ አደረገው? (ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤መጠነውም።} [ዐበሰ፡ 17-19 ]. . ፕሮፌሰሩ ይህን ካዳመጡ በኋላ በአንድ ስብሰባ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳባቸውን ሲገልጹ ፦ ‹‹ቁርኣን ከብዙ ምእተ ዓመታት በፊት አሁን ያነሳነውን የሚደግፍ ሀሳብ ይዞ ነው የመጣው፤ይህም ቁርኣን በእርግጥ የአላህ ቃል መሆኑን ያመለክታል . . ›› ብለዋል።

ማስረጃዎቹን በትክክል ማንበብ እችል ዘንድ ኮምቲውተሬን ልክፈትማ . . በስምንት የዓለም ቋንቋዎች የተተረጎመው ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ማጣቀሻ የሆነው የ The Developing Human መጽሐፍ ደራሲ ፕሮፌሰር ኪሥ ሙር፣በአንድ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ፦ ‹‹በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የቀረበውን የጽንሰት ሂደት ገለጻዎችን በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበረው ሳይንሳዊ ዕውቀት ላይ መመስረት የሚቻል አይደለም።

የማያነብና የማይጽፍ ሰው ስለነበረ እንዲህ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ማወቅ የሚችል ያልነበረ በመሆኑና ስለዚህም ሳይንሳዊ ስልጠና ያላገኘ በመሆኑ፣ብቸኛው ምክንያታዊ ማጠቃለያ እነዚህ ገለጻዎች ከእግዚአብሔር ወደ ሙሐመድ የተላለፉ መሆናቸው ነው›› ብለዋል። ዶክተር ሙር በዚህ ብቻ ሳወሰኑ፣ስለ ጽንስ ዕድገት ደረጃዎች እውነታ የሚናገር ቁርኣናዊ አንቀጾችንና ነቢያዊ ሐዲሦችን በያንዳንዱ የመጽሐፋቸው ገጽ ላይ አስፍረዋል።

የቶኪዮ ጠፈር ምርምር ጣቢያ ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዮሽዮዲ ኮዛን ደግሞ ፦ ‹‹ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑን አምኖ ለመቀበል ችግር የለብኝም። ቁርኣን ውስጥ የቀረበው የጽንስ ገለጻ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በነበረው የሰው ልጅ የሳይንሳዊ ዕውቀት ደረጃ ላይ ከቶም ሊመሰረት አይችልም። ሊደረስበት የሚችለው ብቸኛው ማጠቃለያ እነዚያ ገለጻዎች ከእግዚአብሔር ለሙሐመድ የተገለጡ ናቸው የሚለው ብቻ ነው›› ብለዋል።

ራጂቭ፦ ቁርኣን ውስጥ በሌሎች የዕውቀት መስኮች ላይ የቀረበ ገለጻ ይኖራል?

ራሽድ፦ በተለያዩ ብዙ መስኮች ላይ አያሌ አንቀጾች ይገኛሉ . . ለምሳሌ ያህል ዛሬ በዘመናዊ ዕውቀት ስለተረጋገጡ ታሪካዊ እውነታዎች የሚናገሩ አንቀጾችን እናገኛለን። የሙሴንና የፈርዖን ታሪክ አስመልክቶ ፈርዖን ሰጥሞ መሞቱንና ለመጭው ትልድ መገሰጫ ይሆን ዘንድ በድኑ መትረፉን ቁርኣን ተርኳል። ይህም ቀጣይ ትውልዶች ይህን ታሪክ በተጨባጭ ማየትና ማስተማሪያነቱን ማሰታወስ ይችላሉ ማለት ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

{ዛሬማ፣ከኋላህ ላሉት ታምር ትኾን ዘንድ፣በድን ኾነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን፣(ተባለ)፤ከሰዎችም ብዙዎቹ ከታምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው።} [ዩኑስ፡92 ][ እዚህ ላይ ሦስት ነገሮች ተጠቁመዋል]፦

1) ፈርዖ የሞተው በውሃ ሰጥሞ መሆኑ።

2) በድኑ ከውሃው የወጣ መሆኑ።

3) ይህ በድን ሰዎች መመልከት በሚችሉበት ሁኔታ የተጠበቀ (ደርቆ የተገነዘ) መሆኑ።

ይህ በ1898 በተገኘ የፈርዖው መሚ (የደረቀ የተገነዘ ሬሳ) አማካይነት በዘመናዊ ሳይንስ በተጨባጭ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ይህም ከነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሕልት ከ1200 ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። ፈርዖው የሞተው በውሃ ሰጥሞ መሆኑ የተረጋገጠው ግን በ1981 በመሚው ላይ በተካሄደ ሳይንሳዊ ምርመራ ነበር። ምርመራው የሙስሊሞች መጽሐፍ ቁርኣን ይህን የሚያረጋገጥ መሆኑን ሲያወቁ ሰልመው እስላምን በተቀበሉት ፕሮፌሰር ሞሪስ ቡካይ በተመራ የፈረንሳይ ሳይንቲስቶች አማካይነት በተራቀቁ መሳሪያዎችና ውስብስብ በሆኑ ሂደቶች የተከናወነ ነበር። ፕሮፌሰር ቡካይም ከሰለሙ በኋላ ‹‹ቅዱስ ቁርኣን መጽሐፍ ቅዱስና ዘመናዊው ሳይንስ . . መለኮታዊ መጽሐፍት በዘመናዊ ሳይንስ መነጽር ሲመረመሩ›› የሚለውን ድንቅ መጽሐፋቸውን ጽፈዋል።

በተጨማሪም ቁርኣን ውስጥ በተለያዩ መስኮች የቀረቡ አያሌ ታአምራዊ አንቀጾች የሚገኙ ሲሆን የሚከተለው አንዱ ነው። አላህ ﷻ ሮማውያንና ፋርሶችን አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦

{አ. ለ. መ. (አሊፍ ላም ሚም)። ሩም ተሸነፈች። በጣም ቅርብ በኾነችው ምድር። እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ።} [አልሩም፡1-3 ] . . ..እዚህ ላይ ሁለት ተአምራዊ ገጽታዎች ይታያሉ። አንደኛው ሮማውያን በፋሪሶች ከተሸነፉ በኋላ እስከ ዘጠኝ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ዳግም እንደሚያሸንፉ ቅዱስ ቁርኣን አስቀድሞ መናገሩ ነው። በቁርኣን የተነገረው ትንቢትም ከሰባት ዓመት በኋላ በ627 ዓመተ ልደት በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ጦርነት ሮማውያን ድል በመቀዳጀታቸው ተፈጽሟል።

ሁለተኛው የአንቀጹ ተአምራዊ ገበጽታ ደግሞ፣በዘመኑ የማይታወቀውን ጂኦግራፊያዊ እውነታ ያረጋገጠ መሆኑ ሲሆን፣ይህም ውጊያው የተካሄደው በጣም ቅርብ በሆነ ምድር መሆኑን ማመልከቱ ነው። በጣም ቅርብ (አድና) የሚለው የዐረብኛ ቃል ሁለት ትርጉሞች ያሉት ሲሆን ቅርበትና ዝቅ ማለትን ይገልጻል። የጦርነቱ ቦታ በአንድ በኩል ለዐረቢያ ደሴት አከል በጣም የቀረበ አካባቢ ሲሆን፣በሌላ በኩል ደግሞ ቦታው ከባሕር ጠለል በታች 1312 ጫማ (400 ሜትር ያህል) በመሆኑ በምድር ላይ በጣም ዝቅተኛ ከፍታ ያለው ቦታ ነው። በብሪታኒካ ዐውደ ጥበብ እንደተጠቀሰው በሳተላይት የተመዘገበ በምድር ላይ የሚገኝ የመጨረሻው የየብስ ዝቅተኛ ስፍራ ነው። ጦርነቱ የተካሄደው በሙት ባሕር አካባቢ በሚገኘውና በዓለም ላይ በጣም ዝቅተኛ በሆነው ቦታ ላይ መሆኑን ታሪካዊው እውነታ ይመሰክራል። የቦታን ከፍታ ዛሬ ያሉት ዘመናዊ መሳሪያዎች በሌሉበት በሰባተኛው ክፍለ ዘመንን እንዲህ መገለጹ ተአምር ነው።

ማይክል፦ ራሽድ ይህ በቂ ይመስለኛል።

ራጂቭ፦ እኔ ግን ቁርኣን ስለ ሌሎች የሳይንስ መስኮች፣ለምሳሌ ስለ ስነፈለክ፣ስለ ስነምድር፣ስለ ባሕር . . ተናግሮ እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ።

ራሽድ፦ አዎ ተናግሯል፤እነዚህንና ሌሎች የሳይንስ መስኮችን የሚመለከቱ ጥቆማዎች ቁርኣን ውስጥ ይገኛሉ። ስለ ዩኒቨርስ አፈጣጠር፣ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር፣ስለ ሕክምና ሳይንስ፣ስለ እጽዋት ሳይንስ፣ስለ እንስሳት ሳይንስ፣ስለ ፊዚክስ፣ስለ ብርሃን ሳይንስ . . እንደዚሁም ከቋንቋዊ ምጥቀቱና ሕግ ነክ ተአምራቱ ጎን ታሪካዊና አኃዛዊ ተአምራትን የሚመለከቱ ጥቆማዎችንም አካቷል።

ማይክል፦ ልንነጋግርባቸው የሚገቡ ርእሰ ጉዳዮች ብዙ ናቸው። የመልስ ጉዞአችን ነገ በመሆኑ ከወዳጃችን ራጂቭ የምንለያየው እያዘን ነው።

ራጂቭ፦ እኔም በጣም እየዘንኩ ነው የምለያችሁ፤ከናንተ ጋር በመተዋወቄ ዕድለኛ ነኝ፤ ከናንተ ጋር በነበሩኝ ውይቶችም በእጅጉ ተጠቅሜያለሁ . . በኢንተርኔት ማሕበራዊ ድረገጾች አማካይነት ግንኙነታችንና ውይይታችንን መቀጠል እንችላለን።

ራሽድ፦ ድንቅ ሀሳብ ነው። ሌላ ሀሳብም እንካችሁ . . ይህን አጋጣሚ በማይረሳ ትዝታ ለመቋጨት የስንብት ፕሮግራም ቢኖረን ምን ይመስላችኋል?

ማይክልና ራጂቭ፦ ግሩም ሀሳብ ነው።