የመዳኛው ጥግ

የመዳኛው ጥግ

ራሽድና ማይክል ወደ ለንደን ለመመለስ በባቡር ተሳፈሩ፤ባቡሩ ጉዞ ከጀመረ በኋላ ማይክል ራሽድን ማናገር ጀመረ፦

በንግግሮችህ ውስጥ ብዙ ጊዜ የምታነሳውና በሚገባ ያልተብራራ ግን አስፈላጊ መስሎ የሚታኝ አንድ ነጥብ ነበር . . )የሰው ልጅ የተፈጠረበት ግብና ዓለማ( የሚለውን ብዙ ትደጋግም ነበር። የተፈጠረው እግዚአብሔርን ለማመምለክ ዓላማ መሆኑንም አንዴ መጥቀስህን አስታውሳለሁ . . ይህ እኔንም ሆነ የማውቃቸውን ብዙ ሰዎች የሚያሳስበን ጥያቄ ነው . . እኔ በዚህ ዓለም ላይ የተገኘሁት ለምንድነው? ይህ ሁሉ ጭንቀትና ሲቃይስ ለምንድነው? በሰው ልጆች መካከል እርስ በርስ የሚካሄደውና በሰውና በፍጥረተ ዓለም መካከል የሚታየው ፍጥጫስ ለምንድነው? . . እነዚህ ሁሉ በጣም አሳሳቢ ጥያቄዎች አይደሉምን?

ራሽድ፦ በእርግጥ ናቸው። ለዚህ መነሻው የምዕራቡ ዓለም ሰው እሴታዊና ባህላዊ እነጻና አስተሳሰቡ ይመስለኛል። ትግልና ፍጥጫ የምዕራቡ ዓለም ቁሳዊ ባሕል ከታነጸባቸው የመሰረት ድንጋዮች አንዱ ሲሆን፣ዘመናዊው የምዕራባውያን ባህል በፍርስራሻቸው ላይ ከቆመው ከጥንታዊዎቹ የሮማንና የግሪክ ባሕል የተወረሰ ነው። )የትግልና የፍጥቻ አይቀሬነት( በሁለቱ ሥልጣኔዎች ዘንድ ከመሰረታዊ እሳቤዎች አንዱ የነበረ ሲሆን፣በአማልክት መካከል ፍጥጫ፣በሰውና በአምላክ መካከል ፍጥጫ፣በሰው ልጅና በተፈጥሮ መካከል ፍጥጫ፣በበጎና እኩይ ኃይሎች መካከል ፍጥጫ፣ከሁሉም ጋር ፍጥጫና ትግል ነው። የዘመናዊው የምዕራቡ ዓለም ቁሳዊ ሥልጣኔ ዓይነተኛ መገለጫና ውጤት የሆነው መንፈሰ ባዶነትም ሌላው ነው።

ማይክል፦ ለሰው ልጅ ልታቀርብለት የምትችለው አንዳች ዓይነት ምትሃታዊ ተለዋጭ መፍትሔ በእጅህ እንዳለህ ሆነህ ነው የምትናገረው።

ራሽድ፦ ትክክለኛ እምነት ባለው አንድ ሙስሊም ዘንድ ጉዳዩ እንዲህ በግራ መጋባትና በብኩንነት የጨፈገገ አይደለም። ማንኛውም ሙስሊም በእስላማዊ ሃይማኖቱ አማካይነት ከየት እንደመጣ፣መጨረሻው ምን እንደሆነ፣የሚኖርባት ይህችን ዓለም ምንነት፣የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ፣የሰው ልጅ የሕይወት ተልእኮ ምን እንደሆነ ያውቃል።

ማይክል፦ ጥያቄዬ አልተመለሰም፤እንዲያውም ተጨማሪ ጥቄዎችን እንዳክልበት ነው ያደረገኝ። እስላም ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ያለው እሳቤ ምንድነው?

ራሽድ፦ ሙስሊም ሰው ከዩኒቨርስና በውስጡ ካሉት ጋር በመጣጣም ሁኔታ ላይ መሆኑ ይሰማዋል። ፍጥረተ ዓለሙ በመላ ለአላህ ተገዥ በመሆንና እርሱን በማወደስ ረገድ ቅኑን የአላህ ተገዥ ይጋራል። አምልኮውና ውዳሴው ግን በሰው ልጆች ዓለም እንዳለው በምርጫና በተወሰነ የአፈጻጸም መንገድ፣ወይም እኛ በማናውቀው ተፈጥሯዊ መንገድ ሊሆን ይችላል . . በዩኒቨርስ ውስጥ ያለው ሁሉ እርሱን የሚያጠራና የሚያወድሰው መሆኑ ቁርኣን ውስጥ ማጥራት {ተስቢሕ} በሚል ቃል ከሰላሳ ጊዜ በላይ ተደጋግሟል። በሌላ አገላለጽም ብዙ ጊዜ ተጠቀሷል። በዚህ መልኩ ነው ንቁው ሙስሊም አላህን ﷻ በማጥራትና በማወደስ የሚያዜመው ዩኒቨርሳል ዝማሬ ቡድን አባል መሆኑን የሚገነዘበው። እናም ከፍጥረተ ዓለም ጋር በሚጣጣምና በሚናበብ ሁኔታ ላይ እንጂ በግጭትና በፍጥጫ ሁኔታ ውስጥ አይደለም።

ለተፈጥሮ ያለው ስሜትና ዝንባሌ የመላመድ የመጣጣምና የወዳጅነት እንጂ ጥላቻና የመራራቅ ስሜት አይደለም። በዩኒቨርስ ውስጥ ያለው ሁሉ ለሰው ልጆች አገልግሎት የተገራ መሆኑን ቁርኣን ያረጋግጣል። ይህ (መግራት) በሚለው አገላለጽ ቁርኣን ውስጥ ከሃያ ጊዜ በላይ ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን በሌሎች አገላለጾችም ብዙ ጊዜ ተደጋግሟል።

ማይክል፦ ከዚህ ጀርባ ያለው ዓለማ ምንድነው? . . በዚህ ላይ ምን ይመሰረታል?

ራሽድ፦ የሰው ልጅ ልቦናው እንዲረጋጋ፣የአእምሮ ሰላም አግኝቶ በደስታና በእርካታ ለመኖር ምን ይፈልጋል? የሚለውን ስንመለከት . . የሚያስፈልጉት ነገሮች በአምስት ቃላት የሚወከሉ ሆነው እናገኛለን። እነሱም፦ መስለም፣ ተገዥነት፣ታዛዥነት፣ፍጹምነት እና እርጋታ ናቸው። ይህ በተግባር እውን የሚሆነው የሰው ልጅ መላውን ዩኒቨርስ በሚያካትተው የአላህ ﷻ አምልኮት (ዕባዳ) ጥላ ስር ሲጠለል ነው። እነዚህ አምስት ቃላትም የእስላም ትርጉም መሆናቸውን እናስተውላለን።

ማይክል፦ የበለጠ እንድታብራራው እፈልጋለሁ።

ራሽድ፦ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ትስስር ከሚመለከተው ከዚህ እሳቤ ዋነኛ ውጤቶች አንዱ፦ ከገዛ ራሱና በዙሪያው ካሉት ጋር የሚኖረውና የሚሰማው ውስጣዊ ስሜትና የአንድነትን መርሕ በተግባር መኖሩን በአማኙ ላይ ማንጸባረቁ ነው። ይህም ከስሜት አንድነት ወደ ቅንጅትና ስነምግባር አንድነት የሚደረገውን ሽግግር ቀላል ያደርግለታል። በሕይወቱ ውስጥ ሁሉንም የሰብአዊነት ገጽታዎች፣መንፈሳዊውን፣ሕሊናዊውንና አካላዊውን ጎኖች ሁሉ ግምት ውስጥ የሚያስገባ ሚዘናዊነት እንዲኖር ያደርጋል።

አላህ ﷻ ፦

{እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለናንተ የፈጠረ ነው፤ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፤እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።}[አልበቀራህ፡ 29 ]

{ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን በመላ ከርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፤በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራት አለበት።}]አልጃሢያ፡ 13]በማለት አላህ ﷻ በምድር ያለውን ሁሉ የገራልን መሆኑን የሚያውቀው ሙስሊም፣ አላህ ﷻ ለኛ ከፈጠረና ለአገልግሎታችን የተገራ ካደረገው በኋላ ከተፈጥሮ ጋር ምንም ግንኙነትም ሆነ ትስስር እንዳኖረን እንደማያደርግም ያውቃል! ስለዚህም የሰው ልጅ አላህ ከገራለት ተፈጥሮ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ማብራራት አይቀሬ ይሆናል። ነገሩ እንዲያ ከሆነ ደግሞ በሰው ልጅና በነዚህ ፍጥረታት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገዛበትን ዕውቀት ማስተላለፉም አይቀሬ ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏልና ፦

{ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፤ከዚያም በዐርሹ (በዙፋኑ) ላይ ተደላደለ፤።}[አልአዕራፍ፡54]በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦

{ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?}[አልቅያማ፡36]

ይህም የሰው ልጅ በዚህ ዓለም ላይ ያለ መመሪያ ያለ ትእዛዝና እገዳ እንዲሁ ያሻውን እንዲሰራ ነጻ የተለቀቀ አይምሰለው ማለት ነው። ነገሩ እንደዚህ ከሆነ ዘንዳም ሙስሊሙ በምድሪቱ ላይ ዩኒቨርሳልና ሸሪዓዊ ፍትሕን ማረጋገጥ የሚያስችለውን ዕውቀት መማርና ሃይማኖቱን ማስተንተን ይኖርበታል።

እስላም ከዚህ መነሻ በመንደርደር የተሟላ የሕይወት መመሪያ ያቀርባል። ሙስሊሙ ከፈጣሪ ጌታው ጋር ያለውን ግንኙነት፣በመንፈሳዊ አምልኮታዊ ጎኑም ሆነ ጋብቻን፣ፍችን፣ሽያጭና ግብይትን፣ምግብና መጠጡን፣ እንቅልፉን፣አለባበሱን፣ቤት መግባትና መውጣትን፣ግላዊ ንጽሕናው እንኳ ሳይቀር የሚመለከቱ ስነምግባሮችን . . ያደራጃል። በተጨማሪም ከሕብረተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ከመንግስቱ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ከሌሎች ማሕበረሰቦች ጋር ያለውን ግንኙነት፣ሁሉንም የተለያዩ መሰረታዊ የሕይወት ፈርጆች ሕጋዊውን፣ኢኮኖሚያዊውን፣ ፖለቲካዊውን፣ባህላዊውንና ማሕበራዊውን ባካተተ መልኩ ሁሉ አቀፍ እንዲሆን ያደርጋል . . እስላም ከዚህ የሚንደረደረው የተሟላ ወጥና ሁሉ አቀፍ ሥርዓት ለማነጽ ነው።

እስላም የሙስሊሙን ስሜትና ዝንባሌውን እንደሚመራ ሁሉ፣ሕግጋትን ይደነግግለታል። የፍትሕና የርትእ ሚዛን ያቆምለታል። ምድርን እንዲያለማና እንዲገነባት፣የተፈጥሮን አድማሳትና ራስን የመፈተሽ የማያቋርጥ ጥረትና አሰሳ እንዲያደርግ ያዘዋል . . ይህ ሁሉ የሚንደረደረው ከአላህ ﷻ በሚኖረው ግንኙነትና ለርሱ በሚደረገው አምልኮና ተገዥነት ማእቀፍ ውስጥ ነው። እነዚህ የተለመዱ የእለታዊ ኑሮ እንቅስቃሴዎች ከአላህ ሕግና መመሪያ ጋር የተሳሰሩ በሚሆኑበት ጊዜ፣ወደ ዕባዳ (አምልኮተ አላህ) ይለወጣሉ።

ማይክል፦ ያነሳኸው ነጥብ ግን ወደ ማክረርና ወደ አጥባቂነት ማዘንበል እንዳይሆን የሚል ስጋት ያሳደስርብኛል። ግልጽ ለመሆን ሃይማኖት ሁሉንም የሕይወት ፈርጆች የሚቆጣጠር እንዳይሆን ስጋት አለኝ።

ራሽድ፦ ሁሉም ነገር በውስጡ ያሉትን አቀናጅቶና አደራጅቶ የሚመራበት ሥርዓት ያለው ሲሆን፣በውስጡ የታቀፉት ሁሉ የየራሳቸው ሚና እና ፋይዳ አላቸው። እነዚህን ሁሉ እርስ በርስ በማስተሳሰርና በተሟላ መልኩ በማቀናጀት ነው የሥርዓቱ ፋይዳ በተግባር የሚታውና ሁለንተናዊ ዓላማው የሚረጋገጠው። ይህም አላህﷻ በቀጣዩ ቁርኣናዊ አንቀጽ ውስጥ ሚዛን ብሎ የሰየመው ነው፦

{ሰማይንም አጓናት፤ትክክለኛነትንም ደነገገ። በሚዛን (ስትመዝን) እንዳትበድሉ። መመዘንንም በትክክል መዝኑ፤ተመዛኙንም አታጓድሉ።}[አልረሕማን፡7-9]ሚዛን በሁሉም ነገር ውስጥ መንጸባረቅ ያለበት ፍትሕ ማለት ነው። ይህ ዩኒቨርስ በሚዛን በእቅድና በልክ ላይ የቆመ እንደሆነ ሁሉ አጠቃላዩና ዝርዝሩ ሥርዓትም በዚሁ ላይ ይቆማል። ከዚህ ዩኒቨርስ ፈጣሪ የተላለፈው ይህ ሃይማኖትም እንዲሁ በሚዛንና በፍትሕ መሰረት ላይ የቆመ ነው።

ሚዘናዊነትና የመብቶች እርስ በርስ አለመገፋፋት የእስላም አጠቃላይ መገለጫ ሲሆን፣የሰው ልጅ በራሱና ከሌሎች ጋር በሚኖረው በይነሰባዊ ግንኙነት ውስጥም በፍትሐዊነት በመካከለኛነትና በለዘብተኝነት የሚገለጽ ነው . .

የሰው ልጅ ስለራሱ ባለው እሳቤና በሚሰጠው ብያኔ ላይ የሚኖረው ሚዘናዊነትና መካከለኛነት ብዙውን ጊዜ ስለ ሌሎች በሚኖረው እሳቤና በሚሰጠው ብያኔ ላይም አሻራውን ያሳርፋል። ቀጣዮቹ አንቀጾችም ይህንኑ ሚዘናዊነትና መካከለኛነት ያመለክታሉ። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦

{ከነርሱም ውስጥ፦ ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን)፣በመጨረሻይቱም አገር ደግን ነገር (ገነትን)፣ስጠን፤የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን የሚሉ ሰዎች አልሉ፤}[አልበቀራህ፡201 ]

{አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፤ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፤አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገ ሁሉ አንተም መልካምን አድርግ፤በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፤አላህ አጥፊዎችን አይወድምና፣(አሉት)።}[አልቀሶስ፡77]

{እነዚያም፣በለገሱ ጊዜ የማያባክኑት፣የማይቆጥቡትም ናቸው፤በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው።}[አልፉርቃን፡67]

{እጅህንም ወደ አንገትህ የታሠረች አታድርግ፣ መዘርጋትንም ሁሉ፣አትዘርጋት፤የተወቀስክ፣ የተቆጨህ፣ትሆናለህና።}[አልእስራእ፡29]

ራሽድ፦ በተጨማሪም ሌላ እንቅልፍ የሚነሳኝ ጉዳይ አለ። የሰው ልጅ የወንድሙን ደም በማፍሰስ ደም መጣጭ ሆኗል። ሞራላዊ ስነምግባሩ ክፉኛ አሽቆልሏል። እግዚአብሔር የሰጠውን አቅምና ኃይል ለብልጽግና ለሰላም ለልማትና ለተደላደለ ሕይወት . . ከማዋል ይልቅ ለጥፋትና ለውድመት እየተገለገለበት ነው። እስላም ይህን ችግር እንዴት ይመለከታል?

ራሽድ፦ ይህችን ዓለም የሰው ልጅ በገዛ ራሱ የመቀጣጫ አገር አድርጎ አዘጋጅቷታል። ይህም የሰው ልጅ እንዴት እንደሚሰራና የንኡሳን ክፍሎቹን አሰራር የሚመለከት ዕውቀት የሌለውን ማሽን ለማሠራት በከንቱ በመሞከሩ የመጣ ጣጣ ነው። የዚህን ሰብአዊ ማሽን ምስጢሮች የሚያውቀው የሠራውና የፈጠረው ብቻ ሲሆን፣ስለ ተፈጥሮውና ስለ ባሕርይውም ከርሱ በስተቀር የሚያውቅ የለም። በቅንጅትና በተጣጣመ ሁኔታ እንዴት እንደሚሠራ የሚያውቀውም እርሱ ብቻ ነው። አሁን የሰው ልጅ ይህን ጅልነት ከመፈጸም ራሱን ከገታና ማሽኑን የሰራው ፈጣሪ የደነገገውን ሕግና መመሩያ ለመከተል ከወሰነ፣እስካሁን ያበላሸውን ዳግም የማስተካከል ተስፋ ይኖረዋል። ካልሆነ ግን አሁን ካለበት መከራና ሰቆቃ፣ውድመትና ጥፋት፣ዋይታና ኡኡታ. . የሚገላግለው መፍትሔ አይኖርም።

ማይክል፦ የእስላምን መርሕ ከመከተል ውጭ መድህን የለም፣አልያ የሰው ዘር በዚህ የሰቆቃ ሁኔታ ውስጥ መኖሩን ይቀጥላል ማለትህ ነው?!

ራሽድ፦ ይህ በጣም ግልጽ ነው። በግለሰብ ደረጃም ሆነ በሕብረተሰብ ደረጃ፣በዱንያም ሆነ በኣኽራ፣ያለበት ኃላፊነት ግዴታ የሚሰማው ካልሆነ በስተቀር የሰውን ልጅ በዚህች ዓለም ላይ ከሚፈጽመው እብሪት ሊገታው የሚችል ነገር የለም። አንድ ግለሰብ በዚህ ዓለም ላይ በሚሠራው ነገር ለምን ብሎ የሚጠይቀውና የሚቀጣው የበላይ ኃይል የለም ብሎ ያሻውን የሚሰራ ከሆነ፣ለጥፋቱና ለእብሪቱ ገደብም ሆነ ልጓም አይኖረውም። ይህ ግለሰብን በሚመለከት ትክክል ከሆነ፣ቤተሰብን ሕብረተሰብን ሕዝብንና መላውን የምድር ነዋሪ በተመለከተም እውነት ነው። እናም ለሁላችን የቀረበ ፈተና ነው ማለት ነው። ለፈጠረንና ለሚገዛን አምላካችን ያለን ተገዥነትና ተመሪነት የሚሞከርበት መፈተኛችን ነው።

እኔና አንተም፣የአላህ ﷻ በምድሪቱ ላይ ያመቻቸላቸው ሁሉም ይህን ፈተና በጋራ እንጋፈጣለን። ሁላችንም በአእምሯችን፣በሰብእናችን፣በኃላፊነት ስሜታችንና በታማኝነታችን ተፈታኞች ነን። እናም እያንዳንዳችን ለእውነተኛው ገዥ አምላኩ በእውነት ታማኝ ነኝ ወይስ ከሓዲ ነኝ? የሚለውን መወሰን ይኖርብናል።

እኔ በበኩሌ የታዛዥነትና የታማኝነት መንገድ ለመከተል ወስኛለሁ። በአላህ ﷻ ትእዛዝ ላይ ካመጸውና ከርሱ ተገዥነት ከወጣ ሰው ትእዛዝና ተገዥነትም ወጥቻለሁ . . የመዳኛው ጥግም ይኸ ነው።

ማይክል፦ ባቡሩ ወደ መጨረሻው ጣቢያ ደርሷል . . በል እንውረድ።