ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር (1)

ጆርጅ ሌሊቱን ከልጆቹና ከባለቤቱ ጋር ለማሳለፍ በቂ ጊዜ በመፈለጉ ለጉዞው የሚያደርገውን ዝግጅት ያጠናቀቀው በጊዜ ነበር። ከሕንድ ከተመለሰ ወዲህ ተደራራቢ ሥራ፣የስምምነቶቹን ዝርዝር ጉዳዮች የሚመለከቱ ረዣዥሞቹ የካኽ ስብሰባዎችና ከመጓዙ በፊት ስለ አይሁዳዊነት ለማንበብ መወሰኑ ለቤተሰቡ መስጠት የነበረበትን ጊዜ ሲሻሙበት ቆይተዋል። የጉዞውን ዓላማ በሥራ ተልእኮው ላይ ብቻ ሳይወስን ለትላልቅ ጥያቄዎቹ ምላሽ ፍለጋ ለሚያደርገው ጥረትም አጋጣሚውን ለመጠቀም ወስኗል።

- ጣፋጯ ካትሪና . . ከቴል አቪቭ እንዲመጣልሽ የምትፈልጊው ነገር ይኖራል?

- የትንሣኤን ቤተክርስቲያንና የቅድስት ማርያምን ቤተክርስቲያን ጎብኝተህ በውስጣቸው ጸሎት እንድታደርስ ነው የምፈልገው።

- ስለ ትንሣኤ ቤተክርስቲያን ብዙ ነገር አንብቤያለሁ። ቤተክርስቲያኑን በ335 ዓመተ ልደት ያሳነጸችው የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ናት። ቤተክርስቲያኑ የተሰራው ኢየሱስ የተሰቀለበት ነው የሚባለው እንጨት ተገኘበት ተብሎ በሚታሰበው ኮረብታ ላይ ነው። ሥራው 270 ዓመታት የፈጀ ሲሆን ከዚያ በኋላ ፐርሽያውያን አገሩን በያዙ ጊዜ ተቃጥሎ ነበር። በ617 ሞደስቲ በተባለ የገዳም መነኩሴ አማካይነት እንደገና ተሰራ። ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ በተለይም በቆስጠንጢኖስ ዘመን በ1048 እድሳት ተደርጎለታል። ወራሪዎቹ መስቀላውያን ቅድስት አገርን በ1099 ሲይዙ ሁሉንም ቤተ አምልኮዎች አንድ ላይ በማሰባሰብ አሁን ባለው ቤተክርስቲያን እንዲሰባሰብ አደረጉ። ቤተክርስቲያኑ በኛ በፕሮቴስታንቶች ዘንድ የተቀደሰ ባይሆንም ላንቺ ስል ጎብኝቼ እጸልይበታለሁ። የማርያም ቤተክርስቲያንንም እንዲሁ እጎበኛለሁ። ሌላ የምትፈልጊው ነገር የለም ?

- አመሰግነሃለሁ፣ስለ ቅድስት አገር ብዙ አንብበሃል ማለት ነው።

- በጣም ብዙ የሚባል አይደለም፣አሁንም ገና በማንበብ ላይ ነኝ።

- ቅድስት አገር የአይሁዶች ሳይሆን የክርስቲያኖች ብዙ ታሪካዊ ስፍራዎች ያሉባት አገር ነች። ከኢየሱስ ታሪክ ጋር የተያያዙ ብዙ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትም ይገኙባታል።

- የእስራኤል ቆይታዬ በጣም አጭር ቢሆንም፣የክርስቲያን ታሪካዊ ሥፍራዎችን ለመጎብኘትና ከክርስቲያኖች ጋር ለመገናኘት ጥረት አደርጋለሁ።

- ወይኔ! . . እነዚህን ታሪካዊ ቦታዎች መጎብኘትና በአካል ሄጄ ለጌታ መጸለይ ምን ያህል እንደምመኝ ሊነግርህ አልችልም።

- ለምን አብረን አንጓዝም ?

- አሁን እንኳ ብዙ የቤተክርስቲያን የሥራ ቀጠሮዎች ስላሉብኝ አልችልም። ምናልባት ከአይሁዶች በኩል አሁን የሚደርስብን ግፍ ከቆመ በኋላ ወደፊት እንሄድ ይሆናል።

- ግፍ ?!

- አይሁዶች በቅድስት አገር የሚገኙ ክርስቲያናዊ ቅርሶችን ከማድበስበስና እዚያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትንና ክርስቲያኖችን ከማጎሳቀል ተቆጥበው አያውቁም።

- የቅድስት አገር ታሪክ ስሜት የሚነካ ነው። የመለኮታዊ ሃይማኖቶች የትግልና የፍጥጫ ሜዳ ሆና ነው ለዘመናት የኖረችው። ሁለት ጊዜ ለውድመት ተጋልጣለች። 23 ጊዜ ተከባለች። 52 ጊዜ ጥቃት ተሰንዝሮባታል። 44 ጊዜ ተወራ ሕልውናዋን አጥታለች። አሁንም ድረስ መለኮታዊ ሃይማኖቶች ግዙፍ የሆኑ ታላላቅ ውጊያዎችን ገና ታስተናግዳለች ብለው ይጠብቃሉ። ቁድስ በእርግጥም የጦርነት ፍጥጫዎች ምድር ናት። አነጋገርሽ ግን አስገርሞኛል . . ለአይሁዶች አሳልፋ ያስረከበቻት እንግሊዝ ናት! ከዬት ስለ መጣው በክርስትና ላይ ያነጣጠረ ጭቆናና ግፍ ነው የምትናገሪው ?

- በጣም አሳዛኝ ቢሆንም ልክ ነህ። አንተ ማለት የፈለከውና ‹‹የበልፎር ቃል ኪዳን›› እየተባለ የሚጠራው አያሌ ፖለቲካዊ መንስኤዎች ያሉትና በኃያላን አገሮች መካከከል የነበረውን ትግል የተንተራሰ ነው።

- እንዴት ማለት ? የተባሉት መንስኤዎችስ ምንድናቸው ?

- ከምክንያቶቹ መካከል ፦ የእንግሊዝ ወደ አንደኛው የዓለም ጦርነት (1914-1918) መግባት አንዱ ሲሆን፣በዚህ ወቅት የአይሁዶች ፖለቲካዊና ሳይንሳዊ ድጋፍ ለእንግሊዞች በጣም ወሳኝ ነበር። የጽዮናዊነት ንቅናቄ ደግሞ በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት በፍሌስጥኤም ምድር ላይ የአይሁድ ብሔራዊ መንግስት ለመመስረት የሚያራምደውን ዓለማ የሚደግፍለት ወገን ይፈልግ ነበር።

- የመጠቃቀም ነገር ብቻ ነበር ማለት ነው? !

- አይደለም፣ሌሎች አውሮፓዊ ምክንያቶችም ነበሩ። አንዱና ዋነኛው አይሁዶችን ከአውሮፓ ምድር አስወጥተው ለመገላገል በአውሮፓውያን ዘንድ የነበረው ብርቱ ፍላጎት ነው። ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዶች፣ ከሚኖሩባቸው ሕብረተሰቦች ጋር ተሰባጥረውና ተጣጥመው መኖር ባለመቻላቸው በሚገኙባቸው አገሮች ሁሉ ከአገሩ መንግስት የተነጠለ እንግዳ አካል ተደርገው ይወሰዱ ነበር።ግብጽና አፍሪካን የኤስያ ዐረብና ሙስሊሞችን የሚያገናኝ ድልድል በሆነችው ፍልስጥኤም የተለያዩ ኃይሎችን መትከልም ሌላው ምክንያት ነበር። በተጨማሪም አውሮፓውያን እንደ አደጋ ይመለከቱት በነበረው በቱርክ ዑሥማናዊ ኸሊፋ መንግስት ውስጥ አይሁዶች አንዳንድ ወሳኝ የሥልጣን ቦታዎችን ይቆጣጠሩ ስለነበር የቱርክ ኤምፓይርን የመውረስ ዓላማ የነበራት እንግሊዝ የአይሁዶችን ትብብር መፈለጓ ሌላው ምክንያት ነበር።

- በእንግሊዞች ላይ ትንሽ ጫን ያልሽ መሰለኝ!

- ፈጽሞ፣ጫናዬ የሃይማኖትን ጉዳይ ግምት ውስጥ በማያስገባው ፖሊሲ ላይ ነው። ኢየሩሳሌምን ተቆጣጥረው የክርስትና መዲና ማድረግ ይገባ አልነበረምን ?

- እናማ መሆን የነበረበት በይሁዳዊው ወረራ ፈንታ ሌላ ዓይነት ክርስቲያናዊ ወረራ ነው ማለት ነው!! በዚህ ላይ ካንቺ እለያለሁ፣የቤልፎር ቃል ኪዳን በከፊል ሃይማኖታዊ ነበር የሚል እምነት አለኝ።

- በአንተ አመለካከት ሃይማኖታዊው ምክንያት ምንድነው ?

- ለክርስትና ትምህርቶች የተሰጡ የተሳሳቱ ትርጓሜዎች፣ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የጽዮናዊነት አቀንቃኝ መስመር በስፋት እንዲስፋፋና በሃይማኖት ስም ዘረኝነት እንዲሰፍንና የጦርነት ወንወጀሎች እንዲፈጸሙ አድርገዋል።

- ይቅርታ፣ይህ በካቶሊኮች ዘንድ የለም።

- ልክ ነሽ፣ይህ ደዌ በስፋት የሚስተዋለው እኛ -ፕሮቴስታንት - ዘንድ ነው። በ1948 የእስራኤል መንግስት መመስረት፣በብሉይና ሐዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ትንቢቶች ለመሙላት የግድ መሆን የነበረበት ጉዳይ መሆኑና ይህም ኢየሱስ ዳግም ወደ ምድር ድል አድራጊ ንጉሥ ሆኖ እንዲመጣ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን የሚያምኑ አያሌ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ። ጽዮናውያን ክርስቲያኖች የአይሁድን ሕዝብ በአጠቃላይና አይሁዳዊቷን አገር ደግሞ በተለይ መጠበቅና መከላከል ክርስቲያናዊ ሃይማኖታዊ ግዴታችን ነው ብለው ያምናሉ። (ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ እውነቱን ለመናገር አንቺ እንግሊዝን ሳይሆን ፕሮቴስታዊነትን የምትኮንኚው ለዚህ ነው። ለማንኛውም እስራኤል አሁን እውን ሆናለች።

- ይሁንና ግን ቤተ ክርስቲያኖቻችን፣ቅዱሳን ቦታዎቻችንና ቀሳውስቶቻችን እንዳይጨቆኑ ይገባል።

- ግፍና ጭቆና አይሁዳዊም ይሁን ክርስቲያናዊ በሁሉም መልኩና በሁሉም ገጽታው እኩይ ተግባር ነው። ክርስቲያኖች በአይሁዶች ሲጨቆኑ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፣ልክ አይደለም ? !

- ልክ ነው፤በአይሁዶች ከተገደለውና ራሱን ለሰው ልጆች ቤዛ ካደረገው ከኢየሱስ ጀምሮ፣ከርሱ በኋላ በተከታዮቹ ላይ የተፈጸመው ግፍና ሰቆቃ፣ዛሬ በቅድስት አገር በወንድሞቻችን ላይ የሚደርሰው ጭቆናም የዚህ አካል ነው።

- እህህ፣ወደ ኢየሩሳሌም ከመድረሴ በፊት በሃይማኖቶች ጦርነትና በፍጥጫዎቹ ውስጥ የገባሁ መሰለኝ። በይ ጊዜ ሄዷል አሁን እንተኛ። ከእኩለ ሌሊት በፊት ወደ አይሮፕላን ማረፊያ ማምራት አለብኝ።

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር (2)

ጆርጅ ከጧቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ ቴል አቪቭ ደረሰ . . ብንያምን ነበር አቀባበል ያደረገለት። ብልጠትና መሰሪነትን ከብንያምን ዓይኖች ውስጥ ጎልተው

ታት . .

- ሰላም . . ወደ ቅድስት አገር ወደ ኢየሩሳሌም እንኳን ደህና መጣህ።

- ሰላም፣ወደዚች ቅድስት ምድር በመምጣቴ ደስታዬ ወደር የለውም።

- ጉዞህ አጭርና ለአራት ቀናት ብቻ መሆኑን ካኽ ነግሮኛል።

- አዎ፣ለኔ ተከታታይ ጉዞ በመሆኑ ረዥም እንዲሆን አልፈለኩም። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት ሕንድ ነበርኩ። ካኽ ነው የገፋፋኝና ቅድስት አገርን እንድጎበኝ ያደረገኝ።

- ሁሉንም ነገር አሰናድቻለሁ፤ውሉ በሁለት ቀናት ውስጥ ይፈረማል። በዚህ ረገድ ምንም የሚያሳስብህ ነገር አይኖርም። እዚህ መገኘትህ ውሉ የተፈረመው በመደበኛው ሂደት ውስጥ አልፎ መሆኑን ለማረጋገጥ ብቻ ነው።

- በጣም ጥሩ ነው።

- ወደ ሆቴል ወይስ ወደ ኩባንያው እንሂድ ?

- ወደ ሆቴሉ እንሂድና ሻንጣዬን አስቀምጬ ከዚያ በቀጥታ ወደ ኩባንያው እናመራለን።

- መልካም፣ተነገወዲያ ቅዳሜ ስለሆነ ሌቪ ሰንበት ቀን አትሰራም። በመሆኑም ዛሬና ነገ ከርሷ ጋር መገናኘት ያስፈልግህ ይሆናል። ሌቪ በጣም ሃይማኖተኛና የወጣላት የቴክኒክ ሰው ስለሆነች የደህንነት ሶፍትዌሩ ከሽብርተኞች ጥሶ የመግባት አቅም ይበልጥ ጠንካራ ሆኖ መገኘቱ ዋነኛ ትኩረቷ ነው።

- ያቀረብንላችሁ የሰኩሪቲ ፕሮግራም እጅግ በጣም ጠንካራ ሶፍትዌር በመሆኑ በዚህ በኩል ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር የለም።

- ከሌቪ ጋር ስትገናኝ ትኩረትህ በዚህ ነጥብ ላይ ይሁን። ለእስራኤል ደህንነትና ጸጥታ በጽኑ የምታስብ መሆንህን አሳያት። በጣም የሚያሳስባት ነገር ይህ ነውና። እንዲያውም ከርሷ ጋር በሚኖርህ ቆይታ ውይይታችሁ ከቴክኒካዊ ገጽታው ሌላ ሃይማኖታዊና ፍልስፍናዊ ገጽታ ይዞ ሊያስገርምህ ይችላል።

- ሃይማኖታዊና ፍልስፍናዊ ?!

- አዎ፣ይህ ከመጥፎ ጸባይዋ አንዱ ክፍል ነው። ለማንኛውም ከርሷ ጋር በሚኖረው ነገር ችግሮች ካጋጠሙህ ትነግረኛለህ። (ፈገግ ብሎ ቀጠለ) ፦ ሞገደኛ ብትሆንም ከኔ ቃለል ፈጽሞ አትወጣም።

- በጣም ጥሩ።

ወደ ሆቴሉ ደረሱ፣ጆርጅ ወደ ክፍሉ ሄዶ ሸንጣዎቹን አስቀመጠና ወደ ብንያምን ተመልሶ መጣ። ተያይዘው ወደ ኩባንያው ቢሮ ሄዱ . . የኩባንያው ሕንጻ ትልቅና ትኩረት የሚስብ አልነበረም፣መካከለኛ ሆኖ በሠራተኞች የተጨናነቀ ነው። በሰፈሩ መግቢያ ኬላ ላይ ጥበቃው በጣም የተጠናከረ ሲሆን በኩባንያው መግቢያ በር ላይም እንደዚሁ ነበር።
ወደ ብንያምን ቢሮ አመሩ፣እንደ ደረሱ

ብንያምን

ለሌቪ ደውሎ እንድትመጣ ጠየቃት . .

- ችግር አሁን ትመጣለች።

- ችግር ! እንዴት ?

- የሃይማኖት አክራሪነቷ ሕይወትን በተገቢው መንገድ እንዳትረዳ ያደርጋታል። እንደዚሁም ክርክር ትወዳለች፣አይሰለቻትም፣በመጨረሻ ግን በጫና ትለሰልሳለች።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጣም ቆንጆ የሆነች ኮረዳ ብቅ አለች። የለበሰችው ልብስ የጨዋ ሊባል የሚችል ቢሆንም ወበቷን የሚደብቅ አልነበረም።

ብንያምን

ከጆርጅ ጋር አስተዋወቃት፦

- ሌቪ የኩባንያችን የቴክኒክ መምሪያ ኃላፊ ናት . . (ወደ ጆርጅ እያመለከተ) ፦ ይህ ጆርጅ ነው፣እንግሊዝ አገር የሚገኘው የተራቀቀ የኤሌክትሮኒክስ ማምረቻ ኩባንያ የፕሮግራሚንግ መምሪያ ኃላፊ ነው።

- እንኳን ደህና መጣህ፣እዚህ በመምጣትህ አመሰግናለሁ። ብዙ ቴክኖሎጂያዊና ቴክኒካዊ ጥያቄዎች አሉኝ።

- ለመመለስ ደስተኛ ነኝ።

- ከፈለጋችሁ በመሰብሰቢያው ክፍል ውስጥ ሆናችሁ ስብሰባችሁን ማካሄድ ትችላላችሁ።

- መልካም፣ሚስተር ጆርጅ እባክህን ወደ ክፍሉ እንሂድ።

ጆርጅና ሌቪ ወደ ስብሰባ ክፍሉ ሄዱ

ትንሽ ክፍል ብትሆንም በሥርዓት የተደራጀችና ምቹ ክፍል ናት . .

- ግባ።

- አመሰግናለሁ፣ኩባንያችን ባቀረበው የሰኩሪቲ ሶፍትዌር እምብዛም የረካሽ አትመስይም ?

- አይደለም፤እንደዚያ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አርኪና አስተማማኝ እንዲሆን ስለምፈልግ ብቻ ነው። እንደ አይሁድ ደህንነታችንና ጸጥታችን ከምንም ነገር በላይ ያሳስበኛል።

- ፕሮግራሙ አሁን ካሉት የሰኩሪቲ ፕሮግራሞች ሁሉ እጅግ ጠንካራው ነው። በደህንነትና በጥበቃ ጉዳይ ላይ ከሚገባው በላይ እንድታከሩ የሚያደርጋችሁ ፎቢያ እንዳለባችሁ ነው የሚሰማኝ።

- እንዴት ማለት?

- የሰፈር ጥበቃ፣የሕንጻ ጥበቃ፣በሕይወቴ እንዲህ ያለውን አይቼ አላውቅም!

- እኛ ለዘመናት ጭቆና ስር የኖርን ሕዝብ ነን፤በመሆኑም በተቻለኝ አቅም ሁሉ ይህን ሕዝብ መጠበቅ ኃላፊነቴ ሆኖ ይሰማኛል።

- መልካም፣የኔም ኃላፊነትና ተልእኮም በዚህ ረገድ ቴክኒካዊ እገዛ ለናንተ ማቅረብ ነው።

- ታግዘናለህ ! ለምንድነው የምታግዘን ?

- አልገባኝም! አሁን በምንፈራረምበት በዚህ ልዩ የሆነ የደህንነት ጥበቃ ፕሮግራም አግዛችኋለሁ።

- ይቅርታ አድርግልኝና የለመድኩት ሰዎች ሁሉ የኛ የአይሁዶች ጸር መሆናቸውን ነው።

- እኔ እንግሊዛዊ ፕሮቴስታንት ክርስቲያን ነኝ። ይህን አገርና ይህን መሬት ለናንተ የሰጣችሁ እንግሊዛዊው ፕሮቴስታንት ክርስቲያን ቤልፎር አይደለምን?

- ይህች አገራችንና መሬታችን ናት፤ማንም አልሰጠነም።በመሆኑም እኛው ራሳችን ልንጠብቃት ይገባል።

- ክርክር ወዳድ ትመስይያለሽ፤ግልጽነትን ትወጂያለሽ ?

- ክርክር እወዳለሁ፤አፈቅራለሁ፤ግልጽነትንም እወደዋለሁ፤ እፈልጋለሁ።

- እንደምትዪው ግልጽነትን የምትወጂ ከሆነ ከዬት ነው የመጣሽው ? ገጽታሽ አውሮፓዊ ይመስላል?!

- እኔ ከእስራኤል ነኝ።

- አባትና እናትሽም እስራኤል ውስጥ ነው የተወለዱት?

- ወላጆቼ በ1970 የመጡ ነምሳውያን ሲሆኑ እኔ እዚህ እስራኤል ውስጥ ነው የተወለድኩት። በመሆኑም የነምሳ ዜግነት ቢኖረኝም እኔ እስራኤላዊ ነኝ።

- እናም አንቺ የእስራኤልን ደህንነት የምትጠብቂ ነምሳዊት ነሽ፤እኔ ደግሞ የደህንነት ጥበቃ ሶፍትዌር የማቀርብልሽ እንግሊዛዊ ነኝ ማለት ነው።

- እኔ አይሁዳዊት ስሆን፣አንተ ግን ፕሮቴስታንት ነህ!

- አባትሽ ይሁዲ ነው?

- አይደለም፣አባቴ ኤቲስት ክርስቲያን ነበር፤አይሁዳዊነት የሚመጣው ከእናት በኩል እንጂ ከአባት አይደለም።

- ግልጽ ልሁንና ወደ ኢየሩሳሌም የመጣሁት ለሁለት ነገር ነው። አንደኛው ውሉን ለመፈራረም ሲሆን፣ሁለተኛው የአይሁድ ሃይማኖትን ለማወቅ ነው። ምናልባት አይሁዳዊ ልሆን እችል ይሆናልና በሃይማኖት ጉዳይ ላይ በጥልቀት ብንወያይ ምን ይመስልሻል ?

- በጣም ደስ እያለኝ፣ይሁን እንጂ እናትህ አይሁዳዊት እስካልሆነች ድረስ አይሁዳዊ መሆን አትችልም።

- እንዴት ማለት?

- እኛ ምርጥ ሕዝብ ነን፤በዝርያውና በእምነቶቹ በእግዚአብሔር የተመረጥን ሕዝብ ነን።

- ስለዚህም ሌሎች ሃይማኖታችሁን እንዲቀበሉ ጥሪ አታደርጉም፣አታስተምሩም ማለት ነው ?

- ፈጽሞ አናደርግም፤ጥሪ የምናደርገውና የምናስተምረው ሌሎች ይህን ምርጥ ሕዝብ እንዲያገለግሉ ብቻ ነው።

- ሌላው የናንተ አገልጋይ እንዲሆን ብቻ ነው ማለት ነዋ!!

- ዋጋ የማይከፈልበት አገልግሎት የለም።

- የደህንነት ጥበቃ ውሉን ስትፈርሙ ለኛ የምንስማማበትን ዋጋ ትከፍሉናላችሁ። ይኸ አገልግሎት አይደለም ! ሽያጭና ግዥ፣ግብይት ነው።

- የናንተ ኩባንያ ዳይሬክተር አይሁዳዊ ባይሆን ኖሮ፣ የሰኩሪቲ ሶፍትዌሩን ለኛ ለማቅረብ ኩባንያችሁ ባልተመረጠ ነበር።

- ካኽ ግን ሴኩላሪስት ነው !

- ቢሆንም ከምርጡ ሕዝብ የወጣ አይሁዳዊ መሆኑ አልቀረም . . አንተ ግን ሃይማኖተኛ ትመስላለህ !

በዚህ ወቅት አስተናጋጅ በሩን አንኳኳ። ምን እንደሚወስድ ሌቪ ጆርጅን ጠየቀች . .

- ውሃና ቡና . . ጉዳዩን ከመነሻው ብንጀምር ምን ይመስልሻል ?

- ይሁን ቀጥል፣የሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች እናት የሆነው ሃይማኖት ትኩረትህን የሳበ ትመስላለህ።

- የመለኮታዊ ሃይማኖቶች እናት ስትይ፣አይሁዳዊነትና ሙሴ አይሁዶች፣ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የሚያምኑበት ነው ማለትሽ ነው?

- አዎ፣ከርሱ በኋላ በመጡት ላይ ስምምነት አልተደረገም። አይሁዶች በኢየሱስ፣ክርስቲያኖች ደግሞ በሙሐመድ አያምኑም።

- ሙስሊሞች በሁሉም ያምናሉ ማለት ይቻላል፤አይሁዶች ግን ከራሳቸው ነብይ ከሙሴ በስተቀር በየትኛውም አያምኑም . . አሁን ይህን ተይውና ከመለኮታዊ ሃይማኖቶች ጥንታዊ ስለሆነው እምነት በዝርዝር ማወቅ ስለምፈልግ ልታግዢኝ ትችያለሽ ?

- የፕሮግራሚንግ ሳይሆን የሃይማኖትቶች ኤክስፐርት ነው የምትመስለው ! መቀጠል ትችላለህ።

ጆርጅ ፊትለፊት ለመጋፈጥና ስለ አይሁዳዊነት የሚታውቀውን ሁሉ እንዲትነግረው ሊያግባባት ወሰነ።
መሰረታዊ ያልሆነ ፍሬ አልባ መረጃ ሳይሆን እውነታውን ማወቅ ነው ዋነኛ ዓለማው . .

- አይሁዶች በእግዚአብሔር ያላቸው እምነት ምን ይመስላል? እንዴት ነው የሚገልጹት? እንዴት ነው ብለው ያስተዋውቁታል?

- ማለት የፈለከው አልገባኝም? ጌታ አምላክ ግን ፈጣሪና ሲሳይ ሰጭ አምላክ ነው።

- የእግዚአብሔር ባሕርያት በአይሁዶች ዘንድ እንዴት እንደሚገለጽ ለማወቅ ብዙ ነገሮችን ያነበብኩ ሲሆን ብዙ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አድርጎኛል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካነበብኩት መካከል አንዱ እንዲህ ይላል ፦ ‹‹የእግዚአብሔርም ቃል ፦ ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፣ትንቢቴንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ።›› ኦሪት ዘ ጸአት ውስጥ ደግሞ ፦ ‹‹የልቅሶአቸውን ድምጽ ሰማ፣እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ።›› የሚል አነበብኩ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ወስጥም ፦ ‹‹አሁን ሄደህ አማሌቅን ምታ፣ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፣አትማራቸውም ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕጻኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።›› የሚለውን አነበብኩ። ይህንን የመሳሰሉ ሌሎች ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። የኔ ጥያቄ እግዚአብሔር ይጸጸታል? ይረሳና ያስባል? ያለ ምሕረት ሕጻናትንም ጭምር እንዲገደሉ ያዛል?! እንዲህ ያለው አምላክ ምን ዓይነት አምላክ ነው?!

 

- ጥሩ አንባቢ ትመስላለህ፤ግን ቁንጽል አንባቢ ነህ። ያልከው ነገር ትክክል ነው። ከዚህም ሌላ ብዙ ይኖራል፤ይሁን እንጂ ይህ በአይሁዳዊነት ብቻ የተወሰነ ነው ወይ? እናንተም ብትሆኑ የዚህ ዓይነት እጥፍ ድርብ አላችሁ።

- እህህ፣ልክ ነሽ ተመሳሳዩ እኛ ዘንድም በብዛት ይገኛል፤ግን እኔ ወደ ይሁዳዊነት ለመለወጥ ስለማስብ ነው። ወደፊት ስለ አይሁዳዊነት እምነቶች የጀመርነውን ብንቀጥልበት ምን ይመስልሻል? ዛሬና ነገ የስምምነት ፊርማውን ጉዳይ ብጠናቅቅ ደስታዬ ነበር፤ተነገወዲያ ቅዳሜ ስለሆነ እናንተ አትሰሩም።

- ልክ ነህ፣ቅዳሜ የዕረፍትና የአምልኮ ቀን ነው። ሰንበትን ማክበር ከአስርቱ ትእዛዛት አንዱ ነው። እግዚአብሔር ሰማያትና ምድርን ፈጥሮ ያረፈው ቅዳሜ ዕለት ነው።

- ያረፈው?!

- አዎ፣ሰንበት ነው ያረፈው። እግዚአብሔርን በሚመለከቱ አንዳንድ ቃላት ላይ ስሜታዊነትን ታንጸባርቃለህ፤መቼም ይህ ያንተ ችግር ነው።

- ሊሆን ይችላል፣ዋናው ነገር በውል ስምምነቱ ላይ የምናደርገውን ውይይት በሁለት ቀን ውስጥ እንድናጠቃልል ነው። አሁን ድካም ተሰምቶኛል፣ከአይሮፕላን ማረፊያ እንደመጣሁ ሳላርፍ ነው በቀጥታ ወደ ኩባንያው የመጣሁት።

- አሁን ሄደህ ማረፍ ትችላለህ፣ከፈለግህ ማታ መቀጠል እንችላለን።

- ከአስር ሰዓት ተኩል በኋላ በሆቴሉ ብንቀጠል ያስቸግርሻል?

- ፈጽሞ . . አስር ተኩል ላይ ወደ ሄቴሉ እመጣልሃለሁ።

- መልካም አብረን ምሳ እንበላለን፤ምናልባትም ይበልጥ ተረጋግተሸ ሳታፋጥጭኝ እንጨርስ ይሆናል።

- ማለት የፈለከው አልገባኝም? ! ዛሬ እንኳ አፋጣጩ አንተ ነበርክ፤አስቀይመህ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

- አፋጣጭ ሆኘ ከነበረ እኔ ነኝ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ። እንዳች ያለችን ቆንጆ መፋጠጥና መቀየም አይገባትም።

- ይህ ያንተ ትሁትነት ነው፣ግን የቀድሞ ማፋጠጥህን ካሁኑ ማሽኩርመምህ ይበልጥ እወደዋለሁ . . ፈገግ ብላ ቀጠለች ፦ እኔ የምኖረው ሕይወቴን በሙሉ ለጌታ ሰጥቼ ነው።

- ከመሄዴ በፊት ብንያምን ብሰናበት ደስ ይለኛል።

- በል እንሄድለት።

ወደ ብንያምን
ቢሮ አብረው አመሩ። ተሸቀዳድሞ ስለ ስብሰባቸው ጠየቃቸው . .

- ውይይቶቹ መልካምና ባለ ብዙ ፈርጅ ነበሩ።

- ፍቀዱልኘና እኔ ወደ ሥራዬ ልመለስ።

- እሽ ሌቪ፣ግና ጆርጅ እንግዳችን ስለሆነ በሚገባ ሊስተናገድ ይገባል።

- ጥሩ ነው፣በሉ ደህና ሁኑ።

- ትንሽ ዕረፍት ለማድረግ ወደ ሆቴሉ እንድሄድ ነው የተስማማነው። ድርድሩን ለመቀጠል ሌቪ በኋላ ወደ ሆቴሉ ትመጣለች . . ውሉን ለመፈራረም በትንሹ ለምን ሁለት ቀን እንደሚያስፈልገን አሁን ተረድቻለሁ፤ክርክርና ማስፋት ትወዳለች።

- ውይይቱን በሆቴሉ ውስጥ የመቀጠል ሀሳቡ ግሩም ሀሳብ ነው፤ከይፋዊ የሥራ መንፈስ ወጣ ባለ ስሜት ዘና ብላችሁ እንድትቀጥሉ ይረዳል።

- ልክ ነህ፤ሌቪ ግን ትንሽ አስቸጋሪ ብጤ ነች !

- ከአስቸጋሪነቷም ጋር ጥሩና ቆንጆም ናት። ዛሬ ወዳንተ ከመምጣቷ በፊት ግትርነቷንና የማክረር አካሄዷን እንድትቀይር እነግራታለሁ።

- መልካም፣ፍቀድልኝ ትንሽ እየደካከመኝ ነው።

- በል ሂድ፣ሾፌሩ ወደ ሆቴል ያደርሰሃል።

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር (3)

ጆርጅ ሰባት ተኩል ላይ ወደ ሆቴሉ ደረሰ። ወደ ክፍሉ ገብቶ አልጋው ላይ ተጋደመና እንቅልፍ ወስዶት ጭልጥ አለ። የነቃው አስር ሰዓት ከሩብ ላይ ነበር . . በችኮላ ፊቱን ተጣጥቦ ልብሱን ሲቀይር የክፍሉ ስልክ እያቃጨለ ነበር . . የእንግዳ መቀበያ ሠራተኛው ሌቪ የተባለች ሴት እየጠበቀችው መሆኑን ነገረው . .
ጆርጅ በፍጥነት ወደ እንግዳ መቀበያው ወረደ።
ሌቪ ወርቃማ ጸጉሯን ለቃ፣ትንሽም ቢሆን ጨዋነት ያላጣና ወደ እራት ምሽት ልብስነት የቀረበ ልብስ ለብሳ አምራ ደምቃ አገኛት . . ጨበጣት።
ቀልብ የሚሰልብ ውበቷን ይበልጥ ያጎላ ፈገግታ ቦግ አደረገችበት . .

- ጧት ከነበርሽበት ይበልጥ ውብ ሆነሻል !

- ለምርጫህ አመሰግናለሁ።

- በይ ወደ ምግብ ቤቱ እንሂድና ምሳ እየበላን ውይይታችንን እንቀጠል።

ወጣ ብሎ የሚገኘውን ጠረጴዛ መረጡና ፊትለፊት ሆነው ተቀመጡ . . ጆርጅ አስተናጋጁን ጠራና የሚፈልጉትን አዘዘ . .

- ስንበላ ስለ ሥራ ባናወራ ምን ይመስልሻል?

- እንዳሻህ።

- እጅግ በጣም ቆንጆ ነሽ፤ባለትዳር ነሽ?

- አይደለሁም፣ገና ነኝ። ከካኽ ትለያለህ የሚል ግምት ነበረኝ።

- እንዴት ማለት?

- አንተ ለሃይማኖት ለኦሪትና ለወንጌል ትኩረት ትሰጣለህ። ካኽ ግን ጭንቀትና ሀሳቡ ሁሉ ገንዘብና ሴት ብቻ ነው።

- ልክ ነው። የምንመሳሰልበት ነጥብስ?

- ገንዘብን ብዙ የማትወድና ውበትም የማያሳስብህ መስሎኝ ነበር . .

- ገንዘብና ቆንጆን የማይወድና የማያሳስበው ሰው ማን አለ? ይሁን እንጂ ማለት የፈለክሽው ነገር አልገባኝም !

- አንተ ከሄድክ በኋላ ስብሰባው በሆቴል እንዲሆን የተደረገበትን ዓላማ ብንያምን ነግሮኛል።

- ምን ማለትሽ ነው?

- አንተም እንደ ካኽ መደሰትና መዝናናት ትፈልጋለህ . . መደሰት ብቻ።

- በይበልጥ አብራሪው !

- ራስህን ብዙ አታጃጅል፣እኔ ዝግጁ ነኝ።

ጆርጅ ሆን ብሎ ለመጃጃል ፈለገ።
ማለት የፈለገችው ያልገባው መስሎ ለመታየት ሞከረ . .

- ውይይቱን ለመቀጠል እኔም ዝግጁ ነኝ፤ግና ምሳዬን ተመግቤ ካበቃሁ በኋላ ነው።

- መልካም፣ሞቅ ያለ ውይይት እንዲሆን ትፈልጋለህ?

- አንቺን ደስ እንዳለሽ።

- ብንያምን የጠየቀኝን ነገር እምቢ ማለት አልወድም፤ስለዚህ አንተ እንደፈለከው ይሁን።

- ብንያምንን ከውይይታችን ጋር ምን አገናኘው? !

- እቅጩን ልናገርና . . እናንተ ወንዶች ስትባሉ ከወሲብ በስተቀር የሚያሳስባችሁ ነገር የለም።

- እኔ የምናገረው ሌላ፣አንቺ የምታወሪው ስለ ሌላ ነገር መሰለኝ !

ጆርጅ ይበልጥ መረዳት፣የሌቪን ንግግር ከካኽና ከብንያምን
አነጋገር ጋር አያይዞ ማስተዋል ጀመረ። ከምግብ ቤቱ ሲወጡ ወደ ሆቴሉ የውጭ መናፈሻ አመራና፦

- የሚስማማሽ ከሆነ በሆቴሉ መናፈሻ ውስጥ እንድንቀመጥ ሀሳብ አቀርባለሁ።

- መናፈሻ ውስጥ !! ደስ እንዳለህ ይሁን !!

- ቦታው አስደሳች ነው፤ለግልጽነትም የሚመች ይመስላል።

- ልክ ነው፤አስደሳች ነው፣ግን ለሰው ዓይን የተጋለጠ ግልጽ ቦታ ነው። ምንድነው የምትፈልገው?

- ውይይታችንን መቀጠል ነው የምፈልገው።

- መጫወቻ እያደረግከኝ ነው'ንዴ? ብንያምን እንደነገረኝ ነግሬሃለሁ፣እኔ ዝግጁ ነኝ።

- እኔም ውይይቱን ለመጀመር ዝግጁ ነኝ፤ብንያምን በተሳሳተ መንገድ የተረዳኝ መሰለኝ፣እኔ ካኽ አይደለሁም።

- ከብንያምን የተረዳሁት ሁለታችሁም አንድ መሆናችሁን ነው፤ለዚህ ነው እንደምታየኝ ዝግጁ ሆኜልህ የመጣሁት።

- መሽኮርመም አልወድም፤ሕይወቴን በሙሉ የምኖረው ለእግዚአብሔር ነው ብለሽኝ አልነበረም?!

- እኔ . . እኔ በነገሩ የተስማማሁት እግዚአብሔርን ለማገልገል ዓላማ ነው።

- እግዚአብሔርን ለማገልገል ዓላማ!! እንዴት ሆኖ?

- እኛ ዘንድ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ዋነኛው አምልኮና አገልግሎት፣የእስራኤልን መንግስት ማገልገል እና የእግዚአብሔርን ምርጥ ይሁዳዊ ሕዝብ መጥቀምና ማገልገል ነው።

- አዝናለሁ፤አንቺ ባጣም ርካሽ ነሽ!! ቢያንስ ቢያንስ ለሰብእናሽ እንኳ ቅንጣት ክብር አትሰጭም?!

- በአጥቂነት የጀመርክ ብትሆንም በግልጽነት ነው የምናገረው። በአይሁዳዊነት ውስጥ ሴት ልጅ ያላት ቦታ የተለየ ነው፤እንደ ወንድ አትታይም . . በዚህ ላይ መናገር ደስ አይለኝም። መልካም ፈቃድህ ሆኖ ርእሱን ብትቀይረው?

- አልገባኝም?! ሳትወጅ እንድትናገሪ አልፈልግም። ግን ውይይትና ክርክር እወዳለሁ ብለሽኝ አልነበር? !

- ውይይት እወዳለሁ ግን በተሳሳተ መንገድ እንዳትረዳኝ እፈራለሁ . . በትክክለኛው መንገድ እንደምተረዳኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

- እባክሽን ቀጥይ።

- ወሲብና ሴት በአይሁድ ሃይማኖት ውስጥ ያላቸውን ቦታ ለማወቅ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ ማየት አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ያህል እኛ ዘንድ ትክክለኛው ተፈጥሯዊ ወሲብ በባልና ሚስት መካከል ልጅ ለመውለድ ዓላማ ተብሎ የሚደረገው ብቻ ነው። ይሁን እንጂ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ሴት የተዋረደችና እንደ ሕጻን ወይም እንደ እብድ ወይም እንደ እንስሳ ነው የሚያዩዋት። ወንድን ለማስደሰት ብቻ የተፈጠረች ናት። ቴልሙድ ውስጥ ፦ ‹‹ሴት በዓይነምድር የተሞላች እቃ ናት›› . . የሚል ሰፍሯል። (በቁጣ ዞር አለችና) ፦ ይኸን ነው የፈለከው?! ወይስ ያለህን ነገር ከፈትለፊትህ በተቀመጠች በዚች የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ማራገፍ ትፈልጋለህ?!

- አስከፍቼሽ ከሆነ ይቅርታ አድርጊልኝ፤በእውነቱ ይህ የከፋ አድልዖና ጭቆና ነው የሚል እምነት አለኝ። ዘና ባለ መንፈስ እንድናሟላ እሻለሁ። እንዲያ እንድትሆኚ የሚያስገድድሽ ነገር ምንድነው?

- ብንያምን ነው ! ትእዛዙን መፈጸም ግዴታዬ ነው !

- አልገባኝም ! የተነሳውን ነገር ለብንያምን ትእዛዝ በፍጹምነት ተገዥ ከመሆን ጋር ምን ያገናኛል?

- ብንያምን የናቴ ባል ነው።

- አባትሽ !

- አይ፣አይደለም፤አባቴ ባንድ ወራዳ ሙስሊም አሸባሪ ፍንዳታ ነው የተገደለው . . አጎቴ እናቴን ወረሳት፣ሚስቱ ሆነች። ኦሪት ዘዳግም ውስጥ ባል የሞተባት ሴት የባልዋን ወንድም ማግባት አለባት የሚል ሰፍሯል።

- እናትሽን አጎትሽ ወረሳት! የምትወረስ እቃ ነች ማለት ነው ?!

- አዎ፣በጣም የሚያሳዝነው የባልዋን ወንድም ለማግባት ትገደዳለች።

- ይቅርታ አድርጊልኝ፤አንቺን ማስተባበሌ አይደለም፣ግን የምትናገሪውን ማመን ይከብደኛል ! አክራሪ አይሁዳዊት ነኝ እያልሽም ኦሪትን ከሚገባው በላይ እየወረፍሽ ነው የሚመስለኝ !

- ዋይ፣ምናልባት ሞቅ አድርጌ ተናግሬ ይሆናል ! ለነገሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት አልወድም፣አንተ ነህ የፈለከው ! (ቀና ካለች በኋላ እንደ ገና አቀርቅራ) ፦ እስካሁን ብዙውን ላለመናገር ራሴን ቆጥቤያለሁ።

- ከተናገርሽው ይበልጥ የከፋ ነገር አለ ማለት ነው?!

የሌቪ ውብ ዓይኖች በእንባ ተሞሉ፤ቀጠለች . .

- እስከ ጠየከኝ ድረስ፣አዝናለሁ አዎ አሉ ! ያንድ መቶ ሴቶች ምስክርነት ከአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል ነው ! ሴት ሳይጣናዊ ፍጡር ናት፣በፍጥረቷ ከወንድ ያነሰች ናት ! . . ተልሙድ ውስትጥ እንደተመለከተው ሁሉ ፦ ‹‹ወንድ በሁለት ሴቶች መካከል፣ወይም በሁለት ውሾች መካከል፣ወይም በሁለት አሳሞች መካከል መተላለፍ የለበትም። ሁለት ወንዶችም ሴት ወይም ውሻ ወይም አሳማ በመካከላቸው እንዲያልፍ መፍቀድ የለባቸውም።›› እኔ ሴት ስለሆንኩ በየዕለቱ ማለዳ ላይ በመንፈሳዊ ስሜት ተናንሽ ፦ ‹‹በፈቃድህ መሰረት የፈጠርከኝ ጌታ አንተ የተባረክ ነህ›› ብየ እጸልያለሁ። ወንዱ ግን ‹‹ጣዖት ወይም ሴት ወይም አላዋቂ አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አንተ የተባረክ ጌታ ነህ›› ብሎ ነው የሚያመሰግነው።

ጆርጅ ውቧን ሌቪና የሚያነቡ ሰማያዊ ዓይኖቿን በአዘኔታ ስሜት እየተመለከተ ነበር። ባላሰበው ሁኔታ ከርሷ ጋር ለተጣበቀው የገዛ ልቡና ዓይኖቹም እንዲሁ ማዘናቸው አልቀረም። ከአፍዋ በሚወጣ እያንዳንዱ ቃል ስሜቱ ተነክቷል . .

- ይቅርታ አድርጊልኝ . . ርእሱን እንለውጥ ይሆን? በጣም አደከምኩሽ፣በማስቸገሬ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

- ከመጀመሪያው ብየህ ነበር።

- መቼም እነዚህ ነገሮች ሁሉ በእርግጥ ለአይሁዳዊት ሴት ብቻ አይሆኑም !

- ፈጽሞ . . ይህ ለአይሁዳዊቱ ብቻ ነው። አይሁዳዊት ያልሆነችው ሴትማ ጉዳዩዋ ሌላ ነው!! እንደማትናደድና እንደማትከፋ ተስፋ አደርጋለሁ፤ሴት ቴልሙድ ውስጥ (ከኦሪት ቀጥሎ ሁለተኛው የአይሁዶች መጽሐፍ ነው) የሚከተለውን እናገኛለን ፦ ‹‹ከእስራኤል ሕዝብ ወገን ያልሆነች ሴት እንስሳ እንጂ ሌላ አይደለችም። ስለዚህም ከርሷ ጋር ዝሙት መፈጸም ወንጀል ተደርጎ አይቆጠርም፣የእንስሳት ዝርያ ናትና።››

- ምን ዓይነት ዘረኝነት ነው ! እንዴት ያለ አድልዖና ጠባብነት ነው! አሁንም እደግማለሁ የምትይውን ነገር አምኖ መቀበል ይከብደኛል። ስለ አይሁዳዊነት አንብቤያለሁ፣ኦሪትንም አብዛኛውን አንብቤያለሁ፤ይሁን እንጂ ምናልባት አንቺ ራስሽ ኦሪትን እንዳሻሽ እየተረጎምሽ ነው የሚመስለኝ።

- እንዲወጣልኝና እንዲቀለኝ በዝርዝር ለምን እንደነገርኩህ አላውቅም! ለግንዛቤ ያህል እናንተ ፕሮቴስታንቶች ወንጌልን እንደምታነቡት እኛ ኦሪትን አናነብም።

- እንዴት?

- ኦሪት የአምላክ መልክት ሲሆን ቴልሙድ ደግሞ የኦሪት ትንታኔና ማብራሪያ ነው። ኦሪትን ከቴልሙድ ለይተን በተናጠል መረዳት ትክክለኛ ተደርጎ አይወሰድም።

- ቴልሙድን ማነው የጻፈው?

- በአንድ ሺህ ዓመታት ውስጥ የተጻፈ ሲሆን ጸሐፊዎቹም እጅግ ብዙ ናቸው። ለምን ጠየቅህ?

- በጣም ስለ ተከፋሁና የሴቶች ጉዳይ በጣም ስለ አሳዘነኝ ነው። ከይቅርታ ጋር ስለ ሴቶች የነገርሽኝን ነገር አምኖ መቀበል ከብዶኛል።

- የነገርኩህ በአብዛኛው በቀጥታ ከኦሪት የተጠቀሰ ነው። ከቴልሙድ እንዲነግርህ ትፈልጋለህ? የቴልሙድ መጽሐፎች ጠቅላላ ድምር ስልሳ አራት ጥራዝ ነው። በውስጡ ከሰፈሩት ነገሮች ውስጥ ጥቂቱን መስማት ትፈልጋለህ?

- የሚያስከፋሽ ካልሆነ እባክሽን ንገሪኝ።

- እንግዲያውስ ድንቃድንቁን አዳምጥ . . በአንደኛው የቴልሙድ መጽሐፍ ውስጥ የሚከተለውን ታነባለህ ፦ ‹‹ሴት ሕጻን መሬት በማጽዳት ላይ እያለች ለማዳ ውሻ ዘሎባት ብልቱን አስገብቶ ቢገናኛት የረከሰች ተደርጋ አትቆጠርም፤እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሓኻም ድረስ እንዲያገባት ይፈቀድላታል!›› ለሴት ልጅ ወሲብ መፈጸም የሚፈቀድላትን የዕድሜ ገደብ ቴልሙድ በሦስት ዓመት ከአንድ ቀን ይወስናል!! በዚህ ዕድሜ ላይ ያለች ሴት ሕጻን የሓኻም (የሃይማኖቱ ከፍተኛ ሊቅ) ሚስት መሆን ችላለች።›› ወንድ ልጅ ወሲብ መፈጸም የሚፈቅድለትን ዕድሜ በተመለከተ የቴልሙድ ጸሐፊዎች በዘጠኝ ዓመት ከአንድ ቀን ይወስናሉ። አንዳንዶቹ ሓኻሞች ደግሞ ስምንት ዓመት ከአንድ ቀን ያደርጉታል። ቴልሙድ ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል ፦ ‹‹አንድ ወንድ ዕድሜዋ ከሦስት ዓመት ከአንድ ቀን በታች ከሆነች ሴት ሕጻን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ወሲብ ተደርጎ አይቆጠርም!! ይህ ሰውየው በልጅቷ ዓይን ውስጥ ጣቱን እንዳደረገ ብቻ ነው የሚቆጠረው!! ዕድሜው ከዘጠኝ ዓመት ከአንድ ቀን በታች የሆነ ልጅ ከደረሰች ሴት ጋር ወሲብ ቢፈጽም በእንጨት ስንጥር እንደ ወጋት ያህል ስለሚወሰድ ዝሙት ተደርጎ አይቆጠርም!! በእንስሳት ወሲብ መፈጸም ዝሙት ተደርጎ አይቆጠርም፣አድራጊውም አይቀጣም ! ከእንስሳት ጋር ወሲብ የፈጸመች ሴትም ዝሙተኛ አይደለችም፣መቀጫም አይጣልባትም፣የሚቀጣው እንስሳው ነው! ቀጥ ብሎ ባልቆመ ብልት ግንኙነት መፈጸምም እንደዚሁ ከዝሙት አይቆጠርም፣ቅጣትም አያስከትልም !

- ይቅርታ፣ይቅርታ ይበቃል። ይህ አነጋገር አቅለሽልሾኛል። አሁንም ለግልጽነቴ ይቅርታ አድርጊልኝና አንድ ጥያቄ አለኝ ፦ ለመሆኑ አንቺ ሃይማኖተኛ ነሽ ወይስ በአይሁድ ሃይማኖት ላይ ቂምና ቁጭት ያለሽ ሰው ነሽ?! በድጋሜ ይቅርታ አድርጊልኝና ሁሉም አይሁዶች እንደዚህ አይመስሉኝም !

- ልክ ነው . . ሁሉም አይሁዶች እንዳልኩህ አይደሉም፤እንደ ወዳጅህ እንደ ካኽ ያሉና ኦሪትም ሆነ ቴልሙድ ግድ የማይሰጣቸው ሴኩላሪስቶች አሉ። ሌሎች ብዙ የተለያዩ ሴክቶችም ይገኛሉ። አሳዛኝ ሆኖ እኛ ግን በጣም አጥባቂ ከሆነ ሃይማኖተኛ ቤተሰብ ነን፤እኔም ሃይማኖተኛ ነኝ። እናም ያልኩትን ሁሉ ለምን እንደነገርኩህ አላውቅም! ምናልባት ወጥቶልኝ እንዲቀለኝ ፈልጌ፣ወይም ተሳስቼ፣አሊያም ራሴን ላንተ ለማቅረብ መጥቼ እምቢ ስትለኝ የተዋራጅነት መንፈስ ተሰምቶኝ ራሴን ለመከላከል አድርጌው ይሆናል።

- ፈጽሞ አንቺን ለማዋረድ አልፈለኩም፤ይህ ጠባየም አይደለም። ለመሆኑ ብንያምን አንቺን ወደኔ ሲልክሽ ምን ፈልጎ ነው?

- በትክክል ምን እንደሆነ አላውቅም። የማወቀው ነገር ቢኖር ገና ያልሰጠኸው ገንዘብ አንተ ዘንድ እንዳለ ነው። እኔ በገላዬ አንተን እስካላዝናናሁ ድረስ ገንዘቡን እንደማትሰጠው አድርጎ ያመነ ይመስለኛል።

- ገላሽ ውብና ግሩም ድንቅ ነው፣ብደሰትበት በጣም ደስ ባለኝ ግና . . እኔ ባለትዳርና ለመርሆዬ የምገዛ ሰው ነኝ። ምናልባት ከሚገባው በላይ አጥባቂ ሆኜ ይሆናል። ይቅርታ አድርጊልኝና ብንያምን በተሳሳተ መንገድ ተረድቶኝ ይሆናል። እኔ ፈጽሞ እንዲህ አላልኩትም፣እንደዚያ ማለትም ፈጽሞ ተገቢዬ አይደለም።

- አዝናለሁ፣መቼም እኔ የመገልገያ ሸቀጥ ነኝ . . (ዓይኖቿ እንባ አቀረሩ፣ራሷን መቆጣጠር ተስኗት ለቅሷ ፈነዳ) . . ምናልባት በካኽ ምክንያት እንደዚያ ገምቶህ ይሆናል።

- እባክሽን ተረጋጊ . . ካኽ ከተፈጠረው ነገር ምን ግንኙነት አለው?

- ካኽ በመጣ ቁጥር ለብንያምን ይነግረውና አንድ ወይም ሁለት ቀን አብሬው አድራለሁ። ካኽ ይሁዲ ነው፣ለዚህ ነው ኮንትራቱም ሴቱም ገንዘቡም ለርሱ የሚደረገው። በመሆኑም የካኽ መልክተኛም ልክ እንደ ካኽ ሊስተናገድ ይገባል ማለቱ ነው፣ዋይ ውርደቴ ! ዋይ ቅለቴ !

ጆርጅ የሌቪን እንባ ሲመለከት የሚናገረው ጠፋው . . ማራኪ ውበቷንና ትኩስ እንባዋን እየተመለከተ በዝምታ ቆየ። ከልብ አሳዘነችው፣ገላው ወደ ገላዋ ሲሳብ ተሰማው።
እንደሷ ላለች ሴት አዋራጅና አሰቃቂ የሆኑ ቃላት እንዲትናገር ስለ ገፋፋት የአጥፊነት ስሜት ተሰማው . .

- ሌቪ እባክሽ እንባሽን ጥረጊ . . በጣም አዝናለሁ፣ሁለተኛ እንዲህ ያለውን ነገር አላነሳመም። ፍንጃን ቡና ቢመጣልሽስ?

- ይቅርታ አትጠይቅ . . አንተ ምንም አላጠፋህም።

ወደ ሆቴሉ ካፌ አብረው ሄዱ። ጆርጅ የጨዋታውን ርእስ ለመለወጥና ከሥጋዊ ስሜቱ ራሱን ለማራቅ ቆርጧል . .

- ከኩባንያችን ጋር የደህንነት ጥበቃ ውሉን መፈረም በተመለከተ ያለሽ ስጋት ምንድነው?

- ምንም ስጋት የለኝም።

- ላንቺ ጥያቄዎችና ለስጋቶችሽ መልስና ማብራሪያ እንድሰጥ ስለ ተጠየቀ ነው ከእንግሊዝ አገር የመጣሁት።

- አይ፣እውነቱ እንኳ ለብንያምን የሚሰጠውን ገንዘብ ይዘህ እንድትመጣ ስለ ተፈለገ ብቻ ነው። ገንዘቡን አምጠተህ ለብንያምን አስረክበህ ከሆነ ውሉ እንደተፈረመ አድርገህ ቁጠረው።

- በእርግጥ ገንዘቡን ይዣለሁ፣ላንቺ ላስረክብ ወይስ ለብንያምን ልስጥ ?

- ለብንያምን ስጥ . . (በአዘኔታ መንፈስ ፈገግ አለችና) ፦ አንተም ጭምር ከመርሆህ ጋር ተጻራሪ ቢሆን እንኳ ለብንያምንና ለካኽ አገልግሎት ለመስጠት ትሰማራለህ ማለት ነው !

- በጣም አዝናለሁ፣የምትናገሪው ሁሉ እውነት ነው። መወዳደር የነበረብን በምርታችን ጥራት እንጂ በጉቦና በሙስና መሆን አልነበረበትም . .

- እናም አይሁዳዊነት ከክርስትና የከፋ አይደለም ማለት ነዋ !

- ሊሆን ይችላል፣ይህን ያህል ለኔ ግልጽ ከሆንሽልኝ ዘንዳ እውነታውን እንድነግርሽ ፍቀጂልኝ።

- የትኛውን እውነታ ነው ? !

- ለትላልቆቹ ጥያቄዎቼ ምላሽ ማግኘት ባለመቻሌ ምክንያት ለጭንቀትና ለውጥረት ከተጋለጥኩ በኋላ በደስተኝነት ፍለጋ ጉዞ ላይ እገኛለሁ። ለዚህም ሃይማኖቶችን መመራመር ጀመርኩ። አሁን አይሁዳዊነትን በመመርመር ላይ እገኛለሁ፤ከዚያ ክርስትናንና እስላምን አስከትላለሁ።

- ‹‹ደስተኝነት›› ግሩም ድንቅ ቃል ነው፣ዳሩ ግና በአይሁዳዊነት ውስጥ በተለይ ለወንዶች ብቻ የተወሰነ ነው የሚመስለው፣ወንድ በሆንኩ ብዬ ሁሌም እመኛለሁ !

- ደስተኛ ለመሆን አይደለም እንዴ ሃይማኖተኛ የሆንሽው ?

- ነበረ፣ግና የወዳኛው ዓለም ደስተኝነት ብቻ ነው መሰለኝ።

- ሃይማኖትሽን ለምን አልለወጥሽም ?

- አይሁዳዊነት ከከክርስትና እና ከእስላም የተሻለ ነው። ጥንታዊው ሃይማኖት ከመሆኑም በላይ የአይሁድ ሕዝብም ምርጡ ሕዝብ ነው። የተናገርኩት ሁሉ ምናልባት የተሰማኝን የተዋራጅነት ስሜት ከራሴ ለማባረር ሊሆን ይችላል። ይቅርታ አድርግልኝና መርሆዎችህን ተጻርረህ ጉቦ ስትሰጥ ግን የተዋራጅነት ስሜት አይሰማህም ?!

- አዎ ይሰማኛል፤ሕይወት ብዙ ጊዜ ወደ ሰዎች መጫወቻ እቃነት ትለውጠናለች። ግና ተጫዋቾቹ በሙሉ አይሁዶች መሆናቸውን አላስተዋልሽም?!

- እህህ፣ይህማ ትክክለኛና ተፈጥሯዊ ነገር ነው። እኛ ምርጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን . . እናም ይህን ተመራጭነት ይህን አይሁዳዊነት እንድተው ትፈልጋለህ?!

- ውበትሽ በድጋሜ ቦግ እንደማለቱ፣የውሉ ጉዳይ እና ጥቄዎችሽም እልባት ያገኙ እንደ መሆናቸው፣በአይሁዳዊነት ላይ የጀመርነውን ውይይት ብንቀጠል ቅር ይልሻል? የሴቶችን ጉዳይ አናነሳም፣ይህን ዕድሜ ጠገብ ሃይማኖታችሁን ይበልጥ ማወቅ እፈልጋለሁ።

የጆርጅ ስልክ አቃጨለ፣ብንያምን ነበር የደወለው።
ለማናገር ሌቪን ይቅርታ ጠየቀ . . ከሌቪ ጋር ምን ላይ እንደ ደረሱና ግንኙነታቸው እንዴት እንደ ነበረ ለመጠየቅ ነበር የደወለው . .

- ደህና ነኝ፣ሌቪም ደህና ነች፤ሥራችንን በተመለከተ አሁንም በመወያየት ላይ ነን።

- እንዴ ! እስካሁን አላጠናቀቃችሁም ?

- ገና ነው . . ምናልባት ዛሬ እንጨርሰው ይሆናል።

- ከፈለክ ዛሬና ነገ በሆቴሉ ማሟላት ትችላላችሁ፤እኛ የምትፈልጉትን ሁሉ ለመታዘዝ ዝግጁ ነን።

- መልካም፣ከተቻለ ግን ነገ ላገኝህ እፈልጋለሁ፤ውሉን እንድንፈራረም ላንተ የሚሰጥ ቼክ ይዣለሁ።

- ከሌቪ ጋር ከጨረሳችሁት እኔ በፈለከው ሰዓት ታዛዥ ነኝ።

- አመሰግናለሁ፣ሰዓት ለመቀጣጠር እደውልልሃለሁ።

- ስልክህን እጠብቃለሁ፣ከፈለክ ሌቪ ነገ በቅድስቷ ከተማ አንዳንድ ቦታዎችን ለመጎብኘት ልትወስድህ ትችላለች።

- በዚህ ላይ ከርሷ ጋር እንመካከራለን . .

- በሉ እንግዲህ፣ጌታ ይባርካችሁ።

ጆርጅ የስልክ ጥሪውን አበቃ።
ወደ ሌቪ ውብ ሰማያዊ ዓይኖች ተመለከተ . .

- ብንያምን የቼኩን ጉዳይ ማረጋገጥ ነው የፈለገው።

- ከኔ የተፈለገውን ሁሉ መፈጸሜንም ማረጋገጥ ነው የፈለገው።

- አንድ ጥሩ ሀሳብ አቅርቦልኛል።

- ጥሩ ሀሳብ ያመነጫል ብዬ አልገምትም፣ምን አለ ?

- ነገ ወደ ቅዱሳን ሥፍራዎች ለጉብኝት እንድንሄድ ነው።

- መልካም ነው . . ግን እንግዳ ነገር ነው። አንዳንድ ጊዜ ካልተጠበቀ ሰው ጥሩ ሀሳብ ይቀርባል።

- አሁን አስራ ሁለት ሰዓት ነው፣ከፈለክ ስለ አይሁዳዊነት የጀመርነውን እንቀጥለሳለን። ነገ ደግሞ የአይሁድ ቅዱሳን ሥፍራዎችን ለመጎብኘት በጧት እጠብቀሃለሁ።

- መልካም፣አሁን በውይይታችን እንቀጥልና የቅዱሳን ስፍራዎች ጉብኝታችን ተነገወዲያ ማለትም ቅዳሜ ይሁን እላለሁ። (በመቀጠል በማፈር ስሜት ፈገግ አለችና) ፦ ቅዳሜ ለጉብኝት እንሄዳለን፣ሌላ የምትፈልገው ነገር ካለ ዛሬ ወይም ነገ ነው።

- ሌላ ነገር . . ገባኝ፣በእርግጥ ውበትሽ ተፈታታኝ ነው።ይሁን እንጂ እኔ ባለትዳር ነኝ፣መርሆዬ ይከለክለኛል ብየሻለሁ።

- የበለጠ ግልጽ ለመሆን፣ባለትዳርና ሃይማኖተኛ የሆኑ ክርስቲያኖች ናቸው እንዲህ ያሉ ነገሮችን እምቢ የማይሉት።

- ልክ ነው . . አዝናለሁ እውነትሽን ነው። እኔ ግን በባለቤቴ ላይ ክህደት መፈጸም ስለሆነ ለኔ ተገቢ አይደለም የሚል እምነት አለኝ፤እሷ እንድትፈጽም እንደማልቀበል ሁሉ እኔም አልቀበልም።

- የማስመሰል ሳይሆን አንተ በእውነት ድንቅ ሰው ነህ፣ላንተ ያለኝ አክብሮት የበዛ ነው።

ግልጽ በሆነ የአድናቆት ስሜት ሁለቱም ዓይን ለዓይን መተያየቱን ቀጠሉ። ሳያስብ እጁ ለስላሳ እጇን ያዝ አደረገ፤ግን ወዲያውኑ ነቃና እጁን አላቆ በማፈር ስሜት እንዲህ አላት . .

- ምስጋና የሚገባው ላንቺ ነው። እኔ መመስገን ያለብኝ አይመስለኝም። ዋናው ነገር አንቺ እንዳልሽው ጉብኝታችን ቅዳሜ ቢሆን መልካም ነው ባይ ነኝ።

- ጥሩ . . ውይይታችንን እንቀጥል።

- ኦሪትንና ተልሙድን ይበልጥ ለማወቅ እፈልጋለሁ።

- እንዳልኩህ ሁሉ ኦሪት ከእግዚአብሔር የተላለፈ ነው ብለን ነው የምናምነው። ተልሙድ ግን የኦሪት ማብራሪዎች፣ትንታኔዎችና ሕግጋት ዝርዝር ሲሆን ቀደም ብሎ በቃል ሲተላለፍ ቆይቶ ኋለ ላይ በጽሑፍ የተጠናቀረ ነው።

- ቴልሞድ የሰዎች ቃል ነው ማለት ነው !

- አዎ፣ግን በርሱ አማካይነት ብቻ እንጂ ኦሪትን መረዳት አይቻልም። ቅድም እንዳልኩህ እኛ እንደ ክርስቲያኖች አይደለንም።

- ኦሪት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ ለምን አትወስዱትም ?

- ላንተ ፍጹም ለመሆን ቃል ገብቻለሁ፤እውነቱን ለመናገር ኦሪት ራሱ ብዙ ችግሮች አሉበት። ምናልባት ስለ ሴቶች የሚናገረውን አንብበህ ይሆናል።

- የእግዚአብሔር ቃል እንዴት ችግር ይኖርበታል? አልገባኝም!

- በጣም ያሳዝናል፣እኛ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ ነው እንላለን፤ዳሩ ግን የመዛባትና የመለዋወጥ ሁኔታ የደረሰበት መሆኑን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ይገኛሉ።

- ስለ መዛባቱ ማስረጃ ?! ኦሪጂናል ቅጂው ዬት ነው ያለው ?

- የኦሪት ኦሪጂናል ቅጂ ጠፍቷል። ያሉት ሦስት የተለያዩ ቅጂዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ጭማሬ ያለባቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ እርስበርስ የሚጋጩ ነገሮች አሉባቸው። ከሦስቱ ቅጂዎች አንዱ የሆነው የግሪክ ቅጂ እሰከ አስራ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ተሰጥቶት የቆየ ቅጂ ነው። በዚያን ጊዜ ውስጥ የዕብራይስጡን ቅጂ የተዛባና ተአማኒነት የጎደለው አድርገው ይቆጥሩት ነበር። የግሪክ ቅጂ በግሪክ ቤተክርስቲያንና በተቀሩትም የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ አሁንም ድረስ ተቀባይነት ያለው ቅጂ ነው። የዕብራይስጡ ቅጂ ደግሞ በአይሁዶችና በፕሮቴስታንቶች ዘንድ ዕውቅና የተሰጠው ሲሆን 39 መጽሐፎችን ያካተተ ነው። እስከ አስራ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የግሪኩ ቅጂ በክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት የተቸረው ትክክለኛው ቅጂ ተደርጎ ሲወሰድ የቆየ ሲሆን፣የዕብራይስጡ ቅጂ ግን በወቅቱ ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት በነበረው በግሪኩ ቅጂ ላይ ጥርጣሬ ለማሳደር ዓላማ ሆን ተብሎ በአይሁዶች እጅ በ130 ዓመተ ልደት እንዲዛባ ተደርጓል ተብሎ ይታመናል። ማዛባቱ ከክርስቲያኖች በተጨማሪ ሳምራውያን አይሁዶችንም ዒላማ ያደረገ ነበር። በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የፕሮቴስታንት እምነት ከመጣ በኋላ ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና ፕሮቴስታንቶች ለዕብራይስጡ ቅጂ ትክክለኛነት ዕውቅና በመስጠት የግሪኩ ቅጂ የተዛባና ተአማሚነት የሌለው ነው የሚል አቋም ማራመድ ጀመሩ። ሦስተኛው የሳምራዊው ቅጂ ነው። ሳምራ በናፖሊስ ተራሮች የሚኖሩ አይሁዶች ጭፍራ ሲሆን ይህ ቅጂ ከብሉይ ኪዳን ሰባት መጽሐፎችን ብቻ የሚያካትት ነው፡፡ ከሰባቱ ውጭ ያሉት በሳምራ አይሁዶች ዘንድ የተዛባና መሰረት የሌለው ጭማሬ ነው፡፡ ቅጂው በሌሎች ቅጂዎች ውስጥ የማይገኙ ዐረፍተ ነገሮችንና አንቀጾችን ያቀፈ ሲሆን አንዳንድ የፕሮቴስታንት ተመራማሪዎች ከዕብራይስጡ ቅጂ ያነሰ አድርገው ቢወስዱትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከዕብራይስጡ ቅድሚያ ይሰጡታል።

- በጣም የሚገርም ታሪክና ትኩረትን የሚስብ መፋለስ ነው። ይሁንና የዚህ መዛባትና ኢተአማሚነት መገለጫዎች ምንድናቸው ? . . ማለቴ ከሴቶችና ከወሲብ ርእሰ ጉዳይ ውጭ ያሉት ?

- በጣም ብዙ ናቸው! ከነዚህ መካከል ጧት ያነሳነውና ፈጣሪ አምላክን ተገቢው ባልሆኑ ባህርያት መግለጽ አንዱ ሲሆን፣ ነብያትን በኃጢአት ሥራዎች ፈጻሚነትና በእኩይነት መግለጽም ይገኙበታል። ሌሎች ብዙ ብዙ ነገሮችም . .

- ይቅርታ ላቋርጥሽና . . ነብያትን በኃጢአት ሥራዎች ፈጻሚነትና በእኩይነት መግለጽ ነው ያልሽው? !

- ታውቃለህ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደዚህ የምናገረው! እውነቱን ለመናገር ሁኔታዬ ለኔ ለራሴም በጣም አስገርሞኛል። ይሁን እንጂ ይህን በማድረጌ ከውስጤ ደስታ ይሰማኛል፤አንድ ዓይነት የስሜት ማስተንፈሻ መንገድ ይሆን ወይስ የሰይጣን ጉትጎታ?! እኔ እንጃ ግና ይህን በማድረጌ ደስተኛ ነኝ። ምሳሌዎችን ልስጥህ ፦ ኦሪት ውስጥ የእግዚአብሔር ነብይ ኖሕ አስካሪ መጠጥ ጠጥቶ ራቆቱን እንደሆነ ተደርጎ ሲገለጽ እንዲህ ተብሏል ፦ ‹‹ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፣ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤በድንኳኑም ውስጥ ዕወራቆቱን ሆነ።›› ነብዩ ሎጥን በተመለከተም ፦ ‹‹ሎጥም . . ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፤በዋሻም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ተቀመጠ። ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት ፦ አባታችን ሸመገለ፣ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም፤ነዪ አባታችንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋራ እንተኛ፣ከአባታችንም ዘር እናስቀር። አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት፤ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፤እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው። ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ፦ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው፤እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።›› የሚል ሰፍሯል። ሌሎችም ብዙ ብዙ መሰል ነገሮች አሉ። ለጊዜው እነዚህ ሁለት ምሳሌዎች በቂ ይመስሉኛል።

- ሌቪ ይቅርታሽን፣ትተን ባለፍን ቁጥር ለምንድነው ወደ ወሲባዊ ጉዳዮቹ ዳግም የምትመለሺው?

- ላንተ ፍጹም እውነተኛ ለመሆን ለራሴ ቃል የገባሁ በመሆኔ ነው፤የጠየከኝ ደግሞ አንተው ነህ።

- ወደ ሌላ ርእሰ ጉዳይ መሄድ እፈልጋለሁ።

ሌቪ ፈገግ አለች፣ጉንጮቿ በሀፍረት ቀሉ

ቁንጅናዋና ፍካቷ ይበልጥ ደመቀ . .

- እሽ፣በል ቀጥል ጥያቄዎችህን ወደ ወሲብና የሴቶች ጉዳይ እንደማትለውጥ ተስፋ አደርጋለሁ።

የጆርጅ ከጾታዊ ጉዳዮች የመራቅ ጥያቄ፣ከፈትለፊቱ በተቀመጠችው እንቡጥ ጽጌሬዳ ኮረዳ ውበት ምክንያት ዓይኖቹ በአካሉ
ላይ
ከሚያደርጉት
ጉትጎታ
ለመሸሽ
እንጂ
ሌላ አልነበረም። ከፊቱ ከተቀመጠው ፈታኝ ውበት ተጎንጭቶ የመርካት ብርቱ ጥማትና ጥልቅ ፍላጎት እያደረበት የመጣ አካሉን ጆሮው እንዲጎተጉተው አይፈልግም። በካትሪና እና በመርሆው ላይ ክህደት እንዳይፈጽም ስጋት አድሮበታል። ሕይወት ምነኛ ወራዳና ምነኛ አስቸጋሪ ናት! ‹‹ደስተኝነት ነገሮችን አቅልሎ በመውሰድ ውስጥ ነው›› የሚለው የኣደም ተደጋጋሚ ብሂል ትዝ አለው። በውስጡ አጉተመተመና ‹‹ወይኔ ከመርሆዬ ጋር በቀላሉ መኖር በቻልኩ›› ብሎ ርእሱን ለመቀየር ሞከረ . .

- መሰረትሽ ከኦስትሪያ ነው ብለሽኛል።

- ኣይ፣ከእስራኤል ነኝ ነው ያልኩት።

- አዎ፣ማለቴ ወላጆችሽ ከኦስትሪያ የመጡ ናቸው። ይቅርታ አድርግልኝና በእንግሊዝ አኃዛዊ መረጃ መሰረት በ1945 በፍልስጥኤም ውስጥ የአይሁዶች ቁጥር 38%፣የሙስሊሞች ቁጥር 58%፣የክርስቲያኖች ቁጥር ደግሞ 8% ነበር። ዛሬ ያለው የአይሁዶች ቁጥር ከፍ ያለው ከ500000 እስከ 600000 የሚደርሱና አይሁዶች ነን የሚሉ ሰዎች ከ1920 እስከ 1945 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ መጥተው በመስፈራቸው ምክንያት ነው። ታዲያ ከውጭ መጥታችሁ መሬታቸውን በወረራ የያዛችሁት እናንተ ስትሆኑ እንዴት ነው ሙስሊሞችንና ክርስቲኖችን ሽብርተኞች አድርጋችሁ የምትወስዱት?!

- ይቅርታ . . ወራሪዎቹ እናንተ እንግሊዞች ናችሁ፣እናንተ ናችሁ መሬታችንን የሰጣችሁንና መብታችንን የመለሳችሁልን።

- እንግሊዞች አንቺ እንደምትይው መብታችሁን የመለሱላችሁ ለምንድነው ? ለናንተ ነጻ ግልጋሎት ለማበርከት ዓላማ ብቻ ይሆን?!

- የኔ ጉዳይ መሬታችን መሆኑና ለኛ የተመለሰልን መሆኑ ነው። እንግሊዝ ለኛ አገልጋይ ለምን ሆነች ? የሚለው ላንተ እንጂ ለኔ የሚቀርብ ጥያቄ አይደለም . . እንግሊዝና አውሮፓ እንደ አገለገሉን ሁሉ በአስከፊ ሁኔታ ጨፍጭፈውናል፣ይህን አታውቅም?!

- ሆሎኮስትን ማለትሽ ነው?!

- እኛ ለዘመናት ብዙ የተጨቆን ሕዝብ ነን። ሆሎኮስትም በኛ ላይ ከተፈጸሙት ኢሞራላዊ ግፎች የቅርብ ዘመኑ አንዱ ምዕራፍ እንጂ ሌላ አይደለም።

- ወደዚህ በመጣሁበት ምሽት ካቶሊካዊቷ ባለቤቴ አይሁዶች በክርስቲያኖች ላይ ስለ ፈጸሙት ግፍና ጭቆና ስትነግረኝ ነበር። ሁሉም የዓለም ሕዝቦች ተጨቁነናል ይላሉ ማለት ነዋ!

- ልክ ነህ . . ሌላው ቀርቶ አባቴን የገደሉት አረመኔዎቹ ሙስሊሞች እንኳ ተጨቁነናል ይላሉ። ዳሩ ግና ታሪክና ተጨባጩ ሁኔታ እውነታውን ይሰጡሃል።

- ክርክር እንደምትወጂና ግልጸኝነትም እንደማያስጨንቅሽ ነግሬሽኛል። ታዲያ ሙስሊሞች መጨቆናቸው፣መሬታቸው በወረራ ተወስዶ ከገዛ አገራቸው መባረራቸው፣መገደላቸውና መሰደዳቸው እንዴት አልታየሽም ? !

- ለአሸባሪዎች ይህና ከዚህም የከፋ ይገባቸዋል። ደሞም ይህን ያደረገው ማን ሆነና! ከኛ በፊት እናንተው ናችሁና እኛን አትተቹን።

- ወደ አጥቂነት ተሸጋግረሻል፣ልክ ነው ከናንተ በፊት ለናንተ ስንል እኛ አድርገነዋል። ይሁንና ግፍ የተዋለባቸው ጭቁኖች መሆናቸው እንዴት አይታሽም ?

- ነገርኩህ እኮ፣ይህና ከዚህም የከፋ ነገር ይገባቸዋል። አረመኔዎች፣ኋላ ቀሮች፣ጨካኞችና አሸባሪዎች ናቸው . .

- ፍልስጥኤም ውስጥ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆኑ ክርስቲያኖችም ተጨቋኞች ናቸው !

- ፍልስጥኤም ሳይሆን እስራኤል ማለትህ ነው።

- አዎ፣ክርስቲያኖች እስራኤል ውስጥ ከአይሁዶች በኩል ግፍና ጭቆና ይፈጸምባቸዋል !

- አትቆጣ፣ክርስቲያኖች አያያዛችን ካላማራቸው ወደ አውሮፓና ወደ አሜሪካ ወይም ወደ ፈለጉት ቦታ መሄድ ይችላሉ!

- እህህ፣ይህ ጨካኝ ቁርጠኛ አነጋገርሽ ከቁንጅናሽ ጋር ይጋጫል። አንቺን የመሰለች ውብ ቆንጆ እንዲህ ያለውን ጭካኔ የተሞላበት ግርድፍ ነገር ትናገራለች ብዬ ማሰብ ይከብደኛል!

- እኛን ለማገልገል ዝግጁ ያልሆነ ሁሉ እኛ ዘንድ የሚጠብቀው ግድያ ብቻ ነው! ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ነው።

- የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች እንዲህ ናቸው ማለት ነው ?!

- አዎ፣ኦሪት ውስጥ የሚከተለው ሰፍሯል ፦ ‹‹የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፣በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፣የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው።›› በተጨማሪም ፦ ‹‹እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤ሽማግሌውንና ጎበዙን ቆንጆይቱንም ሕጻናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤›› ይላል። ብሉይ ኪዳን ሌላ ቦታ ላይ ፦ ‹‹አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፣ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፣አትማራቸውም፤ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕጻኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።›› ይለናል፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ይበቁሃል ወይስ ልጨምርልህ?

- ይቅርታ . . አስከፋሁሽ መሰለኝ። ትንሽ ተረጋጊ . . ይኸ ማንም ልሰማው የማይችል ሽብርና ሽብርተኝነት ነው !

- እኔ የተረጋጋሁ ነኝ። የነገርኩህ ግን ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰፈረውን የእግዚአብሔር ቃል እንጂ የራሴን ቃል አይደለም !

ጆርጅ አስተናጋጁን ጠራና የብርቱካን ጭማቂ እንዲያመጣለት አዘዘ . . ውጥረቷንና ስሜታዊነቷን ለመሸሸግ ስትሞክር ወደነበረቸው ሌቪ ዞር አለና . .

- ይበልጥ ለመረጋጋት ምን ይምጣልሽ ?

- መልካም ፈቃድህ ከሆነ የሎሚ ጭማቂ።

ጆርጅ ወደ ሌቪ እተመለከተ፣በውበቷ ልስላሴና በመግደል፣በማፈናቀልና በምትናገረው ርህራሄ አልባ ጭካኔ መካከል ያለውን ተቃርኖ እያስተዋለ ለአፍታ በዝምታ ቆየ . . አቀርቅራ የቆየችው ሌቪ እያነባች ራሷን ቀና አደረገች . .

- አባተ ሞተ፣እኔም የብንያምን መጫወቻ ሆንኩ። ይህ ሁሉ ለዘመናት የተጨቆን በመሆኑ ምክንያት ነው። እናም እነዚያ አሸባሪዎች ተጨቋኞች መሆናቸውን አምኜ እንድቀበል ነው የምትፈልገው?!

- በይ ሎሚውን ጠጭው . . የሚረብሽሽ እስከሆነ ድረስ ይህን ርእስ ተዪው . .

- አይረብሸኝም፣መቀጠል ትችላለህ፤አሁን በጣም ተረጋግቻለሁ።

- ግልጽ ሆነሽ እውነቱን ንገሪኝና አሁን የጠቀስሽያቸውን የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች አምነሽ ትቀበያለሽ ?

- ግልጽ ሆኜ እውነቱን ለመናገር . . አልቀበልም።

- ለምን ?

- ብሉይ ኪዳን በስህተትና በመዛባት የተሞላ ነው ብየህ አልነበረም? እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ ከርህሩሁ እግዚአብሔር አምላክ ዘንድ የተላለፈ ሊሆን አይችልም !

- እውነትሽን ነው . . እግዚአብሔር ርህሩህ አዛኝ ነው።

- እንደገና ወደ ወሲብና ሴቶች ጉዳይ ልመልስህና የሚከተለውን የብሉይ ኪዳን ጥቅስ አዳምጥ ፦ ‹‹አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፣ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ አድኑአቸው።›› (በድጋሜ ፈገግ አለችና) ፦ ከፈለክ ይህን ጥቅስም አክልበት ፦ ‹‹የብንያምንም ልጆች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው ፦ ሂዱ በወይኑም ስፍራ ተደበቁ፤ተመልከቱም፣እነሆም፣የሴሎ ሴቶች ልጆች አታሞ ይዘው ለዘፈን ሲወጡ ከወይኑ ስፍራ ውጡ፣ከሴሎም ሴቶች ልጆች ለየራሳችሁ ሚስት ንጠቁ፣ወደ ብንያም ምድርም ሂዱ።›› (በሹፈት ሳቀችና) ፦ አሁንም ወደ ወሲብና ወደ ሴቶች ተመለስን፣ያሁኑ ግን በግድያና በጠለፋ መልኩ ነው ! ርእሰ ጉዳዩን እርግፍ አድርገን እንድንተወው ትፈልጋለህ ?

- በጣም የሚገርም ነው ! የምሰማውን ለማመን እየተቸገርኩ ነው ! አዎ፣ርእሱን ብንተው ይመረጣል። መልካም ፈቃድሽ ከሆነ ግን የሴሎ ሴት ልጆች ማን ናቸው ? ሴሎስ ማነው ?

- ሴሎ ማለት እኛ ዘንድ በሚሰራባቸው ትንታኔዎች ክርስቶስ ወይም መሲሑ ማለት ነው። ዋናው ነገር የተጠቀሱት አይሁዳዊያት ያልሆኑ የናንተንና የሙስሊሞችን ሴቶች የመሳሰሉ ሴቶች ናቸው። ይቅርታ አድርግልኝና አስበርግገህ ሚዛኔን አሳጣሀኝ።

- ምንም አይደለም፣አሁን ጊዜው በጣም የሄደ ይመስለኛል፤እንድትረጋጊ እራት ልጋብዝሽ።

- ኦህ . . ለካስ ሳይታወቀኝ በጣም መሽቷል፤አሁን ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሆኗል። ትእዛዝህ ከሆነ እሽ እቀበላለሁ፤ አለዚያ ግን መልካም ፈቃድህ ከሆነ መሄድ እፈልጋለሁ።

- እንዲህ ዓይነት አነጋገር አያስደስተኝም፣እኔ አንቺን ለማዘዝ አልመጣሁም። ግልጸኝነትሽ በጣም እንዳስደሰተኝ ነግሬሻለሁ። መታደልን ፍለጋ በማደርገው ጉዞ ላይ ብዙ ትጠቅሚኛለሽ፣ ያንቺ ፍላጎት ከሆነ ብቻ ነው ካንቺ ጋር መወያየት ደስ የሚለኝ።

- ለትህትናህ በጣም አመሰግናለሁ፣እናም ነገ እንገናኝ።

- የምንገናኘው ተነገ ወዲያ ቅዳሜ እንዲሆን ተስማምተናል !

- የአይሁድ ቅዱሳን ስፍራዎችን የምንጎበኘው ተነገ ወዲያ ነው። ከፈለክ ግን ውይይታችንን ነገ መቀጠል ይቻላል።

- ነገ ጧት ብንያምንን ለማግኘት ስመጣ እንገናኛለን። ከተቻለ ግን የትንሣኤ ቤተክርስቲያንን እና የማርያምን ቤተክርስቲያን መጎብኝት እፈልጋለሁ።

- የትንሣኤ ቤተክርስቲያን ግን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን አይደለም፣ፕሮቴስታንት ነኝ ብለህ የለ? . . (መስህብነትን በተላበሰ የመሽኮርመም ስሜት ቀጠለችና) ፦ ወይስ እያታለልከኝ ነው ?

- ለምን አታልልሻለሁ? እጎበኛለሁ ብዬ ለካቶሊካዊቷ ባለቤቴ ቃል ስለ ገባሁ እጎበኛለሁ።

- ባለቤትህን በጣም ትወዳታለህ ማለት ነው። ወደ ብንያምን ቢሮ እንዲያደርስህ ጧት ሁለት ሰዓት ላይ ሾፌሩን እልክልሃለሁ። ነገ ዓርብ ስለሆነ ሁለቱን ቤተክርስቲያኖች ለመጎብኘት በጊዜ መውጣት ይኖርብሃል።

- ዓርብ ነው ስትዪ ምን ማለትሽ ነው?

- ማለቴ በሁሉም መንገዶች ላይ የፍተሻ ኬላዎች ይኖራሉ። አሸደባሪዎቹ ለዓርብ ጸሎት ሲሄዱ የሽብር ጥቃት እንዳይፈጽሙ እርግጠኛ ለመሆን ሲባል ፍተሻዎች ይበዛሉ።

ወደ ቢሮው ለመሄድ ሁለት ሰዓት ላይ ዝግጁ ሆኜ እጠባበቃለሁ . . ብድግ ብሎ ሌቪን ጨበጣትና ዓይን ዓይኗን እያየ ፦ በጣም ነው የማመሰግነው፤ስለ ረበሽኩሽ ይቅርታ አድርጊልኝ።

- ለትሕትናህ፣ለጨዋነትህ፣ለግልጽነትህ፣ለባለቤትህና ለመርሆህ ታማኝ በመሆንህ ማመስገን ያለብኝ እኔ ነኝ።

- አንቺ ግሩም ድንቅ ሰው ነሽ !

- አንተ በምትጓዝበት የደስተኝነት ጎደና ካንተ ጋር ብጓዝ ምነኛ ደስ ባለኝ ነበር! ዳሩ ግና ያለሁበት ሁኔታ አያስችለኝም።

- ማን ያውቃል? ሊሆን ይችላል . . ለማንኛውም አንቺ ቆንጂት ጧት እንገናኛለን።

ሌቪ ከሄደች በኋላ ጆርጅ እራቱን በችኮላ በላ።
ምስሏ ግን ከአእምሮው አልጠፋ ብሎታል . . ከፍተኛ የሆነ የቅርበት ስሜት
አሳድራበታለች፤ለምን እንደሆነ ግን አያውቅም። በተፈታታኝ ውበቷ ምክንያት ይሆን
? ወይስ ለርሱ በጣም ግልጽ በመሆኗ? ወይስ ስለ አሳዘነችው ይሆን? . .
ግራ የመጋባት ስሜት ውስጥ ነው። ፈገግታዋ፣እንባዋ፣ቁጣዋና ስሜታዊነቷ . . ሁሉ ነገሯ ትዝ ትዝ ይለዋል . . ሁለመናዋ ከፊቱ ድቅን ይላል። ከልብ አዘነላት . . የተዛባ ጨቋኝ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ሰለባ ነች . . በእግዚአብሔር አምላክ ስም የሚፈጸምባትን ይህን ሁሉ ግፍና ጭቆና ይህች ሚስኪን ሴት እንዴት ሆና ትቋቋማለች!!
ሌቪንና ውበቷን ለመርሳት እየሞከረ ወደ ክፍሉ ሄደና ዜና ለመስማት ቲቪ ከፈተ። የለንደኑ ፍንዳታ ዜና ጋብ ብሏል፤የፍንዳታው ተጠያቂ የሲታ ተገንጣይ ቡድን መሆኑ፣ሲፈለግ የነበረው ፓኪስታናዊ የተያዘ ቢሆንም ፈርቶ ከመደበቁ ውጭ ከፍንዳታው ጋር ምንም ግንኙት የሌለው መሆኑ በመረጋገጡ በነጻ መለቀቁን ተረዳ። . .
‹‹አንተ ከሪሙሏህ ነጻ መሆንህ ተረጋገጠ!›› አለ ለራሱ። ከዜናዎቹ አንዱ የእስራኤል መንግስት ለነገው የዕለተ ዓርብ የሙስሊሞች ጸሎት ዕድሜያቸው ከሃምሳ በታች የሆኑትን ሙስሊሞች የሽብር ጥቃትን ለመከላከል ሲባል በአል አቅሷ መስጊድ እንዳይሰግዱ መከልከሉን የሚመለከት
ነበር
.
.
ቲቪውን ዘግቶ ኢሜይሉን ከፈተ።
ለአዳዲስ መልክቶች መልስ ከሰጠ በኋላ ሌቪ ከነገረችው የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ጽፎ ለቶምና ለኣደም ለመላክ ወሰነ . . መልእክቱን ከላከላቸው በኋላ ሰዓቱን ሲመለከት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነበር። ለመተኛት ወደ አልጋው ሄደ፣ግና የሌቪን ሀሳብ ከአእምሮው ማራቅ አልቻለም። ምሽቱን ከርሱ ጋር እንዳታድር ባለማድረጉ ተሳስቶ እንደሆን ራሱን ጠየቀ
! አድርጎ ቢሆን ኖሮ፣እሽ ብሏት ኖሮ፣እንዴት ያለ አዝናኝና አስደሳች ሌሊት ይሆን ነበር። እርሷ ለሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኗን ገልጻለት ነበር፤ ከዚያ በፊትም ከካኽ ጋር ፈጽማው ነበር። በዓለማዊ ሕይወት ከመደሰትና አዝናኝ ሕይወትን መኖር የሚከለክል መርህ የምን መርህ ነው?! ካትሪና ከቶም ጋር ክህደት ፈጽማብኛለች ብሎ በገመተ ጊዜ ተሰምቶት የነበረው የቅናትና
የቁጣ ስሜት በዚህ ጊዜ ለምን እንዳስታወሰ አያውቅም። ‹‹ምን ዓይነት የግጭትና የመፋለስ ሁኔታ ውስጥ ገባሁ›› ሲል በውስጡ አጉረመረመ። ለራሴ ክህደት መፈጸም እፈልጋለሁ፣በኔ ላይ ሲፈጸም ግን እናደዳለሁ፤ጉቦ እሰጣለሁ፣ጉቦ የሚቀበል ሰው መርህና ስነ ምግባር የጎደለው ሰው ነው የሚል አቋም አራምዳለሁ። መንፈሴ፣ነፍሴ፣አመለካከቴ፣ሕይወቴ፣ደስተኝነቴና መርሆዎቼ ጽናት ያላቸው እንዲሆኑ ስንቴ እመኛለሁ . .

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር (4)

ጆርጅ ጧት ከሁለት ሰዓት አስቀድሞ ነበር ቁርሱን በልቶ ሾፌሩ እስኪመጣ ድረስ ወደ ክፍሉ የተመለሰው። ልክ ሁለት ሰዓት ከእንግዳ መቀበያ ተደውሎ ሰው እየጠበቀው መሆኑ ተነገረው። ሲሄድ ባልጠበቀው ሁኔታ የመጣው እንደ ተባለው ሾፌሩ ሳይሆን ሌቪ ራሷ ነበረች። በጣም ደስ ብሎት በፈገግታ ጨበጣት . .

- አንቺን ማስቸገር አልፈለኩም ነበር።

- ተገቢህ ነው . . ውይይትህም በጣም ነው የሚያረካኝ።

- ለበጎ ግምትሽ፣ለጸባይሽና ለመልካም ስነ ምግባርሽ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ብንያምን አሁን እቢሮው ይኖራል ?

- አዎ፣እቢሮው ይጠብቀሃል፣እንደምትመጣ ነግሬዋለሁ።

- አመሰግናለሁ፣ረስቼ አልደወልኩለትም ነበር።

ፊቷን በፍካት ያሸበረቀ ማራኪ ፈገግታ አሳየችው . .

- ካንተ ዘንድ ወጥቸቼ ወደ ቤት ከመድረሴ በፊት ካንተ ጋር ማደሬን ለማረጋገጥ ብንያምን ሲደውልልኝ ነበር። አንተ ካኽ አለመሆንህን እና እኔን የማትፈልግ መሆንህን አምኖ አልተቀበለም። ጧት ወዳንተ ስለሚመጣ ከርሱ ከራሱ ማረጋገጥ ትችላለህ ነበር ያልኩት።

በቁርጠኝነትና በምር እየተመለከታት እንዲህ አላት

አይፈልግሽም ያለው ማነው?!

ሌቪ ውስጧ ተረበሸ። የስሜቶቿ፣የአመለካከቶቿ፣የሥጋዊ ፍላጎቶቿ . . ውስጣዊ ግጭቶች ከገጽታዋ በግልጽ ተነበቡ . .

- ምን እያልክ ነው? እኔ ከሄድኩ በኋላ የተለወጠ ነገር አለ'ንዴ?

- ኣይ፣ዕውቀትሽን፣ብሩህ አእምሮሽን፣መንፈስሽን፣ጸባይና ስነ ምግባርሽን እፈልጋለሁ። ገላሽ ግን እንደ ዕንቁ ለእይታና እንደ ጽጌሬዳ ለመዓዛው የሚያጓጓ ነው። ግና ሴትን ከሴትነቷና ከገላዋ አንጻር ብቻ መመልከት አሳፋሪ ተግባር ነው። አንቺን ማጣት ወይም የራሴን መርሆ ማጣት አልፈልግም።

እንደ ስሜቷ ሁሉ ባልተረጋጋ እንቅስቃሴ የጸጉሯን ዘለላዎች ከፊቷ ላይ ከፍ ስታደርግ ግንባሯን በግራ እጇ አባበሰች።

- ወይኔ . . ለምን ብዙ እንደፈራሁ አላውቅም ?

- እርሱ ባቀረበው ሀሳብ መሰረት ቅዱሳን ስፍራዎችን ለመጎብኘት እንደምንሄድ ነግረሽዋል ?

- አልነገርኩትም፣አንተ ንገረው።

- እውነቱን ለመናገር ብንያምን ብዙም አያስደስተኝም፣መርሆዬን ረግጬ ጉቦ ስሰጠው ውርደት ይሰማኛል። ይሁን እንጂ ወደዚህ አገር ከመምጣቴ በፊት በጉዳዩ ላይ አላሰብኩበትም እንጂ አስቀድሜ አስቤበት ቢሆን ኖሮ አልቀበልም ነበር። ለማንኛውም ለአሁኑ ነገሩን እዚህ ላይ እንቋጨውና ስመለስ የሚሆነው ይሆናል።

- መልካም፣አንተ ገንዘቡን ባታስረክበው ኖሮ ብንያምን የተሰጠኝን ሥራ በአግባቡ እንዳልተወጣሁ አድርጎ ይረዳ ነበር።

- የሰው ልጅ ለገንዘብ፣ለወሲብ ወይም ለሥልጣን ብሎ መርሆዎቹን የሚጥስበት ሕይወት ወራዳ ሕይወት ነው !

- ራሴን በራሴ ተጻርሬ ሊሆን ይችላል፤ይሁንና ሰዎች መርሆዎቻቸውን ለገንዘብ፣ለወሲብና ለሥልጣን ብለው ወደ ጎን ባይሉ ኖሮ እስራኤል ባልተመሰረተችና ሕልውናዋን ጠብቃ መቀጠልም ባልቻለች ነበር።

- ጉቦውን ለመስጠት ወደዚያ ሳመራ የሕይወት ወራዳነትና የራሴ የግሌ ወራዳነት ጠልቆ እየተሰማኝ ነው። ካኽ ሲነግረኝ በጉዳዩ ላይ እንዴት ሳላስብበት እንደቀረሁ አላውቅም !

- ለማንኛውም ኩባንያው ይኸውና ደርሰናል፣የውል ስምምነቱን ሰነድ ለፊርማ ዝግጁ ሆኖ ብንያምን ዘንድ ታገኘዋለህ።

- በፍጥነት እንድንጨርሰው እፈልጋለሁ፤ካጠናቀኩ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኖቹ ለጉብኝት የሚወስደኝ ሾፌር ያስፈልገኛል።

- ይቅርታ አድርግልኝ . . እኔ ነገ ወደ ቤተክርስቲያኖቹ ልወስድህ አልችልም፤ሾፌሩ ይጠብቀሃል።

ጆርጅና

ሌቪ ወደ ብንያምን ቢሮ ሲገቡ ብንያምን ብድግ ብሎ
ሞቅ
ያለ
አቀባበል በማድረግ
ጆርጅን
በፈገግታ
ጨበጠው . .

- ትናንት ቀናችሁን እንዴት አሳለፋችሁ? አዳራችሁስ እንዴት ነበር?

- ከሌቪ ጋር ብዙ ሥራዎችን ያጠናቀቅንበት ጥሩ ቀን ነበር።

- አዎ . . ውሉን ለመፈራረም ዝግጁ መሆንህንና ለቴክኒካል ስጋቶቿ ምላሽ የሰጠህ መሆንህን ሌቪ ነግራኛለች። (ወደ ሌቪ ዞር ብሎ) ፦ ከጆርጅ ጋር ውሉን ተፈራርመን እስክንጨርስ ድረስ አንቺ ወደ ሥራሽ መሄድ ትችያለሽ።

- አንዳንድ ሥራዎች ስላሉኝ እሄዳለሁ . . (ወደ ጆርጅ ዞር ብላ) ፦ እንደ ጨረስክ ሾፌሩን ታገኘዋለህ።

- ለምን ሾፌር ? ሌቪ ራሷ ልትወስድህ ትችላለች ? አልተመቸችህም እንዴ ? አልማረከችህም ?

- አንተ ባቀረብከው ሀሳብ መሰረት ነገ አብረን በቅዱሳን ስፍራዎች ጉብኝት ለማድረግ ተስማምተናል፤ዛሬ ግን ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ነው የምጎበኘው።

- ሌቪ ትናንተ ካንተ ጋር እንዴት ነበረች?

- ግሩም ድንቅ ሰው ናት።

- ማታ ሦስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ደውዬላት ወደ ቤቷ ለመድረስ እንደ ተቃረበች ስትነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ። ግሩም ድንቅ ናት ካልክ የበለጠ ጊዜ ወስደህ አብረሃት ማሳለፍ ትችል ነበር።

- ውይይታችንን ማታ ሦስት ሰዓት ላይ ስናበቃ ነው የሄደችው። ውሉን ለመፈራረም አንተን ለማግኘትና ጉዳዩን ለመጨረስ በስልክ ነግረህ ነበር . . ይህ ከካኽ የተላከልህ ቼክ ነው።

- አንተንም ካኽንም አመሰግናለሁ። ይኸውና ውሉ ለፊርማ ተዘጋጅቷል።

- ጨረስን ?

- አዎ የውሉን ጉዳይ አጠናቀናል። ግና ከኛ ጋር ሦስት ቀናት አሉህ፣እኔና ሌቪ ለአገልግሎትህ ዝግጁ ነን።

- ስለ መስተንግዶህ አመሰግናለሁ።

- ነገ ከጉብኝታችሁ በኋላ አብራችሁ ለማምሸት ወደ ሆቴልህ እንድትመጣልህ ከፈለክ እንኳ እርሷ ዝግጁ ነች።

- ከጉብኝቱ በኋላ ይደካክመኛል ብዬ አስባለሁ፣በመሆኑም ለማረፍ በጊዜ መተኛት ስለሚያስፈልገኝ ማምሸት አልችልም !!

- እህህ፣ሌቪ በማዝናናት እንድታሳርፍህ ሞክር . . ካኽ ውል ለመፈረም ሲመጣ ሌቪ አዝናንታው ካላስደሰተችው በስተቀር ፈጽሞ አይረካም ነበር።

- አሁን ውሉን ተፈራርመን ጨርሰናል። ከውሉ ጋር ግንኙነት በሌለው ሌላ ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ሀሳብ ብንለዋወጥ ምን ይመስለሃል ?

- ማለት የፈለከው አልገባኝም . . በል ቀጠል . .

በግልጸኝነት ያለ ማሸማቀቅ ልናገርና ውሉን ለመፈረም ገንዘብ የምትቀበለው ለምንድነው? ይህ ጉቦ አይደለም ወይ ?

- እህህ፣ግልጸኝነትን የምትወድ ከሆነ አንተና ካኽም ውሉን ለመፈረም ለምንድነው በሌቪ የምትደሰቱት? ይሄስ የወሲብ ጉቦ አይደለም?!

- ልክ ነህ ወሲባዊ ጉቦ ነው፣አምቢ እንድል ካደረጉኝ ምክንያቶችም ይህ አንደኛው ነው።

- ካኽ ግን እምቢ ብሎ ራሱን አቅቦ አያውቅም፤እንዲያውም በግልጽና በይፋ ይጠይቅ ነበር። አንተም ብትሆን ትናንተ በተዘዋዋሪ መንገድ ጠይቀሃል፤እንደምትለው በሌቪ ሳትደሰት ቀርተህ ከሆነ ይሀ ያንተ ችግር ነው። ደሞስ እንደምትለው ጉቦ ከሆነ ለምን ሰጠኸኝ?!

- ጉቦ ከሆነ ለምን ትከፍላለህ የሚለው አነጋገርህ ትክክለኛና ምክንያታዊ ነው . . ለማንኛውም ገንዘብና ወሲብ ደስተኝነትን ያጎናጽፉሃል ?

- ያለ ጥርጥር ዓለማዊ ደስታ የሚገኘው በወሲብ በገንዘብና በሥልጣን ነው . . (ተመቻችቶ በመቀመጥ ቀጠለና) ፦ እነዚህ መደሰቻዎች ራሳቸው እርግማን የሚያመጡብን ቢሆኑም እንኳ . .

- አልገባኝም፣የሕይወት መደሰቻዎች ተመልሰው እንዴት መርገምት ይሆናሉ?!

- ወዳጄ ይህ የሕይወት ተጻራሪ ገጽታ ነው። ወሲብ ገንዘብና ሥልጣን የቁሳዊ ሕይወት ዋነኛ መደሰቻዎች ሲሆኑ አንዳንዴ ግን መንፈሳዊ ሕይወታችንን በመጉዳት መርገምት ይሆናሉ። ልክ ከደስታ ስሜት እንደራቁትና ሁሌም በሀዘን ድባብ ውስጥ ብቻ እንደሚከበሩት የኛ የአይሁዶች በዓላት ማለት ነው። በዓላት በሕይወታችን ውስጥ በጣም አስደሳች ጊዜያት መሆን አለባቸው ተብሎ አይደለም የሚጠበቀው? አዎ ብየ ነው የምመልስልህ፤ግና እኛ ዘንድ በዓላት የሀዘን ቀናት ናቸው።

- እንዴት ?

- ሌቪ ከኔ በተሻለ ልታብራራልህ ትችላለች . . እህህ፣ ከሁሉም በላይ ቆንጆም ናት፣ውይይቱን ከርሷ ጋር በሚመችህ ቦታና አኳኋን መቀጠል ትችላለህ።

- እንግዲያውስ አመሰግነሃለሁ።

ጆርጅ ብንያምንን ተሰናብቶ ሲወጣ ጸሐፊውን የሌቪን ቢሮ እንዲያሳየው ጠየቀና ወደዚያ አመራ . . ሲገባ በመጓጓት ስሜት ጠየቀችው

- ምን ተባባላችሁ?

- ውርደት ነው የምሰማኝ፣ጉቦውን ሰጥቼው ውሉን ተፈራርመናል።

- ስለ ጉቦው ወይም ስለኔ ከርሱ ጋር ተነጋግረሃል?

- አዎ፣ስላንቺ ብዙ ነው የተነጋገርነው፤አዝናለሁ እንድዝናናበት አሁንም ገላሽን ለግብዣ እያቀረበልኝ ነው . . (ፈገግ አለና) ፦ አዲስ ነገር ቢኖር፣ለአንዳንድ ጉዳዮች ካንቺ ማብራሪያ እንድጠይቅ ሀሳብ ያቀረበልኝ መሆኑ ብቻ ነው።

- ከኔ ነው ማብራሪያ የምትጠይቀው?!

- ስለ ጉቦው ባነሳሁለት ጊዜ አንተና ካኽም ጉቦ ትቀበላላችሁ፣ የናንተ ጉቦ ግን ገንዘብ ሳይሆን የወሲብ አገልግሎት ነው ብሎ አፋጠጠኝ። እኔ ያመጣሁለትን ጉቦ እርሱ የተቀበለው በመሆኑም ሁለታችንም እኩል ነን በማለት ምላሽ አሳጣኝ።

- መቼም ያሳዝናል፣የሰው ልጅ አንዳንዴ በክርክርና ለጥፋቶቹ ፍልስፍናዊ ማመካኛ በማቅረብ የተካነ ነው።

- ማንን ማለትሽ ነው ?!

- ብንያምንን ማለቴ ነው፤አቀርቅራ ላፍታ ዝም ካለ በኋላ ፦ ራሴንም ማለቴ ነው፣ይቅርታ አድርግልኝና አንቴንም ማለቴ ነው።

ጆርጅ በሀዘን ስሜት ጣሪያውን እየተመለከተ

- እውነትሽን ነው . . መቼ ይሆን ፍልስፍናችን የጥፋትና የጉቦ ማመካኛ ፍልስፍና ከመሆን ወጥቶ የደስተኝነታችንና የዕድገታችን ፍልስፍና የሚሆነው ?

- ከኔ ማብራሪያ ስለምትጠይቅበት ጉዳይ ግን አልነገርከኝም።

- ብንያምን የሚለው ይህ የሕይወት ባህሪ ነው፣ውስብስብ ሕይወት ነች፤ደስታና ተድላዋ ለመንፈሳችን መርገምት ነው፤ምሳሌዋ የደስታ ቀናት ይሆናሉ ተብለው እንደሚጠበቁትና ግና የሀዘን ቀናት እንደሆኑት አይሁዳዊ በዓሎቻችን ምሳሌ ነው።

- ምናልባት ይህ ቀደም ሲል ከተነጋገርንባቸው የማዛባት መገለጫዎች አንዱ ሊሆን ይችላል። አይሁዳዊነት ውስብስብ ሃይማኖት ነው። ችግሩ ያንተ የግንዛቤ ችግር ሳይሆን የአይሁዳዊነት እውነታ ውስብስብነት ነው። ዋናው ነገር የአይሁዶች በዓላት በአብዛኛው የደስታና የፈንጠዚያ ሳይሆኑ የሀዘንና የለቅሶ በዓላት ናቸው።

- እንዴት ማለት ?

- በዓላት ከአምልኮ ጋር የተያያዙ ሲሆን የአይሁዶች አምልኮ ለቅሶና ሀዘን ነው። የማልቀሻ ግንብ ስለሚባለውን የአይሁድ አምልኮ ስፍራ ሰምተህ የለ?! የሰንበቶች ሰንበት ብለን በምንጠራውና ከኛ በዓላት ሁሉ ዋነኛው በሆነው የምሕረት ቀን በዓል ጊዜ፣ቀንና ሌሊት በተከታታይ ለሃያ አራት ሰዓት እንጾማለን። ከአምልኮ ውጭ ምንም ነገር አንሰራም። በአጠቃላይ ብዙ በዓላት ያሉን ሲሆን አብዛኞቹ አይሁዶች በተለይም ሴኩላሪስቶቹ ከቅርጽ ያለፈ ይዘት የሌላቸው አምልኮ አልባ በዓላት አድርገው ያከብራሉ።

- ይኸ ብዙም አስፈላጊ ነጥብ አይደለም፤ግና ሕይወት ደስተኝነትን ለእርግማን በሚዳርገን ነገር ውስጥ ብቻ እንጂ ማግኘት እስከማንችልበት ደረጃ ድረስ ውስብስብ መሆን ትችላለች ማለት ነው? !

- ይህ ጥያቄ ሁሌ አእምሮዬ ውስጥ ይመላለሳል። ኦሪትና ተልሙድንም በጥልቀት ያጠናሁና የመረመርኩ ቢሆንም ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም። ምናልባት ይህ የሆነው በአይሁዳዊነት ወይም በአይሁድ ሃይማኖት የአስተሳሰብ ውስብስብነት ባህሪ ምክንያት ሊሆን ይችላል። አሊያም ወደ መልሱ ለመድረስ የበለጠ ዕውቀት ስለሚያስፈልገኝ ሊሆን ይችላል።

- እኔ እንጃ . . እኔ ግን ውስብስብነትንና ማወሳሰብን እጠላለሁ። ማወሳሰብ ወደ እርግማን እንጂ ወዴትም ማድረስ አይችልም የሚል እምነት አለኝ።

- እኔም ማወሳሰብን እጠላለሁ፣ዳሩ ግን ተነክሬበታለሁ። ለማንኛውም አራት ሰዓት ነው፣ጊዜ እንዳያጥርህ፣ከዶክተር ሐበቢብ ዘግይትህበታል፣ውጭ እየጠበቀህ ነው።

- ዶክተር ሐቢብ ማነው?

- የሃይማኖቶች ተመራማሪ የሆነ ካቶሊክ ክርስቲያን ነው . . ካንተ ጋር መሆን የሚገባውንና የሚመችህን ሰው ስለማውቅ እኔ ራሴ ነኝ በጉብኝቱ ላይ ባልደረባህ እንዲሆን የመረትጥኩልህ።

ጆርጅ ለአፍታ በዝምታ ቆየ። ከርሷ መለየት አልፈለገም ነበርና በውበቷ ዓይኖቹን ለመሙላት ሞከረ . . በትከሻዋ ላይ በተዘናፈለው
ጸጉሯ፣በሚንቦገቦጉ ዓይኖቿ፣በተሰረጎዱ ጉንጮቿ፣ በማራኪ ተክለሰውነቷና በእንቅስቃዋ፣በሁለመናዋ . . የሥጋዊ ፍላጎቴን ጥማት የሚያረካ ሌሊት አብሬያት ባለማሳለፌ ተሳስቼ ይሆን? ብንያምን ‹‹የገላ እርካታ የመንፈስ መርገምት ነው›› ያለው እውነት ይሆን? ወይኔ በዚህ ነጥብ ላይ ረስቼ ሳልከራከረው ቀረሁ!
ጆርጅ የተከለባት የእይታ ጨረራ በያንዳንዱ የገላዋ ክፍል ላይ እያረፈ መሆኑ ሌቪ ተሰምቷታል። በዚህ እይታ የመነሳሳትና የትኩሳት ስሜት ለምን እንዳደረባት አታውቅም። ከርሱ ጋር ለመደሰት ፈልጋ ከሆነ ለምን ተወች? የተወችው ራሷን ለማስወደድና እንዲከተላት ፈልጋ እርሱ ስላላደረገ ይሆን? እሱስ ቢሆን እንዲህ በዓይን እይታ እየበላት ለምን ተዋት? ሀሳቡን ቀይሮ ይሆን? ማን ያውቃል፣የልቧን አውጥታ ነግራው ዛሬ አብራው ትደር ወይስ ምንታደርግ
?!

- በጣም ነው የማመሰግነው፣ነገ ጧት ሁለት ሰዓት ላይ እጠብቅሻለሁ።

- ጆርጅ እኔም አመሰግናለሁ።

ጆርጅ ወጥቶ ለዶክተር ሐቢብ ሰላምታ አቀረበ፣ተያይዘው ወደ መኪናው ሄዱ . .

- መጀመሪያ የምናመራው ወደ ትንሣኤ ቤተክርስቲያን ነው። ዛሬ ዓርብ ስለሆነ መንገዶች ሁሉ በፍተሸ የተጨናነቁ ናቸው፣ሁለት ሰዓት ሊወስድብን ይችላል።

- ሁለት ሰዓት?!

- አዝናለሁ፣አዎ ሁለት ሰዓት። በሌላው ጊዚ የአርባ አምስት ደቂቃ መንገድ ነበር፤ዛሬ ዓርብ ስለሆነ በፍተሻ ኬላዎች ብዛት መንገዶች ሁሉ የተዘጋጉ ናቸው።

- የጊዜ ብክነትና አስቸጋሪነቱ ከፍተኛ ቢሆንም ሽብርተኝነት በሰው ዘር ላይ ያንዣበበ አደጋ በመሆኑ ነገሩ ተገቢ ነው።

- ስለ የትኛው ሽብር ነው ምታወራው?

- ስለ ዐረብ ሙስሊሞች ሽብር ነዋ !

- ይቅርታ፣እኔ ዐረብ ካቶሊካዊ ክርስቲያን ነኝ፣ሙስሊም አይደለሁም። እውነተኛው ሽብር ግን የአይሁዶቹ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ነው። ሰዎች በመስጊዶቻቸው ተገኝተው እንዳይሰግዱ ለምንድነው የሚከለከሉት? በመስጊዳቸው መስገድ ምኑ ላይ ነው ሽብር የሚሆነው?!

- ይቅርታ፣እኔ የታሪክ፣የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖቶች ኤክስፐርት አይደሰለሁም። ያገጠመኝ ሰው ባለሞያ መሰለኝ፣ለመሆኑ አይሁዶችን ለመግደል ራሳቸውን በማፈንዳት ባቡሮችንና አውቶቢሶችን የሚያፈነዱት ሙስሊሞች አይደሉም? !

- ልክ ነህ ያደርጋሉ፣አንድን ሰው ራሱን ወደ መግደል የሚያደርሰው ምንድነው ብዬ ብጠይቅህ ምን ትላለህ?

- በተለምዶው አንድ ሰው መሞትን ከመኖር ከሚመርጥበት ሁኔታ ላይ ካልደረሰ በስተቀር ራሱን አይገድልም ብዬ አስባለሁ።

- እዚህ አገር ሙስሊሞችን ከዚህ ሁኔታ ላይ ምን አደረሳቸው?

- እኔ እንጃ፣ምንድነው ያደረሳቸው?

- ግፍ፣ጭቆና፣ወረራና የተዋራጅነት ስሜት ነው።

- ለሙስሊሞች በጣም የወገንክ ትመስላለህ።

- በፍጹም፣እኔ ሙስሊም አይደለሁም። ግና ያገሩ ባለቤት ለሆኑት ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መብት እወግናለሁ። ክብራቸው ተዋርዷል፣መሬታቸውን እና መብታቸውን ተነጥቀዋል። ታውቃለህ እኛ የፍልስጥኤም ክርስቲያኖችም ከመሬታችን እንባረራለን፣እንሰደዳለን፣ቅዱሳን ስፍራዎቻችን ይዋረዳሉ።

- ግን እንደ ሙስሊሞቹ ራሳችሁን አላፈነዳችሁም?

- እኛ በቁጥር አናሳ ነን። ይሁን እንጂ እያዋረዱንና እየጨቆኑንም ከሙስሊሞቹ የተሻለ አያያዘ ያደርጉልናል። ይህም ለኛ ተብሎ ሳይሆን የዓለም ክርስቲያኖችን ስሜት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው።

- የዓለም ሙስሊሞችን ስሜት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለሙስሊሞች የተሻለ አያያዝ ለምን አይደረግላቸውም?

- በግልጽና በአጭሩ ለማስቀመጥ ለኃይልና ለኃይል ብቻ አክብሮት በሚሰጥ ዓለም ላይ ነው የምንኖረው . . ይህን ተወኝና የትንሣኤን ቤተክርስቲያን ታውቃለህ?

- በተወሰነ ደረጃ አውቃለሁ፣በርሱ ላይ ብዙ አንብቤያለሁ።

- መልካም ነው፣ሌቪ እንደነገረችኝ ፕሮቴስታንት ነህ።

- ልክ ነህ፣ ሌቪ ስለሁሉም ነገር የነገረችህ ይመስለኛል።

- ሌቪን ለአምስት ዓመታት ያህል አውቃታለሁ፤ላንተና ለምቾትህ ትኩረት የሰጠችውን ያህል ለሌላ ሰው ስትሰጥ አይቼ አላውቅም።

- ሌቪን ያወቅኋት በዚህ ሰሞን ነው፣ይህን ያደረገችው በተገራ ጠባይዋና በመልካም ስነ ምግባሯ ነው . . አንተ ከሌቪ ጋር የተዋወከው እንዴት ነበር?

- አይሁዳዊነት ሰልችቷት ነበር ወደ እኔ የመጣችው። ክርስትናን ለመቀበል ታስብ ስለነበረ በካቶሊካዊነት ዙሪያ ከኔ ጋር ለመከራከር ነበር አመጣጧ። ክርክርና ውይይት በጣም ትወዳለች።

- ክርስትናን ተቀበለች?!

- በእርግጥ አልተቀበለችም፣በጣም ሃይማኖተኛ ከመሆኗም ጋር ካቶሊካዊነትንም ሆነ አይሁዳዊነትን አሳማኝ ሆኖ አላገኘችም። ከአክራሪ አይሁዶች ቤተሰብ የተወለደች በመሆኗ ክርስትናን ብትቀበል ሊትገደል፣ልትታሰር ወይም የሆነ ዓይነት ጥቃት ሊፈጸምባት ይችላል።

- ካቶሊካዊነትን እንድትቀበል እንዴት ልታሳምናት አልቻልክም?

- ምናልባት በውስጡ ባሉት ግጭቶች ምክንያት፣አሊያም በአይሁዳዊነት ውስብስብ ባህሪ ምክንያት ሊሆን ይችላል !

- ምናልባትም በራሱ በካቶሊካዊነት ውስብስብ ባህሪ ምክንያትም ሊሆን ይችላል።

- እህህ፣ሊሆን ይችላል።

- የሃይማኖቶች ጉዳይ ተመራማሪ መሆንህን ሌቪ ነግራኛለች።

- አዎ . . በዩኒቨርሲቲ የሃይማኖቶች ታሪክ ኮርስ የማስተምር ዶክተር ነኝ።

- የሃይማኖቶች ታሪክ በፍልስጥኤም ምን እንደሚመስል ልትነግረኝ ትችላለህ?

- በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ውስብስቦች የታጠረ ቢሆንም ነገሩ በጣም ቀላል ነው።

- ማቅለልንና አለማካበድን አፈቅራለሁ . . እባክህን ቀለል ባለ መልኩ ንገረኝ።

- ቀለል ባለ መልኩ . . ያለ ጥርጥር ከሃይማኖቶች በፊት በዚህ መሬት ላይ ሰዎች ይኖሩ ነበር። ሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች በዚች ቅድስት አገር ውስጥ አልፈዋል። አይሁዳዊነት ከክርስትና እና ከእስላም ይቀድማል። ከሁሉም ሃይማኖቶች በፊት ግን ነዋሪዎች ነበሩ። ወደዚህ አገር የደረሱ ሃይማኖቶች ሁሉ ከመሬቱና ከአገሩ ጋር እየተቀላቀሉ ይሰባጠሩና ተቻችለው ይኖሩ ነበር። ከቅርብ ዘመን ወዲህ አይሁዶች ከየአገሩ እየመጡ ነባሮቹን ቀደምት ነዋሪዎች እየገደሉ እያባረሩና እያፈናቀሉ በመስፈር መሬቱን በወረራ መያዝ እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ ሁሉም እምነቶች በአብሮነት በሰላም የኖሩባት አገር ነበረች።

- ቀደም ሲል ሙስሊሞች ሌሎቹን አላባረሩም ነበር?

- ፈጽሞ፣እውነቱን ለመናገር ዑመር ብን አልኸጧብ ወደዚህ ሲገቡም ቤተክርስቲያኖቻችን እንደነበሩ ነው የቀጠሉት፣ ምንም ዓይነት ጉዳት ደርሶባቸው አያውቅም።

- የመስቀል ጦርነቶችስ?

- የመስቀል ጦርነቶች በሁለት ሃይማኖቶች መካከል፣በነባሮቹ ሙስሊም ነዋሪዎችና ከነሱ ጋር ነባሮቹ የአገሩ የተወሰኑ ክርስቲያኖች በአንድ በኩል ሆነው ከአውሮፓ የመጡ መስቀላውያንን ወረራ ለመመከት የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው። ከአውሮፓ መስቀላውያን መምጣት በፊት ሕዝቡ በፍቅርና በመቻቻል ይኖር ነበር።

- ክርስቲያኖችስ አይሁዶችን አልጨቆኑም?

- እኔ ክርስቲያን ነኝ፣አይሁዶች በቅርቡ ዘመን የተጨቆኑት አውሮፓ ውስጥ እንጂ ፍልስጥኤም ውስጥ አይደለም። ይህች ምድር ግን የመቻቻል ምድር ነች . . የጥንቱን ዘመን በተመለከተ የሮማውያን መንግስት ከኢየሱስ መምጣትና አይሁዶች ካስተባበሉት በኋላ እልቂት አድርሶባቸዋል፣ደማቸውን አፍስሷል።

- እስላም የዐረቦች ሃይማኖት በመሆኑ፣ከክርስትናህ ይልቅ ዐረባዊነትህ ለሙስሊሞች ተቆርቋሪ እንድትሆን ያደረገህ ትመስላለህ !

- ሊሆን ይችላል፣ግና እስላም የዐረቦች ሃይማኖት አይደለም።አብዛኞቹ ሙስሊሞች ዐረብ አይደሉም። እኔ ዐረባዊ እንጂ ሙስሊም አይደለሁም፤የአካዳሚክስ ሰው በመሆኔ ግን በተቻለ መጠን መልሴ ሳይንሳዊ እንዲሆን ጥረት አደርጋለሁ። ዐረቦች ወደ ቅድስት አገር የደረሱት ከእስላም መምጣት በፊት ነበር፤አብርሃም የያዕቆብና የእስማዒል አባት አይደለም?! አብርሃም ደግሞ ከአይሁዳዊነትም ሆነ ከእስላም በፊት ነው የኖረው።

- በማቋረጤ ይቅርታ፣አሁን የደረስንበት አካባቢ ሰፈሩ በጣም ጥንታዊ ይመስላል።

- አዎ፣የትንሣኤ ቤተክርስቲያን ወደሚገኝበት ወደ ጥንታዊው የከተማው ክፍል ተቃርበናል። እስካሁን ከአስራ አምስት የበለጡ የፍተሻ ኬላዎችን እንዳለፍን አስተውለህ የለም?!

- በፍተሻ ኬላዎቹ ላይ የተኮለኮሉ በእድሜ የገፉ ሰዎችን ሳይ ውስጤ በጣም ነው የተረበሸው፤በጣም አሳዛኝ ነው !

- በፈታሽ መኮንኖች ዘንድ የምታወቅ ክርስቲያን መሆኔ ኬላዎቹን በፍጥነት እንድናልፍ ረድቶናል። በዕድሜ የገፉ ሰዎች በብዛት ተሰልፈው የሚታዩት እድሜያቸው ከሃምሳ ዓመት በታች የሆኑት ከእለተ ዓርብ ሶላት የተከለከሉ በመሆናቸው ምክንያት ነው . . ይህም ማለት ሕጉ በኛም ላይ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ እኔና አንተም ወደ ትንሣኤ ቤተክርስቲያን መድረስ እንከለከል ነበር ማለት ነው።

- አሮጌው ከተማ የክርስትና ታሪካዊ ቅርሶች ማእከል ሳይሆን አይቀርም !

- ልክ ነህ ለሙስሊሞችም እንደዚሁ።

- ለአይሁዶችም ጭምር።

- እነሱ ይላሉ፣ታሪክና ተጨባጩ ሁኔታ ግን አይደግፋቸውም . . (ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ የጫካ ሕግ በሰፈነባት ዓለማችን ላይ ዋነኛ የሆነው ኃይልና ጡንቻ ግን ይደግፋቸዋል።

- በአይሁዶች ላይ በጣም የምትጫን ትመስላለህ!

- ይህን ያረጋገጠው ሳይንሱ ነው፤መሬቴን ስለ ነጠቁ፣መብቴን ስለጣሱ፣ነጻነቴን ቀምተው ከአምልኮቴ ስለ ከለከሉኝ አምርሬባቸው ሊሆን ይችላል።

- ሁሉም ሃይማኖት እንደዚህ ስለሚናገር ይህን እንተውና ወደ ቤተክርስቲያኑ የደረስን መሰለኝ?

- ልክ ነህ፣ጉልላቶቹንና መስቀሎቹን ማየት ትችላለህ፤የተቀረውን መንገድ በእግር እንጓዛለን።

- ሙስሊሞችን አትፈራቸውም?

- ከአይሁዶች ጥቃት ከተረፍክ ከዚያ በኋላ ያለው ነገር ሁሉ ቀላል ነው። ሙስሊሞች ቁድስ ወይም ኢየሩሳሌም ውስጥ አንድም ክርስቲያን መግደላቸውን ሰምተህ ታውቃለህ?

አብረው ጥቂት በእግር ተጓዙ . . ጥንታዊው የቤተክርስቲያን ሕንጻ ከፊትለፊታቸው ቆሞ አዩት። የኪነ ሕንጻው ጥበብና ውበት ያስደመመው ጆርጅ በአድናቆት ተውጦ እየዞረ ያስተውለው ጀመር . .

- ወደ ውስጥ ስትገባ ደግሞ ከዚህ በበለጠ በአድናቆት ትዋልላለህ።

- እንግዲያውስ እንግባ . .

ሲገቡ ጆርጅ የኢየሱስን የስቅለት ሥዕል በትልቁ ግድግዳው ላይ ተስሎ ተመለከተ

ከግርጌው የድንግል ማርያም ትልቅ ሥዕል፣ቀጥሎም የዮሴፍ . .

- ሥዕሎች ይበልጥ ተገቢ የሚሆኑት ለሙዝየሞች ነው የሚል እምነት አለኝ ! እንዲህ ያሉ ሥዕሎች ለአምልኮተ እግዚአብሔር በተዘጋጁ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ መደረጋቸው ተገቢ ነው?

- እናንተ ፕሮቴስታንቶች መቼም ይህ የተለመደ ዐመላችሁ ነው። በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሥዕላ ሥዕሎችን ማየት አትወዱም . . (በምጸት ፈገግ አለና) ፦ በዚህ ረገድ ከሙስሊሞቹ ጋር ትመሳሰላችሁ!

- ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊሞችን ትመስላላችሁ ስንባል መስማቴ ነው፣የተለመደው አይሁዶችን ትመስላላችሁ የሚል ነበር።

ጆርጅ ከጉልላቱ የሚወጣውንና ወደ አስራ ሁለት ጮራዎች የሚከፋፈለውን የብርሃን ፍንጣቂ በከፍተኛ አድናቆት ትኩር ብሎ ሲመለከት ቆየ . .

- ይህ ከዓለም ድንቃድንቅ ነገሮች አንዱ ነው። ከጉልላቱ ወደታች የሚወርደው ከአናት ባለው የጉልላቱ ክፍተት መሀል ላይ ብርሃን ያፈነጠቀችውን ጸሐይ የሚወክል ሲሆን፣ከዚህ ብርሃን አስራ ሁለት ጨረሮች ይወጣሉ። ተምሣሌቱ ግልጽ ነው። የብርሃን ምንጩ ኢየሱስን ሲያመለክት ጨረሮቹ አስራ ሁለቱን ሐዋርያት ይወክላሉ። ብርሃኑ እምነት በምድር ላይ መሰራጨቱን ያሳያል። ይህ ጉልላት ተሰርቶ የተመረቀው ጃንዋሪ 1997 ነበር።

- በእውነት ግሩም ድንቅ ትእይንት ነው። እንዲህ ባለ ቦታ ላይ ስትሆን በእምነት የተሞላ መንፈሳዊነት ይሰመሃል።

- እናንተ ፕሮቴስታንቶች ግን ይህን ቦታ ብዙም አትወዱም!

- እህህ፣ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል አለበት የሚባለውን ቦታ ማን የማይወድ ይኖራል!

- ለዚህ ቤተክርስቲያን የበለጠ ትኩረት የሚሰጡት ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች ናቸው።

- ቀደም ሲል ሙስሊሞች አፍርሰውት ነበር! አንተ ግን ሙስሊሞች አንድም የአምልኮ ቦታ አላፈረሱም ነው የምትለው!

- ልክ ነህ . . አልሓክም ብአምርልላ የሚባለው የሺዓው ፋጥማዊ ገዥ አፍርሶት ነበር። በታሪክ እንደምናውቀው ክርስትናን እንዳፈረሰ ሁሉ እስላምንም አፍርሷል . . ሆኖም ግን ካፈረሰ ከአርባ ዓመት በኋላ እንደገና እንዲገነባ ተደረገ . . እኔ ሙስሊም አይደለሁም፣ሙስሊሞች ስለ ፈጸሙት ግፍ መናገር ፈጽሞ አያስጨንቀኝም። አልፎ አልፎ ተከስቷል፣ይሁን እንጂ ከአይሁዶች ግፍና ጭቆና ጋር የሚነጻጸር በፖሊሲ የተደገፈ አይደለም፤ክርስቲያኖች በአይሁዶች ላይ ከፈጸሙት ግፍ ጋርም አይነጻጸርም። በነገራችን ላይ ቤተክርስቲያኑን በ336 ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራው አውሮፓዊ ሳይሆን ዚኖቢዮስ የተባለ ሶርያዊ መሀንዲስ ነው።

- የሚገርም ነው፣በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ብዙ ሰዎች የሉም።

- እንደሚታውቀው የቅዳሴ ቀን እሁድ ነው። ዛሬ ዓርብ ሲሆን መንገዱም የተዘጋጋ ነው፡፡ ባይሆን ኖሮ ግን ይህ ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተቀደሰና ቦታውም ከሁሉም በላይ የተከበረ ቦታ ነው።

ጀርጅ ለካትሪና የገባውን ቃል ለመፈጸም ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጸሎት አደረሰ። ለጥያቄዎቹ መልስ እየሰጠ ከሚያስጎበኘው ሐቢብ ጋር የቤተክርስቲያኑን የተለያዩ ክፍሎች እየተዘዋወሩ አዩ . . ወደ ማርያም ቤተክርስቲያን ለመሄድ ወጡ . . ሐቢብ ሰዓቱን ሲመለከት ለስምንት ሩብ ጉዳይ ሆኗል . .

- ብዙ እንዳልዘገየን ተስፋ አደርጋለሁ፤ወደ ማርያም ቤተክርስቲያን ለመድረስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ያስፈልገናል። ለመመለስም የዚያኑ ያህል ስለሚወስድብን ከጸሐይ መጥለቅ በፊት እንመለሳለን በዬ አስባለሁ።

- መልካም፣እንግዲያውስ ትንሽ ስለ ደካከመኝ መኪና ውስጥ ለግማሽ ሰዓት ያህል እረፍት እንዳደርግ ፍቀድልኝ።

- ጥሩ አረፍ በል።

ጆርጅ መቀመጫውን ወደ ኋላ ለቀቅ አድርጎ ተኛና ዓይኖቹን ጨፈነ። በዚህ ጉዞው የሁነቶች ክስተትና ክትትል በጣም ፈጣን መሆኑ እየታወሰው ነው። የጉዞውን የመጀመሪያ ዓላማ ቶሎ ማሳካቱ ትዝ አለው። ሁለተኛ ዓላማው የሆነውን የደስተኝነት መንገድ ፍለጋ ጉዳይን አሰበ። ከሌቪ፣ከብንያምንና ከሐቢብም ጋር ያደረጋቸውን ውይይቶች አስታወሳቸው። ይህ ሁሉ የተፈጸመው በአንድ ቀን ተኩል ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው። በቀሪው የሁለት ቀን ተኩል ጊዜ ውስጥ ምን ሊፈጸም ይችላል? . . ካትሪና፣ቶምና ኣደም ትዝ አሉት። ሁሉም አብረውት ሆነው ውይይቶቹን ቢሰሙ ምኞቱ ነበር። በተመለከታቸውና በሰማቸው መረጃዎች ላይ የራሱን ግላዊ አቋም ለመውሰድ እስከ አለመቻል ደረጃ ድረስ የመረጃው መጠን ጭንቅላቱን ያጨናነቀ ሆኖ ተሰማው። ጥያቄዎቹን አስታውሶ ቀደም ሲል ያስጨንቁት እንደ ነበረው ባለመሆናቸው ፈጣሪውን አመሰገነ . . ይህ የሆነው ወደ ደስተኝነት መንገድ ለመድረስ እየታገለ በመሆኑ ምክንያት ይሆን? ይሁን እንጂ የደስተኝነት መንገድ ፍለጋ ጥያቄዎችና የሰበሰባቸው አያሌ መረጃዎችም አድክመውታል።
በነዚህ የሀሳብና የትግል ማዕበል ውስጥ ሲላጋ ቆይቶ ወደ ሕልም ዓለም ተሸጋገረና አንቀላፋ።

ኢየሩሳሌም የሃይማኖቶችና የፍጥጫ አገር (5)

ጆርጅ ከእንቅልፉ ሲነቃ መቀመጫውን አስተካከለና ወደ ሐቢብ ተመለከተ

ይቅርታ በጣም ደከመኝ መሰለኝ !

- ሳይሆን አልቀረም።

- ኦህ፣አንድ ሰዓት ሙሉ ነው የተኛሁት ! ወደ ቤተክርስቲያኑ ለመድረስ ምን ያህል ይቀረናል?

- ሩብ ሰዓት ያህል ይቀረናል . . (ፈገግ እያለ ቀጠለና) ፦ ይቅርታ አድርግልኝና ብርቱ ውስጣዊ ግጭቶች ያሉብህ ትመስላለህ። ካትሪና፣ብንያምን፣ቶም፣ሽማግሌው፣ማይክል፣ጆስቲና፣ካኽ፣ሌቪ . .

- እነዚህን ስሞች ከየት አገኘሃቸው?!

- ተኝተህ በእንቅልፍ ልብ ትደጋጋማቸው ነበር።

- በእርግጥ ከባድ ድካም አለብኝ ማለት ነው። መረጃዎችና ክስተቶች ጭንቅላቴ ውስጥ ዝብርቅርቅ ብለውብኛል። አካሌንም ጫን ብሎኛል።

- አንድ ሰው ለጉዳዮቹ እልባት ካልሰጠ ነገሮች አእምሮው ውስጥ ተጠላልፈው ስለሚዘበራረቁበት መንፈሱ ሊታወክና አካሉም ሊዳክም ይችላል።

- የኔ ችግር በትክክል ይህ ሳይሆን አይቀርም።

- በነገራችን ላይ ብዙ ጊዜ ስትደጋግመው የነበርከው አንድ አባባል በጣም ማርኮኛል።

- የቱ ይሆን ?

- ‹‹የደስተኝነት መንገድ›› የሚለው ነው፤ደጋግመህ ‹‹የደስተኝነትን መንገድ እፈልጋለሁ›› ስትል ነበር፣ድንቅ አባባል ነው።

- ታድያ በደስተኝነት መንገድ ርእስ ላይ ሀሳብ ብንለዋወጥ ምን ይመስለሃል ? አንድ ጥያቄ ላቀርብልህ እፈልጋለሁ።

- ጥሩ፣ አቅርብ።

- አንተ ደስተኛ ነህ ?

- በጣም ትልቅ ጥያቄ ነው፤መልስ ሊኖረው የሚችል ነው ብለህ ታምናለህ ? !

- አዎ ይቻላል የሚል እምነት አለኝ።

- ሁሉም ሃይማኖቶች፣ርእዮቶችና ቡድኖች ይህን ይፈልጋሉ።

- አንተ የሃይማኖቶች ታሪክ መምህር ነህና ከሃይማኖቶች መካከል ለደስተኝነትና ለተድላ የቀረበው ሃይማኖት የትኛው ነው?

- እንዲህ ያለው ትልቅ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ይህ የመጀመሪያው ነው . . መልሱን ለማግኘት የቻልኩትን ያህል ጥረት አድርጌያለሁ፣አሁንም በፍለጋና በምርምር ላይ ነኝ።

- በአንተ አመለካከት መንገዱ ከሃይማኖት ውጭ ሊሆን ይችላል ?

- ያ የማይታሰብ ነው። አብዛኞቹ ኢአማኒያን ኤቲስቶች የስነ ልቦና ወይም የአእምሮ ሕሙማን መሆናቸውንና የውሸት ኤቲስቶች መሆናቸውን ሳይንስ ያረጋግጣል።

- አልገባኝም . . የውሸት ኤቲስቶች?!

- ማለትም ኤቲስቶች መስለው ለመታየት ቢሞክሩም ፈጣሪ አምላክ መኖሩን በውስጣቸው ያምናሉ። እውነቱን ለመናገር ኤቲዝም ከሃይማኖትና ከግዴታዎች ለመገላገል የሚደረግ ሽሽት ነው።

- ሃይማኖት የደስተኝነትና የተድላ ጎዳና ከሆነ የሃይማኖቶች ተመራማሪ የሆነ ምሁር ለምን መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም ?

- ይህን ማለት መብትህ ነው። እኔ አሁንም በምርምርና በፍለጋ ላይ ነኝ፤በቅርቡም ወደ መልሱ እደርሳለሁ።

- ይህን መልስ ስታገኝ እንደምትነግረኝ ቃል ግባልኝ።

- ቃል ገብቻለሁ፣ቃሌ ነው። ሌቪ እንዳለችው ሁሉ ለሃይማኖቶች ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለህ።

- እርስበርስ የሚጋጩ ነገሮችን አልወድም፤ውስብስብ ነገሮችንም አልወድም። በአእምሮ፣በመንፈስና በሥጋ መካከል፣በመርሆዎችና በዓለማዊ ደስታ መካከል ሚዘናዊነትና መጣጣም እንዲኖር እፈልጋለሁ። ማካበድን አልወድም፣ጥልቀት ያለው ቅለትን እወዳለሁ።

- ግሩም፣እኔም በትክክል አንተ የወደድከውን እወዳለሁ። ፈላስፋ መሰልከኝ፣በውይይቱ ልንቀጥል ይገባል፣ግና ወደ መግደላዊት ማርያም ቤተክርስቲያን የደረስን መሰለኝ፣ይኸው ከፊትለፊትህ።

- አስደማሚ የሕንጻ ጥበብ!

- ይህ ሩሲያዊ የሕንጻ ጥበብ ነው። ሩሲያዊው እስክድር ነበር በዚህ ውብ ወርቃማ ጉልላቶች አስውቦ የገነባው።

- የቅርብ ጊዜ ቤተክርስቲያን ነው ማለት ነው?

- ከትንሣኤ ቤተክርስቲያን ጋር ሲነጻጻር ያለ ጥርጥር አዲስ ነው። ትንሣኤ ቤተክርስቲያን የተገነባው በ335 ሲሆን፣የማርያም ቤተክርስቲያን የተገነባው በ1886 ነው። በመካከላቸው ያለው ልዩነት የ1500 ዓመት ነው።

- የሚገርመኝ አብዛኞቹ የክርስትና ቅርሶቻችንና ታሪካዊ ቦታዎቻችን ከባለ ታሪኮቹ ሕይወት በኋላ ብዙ ዘመናት ዘግይተው የተመሰረቱ መሆናቸው ነው። ይህ ደግሞ እውን ቅዱሳን ስለ መሆናቸው ጥርጣሬ የሚያሳድር ነው።

- አዎ ያሳዝናል፣ያልከው ነገር መቶ በመቶ እውነት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተም እንኳ እውነታው ይኸው ነው . . አሁን ደርሰናል በል ውረድ፣የቀረውን ስንመለስ እንጫወታለን። ጸሐይ ከመጥለቋ በፊት መመለስ እንድንችል ጉብኝቱን ቶሎ መጨረስ ይኖርብናል።

- ጥሩ፣ቶሎ እንጨርሳለን።

ቤተክርስቲያኑን ቶሎ ቶሎ ሲጎበኙ በድጋሜ የጆርጅን ትኩረት የሳበው በተለይ በውስጥ ጣሪያው ላይ የተሳሉት የሥዕሎች ብዛት ነበር። በጆርጅ እምነት ሥዕሎችን በአምልኮ ሥፍራ ማኖር ተገቢ አይደለም . . ውብ ጌጦቹና የጸሐይን ብርሃን የሚያንጸባርቁ ሰባቱ ጉልላቶችም ዓይን የሚስቡ ናቸው። ድንቅ ጥበብ የሚስተዋልበት ሕንጻ ነው። ጆርጅ በችኮላ ጸሎት አደረሰና ለቀው ወጡ . .

- የሚማርክ እጅግ የተዋበ ሕንጻ ነው።

- አዎ፣ምርጥ ከሚባሉ የኪነ ሕንጻ ጥበቦች አንዱ ነው።

- እናንተ ካቶሊኮች ግን በአምልኮ ቦታዎች ውስጥ ሥዕሎችን ትወዳለችሁ። እኔ ግን ይህ በአምልኮ ቤት ውስጥ መኖር የሌለበት ተገቢ ያልሆነ ነገር ነው የሚል እምነት አለኝ። እንዳውም የጣዖት አምላኪዎችን የማምለኪያ ስፍራዎች ያስታውሱኛል።

- በመጀመሪያ ደረጃ ቤተክርስቲያኑ የካቶሊክ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ነው። ሁለተኛ እናንተ ፕሮቴስታንቶች በዚህ በኩል ከሙስሊሞች ጋር ትመሳሰላላችሁ ብየሃለሁ።

- የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አይደለም?! ታዲያ ባለቤቴ ካትሪና እውስጡ እንድጸልይ ለምን ፈለገች?!

- እኔ እንጃ !

- የሃይማኖቶች ጉዳይ ምሁርና ተመራማሪ እንደ መሆንህ በኦርቶዶክስ፣በካቶሊክና በፕሮቴስታንት መካከል ያሉትን ልዩነቶች በአንተ አመለካከት ምን እንደሆነ ልታብራራልኝ ትችላለህ?

- ለመመለስ አስቸጋሪ የሆነ ውስብስብ ጥያቄ ነው።

- ነገሮችን ማቅለል ትወድ የለ ? ቀለል አድርገህ ንገረኝ።

- እሞክራለሁ ግን . . ጠቅለል ባለ አነጋገር ቁጥራቸው እጅግ የበዙ የክርስትና ቡድኖች፣ጎራዎችና ሴክቶች ይገኛሉ። ለማቅለል ያህል በጠቀስካቸው ሶስቱ ትላልቅ ቡድኖች ብንወሰን በመጀመሪያ ኦርቶዶክስን እናገኛለን። ትርጉሙ ትክክለኛው፣እውነተኛው፣የጥንቱ፣ሃይማኖት አጥባቂው፣መደበኛው ማለት ነው። ኦርቶዶክስ ጥንተ መሰረት ሲሆን ካቶሊክ ከ451 ጀምሮ ከርሱ ተገንጥሎ የወጣ ነው፡፡ ትርጉሙ አጠቃላዩ ወይም ዓለም አቀፉ ማለት ነው። ፕሮቴስታንት ደግሞ ከካቶሊክ የተገነጠለና በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አውሮፓን ባጥለቀለቀው የሃይማኖት ተሐድሶ ንቅናቄ በማርቲን ሉተር መሪነት የተመሰረተ ነው።

- እናም ጥንተ መሰረቱ ኦርቶዶክስ እንጂ እናንተ ካቶሊኮች አይደላችሁም ማለት ነው?

- አዎ አይደለንም፣ለናንተ ለፕሮቴስታንቶች ግን መሰረት ነን። ዋናው ነገር የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ቤተክርስቲያን ወይም የምስራቃውያን ሮም ቤተክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። ተከታዮቹ እንደ ሩሲያ፣የበልቃን አገሮች ያሉ የምስራቅ አውሮፓ አገሮችና ግሪክ ናቸው። የጥንት ዋና መቀመጫው የቆስጠንጥኒያ (ኮንስታንትኖፕል) ከተማ ስትሆን፣የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ፣የአርመንና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያኖች የዚህ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ናቸው። የኦርቶዶክስ (ምስራቅና ኦሪየንታል) ሃይማኖት ተከታዮች ቁጥር 312 ሚሊዮን ያህል ነው።

- 312 ሚሊዮን ተከታዮች!

- የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደግሞ የምዕራብ ቤተክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። በምዕራብ ላቲን በኢጣሊያ፣በቤልጂየም፣በፈረንሳይ፣በእስፔን እና በፖርቱጋል የተስፋፋ ሲሆን በአውሮፓ፣በብራዚል፣በሰሜንና ደቡባዊ አሜሪካ አገሮች፣በአፍሪካና በኤስያም ተከታዮች አሉት። የቤተክርስቲያኑ መስራች የሐዋርያት አለቃ የሆነው ጴጥሮስ ሲሆን የሮማ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የርሱ እንደራሴ ነው ብለው ያምናሉ። በተጨማሪም የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እናትና አስተማሪ አድርገው ራሳቸውን ሲቆጥሩ የቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ የሊቀ ጳጳሱን ፈቃድ የማወጅ መብት አለው። ፓፓው የኢየሱስ ሐዋርያና እንደራሴ የጴጥሮስ ተጠሪ በመሆኑ የፓፓው ፈቃድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ተደርጎ ይታመናል። በመሆኑም የሊቀ ጳጳሱ ፈቃድና ውሳኔ ጥያቄና ክርክር ሊቀርብበት የማይችል መለኮታዊ ፈቃድና ውሳኔ ነው ብለው ያምናሉ። የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ቁጥር አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ያህል ነው።

- መልካም፣የፕሮቴስታንቶችን ደግሞ ቀጥልልኝ ?

- ፕሮቴሰታን ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ ማለትም ተከታዮቹ ወንጌልን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በቀጥታ ለራሳቸው ተረድተው የሚከተሉበት ቤተክርስቲያን ሲሆን ካህናትና የቤተክርስቲያን መሪዎች ከአማኙ የተለየ ግነዛቤና ራእይ አላቸው ብለው አያምኑም። በአጠቃላይ መልኩ በመሰረታዊ የክርስትና እምነቶች የሚምኑ ክርስቲያኖች ሲሆኑ በብዙዎቹ የቤተክርስቲያን ምስጢራት፣ልማዶችና ስርዓቶች፣ በቤተከርስቲያን በተደነገጉ ጸሎቶች፣በጥምቀትና በመሳሰሉት ግን አያምኑም። አንዳንዶቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎችና አያሌ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ወግና ልማዶችንም አይቀበሉም። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ቁጥር ከ600 እስከ 800 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

- ከክርስትና ውጭ ልታደርጉን ነው የምትፈልጉት? ግድ የለም፤ለመሆኑ በሦስቱ ቡድኖች መካከል ያሉት መሰረታዊ ልዩነቶች ምንድናቸው ?

- ከክርስትና ውጭ ልታደርጉን ነው የምትፈልጉት ስትል መሰረታዊውን ጉዳይ ጠቅሰሃል። እውነቱን ለመናገር በተለያዩት አብያተክርስቲያናት እና ቡድኖች መካከል ያሉት ልዩነቶች፣በአንዳንዶች ዘንድ ራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ ሃይማኖቶች እንጅ በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው ብሎ መውሰድ እስከማይቻልበት ደረጃ እጅግ በጣም የሰፉ ናቸው።

- እንዴት ማለት? ብታብራራልኝ?

- ሁሉም ቡድኖች በሁሉም የክርስትና እምነቶች ላይ ልዩነቶች አሏቸው። ስለዚህም መኪና ውስጥ ሆነን እንዲህ በቀላሉ መዘርዘር አንችልም። በእግዚአብሔር አምላክ ማንነትና ባህርያት ላይ፣በኢየሱስ ማንነትና ባህርያት ላይ፣በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ፣በአምልኮ ደንብና ሥርዓቶች ላይ፣ በሌሎች ብዙ ብዙ ጉዳዮች ላይ ይለያያሉ።

- ልየነቶቹ እስከዚህ ድረስ የገዘፉና የበዙ ከሆኑ እንዴት አንድ ሃይማኖት ሊሆን ይችላል ? የግድ አንደኛቸው ትክክል ይሆናል።

- አንዱ ብቻ ትክክለኛ ነው የሚለው አስተሳሰብ ነው በነዚህ የተለያዩ የክርስትና ቡድኖችና ጎራዎች መካከል ጦርነቶችን የጫረው።

- ጦርነቶችን? !

- አዎ፣ብዙ ሚሊዮኖች ያለቁባቸው ጦርነቶች። ለምሳሌ ያህል ከ1618 እስከ 1648 ባሉት ዓመታት በካቶሊኮች እና በፕሮቴስታንቶች መካከል በአገሮች ደረጃ የተደረገው የሰላሳ ዓመት ጦርነት የብዙ ሚሊዮን አውሮፓውያንን ሕይወት ቀጥፏል። ጀርመን ብቻዋን ግማሽ የሚሆኑ ወንድ ዜጎቿን አጥታለች። የዜጎቿ ቁጥር ከሃያ ሚሊዮን ወደ አስራ ሦስት ሚሊዮን ተኩል አሽቆልቅሏል!

ሽብርተኝነትን እና አክራሪነትን በሁሉም መልካቸው የሚጠላው ጆርጅ ይህን ሲሰማ ስሜቱ ክፉኛ ተነካ። የደስተኝነትና የተድላ መንገድ በደም የተጥለቀለቀና የጨቀየ ሊሆን ይችላል? ሲል ራሱን በራሱ ጠየቀ። ጌታዬ በእዝነትህ እየን፣የሰው ልጅ በዚህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ጭካኔ ተድላና ደስታን ማግኘት አይችልም . .

- ምን ዓይነት ጭካኔ ነው?!

- ወደድንም ጠላን፣በእምነት ምክንያት የሚነሱ የከረሩ ልዩነቶች ወደ ግጭቶች የሚለወጡ መሆናቸውን ታሪክ ያረጋግጣል።

- በጣም አስፈሪ የሆነ አሸባሪ ታሪክ ነው!

- አዎ ያሳዝናል፣በአጠቃላይ የሃይማኖቶች ግጭት አይሁዶች በክርስቲያኖች ላይ ካካሄዱት ጦርነትና ከፈጸሙባቸው ግፍ አንስቶ፣ኢየሱስን መግደላቸው፣በኋላ ላይ ደግሞ ክርስቲያኖች አይሁዶችን መጮቆናቸው፣ቀጥሎም ዛሬ አይሁዶች ሙስሊሞችን እና ክርስቲያኖችን መጨቆናቸው በጣም አሳሳቢና አስጨናቂ ነው።

- አሁንም በድጋሜ ሙስሊሞች አይሁዶችን ወይም ክርስቲያኖችን ስለ መጨቆናቸው አላነሳህም !

- በታሪክ መከሰቱን ስለማላውቅ ነው፣አንድ ምሳሌ ልትሰጠኝ ትችላለህ ?

- ሙስሊሞች የትንሣኤን ቤተክርስቲያን ማፍረሳቸው።

- እንዲህ ያሉ ነጠላ ክስተቶች ብዙ ናቸው። እኔ የምናገረው ግን አጠቃላይ ስለሆነ ግፍና ጭቆና ነው። ሰዎችን ስለ መግደልና ሃይማኖታዊ ስርዓቶቻቸውን እንዳይፈጽሙ ስለ ማገድ ነው። እስላም ቤተክርስቲያንና ገዳማትን ማፍረስም ሆነ በጦርነት ውስጥ ቢሆን እንኳ መነኮሳትን መግደል ይከለክላል። በዚህ ረገድ የደረሱ ነጠላ ሁነቶች ፈጽሞ አጠቃላይ ወደ ሆነ የታቀደ ግፍና ጭቆና ደረጃ የሚደርስ አልነበረም።

- በክርስትና ውስጥ የተደበቅክ ሙስሊም ሳትሆን አልቀረም።

- እህህ፣ሊሆን ይችላል፣ማን ያውቃል ምናልባት አንድ ቀን ሙስሊም ወይም ፕሮቴስታንት እሆን ይሆናል። እናንተ እንደነሱ በአምልኮ ቦታ ሥዕልና ቅርጻ ቅርጾችን አትወዱም አላልኩህም ነበር። (ወደ ጆርጅ ዞር አለና) ፦ ወይ ደግሞ ካንተ ጋር በደስተኝነት ጎዳና እጓዝ ይሆናል። ጎሽ አስታወስከኝ . . ‹የደስተኝነት መንገድ› ጉዳይ ምን እንደሆነ አልነገርከኝም፣ምን ይሆን?!

- ‹የደስተኝነት መንገድ› ጉዳይ ታሪኩ በጣም ረዥም ነው።

- ቀለል አድርገህና አሳጥረህ ንገረኝ።

- እውነቱን ለመናገር የሕይወት ትላልቅ ጥያቄዎች ማለትም ለምን ተፈጠርን? ማን ፈጠረን? ለምንድነው የምንኖረው? መጨረሻችንስ ወዴት ነው? የሚሉት በጣም ነው ያደከሙኝ። ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እሳከገኝላቸው ድረስ ደስተኛ መሆን እንደማልችል ስለ ተረዳሁ የደስተኝነትን መንገድ ለማግኘት ፍለጋ ጀመርኩ። (ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ ተኝቼ ሳለሁ ሰማሁ ያልከኝ ስሞች በደስተኝነት መንገድ ፍለጋ ሂደት ውስጥ ያገኘኋቸውና ያጋጠሙኝ ግለሰቦች ናቸው።

- የዚች ቅድስት ከተማ ጉብኝትህ፣ክርክሮችህና ውይቶችህ ሁሉ የደስተኝነት መንገድ ፍለጋ ጥረትህ አካላት ናቸው?

- የመጣሁት ለሥራ ጉብኝት ነው፤እንድመጣ የቀሰቀሰኝ እውነታ ግን አንተ ያልከው ነው።

- ይህን መንገድ መቼ ነው የምታጠናቅቀው ?

- አላውቅም፣ለመድረስ ግን ቁርጠኛ ነኝ። (ፈገግ እያለ ወደሱ ዞረና) ፦ የደስተኝነት መንገድ ፍለጋው ራሱ ደስተኝነት ነው።

- በእኔ በአንተና በሌቪ መካከል ብዙ መመሳሰሎች ያሉ ይመስለኛል።

- እንዴት?

- ከአይሁዳዊነት ውጭ ደስተኝነትን ፍለጋ እኔ ዘንድ መጥታ ካቶሊካዊነት ሊያረካት አልቻለም። እኔ ደግሞ ኦርቶዶክስ ነበርኩ ወደ ካቶሊክነት ተለውጬ አሁንም ድረስ በፍለጋና በምርምር ላይ ነኝ።

- ፕሮቴስታንትን ሞክር . . ምናልባት መፍትሔ ሊሆንህ ይችላል። ለካቶሊካዊቷ ባለቤቴ አዘውትሬ፣ሃይማኖታችሁ በአያሌ መንፈሳዊ ሥርዓቶችና ምክንያታዊ ባልሆኑ ሚስጥራት የተወሳሰበ ነው እላታለሁ።

- ምናልባት ይሆናል፣በደስተኝነት ፍለጋ ጉዞህ ግን የት ደርሰሃል?

- ይቅርታ፣ወደ ሆቴሉ ለመድረስ የት ደርሰናል? አንዳች የጤና መታወክ እየጀመረኝ ይመስለኛል፣ከመጠነኛ ማዞር ጋር ገላዬ ከባብዶኛል።

- አይዞህ በርታ፣ጌታ ይባርክህ፣ሩብ ሰዓት ያህል ብቻ ነው የሚቀረን።

- በጣም ነው የማመሰግንህ፣በብዙ ነገር ጠቅመህኛል።

- ካንተ ጋር ያስተዋወቀችኝ ሌቪ ነች መመስገን ያለባት፤እርሷን አመስግናት። በከፍተኛ ደረጃ ነው ለምቾትህ የተጨነቀችው።

- ልክ ነህ፣ሌቪ በጣም ልዩ የሆነች ሴት ናት፤በጣም አመሰግናታለሁ።

- የምትወዳት ትመስላለህ፣ባለትዳር ነኝ ብለሀኝ የለ?

- አዎ ባለትዳር ነኝ፣እሷ በጣም ውብ ኮረዳ ነች፤አሳሳች ቁንጅናና መግናጢሳዊ መስህብነት ቢኖራትም ከገላዋ ይበልጥ መንፈሷን ነው የምወደው።

- ተምኔታዊ አፍቃሪ ትመስላለህ!

- እህህ፣ወይም ብዙዎቹ የሚያውቁኝ ሰዎች እንደሚሉኝ ውስብስብ ሕመምተኛ ነኝ።

- በቁሳዊ ማህበረሰቦቻችን ውስጥ በአምልኮቱና በዓለማዊ መደሰቻው መስክም ከመንፈሳዊ ጎን ይልቅ ቁሳዊ ጎን ቅድሚያ ይሰጣል። በብዙዋቻችን ዘንድ እውነታው ይህ ሲሆን በአይሁዶች ዘንድ ደግሞ ብልጫው የጎላ ነው።

- እንዴት?

- ከክርስትና መገለጫዎች አንዱ ነገሮችን በመንፈሳዊ ጎናቸው መመልከት ነው። ይሁን እንጅ ቁሳዊ ሕብረተሰቦቻችን ትኩረት የሚሰጡት ለመንፈሳዊ ደስታዎች ሳይሆን ለሥጋዊ ደስታዎች ነው። የአይሁዶች ታሪክ ግን ለሁሉም ነገር፣ለአምላክ፣ለወዳኛው ዓለም፣ለሞራልና ለስነ ምግባር . . ቁሳዊ አመለካከት እንዳለቸው ነው የሚያረጋግጠው። ሁሉም ነገር ሊሸጥ፣ሊገዛና ሊለወጥ ይችላል፣ሽያጭና ግዥ ግብይት ሲባል ሸቀጥ ብቻ ማለት አይደለም።

- በአይሁዶች ላይ ትጫናለህ ብየህ የለ?

- በዚህ ላይ ከሌቪ ጋር መነጋገር ትችላለህ። ፈታኝና ማራኪ አይሁዳዊት ስለሆነች በአይሁዶች ላይ የምትጫን አትሆንም። በተጨማሪም ታሪክንና ተጨባጩን ነገር ማየት ትችላለህ።

- እንደልማድህ ረታሀኝ፣በጣም ደከመኝ ደርሰናል?

- ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ፣አይዞህ በርታ እንደርሳለን።

የጆርጅ ስልክ አቃጨለ . . የሌቪ ውብ ድምጽ ነበር . .

- ሃሎ ጆርጅ።

- ሃሎ።

- ጉዟችሁ እንዴት ነበር?

- ግሩም ነበር፣እንዴታ ከመረጥሽልኝ ድንቅ ባልደረባ ከዶክተር ሐቢብ ጋር ሆኜ !

- ምርጫዬ በጣም ጥሩ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

- እጅግ በጣም ጥሩ እንጂ፣አመሰግናለሁ።

- ጸሐይ ከመጥለቋና ሰንበት ከመግባቱ በፊት ደህንነትን ለማወቅ ነው የደወልኩት።

- እኔ ደህና ነኝ፣በመደወልሽ አመሰግናለሁ። ለአዘገጀሽልኝ የተመቻቸ ጉብኝትም ምስጋናዬ የላቀ ነው። ነገ ምን ጊዜ ነው የማገኝሽ ?

- በፈለከው ሰዓት፣እኔም ላገኝህ ጓግቻለሁ።

- እኔም ናፍቄያለሁ፤እንግዲያውስ ትንሽ ስለ ደካከመኝ በቂ እረፍት መውሰድ እፈልጋለሁና ቀጠሯችን ጧት ሦስት ሰዓት ነው።

ጆርጅ ትንሽ የመርበትበት ስሜት አሳየና ሰረቅ አድርጎ ወደ ሐቢብ ሲመለከት ፈገግታውን ለመደበቅ ሲሞክር አየው . .

- አይዞህ፣ጌታ በጥበቃው ካንተ ጋር ይሁን፤ሐኪም ላምጣልህ እንዴ ?

- ሌቪ አመሰግናለሁ፣ነገ ሙሉ ንቃቴ ተመልሶ ሦስት ሰዓት ላይ ዝግጁ ሆኜ ታገኚኛለሽ።

- ደህና ሁን . .

- አመሰግናለሁ፣ደህና ሁኚ . .

- . . ሞቅ ያለ የስልክ ጥሪ ነው!!

- ምን ማለትህ ነው ?

- ምንም፣ሌቪ አንተ እንደምትለው ግሩም ድንቅ የሆነች ፈታኝ ቆንጆ ኮረዳ ናት።

- ምን ማለትህ ነው ?

- እየቀለድኩብህ ነው። አንተ እንደምታደንቃት ሁሉ ሌቪም በጣም የምታደንቅህ ነው የሚመስለኝ። አንደኛችሁ አድናቆቱን በሌላው መንፈስ፣አመለካከትና ሞራል ላይ እንዲያተኩር ለማድረግ ይሞክራል . . (ፈገግ ብሎ ቀጠለና) ፦ ለመንፈሱ ብቻ ሳይሆን አንዱ ለሌላው ገላም እንዲሁ አድናቂ ነው፣በመሆኑም የመንፈስ አድናቆቱ ወደ ገላ አድናቆት እንዳይሸጋገር ጥንቃቄ አድርግ። ሌቪ የነገረችኝን መርሆዎቻችሁን ለመጣስ ወደሚዳርጋችሁና ወደማትፈልጉት ነገር እንዳትደርሱ ራሳችሁን ያዝ አድርጉ። ለማንኛውም ይሀውና ሆቴሉ ደርሰናል።

- ከልብ ለመነጨው እውነተኛና አስቸጋሪ ምክር አመሰግናለሁ። ምሳ ወይም እራት አብረን እንብላ፣እስካሁን ምሳም አልበላንም።

- አንተ በጣም ደክሞሃል፣እኔም እንደዚያው ነኝና ይቅርታ አድርግልኝ።

- አመሰግናለሁ፣ብዙ ነገር ነው ካንተ የተማርኩት። ይህ የቢዝነስ ካርዴ ነው፣ግንኙነታችን እንደሚቀጠል ተስፋ አደርጋለሁ . . እህህ፣ነገ ሙሉውን ቀን ከሌቪ ጋር ስለሚሆን በመካከላችን ጠባቂ ዘበኛ ብትሆን ችግር የለውም።

- ለባህል፣ለስልጣኔ፣ለእሳቤ እና ለመርህ ያለህን ትኩረት አውቃለሁ። ግና እርሷንም እንዳስጠነቀቅኩ ሁሉ አንዳንዴ ነገሮች እንዳይደበላለቁብህ እና ሰዎች እንደመሆናችን ሰብአዊ ድክመት እንዳለብን ላሳስብህ እወዳለሁ፤አመሰግናለሁ . . ተመልሰህ ከመሄድህ በፊት ለመገናኘት ተስፋ አደርጋለሁ . . ይሀውና የቢዝነስ ካርዴ . . የደስተኝነት መንገድ ፍለጋህ የት እንደደረሰ ሁሌ አሳውቀኝ።

ከፍተኛ ድካም እየተሰማው ወደ ክፍሉ ሄደና በመጀመሪያ ሻውር ወሰደ . . እንደልማዱ ቲቪ ከፍቶ ዜና ተከታተለ

አዲስ ነገር አልነበረም። ኢሜይሉን ለማየት ኮምፒውተሩን ከፈተና ከኣደም የተላከውን የሚከተለውን መልእክት አገኘ

 

‹‹ከሰላምታ በኋላ

የላክልኝን የተዛቡና የተበረዙ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን አነበብኳቸው፤የሚታመንና ይሆናል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም። በመላክህ አመሰግናለሁ፤ስትመለስ እንወያይባቸዋለን። እንዲህ ያሉትን መልእክቶች መላኩን ትቀጥላህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፣እጅግ በጣም ይጠቅሙኛል።››

ቀጥሎም ተከታዩን የቶም መልእክት አገኘ፦

‹‹ከሰላምታ በኋላ

የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን በተመለከተ ቀደም ብዬ ሁሉም ሃይማኖቶች ዋጋ እንደ ሌላቸው ነግረሃለሁ። ይህ መልእክትህ እስከ ደረሰኝ ድረስ አቋሜን ለማስቀየር ተቃርበህ ነበር፤አሁን ግን የኔን አምነህ መቀበል ጀምረሃል ብዬ ጠርጥሬያለሁ።ክርስቲያኖችም በዚህ በምትተቸው ብሉይ ኪዳን የሚያምኑ መሆናቸውን አትርሳ። በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ቀጠሮአችን ማክሰኞ ስምንት ሰዓት ነው። ሌሎች ነገሮች ካሉህ ላክልኝ።››

ጆርጅ ዛሬ ያሳለፈውን ሁሉ ሊጽፍላቸው ፍላጎት ነበረው፣ዳሩ ግን ድካሙ እየተባባሰበት በመሆኑ አልቻለም
። በመሆኑም አንድ ደብዳቤ በአጭሩ ብቻ ሊጽፍላቸው ወሰነ . . ከሰላምታ በኋላ ሚከተለውን አሰፈረ፦

‹‹መልስህን አንብቤያለሁ፣ዝርዝር ጉዳዮችን አንድ በአንድ እጽፍልሃለሁ። የዛሬው ቀን እንደ ትናንቱ ሁሉ በሁነቶች የተሞላ ነበር። በሃይማኖቶች ውስብስብ ጉዳዮች፣በሃይማኖት ግጭቶች እና ጭቆናዎች፣በተለያዩ የክርስትና ቡድኖች እና አብያተክርስቲያናት መካከል ባሉት ልዩነቶችና ቅራኔዎች . . ላይ ያተኮረ ነበር። ትንሽ ስለ ደካከመኝ የደረስኩባቸውን አንዳንድ ጉዳዮች ነገ እልክላችኋለሁ።››

ኮምፒውተሩን ዘጋና አልጋው ላይ ተንጋለለ። በጣም የደከመውና ድቅቅ ያለ ቢሆንም የሌቪ ምስል፣ደማቅ ፈገግታዋና ሰማያዊ ማራኪ ዓይኖቿ ከሕሊናው ሊጠፉ አልቻሉም። ነገሮች አንዳንዴ ሊደበላለቁ ይችላሉ የሚለው የዶክተር ሐቢብ ቃል ታወሰው።
ስጋት ቢኖረውም በራሱ ይተማመናል፣በሌቪም እንዲሁ ይተማመናል።