አምላክህን እወቅ!!

አምላክህን እወቅ!!

ጥርት ባለ ፀሐያማ ቀን ከሰዓት በኋላ ሦስቱ ወዳጆች በቀጠሮው መሰረት በሴይን ወንዝ ዳርቻ ተገናኙ። ራጂቭወዳጆቹን የቅንጦትበሚመስለው የወንዝ ጀልባ እንዲሳፈሩ ጋበዛቸው . . ሦስቱ ወዳጆች ጀልባዋ ላይ ሆነው በወንዙና በበዳርቻዎቹ በተንጣለለው አስደሳችና ማራኪ አረንጓዴትእይንት እየተዝናኑ ተጓዙ . . ራሽድ አድማሱን አሻግሮ እየተመለከተ ለወዳጆቹ እንዲህ አለ፦

ወንዞች፣ባህሮች፣እጽዋት፣እንስሳት፣ተራሮች፣የሰው ልጅና በዚህ ዓለም ላይ የምናያቸውና የማናያቸውም ፍጥረታት ሁሉ . . እነዚህ ነገሮች ሕይወት እንዲዘሩያደረገ ታላቅ ታምራዊ ጥበብ መኖሩንና ይህ ድንቅ ዓለም ፈጣሪ አምላክ እንዳለው በጉልህ ያመለክታል . . በዚህ ላይ ከኔ ጋር አትስማሙም?

ራጂቭ፦ ካለፈው ውይይታችን አስቀድሞ በነበረን ቆይታ ይህ ዓለም የግድ ፈጣሪ ሊኖረው እንደሚገባ ተስማምተናል። ይሁን እንጂ ከዚህ ጋር የተያያዙና ውይይትና ብጠራ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ይገኛሉ።

ማይክል፦ ልንጀምርበት የሚገባው ዋነኛው ነጥብ ኢንጂነር ራጂቭ ቀደም ሲል እውነተኛው አምላክ ሊገለጽባቸው የሚገቡ ባሕርያትን አስመልክቶ ያነሳው ጥያቄ ነው ብዬ አስባለሁ።

ራሽድ፦ አሁን ያለንበትና የምናስተውለው የተፈጥሮ ውበትና ድንቅ ቅንብር አንተ ከምትለው ጉዳይ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው። አላህ ﷻእውነተኛው ፈጣሪ አምላክ መሆኑን የማመንና እርግጠኛ የመሆን መሰረቱ፣የገዛ ራስህን ሕልውና ጨምሮ ይህንን ፍጥረተ ዓለም አስመልክቶ ‹‹ትክክለኛ የሆነ እሳቤ›› ያለህ መሆኑ ነው። ይህም ይዘቶቹን፣ቅንጅትና ቅንብሮቹን፣እውስጡ የታቀፈውንየእያንዳንዱን ፍጡር ግብና ዓለማን በማወቅ ነው።

ማይክል፦ ይህ ዩኒቨርስ ፈጣሪ አምላክ እንዳለው ተቀብለናል። ስለዚህ አምላክ ያለው ግንዛቤና እሳቤ ከሃይማኖት ሃይማኖት የሚለያይ ሲሆን፣በእሳቤዎቹ መካከል ያለው ልዩነትና ተቃርኖ፣አንዳንድ ሰዎችን ርእሰ ጉዳዩን ከመመርመር ሸሽተው በግልጽ ነን ብለው ባያረጋግጡም ወደ ኤቲዝም የቀረበ ሕይወት እንዲኖሩ ገፋፍቷቸዋል።

ራሽድ፦ ወዳጄ እውነት አለህ። ይሁን አንጂ ያ ሽሽትግን የሆነ አምላክ የማምለክ አስፈላጊነት እንዳይሰማቸው ያላደረጋቸው መሆኑን እጨምርበታለሁ። ከዚህም አልፎ እውነቱን ለመናገር አንዳንዶቻቸው የአምላክን መኖር ሲክዱ የሚያመልኩት የገዛ ራሳቸውን ነው . . ግላዊ ዝንባሌያቸውን ያመልካሉ። እብሪተኞቹ ኤቲስቶች አላህን ﷻ ከማወቅና በርሱ ከማመን የሸሹት፣ከኖሩት ወይም ካስተዋሉት የተዛባ የአምላክ እሳቤ ከመሸሽ በስተቀር አሳማኝ ምክንያ ሳይኖራቸው፣ለእውነተኛው አምላክ ብቻ እንጂ ለሌላ ሊሆን የማይገባ ደረጃና ተመሳሳይ ባሕርያትን ወደ ሰጧቸው ሌሎች ነገሮች ነው የሸሹት።

ራጂቭ፦ ወደ ርእሰ ጉዳያችን ለመግባት አምላክ የግድ በተመሳሳይ ጊዜ የሚፈራና የሚወደድ፣የርሱ አስፈላጊነትም ለሰው ልጆች ከውስጣዊ ስሜታቸው የሚሰማቸው መሆን ይኖርበታል። ይህ ከሰው ልጅ አንጻር ሲሆን፣እነዚህ ባሕርያት ግን በመሰረቱ የሰውን ልጅ ሁኔታ የሚወክሉና ከአንድ የበለጠ አምላክን አስመልክቶ ከአንድ በበለጠ ግለሰብ ዘንድ እውን ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው። ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ሊስማሙባቸው የሚገቡ የእውነተኛው አምላክ ባሕርያትን አቅርበን እንመልከት።

ራሽድ፦ አነጋገርህ ጥሩና ትክክለኛ ነው . . ጉዳዩ ከጀመርነው ነገር ጋር የተያያዘ ነው። የአምላክ መኖር ፍጹም ግዴታ መሆኑን ባረጋገጥን ጊዜ፣ይህ ድንቅ ቅንጅት ያለው ዩኒቨርስ፣ያቀደውና ያስገኘው፣ካለመኖር ወደመኖር ያመጣው ፈጣሪ እንዳለው ተስማምተናል። ይህን ፈጣሪ ነው ጌታ አምላክ ነው ብለን የምንገልጸው። ይህ እኛንና ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ ጌታም፣አምልኮት የሚገባው፣ከርሱ በቀር ማንምና ምንም ሊመለክ የማይገባ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ነው። አንተ እንዳልከውም ማንም ሰው ፍጹማዊ ክብርን፣ፍጹማዊ ፍራቻና ፍቅርን፣ፍጹማዊተስፋና አለኝታን ለርሱና ከርሱ በስተቀር ለማንምና ከማንም ማድረግና መጠበቅ የለበትም . . ከዚህ በመንደርደር ነው የዚህን እውነተኛ አምላክ ባሕርያት ማወቅ የምንችለው።

ራጂቭ፦ የተናገርከውን ተቀብለን ካጸደቅን፣የመጀመሪያዎቹ መሰረታዊ ባሕርያት ይህ አምላክ ሕያውና ሕልውና ያለው፣ይህ ጌታ አምላክም ፈጣሪ መሆን የሚገባው መሆኑ ናቸው ማለት እንችላለን።

ራሽድ፦ ትክክል ነው። ያም በተራው ይህ አምላክ በእርሱነቱና በባሕርያቱ ፍጡር አለመሆኑን ግዴታ ያደርጋል። ፍጡር ቢሆን ኖሮ እንደኛው ፈጣሪ ሊኖረው ግድ ከመሆኑም በላይ አምላክ ሊሆንና አምልኮት ሊደረግለትም አይገባም ነበር። በዚህ መሰረትም ፍጡራን ሁሉ አምላክ ለመሆን ብቁ አይደሉም።

ማይክል፦ እንግዲያውስ ፈጣሪ ማለት ምን እንደሆነ ትርጉሙን የግድ ማወቅ ይኖርብናል።

ራሽድ፦ በአጭሩ እንዲህ ማስቀመጥ እችላለሁ። መፍጠር ማለት ቀዳሚ ምሳሌ ወይም ሞዴል ሳይኖራቸው ነገሮችን ከምንም ፈጥሮ ማስገኘት ነው። ፈጣሪምፍጥረታትን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ሕልውና የሰጣቸው ፈጣሪ አምላክ ነው ማለት ነው። ነገሮችን ሁሉ በፍጹማዊ ጥበቡ አቅዶና ወስኖ ያስገኘ፣ያቀናጀና ያቀነባበረ በመሆኑ በፍጥረቱ ውስጥ ዓላማ ቢስ ከንቱነትና አጋጣሚ ይሆንታ ቦታ የላቸውም ማለት ነው።

የየፍጡራን ባሕርያትን በተመለከተ ግን ዋነኛው ነገር፣ ከመፈጠራቸው በፊት ያልነበሩ ማለትም ካለመኖር ወደ መኖር የመጡ መጀመሪያ ያላቸው ክስተቶች መሆናቸው ነው። ሌላው መጀመሪያ እንዳላቸው ሁሉ የግዴታ መጨረሻና ማብቂያ ያላቸው አላፊ መሆናቸው ነው። በተጨማሪም አቅምና ችሎታቸው ውስን በመሆኑ ሁሌም የሌላን እገዛና ረድኤት የሚፈልጉ መሆናቸው ነው።

ራጂቭ፦ ይህ አምላክ ፈጣሪ ጌታከሆነ ዘንዳ፣ለፈጠራቸው ፍጡራን ገዥና ባለቤት መሆኑ የግድ ነው።

በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ የርሱ ነው፤በእርሱ የተፈጠረ ነው ካልንም፣እርሱ ሁሉንም የሚያውቀውና በዕውቀቱ ስር መሆኑም የግድ ይሆናል። ከርሱ የሚሰወር ነገር ቢኖር ኖሮ የፍጡራኑ ሁኔታ ከፈጣሪያቸው ነጻ ሆኖ መደበቅ በቻለ ነበር። ፍጹማዊ ዕውቀቱ ፍጥረታቱን ያካበበ ለመሆኑ ማስረጃው በፍጥረታቱ ውስጥ የምንመለከተው ፍጹማዊ ስምረትና የተራቀቀ ቅንብር ነው። ይህ ሊሆን የሚችለውና የሚመነጨው ከፍጹማዊ ምሉእ ዕውቀት ብቻ ነው።

ራሽድ፦ የባለቤትነት መብት በሰማያት በምድርና በመካከላቸው ባለው ሁሉ ላይ ፍጹማዊ ባለሥልጣን መሆንን ያስከትላል። ፍጹማዊ ባለሥልጣንነትና ዕውቀት ደግሞ የማቀናበር የመምራትና የተፈጥሮ ሕግጋትን የማኖርና የመደንገግ መብትን ያስከትላል።

ማይክል፦ ይሁንና እኔ ራሴም የአንዳንዳንድ ነገሮች ባለቤት ነኝ፤ብዙ ነገሮችንም አውቃለሁ። እንዲህ መሆኑ እኔም መለኮታዊ ባሕርያት እንዳሉብኝ ያመለክታል ማለት ነውን? . . መቼም ይህ ትክክል መስሎ አይታየኝም!

ራሽድ፦ ወዳጄ በጣም አስፈላጊ አስተያየት ነው። በዚህ መንገድ ባሕርያቱን አንድ በአንድ አንስቶ ማቅረቡ አስገላጊ ቢሆንም ረዥም ጊዜ ይወስድብናል። በመሆኑም ለባሕርያቱ መስፈርት አድርገን ወደምንወስደው አጠቃላይ መርህ መድረስ እንችላለን። በመስፈርቱ አማካይነትም ባሕርያቱን ከሞላ ጎደል ለይተን ማውጣት እንችላለን። የዚህን አጠቃላይ መርህ ገጽታዎች እንዳቀርብ ፍቀዱልኝ፤በእርግጥ በእስላማዊ ዕውቀቴ ላይ በሚሞረኮዝ እሳቤ መሰረት የተቃኘ ነው የሚሆነው።

ማይክልና ራጂቭ፦ መቀጠል ትችላለህ . .

ራሽድ፦ ይህን አጠቃላይ መርህ እንደሚከተለው ማሳጠር ይቻላል፦

አንደኛ፦ ባሕርያትን በጥቅሉ የምሉእነትና የጉድለት ባሕርያት ብሎ በሁለት መክፈል ይቻላል።

የምሉእነት የሚባለው ተገላጩን በመልካም ባሕርያት መግለጽ፣ተቃራኒውንአፍራሽ ባህሪ ከርሱ ማራቅ ማለት ነው።

የጉድለት ባህሪ የሚባለው ደግሞ ተገላጩን አፍራሽ በሆኑ ባህርያት በጎና ገንቢ ተቃራኒውን ከርሱ በማራቅ መግለጽ ማለት ነው።

በዚህ መሰረትም በአፍራሽ ባሕርያት መገለጽን ማስተባበል የማጥራት ማስተባበል ስለሚሆን፣በዚህ ተቃራኒ ማለትም ከምሉእነት ባሕርያት በአንዱ መግለጽ ግዴታ ይሆናል ማለት ነው። አለዚያ ማስተባበሉ የጉድለት ማስተባበል ይሆናል፤በዚህ አለመገለጽ በራሱ ጉድለትና ድክመት ነውና።

ሁለተኛ፦ አንድ ፍጡር ለራሱ የማይፈልገውንና የሚንቀውን ባሕሪ ለፈጣሪ ማረጋገጥ አይቻልም። የወቀሳና የነውር ባህሪ በመሆኑ ለፍጡራን ተገቢ ካልሆነ ባህሪ ሁሉ፣ፈጣሪ ጌታ የጠራና የተቀደሰ መሆኑ የግድ ነው። አምላክ ከሁሉም አንጻር ምሉእ በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱ የነውርና የእንከን ባህሪ በምንም መልኩ ወደ ባህሪያቱ መግባት ተገቢ አይደለም።

ሦስተኛ፦ ፈጣሪን ከፍጡራን ሙሉ በሙሉ የተለየ ማድረግ። ፈጣሪ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር ከቶም የለም . . ለፈጣሪም ሆነ ለፍጡራን መገለጫነት የቀረቡትንና እንደ ዕውቀት፣ርኅራሄ፣ፍቅር፣ . . የመሳሰሉትን ባህርያት በተመለከተ ግን በእውነተኛው የተሟላ ትርጉም በመካከላቸው ተመሳስሎ የለም። የፍጡራን ባህርያት ከጉድለት ከእንከንና ከምክንያት ያልጠሩ በመሆናቸው የፈጣሪ ባህርያት ከፍጡራኑ ባህርያት ፍጹም የተለዩ ናቸው።

ማይክል፦ የምትናገረውን በምሳሌ እያብራራህ ቢሆን መልካም ነው።

ራጂቭ፦ ከጠቀስካቸው ነጥቦች ጋር እያስተሳሰርክ ብታብራራውና ምሳሌዎች ቀደም ሲል ከተነጋገርንባቸው የመጡ ወይም ተጫባጭ የሆኑ ምሳሌዎች ቢሆኑ ተመራጭ ነው።

ራሽድ፦ መልካም፤የመጀመሪያው ነጥብ ሁሉም አስተዋይ ሰዎች ድክመት የጉድለት ባህሪ መሆኑን ይስማሙበታል።የሌሎች ሰዎችን ወይም ነገሮችን እገዛ መፈለግና ራስን አለመቻልም እንዲሁ የጉድለት ባህሪ ነው። በመሆኑም እውነተኛው አምላክ ከነዚህ ሁለት ባህርያት በአንዱም የሚገለጽ መሆን ተገቢው አይደለም። ይልቁንም የግድ ከነዚህ ሁለት ባህርያት የጠራና በተመሳሳይ ወቅትም ተቃራኒያቸው በሆኑ የኃይልና ከሌሎች የመብቃቃት የምሉእነት ባህርያት መገለጽ ይኖርበታል . . ከዚህ በመነሳት ነው የኛ ቁርኣን ጉዳዩን ቁልጭ አድርጎ ባስቀመጡ ሦስት ቃላት አልመሲሕ ዒሳ  እና እናታቸው ፈጽሞ የአምላክነት ባህሪ እንደሌላቸው ያረጋገጠው። አላህﷻ እንዲህ ብሏል፦

{(ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤}[አልማኢዳህ፡75 ]። ምግብ መብላት የሚያስፈልገው ፍጡር ረሃብና የሚያስከትላቸው ድካምና ጉልበት የማጣት ሁኔታዎች ስለሚሰሙት ነው። እናም ምግብ የሚበላ ሰው እንደ ሌለው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ያን ምግብ ማግኘት ያስፈልገዋል። ስለዚህ ሁለቱም ወይም አንዳቸውም የእውነተኛው አምላክ ባህሪ የሌለባቸው በመሆኑ አምላክ ሊሆኑ አይችሉም ማለት ነው።

እውነተኛው አምላክ ከልጅ መውለድም እንደዚሁ የጠራ ነው። እውነተኛው አምላክ እንከንና ነውር ያለባቸውን ደካማ ፍጡራን ከመምሰል ጉድለት የጠራ ነው። ልጅ የሚፈለገውስም እንዲያስጠራ፣እንዲያግዝ፣እንዲወርስ፣ዘር እንዲያስቀጥልና ለመሳሰሉት ፍላጎቶች ነው። እነዚህ ሁሉ ለእውነተኛው አምላክ የማይገቡ የጉድለትና የድክመት ባህርያት ናቸው።

ሁለተኛው ነጥብ፣አስተዋይ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ለምሳሌ ያህል በድክመት ባህሪ መገለጽን ይጸየፋሉ። እናም እውነተኛው አምላክ በዚህ ባህሪ አለመገለጽ ከማንም በላይ ተገቢው ይሆናል። ይልቅዬ የግድ ተቃራኒው በሆነው የምሉእነት ባህሪ ማለትም በኃይልና በብቃት ባህሪ መገለጽ ይኖርበታል። በዚህ መልኩም አልመሲሕ ዒሳ  ከጠላቶቻቸው ጥቃት ራሳቸውን ማዳን የተሳናቸው ከሆኑ ዘንዳ፣በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ አማልክት ተደርገው የሚወሰዱ ጣዖታት ወይም እንስሳትም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እስከሆኑ ድረስ . . ሌሎችን ከክፉ ነገር መጠበቅ፣አምላኪዎቻቸቸውንና አፍቃሪዎቻቸውንም ከቶም ማዳን አይችሉም። ይህ ማንም የሚረዳው ቀላል እውነታ ነው። ስለዚህም ደካማው አቅመቢስ እውነተኛ አምላክ ለመሆን ብቁ አይሆንም።

አርቀው የሚያስተውሉ ሰዎች ለምሳሌ ያህል በግፈኝነት ባህሪ መገለጽን ይቃወማሉ። ስለዚህም እውነተኛው አምላክ ፍትሐዊ በመሆኑ አይበድልም . . በዚህ መልኩ እያንዳንዱን የጉድለት ማስተባበያ ተቃራኒው የሆነ የምልአት ማረጋገጫ ይኖረዋል . .

በመጨረሻውና በሦስተኛው ነጥብ፣ለምሳሌ የዕውቀትን ባህሪ እንውሰድ። ዕውቀት መልካም ባህሪ ሲሆን አፍራሽ ተቃራኒው አለዐዋቂነት ነው . . ምሉእነት አለዐዋቂነትና ማይምነት ተስተባብሎልህ በዐዋቂነት መገለጽ ነው . . ጉድለትና እንከን ደግሞ በማይምነትና በአለዐዋቂነት ተገልጸህ ከዕውቀት መራቆትህ ነው . . አላህ ﷻበፍጹማዊ ዕውቀት የሚገለጽና ከአለማወቅ ፍጹም የጠራ በመሆኑ፣በዕውቀት ባህሪው ፍጹማዊ የሆነ ምሉእነት አለው።

የሰው ልጅ ግን አንዳንድ ነገሮችን በማወቅ ሲገልጽ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ነገሮችን ባለማወቅም የሚገለጽ በመሆኑ . . የዕውቀት ባህሪው ምሉእነት አንጻራዊ ብቻ ነው . . በተቀሩት ባህርያቱም እንደዚሁ ነው።

ማይክል፦ ከሌሊቱ መግባት ጋር ብርድ እየተሰማኝ ነው። የዛሬውን በዚህ ማብቃት ያለብን ይመስለኛል።