ነሲም ሱሳ

quotes:
  • እስላም . . ሰላምና አማን ነው
  • ‹‹አይሁዶች በእስላም ሰንደቅ ስር ከጭቆና እና ከጥቃት ተጠብቀው ፍትሕን አግኝተዋል። ለበርካታ ምእተ ዓመታትም በመልካም አያያዝ የብልጽግና ኑሮ መርተዋል።››


  • የሰው ልጆች መታደል
  • ‹‹ዘመናዊው የምዕራብ ሥልጣኔ ነፍስን ማርካት የተሳነውና ለሰው ልጆች ደስተኝነትን ማጎናጸፍ ያቃተው መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። በዚህ ውድቀቱ ምክንያትም ሰውን ወደ እድለ ቢስነትና ወደ ውጥረት መቀመቅ እንዲዘቅጥ አድርጎታል። የዘመናዊው ሳይንስ ጥረቶችም ወደ ውድመትና ጥፋት ያነጣጠሩ በመሆናቸው፣ሳይንስም በዚህ ሁኔታ በምሉእነት ከመገለጽ፣ወይም በዘመነ እስላም እንደ ነበረው የሰብአዊ ፍጡራን መገልገያ መሣሪያ ከመሆን የራቀ ነው።››


  • የምዕራቡን ስልጣኔ በጥልቀት
  • ‹‹የምዕራቡ ስልጣኔ እውስጡ ሰርስሮ የገባና፣ ውስጠ ይዘቱን የተገነዘበ፣ጥልቅ የሆነ ንድፈ ሀሳባዊና ተግባራዊ ፍተሻም ያካሄደበት ሰው፣ጥማቱን ለማርካት ሲል ስውር በሆነ ስነልቦናዊ ኃይል ወደ እስላማዊ እምነት ምንጭ መሳቡና ማምራቱ የግድ ነው።




Tags: