ሄንሪ ዴ ካስትሬ

quotes:
  • ተአምራዊው ቁርኣን
  • ‹‹ቁርኣን ሀሳብን ተቆጣጥሮ ይይዛል፤ልቦናን ሙሉ በሙሉ ይማርካል። ወደ ሙሐመድ የተላለፈው ስለ እውነተኛነቱ አረጋጋጭ አስረጅ ሆኖ ነው።››


  • ሃይማኖት በመሰረቱ አንድ ነውድን
  • ‹‹የሁሉም ነቢያት ሃይማኖት አንድ ነው። ከአደም ጀምሮ እስከ ሙሐመድ ድረስ በአንድ መንገድ ላይ ይስማማሉ። ሦስት መለኮታዊ መጽሐፎች የተገለጡ ሲሆን እነሱም መዝሙር፣ኦሪትና ቁርኣን ናቸው። ቁርኣን ከኦሪት ጋር ያለው ትስስር ኦሪት ከመዝሙር ጋር ያለው ትስስር ዓይነት ነው። ሙሐመድ ከዒሳ አንጻር የሚታየው ዒሳ ከሙሳ አንጻር በሚታይበት መልኩ ነው። እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ግን ቁርኣን ወደ ሰዎች የተላለፈ የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐ ሲሆን ነቢዩ መሐመድም የነቢያትና የመልክተኞች መደምደሚያ መሆኑ ነው። በመሆኑም ከቁርኣን በኋላ ሌላ መጽሐፍ፣ከሙሐመድ በኋላም ሌላ ነቢይ የለም።››


  • የማያነብና የማይጽፍ መልክተኛ
  • ‹‹እነዚያ አንቀጾች ከአንድ ማንበብና መጻፍ ከማይችል ሰው እንዴት ሊመነጩ እንደሚችሉ ለማወቅ አእምሮ ግራ ይጋባል። መላው የምሥራቅ ሕዝብ በቃላቸውም ሆነ በይዘታቸው መሰሎቻቸውን የሰው ልጅ አእምሮ ማመንጨት የሚሳነው አንቀጾች መሆናቸውን አምኖ ይቀበላል።››




Tags: