የክህደት ጥርጣሬ . .

የክህደት ጥርጣሬ . .

የክህደት ጥርጣሬ . . (1)

ካትሪና እንደ ልማዷ ቤተክርስቲያን አላመሸችም ነበርና ወትሮ ከሚመለስበት ሰዓቱ የዘገየውን የጆርጅን ለመጠበቅ ቁጭ ብላለች። እንደ ደረሰ በሩ ላይ ተቀበለችውና ለምን እንደ ዘገየ ጠየቀቸው . . ዓይኑና ዓይኗ ሲጋጩ ከቶም ጋር ያላትን ግነኙነትና መደወሉን ከርሱ መደበቋን አስታወሰ። ሆኖም መጠየቅ ተወና ለሌላ ጊዜ ለማዘግየት ወሰነ።

- ባለፈው ጊዜ ወደነገርኩሽ አስተናጋጅ ሄጄ አብረን እራት በላን።

- ውይይታችሁ እንዴት ነበር? ስለርሱ ያለህ አስተያየት እንደነበረ ነው ያለው ?

- ግሩም ድንቅ ውይይት ነበር። ትምህርተ መለኮትን የሚያጠና ተማሪ ነው። ይሁን እንጂ ቀለል ባለ ገርና አሳማኝ . . በሆነ መንገድ ነው የሚናገረው።

- በቃ . . በቃ፣ይህ ሁሉ ሙገሳ ምንድነው ! ከፍተኛ አድናቆት ያሳደረብህ ይመሰላል። እህ፣ነገሩማ በጣም የተለመደ ነው፣ትምህርተ መለኮትን የሚያጠና ሰው የግድ እንደዚያ መሆን ይኖርበታል። ግን ምን አለህ ?

- ንግግሩ ራሴን ለማጥፋት አስቤ በነበረበት ጊዜ አግኝቼው የነበረውን ሽማግሌ ንግግር ይመስላል፤አስታወስሽው ?

- አዎ ! ! !

- ከኤቲስቱ ሐኪም ከቶም አነጋገር ጋርም ይመሳሰላል ! ሃይማኖተኛ ሆኖ ንግግሩ ከኢአማኝ ኤቲስት ንግግር ጋር መመሳሰሉ አይገርምም ? !

- ሐኪሙን በኤቲስትነት ስትገልጸው አላግባብ እየተጫንከው ይመሰለኛል፤በአብሬው ተቀምጫለሁ፣ይህን ፈጽሞ አላየሁበትም።

- አብረን በሄድን ጊዜ ክሊኒኩ ውስጥ የነበረወውን ግንኙነት ማለትሽ ነው፣ወይስ ሌላ ግንኙነት ነበር ? !

- አንተ ጆርጅ ! አዎና የክሊኒኩ ግንኙነት ነው። በቤተክርስቲያን የሙሉ ጊዜ የትምህርተ መለኮት አስተማሪ መሆኔን ነግሬው ምንም ትችት አልሰነዘረም፣እንዲያውም አድናቆቱን ነበር የገለጸው።

- ኤቲስት በመሆኑም ይኩራራል፤ከፈለግሽ በፌስቡክ ገጹ ላይ ማየት ትችላለሽ . . ትኩረቱን አሰረፈባትና ፡- በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ካንቺ ጋር መለሳለሱ ከጀርባው ያቀደው ነገር ስላለ ይመስለኛል።

- ምን እያልክ ነው ? ! !

- ምንም . . ምንም አይደለም፣ እንዳው አእምሮዬ ውስጥ ሽው ያለ ግምት ነው። ዋናው ነገር ምናልባት ወደ ሕንድ ልጓዝ እችላለሁና ምን ትያለሽ ?

- ግሩም፣መቼ ነው ?

- ከአስር ቀናት በኋላ።

- ጆርጅ፣የዘር ግንዴ ከሕንድ በተለይም ከደልሂ መሆኑን መቼም ታውቃለህ . . ሕንድ የድንቃድንቅ አገር ነች። ብዙ ችግሮችን ታስረሳሃለች፣ዘና እንድትልም ታደርገሃለች። ይሁንና የሐኪም ቀጠሮውን እንዴት ታደርጋለህ ?

- መጪው ሰኞ ቀጠሮ ስላለኝ ቀጣዩን ቀጠሮ እንዲያዘገይልኝ እጠይቀዋለሁ።

- በጣም ጥሩ።

የክህደት ጥርጣሬ . . (2)

ጆርጅ፣ ካትሪና ከቶም ጋር ያላትን ግንኙት ካወቀ በኋላ ራሱን ለማረጋጋትና ግድ የሌለው አድርጎ ራሱን ለማሳመን ቢሞክርም፣ ውስጡ እየተረበሸ መጥቷል። ረቡዕ ጧት ግን ከካትሪናና ቶም የስልክ ምልልስ ሰምቶት የነበረውን የዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ቀጠሯቸውን ጠብቆ በድንገት ለመያዝ አሰበና ቶሎ ብሎ ወደ ዶክተር ቶም ክሊኒክ ስልክ ደወለ። የእንደግዳ መቀበያ ሰራተኛውን በራድን የሚቻል ከሆነ ቀጠሮው ወደ ዛሬ ምሽት እንዲሸጋሸግለት ጠየቀ።

- ዛሬ ማድረግ አይቻልም።

- ለምን ?

- ኣ፣ዶክተር ዛሬ ሁለት ሰዓት ላይ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ቀጠሮ ያለው በመሆኑ ።

- እስከዚህ ድረስ በጣም አስፈላጊ ነው?

- ምናልባት፣ዋናው ነገር ቀጠሮውን ወደዚህ ማሸጋሸግ የማይቻል ነው። ቀጠለና ጎላ ባለ ድምጽ ሳቀ።

- አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ወደ ክሊኒኩ እመጣና ባለ ቀጠሮው ታካሚ ምናልባት ከዘገየ በርሱ ፈንታ እኔ እገባለሁ።

- አይ፣አይቻልም አልኩ'ኮ፣ደግሞም የዶክተሩ ቀጠሮ እዚህ ክሊኒክ ውስጥ አይደለም . . ልክ በዚህ ሰዓት መምጣት በጣም ያሳሰበህ ትመስላለህ፣ የምትፈልገው ይገባኛል!! አለው በማፌዝ። ቀጠለና ፡- ለማንኛውም መምጣት ተችላለህ፣ና የምትፈልገውን ሁሉ በትክክል እነግረሃለሁ፤ችግርህን ሁሉ እፈታልሃለሁ . . ዳግም ከፍ ባለ ድምጽ ሳቀና ፡- እጠብቀሃለሁ እንዳትቀር፣አለው።

ጆርጅ የሥራ ሰዓቱ ሲያበቃ አደምን ለማግኘት እየተቻኮለ ወጣ። የቶምና የካትሪና ጉዳይ በጣም ስለ አሳሰበው በጉዳዩ ላይ አደምን የማማከር ሀሳብ አድሮበታል። መኪናውን ካፌው ፊትለፊት አቁሞ አዳም ከሥራ የሚወጣበትን ሰዓት መጠባበቅ ጀመረ። ከተዋወቁ ገና ጥቂት ቀናት ብቻ የተቆጠሩ እየሆነ የግል ሕይወቱን ጉዳይ እስከማማከር ደረጃ ድረስ ይህ ሰው ልቡ ውስጥ መግባት እንዴት እንደቻለ ራሱን ደጋግሞ ጠየቀ።
አደም የጆርጅ መኪና መቆሟን አየና ተራው ሲያበቃ የሥራ ልብሱን ቀይሮ ወዲያውኑ ወደ ጆርጅ አመራ። ጆርጅ ሲያየው ወደ ቤቱ ያድርሰው ዘንድ እንዲገባ ጠየቀውና አደም እሽ ብሎ ገባ።

- አደም . . በጣም በሚቀርብህ ሰው ላይ ጥርጣሬ አድሮብህ ታውቃለህ?

- ፈጽሞ አላጋጠመኝም፣በጣም ከባድ መሆኑ ግን ይሰማኛል።

- ባለ ትዳር ነህ?

- አይደለሁም።

- ከተቃራኒ ጾታ ጋር ያለህ የፍቅር ግንኙነትስ እንዴት ነው?

- ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም ዓይነት የፍቅር ግንኙነት የለኝም ! ጆርጅ ምንድነው የፈለከው?

- የኔ ሐኪም ጨዋነት የጎደለው ሰው ነው አላልኩህም ነበር?

- ብለሀኛል !

- ባለቤቴ ሃይማኖተኛ ከመሆኗ ጋር ጠጪና ጥርጣሬን በሚጭር ሁኔታ በምሽት ድግሶች ላይ ታመሻለች ብየህ አልነበረም?

- ብለሀኛል !

- ወየውልኝ፣በርሱና በባለቤቴ መካከል ኢሞራላዊ የሆነ ግንኙነት ይኖራል ብዬ መጠራጠር ጀምሬያለሁ፣ዝም ብዬ እየተወሰወስኩ ይሆን?

አደም ትካዜ የሚነበብበትን የጆርጅ ፊት እያስተዋለ ጥቂት ጊዜ በዝምታ ካሳለፈ በኋላ፡-

- ምን እንደምል አላውቅም፣ምን እንደሚሰማህ እረዳለሁ . . በመሰረቱ ሰዎች ላይ ቅን አመለካከት ልኖረንና በበጎ ልቦና ልናያቸው ይገባል። እርግጠኛ እስካለሆንክ ድረስ እንዲየው ዝም ብለህ ሰዎችን ለመጠራጠርና ለመወንጀል አትቻኮል።

- ዛሬ ከርሱ ጋር ለማምሸት ቀጠሮ ይዛለች !

- እርግጠኛ ነህ?! ደሞም ብዙ ጊዜ እንደሚትጠጣና እንደምሚታመሽ ነግረሀኛል፣ከቶም ጋር ማምሸትን ከሌላው ጋር ከማምሸት ምን ለየው?

- ቶም ከሴት ታካሚዎቹ ጋር ያለው ግንኙነት የሚያስጠረጥረው ሲሆን ሰውየው ጨዋ ስነምግባር የሌውም። ካትሪናም እንዲሁ ማምሸቷ የሚያስጠረጥራት ነው። በተጨማሪም ግንኙነቱን ሆን ብላ ከኔ ሸሽጋለች። የ . . የበራድ አነጋገርም በጣም እንግዳ የሆነ አነጋገር ነበር!

- በራድ የምትለው ደሞ ማነው?

- የቶም ጸሐፊ ነው። ፈጽሞ የማይመች ዓይነት ሰው ነው። የሚረብሹና የተድበሰበሱ ነገሮችን ይጠቋቁመሃል!

- አሁን ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ነው፣ለካትሪና ደውለህ በአንድ ታዋቂ ሬስቶራንት ለራት ግብዣ ብትጠራት ምን ይስለሃል?

- እሞክራለሁ !

ጀርጅ ለካትሪና ደወለ። ከድምጹ ቅላጼ የሚገኝበትን ስሜታዊነት እንዳታውቅ የተቻለውን እየሞከረ አደም የነገረውን ሀሳብ አቀረበላት። በዝነኛ ሬስቶራንትና አብረው ቢሚያሳልፉት ውብ ምሽት ልቧን ለማማለል ሞከረ። ይሁን እንጂ ደግማ ደጋግማ ይቅርታ በመለመን ግበዣውን ለሌላ ቀን እንዲያስተላልፈው ጠየቀች። የቤተክርስቲያን የድግስ ሥርዓት በመሆኑ መቅረት የማትችል መሆኗን ነገረቸው።

- ይኸውልህ በቤተክርስቲያን የምሽት ድግስ በማሳበብ እምቢ ብላለች።

- እናማ የቤተክርስቲያን የድግስ ሥርዓት ከሆነ ዘንዳ ለምን ትወነጅላታለህ?

- የቤተክርስቲያን የምሽት ድግስ ቀይ ቅሌቶች እጅግ አሳፋሪና ጠረናቸው ከርቀት የሚረብሽ ነው !

- ምናልበት እኔ ላላውቃቸው እችላለሁ !

ጆርጅ ወደ አደም መኖሪያ ቤት ደረሰ፤ለትህትናውና ላደረገለት እገዛ አመሰገነውና . .

- በግላዊ ጉዳይ ለምን እንደ ረበሽኩህ አላውቅም ! እባክህን ይቅርታዬን ተቀበለኝ።

- ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግህም፣የማደርግልህ አንዳች ነገር ቢኖር እንዴት ደስ ባለኝ ነበር። በል በቸር እንገናኝ . . አንድ ነገር ብቻ ልነግርህ እፈልጋለሁ ፡- ስለርሱ የነገርከኝን ያን በራድ ያልከውን ሰውዬ ተጠንቀቅ። በጥርጣሬና በግራ መጋባት ስንጠመድ በከፍተኛው የድክመት ደረጃችን ላይ ስለምንሆን በስሜትህ እንዲጫወት አትፍቀድለት።

- ድክምክም ብሎኛል፣ ከሁለት ሰዓት በፊት የግድ መፍትሔ ማግኘት ይኖርብኛል ! ፈቃድህ ይሁንና እኔ ልሂድ።

የክህደት ጥርጣሬ . . (3)

የጆርጅ ስልክ አቃጨለ . . የደወለው በራድ ነበር። ጆርጅ ግን የሚረብሹ አስተያየቶችን ከርሱ ለመቀበል በሚፈቅድለት ሁኔታ ላይ አልነበረም። ይሁን እንጂ ደጋግሞ መደወሉ ስልኩን እንዲያነሳና ምን እንደሚል እንዲያውቅ ገፋፋው።

- ሃሎ . . የት ነህ? አንተን በመጠበቅ ላይ ነኝ። ቶም ወደ አስፈላጊ ቀጠሮው ሄዷል !

- ወዴት?

- ወደ ቀጠሮው ነዋ ! ምኑን ማወቅ ነው የፈለከው?

- እባክህን እኔ ታክቶኛል !

- ኣ፣ ለማንኛውም ወደኔ ና፣ ለችግርህ ከኔ ዘንድ መፍትሔ ታገኛለህ።

- መፍትሔ አንተ ዘንድ ይገኛል? ! እንግዲያውስ አሁኑኑ እመጣለሁ።

ጆርጅ ወደ ክሊኒኩ ሲደርስ በራድ እየተጠባበቀው ነበርና ጠንከር ባለ አነጋገር ያናግረው ገባ . .

- ቶም የትነው ያለው?

- ከአፍታ በፊት ወጥቶ ሄዷል።

- ከማን ጋር?

- ከማን ጋር እንደሆነ ታውቃለህ። ይልቅ ቶም ክሊኒክ ውስጥ እንቀመጥ፣አረፍ በል !

- እኔ የማውቀው ምንም ነገር የለም፣ከኔ ምንድነው የምትፈልገው?

- ቶም የወጣው ከካትሪና ጋር ነው።

- እየዋሸህ ላለመሆንህ ዋስትናዬ ምንድነው?

- እኔ አልዋሸሁም !

የሚያደርገው ጠፍቶት ጆርጅ ራሱን አቀረቀረ፤ከዚያ ቀና ሲል ዓይኖቹ በድንገት ጠረጴዛው ላይ ባለው ትንሽ የሴት ቦርሳ ላይ አረፉ። ከካትሪና ቦርሳ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በራድ ላይ ጮኸ፡-

- ይኸ ምንድነው?

- እህ፣የማይታመን ነው ካትሪና ቦርሳዋን ረሳች? ! የተናገርኩት እውነት ስለመሆኑ ይኸውልሃ ማስረጃው።

- ወዴት ነው የሄዱት?

- የምሽት ፕሮግራም አላቸው . . እዚያው ቤተክርስቲያን መሰለኝ።

- ቶም 'ኮ ኢአማኝ ነው፣ኤቲስት ነው . .

- ለምን አብረሃቸው አልሄድክም? ወይስ አንተ ባለህበት የማይፈጸም የተለየ ጉዳይ ኖሯቸው ነው? በከፍተኛ ድምጽ ሳቀ . . ከዚያም ቀጠለና ፡- ወዳጄ ያለህበትን ሁኔታ አስቸጋሪነትና ስሜትህን እረዳለሁ። ከዚህ የስነልቦና ጫና የሚያሳርፍህ ነገር አለኝ።

- ምን ይሆን?

- አንዲት የደስተኝነት እንክብል ናት። ምናልባት ስለ ሄሮይን አደገኛነት ሰምተህ ይሆናል። ግና ተጠቃሚው የሚሰማው የደስተኝነት ስሜት ምን ያህል እንደሆነ አንተ እንደማታውቅ እኔ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኘ። አንዷ እንክብል ብቻ በፍለጋ የምታሳድደውን ደስተኝነት ታጎናጽፈሃለች፣ ትፈልጋለህ?

- አንዷ እንክብል ብቻ !

ጆርጅ ውስጡ
ድል የተመታና
እጅ
የሰጠ መስሎ ስለተሰማው፣ በራድ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ጠብቀኝ፣የደስተኝነት እንክብል ይዤልህ እመጣለሁ፣አልቆይም ብሎት
ወጣ። ጆርጅ በዚህ ጊዜ በስነልቦና ጫናው ምክንያት መንፈሱ እንደተናደ ሲሆን በራድ እንደ ወጣ ባዶነት ተሰማው . . ሞባይሉን አውጥቶ በመጨረሻ ያደረጋቸውን ጥሪዎች
ተመለከተ።
የበራድ፣የካትሪናና የአደምን ቁጥሮች ነበሩ። ወዲያውኑ ለአደም ደወለ።

- ሃሎ፣ጆርጅ።

- የነገርኩህ ነገር እርግጠኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ።

- ነገሮችን ቀለል አድርገህ ውሰዳቸው። አብረው መውጣታቸውን ብታረጋግጥ እንኳ፣ያ ማለት ባንተ ላይ ክህደት ትፈጽማለች ማለት ነው?

- አደም እኔ በጣም ተንከራትቻለሁ። በራድ ውጥረቴን የሚቀንስና መንፈሴን የሚያረጋጋ ነገር ሊያመጣልኝ ለጥቂት ደቂቃዎች ትቶኝ ሄዷል።

- የሚያዝናናህና ውጥረትህን የሚያረጋጋው ምንድነው?

- አንዲት የደስተኝነት እንክብል ብቻ ነች ነው ያለኝ !

- አደንዛዥ እጽ ! አብደሃል'ንዴ? በግራ መጋባትና በጥርጣሬ ጊዜ ሌሎች በቀላሉ ይጫወቱብናል አላልኩህም ነበር . . ጆርጅ ምን ነካህ? ይኸ ሽሽት ነው። በሽሽት ደስተኝነትን አገኛለሁ ብለህ ታምናለህ? እባክህን አሁኑኑ በቀጥታ ወደኔ መምጣት አለብህ . .

- ሞራሌ ምን ያህል ድባቅ እንደ ተመታ ልነግርህ አልችልም፤ ሰውየውም ገና አልመጣም፣ እሽ . . መልካም፣መጣሁ።

ጆርጅ ወደ አዳም መኖሪያ ቤት ሲደርስ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ነበር። አዳም ተቀበለውና ወደ ውስጥ እንዲገባ ጋበዘው። የአዳም ቤት ትንሽ ሆና በሥርዓት የተያዘችና ቀለል ያለች ቤት ናት። ጆርጅ አንዱ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ አደም ሻይ አዘጋጀለት። ሲጠጣም ትንሽ የመዝናናት ስሜት ተሰማው።

- ነገሮቹ አሁን እንዴት እየሄዱ ናቸው? አብረን የአካል እንቅስቃሴ ብናደርግ ምን ይመስለሃል?

- እስፖርት ! አሁን ጊዜው ነው ብለህ ነው?

- በየለቱ ከ3-5 ኪሎ ሜትር በእግር የመጓዝ ወይም ሶምሶማ የመሮጥ ልማድ አለኝ። ዛሬ ገና አልተጓዝኩምና በል ጆርጅ ከጎኔ ሁን፣ቤቴ ለእግር ጉዙ አመቺ ቦታ ላይ ነው የሚገኘው።

- እሽ . . ይሁን፣ምንም አይደለም !

አብረው በመጓዝ ላይ እያሉ አደም ወደ ጆርጅ ፊቱን አዙሮ ስለ አካል እንቅስቃሴ ጥቅሞች፣መንፈስን ለማነቃቃትና የስነልቦና ሁኔታን በማሻሻል ረገድ ስለሚጫወተው ሚና በማውራት ላይ እያለ ሳያስብ የጆርጅ ዓይኖች ሲያነቡ ተመለከተ።

- ሚስቱ በሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ባለችበት ጊዜ አካላዊ እንቅስቃሴ ለሚያደርግ እንዳኔ ላለና ሞራሉ ለተንኮታኮተ ሰው፣እስፖርት ደስታ ሊያስገኝለት ይችላል ብለህ ታምናለህ?

- እስፖርት ሞራል ያነቃቃል፣መንፈስን ያድሳል። ይሁን እንጂ ብቻውን ማንንም ደስተኛ አያደርግም። ደስተኝነት ከውስጣችን እንጂ ከየትም አይመነጭም፤ሊመጣ የሚችለው ከውስጣችን ብቻ ነው፣አደንዛዥ እጽና አስካሪ መጠጦች ቀርተው እስፖርትም ሊያመጣው አይችልም !

- በድክመት ሁኔታ ላይ ነበርኩ፣በራድ መጫወቻ ሲያደርገኝ ነበር።

- በድክመታችን ጊዜ ወንጀለኞች በኛ እነዲጫወቱ እድል ልንሰጣቸው አይገባም !

- ካንተ ጋር በመጓዝ ላይ እያለሁ ውስጤ ሲናድና ድል ስመታ፣መንፈሴ በየሰከንዱ ሲሞት ይሰማኛል።

- ሀሳብ ጭንቀትና ውጥረት ሲያጋጥምህ ቀደም ሲል ምን ታደርግ ነበር? !

- ትዝ አለኝ፣የዱሮው ሐኪም የሰጠኝን የሚየረጋጋ አስታጋሽ እንክብል እወስድ ነበር . . ግን እንቅልፍ እንድተኛ ያደርገኛል።

- የማስታገሻ እንክብል ከወንጀለኛ ሳይሆን ከእስቴሽያሊስት ሐኪም ከሆነ ደግ ነው፣እንክብሎቹን አሁን ይዘሃቸዋል?

- አዎ መኪና ውስጥ አሉ።

- ወደ ቤት እንመለስና አንዱን ፍሬ ትወስዳለህ።

- ወደ ቤቴ እሄድና አወስደዋለሁ።

- እዚሁ ውሰደውና እኔ ዘንድ ተኛ።

- ካትሪና የት እንዳለች አላውቅም አንተ ዘንድ እተኛለሁ ! !

- ጥርጣሬህን የወንጀሏ ማስረጃ አድርገህ አትውሰድ፣ምናልባት ከቶም ጋር የሆነችው እሱን ወደ ክርስትና ለመጥራት ሊሆን ይችላል !

- ሊሆን ይችላል፤እርግጠኛ ብሆን እንዴት ደስ ባለኝ፤አሁን ካለሁበት ጥርጣሬ ይሻለኝ ነበር።

የወሰደው እንክብል መስራት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ጆርጅ ረዘም ላለ ጊዜ አንቀላፋ . . ጧት አራት ሰዓት ላይ ሲነቃ አደም ቁርስ አዘጋጅቶለት አገኘው . .

- እንደምን አደርክ፣ቁርስ ተዘጋጅቷል።

- ስንት ሰዓት ሆነ?

- አራት ሰዓት ነው።

- አዝናለሁ፣አንተን ከሥራህ አስቀረሁ፣እኔም ከሥራዬ ተስተጓጎልኩ።

- ምንም አይደለም፣እኔ አስፈቅጃለሁ፤አንተ ምክትል ዳይሬክተር በመሆንህ አንድ ቀን መቅረት ችግር አያስከትልብህም።

ጆርጅ ከአደም ጋር ቁርሱን በልቶ ላደረገለት መስተንግዶና ላሳየው ትሕትና አመሰገነው። ሁኔታው ትናንት ከነበረበት በጣም የተሻለ ሲሆን ጥሩ ውስጣዊ መረጋጋትም ተሰምቶታል።

- በጣም ጥሩ፣የበለጠ ልትረጋጋ ይገባሃል። ከፍተኛ ጭንቀትና ያልተጠበቁ ለውጦች ብዙውን ጊዜ ውስጣዊ ደስተኝነትን ይነሳሉ።

- ምን ማለትህ ነው?

- ለዋነኞቹ ጥያቄዎችህ እልባት ካገኝህ ለሌሎች ችግሮችህ የተሻለ አያያዝ ማድረግ ትችላለህ። የሚያጋጥሙህን ጫናዎችና ችግሮች ለመቋቋም የበለጠ የመንፈስ ጥንካሬና ብቃት ይኖረሃል።

- የካትሪና ጉዳይ ቀላል ነው እያልከኝ ነው?

- አይደለም፣ማለት የፈለኩት ውስጣዊ ደስተኝነት ጥርጣሬያችንን ያስወግዳል፣ትናንሾቹን ችግሮቻችንን ይፈታል፤ሰለዚህም ትኩረትህ በደስተኝነት ፍለጋውና ለጥያቄዎችህ ምላሽ በማግኘት ወደዚያ የሚያደርሰውን መንገድ በመከተሱ ላይ ይሁን ነው። ይህን ስታደርግ ሕይወት እንደገና እንዴት እንደሚቀመርና ለሕይወት ያለህ አመለካከት ሙሉ በሙሉ እንዴት እንደሚለወጥ ታያለህ።

- ከተናገርከው ውስጥ ያልተረዳሁት ነገር ቢኖርም ያልከውን ለማድረግ ቃል እገባልሃለሁ።

- ንግግሬ ግልጽ ነው። ቅለትና ጥልቀት ባለው ስልት በዋነኛው ጉዳይህ ላይ አትኩር። ያን ስታደርግ ደስተኝነት ከውስጥህ ከራስህ መንፈስ ይመነጫል፣ይህ ሲሆን ለችግሮችህ ሁሉ መፍትሔ ታገኛለህ።

- ምናልባት . . አመሰግናለሁ። ከኔ ጋር ለፍተሃል . . አሁን ወደ ሥራ እሄዳለሁ፣በተጨማሪም ዛሬ ከሐኪሙ ጋር ቀጠሮ አለኝ።

- በካትሪናና በቶም ላይ ከተለመደው የተለየ ነገር ላለማሳየት ሞክር። በቅርብ ወደ ሕንድ መሳፈርህ ነውና ከጉዞው ስትመለስ የሚሆነው ይሆናል። ነገሮችን የምትወስዳቸው ቀለል አድርገህ ሳታወሳስብ፣በደስተኝነት መንፈስ እንጂ በትካዜ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን።

- እሞክራለሁ።

የክህደት ጥርጣሬ . . (4)

ጆርጅ በቀጠሮው መሰረት ማታ ወደ ቶም ክሊኒክ ሄደ። ሲገባ በራድ በክፉ ፊት ተቀበለው . .

- ትናንት ወዴት ነው የፈረጠጥከው?

- አልፈረጠጥኩም፣ሥራ ነበረኝ።

- ለምን አልጠበቅከኝም?

- አደንዛዥ እጽን እጠላለሁ፣ከራሴ ችግሮች መሸሽንም እጠላለሁ።

- ነው'ንዴ! . . ጥሩ፣ችግሮችህን ተጋፍጠሃላ?

- ከቶም ጋር ቀጠሮ አለኝ፣አለ ወይስ ትቼ ልሂድ?

- እህ . . አለ፣የደስተኝነት እንክብል እንደሚያስፈልግህ ግን እርግጠኛ ነኝ፣አንድ ቀን ለመፈለግ መመለስህ አይቀርም። ሐኪሙ እየጠበቀህ ነው፣የካትሪናን ባል ለማግኘት በጣም ጓግቷል መሰለኝ፣ በል ግባ!

ጆርጅ ሲገባ ቶም ፊቱ ጨፍግጎና የታከተው ሆኖ ተቀበለውና ሻይ አቀረበለት። እሰከ ሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ በማምሸቱ ትንሽ ድካም የተሰማው መሆኑን ገልጾለት ይቅርታ ጠየቅ . . ሐኪሞች በተለምዶ ማምሸትን የሚከለክሉ በመሆኑ ጆርጅ በቶም አነጋገር የመገረም ስሜት ቢያሳይም ቶም ግድ የሌለው በመምሰል ወዲያውኑ አርእስቱን ቀየረው። በመቀጠልም መልሱን እንዳላገኘ በመገመት ለጆርጅ ጥያቄ አቀረበ፡-

- ለበቀደሙ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተሃል?

- አግኝቻለሁም፣አላገኘሁምም።

- እንዴት? መልካም ፈቀድህ ከሆነ አብራራልኘ?

- በጣም አሳማኝ የሆነ ምላሽ አለኝ፣ነገር ግን የተሟላ አይደለም።

- ጥሩ፣መልሱን ከየት ነው የምናገኘው?

- መልሱ ፡- ጥያቄዎቹን በቅለት እንጂ በአስቸጋሪነታቸው አለመመልከት ነው፤ይህን ስናደርግ መልሱ በቀጥታና ቀለል ባለ ሁኔታ ግልጽ ይሆናል።

- ፍልስፍናዊው መንገድ በአብዛኛው - የሰላ አእምሮ ያለንና በጥልቀት የምንገነዘብ መሆናችንን ለማሳያት ሲባል - ነገሮችን በማወሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነው።

- የበለጠ ጥልቀት ያለው ግን በማቅለል ውስጥ ነው። ለጥያቄዎች በጥልቀት ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ይበልጥ ተመራጭ አይደለምን?!

- በጉዳዩ መፈላሰፍ የጀመርክ መሰለኝ . . እስኪ አድርገው በሚል ቅላጼ ፡- ነገሩን እንዳሻህ አቅልለውና ለጥያቄዎቹ መልሱን ከየት ታመጣለህ?

- ከፍጥረታት ለማግኘት ፈላልጌ ከግዑዝ አካላትም ሆነ ከእንስሳት ዘንድ ማምጣት እንደማንችል ተገንዝቤያለሁ . . እናም ምን ቀረ?

ጆርጅ ዓይን ዓይኑን እያየ ቁርጥ ባለ አነጋገር፡-
-አሃ፣ ሰዎች ቀሩ ልትለኝ ነዋ!

- ልክ ነህ፣ከሰዎች ወይም ከጌታቸውና ከፈጣሪያቸው ዘንድ ነው።

- የሰዎች ፈጣሪ ጌታ መኖሩን አላምንም !

- ታድያ ፍተጥረታት እንዴት ሊገኙ ቻሉ? !

- በአጋጣሚ እንበል፣ራሳቸውን በራሳቸው ፈጠሩ እንበል፣በሆነ ሌላ ነገር ነው እንበል ! በዚህ ጥያቄ ራሴን ምቾት መንሳት አልወድም።

- ፈላስፋው ! ይህማ የፈላስፎች ስልት ሳይሆን ከጥያቄዎቹ የመሸሽ ስልት ነው። የጠቀስካቸው መላምቶች ሁሉ ምክንያታዊ አይደሉም። አንድ ነገር ራሱን በራሱ ይፈጥራል ብሎ የሚቀበል አእምሮ የለም። አጋጣሚም እንዲህ የተራቀቀና የተቀናጀ ሊሆን አይችልም። ሌላ የምልህ ነገርም የለኝም . . ከመቀመጫው ብድግ ብሎ ቀጠለ ፡- ባንተ መንገድ ልጓዝና ወዴት እንደምንደርስ እናያለን፣መጀመሪያ ላይ አሳማኝ መስሎ ቢታየን እንኳ ወደ እውነታው እስኪያደርሱን ድረስ ጥያቄዎቹን መለጎም የለብንም።

- ጥያቄዬን አልመለስክልኝም . . ለጥያቄዎቹ መልስ የምናመጣው ከወዴት ነው?

- ከሰዎች ፈጣሪ ዘንድ፣ከማንም በላይ የሚያውቃቸው እርሱ ነውና።

ቶም ለረዥም ጊዜ ራሱን አቀርቅሮ ቆየና ቀና ብሎ፡-

- የተናገርከውን ባልስማማበትም አደንቀዋለሁ፣በመሆኑም በተናገርከው ላይ አልከራከርም፤ይሁን እንጂ ጥያቄዎችን ማቅረብ እቀጥላለሁ። ስህተትህን የሚገልጹ ጥያቄዎች አቀርብልሃለሁ። አንተ የምትለውን እውነት ነው ብለን እንቀበለውና . . ምላሽ የሚሰጠን የሰዎች ፈጣሪ ጌታ ቡድሃ ነው፣ጸሐይ ነች፣ወይስ መንፈስ ቅዱስ፣ወይስ ሌላ ነው . . ? የሰዎች አማልክት የተለያዩና የሚለዋወጡ ናቸውና ከመካከላቸው እውነተኛው አምላክ የቱ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እንችላለን? የሃይማኖቶች ቁጥር በጣም ብዙ መሆኑን ታውቅ የለ ? !

- ልክ ነህ ከ10000 የሚበልጡ እምነቶች ይገኛሉ። ከነዚህ አንዱ የሆነው የክርስትና ሃይማኖት ብቻ 338830 የተለያዩ ሰክቶችና ፈለጎች ይገኙበታል።

- ያጋጠመኝ የሞቀ ክርክርና ጥልቅ እውቀት ያለው ግለሰብ ነው። መልሱን ትክክለኛ ነው ብለን በመውሰድ ጥያቄውን እናሟላውና ፡- መልሱ ትክክለኛ ስለመሆኑ ዋስትናው ምንድነው?

- በቀላሉ ለመመለስ አጠር ያለ ቀላልና ውስብስብ አለመሆኑ፣ደስተኝነትን የሚያጎናጽፈን፣ከአእምሮና ከሎጂክ ጋር የማይቃረን፣ወይም ከሳይንስ ጋር የማይጋጭና እርስ በርሱም የማይጻረር መሆን፣ሁሉንም የሕይወት ፈርጆች የሚሸፍን መሆን ነው።

- ቀለል ያለ ጥልቀት ያለውና ትክክለኛ የሆነ መልስ . . ስትል ማንኛውም መልስ ትክክለኛ ሆኖ ቢገኝና ደስተኝነት የማያጎናጽፈን ወይም አእምሮና ሎጂክን የሚጻረር ከሆነ፣ወይም ውስብስብና ሁሉንም የሰው ልጅ የሕይወት ፈርጆች የማይሸፍን ከሆነ አንቀበለውም ማለትህ ነው !

- አዎ . . በትክክል እንደዚያ ነው !

- ግሩም ነው ! እንዲህ ያለው ምላሽ ከተገኘ እኔ ካንተ ጋር ነኝ። ከዚያም ፈገግ ብሎ ቀጠለ ፡- የመልሳችንን ትክክለኛነትና የተከተልነው ስልት ትክክለኛ ወይም የተሳሳተ መሆን አለመሆኑን የሚያሳዩ አዳዲስ ጥያቄዎችን እሰጠሃለሁ . . አሁንም አፈገገና ቀጠለ ፡- የኤቲዝም ማስረጃና እግዚአብሔርን መካድ ተራ ዝቅጠት በመሆኑ ላይ ካንተ ጋር ብስማማም፣አሁንም አምላክ የለም የሚል እምነት አለኝ . . ለማንኛውም ወዴት እንደሚያደርሰን በማናውቀው መንገድ አብረን እንጓዛለን። የማቀርብልህ ጥያቄ ግን ፡- መልሱን የምታገኝበት አምላክ የትኛው ነው? በየትኛውስ ሃይማኖት መንገድ ነው?

- ጉዳዩን ቀላል እናድርገውና ሁለት የሃይማኖቶችና የአመለካከቶች ጎራዎች ይገኛሉ። የመለኮታዊ ሃይማኖቶች ጎራና የምድራዊ ሃይማኖቶች ጎራ። ስለ የትኛው ስብስብ ይሆን የምትጠይቀው?

- ልክ ነህ . . ሃይማኖቶች ብዙ ናቸው። ለማቅለል ሲባል በዋነኛ ምድቦች ብቻ መክፈሉ የግድ ነው። ይህን አላሰብኩም ነበር። አንተ ወደ ሕንድ መሄድህ ነውና ጥያቄውን ፡- ከሃይማኖቶች ውስጥ የተሻለው መለኮታዊው ነው ወይስ ምድራዊው ሰው ሰራሽ? ወደሚለው እንለውጥ። ለጥያቄው በምትሰጠው ምላሽ ላይ ተመርኩዘን ከሁለት ሳምንታት በኋላ ስትመለስ በሚኖረን ቀጠሮ ዝርዝሩን እንመለከታለን። በአገረ ሕንድ እኔ ወዳለሁበት ኢአማኝ ኤቲስትነትና ሁሉንም እርግፍ አድርጎ ወደ መተው የሚያደርሱ ሃይማኖቶች ያጋጥሙሃል ብዬ አስባለሁ።

- ወደ ሕንድ ትጓዛለህ ! እንዴት አወቅህ?

ቶም ተርበትብቶ አንደበቱ ተሳሰረ፤መውጫ ለመፈለግ ቢሞክርም መጣፊያ አጠረው!

- ከ . . ከካትሪና ነው ያወቅኩት . . ድንገት ቤተክርስቲያን ውስጥ . . በአጋጣሚ አይቻት ነበር።

- ፈጣሪ አምላክን የሚያስተባብል ኤቲስት ወደ ቤተክርስቲያን መሄዱ ደግ ነገር ነው !

- ወደ ቤተክርስቲያን የሄድኩት የአማኞችን ባህሪና ስነ ልቦናቸውን ለማጥናት እንጂ ለአምልኮ አይደለም።

- አሃሃ፣የካትሪናን ስነልቦናዊ ሁኔታ እንዴት አገኘኸው?

- በአመለካከቷ፣በመንፈሷ፣በገጽታዋ፣በተክለ ሰውነቷ ምስራቃዊ መስህብነት የሚስተዋልባት ሴት፣ ብልህና ሃይማኖተኛ ሴት ሆና ነው ያገኘኋት።

- ትኩረትና አድናቆትህን የሳበች ይመስላል? !

- እውነቱን ለመናገር በሃይማኖት አጥባቂነቷና በእርግጠኛነቷ ተደንቄያለሁ። ያንተ በመሆኗ እንኳ ደስ አለህ እለሃለሁ፣ደሞም በጣም ነው የምታፈቅርህ . .

- ኢአማኝ ኤቲስት ሆኖ ሃይማኖተኝነትን ማድነቅ አስደናቂ አይደለም? !

- ‹‹ምናልባት›› አለና ርእሱን ለመቀየር ሞከረ ፡- የሕንድን ውበት አልጠገብክምና ነው ወደ ሕንድ መጓዝ የምትፈልገው?

- አልገባኝም።

- የካትሪና ውበት አላረካህምና ነው በሌሎች የሕንድ ቆነጃጅት ለመደሰትና ከነሱ ጋር ለመጫወት የምትሻው? !

- ይህን ወዲያ በለው . . እኔ የምሳፈረው የተለያዩ ሃይማኖቶችንና ርእዮቶችን ለማወቅና የሥራ ውል ለመፈራረም ነው። በል ደህና ሁን፣ቀጠሮአችን ከሁለት ሳምት በኋላ ነው።

- ተስማምተናል። ገና ስትቀርባቸው ሁሉንም ሃይማኖቶች ችላ እንደምትል እርግጠኛ ነኝ። መልካም ሕንዳዊ ጥቅምና መደሰቻ እንዲገጥምህ እመኝልሃለሁ።

የክህደት ጥርጣሬ . . (5)

ካትሪና ጆርጅ መምጣቱን ስታውቅ በፍጥነት ተነስታ በሩ ዘንድ ተቀበለችው . . የሞቀ ሰላምታዋን በቀዘቀዘ መንፈስና ደስተኛ አለመሆኑን በሚያሳብቅ ቅላጼ መለሰላት . . ራሷን ለማዋደድም ሞከረች . .

- ከባድ ሃሳብ ላይ ነው የጣልከኝ፣ትናንት ዬት ነበርክ፣እቤት አላደርክም? !

- ትናንት በጣም አምሽተሸ እንጂ አልመጣሽም፤እቤት ወይም ውጭ ማደሬ ላንቺ ምንሽም አይደለም።

- አዎ፣ትናንት ቤተከርስቲያን ውስጥ በጣም አምሽተን ነበር፣በጣም አስፈላጊና ድንቅ የሆነ የቤተክርስቲያን የምሽት ድግስ ነበር።

- እርሱ የተሳተፈበት በመሆኑ ድንቅ ነበር።

- ማንን ማለትህ ነው?

- በምሽት ፕሮግራሙ ላይ ካንቺ ጋር የነበረው ማነው?

- ብዙ ናቸው፣በጣም ብዙ።

- ከተገኙት መካከል እኔ የማውቀው ማን አለ?

- ጆርጅ፣እየመረመርከኝ ነው? ለማንኛውም መልስ ልስጥህና ቄስ ሞሪስ፣ሳሊ፣ፒተር፣ሄላሪ፣ሲምፕሰን፣ እና . .

- መልከ መልካም ሎጋው ቶምስ?

- አዎ . . ሐኪም ቶምም ተገኝቶ ነበር። በጌታ ያለውን እምነትና እርግጠኝነት ለማጠናከር ነው የመጣው፣የቅዳሴ ሥርዓቱን በሙሉ ከኛ ጋር ተሳትፏል !

- እጅግ በጣም ጥሩ ነው . . ሃይማኖት የለሽ ኤቲስት የመጣው በቅዳሴ ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው ወይስ በመጠጥና በምሽት ጭፈራ ድግሱ ለመዝናናት? !

- እኔን እያዋረድከኝ ነው፣ቤተክርስቲያኒቱንም እያዋረድካት ነው፣ምን ለማለት ነው የፈለከው? እርሱ በምሽት ድግሱ ላይ ማለቴ በቅዳሴ ሥርዓቱ ላይ መሳተፉን ማን ነገረህ?

- የለም፣አንቺን አላዋረድኩም፣ቤተክርስቲያኑንም አላዋረድኩም። እርሱ ራሱ ነው ከማራኪዋ ካትሪና ጋር በማምሸቱ መደሰቱን የነገረኝ። እምነቱን መጨመርና ማጠናከር የሚፈልገው ቶም ነው በጉዞዬ በሕንድ ሴቶች ውበት እንድደሰትና ከነሱ ጋር እንድዝናና በመምከር የገፋፋኝ !

- እንደዚህ አለ !

- አዎ፣ምኑ ነው የሚያስደንቀው?

- ምንም ! ግን . .

- በጣም ደክሞኛልና መተኛት እፈልጋለሁ፣ፍቀጅልኝና ወደ መኝታ ክፍል እሄዳለሁ።

ጧት አማልዶ ወደ ሥራ ሲሄድ ካኽ እሱን በመጠባበቅ ላይ ነበር . .

- የምሥራች ንገረኘ እስኪ፣ጆርጅ የመጨረሻ ውሳኔህ ምንድነው?

- በመካከላችን ያሉትን የሥራ ስምምነቶች ካጠናቀቅን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ወደ ሕንድ እጓዛለሁ፣በራሴ በኩል ያለውን አመቻችቻለሁ።

- በጣም ግሩም፣የሚፈለጉ ዝርዝር ውሎችንና የሀገሩን ሰዎች ዝርዝር የስነ ልቦና ሁኔታ ለማወቅ ረዣዥም የሁለትዮሽ ስብሰባዎች ያስፈልጉናል።

- ካንድ ሰዓት በኋላ ለሦስት ሰዓት የሚቆይ ስብሰባ ለመጀመር አንተ ዘንድ እሆናለሁ፣ነገም እንደዚሁ ይኖረናል።

ከሕንድ ኩባንያዎች ጋር የሚፈረመው ስምምነት ማስገኘት በሚችለው የገንዘብ ጥቅም ዝርዝር ላይ፣ ካኽ ከፍተኛ ጉጉት አድሮበታል። ለዚህም ነው ከጆርጅ ጋር የሥራ ግንኙነት የሚያደርጉ ግለሰቦችን ዝርዝር የስነ ልቦና ሁኔታ ለጆርጅ ግልጽ ለማድረግ የፈለገው፡፡ ስለያንዳንዱ ግለሰብ የሚያውቀውን ትልቅ ትንሹን ሳይል ሁሉንም ዝርዝሮ ነበር ያስረዳው።

- የምትፈልገው ተጨማሪ ማብራሪያ አለህ?

- የለም፣ነገሮች ከሞላ ጎደል በሚገባ የተብራሩ ይመስለኛል። ለሁለቱም ወገኖች ቁሳዊ፣ ሕሊናዊና መርሃዊ ጥቅሞችን በሚያስገኙ መሰረቶች ላይ የሚፈጸሙ የውል ስምምነቶች ከረዥም ጊዜ አኳያ ይበልጥ ጠንካራና ይበልጥ የጠበቁ ናቸው የሚል እምነት ቢኖረኝም ሁሉም ነገር ግልጽ ነው።

- ማትረፍ ማለት በአነስተኛ ክፍያ የተቻለህን ያህል ከፍተኛ ጥቅም ማግኘት ነው . . በመቀጠል ፈግግ ብሎ ፡- የገንዘብ ጥቅም ለኔ ይሁን፣መርሃዊና መንፈሳዊ ጥቅም ደግሞ ላንተ ይሁን።

- ተስማምተናል ! !

- የደበቅኩትን ድንገተኛ የምስራች ሳልነግርህ ረስቼ።

- የምን ምስራች? !

- ጥያቄዎችን የሚያስረሳህ፣ሐኪምህንም ጭምር የሚያስረሳህ የምነግርህ ድንገተኛ የምስራች አለኝ ብየህ አልነበር ?

- ምን ይሆን?

- የሕንድን መደሰቻ ቀምሰህ እየው።

- የትኛውን መደሰቻ ማለትህ ነው?

- አንዳንዴ በጣም ደደብ ትሆናለህ፣የሕንድ ሴቶችን ውበት ቅመስ፣ተደሰት እያልኩህ ነው፣ ለሁሉም ጥያቄዎችህ ምላሽ ይሰጡሃል . . የነገርኩህ የሠራተኛ አስቀጣሪ ኩባንያው ዳይሬክተር ማክል ሁሉንም ነገር ያመቻችልሃል . . የሹፈት ሳቅ ለቀቀና ፡- ማይክል በጣም ሃይማኖተኛ የሆነ ክርስቲያን ነው ብየህ የለም?

 

ለመሆኑ ቶምና ካኽን ያመሳሰላቸው ምክንያት ምን ይሆን

! የሥጋዊነትና የኢአማኝነት ባህሪያቸው ይሆን? ወይስ ሁለቱም ከእውነታ የሚሸሹ የመሆናቸው ሁኔታ? . . ጆርጅ ራሱን ጠየቀ። ይህች እውነታ ምንኛ አደናጋሪ ነች!
! የፈለገውንም ቢሆን ወደርሷ ለመድረስ ቆርጫለሁ . . እያለ ከራሱ ጋር አወራ።

- ጉዞዬ ረቡዕ ጧት ነው፣ከኔ የምትፈልገው ሌላ ነገር አለ?

- መልካም ጉዞ፣መርሃዊ ሳይሆን፣ቁሳዊ የገንዘብ ጥቅም የሚያስገኙ ስምምነቶች፣አስደሳችና ማራኪ ሴቶች፣ . . እመኝልሃለሁ፤ደህና ሁን።

ጆርጅ፣ስግብግብነትና ጭልጥ ያለ ቁሳዊ አመለካከትን በአለቃው በካኽ ላይ ብዙ ጊዜ አስተውሏል። በተለይም የሕንድ ጉዞውን አስመልክተው ባደረጓቸው የመጨረሸዎቹ ስብሰባዎች ላይ። በሕንድ ስላሉት የሶፍትዌር መሸጫዎች እንዲያውቅና ርካሽ የሆነ የቴክኒክ ባለሙያ የሰው ኃይል በማስገኘት ላይ እንዲያተኩር ሲያሳስበው ነበር። መቼም ሕንድ በሕዝብ ቁጥሯ ብዛት ትልቅ ገበያ መሆኗን፣የተትረፈረፈ ርካሽ የሰው ኃይል የዚህ ግዙፍ ገበያ ዓይነተኛ መለያ መሆኑን ካኽ ሲደሰኩርለት ጆርጅ በጸጥታ ያዳምጠው ነበር። ከገንዘብና ከወሲብ ውጭ ከሕይወት ውስጥ ለምንም ግድ ባልነበራቸውና በሁለቱ ዙሪያ ብቻ በሚሽከረከሩ የካኽ ቃላት ላይ ሀሳብ ለመስጠት ግን ፍላጎት አልነበረውም።
የሕንዱ ዓለም አቀፍ የሠራተኛ አስቀጣሪ ኩባንያ ዳይሬክተር ማይክል፣አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ አቀባበል እንደሚያደርግለት ነግሮት፣ጥብቅ ሃይማኖተኛ መሆኑን አስጠነቀቀውና በመቀጠል፡-

- በውሉ የመለወጥና የመቀየር እድል እስከሰጠን ድረስ . . የፈለገውን ቢሆን ጉዳያችን አይደለም። የፌዝ ሳቅ እየሳቀ በመቀጠል ፡- ብልጥ ሃይማኖተኝነት እንዲህ ነው፣በኔ በኩል ይበልጥ አትራፊ፣ይበልጥ ተጠቃሚና አስደሳች የሚያደርገኝን ሰው ለማምለክና ለማገልገል ዝግጁ ነኝ !

ጨርሰው ለመውጣት ሲነሱ ካኽ ጆርጅን ጠቀሰውና የመጨረሻ ማሳሰቢያው፡-
በሕንዳዊ ውበት መደሰት እንዳያመልጠውና አልፎ አልፎ ብቻ የሚገኝ ውበት መሆኑን ነገረው። ጆርጅ በቸልተኝነት ስሜት፡-

- የትኛውን ውበት ማለትህ ነው?

- የሕንዳውያቱ ውበት ነዋ ! የምሥራቆቹ ጭፈራ ነዋ !

ጆርጅ በማናናቅ ስሜት ከንፈሩን መጠጠና ተሰናብቶት ወዲያውኑ ሄደ።
ጅርጅ እቤቱ ሲደርስ በጣም ደካክሞት ነበር። ካትሪና አለወትሯ ስትጠብቀው አገኛት። ዛሬ እንደ ልማዷ አላመሸችም . . በፈገግታና በናፍቆት ስሜት ተቀበለችው . .

- የኔ ፍቅር በጣም ዘገየህ፤ለሁለት ሰዓታት ስጠብቅህ ነበር? !

- ስለ ጉዞው ጉዳይ ከካኽ ጋር ረዣዥም ስብሰባዎች ነበሩኝ።

- ልክ ነው ! ዘንግቸው ነበር። ትናንት ከሐኪም ቶም ጋር የነበረህ ቀጠሮ እንዴት እንደ ነበረ አልነገርከኝም?

- የአስተናጋጁን መልሶች ነው የሰጠሁት ! እኔን አሳምኖኛል፣ ለሱም እንደዚሁ አሳማኝ ሆነዋል።

- በጣም ጥሩ . . ዋናው ነገር በመንገገዱ እየተጓዛችሁ መሆኑ ነው።

- ተጨማሪ አዳዲስ ጥቄዎችም ሰጥቶኛል !

- አዳዲሶቹ ጥያቄዎች ምንድነው?

- መልሱን የምናገኝበትን የተሻለ ሃይማኖት እንድለይና ምላሽ የሚሰጠን ፈጣሪ አምላክ የትኛው እንደሆነ እንድነግረው ነው የጠየቀኝ።

- መልሱ በጣም ግልጽ ነው። አብ፣ወልድና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፣ሦስትም አንድ ናቸው፤ሰዎችን የፈጠሩት እነሱ ናቸው። ከዚህ ውጭ የሚያምን ሰው ከሃዲ ኢአማኝ ነው . . በመቀጠልም ልቅ ሳቅ መሳቅ ጀመረች።

- ወደ ሕንድ ስሄድ ሃይማኖቶችን እንድመረምርና ከንጽጽሮሽ በኋላ በመጀመሪያ ከመለኮታዊ ሃይማኖቶችና ከሰው ሰራሽ ምድራዊ ሃይማኖቶች የትኞቹ እንደሚሻሉ እንድወስንም መክሮኛል።

- ተጓዝ ሕንድ ውስጥ አስበህ የማታውቃቸውን ድንቃድንቅ ነገሮች ታያለህ። በእርግጥ የአግራሞት አገር ነች። የነገርኩህ ሁሉ እውነት መሆኑን እርግጠኛ ሆነህ ነው የምትመለሰው።

- በሕንዳዊያት ቆነጃጅት እንድደሰት ከቶም የተሰጠኝን ምክርሳ? !

ካትሪና መረበሿን ለመሸሸግ ሞከረች . .

- የኔ ፍቅር በዚህማ ቃሉን አትፈጽም።

- ትጠረጥሪኛለሽ? !

ካትሪና ፈገግ አለች፤ ርእሱን የማስቀየሻ አጋጣሚ አገኘች . . ራሷን ቀና አድርጋም ወደ ጆርጅ ተመለከተች . .

- የዘር ግንዴ ከሕንድ ነው፣ይሁን እንጂ ከሃያ ዓመታት ወዲህ ሕንድን አላየሁም። ከሕንድ ስጦታ ልታመጣልኝ ትችላለህ?

- በጣም ደስ እያለኝ . . ምን ላምጣልሽ?

- የሕንድ የእጅ ሥራ የሆነ መስቀል እፈልጋለሁ።

- ምርጥ የሆነ የሕንድ መስቀል ይመጣልሻል፣ ግን ከቀላል ግዴታ ጋር ነው።

- በል አቅርብ።

- ዛሬ ለየት ያለ ሌሊት እንዲኖረን እፈልጋለሁ . . በይ ወደ መኝታችን ክፍላችን እንሂድ።