የእውነተኛው ሃይማኖት መገለጫ ባሕርያት

የእውነተኛው ሃይማኖት መገለጫ ባሕርያት

በተስማሙበት መሰረት ራሽድ ወዳጆቹን ሉቨር ቤተመዘክር መግቢያ በር ላይ ተቀበላቸው፤እንዲህ በማለትም ቤተመዘክሩን ለመጎብኘት ጠየቃቸው፦

እዚህ እንድንገናኝ የመረጥኩት፣ዛሬ የምንወያይበትን ርእስ ከመጀመራችን በፊት የሰው ልጆችን ታሪክ አንዱን ጎን ወደኋላ መለስ ብለን እንመልከት ዘንድ ቤተመዝክሩን እንድንጎበኝ ጥሪ ላደርግላችሁ አስቤ ነው . . በሀሳቡ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ? ይቅር ካላችሁ መሰረዝ እንችላለን . .

ማይክል፦ አንተ ራሽድ፣በጣም ትገርማለህ . . እዚህ ከተገኝን በኋ ነው አስተያየታችንን የምትጠይቀው? ሳንመጣ ልታማክረን ይገባ ነበር . . ለማንኛውም በኔ በኩል ችግር የለውም . . ራጂቭ ምን ትላለህ?

ራጂቭ፦ በኔ በኩልም ችግር የለውም፤ይሁን እንጂ በተስማማነው መሰረት ውይታችንን ማስኬድ ከፈለግን ጉብኝቱን አጭርና ፈጣን ማድረግ ይኖርብናል። የሉቨር ቤተመዘክር በጣም ትልቅ በመሆኑ ማዳረሱ ጊዜና ጉልበታችንን የሚሻማ ነው።

ራሽድ፦ ለፈጸምኩት ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሀሳቤ ያልጠበቃችሁ ዱብ እዳ አድርጌ ላስደስታችሁ ነበር፤በአካሄዴ ተሳስቻለሁ።

ማይክል፦ ምንም አይደለም፣ቀላል ነው። አሁን ቀልጠፍ ማለት አለብን። የቤተመዘክሩ አዳራሾች ጠቅላላ ስፋት ወደ13 ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ቅርሶች አሉበት።

ራሽድ፦ የጉብኝቴ ዓላማ የሉቨርን ቤተመዘክር ማየት ሳይሆን አሁን በምንወያይበት ርእስ ላይ አንዳንድ ሕያው መረጃዎችን ከዚህ ለመሰነቅ ብቻ ነው . . ትኩረታችን በጥንታዊ ሥልጣኔዎች ቅርሶች ላይ ያነጣጠረ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። እነዚህ የሚገኙት በቤተመዘክሩ ምድርቤትና በአንደኘው ፎቅ ላይ ነው . .

ከሁለት ሰዓት ያህል ቆይታ በኋላ ሦስቱ ወዳጆች ቤተመዘክሩን ለቀው ሲወጡ ድካም ብጤ ከፊታቸው ይነበብ ነበር።

ራሽድ፦ አሁን ማረፍና ምሳ መብላት እንችላለን። ከቤተመዘከልሩ ቅርብ ርቀት ላይ አንድ ሬስቶራንት መኖሩን ከኢንተርኔት ላይ ተመልክቻለሁና ወደዚያ እናመራለን።

ወደዚያ በመጓዝ ላይ እያሉ ራሽድ ንግግሩን ቀጠለ፦

የተመለክታናቸውና ከተለያዩ ሥልጣኔዎች የተገኙ አብዛኞቹ ቅርሶች፣በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከሃይማኖት ጋር ተያያዥነት አላቸው። ታድያ ይህ ታሪኩ ወይም ቦታው ምንም ይሁን ምን፣ሃይማኖት በሰው ልጆች ዘንድ የሚይዘውን ስፍራ አመላካች አይደለምን?!

ራጂቭ፦ የተናገርከው ከሞላ ጎደል በአንትሮፖሎጂ ሊቃውንት ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ነው። የሰውን ልጅ አመጣጥ ታሪክና ቅርሶቹን በማጥናት ደረስንበት እንደሚሉት ፋብሪካና እንዱስትሪ የሌላቸው ስልጣኔዎች፣ሕንጻና ግንባታ የሌላቸው ሥልጣኔዎች፣ሳይንስና ፍልስፍና የሌለባቸው ሥልጣኔዎች ሊኖሩ ይችላሉ . . ይሁን እንጂ የአምልኮ ቦታ የሌላቸው ሥልጣኔዎችን አላገኙም።

ማይክል፦ እውነቱን ለመናገር ማንም አርቆ አስተዋይ ሰው ሃይማኖት መጥፎ ነገር አይደለም ይላል። ለሰው ልጆች ሕልውና ከመሰረታዊ የሥልጣኔ መገንቢያ አሃዶች አንዱ ነው። እዚህ ላይ ችግሩ የሚመጣው ግን ሁሉም የሃይማኖት ባለቤቶች እነርሱ የሚከተሉትን ሃይማኖት ብቻ እውነተኛው ሃይማኖት አድርገው የሚያምኑ በመሆኑ ነው። ሁሉም ወደየራሳቸው ሃይማኖት ጥሪ ያደርጋሉ። ሰዎች ሁሉ እምነታቸውን እንዲቀበሉ፣የሃይማኖታቸውን መሪ እንዲከቱሉና እንዲያከብሩት ያስተምራሉ። ሁሉም እውነተኛው ሃይማኖት የኔ ሃይማኖት ብቻ ነው ብሎ ሲያምን ሰው ግራ ይጋባል። እናም እውነተኛው ሃይማኖት ይሁዳዊነት ነውን? ክርስትና ነውን? ቡድሂዝም ነውን? ወይም እስላም ነውን? . . . እውነተኛው የትኛው እንደሆነ ማወቅ የሚቻለውስ እንዴት ነው?! ወይስ ፍላጎታቸውን እስካሟላ ድረስ አማኞች የሚከተሉት ሃይማኖት ሁሉ ትክክለኛ መንገድ ነው እንበል?! . . በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤አይመስላችሁም?!

ራሽድ፦ ልክ ነው፣ግራ ያጋባል። ይሁን እንጂ ጥቂት በማስተዋልና በማመዛዘን ብቻ ከዚህ ግራ መጋባት መውጣት እንችላለን . . አሁን እኛ በጣም እየራበን ለሰው ልጅ ወይም ለእንስሳት ተስማሚ ይሁን አይሁን ሳናውቅ ያገኘነውን ምግብ ሁሉ መብላትንና ሆዳችንን ማስታገስን አንፈልግም፤አንቀበልምም። ረሃቡን ለማስታገስ ብለን ማንኛውንም ነገር አንበላም . . ሥጋዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት አቋማችን ይህ ከሆነ፣መንፈሳዊ ሕሊናዊ ፍላጎታችንን ለማርካት የምንወስደው ጥንቃቄና አቋም ምን መሆን እንዳለበት ሳይታለም የተፈታ ነው . . እናም ተገቢውንና ተስማሚውን ቀለብ መምረጥ ግድ ይለናል . .

እውነት ብዙ ሊሆን የማይችል አንድና አንድ ብቻ በመሆኑ፣ሁሉም በእውነተኛው መንገድ ላይ ናቸው ብሎ ማሰብ ፈጽሞ ሊሆን የሚችል አይደለም። እነዚህ ሁሉ ሃይማኖቶች፣እምነቶችና ቡድኖች ከአላህ ዘንድ የመጡና ሁሉም ትክክለኞች ሊሆኑ አይችሉም። እውነት አንድ ከሆነና ሃይማኖቶች ደግሞ ብዙ ከሆኑ፣እውነተኛው የትኛው ነው? የሚለው ጥያቄ እንደተደቀነ ይቆያል። ስለዚህም እውነተኛውን ሃይማኖት ከሐሰተኛው ሃይማኖት ለይተን የምናውቅባቸውና የምናበጥርባቸው መስፈርቶች የግድ ያስፈልጉናል። አንድ ሃይማኖት መስፈርቶቹን ሙሉ በሙሉ አሟልቶ ከተገኘ እውነተኛው ሃይማኖት እርሱ መሆኑን አወቅን ማለት ነው። መስፈርቶቹን በሙሉም ሆነ በከፊል ሳያሟላ የቀረ ማንኛውም ሃይማኖት ደግሞ ሐሰተኛ ሃይማኖት መሆኑን አወቅን ማለት ነው።

ራጂቭ፦ አሁን በተናገርከው ይዘት ውስጥ የመጀመሪያውን መስፈርት ማለት ሃይማኖቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ መሆን እንዳለበት በተዘዋዋሪ ገልጸሃል። እናም ሃይማኖቱ የግድ መለኮታዊ መሆን ይኖርበታል ማለት ነው? በዓለም ላይ ቡድሂዝምን፣ህንዱይዝምን፣ኮንፊሽዋንዝምንና የመሳሰሉ ሌሎች መለኮታዊ ያልሆኑ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች የሚከተሏቸው ሃይማኖቶች ይገኛሉ . .

ራሽድ፦ የማንኛውም ሃይማኖት መሰረት አምላክን ወይም አማልክትን ማምለክ በመሆኑ፣ይህ በጣም ግልጽ ነው። ዩኒቨርስንና ሰውን የፈጠረው አምላክ አንድ ብቻ መሆኑን፣በምድር ያለውን ሁሉ ለሰው ልጆች የገራው፣ሲሳይና ጸጋዎቹን የቸራቸው መሆኑን በእውነት የምናረጋግጥ ከሆን፣እውነተኛው አምልኮ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ማረጋገጥ ግድ ይለናል። ምንም ተቀናቃኝና ተጋሪ ሸሪክ ሳይኖረው እርሱ ብቻ ሊመለክ ይገባል። ፈጣሪና ሲሳይ ሰጭ እርሱ ብቻ ሆኖ እያለ፣ከርሱ በስተቀር ሌላ እንዴት ሊመሰገንና ለመለክ ይችላል?! በተጨማሪም እውነተኛው ሃይማኖት አንድ ፈጣሪ አምላክን ብቻ ለማምለክ የግድ ጥሪ ማድረግ ይኖርበታል። የእውነተኛውን አምላክ ባሕርያት ሊያረጋግጥለትና ከርሱ የተላኩ መልእክተኞችን ማላቅና ማክበርም ይኖርበታል።

ባለፈው ውይይታችን የእውነተኛው አምላክ ባሕርያትና የሰው ልጆች ፍላጎት፣ሰዎችን የሚመራና ሕይወታቸውን የሚያደራጅ፣ተድላና ደስታን እውን የሚያደርግላቸው መመሪያ እንዲኖር የሚጠይቁ መሆናቸውን ተስማምተንበታል። ይህ መመሪያም ስለፈጠራቸው ፍጡራን ከማንም በላይ የሚያውቀው ፈጣሪ የሚወደው ሃይማኖት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።

በተጨማሪም ሰዎች በሠሩት ሥራ የሚጠየቁበትና ሁሉም ዋጋውን የሚያገኝበት የፍርድ ቀን መኖር ግድ መሆኑንም ተስማምተንበታል። በትንሣኤው ቀን ፍጡራንን ሁሉ የሚመረምረውና የሚፈርደው እርሱ ብቻ ከሆነ ዘንዳ፣ፍርድና ምርመራቸው እርሱ ራሱ ባስተላለፈው ሃይማኖት መሠረት መሆን ያለበት መሆኑም የግድ ነው። በዚህ መሰረትም አንድ ሰው ይዞ መጥቶ ከራሱ ጋር የሚያስተሳስረው ማንኛውም ሃይማኖት የግድ ውድቅና ተቀባይነት የሌለው ሃይማኖት ነው።

እዚህ ላይ መጠቆም የምፈልገው ነጥብ፣አብዛኞቹ የሃይማኖቶች ተከታዮች የእምነታቸው ማስረጃ ምን እንደሆነ ሲጠየቁ፣የሚሰጡት መልስ አባቶቻችን ይህን ሃይማኖት ሲከተሉና በዚህ መንገድ ሲጓዙ ስላገኘናቸው ነው፣የሚል መሆኑን ነው። በማስከተልም መሰረት የሌላቸውን ትረካዎችና ንግርቶች ይጠቃቅሳሉ። ማን እንደተናገራቸውም ሆነ ማን እንደ ጻፋቸው፣በየትኛው ቋንቋ መጀመሪያ እንደተጻፉም ሆነ፣በየትኛው አገር መጀመሪያ እንደተገኙ በማይታወቁ መጽሐፎች ላይም ይመረኮዛሉ። ዋቢ መጣቀሻ አድርገው የሚይዟቸው እነዚህ አንድ ላይ የተሰባሰቡ የተለያዩ ቅይጦች እንጂ ሌላ ሳይሆኑ ከበሬታ ተሰጥቷቸው አንዳች ሳይንሳዊ ብጠራ ሳይደረግባቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወራረሱ የመጡ ናቸው። ይህ በጣም ልንጠነቀቀው የሚገባን ነገር ነው። ከዚህ ስንነሳም፣ከእውነተኛው ሃይማኖት አበይት መገለጫ ባሕርያት መካከል አንዱ ከምንጩ ጋር ያለው ትስስር የጸና እና የተረጋገጠ መሆንና ከአላህ ተልኮ ሃይማኖቱን የሚያደርሰው መልክተኛ (ነብይ) ማስረጃዎች ትክክለኛነት ነው።

ራጂቭ፦ መልካም፣እንግዲያውስ መነሳት ያለብን ከተስማማንባቸው መሰረቶች ነው። የማስረጃዎች አቀራረብን፣አእምሮን፣ሳይንስንና ተፈጥሯዊ ግንዛቤን መጠቀምን በተመለከተም ሆነ፤ቀደም ሲል የተስማማንባቸውን እውነታዎች ማለትም የፈጣሪ አምላክ መኖርንና የእውነተኛው አምላክ ባሕርያትን፣እንዲሁም የሰው ልጆች ለምን የግድ መለኮታዊ መመሪያ እንደሚያስፈልጋቸው መተንተንን በተመለከተ ከዚያው መንደርደር አለብን ማለቴ ነው።

ማይክል፦ በዚህ ላይ ከተስማማን፣ቀጣይ ነጥቦች ሃይማኖት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላለፈ መሆን፣እርሱ ብቻ እንጅ ማንም የማይመለክ መሆን፣ሃይማኖት ሳይንስን ማጉላት እንጂ የማይጻረረው መሆንና ከሚዘናዊ አስተዋይ አእምሮ ጋርም የሚጣጣም መሆን ናቸው። እውነተኛው ሃይማኖት የእግዚአብሔር ሃይማኖት ነው፣አስተዋይ ሚዘናዊ አእምሮም የአላህ ፍጡር ነው ብለን ካልን፣ከእግዚአብሔር የተላለፈ ሃይማኖት ከርሱ ፍጡር (አእምሮ) ጋር ይጻረራል ማለት የማይታሰብ ነው።

ራሽድ፦ በዚህ እስማማለሁ፤ግና ለሁለት ጉዳዮች አጽንኦት ከመስጠት ጋር ነው፦

አንደኛው፦ ቀደም ሲል የተቀበልነውና አእምሮ ሊሆን አይችልም ብሎ በሚቆርጠው፣ወይም ሊሆን ይችላል ብሎ በሚያረጋግጠው ነገርና አእምሮ ጭራሹኑ ለማሰብ በሚሳነው ነገር መካከል ያለው ልዩነት ነው። በሃይማኖት ማእቀፍ ውስጥ የሰው ልጅ አእምሮ ትክክለኛ ምንነቱንና አኳኋኑን አስቦ ከግንዛቤው ስር ማዋል የሚቸግር ክፍል ሲኖር፣ እርሱም ከሕዋሳዊ ግንዛቤ በላይ የሆነው (ጓይብ) ነው . . ለምሳሌ ያህል የመላእክትና የሰይጣናት መኖር፣የሰው ልጅ ወደ ሆነው መልክተኛ የአላህ መልእክት እንዴት እንደሚተላለፍ፣የትንሳኤው ቀን ዝርዝር ጉዳዮች . . እነዚህ ነገሮች ግን አእምሮ በቁርጠኝነት ሊሆን ወይም ሊከሰት አይችልም ብሎ ከሚያስተባብለው ነገር ይለያሉ . .

ለምሳሌ ያህል፣ከአንድ መቶ ዓመት በፊት የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ ሊያርፍ ቀርቶ መንኩራኩር እንኳ ሊልክ፣በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘውን ሌላ ሰው መስማት ወይም ማየት ይችላል ብሎ ማሰብ ለአእምሮ የሚከብድ ነገር ነበር። ይሁን እንጂ ያን ለማመን የሚያስቸግረውን ነገር ፈጽሞ ሊሆን አይችልም ብሎ የመደምደም ሀሳብ አእምሮ ውስጥ የለም። በተጻራሪው ግን ሰው ራሱ በአካሉ በአንድ ጊዜ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ይገኛል፣ወይም 1+1+1=1 ካልን አእምሮ ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም ብሎ ይደመድማል።

ሁለተኛው፦ በላይኛው ነጥብ ላይ በመመርኮዝ፣አንዳንድ የሃይማኖት ዝርዝር ጉዳዮች ከአእምሯችን ጋር ባይጋጩም አእምሯዊ ምክንያታዊ ትንተናቸው ለኛ ግልጽ ላይሆን ይችላል። እዚህ ላይ እምነታችንን በጤናማ የአስረጅነት መሰረት ላይ ያቆምን እስከሆን ድረስ፣አምነን መቀበል ግዴታ ነው። ለምሳሌ አንድን ግለሰብ በአእምሮህ 100% እምነት የሚጣልበት መሆኑን ከተገነዘብክና ለተአማኒነቱ ቅንጣት ጥርጣሬ የማይኖርህ ከሆነ፣ይህ ግለሰብ አንተ በርሱ ላይ ያለህን መተማመን ለመፈተን ፈልጎ ‹‹በነዚህ ባዶ ወረቀቶች ላይ ፈርምልኝ›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርብልህ፣የወረቀቱን ምንነት ሳትጠይቀው ትፈርማለህ። በርሱ ላይ ያለህ እምነት የተሟላ ካልሆነ ግን ወረቀቱ ምን እንደሆነ ትጠይቀዋለህ። በተመሳሳይ መልኩ ‹‹ኢማን ወይም ዐቂዳ›› በአእምሮና በእሳቤ አማካይነት በአላህ ﷻ ላይ እምነት መጣልና በርሱ መተማመን ነው፤‹‹የሃይማኖት ዝርዝር ጉዳዮች ደግሞ በአላህ ላይ ስላለህ አመኔታና መተማመንህ የምታቀርበው ማስረጃ ነው።

ማይክል፦ ስለዚህም ከእውነተኛው ሃይማኖት መገለጫ ባሕርያት መካከል፣እርስ በርሱ የሚጋጭና የሚጻረር አለመሆን፣አንድ ነገር እያዘዘ በሌላ ትእዛዝ ደግሞ የማይከለክል፣አንድን ነገር የተፈቀደ አድርጎ ተመሳሳይ የሆነ ሌላ ነገር ደግሞ ያለ ምክንያት እርም አድርጎ የማይከለክል፣አንድን ነገር ለአንድ ቡድን የተከለከለ ወይም የተፈቀደ አድርጎ ለሌላው ቡድን ደግሞ የተከለከለ የማያደርግ መሆን ይገኙበታል ማለት ነው።

ራጂቭ፦ ይህ ሃይማኖት ፈጣሪያቸው ከነርሱ የሚፈልገውን አስመልክቶ ለሰው ልጆች እንደ መመሪያ ነው ብለን ካልን፣ሃይማኖቱ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመለክ፣ከሰው ልጅ ምን እንደሚፈልግና ሰዎች ሊከተሉት የሚገባው ሥርዓት የቱ እንደሆነ የግድ መንገዱን ማሳየትና ማመላከት ይኖርበታል። ለሰው ልጅ ታላላቆቹ የሕይወት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ በመስጠት፣ከየት እንደ መጣና መጨረሻው ወዴት እንደሆነ መንገር መቻል ይጠበቅበታል።

ማይክል፦ ሃይማኖቱ ወደ ሰናይ ተግባራትና መልካም ስነምግባራት ጥሪ ማድረግ፣ከመጥፎና እኩይ ድርጊቶች መከልከል፣በደሉ መብቶችን በመጋፋትም ይሁን በምዝበራ ወይም ታላላቆች ታናናሾችን በማጥመም፣ፍጡራን እርስ በርሳቸውም ሆነ ራሳቸውን እንዳይበድሉ ርኅሩህ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።

ራሽድ፦ የዘነጋነው አንድ አስፈላጊ መስፈርት አለ፤ያም ሃይማኖቱ እነዚህን መገለጫ ባሕርያት በሙሉ አንድ ላይ አካቶ መያዝና አንድም ባሕሪ የማይጎድል መሆን ነው።

ማይክል፦ ራሽድ፣እባክህን ስለ ሃይማኖትህ ዘርዘር አድርገህ እንድትነግረን እፈልጋለሁ። ስለ ሃይማኖቱ ያለኝ መረጃ አነስተኛ መሆኑንና ከፊሉም የተዛባ መሆኑን አሁን ገና ተረድቻለሁ።

ማይክል፦ በቀጣዩ ግንኙነታችን ያንን ለማድረግ ቃል እገባልሃለሁ።