የመንፈስ ባዶነትን መምላት

የመንፈስ ባዶነትን መምላት

‹‹በግል ሕይወቴ አንድ ወቅት ላይ፣በጭንቀትና በውጥረት ብዙ ስሰቃይ ከቆየሁና የውስጤን ባዶነት ለመሙላት ከፍተኛ ዝግጁነት ከተሰማኝ በኋላ፣አላህ በወሰን የለሽ ዕውቀቱና በችሮታው ጸጋውን አድሎኝ ሙስሊም ሆንኩ። ከመስለሜ በፊት በሕይወቴ ውስጥ የፍቅርን ትርጉም የማውቅ አልነበርኩም። ቁርኣንን ባነበብኩ ጊዜ ግን የበዛ የእዝነት የርኅራሄና የመተሳሰብ ጎርፍ ሲያጥለቀልቀኝ ተሰማኝ። ልቤ ውስጥም የፍቅር ዘላለማዊነት ስሜት ሲሰርጽ ይሰማኝ ጀመር። ወደ እስላም የመራኝም ሊቃወሙት የማይቻለው የአላህ ፍቅር ነው።››


Tags: