አንዲት ሚስት . . በቂ ናት?!

አንዲት ሚስት . . በቂ ናት?!

ራሽድ በተስማሙበት የቀጠሮ ሰዓት የደረሰ ቢሆንም ማይክልን ግን አስቀድሞ ደርሶ ሲጠብቀው ነበር ያገኘው። አስቀድሞ መድረስ ብቻ ሳይሆን የሚጠጣ ነገር አዞለት ቀርቦ አገኘ . . ሰላምታ ተለዋውጠው መቀመጫውን ይዞ ተቀመጠ . .

ማይክል፦ ተመራጭ መጠጥህን ሻይ በሎሚ እንዲቀርብልህ አድርጌያለሁ . . ሁሌም የመጠጥ ምርጫህ እሱ ነው ብዬ ነው።

ራሽድ፦ በአክብሮት ተቀብያለሁ፤በእርግጥ ይህ ምርጫዬ ነው። ይሁን እንጂ የሁለተኛ ደረጃ ምርጫ እንኳ ቢሆን ለውጥና ቅያሬንም እወዳለሁ . . ይህ የሰው ልጅ አጠቃላይ ተፈጥሮ ይመስለኛል።

ማይክል፦ በዚህ ልስማማ እችላለሁ፤ይህን ተውውና ወደ ርእሳ ጉዳያችን እንግባ . . ይቅርታ ሌላ የሚጠጣ ነገር ልዘዝልህ'ንዴ?

ራሽድ፦ የለም፣የለም፣አመሰግናለሁ . . ለውይይቱ የጓጓህ ትመስላለህ!

ማይክል፦ እስከዚህም አይደለም፤ግን ባለፈው ውይይት እንደሆነው ዓይነት ለሌላ ርእስ ጊዜ እንዳይጠበን ስለሰጋሁ ብቻ ነው።

ራሽድ፦ እንግዲያውስ ቀጥል።

ማይክል፦ በናንተ ሕብረተሰብ ውስጥ በስፋት ሰፍኖ የሚገኘው የዚህ ተቃራኒ መሆኑን ባውቅም፣ባለፈው ውይይት እንዳልኩህ ሁሉ የመወያያ ርእሳችን እንዲሆን በምፈለገው ላይ ትስማማለህ የሚል እምነት አለኝ።

ራሽድ፦ በጣም ጥሩ፣እኔ ልዩነትን አልወድም፤ካንተ ጋር የምወያየውና የምከራከረው የጋራ ወደ ሆነ ማሳመኛ ለመድረስ ነው፤ወይም ቢያንስ ስለያንዳንዳችን አመለካከከት ትክክለኛ የሆነ ግንዛቤ ለመጨበጥ ነው . . እናም ማንሳት የፈለግከው ርእስ ምንድነው?

ማይክል፦ ጉዳዩ በአጭሩ ትዳራዊ ግንኙነት በሁለቱም ወገን አንድዮሽ ብቻ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ። ይበልጥ ግልጽ ለመሆን እስላም የሚፈቅደው ከአንድ ሚስት በላይ የማግባት የጋብቻ ሥርዓት ለሴት ልጅ በደልና ጭቆና ነው . . በዚህ ላይ ከኔ ጋር አትስማማም?!

ራሽድ፦ የትኛዋን ሴት ማለትህ ነው?

ማይክል (በመገረም)፦ ሴት ነዋ! ሚስት ናታ! . . በዚህ ግንኙነት ውስጥ ሌላ ሴት አለችን'ዴ?!

ራሽድ፦ ቀደም ሲል እንደተስማማነው ሁሉ ነገሮችን የመመርመር ትክክለኛው መንገድ፣ጉዳዮች ሁሉ በመልክ በመልካቸው በሚሰደሩበትና በሁሉም አቅጣጫና ገጽታ በሚታዩበት አጠቃላይ ማእቀፍ ውስጥ መሆን ይገባል።

ማይክል፦ መልካም፣ይህ በኛ ርእስ ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?

ራሽድ፦ ተጽእኖው ይህን ጉዳይ ስንመረምር የሴት ልጅ ጥቅሞችን ሴቶችን በሞላ በሚያጠቃልል፣የመላውን ሕብረተሰብ ጥቅሞችና ከዚያም አልፎ የወንዱን ጥቅምና በርሱና በሴትዋ መካከል ያሉትን ልዩነቶች ግምት ውስጥ በሚያስገባ መልኩ መሆን ይገባል . .

ማይክል (በማቋረጥ)፦ ይኸውልሃ እናንተ ዘንድ በሴቶች ላይ ይደርሳል ወደምንለው ግፍና ጭቆና መንስኤ ደረስን! በወንድና በሴቶች መካከል ያለው አድልዖ! . . የምትሏቸው እነዚህ ልዩነቶች ተባዕታዊው ምሥራቃዊ ሕብረተሰብ ሴትዋን መገልገያና መደሰቻው ለማድረግ ያኖራቸው እሴቶች እንጂ ሌላ አይደሉም . . እንዴት ያሉ ልየነቶች ናቸው በል?! ከአንድ ባል በላይ ማግባትስ ለምን የሴትዋም መብት ጭምር አይሆንም?! ይህ የዚያ ሕብረተሰብ ወንዶች የሥጋዊ ፍላጎቶች ተገዥ መሆናቸውን አያረጋግጥምን?!

ራሽድ፦ ረጋ በል፣ወዳጄ ተረጋጋ . . በውይይት ላይ መጠቀም የተከለከለውን የጥያቄዎች ተስፈንጣሪ ቦንብ ነው የተኮስክብኝ። በአንዴ ልንከላከለው አንችልም . . ሁሉንም አንድ በአንድ እንነጋገርበታለን፤ግና ፈንጂውን እናክሽፈውና ከከነከነህ ነጥብ እንጀምር። እናም ወንድና ሴትን የሚለያዩዋቸው ነጥቦች መኖራቸውን አታምንም?

ማይክል፦ ምን ዓይነት ልዩነቶች?

ራሽድ፦ በቅድሚያ . . ስነሕይወታዊ ልዩነቶች፣በወንድና በሴት አካላዊ ተፈጥሮ መካከል የሚገኙ ልዩነቶች!

ማይክል፦ በትክክል ስነሕይወታዊ ልዩነቶች አሉ፤ይሁንና ልዩነቶቹ ከኛ ርእስ ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?

ራሽድ፦ አምኖና ወዶ የመቀበል ግዴታን ከሚመለከተውና እኔ ከማምንበት ሃይማኖታዊ መንደርደሪያ በመነሳት አላወራም። የማናግርህ እንደምታምንባቸው ቀደም ሲል ከነገርከኝ የሳይንስና የአእምሮ መንደርደሪያ በመነሳት ነው . . የኔ ጌታ አድምጠኝማ፦

በቅርቡ የተካሄዱ ሳይንሳዊ ጥናቶች ወንድ ዘንድ የሚገኘው የፍቅር ቅመም ሴትዋ ዘንድ ከሚገኘው የፍቅር ቅመም የሚለይ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህም አያሌ የሳይንስና የምርምር ተቋማትን በወንድና በሴት መካከል በሚገኙት የፍቅር ስሜቶች ልዩነቶች ላይ ጥልቅ ምርምር እንዲያደርጉ ገፋፍቷቸዋል። ሳይንቲስቶቹ የደረሱበት ውጤት በጣም አስደማሚ ሲሆን፣የወንድ ጂኖች ብዙ ግንኙነቶች እንዲኖሩት ሲገፋፉት የሴቷ ጂኖች ደግሞ ወደ መረጋጋትና ወደ ነጠላ ግንኙነት ይገፋፏታል። ወንድ ከአንድ በላይ ሴቶችን በአንድ ጊዜ ለአንዷ ያለው ፍቅር ለሌላዋ ባለው ፍቅር ላይ ምንም ተጽእኖ ሳይፈጥርበት ማፍቀር የሚችል መሆኑን ዘመናዊው ሳይንስ በተጨባጭ አረጋግጧል።

የ CNN ድረገጽ በዮታ እስቴት ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑትን ሊዛ ዳይመንድን በመጥቀስ እንዳስነበበው፣የወንዶች ወሲባዊ ግንኙነት ከአንድ በላይ ሴት ጋር የመሆኑ ሁኔታ ከአካላዊ አፈጣጠራቸው የሚመነጭ ስለመሆኑ ስነሕይወታዊ ማስረጃዎች መኖራቸው ተረጋግጧል።

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡደን በ2007 ባካሄደው አንድ ምርምር ሴቶች ከወንዶች በተቃራኒ፣ ዋነኛ ትኩረታቸው የሚያነጣጥረው በሰውነቶቻቸው ላይ ወይም በልጆቻቸው እንክብካቤ ላይ መሆኑንና ይህም ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የመተሳሰር ስሜት በሚጨምረው አክስቶሲን ሆርሞን ምክንያት መሆኑን ደርሰውበታል።

የተወሰኑ የወንዶች የአንጎል ክፍሎች ከሴቶቹ በእጥፍ ያህል የሚበልጡ መሆናቸውን፣በተባዕትና በእነስት አንጎል መካከል ያለው ትልቁ ልዩነትም፣በወንዶች ዘንድ ላለው ወሲባዊ ፍላጎት ተጠያቂ የሆነው የአንጎል ክፍል፣ከሴቶቹ ተመሳሳይ የአንጎል ክፍል በሁለት ተኩል እጥፍ ያህል የሚበልጥ መሆኑ ነው።

እናም ወዳጄ፣እነዚህ ልዩነቶች ተጨባጭ የሆነ ተጽእኖ የላቸውም ብለህ ታምናለህ?!

ማይክል፦ እነዚህ መረጃዎች ትክክለኛ ከሆኑ ተጽእኖ ማሳደራቸው የታወቀ ነው።

ራሽድ፦ ስለዚህም የወንዱ ‹‹የሥጋዊ ፍላጎቶች ተገዥነት›› ያልከውና ከአንድ በላይ ከሆኑት ሴቶች ጋር ያለው ግንኙነት ከእስላም ወይም ከምሥራቃዊው ሕብረተብ ጋር ተያየዥነት ያለው ጉዳይ አይደለም . . እኔም በተራዬ አንድ ጥያቄ ላቀርብልህና በተለመደው ግልጽነትህ እንድምትመልስልኝ ተስፋ አደሰርጋለሁ። የአንተን የግልህን ግንኙነቶች ልተወውና ከጓደኞችህና ከወዳጆችህ መካከል ከተለያዩ ብዙ ሴቶች ጋር ግንኙነቶች የሌላቸው ስንቶቹ ናቸው?

ማይክል፦ የኔን የራሴንም ግንኙነቶች ቢሆን እንኳ፣ይህ ነገር እኛ ዘንድና በሕብረተሰቦቻችን ውስጥ በስፋት የተሰራጨና ዕውቅና የተሰጠው ጉዳይ ነው . . ይሁን እንጂ ጋብቻ አይደለም።

ራሽድ፦ እናም የኛን ሕብረተሰቦች የወቀስክበት ነገር በናንተም ሕብረተሰቦች ውስጥ አለ ማለት ነው፤ግን በመካከላቸው ካለውና ከምጠቅስልህ ትልቅ ልዩነት ጋር ነው የተንሰራፋው።

እኔ ግን ሌላም እጨምርልሃሁ፦ ብዙ ሚስት የማግባት ሥርዓት በእስላም የተጀመረ አይደለም። ከአንድ በላይ ሴት ማግባት በሁሉም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ለዚያውም የተወሰነ ቁጥር ተለይቶ ሳይታወቅና ገደብ ሳይኖረው ነው። ብዙ ሚስት የማግባት ሥርዓት በሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች ውስጥም የሚታወቅ ነው። በአይሁድ ሃይማኖት ውስጥ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን፣ራቢ ገርሹም አሽክናዚ (960-1040) ከአንድ በላይ ማግባትን ክልክል እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የተፈቀደ ሆኖ ቆይቷል። በክርስቲያኑ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ግን ብዙ ሚስት ማግባት ከአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ እንጂ ክልክል ተደርጎ አያውቅም። እስከ ዛሬም ድረስ ሞርሞንን በመሳሰሉ አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ እንደ ተፈቀደ ቀጥሏል።

ማይክል፦ እናም ይህ በጥንቱ ዘመን የነበረ ነው፤ዛሬ ግን የሰው ልጅ በሥልጣኔ ተራምዷል።

ራሽድ፦ ዕድገትና ሥልጣኔ ከሰው ልጆች ተፈጥሮ ጋር በመላተም፣ለፍላጎቶቻቸው ምላሽ ባለመስጠትና ከጥቅሞቻቸው በላይ በመሆን እውን አይሆንም። የሰው ልጅ በጥንቱ ዘመን የከብት ሥጋ ይበላ ወይም የበጎችን ሱፍ ይለብስ ነበር ተብሎ ዛሬ ሥጋ መብላትንና ሱፍ መልበስን ኋላቀርነትና አለመሰልጠን አድርጎ መገመት የሚታሰብ አይደለም . . ማለት የሚቻለው የሰው ልጅ ሥልጣኔና ዕድገት እነዚህ ነገሮች ለሰው ልጅ ፍላጎቶችና ለጥቅሞቹ ይበልጥ ምላሽ የሚሰጡና ኑሮውን ይበልጥ የተመቻቸ ማድረግ የሚችሉ መሆናቸውን ነው . . ይህ ደግሞ የእስላም ተልእኮ ነው።

ማይክል፦ እንዴት?

ራሽድ፦ በምዕራቡ ሕብረተሰቦቻችሁ ውስጥ ከጋብቻ ማእቀፍ ውጭ የሆኑ የፍቅርና የወሲብ ግንኙነቶች የተስፋፉ መሆናቸውን ተናግረሃል። እውነቱን ለመናገር በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግፍና በደል ማለት፣ለስነልቦናዊ መረጋጋት የማያበቃ፣መብትን የማያስከብርና ጤናማ ማህበረሰብን የማይፈጥር እንዲህ ዓይነቱ ግንኙነት ነው። በጥንታዊ ሥልጣኔዎች ውስጥ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት ያለ ምንም ገደብና መቆጣጠሪያ የነበረ ሲሆን፣እስላም ሲመጣ ግን አንዱን ባል ሕጋዊ ባል አድርጋ ኃላፊነት ባለው መንገድ እንድትጋራ በማድረግ ለሴቷ ፍላጎት ፍትሐዊ ምላሽ ሰጥቷል። ይህ ክቡር ማሕበራዊ ተቋም - ጋብቻና ቤተሰብ - የበለጠ የስኬታማነት ዋስትና ይኖረው ዘንድ እስላም በዚህ ባል ላይ የተለያዩ ግዴታዎችንና ገደቦችን ጥሏል።

እስላም የሴት ልጅ ጥቅሞችን አስጠብቆ፣ከአንድ በላይ በማግባት የሕጋዊ ጋብቻ ማእቀፍ ውስጥ የወንዱን ሥጋዊ ፍላጎቶች በማፈንና ልቅ በማድረግ መካከል ሚዘናዊነትና መቻቻል እንዲኖር አድርጓል። በዚህም እናንተ ዘንድ በአውሮፓ በከፍተኛ ደረጃ ለፈረካከሰው ማሕበራዊ ተቋም - ለቤተሰብ - ከፍተኛ ጥበቃና እንክብካቤ አድርጓል።

ማይክል፦ ተጨባጭ አኃዛዊ መረጃዎች የሚናገሩት ግን የሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ቁጥር አማካይ መቶኛ ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ መሆኑን ነው። ከአንድ ሚስት በላይ የማግባትን መርሕ ተግባራዊ ካደረግን የተወሰኑ ወንዶች ያለ ሚስት ሊቀሩ ነው፤ይህ ደግሞ በራሱ ሌላ አደገኛ ችግር ነው።

ራሽድ፦ ሳይንሳዊ አኃዛዊ መረጃዎች ይህን የሚያረጋግጡ ከሆኑ፣የሴቶች አማካይ ዕድሜ ከወንዶች አማካይ ዕድሜ ከፍ ያለ መሆኑንም መረጃዎቹ ያረጋግጣሉ። በምዕራቡ ዓለም ወንድ በአማካይ ከሴቷ በ7 ዓመት ያነሰ ዕድሜ ይኖራል። ይህ ልዩነት ባለፈው ምእተ ዓመት በቀጣይነት እየጨመረ መጥቷል። ለምሳሌ ያህል በጀርመን፣የሴት አማካይ ዕድሜ 80 ዓመት ሲሆን፣የወንድ አማካይ ዕድሜ ግን 70 ዓመት ነው። ይህ ልዩነት በ1900 ዓመተ ልደት ሁለት ዓመት ብቻ ነበር።

የሚሽገን ዩኒቨርሲቲው ሳይንቲስት ዳንኤል ክሮጀር እንደሚሉት፣በአብዛኞቹ የዓለም አገሮች ወንዶች ከሴቶች ያነሰ ዕድሜ ይኖራሉ። ከዚህ ልዩነት መንስኤዎች አንዱ በወንድና በሴት መካከል ያለው የሆርሞኖች ልዩነት ሲሆን፣የወንድ ሆርሞኖች የልብና የደም ዝውውር በሽታዎችን የሚያስከትሉ ጂኖችን ያነቃቃሉ።

በተጨማሪም ግጭቶችና ውጥረቶች በነገሱባቸው አገሮች ውስጥ በሚቀጣጠሉ ጦርነቶች፣በአደጋ የታጠሩ ከባድና አስቸጋሪ ሥራዎች፣የትራፊክ አደጋን በመሳሰሉ ማሕበራዊ ክስተቶች . . ምክንያት በሚደርሰው ሞት አብዛኛዎቹ ሰለባዎች ወንዶች ናቸው . .

ይህም በሕብረተሰቡ ውስጥ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በልጦ ይገኛል ማለት ነው። ይህ በአብዛኞቹ የዓለም አገራት ውስጥ የሕዝብ ቆጠራ መረጃዎች የሚያረጋግጡት እውነታ ነው። እየተስፋፋ የመጣው የፈቶችና ባል የሞተባቸው ሴቶች ቁጥርም ሌላው ነው . .

እናም ባል የሌላቸው ሴቶች የስነልቦናዊ፣ማሕበራዊና ስነምግባራዊ ችግሮች ሰለባ ሆነው መቅረት አለባችው? ወይስ በራሳቸውም ሆነ በሕብረተሰቡ ደህንነት ላይ አፍራሽ ተጽእኖ በሚያስከትል ሁኔታ፣መብታቸውን እንዲለምኑና ተፈጥሯዊ ፍላጎታቸውን በስውር እንዲያረኩ መገፋፋት አለባቸው? ወይስ የሁሉንም ፍላጎት ያገናዘበ፣በሕጋዊ ደንብና ገደቦች የታጠረ፣የሰው ልጆችን አቅምና ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባ፣ማንንም የማይበድልና በሁሉም ወገኖች ላይ ጫና በማይፈጥር ፍትሐዊ ማእቀፍ ውስጥ ለሁሉም ወገኖች ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ማሕበራዊ ሥርዓት መደንገግ?!

ፈረንሳዊው የስነሕብረተሰብ ሊቅ ዶክተር ጉስታፍ ሊቦን፦ ‹‹ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን የሚፈቅደው የምሥራቁ (እስላማዊው ማለታቸው ነው) የጋብቻ ሥርዓት፣ለሚከተሉት ሕዝቦች ስነምግባራዊ ደረጃን ከፍ የሚያደርግ መልካም ሥርዓት ነው፤የቤተሰብን ትስስር ያጠብቃል፤ለሴት ልጅ አውሮፓ ውስጥ የማታያቸውን አክብሮትና ደስተኝነትን ያጎናጽፋል።›› በማለት ለጥያቄው መልስ ሰጥተዋል።

አንድ ብርጭቆ የሎሚ ጭማቂና ኩባያ ሻይ እንድንጠጣ መልካም ፈቃድህ ይሁን።