አልዶ ሚይሊ

quotes:
  • የአላህ ሥራ!!
  • ‹‹ቀደም ሲል ጥንታዊው የደቀልዲያኖስ ኢምፓይር ክፍል ተደርገው ይቆጠሩ በነበሩ አገሮች ውስጥ ስር በሰደደው የማሽቆልቆል ዘመን፣ከዐረቢያ በረሃዎች እምብርት አንዱድ ባለጋራ በድንገት ብቅ አለ። እርጅና የተጫጫነውን ያንን ኢምፓይር ማሳደድም ያዘ። በስተደቡብ አቆጥቁጠው ለነበሩ አዳዲስ ግዛቶችም ደመኛ ጠላት ሆነ። ይህ ባለጋራ ዓይን እያየ ጥንካሬና ግዝፈት መጨመሩን ቀጠለ። ፍጹምና ቅን የሆኑ፣የአላህ ቋሚ ረድኤት ወደ ጅሃድና ወደ አንጸባራቂ ድል የሚመራቸው ይመስል ነበር። ሶርያና ግብጽን በድል አድራጊነት መያዝም ተከተለ። በአጭር ጊዜ ውስጥም የሳሳኒያውያን ኢምፓይር ፈረካከሰ። የፍልስጥኤም አጋሮችም ያንኑ የሽንፈት ጽዋ ለመጎንጨት ተገደዱ።››
Tags: