ንግሥቲቱ ሴት

ንግሥቲቱ ሴት

ባቡሩ ከተንቀሳቀሰ ከአንድ ሰዓት በኋላ ሁለቱ ወዳጆች ራሽድና ማይክል እየተጓዙ ውይይታቸውን ለመቀጠል ዝግጁ ሆነዋል . .

ማይክል፦ የሴቶችን መብት በሚመለከቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ማለትም ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትንና ሕጃብን አንስተን ተወያይተናል . . ከዚህ ርእስ ጋር በተያያዙ ቀሪ ጉዳዮች ላይ ውይይታችን ቢቀጥል ምን ይመስለሃል?

ራሽድ፦ ጥሩ ሀሳብ ነው፤ምናልባትም በዚሁ ርእሱን እንቋጭ ይሆናል።

ማይክል፦ በዚህ ነጥብ ላይ አእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው የሴት ልጅ ሚና ነው፤ሴቶች በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ውስጥ ከወንዶች እኩል እንዳይሳተፉ ሙስሊሞች ለምን አሻፈረን ይላሉ?

ራሽድ፦ ወዳጄ፣የሰው ልጅ ቁሳዊ ወይም እንስሳዊ ጎን አለው ስንል፣የዚህ መለያ ባሕሪያት፣ግቦቹና ውጤቶቹ እንስሳት ዘንድ ካሉት ባሕሪያትና ውጤቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ማለት አይደለም። በሁለቱ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት ነው። በሰው ልጅ ዘንድ ያለው የወሲባዊ ፍላጎት ዝንባሌ እንስሳት ዘንድ ካለው በብዙ የላቀ ሆኖ ስናገኝ፣በተቃራኒው ደግሞ የሰው ልጅ የወሲብ ብቃትና ሃይሉ ደግሞ ከእንስሳቱ በብዙ እጅ ደካማ ሆኖ እናገኛለን።

የሴቷን ተፈጥሮ ከስሜታዊ ፍላጎት፣ከጾታዊ መስህብነትና ከዓይነ አፋርነት፣ከይሉኝታና ከቁጥብነት፣ከእምቢታና ከጭምትነት አኳያ ግምት ውስጥ ካስገባን፤የሰው ልጅ የጾታዊ መስህብነት ኃይል አለው ሲባል ማለት የተፈለገው በሁለቱ ጾታዎች መካከል ቋሚ የሆነ ትስስርን እውን ማድረግ ነው ወደሚል መደምደሚያ እንደርሳለን። እያንዳንዱ ጾታዊ ስሜትና ፍላጎት በወሲባዊ ተራክቦ ብቻ የሚወሰን አይደለም። ይህም ቁርኣን ከስነልቦና አንጻር አንዴ በሕሊናዊ መረጋጋት (ሰከን)፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ውዴታና ርህራሄ (አልመወደህ ወርረሕመህ) በማለት የገለጸው ነው . . ንግግሬ ግልጽ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ማይክል፦ ከሞላ ጎደል ግልጽ ነው።

ራሽድ፦ ጉዳዩን ከስነሕይታዊ ገጽታው አኳያ ስንመለከተው፣ሴት ከወንዱ በሁሉም ነገር የምትለይ መሆኗን ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ከውጫዊ የሰውነት ቅርጽ ጀምሮ እስከ ወስጣዊ አባላተ አካላት፣እስከ አካል አቶሞችና ሕዋሳት የተለያዩ ናቸው። የሴት ሕዋሳት የአነስታይ ጾታ ባሕሪያትን የተሸከሙ ሲሆን የአካሏ አወቃቀርና የነርቭ ስርዓቷም ከወንዱ ይለያል። የመላ ሰውነቷ አፈጣጠር ልጅ ለመውለድና ለመንከባከብ በሚያዘጋጃት ሁኔታ የተዋቀረ ነው። ይህም ከእናትነት ተልእኮዋ ጋር የተጣጣመ ነው ማለት ነው። ለአቅመ ሕዋን በምትደርስበት ጊዜ የወር አበባ ሁኔታ ያጋጥማታል። ይህም በሁሉም አካላቷ አሰራር ላይ ብቻ ሳይሆን በስነልቦናዋ፣በአእምሮዋና በባሕሪዋ ላይ ጭምር ተጽእኖ ያሳድራል። የእርግዝና የእመጫትነትና የማጥባት ሁኔታዎችም መኖራቸውን ሳንዘነጋ ነው።

ከዚህም አልፎ የሴት ሆርሞኖችና ስነልቦናዋም ከወንዱ ይለያሉ። ከወንዱ ደፋርነትና ተጋፋጭነት አንጻር የሴቷን ዓይነ አገፋርነትና ልስላሴ እናስተውላለን።

በሌላ በኩልም የሰው ልጅ ሕጻን ከእንስሳቱ በተቃራኒ አቅም ለማግኘትና ራሱን ችሎ ለመኖር ጊዜ ስለሚወስድበት፣ለተወሰኑ ዓመታት የወላጆቹን እንክብካቤና አስተዳደግ ይሻል። ይህም አንደዚሁ የወንድና የሴት ግንኙነትን በጾታዊ መፈላለግ ብቻ ላይ እንዳይወሰን ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ነው። ይልቅዬ የዚህ መፈላለግ ፍሬ በሕይወት ውስጥ ተራድኦና መተጋገዝ እንዲኖር ያደርጋል። በዚህም ምክንያት ነው የሰው ልጅ ከተቀሩት እንስሳት ሁሉ ይበልጥ ለልጆቹ ቡቡና አፍቃሪ ሆኖ የተፈጠረው።

ማይክል፦ ከዚያስ?

ራሽድ፦ ከዚህ ማረጋገጥ የምንችለው ለሰው ልጅ ተፈጥሯዊው መሰረታዊ ማህበራዊ አሃድ ቤተሰብ መሆኑን ነው። በዚህ መዋቅር ወይም አሃድ ውስጥም የያንዳንዱ አባል ተግባር ምን እንደሆነ መረዳት የሚቻለን ሲሆን፣እያንዳንዱ አባል ከዚህ አሃድ ዓለማዎችና ባሕሪያት (ሕሊናዊ እርጋታ፣ፍቅርና ርህራሄ) ጋር የሚጣጣም ሚና ይጫወታል። በተጨማሪም የያንዳንዱ ሚና ከአቅሙና ከችሎታ አኳያ የተቃኘ ይሆናል።

ማይክል፦ ማለት የፈለግከው ገብቶኛል። እናም የሴቷ ሚና በቤተሰቡ የፍቅርና የመውደድ መንፈስ ማሰራጨት፣ሕሊናዊና ስነልቦናዊ መረጋጋትን እውን ማድረግ፣ባልና ልጆችን መንከባከብ ነው ማለት ነው።

ራሽድ፦ ትክክል። የወንዱ ሚና ደግሞ ለቤተሰቡ ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማቅረብ፣ይህን እውን ለማድረግ የሚጠየቀውን ችግርና መከራ ሁሉ ተቋቁሞ መስዋእትነት መክፈል ነው።

ማይክል፦ ይህ አመለካከት ግን የሕብረተሰቡን ግማሽ አምራች ኃይል እንድናጣ ያደርገናል።

ራሽድ፦ ፈጽሞ። አመለካከቱ የሕብረተሰቡን አቅም ሙሉ በሙሉ እንድንጠቀም ነው የሚያደርገን። ግን ሁሉም በተሰማራበት መስክ ለራሱ ተስማሚና ከተፈጥሮው ጋር በተጣጣመ አካባቢ ውስጥ ነው የየራሱን ሚና የሚወጣው። የሴት ልጅ ተፈጥሯን ተጋፍጣ ከቤት ውጭ ከወንዶች ጋር ለመስራት በወጣች ጊዜ በአዲሱ ሥራዋ ራሷ ተከፍታ ቤተሰቧንና ባልዋንም አስከፍታለች። በዚህም ሕብረተሰቡ በሙሉ ደስተኛ ሊሆን አልቻለም። ሴቲቱ የቤት ኃላፊነቷንና የልጆቿን እንክብካቤ ከውጭ ሥራዋን ጋር ለማስታረቅና ለማጣጣም በተደጋጋሚ ሞክራ አልተሳካላትም። በአንድ ጊዜ የተረጋጋች ሚስት፣ቡቡና ርህሩህ እናት፣ከቤት ውጭ ደግሞ ንቁ ሠራተኛ መሆንን ማጣመርና በስኬት አንድ ላይ ማስኬድ መች ይቻልና?! ሁኔታው ያስከተለው ውጤት ሌሎች ወገኖች እርሷ በተወችው ክፍተት እንዲገቡ ማድረግ ሲሆን፣እነዚህ ወገኖች ደግሞ ይህን ሚና ለመጨዋት ታማኝነትም ሆነ ብቃት የላቸውም። በተጨማሪም ከቤት ውጭ ለሥራ ከወንዶች ጋር መወዳደሯ ሴቲቱ ከወንዶች ጋር እንድትቀላቀልና ከዚህ በሚመነጨው የትንኮሳና የአስገድዶ መደፈር ወንጀል እንድትጋለጥ፣በብዙዎቹ የሥራ ዓይነቶችና ምደባዎች ተጎጂ እንድትሆን አድርጓታል።

ማይክል፦ የሴቷ ሚና ቤተሰባዊ ነው ካልን፣ይህ ለሴት ልጅ ጭቆና ነው ብዬ ወደማስበው ሌላው ጉዳይ ይወስደናል። እሱም ወንድ በሴቲቱ ላይ ቋሚና አሳዳሪ የመሆኑ ጉዳይ ነው።

ራሽድ፦ የወንዱ ቋሚነትና የበላይ አሳዳሪነት (አልቀዋማህ) ጭቆናም ሆነ አድልኦ ሳይሆን፣‹‹ቤተሰብ›› ተብሎ የለሚጠራን ማህበራዊ ተቋም አደራጅ ነው። ማንኛውም ተቋም አቅሙን ክህሉቱንና ችሎታውን ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ የያንዳንዱን አባል ሚና፣ተግባርና ኃላፊነት መወሰን የግድ ነው። ለምሳሌ ያህል ሥራ አስፈጻሚው ሰፋ ያለ ሥልጣን ስላለው ከሂሳብ ሹሙ ወይም ከሌላው ሠራተኛ በሰውነት ሚዛን የበላይ ነው ሊባል አይችልም።

በተግባራዊ ሕይወታችን ውስጥ እንደምናስተውለው፣አንድ ተቋም ወይም ድርጅት አስገዳጅ ወይም አጋጅ የሆኑ አንዳንድ ገደቦችን፣ከፍተኛው አመራር ወይም የሥራ አመራር ቦርዱ ወሳኝ አስፈላጊነት አለው ብሎ ስላመነ በተቋሙ አባል ሠራተኞች ላይ ሊጥል ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል የተለየ ዩኒፎርም መልበስን፣የተወሰኑ የደህንነት መመሪያዎች ማክበርን፣የተወሰኑ ሥልጠናዎች መውሰድን ግዴታ አድርጎ ሊወስን ይችላል። ያለ ፈቃድ ሥራ ጥሎ መውጣትን ወይም በሥራ ሰዓት በሌላ ነገር መጠመድን ይከለክላል። ከዚህም አልፎ አንዳንድ ተቋማት በሥራ ውላቸው ውስጥ ሠራተኛው ሥራውን ከለቀቀ በኋላ ጭምር ሊያከብራቸው የሚገቡ ገደቦችን ሊያካትቱ ይችላሉ . . ይህ ሁሉ የሚታወቅና ተቃውሞ የማይቀርብበት ነው . . እነዚህን ገደቦች በተቋሙ ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጭቆናና አድልኦ አድርጎ የሚመለከት ማንም ሰው የለም። ይህ ሁሉ የሚፈጸመው ግልጽና ዕውቅ በሆነ ሥርዓት ማእቀፍ ውስጥ ነው . . ከተጣለበት ኃላፊነትና የተጠያቂነት ግዴታ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሥልጣን ያለው ሥራ አስፈጻሚ የሌለው አንድም ስኬታማ ተቋምም ሆነ ድርጅት የለም።

በዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ የቤተሰብ ተቋም ስኬታማ ይሆን ዘንድ፣ሁሉም አባላቱ የሚመሩበት ሥርዓት ሊኖረው ግድ የሚለው። በዚህም ሥርዓት ውስጥ የሚከለክሉ ወይም የሚያዝዙ ገደቦች ሊኖሩ ይችላሉ . . እናም ተቋሙ ከኃላፊነቱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሥልጣን፣የሀሳብ ልዩነተቶች ሲፈጠሩ የመወሰንና የመቁረጥ አቅም ያለው መሪ የግድ ሊኖረው ይገባል። በተጨማሪ ይህ ሥርዓት የሚተገበረውና ይህ ሥልጣን አገልግሎት ላይ የሚውለው፣ቀደም ሲል በተነጋገርንበት የቤተሰባዊ ሕይወት መርህ ማእቅፍ ውስጥ ብቻ መሆኑም እንደዚሁ የግድ ነው። መርሁም ስነልቦናዊና ሕሊናዊ መረጋጋትን እውን የሚያደርገው የመውደድና የርህራሄ መርህ ነው።

ማይክል፦ ነገሩ እንደዚያ ከሆነ የበላይ አስተዳዳሪነቱ ለምንድነው የወንዱ የሚሆነው?! ለምን ለሴቲቱ አይሆንም? ሚዘናዊነትን አያዛባም?

ራሽድ፦ ከዚህ ይልቅ ‹‹ፍትሐዊነት›› የሚለውን ቃል የምመርጥ ከመሆኔም ጋር፣እኩልነት ወይም ፍትሐዊነት መኖር ያለበት በመብቶች ውስጥ ነው እላለሁ፦ እኛ አሁን የያዝነው ርእስ ግን እያንዳንዱ አባል አቅሙን ችሎታውንና ተፈጥሯዊ ዝግጁነቱን ባገናዘበ መልኩ የሚይዛቸውን ማህበራዊ ኃላፊነትና የሚናዎች ክፍፍልን የሚመለከት ነው።

በቤተሰብ ተቋም ውስጥ ወንድና ሴቷ እያንዳንዳቸው በተፈጥሯቸው ለተለያዩ ጉዳዮች የተዘጋጁ ናቸው ብለናል። ይህ የዝግጁነት ሁኔታ ከተለያዩ ማህበረሰባዊ ተግባሮችና ኃላፊነቶች ጋር የተጣጣመ ነው። ለወንድ ከተሰጠው የቋሚነትና አስተዳዳሪነት አንጻር በሴቲቱ ላይ ያልተጣሉ ኃላፊነቶችና ግዴታዎች የተጣሉበት መሆኑን አትርሳ። ቋሚነት (አልቀዋማህ) በዚህ ግንዛቤ መሰረት ከበሬታ ከመሆኑ ይልቅ በወንዱ ጫንቃ ላይ ከባድ ኃላፊነትና ልዩ ሸክም የሚጭን ግዴታ ነው፤ይህ ደግሞ ማስተዋልን ትእግስትን ቻይነትንና ወሳኔ አሰጣጥ ላይ ችኩል አለመሆንን የሚጠይቅ ሲሆን፣የሴቷን ሀሳብ ወድቅ ማድረግና ሰብእናዋን መንካትም ተገቢ አይደለም።

ሴቶች ነብያችን  እንዳሉት ሁሉ ‹‹የአእምሮና የሃይማኖት ጉድለት አለባቸው›› በመሆኑም ሴት ልጅ በተፈጥሯ ለዚህ ማሕበረሰባዊ ኃላፊነት ብቁ አትሆንም።

ማይክል፦ ‹‹የአእምሮ ጉድለት ነው የምትለው?!›› ይህማ ሴትን አንቋሾ መመልከት ነው። ሴት ልጅ በሰይንሱ መስክ ብቃትና ችሎታዋን አስመስክራለች፤በአእምሮ ብስለት መለኪያም ከወንዱ አታንስም።

ራሽድ (እየሳቀ)፦ ወዳጄ፣በጣም የሚገርመው ይህን ሐዲሥ የጠቀስኩላቸው ሰዎች ሁሉ አንተ በተረዳኸው መንገድ የተረዱት መሆኑ ነው። እዚህ ላይ ማለት የተፈለገው የአእምሮ የንቃት ደረጃ ጉድለት ሳይሆን ነገሮችን በትክለኛው መንገድ አመዛዝኖና አስተውሎ በተረጋጋ መንፈስ የመወሰን ችሎታ ነው። ስሜታዊነትንና ግልፍተኝነትን ተቆጣጥሮ ራስን በመግዛት፣በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥና በቀውስ ጊዜ ትክልለኛ ወሳኔ የመወሰን ብቃት ነው። በሌላ አነጋገር የስሜታዊነትና የችኩልነት ተቃራኒ ማለት ነው። ሴት በተፈጥሮዋ ከወንድ ይበልጥ ወደ ስሜታዊነትና ቶሎ በተጽእኖው ስር ወደመሆን የምታዘነብል መሆኑን ማንም ማስተባበል አይችልም። ይህ ስነልቦናዊ ባህሪዋ ነውና ማህበረሰባዊ ሚናዋም ከዚህ ተፈጥሮዋ ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል። ምናልባትም የሴት ልጅ በራሷ ቤተሰባዊውን ሕይወት በመናድ ፍች እንዳትፈጽም ገደብ የተጣለባት በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ማይክል፦ ስለ ሴት ጭቆናና በበታችነት ስለመታየቷ ካነሳን ዘንዳ፣ስለ ውርስ መብቷም ማንሳት የግድ ነው። የሴቷ የውርስ ድርሻ የወንዱ የውርስ ድርሻ ግማሽ የሆነው ለምንድነው?!

ራሽድ፦ አንደኛ- የሴቷ ድርሻ ግማሽ የሚሆነው በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ አይደለም።

ሁለተኛ- የሰብአዊ መብት መርህ ለአንድ ሰው የሚሰጡ መብቶቸ ለሌላው ሰው ከሚሰጡት ጋር የግድ ተመሳሳይ እንዲሆኑ አይጠይቅም። ፍትሐዊ መሆን በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ እኩልነትን ግዴታ አያደርግም። እኩልነት ግዴታ የሚሆነው የሁኔታዎች ተመሳሳይነት በሚኖርበት ጊዜ ነው። ይህም ማለት የሴት ተፈጥሮና በሕይወት ውስጥ የምትጫወተውን ሚና ግምት ውስጥ ማስገባትና መብቶቿን ከግዴታዎቿ ጋር ማመዛዘን የግድ ነው ማለት ነው።

ለምሳሌ ያህል የውርስን ጉዳይ በሚመለከት ሴቷ የምታገኘው ድርሻ የራሷ ብቻ ሲሆን፣ወንዱ የሚወስደውን ድረሻ ግን ከባለቤቱ፣ከልጆቹ፣ካላገቡ እህቶቹ፣በሕይት ካሉና ሌላ ረዳት ከሌላቸው ወጭያቸውን የመሸፈን ግዴታ አለበትና ከወላጆቹ ጋር ይካፈላል። በተጨማሪም ለሚስቷ ሴት መህር (ጥሎሽ) በስጦታ መልክ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣መኖሪያ ቤትና የቤት እቃን ማሰናዳት፣የሚስት የልጆችና የቤተሰቦቹን ሙሉ ወጭ የመሸፈን ግዴታም አለበት። ሚስቱ ሠርታ ገቢ እንድታመጣ የማስገደድ መብት ግን የለውም . . ሚስቲቱ ሀብት ቢኖራት በገንዘቧና በንብረቷ ላይ ምንም ዓይነት መብት አይኖረውም። በተጨማሪም ሴት በሀብቷ ላይ ማንም ጣልቃ በማይገባበት ሁኔታ የማዘዝና ሙሉ የባለቤትነት መብት ያላት ሲሆን፣ይህም ለሴት ልጅ ፍትሐዊ እንደሆነ የሚያወራው የምዕራቡ ዓለም ብዙዎቹ ሴቶች እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ ያልደረሱበት ደረጃ ነው።

በዚህ ፋይል ውስጥ እንድንወያይበት የምትፈልገው የቀረ ነገር አለ?

ማይክል፦ አዎ፣የፍች ጉዳይ ይቀራል፤ይሁን እንጂ ትንሽ ዕረፍት መውሰድ የሚያስፈልገን ይመስለኛል።