በይፋና በአደባባይ

በይፋና በአደባባይ
‹‹እኔ የታላቁ አገራዊ መሪ የጋንዲ ልጅ መሆኔን ሁላችሁም ታውቃላችሁ። እነሆ በይፋና በአደባባይ በዚህ ግዙፍ የሙስሊሞች ስብስብ መካከል ሆኜ እስላምን ማፍቀሬንና ቁርኣንን መውደዴን አውጃለሁ። በአንድ አላህና በብጹኡ መልክተኛ በመሪያችን በሙሐመድ  አምኛለሁ። የነቢያት መደምደሚያ መሆናቸውንና ከርሳቸው በኋላ ነቢይ አለመኖሩን፣ቁርኣን ውስጥ የተካተተው ሁሉ እውነት መሆኑን፣ከአላህ የተላለፉ መለኮታዊ መጽሐፎች ሁሉ እውነት መሆናቸውን፣የአላህ ነቢያትና መልክተኞችም እውነት መሆናቸውን አምናለሁ። ለእስላምና ለቁርኣን ብዬ እናራለሁ፤እሞታለሁም።እከላከልላቸዋለሁ፤እታገላለሁም፤ከታላላቅ ዋልታዎቹም አንዱ እሆናለሁ፤አብሳሪውም እሆናለሁ። ሕዝቤንና ወገኖችን ወደርሱ እጠራለሁ። ይህ ሚዘናዊ ሃይማኖት የዕውቀት፣የስልጣኔ፣የፍትሕ፣የታማኝነት፣የርህራሄና የእኩልነት ሃይማኖት ነው።››


Tags: