በርናርድ ሾው

quotes:
  • የዓለም መንገድ
  • ‹‹የእስላምን ነቢይ የሕይወት ታሪክ በሚገባና ደጋግሜ አንብቤያለሁ። መሆን የሚገባውን ታላቅ ስነምግባር እንጂ ሌላ አላገኘሁበትም፤እስላም የዓለም መንገድ ይሆን ዘንድም በጽኑ ተመኘሁ።››


  • የዛሬው ዓለምና የወዲያኛው ዓለም ሕይወት ሃይማኖት
  • ‹‹ዐዋቂ የሆነ ሰው በተፈጥሮው ወደ እስላም ያዘነብላል። [እስላም] የዚህን ዓለም ሕይወትና የወዲያኛውን ዓለም ሕይወት ጉዳዮችን እኩል አድርጎ የሚመለከት ብቸኛው ሃይማኖት ነውና።››


  • የሰው ልጆች አዳኝ
  • ‹‹ሙሐመድን ‹የሰው ልጆች አዳኝ› ብሎ መሰየም ፍትሐዊነት ነው። እርሱን የመሰለ ሰው የአዲሱን ዓለም መሪነት ቢሾም ለችግሮቹ መፍትሔ ለማግኘት ስኬታማ በሆነና ደስተኝነትና ሰላምን ባስገኘለት ነበር፣የሚል እምነት አለኝ።


  • የሰላምና የመታደል መሰረቶች
  • ‹‹አውሮፓ አሁን አሁን የሙሐመድ ጥበብ ይሰማት ጀምሯል፤ሃይማኖቱንም መውደድ ጀምራለች። በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት የአውሮፓ ሰዎች ከተነዙበት መሰረት የለሽ ውንጀላዎች ነጻ መሆኑንም ታውጃለች። የሙሐመድ ሃይማኖትም የሰላምና የመታደል መሰረቶች የሚታነጹበት ሥርዓት ይሆናል፤የአስቸጋሪ ጉዳዮች መፍቻ፣የግጭቶችና የውጥረቶች መፍትሔም በርሱ ፍልስፍና ላይ የተመረኮዘ ይሆናል።››
Tags: