ሮዝማሪ ሃው

quotes:
  • አጥጋቢ ምላሽ
  • ‹‹የእስላም ሃይማኖት ትምሕርቶችን በመተግበር ለሰው ልጅ ሰብአዊ ተፈጥሮውና እውነተኛ ሰውኛ ሰብእናው ይገለጥለታል። ራሱንና ማንነቱንም ያውቃል። እስላም ግራ ላጋቡኝ ጥያቄዎቼ ምላሽ የሰጠኝ ብቸኛው ሃይማኖት ነው።››


  • አጥጋቢ ምላሽ
  • ‹‹ለመንፈስና ቁስ አካል አስቸጋሪ ጥያቄዎች እስላም ውስጥ አርኪና አሳማኝ መልሶችን አግኝቻለሁ። ልክ እንደ ነፍስና እንደ መንፈስ ሁሉ ለአካልም መፈጸም ያለብን ግዴታ እንዳለብንም ለማወቅ በቅቻለሁ። በእስላም አመለካከት አካላዊ ፍላጎቶች፣የሰው ልጅ ጠንካራ፣አምራችና ንቁ ሆኖ ይኖር ዘንድ ሊረኩ የሚገቡ ተፈጥሯዊ ፍላጎቶች ናቸው። እስላም ለነፍስ እርካታን እውን በሚያደርግና በአላህ ትእዛዛት እንድትገዛ በሚያስችላት ጤናማ መደላድል ላይ የታነጹ መሰረታዊ መርሆዎችን አኑሯል። ለአብነት ያህል ጋብቻ እስላም ውስጥ ወሲባዊ ፍላጎቶችን ለማርካት ብቸኛው መንገድ ነው። ሶላት፣ጾም፣አምልኮዎችና በአላህ ማመን ደግሞ የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ጎን የሚያረኩ መሳሪያዎች ናቸው። በዚህም የሰው ልጅ ክቡር የሆነ ሕይወት ይመራ ዘንድ ግዴታ የሆነው ሚዘናዊነት ይረጋገጣል።››
Tags: