ሞንት ጎመሬ ዋት

quotes:
  • ከግብዝነት ምልክቶች አንዱ ነው
  • ‹‹በዚህ አንድ ዓለም ውስጥ፣ዛሬ ሙስሊምና ክርስቲያን ዐረቦች ከአውሮፓውያን ጋር ያላቸው ትስስር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣እስላም በአውሮፓ ላይ ያሳደረውን ተጽእኖና የተዋቸውን አሻራዎች የሚመለከት ጥናት ይፋ መደረጉ በጣም ተገቢ ነው። አንድ ወቅት ላይ በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት የአውሮፓ ክርስቲያን ጸሐፍት በተለያዩ ጎኖች የእስላምን ገጽታ አበላሽተው ማቅረባቸው የሚታወቅ ነው። በተገባደደው ክፍለ ዘመን ግን ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥረት የበለጠ ተጨባጭነትና ሚዘናዊነት ያለው የእስላም ምስል በምዕራባውያን አእምሮ ውስጥ መቀረጽ ጀምሯል። ከዐረቦችና ከሙስሊሞች ጋር መልካም ግንኙነት ይኖረን ዘንድ፣ሙስሊሞች በኛ ላይ ያላቸውን ትሩፋት ሁሉ አምነን መቀበል ይኖርብናል። ያንን ለመካድ የምናደርጋቸው ጥረቶች ግን ራስን በውሸት ከማሞካሽትና ከግብዝነት ምልክቶች አንዱ ከመሆን አያልፍም።››


  • ተገቢው መሪ ዬት አለ?!
  • ‹‹ስለ እስላም ተገቢውን ንግግር የሚናገር ተገቢው መሪ ከተገኘ፣ይህ ሃይማኖት ከመሰረታዊ ኃያላን ኃይሎች አንዱ ሆኖ በድጋሚ መውጣት ይችላል።››


  • ድንቅ የሆነ ብልህ መፍትሔ
  • ‹‹ቁርኣን ለዘመናችን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ሞራላዊ ችግሮች ድንቅ የሆነ ብልህ መፍትሔ ያስቀምጣል። ሙሐመድ አላህ እንዲያደርስ ያዘዘውን መልክት በማድረስ ስኬታማ ከመሆኑ አኳያ የቁርኣንን ጥበብ መጠራጠር የሚቻል አይደለም። በኔ እምነት ሃይማኖታዊ አቋማችን የፈለገውንም ቢሆን የቁርኣንን መልክት የመካው ሁኔታ ድንቅ ቅርንጫፍ አድርገን መውሰድ ይኖርብናል።›› ,


  • ፍትሐዊነትና ንጽሕና
  • ‹‹ይህ ሰው ለእምነቶቹ ብሎ ግፍና ጭቆናን መቻሉ፣መሪና አዛቸው አድርገውት ያመኑበትና ተከተሉት ሰዎች ያላቸው የመጠቀ ስነምግባርና ባሕሪ፣ፍጹማዊ ከሆኑ ታላላቅ ስኬቶቹ ተደምሮ . . ይህ ሁሉ በሰብእናው ውስጥ የሰረጸውን ፍትሐዊነትና ንጽሕና ያመለክታል። ሙሐመድ አስመሳይ ነው የሚለው ግምት ችግሮችን ይበልጥ የሚያወሳስብ እንጂ የሚፈታ ግምት አይደለም። እንዲያውም ከምዕራባውያን ታላላቅ ታሪካዊ ሰብእናዎች ውስጥ ሙሐመድ ያገኘውን ተገቢ ከበሬታ ያገኘ አንድም ሰብእና የለም።››
Tags: