የአላህ ስሞችና ባሕሪያት

የእሰላም ምንጮች

የእሰላም ምንጮች

$Bashir_Shaad.jpg*

በሺር ሻድ

ሕንዳዊ ሰባኪ
ቁርኣን . . የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐፍ
‹‹በተውሒድ ባመንኩበት ቅጽበት፣ቁርኣን የአላህ መጽሐፍ መሆኑንና የመጨረሻውና የማጠቃለያው መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑን የሚየረጋግጡ ማስረጃዎችን መፈተሸ ጀመርኩ። ለዚህ ጉዳይ መፍትሔ እንዳገኝ ያስቻለኝን አላህ አመሰግናለሁ። ቅዱስ ቁርኣን ለተቀሩት መለኮታዊ መጽሐፎች ሁሉ ዕውቅና የሚሰጥ ብቸኛው መለኮታዊ መጽሐፍ ነው። የተቀሩት ግን አንዱ ሌላውን ያስተባብላል። ይህ በእርግጥ ቅዱስ ቁርኣንን ልዩ ከሚያደርጉት ባህርያት አንዱ ነው።››

የእስላም ሃይማኖት ሕግጋቱን፣ዐቂዳውንና ዝርዝር ሕጎቹን የሚያመነጨው ከመለኮታዊ ወሕይ (መገለጥ) - ከቁርኣንና ከነቢዩ ሱንና - ሲሆን ሁለቱ የእስላም አበይተ መሰረታዊ የሕግ ምንጮች ናቸው። ከዚህ በመቀጠል ከሁለቱ ምንጮች ጋር አጠር ባለ ሁኔታ እንተዋወቃለን፦

ታላቁ ቁርኣን

አላህ (ሱ.ወ.) ቁርኣንን ለጥንቁቆች መመሪያ፣ለሙስሊሞች መተዳደሪያ፣እርሱ መመራት ለሻላቸው ሰዎች ልቦና ፈውስ፣መድህን ለወደደላቸው ሰዎች ችቦና ብርሃን ይሆን ዘንድ ወደ መልክተኛው ወደ ሙሐመድ r አስተላልፎታል። ቁርኣን ነቢያትና መልክተኞች ከአላህ (ሱ.ወ.) ተልከው ይዘው የመጡትን መሰረታዊ መርሆዎች ያካተተ መጽሐፍ ነው። ሙሐመድ r ብቸኛው የአላህ መልክተኛ እንዳልሆኑ ሁሉ ቁርኣንም ብቸኛው የአላህ መጽሐፍ አይደለም። አላህ (ሱ.ወ.) ወደ ኢብራሂም ጽሑፎችን አውርዷል፤ሙሳንም በተውራት፣ዳውድን በዘቡር (መዝሙር) አክብሯቸዋል። አልመሲሕ ዒሳም ኢንጂልን ይዘው መጥተዋል። እነዚህ መጽሐፎች ሁሉም አላህ (ሱ.ወ.) ወደ ነቢያቱና መልክተኞቹ ያስተላለፋቸው ወሕይ (መለኮታዊ መገለጥ) ናቸው። ይህ ቁርኣን ከአላህ (ሱ.ወ.) የተላለፈ ወሕይ መሆኑን ከሚመሰክሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ፣በሁሉም የአላህ መልክተኞችና ነቢያት ያለ ምንም ልዩነት ማመንን የሃይማኖቱ አንድ አቢይ ማእዘን አድርጎ ያረጋገጠ መሆኑ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ የሚክዱ፣በአላህና በመልክተኞቹም መካከል መለያየትን የሚፈልጉ፣በከፊሉም እናምናለን፣በከፊሉም እንክዳለን የሚሉ፣በዚህም መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፤እነዚያ በውነት ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው። ለከሓዲዎችም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል። እነዚያም በአላህና በመልክተኞቹ ያመኑ፣ከነሱም ያልለዩ፣እነዚያ ምንዳዎቻቸውን በእርግጥ ይሰጣቸዋል። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።››[አልኒሳእ፡150-152]

$Will_Durant.jpg*

ዎል ዲዮራንት

አሜሪካዊ ደራሲ
የቁርኣን ደረጃና ትሩፋቱ
‹‹ቁርኣን ምናባቸውን ሲቀሰቅስ፣ስነምግባራቸውን ሲቀርጽ፣በመቶ ሚሊዮኖች የመቆጠሩ ሰዎችን አእምሮና እሳቤ ሲሞርድ ለአስራ አራት ምእተ ዓመታት በሙስሊሞች ትውስታ ውስጥ ተጠብቆ ኖሯል። ቁርኣን ከሁሉም ይበልጥ ገርና ቀለል ያለ፣ከሁሉም ይበልጥ ከውስብስብነት፣ከድፍንፍን ምስጢራት፣ከካህናዊ ጣዖታዊ ስርዓታት የጸዳ ዐቂዳን በሰው ልቦና ውስጥ በሰው ልቦና ውስጥ ይተክላል። የሙስሊሞችን የስነምግባርና የስልጣኔ ደረጃን ከፍ በማድረግ ረገድም ትልቁን ሚና ተጫውቷል። የማሕበራዊ አነዋነዋርና የማሕበረሰባዊ አንድነት ስርዓት መሰረቶችን የተከለላቸውም እርሱ ነው። የጤና አጠባበቅ ሕጎችን እንዲከብሩ አበረታቷል። አእምሮአቸውንም ከብዙ አፈተረቶችና ግምታዊ ቅዠቶች፣ከግፍና ከጭካኔ ነጻ አውጥቷል። የጫንቃ ተገዥዎችን ሁኔታዎችም አሻሽሏል። ግፉአን ተዋራጆች በነበሩት ልብ ውስጥም የክብርና የልዕልና መንፈስ ዘርቷል።››

ዳሩ ግና እነዚህ የቀድሞ መጽሐፍት ብዙው ክፍላቸው ጠፍቷል፤አብዛኞቻቸው ከስመዋል፤ለመዛባት፣ለመጣመም፣ለብረዛና ለክለሳ ተጋልጠዋል።

ታላቁ ቁርኣን ግን አላህ (ሱ.ወ.) ከብረዛና ከክለሳ የመጠበቅ ኃላፊነቱን ለራሱ ወስዷል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፤እኛም ለርሱ ጠባቂዎቹ ነን።››[አል ሕጅር፡9]

በቀደሙት መለኮታዊ መጽሐፎች ላይ ተቆጣጣሪ፣ዋቢና ሻሪ አድርጎታልም። ይህንኑ በማስመልከት አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ [ተቆጣጣሪ] ሲኾን በውነት አወረድን፤››[አልማእዳህ፡48]

ለሁሉም ነገር አብራሪና መሪ አድርጎት ያስተላለፈው መሆኑንም ገልጾአል፦ ‹‹መጽሐፉንም፣ለሁሉ ነገር አብራሪ፣መሪም እዝነትም፣ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው።››[አል ነሕል፡89]

ቁርኣን መመሪያ እዝነትና በረከት መሆኑን ሲገልጽም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ስለዚህ ከጌታችሁ ግልጽ ማስረጃ መምሪያም፣እዝነትም በእርግጥ መጣላችሁ፤››[አልአንዓም፡157]

ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚወስድ መጽሐፍም ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ይህ ቁርኣን ወደዚያች፣እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፤እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል።››[አልእስራእ፡9]

$Sidney_Fischer.jpg*

ሲድኒ ፊሸር

የአሜሪካው ኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር
ሁሉን ያካተተ መጽሐፍ
‹‹ቁርኣን የስልጠና እና የስልጣኔ መጽሐፍ ነው። ያካተታቸው ነገሮች ሁሉ ስለግዴታዎችና ስለ አምልኮተ አላህ አፈጻጸም ብቻ የሚናገሩ አይሉለም። ሙስሊሞች የሚያበረታቷቸው ግብረገብነትና የትሩፋት ሥራዎች ከሁሉም በላይ ውብ ድንቅና በስነምግባር መለኪያዎች ከሁሉም ይበልጥ ሚዛን የሚደፉ ናቸው። የመጽሐፉ ቅን አመራር በትእዛዛቱ እንደሚንጸባረቅ ሁሉ በእገዳዎቹም ይንጸባረቃል።››

የሰው ልጆችን በሁሉም የሕይወት ፈርጆችና የኑሮ ጉዳዮቻቸው ወደ ተመራጩ ቀጥተኛ ጎዳና ይመራቸዋል።

ታላቁ ሕያው መጽሐፍ ቁርኣን ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በምልዓት ያካተተ፣መሰረታዊ መርሆዎችን፣የእምነትና የዐቂዳ፣የሕግጋትና የበይነሰባዊ ግንኙነት፣የስነምግባርና የግብረገብነት . . መሰረቶችን አቅፎ ይዟል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹በመጽሐፉ ውስጥ ምንም ነገር [ሳንገልጽ] አልተውንም።››[አል አንዓም፡38]

ነብያዊ ሱንና

አላህ (ሱ.ወ.) ቅዱስ ቁርኣንን ወደ መልክተኛው r ሲያስተላልፍ ነቢያዊውን ሱንናም አስተላልፎላቸዋል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እርሱ (ንግግሩ) የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም።››[አልነጅም፡4]

$Etienne_Denier.jpg*

ኢይቴን ዲነህ

ፈረንሳዊ ሰዓሊና ፈላስፋ
ተወዳጁ ሱንና
‹‹በምድር ላይ ከተሰራጩ በመቶዎች ሚሊዮኖች ከሚቀጠሩ ሰዎች ልብ በሚፈልቅ ታላቅ ሃይማኖታዊ ፍጹምነት እየተበጠረና እየተለወለ፣ድንቁ የሙሐመድ ሱንና እስከ ዛሬው ዘመናችን ድረስ ተጠብቆ ቆይቷል።

ሱንና እንደ ቁርኣን ሲሆን ይህንኑ በማስመልከት ነቢዩ r እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹ንቁ ዕወቁ! መጽሐፉና መሰሉ (ሱንና) አብረው ተሰጥቶኛል። መጽሐፉና መሰሉ (ሱንና) አብረው ተሰጥቶኛል።›› [በአሕመድ የተዘገበ] ነቢዩ r ለሰዎች የሚያደርሱት እንዲያደርሱ ከአላህ የታዘዙትን ብቻ ነው። አላህ የታዘዙትን ብቻ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወደኔ የሚወረደውን እንጅ ሌላ አልከተልም፤እኔም ግልጽ አስፈራሪ [አስጠንቃቂ] እንጅ ሌላ አይደለሁም በላቸው።››[አልአሕቃፍ፡9]

በመሆኑም ነቢያዊው ሱንና ሁለተኛው የእስላም የሕግ ምንጭ ነው። ሱንና እሰከ ነቢዩ r ድረስ በሚዘልቅ ትክክለኛና አስተማማኝ የዘገባ ሰንሰለት የተዘገበ የነቢዩ ንግግር፣ተግባር፣ገለጻ ወይ ማረጋገጫ ሲሆን የቅዱስ ቁርኣን ተግባራዊ ማብራሪያ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) በቁርኣን ውስጥ የተካተቱ ጠቅለል ያሉ ወይም ማብራሪያና ገለጻ የሚሹ ጉዳዮችን እንዲያብራሩና እንዲተነትኑ ለነቢዩ r ፈቅዶላቸዋል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወደ አንተም ለሰዎች ወደነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን።››[አልነሕል፡44]

$Jack_Ressler.jpg*

ጃክ ሪሳር

ፈረንሳዊ ኦሪየንታሊስት
ቁርኣንና ሐዲስ መሳ ለመሳ
‹‹የነቢዩ ሙሐመድን ሥራዎችና መመሪያዎች የሚመለከቱ ንግግሮች ስብስብ ተደርጎ የሚቆጠረው ሐዲስ የቁርኣን መሙያ (ማብራሪያ) ነው። አንድ ሰው ሐዲስ ውስጥ ከሕይወት ተለዋዋጭ እውነታዎች አንጻር የስነምግባሩ መሰረታዊ አካል የሆነውንና በነቢዩ ሙሐመድ አእምሮ ውስጥ ይመላለስ የነበረውን ነገር ያገኛል። ሱንና የቁርኣን ማብራሪያ በመሆኑ አስፈላጊነቱ የግድ ነው።››

እናም ሱንና ቅዱስ ቁርኣንን ያብራራል፤አንቀጾቹን ይተነትናል፤ጠቅለል ያሉ ድንጋጌዎቹን ይዘረዝራል። ነቢዩ r ወደርሳቸው የወረደውን ቁርኣን አንቀጾች አንዴ በአንደበታቸው ሌላ ጊዜ ደግሞ በተግባራቸው አንዳንዴም በሁለቱም ጭምር ያብራሩ ነበር። ሱንና አንዳንድ ሕጎችንና ድንጋጌዎችን በማብራራት ረገድ ራሱን ችሎ የሚመጣበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል።

ነቢዩ r ከአላህ የታዘዙትን በትጋት ይፈጽሙና ለሰዎች ያብራሩ ስለነበር፣እርሳቸው የሰሩትን አይተው እንዲሰሩ ያዙ ስለነበር የጠራው ነቢያዊ ሱንና የእስላም ሕግጋት እምነት፣አምልኮተ አላህ፣በይነሰባዊ ግንኙነቶችና የስነምግባር ደንቦች ተግባራዊ ማብራሪያና መገለጫ ነው። እምነታቸው ምሉእ ይሆን ዘንድ ምእመናን በተግባራቸውና በአንደበታቸውም የነቢዩን r አርአያ እንዲከተሉ አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ሲል አዟል፦ ‹‹ለናንተ፣አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለኾነ ሰው፣አላህንም በብዙ ለሚያወሳ፣በአላህ መልክተኛ መልካም መከተል [አርአያ] አላቸው።››[አል አሕዛብ፡21]

$Leopold_Weiss.jpg*

ሊዮፖርድ ፋይስ

ነምሳዊ ፈላስፋ
የተበረከተው ሱንና
‹‹የሙሐመድን ሱንና መተግበር የእስላምን ሕልውና እና ዕድገቱን ጠብቆ ለማቆት መሥራት ማለት ነው። ሱንናን መተውም እስላምን ማክሰም ማለት ነው። ሱንና እስላም የታነጸበት የብረት መዋቅርና መሰረት ነው። ያንድን ሕንጻ መሰረትና መዋቅር ካስወገድክ ሕንጻው የካርቶን ቤት ይመስል ፍርክስክስ ቢል ያስገርማልን?! ››

ክቡራን የነቢዩ ባልደረቦች (ሶሓባ) የነቢዩን r ንግግሮችና ሥራዎቻቸውን ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላለፉ ሲሆን ቀጣዩ ትውልድም ሱንናቸውን በመድብሎች ሰብስቦ በማጠናቀር አቆይቶልናል። የሱንና ዘጋቢዎችና አጠናቃሪዎች በዘገባ ሰንሰለት አበጣጠርና በሀዲስ አሰባሰብ ላይ ጥብቅ መስፈርቶችን ይከተሉ ስለነበር፣የዘገባ ሰንሰለቱ እስከ ነቢዩ r ድረስ የሚዘልቅ ይሆን ዘንድ ሐዲሱን የሰማው ሰው ከሰማበት ሰው ጋር በአካል የተገናኘ ዘመነኛው መሆንን፣በዘገባ ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙ ዘጋቢዎች ሁሉ በሃይማኖታቸው በመልካም ስነምግባራቸው የታመኑ፣እምነት የሚጣልባቸው ፍትሐዊነትን የተላበሱ ታማኞች መሆንን ለሐዲሱ ትክክለኛነት በመመዘኛነት ያስቀምጡ ነበር።

$Jack_Ressler.jpg*

ጀሳክ ሪሳር

ፈረንሳዊ ኦሪየንታሊስት
የነቢያዊው ሱንና አሰባሰብ
‹‹በስብስባቸው ሱንናን የሚመሰርቱት እነዚህ ሐዲሶች በአመራረጣቸው ላይ ጥብቅ የሆነ ከፍተኛ ፍተሸ ከማድረግ ጋር በነቢዩ ባልደረቦች ተዘግበው ወይም ከነሱ ተላልፈው የተጠናቀሩ ናቸው።››

ቁርኣንና ሱንና ማመሳከሪያ ዋቢና ያዘዙትን መፈጸም ከከለከሉትም መከልከል የሚገባ ሁለቱ መሰረታዊ የእስላም የሕግ ምንጮች መሆናቸውን አምኖ መቀበል ግዴታ ነው። በሁለቱ ምንጮች ውስጥ የሰፈረው ሁሉ እውነት መሆኑን፣የአላህ (ሱ.ወ.)ስሞች፣ባሕርያትና ተግባራት አስመልክቶ በውስጣቸው በቀረበው ሁሉ ማመንና፣አላህ (ሱ.ወ.) ለምእመናን ወዳጆቹ ያዘጋጀላቸው ታላቅ ምንዳና ለአስተባባይ ከሃዲዎች ያሰናዳው መራር ቅጣትም ፍጹም እውነት መሆኑን ማመን ግዴታ ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹በጌታህም እምላለሁ (አላህ በራሱ መማሉ ነው) በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ፣ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝን እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም (ምእመን አይኾኑም)።››[አልኒሳእ፡65]

በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ።››[አል ሐሽር፡7]

ይህን መንገድ የተከተለ ሰው ምንኛ ታደለ!! የመታደል መንገድም ይህ ነውና!!Tags: