የአላህ ስሞችና ባሕሪያት

ለዓለማት ሁሉ እዝነት

ለዓለማት ሁሉ እዝነት

የነብይነት ማኅተም

$Henri_de_Castries.jpg*

ሄንሪ ዴ ካስትሪ

የፈረንሳይ ጦር የቀድሞ ሻምበል
ሃይማኖት በመሰረቱ አንድ ነውድን
‹‹የሁሉም ነቢያት ሃይማኖት አንድ ነው። ከአደም ጀምሮ እስከ ሙሐመድ ድረስ በአንድ መንገድ ላይ ይስማማሉ። ሦስት መለኮታዊ መጽሐፎች የተገለጡ ሲሆን እነሱም መዝሙር፣ኦሪትና ቁርኣን ናቸው። ቁርኣን ከኦሪት ጋር ያለው ትስስር ኦሪት ከመዝሙር ጋር ያለው ትስስር ዓይነት ነው። ሙሐመድ ከዒሳ አንጻር የሚታየው ዒሳ ከሙሳ አንጻር በሚታይበት መልኩ ነው። እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ግን ቁርኣን ወደ ሰዎች የተላለፈ የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐ ሲሆን ነቢዩ መሐመድም የነቢያትና የመልክተኞች መደምደሚያ መሆኑ ነው። በመሆኑም ከቁርኣን በኋላ ሌላ መጽሐፍ፣ከሙሐመድ በኋላም ሌላ ነቢይ የለም።››

አላህ (ሱ.ወ.) በጥበቡ ለመላው የሰው ልጅ አጠቃላይ፣ለሁሉም ዘመንና ስፍራ ምቹ የሆነ ዩኒቨርሳል መልክቱን አስይዞ ሙሐመድን r ልኳል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፣አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን ቢኾን እንጂ አልላክንህም፤ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።››[ሰበእ፡28]

ይህን ዓለም አቀፍ ዘላለማዊ መልክቱንም ከመለወጥና ከመበረዝ ጠብቆት ከመዛባትና ከመቀያየር እንከን የተጠራ ሆኖ እስከመጨረሻው ድረስ ከሰው ልጆች ጋር የሚኖር ሕያው መልክት አድርጎታል። ለዚህም ነው የመጨረሻውና የማጠቃላያው መለኮታዊ መልክት እንዲሆን የተደረገውና ሙሐመድም r ከኋላቸው ምንም ነቢይ የማይመጣ የነቢያት መደምደሚያ የሆኑት። በዚህም አላህ (ሱ.ወ.) መለኮታዊ መልክቶቹን ምሉእ አድርጎ ሕግጋቶቹን በማጠቃለል ግንባታውን አጠናቋል።

$Washington_Irving.jpg*

ዋሽንግተን ኤርቨንጅ

አሜሪካዊ ኦሪየንታሊስት
የመለኮታዊ መጻሕፍት መደምደሚያ
‹‹ኦሪት አንድ ወቅት ላይ የሰው ልጅ መሪና የስነምግባሩ መሰረት ነበር። አልመሲሕ ዒሳ ሲመጣ ክርስቲያኖች የወንጌልን ትምሕርቶች ተከተሉ። ከዚያም ቁርኣን በሁለቱ ቦታ ተተካ። ቁርኣን ከቀደሙት ሁለቱ መጽሐፎች የበለጠ የአጠቃላይነትና የተንታኝነት ባህርይ ያለው ሲሆን፣በነዚ ሁለቱ መጽሐፎች ላይ የደረሱትን የማዛባት፣የመለዋወጥና የመበረዝ ሁኔታዎች አርሟል። የመለኮታዊ መጻሕፍት ማጠቃለያ እንደመሆኑም ሁሉንም ሕግጋት አጠቃልሎ ይዟል።››

በዚህ ምክንያትም ሙሐመድ r ይዘው የመጡትን መጽሐፍ የቀደሙት መለኮታዊ መጻሕፍት ተቆጣጣሪ ገዥ፣ሸሪዓቸውንም የቀደሙትን ሸሪዓዎች (ሕግጋት) ሁሉ የሚሽር አድርጎ ጠብቆ የማኖር ኃላፊነቱን አላህ (ሱ.ወ.) ራሱ በመውሰዱ ታላቁ ቁርኣን በድምጽና በጽሑፍ ባልተቋረጠ ተከታታይ የዘገባ ሰንሰለት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ላይ ይገኛል። የሃይማኖቱ ሕግጋት ተግባራዊ አፈጻጸምም ከዕባዳዎቹና ከዝርዝር ድንጋጌዎቹ ጋር ምሉእ በሆነ የተአማኒነት ደረጃ ባልተቋረጠ የዘገባ ሰንሰለት ለኛ ደርሷል።

$Arnold_Toynbee.jpg*

አርኖልድ ቶይንቢ

እንግሊዛዊ ታሪክ ጸሐፊ
የሰው ልጆች ሁሉ መምሕር
‹‹የዐረባዊው ነቢይ የሕይወት ታሪክ የተከታዮቹን ልብ ማርኮ ይዟል። ሰብእናውም እነሱ ዘንድ ወደ ሰማየ ሰማያት መጥቋል። በመሆኑም ወደርሱ የተላለፈውን ሁሉ እንዲቀበሉ የሚያደርጋቸውን እምነት በመልክቱ አምነዋል። በሱንና እንደ ተጠናቀረው ሁሉ ተግባራዊ ክንዋኔዎቹም የሕግ ምንጭ ሲሆኑ፣ይህም የእስላማዊውን ማህበረሰብ ሕይወት አቀናጅቶ በመምራት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ድል አድራጊ ሙስሊሞች ሙስሊም ካልሆኑ ዜጎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነትም የሚገዛ ነው።››

የነቢዩን r የሕይወት ታሪክና ነቢያዊ ፈለጋቸው (ሱንና) የተጠናቀሩባቸውን መድበሎች ያነበበ ሰው፣ባልደረቦቻቸው (ሶሓባ) የነቢዩን r አጠቃላይ ሁኔታዎች፣የተናገሩትንና የሠሩትን ሁሉ በተሟላ መልኩ ጠብቀው ለሰው ልጆች አቆይተዋል። አላህን እንዴት ያመልኩ እንደነበረ ዕባዳቸውን፣ዝክራቸውንና ዱዓቸውን፣እስትግፋራቸውን፣ጅሃዳቸውን፣ደግነታቸውንና ፣ለባልደረቦቻቸውና ወደርሳቸው ለሚመጡትም ያደርጉ የነበረውን አያያዝ ወደር በሌለው ታማኝነትና ጥንቃቄ ለትውልዶች ጠብቀው አስተላልፈዋል። ደስታና ሐዘናቸውን፣ጉዞና ዕረፍታቸውን፣እንዴት ይበሉና እንዴት ይጠጡ አንደነበረ፣እንዴት ይተኙና ከእንቅልፍ እንዴት ይነሱ እንደነበረ ጭምር ዘግበዋል።

$Tolstoy.jpg*

ቶሊስቶይ

ሩሲያዊ የስነጽሑፍ ሰው
የነቢያት መደምደሚያ
‹‹የመለኮታዊ መልክቶች ማጠቃላያ የርሱ መልክት እንዲሆንና እርሱ ራሱም የነቢያት መደምደሚያ ይሆን ዘንድ አላህ በመረጠው በነቢዩ ሙሐመድ ከተደመሙ ሰዎች መካከል እኔ አንዱ ነኝ።››
$Washington Irving.jpg*

ዋሽንግተን ኤርቨንጅ

አሜሪካዊ ኦሪየንታሊስት
አላህን ብቻ ተገዙ
‹‹ሙሐመድ የነቢዮች መደምደሚያና ሰዎችን ወደ አምልኮተ አላህ ለመጥራት ከተላኩት መልክተኞችም ታላቁ መልክተኛ ነበር።››

ይህን ሁሉ አስተውለን ስንመለከት ይህ ሃይማኖት ከመበረዝና ከመዛባት አደጋ በአላህ (ሱ.ወ.) ጥበቃ የሚደረግለት ሃይማኖት መሆኑን እንገነዘባለን።

በዚህን ጊዜም ሙሐመድ r የነቢያትና የመለክተኞች መደምደሚያ መሆናቸውን እንረዳለን። አላህ (ሱ.ወ.) ይህ መልክተኛ የነቢያት መደምደሚያ መሆኑን ሲነግረን እንዲህ ብሏልና፦ ‹‹ሙሐመድ፣ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፤ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፤አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።››[አል አሕዛብ፡40]

የዓለማት እዝነትና ርኅራሄ

$Dr._Laura_VecciaVaglieri.jpg*

ኦራ ፊሽያ ቫግሌሬ

ጣሊያናዊት ኦሪየንታሊስት
የእስላም ዓለም አቀፋዊነት
‹‹ወደ ነቢዩ የተላለፈ ለዓለማት ሁሉ እዝነት የሆነ ሃይማኖት መሆኑን በመግለጽ የእስላምን ዓለም አቀፋዊነት የሚያመለክተው ቁርኣናዊ አንቀጽ፣ለመላው ዓለም የተላለፈ ቀጥተኛ ጥሪ ነው። ይህም መልክተኛው ይዞ የመጣው መለኮታዊ መልክት ከዐረብ ሕዝብ ክልል አልፎ እንዲሄድ የተጻፈለት ስለመሆኑ ፍጹማዊ እርግጠኝነት እንደ ነበረው፣አዲሱን ቃል የተለያዩ ቋንቋዎች ላሏቸው የተለያዩ ሕዝቦች የማድረስ ግዴታ እንዳለበትም የሚያመለክት ግልጽ ማስረጃ ነው።››

አላህ (ሱ.ወ.) ነቢዩ ሙሐመድን r ወደ መላው የሰው ዘር የላካቸው፣ለዓለማት ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም፣ለትንሹም ለትልቁም እዝነት ርህራሄና ጸጋ አድርጓቸው ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን በርሳቸው ላላመኑትም ጭምር ረሕመት አድጓቸው ነው አላህ የላካቸው። እዝነትና ጸጋው ነቢዩ r በሕይወት ዘመናቸው በወሰዷቸው አቋሞች ውስጥ የተንጸባረቀ ሲሆን፣በተለይም በርህራሄና በእዝነት ሕዝባቸውን ወደ አላህ ተውሒድ በጠሩ ጊዜ ሰዎቹ አስተባበሏቸው፤ ከትውልድ አገራቸው ከመካ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፤የመግደል ሙከራም ፈጽመውባቸዋል፤አላህ (ሱ.ወ.) ግን በቂያቸው ነበርና የቁረይሾችን ሴራ አክሽፎ ውድቅ አድረገ። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ፣ወይም ሊገድሉህ፣ወይም (ከመካ) ሊያስወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ፣(አስታውስ)፤ይመክራሉም፣አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፤አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው።››[አል አንፋል፡30]

የተፈጸመባቸው ያ ሁሉ ግፍ ግን ለነርሱ ማዘንንና ወደ አላህ መንገድ እንዲመጡ

ያላቸውን ጉጉትን ብቻ ነበር ለነቢዩ የጨመረው። ይህን አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከጎሳችሁ የኾነ፣ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የኾነ፣በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ለምእመናን ርኅሩህ አዛኝ የኾነ መልክተኛ፣በእርግጥ መጣላችሁ።››[አል ተውባህ፡128]

በተጨማሪም ድል አድርጓቸው በአሸናፊነት መካ በገቡት ቀንም ያለ ምንም በቀል ‹‹ነጻ ናችሁ ሂዱ›› ብለው ነበር ምሕረት ያደረጉላቸው። ከሐዲዎቹን በሁለት ተራራዎች መሀል አጣብቆ ለማጥፋት አላህ (ሱ.ወ.) መልኣክ በላከላቸው ጊዜ፣‹‹አላህ (ሱ.ወ.) ከአብራኮቻቸው አንድ አላህን ብቻ የሚግገዙ ሰዎችን ያወጣ ይሆናልና የለም እታገሳለሁ›› ነበር ያሉት። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።››[አል አንቢያ፡107]

ነቢዩ r በእርግጥ ለዓለማት ሁሉ፣ለሰዎች ሁሉ፣የቆዳ ቀለም፣ቋንቋ፣አመለካከት፣እምነትና ቦታ ሳይለይ ለመላው የሰው ዘር የተላኩ እዝነትና ዘላለማዊ የአላህ ጸጋ ናቸው።

የነቢዩ r እዝነትና ጸጋ በሰው ልጆች ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ለእንስሳትና ለግዑዝ አካላትም ጭምር የተዘረጋ ነው። የአንድ የመዲና ነዋሪ ባልደረባቸውን ግመል ባለቤቱ በረሃብ ስላሰቃየው የአላህ መልክተኛ r በግመሉ ሁኔታ አዝነውና ራርተው ባለቤቱ ለግመሉ ደግ እንዲሆን እንዳያስርበውና ከአቅሙ በላይ እንዳይጭንበት አዘዋል። ነቢዩ r አንድ ሰው ጫጩቶቿን የወሰደባትን እርግብ አይተው ልባቸው በማዘኑ ጫጩቶቹን እንዲመልስላት አዘዋል። ‹‹ባረዳችሁ ጊዜ አስተራረዱን አሳምሩ›› [በሙስሊም የተዘገበ] ያሉትም ነቢዩ r ናቸው። እዝነትና ርህራሄያቸው ወደ ግዑዝ አካላትም ተዳርሷል፤በዚህ ረገድ ነቢዩ r ስለተለዩት ዋይታ ላሰማው የተምር ግንድ ሆዳቸው ራርተው ከመናገሪያ ምንበራቸው (መድረክ) ወርደው ግንዱ እስኪረጋጋ ድረስ አቅፈውታል።

$Jan_Lake.jpg*

ጃን ሊክ

እስፔናዊ ኦሪየንታሊስት
ለሰው ልጆች የተበረከተ እዝነት
‹‹ታሪካዊው የሙሐመድ ሕይወት አላህ ‹ለዓለማት እዝነት አድርገንህ እንጂ አልላክንህም› በማለት ከገለጸው ይበልጥ ባማረ አገላለጽ ሊቀርብ አይችልም። ታላቁ የቲም (የሙት ልጅ) ለድኩማን ሁሉና እርዳታውን ለሚሹ ሰዎች ሁሉ ታላቁ እዝነትና ታላቁ ርህራሄ መሆኑን በገዛ ራሱ አስመስክሯል። በእርግጥም ሙሐመድ ለየቲሞች፣ለመንገደኞች፣አደጋ ለደረሰባቸው ሰዎች፣ለድሆች ሁሉና ጥረው ግረው ለሚኖሩ ሠራተኞች እውነተኛው ርህራሄና እውነተኛው እዝነት ነበር።››

ርህራሄና እዝነታቸው በግላዊ አቋምና በሁነቶች ላይ ብቻ የተወሰነ የግል ዝንባሌ ሳይሆን ለሰዎች የደነገጉት መለኮታዊ ትእዛዝ፣ሕግ፣መመሪያና ቋሚ ስነምግባርም ነው። ለሰዎች ርህሩህ አዛኝና ገር መሆንን ሲያበረታቱና አስቸጋሪና አስጨናቂ መሆንን ሲያስጠነቅቁም ነቢዩ r እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹አላህ ሆይ! ከሕዝቦቼ ጉዳዮች መካከል በአንዱ ነገር ኃላፊነት ተሰጥቶ ለነሱ አስቸጋሪና አስጨናቂ የሆነን ሰው አንተ አስቸጋሪና አስጨናቂ ሁንበት፤ከሕዝቦቼ ጉዳዮች መካከል በአንዱ ነገር ኃላፊነት ተሰጥቶ ለነሱ ገርና ርህሩህ የሆነውን ሰው ደግሞ አንተ ገርና ርህሩህ ሁንለት።›› [በሙስሊም የተዘገበ] እናም እዝነትና ርህራሄ ከነቢዩ r ታላላቅ ባህርያት መከከል አንዱ ሲሆን፣የእዝነትና የሰላም ሃይማኖት በሆነው እስላም ውስጥም አንዱ መሰረታዊ መርሕ ነው።

በአላህ መልእክተኛ በሙሐመድ ﷺ መላክ የሰው ልጆች መታደል

$K._LalGaba.jpg*

ኬ.ዊልያም

እንግሊዛዊ ፈላስፋ
የሰው ልጆችን ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚያወጣ
‹‹ነቢዩ ሙሐመድ ፍጡራንን በትንግርታዊ ፍጥነት ወደ መጨረሻው የመታደል ደረጃ አድርሷቸዋል። የሰው ልጆች ከርሱ በፊት የነበሩበትን የጥመት ሁኔታ አስተውሎ የቃኘ ሰው፣ከርሱ በኋላ ያለውን ሁኔታቸውንና በርሱ ዘመን የደረሱበትን ታላቅ ምጥቀት ያስተዋለ ሰው፣በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድርን ያል የተራራቀ መሆኑን ይገነዘባል።››

የሙሐመድ r ዘመነ ተልእኮ መጥቶ በሙሐመድ ነቢይነት በረከት አላህ (ሱ.ወ.) ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው የተውሒድ መንገድ መራቸው። መመሪያው በያዛቸው ማብራሪያዎችና መግለጫዎች ጥልቀትና ምጥቀት ከቃላት ገለጻና ከዐዋቂዎች ዕውቀት በላይ ነው። ጠቃሚ ዕውቀትን፣በጎ ሥራን፣ታላላቅ ስነምግባራትንና ቀጥተኛ ፈለግን ለሰው ልጆች ያበሰረ ሲሆን፤ እውቀትና ተግባርን ያካተተ የሁሉም ሕዝቦች ጥበብ አንድ ላይ ተደምሮ ቢመጣ ከዚህ ዘላለማዊ መለኮታዊ መመሪያ በብዙ እጅ አንሶ ይታያል። ለዚህም ምስጋና ሁሉ ለጌታችን ለአላህ ይሁን።

ዐቂዳን (እምነትን ) በተመለከተ ከሙሐመድ r መላክ በፊት ባእድ አምልኮና በአላህ ማጋራት ቀደም ሲል ለክለሳና ለመዛባት አደጋ የተጋለጡ መለኮታዊ መጻሕፍት ባለቤቶች በሆኑት ዘንድ እንኳ ሳይቀር ምድርን አጥለቅልቀው ነበር። ይህን አስከፊ ሁኔታ ለመለወጥ የአላህ መልክተኛ r የጠራ ተውሒድንና አንድ አላህን ብቻ ከርሱ ጋር ማንንም ምንንም ሳያጋሩ እርሱን ብቻ የመግገዛት እምነትን ይዘው መጡ። ሰዎችንም ከፍጡራን አምልኮ ወደ አንዱ ፈጣሪ ጌታ አምልኮ አሸጋገሩ። በተውሒድ ልቦናን ከሽርክ ርክሰትና ከባዕድ አምልኮ ቆሻሻ አጸዱ። አላህ (ሱ.ወ.) የላካቸው ከርሳቸው የቀደሙ ነቢያትና መልክተኞች ይዘው የመጡትን ትምሕርት በማስያዝ ነበር። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከአንተ በፊትም፣እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።››[አል አንቢያእ፡25] ‹‹አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤(እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው።››[አል በቀራህ፡163]

$Wagner.jpg*

ዋጅነር

ሆላንዳዊ ተመራማሪ
ለሰው ልጆች በመላ የተላለፈ ሃይማኖት
‹‹ሁለቱ ታላላቅ አንቀጾች ማለትም ‹‹አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት እስላም ብቻ ነው፤›› [ኣሊ ዒምራን፡19] እና ‹‹አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፣አብሳሪና አስፈራሪ [አስጠንቃቂ] አድርገን እንጂ አልላክንህም፤›› [ሰበእ፡28] አእምሮዬ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድረዋል፤ምክንያቱም እስላምን ከሌሎች ሥርዓቶችና ሕግጋት ልዩ ለሚያደርገው ለዚያ የዓለም አቀፋዊነት ባህርይውና የነቢዩ ዒሳን u እውነታ አስመልክቶ ላቀረበው የተሟላ ማብራሪያ ማስረጃ በመሆናቸው ነው። ታድያ ሁሉም ነቢያትና መልክተኞች ይዘው የመጡትን ሁሉ እንድናከብር አላህ (ሱ.ወ.) በተጨማሪ እንዲህ ብሏል፦

በማሕበራዊው ሕይወት በኩልም ነቢዩ r የተላኩት ግፍና ጭቆና በተንሰራፋበት፣የሰው ልጆች በጌታና በሎሌ መደብ ተከፋፍለው በአስከፊ የመደብ ጭቆና በሚሰቃይበት ወቅት ነበር። ነቢዩ r ሰዎችን ሁሉ ዐረብና ዐረብ ያልሆነ፣ነጭና ጥቁር ሳይባል እኩልነትን የሚያሰፍን፣አላህን በመፍራትና በሚፈጽሙት መልካም ተግባር ብቻ ካልሆነ ማንም ሰው ከሌላው ሰው ፈጽሞ የማይበልጥ መሆኑን የሚያበስር ሰብአዊ እኩልነትን ይዘው ነው የመጡት። ይህን በማስመልከት አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹በላጫችሁ፣በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤››[አል ሑጁራት፡13]

አላህ (ሱ.ወ.) ለፍትሕ አስተካካይነት፣ለበጎ ሥራና ለማሕበራዊ ተራድኦ ጥሪ ሲያደርግ፣ከግፍ ከመጥፎ ድርጊትና ከማንኛውም በደል ከልክሏል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፤ ከአስከፊም፣(ከማመንዘር)፣ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ከመበደልም ይከለክላል፤ ትገነዘቡ ዘንድ፣ይገሥጻችኋል።››[አል ነሕል፡90]

$H._G._Wells.jpg*

ሄርበርት ጆርጅ ዌልዝ

ከመሰናበቻው ሐጅ ትምሕርቶች
‹‹ሙሐመድ የመሰናበቻውን ሐጅ ከመዲና ወደ መካ ያደረገው ከመሞቱ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ነበር። በዚህ የሐጅ ሥርዓት ላይ ለሕዝቦቹ ታላቅ መካሪ ዲስኩር ያደረገ ሲሆን የንግግሩ የመጀመሪያ አንቀጽ ብቻውን በሙስሊሞች መካከል ያለውን ዝርፊያና ንጥቅያ፣የበቀልና የደም ጉዳዮችን ሁሉ ነቅሎ የመጣል አቅም ነበረው። የዲስኩሩ የማጠቃለያ አንቀጽ ደግሞ ጥቁሩን ሰው ከሙስሊሞች መሪ ኸሊፋ ጋር ፍጹም እኩል የማድረግ ኃይል ነበረው። በእውነትም በዓለም ላይ ፍትሐዊ ለሆነ በይነሰባዊ ግንኙነት ታላቅ መሰረትን ጥሏል።››

ይህ ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ሕሊናዊ መብቶች እንዲከበሩ አድርጎ ሰዎች አንዱ በሌላው ላይ እንዳይሳለቅ ከልክሏል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፤ከነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፤ሴቶችም ከሴቶች (አይሳለቁ)፤ከነሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፤ነፍሶቻችሁንም አታነውሩ (ከፊላችሁ ከፊሉን አይዝለፍ)፤በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፤ከእምነት በኋላ የማመጥ ስም ከፋ፤ያልተጸጸተም ሰው፣እነዚያ እነሱ በዳዮቹ ናቸው።››[አል ሑጁራት፡11]

በስነምግባር መስክም የሰው ልጆች ግብረገብነትና መልካም ባሕርያት ክፉኛ ባዘቀዘቁበት ወቅት ነበር ነቢዩ r የተላኩት። የመጡትም ሰዎችን ወደ መልካም ስነምግባርና ምስጉን ባሕርያት እንዲመለሱና በበጎ በይነሰባዊ ግንኙነቶች እንዲታደሉ ለማድረግ ነው። የአላህ መልክተኛ r እንዲህ ብለዋል፦ ‹‹የተላክሁት መልካም ስነምግባራትን ምሉእ ለማድረግ ነው።›› [በበይሀቂ የተዘገበ] አላህ (ሱ.ወ.) ስለ ነቢዩ r ታላቅ ስነምግባር ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ።››[አልቀለም፡4]

$Abdullah_Quilliam.jpg*

ዐብዱላህ ኮዊልያም

እንግሊዛዊ ፈላስፋ
የነቢዩ ሙሐመድ ስነምግባር
‹‹ሙሐመድ በሰው ልጅ ሊደረስበት በሚቻለው የመጨረሻው ታላቅ መልካም ጸባያትና ክቡር ስነምግባራት ላይ ነበር።የመጨረሻው የይሉኝታ ደረጃና ጥልቅ የሆነ የርህራሄ ስሜት ነበረው። እጅግ አስገራሚ የሆነ የግንዛቤ ኃይል፣ወደር የሌለው የሰላ አእምሮ፣ክቡር የሆኑ የመውደድና የእዝነት ስሜቶች ባለቤትም ነበር። በእርግጥ በታላቅ ስነምግባርና በተወዳጅ ባሕርያት ላይ ነበር።››

ነቢዩ የምጡቅ ስነምግባርና የመልካም ባሕርያት ሁሉ፣የቁጥብነት፣የተግባቦት፣የአብሮነትና የመልካም አነጋገር ቁንጮ ምሳሌ ብቻ ሳይሆኑ የመልካም ነገሮች ሁሉ መልካም አርአያ ነበሩ። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ለናንተ፣አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለኾነ ሰው፣አላህንም በብዙ ለሚያወሳ፣በአላህ መልክተኛ መልካም መከተል [አርአያ] አላቸው።››[አል አሕዛብ፡21]

የሴት ልጅን በተመለከተ በቅድመ እስላም አስከፊ ግፍና ጭቆና ይደርስባት የነበረ ሲሆን፣ነቢዩ r የተላኩት ሴቶች በሕብረተሰቡ ውስጥ ምንም መብት ያልነበራቸውና የተዋረዱ፣ሌላው ቀርቶ ሰው ነች ወይስ አይደለችም? በሚለው ላይ እንኳ ወንዶች በሚወዛገቡበት፣በሕይወት የመኖር መብት አላት ወይስ እንደተወለደች ተግደላ ትቀበር ?! ብለው በሚከራከሩበት ዘመን ነበር። የማህበረሰቡ ሁኔታም አላህ (ሱ.ወ.) ቁርኣን ውስጥ ቀጥሎ የገለጸውን ይመስል ነበር፦ ‹‹አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ፣እርሱ የተቆጨ ኾኖ፣ፊቱ ጠቁሮ ይውላል። በርሱ ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት፣በውርደት ላይ ኾኖ፣ይያዘውን? ወይስ በዐፈር ውስጥ ይደብቀውን? (በማለት እያምታታ) ከሰዎች ይደበቃል፤ንቁ፣የሚፈርዱት (ፍርድ) ምንኛ ከፋ!››[አልነሕል፡58-59]

$Bernard_Shaw.jpg*

በርናርድ ሾው

እንግሊዛዊ ጸሐፊ
የዓለም መንገድ
‹‹የእስላምን ነቢይ የሕይወት ታሪክ በሚገባና ደጋግሜ አንብቤያለሁ። መሆን የሚገባውን ታላቅ ስነምግባር እንጂ ሌላ አላገኘሁበትም፤እስላም የዓለም መንገድ ይሆን ዘንድም በጽኑ ተመኘሁ።››

ሴት ልጅ ተራ መጫወቻና፣የሚገበያዩባት አሻንጉሊትና ተዋራጅ አልባሌ ዕቃ ተደርጋ ትቆጠር ነበር።

አላህ (ሱ.ወ.) ነቢዩን r ሲልካቸው ለሴት ልጅ

ክብሯን አስመለሰላት። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ለናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ፣ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤››[አል ሩም፡21]

$Will_Durant.jpg*

ዎል ዲዮራንት

አሜሪካዊ ደራሲ
የሴት ደረጃ
‹‹እስላም በዐረቦች አገር የሴትን ደረጃ ከፍ አድርጓል። ሴት ሕጻናትን ከነሕይወታቸው የመቅበርን ልማድ አስወግዷል። በፍርድ ሂደቶችና በንብረት ባለቤትነት መብት ወንድና ሴትን እኩል አድርጓል። ለሴቷ ሐላል በሆነ ሥራ ላይ የመሰማራት፣የመውረስና ሠርታ ያገኘችውን ሀብት በባለቤትነት እንዳሻት የማድረግ መብት ሰጥቷል። በዘመነ ጃህሊያ የዐረቦች ልማድ የነበረውን ሴቶችን ከሌላው ንብረት ጋር ከአባት ወደ ልጅ ማስተላፍን ያስቀረ ሲሆን፣የሴትን የውርስ ድርሻ የወንዱ ድርሻ ግማሽ አድርጎ ያለ ፍቃዳቸው እንዳይዳሩም ከልክሏል።››

ይልቅዬም በእናትነቷ አንድትከበርም ትእዛዝ አስተላለፈ። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ጌታህም (እንዲህ አዘዘ)፤- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤››[አል እስራእ፡23]

%%

ግፍና በደል
‹‹በአውሮፓ የፈላስፎች ጉባኤ ይጠራና ሴት እንደ ወንዱ ሁሉ ነፍስ አላት ወይስ የላትም? ያላት ነፍስ የሰው ልጅ ነፍስ ነው ወይስ የእንስሳት ነፍስ ነው? የሚሉ ነጥቦች ለክርክር ይቀርቡ ነበር። ክርክሩም ‹ሴት ነፍስ ወይም መንፈስ አላት ግን ከወንዱ ነፍስ በብዙ ደረጃዎች ያነሰ ነው› በሚል የጋራ አቋም ይቋጭም ነበር።››

ነቢዩም r ለሴት እንደ እናት ከወንድ ቅድሚያ ሰጥተዋታል። አንድ ሰው ወደ ነብዩ r መጥቶ ፦ ‹‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለኔ መልካም አያያዝና ለደግነቴ ከሁሉም ይበልጥ ባለመብት የሆነው ማነው? ሲላቸው ፦ እናትህ ናት አሉት፤ከዚያስ? አላቸው፤እናትህ ናት፣አሉት፤ከዚያስ? አላቸው፤እናትህ ናት አሉት፤ከዚያስ? አላቸው፤አባትህ ነው አሉት።››[በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ትንሽ ልጃገረድ ሆናም አክብሮት እንዲቸራት ሲያዙ ነቢዩ r ፦ ‹‹ሦስት የሚያስጠጋቸው፣የሚራራላቸውና የሚያሳድጋቸው ሴቶች ልጆች ያሉት ሰው ገነት ለርሱ ተገቢው ሆናለች›› ሲሉ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለት ብቻ ቢሆኑም? ተብለው ሲጠየቁ ‹‹አዎ፣ሁለት ብቻ ቢሆኑም›› ብለዋል። [በአሕመድ የተዘገበ] በተጨማሪም እንደ ሚስትም ክብር እንዲሰጣት አዘው ይህን ማድረግ ከበላጭነት መለኪያ ጋር አያይዘዋል፦ ‹‹በላጫችሁ ለቤተሰቡ ከሌላው ይበልጥ ጥሩ የሆነ ሰው ነው፤እኔ ከሁላችሁም ይበልጥ ለቤተሰቤ ጥሩ ነኝ።›› ብለዋል። [በትርምዚ የተዘገበ]Tags: