ሌሎች ጭንቀትን ለመቋቋም ይረዳሉ

‹‹ሌሎችን መርዳት የስነልቦና ውጥረትን እንደሚፈውስ የሚያረጋግጡ ሳይንሳዊ ጥናቶች አሉ። በስነልቦና መስክ ኤክስፐርት የሆኑ ሰዎች እንዳረጋገጡት፣አንድ ሰው ሌሎችን መርዳት የነርቭ ውጥረትን ይቀንሳል። ይኸውም በሌሎች እገዛ ላይ መሰማራት ‹አንዶርፊን› የተባለ ሆርሞንን መመንጨት የሚያፋጥን ሲሆን ሆርሞኑ የደስተኝነት ስሜትና ንቃት እንዲሰማ የሚያጋዝ ነው። አሜሪካ የሚገኘው ‹ጤንነትን የማላቅ›› ተቋም የቀድሞ ዳይሬክተር አለን ሌክስ፣አንድ ሰው ሌሎችን ሲረዳ ስለ ግላዊ ጭንቀቶቹና ውጥረቶቹ ማሰቡን የሚቀንስ በመሆኑና በዚህም የመንፈስ እርካታ የሚሰማው በመሆኑ፣ሌሎችን መርዳት የነርቭ ውጥረትን እንሚያላላ ያረጋግጣሉ።››

Tags: